የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡ። ዘሁልቅ 13:26-30፣ ኤርምያስ 36:20- 26፣ 2ኛ ዜና መጻሕፍት 36:15፣16፣ ማቴዎስ 23:30-35፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 10:6-12።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡“ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥
እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ”
(1ኛ ቆሮንቶስ 10:11)።
ዛሬ አንዳንድ ሰዎች የራሳችን “እውነት--የራሳቸውን ልምምዶች፣ የራሳቸውን
ሀሳቦች፣ የራሳቸውን ፍላጎቶች፣ የራሳቸውን ወሰኖች፣ የራሳቸውን እምነቶች
ምንም ቢሆኑ እንዲናገሩ ይደፋፈራሉ። እያንዳንዱ “እውነት” ዋጋ ጸለው
የሚል አስተሳሰብ ቢኖርም ፈቃድ ሊሰጠው አይገባም። እነዚሀ ስር የሰደዱ
“እውነቶች” ክእውነት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስና ከተጻፈው ቃሉ ጋር ሲጋጩ ምን ይሆናል
አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት ተቀብለው ከስህተታቸው
ይታረማሉ። ሌሎች ደግሞ ከሀሰት ጋር ይጣበቃሉ። አንዳንዶች እውነቱን ሲቀበሉ
ፀባያቸውን ይቀይራሉ። ሌሎች ደግሞ ያምፃሉ። የሰው ታሪክ እንደዚህ ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሊሰሙ የማይፈልጉትን መልእክት
እንዲያስተላልፉ ይታዘዛሉ። ስለዚህ ብዙዎቹ ተነቅፈዋል፣ ተኮንነዋል፣ የሞት ዛቻም
ደርሶባቸዋል። እንዲያውም አንዳንዶች ተገድለዋል (ዕብራውያን 11:32-38)። ይህ
ሁሉ እንዳለ ሆኖ መለኮታዊ የሆነው ትንቢታዊ ምሪት አማራጭ የሌለው ስለነበር
የእግዚአብሔር ነቢያት የሚያስከፍላቸው ግላዊ ዋጋ ምንም ቢሆን መልእክታቸውን
በታማኝነት አስተላልፈዋል።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለህዳር 5 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
በእግዚአብሔር የተመረጠው መሪ፣ ሙሴ፣ ድብልቅ ህዝብን በምድረ በዳ ወደ ተስፋዋ ምድር መምራት የሚያስከትለውን ደስታና ሀዘን ያውቅ ነበር። ዘሁልቅ 14:4-11ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ምንድር ነው? ሕዝቡ በሙሴና በአሮን ላይ ለምን ተበሳጩ?
ጥቅሶቹ በጥንቃቄ ሲነበቡ የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ላይ የተቈጡት እርሱን ስላላመኑት ነው። የእግዚአብሔር የመጨራሻ የበላይነት ሰብአዊ ወኪሎች የሆኑት ሙሴና አሮን ለህዝቡ ቁጣ በቀላሉ ተዳረጉ። ማንኛውም ሰው አካላዊና አእምሮአዊ ጥበቃ(ደህንነት) ማግኘት ዋና አላማው ነው። እነዚህን ደህንነቶቻችንን አደጋ ላይ የሚጥል የሚመስል ነገር ሲያጋጥመን እንበሳጫለን። እንዲያውም አንዳንዴ ራሳችንን እንስታለን። ዘሁልቅ 13:26-30ን ያንብቡ። እስራኤላውያን እንዲህ የፈሩት ለምንድን ነበር? ካሌብ ምን አይነት የማደፋፈሪያ ቃል አካፈላቸው?
እስራኤላውያን የተስፋውን ምድር ለመውረስ በሚያደርጉት ሙከራ
የሚገጥሟቸውን ችግሮች ቢፈሩ አይፈረድባቸውም። ነገር ግን ሰዎች ልባቸውን
ለአለማመን ሲሰጡ ከሰይጣን ቁጥጥር ስር ይውላሉ። ሰይጣን ለምን ያህል ርቀት
እንደሚመራቸው አያውቁም (አበውና ነቢያት ገፅ 389)። በዚህ ቅጽበት ሙሴ
ለመወጣት ወደ አለመቻል የተቃረበ የመሪነት ችግር አጋጠመው። የህዝቡ ፍርሃት
በሙሴና በአሮን ላይ ወደ መቆጣትና በእግዚአብሔር ላይ ወደ ማመፅ ተለወጠ።
ህዝቡ እግዚአብሔር የመረጠውን ነቢይና መሪ በሌላ መሪዎች ለመተካት ሲሞክሩ
(ዘዳግም 34:10-12፣ ዘሁልቅ 14:41) እያሱና ካሌብ ልብሳቸውን ቀደው ቢፈሩም
በእግዚአብሔር እንዲያምኑ ተማፀኑ። ህ”እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና
ማር ወደምታፈስሰው ወደዚህች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል። ነገር ግን
በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤
ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው
ብለው ተናገሩአቸው” (ዘሁልቅ 14:8፣9)።
ነገሮች ሲመቻቹ እግዚአብሔርን ማመን ቀላል ነው። አይደል? መከራ
ሲመጣስ? እግዚአብሔርን ማመን የማይመችና የሚያስቸግር ሲሆንስ?
ታዲያ ያኔ ምን ያደርጋሉ?
መልእክቱን ማጥፋት፦ ክፍል 1 ኤርምያስ 36:20-26ን ያንብቡ። በአደባባዩ (በፍርድ ቤቱ) ውስጥ እየተካሄደ ያለው ነገር ምንድነው? መሪዎቹ ስለ ትንቢታዊው ማስጠንቀቂያ መልስ የሰጡት እንዴት ነበር?
በይሁዳ ላይ ጥፋት ባንዣበበት ዋዜማ ኤርምያስ የእግዚአብሔር ትንቢታዊ
ድምጽ ነበር። በኤርምያስ አማካይነት በይሁዳ እንዳልተደሰተ ለአያሌ አመታት
ሲነግራቸው ኖሯል። ባቢሎን ምርኮኛ አድርጎ እንደሚያግዛቸውም አስጠንቅቋቸዋል
(ኤርምያስ 6:8-19፣ ኤርምያስ 26)። እግዚአብሔር ሊያድናቸው ይፈልጋል። ሊድኑ
ከፈለጉ ግን መታዘዝ ነበረባቸው።
የይሁዳ ሃጥያቶች ብዙ፣ በገሃድ የሚፈጸሙና መለወጥን የማያሳዩ ነበሩ። ጣኦት
አምላኪነት፣ ልጆችን መሰዋት፣ ምንዝር እና ጭቆና በኤርምያስ ጊዜ ተለምደው
ነበር። ቢሆንም የነብዩን ማስጠንቀቂያዎች ሕዝቡ መስማት አልፈልገም።
የኤርምያስ የአገልግሎት ዘመን ሲገባደድ የእግዚአብሔር ማስጠንቀቅያ እየተጠናከረ
ሄደ። መልእክቱም የመታደግን ተስፋ የያዘ ነበር። ለምሳሌ በኤርምያስ 32 ላይ
እግዚአብሔር ኤርምያስን መሬት እንዲገዛ ያዝዘዋል። “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና ሰዎች በዚህች ምድር ቤትንና እርሻን የወይን
ቦታንም እንደገና ይገዛሉ” (ኤርምያስ 32:15)።
ኤርምያስ የመጨረሻ የመመለስና የመታደስ ተማጽእኖ እንዲጽፍ ለማድረግ
እግዚአብሔርን ያንቀሳቀሰው ፍቅር ነበር። ለዚህ መልእክት የኢዮአቄም መልስ
በእግዚአብሔር፣ በመልዕክቱና በመልዕክተኛው ላይ የማሾፍ ነበር።
ኤርምያስ 36:27-31ን ያንብቡ። ለእዮአቄም አመፅ የእግዚአብሔር
መልስ ምን ነበር?
አንዳንዴ የእግዚአብሔርን መልእክተኞች ብናጠፋቸው መልእክቱ እራሱ ይጠፋል
የሚል አስተሳሰብ ሊኖር ይችላል። መልእክቱን ለመስማት አለመፈለጋችን መልዕክቱን
አይሠርዘውም። እንዲያውም እያወቅን በጥፋት መንገዳችን ከገፋንበት በፈቃደኝነት
ከምንፈጽመው አመጽ የተነሳ በራሳችን እና በቤተሰባችን ላይ የሚደርሰው ቅጣት
ከባድ ይሆናል። ነብዩ ኤርምያስ ስለ ንጉስ ኢዮአቄም የተናገረው ትንቢት ለሁላችንም
(ለሰበአዊ ዘር ሁሉ) ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው (ኤርምያስ 36:30፣31)። የክፋታችንና
የሃጥያታችን ውጤት ስለምናጭድ የእግዚአብሔርን ማስጠንቀቂያ ችላ የምንለው
ራሳችንን ለአደጋ አጋልጠን ነው።
ከዓመፃቸው ባይመለሱም እግዚአብሔር ህዝቡን እየደጋገመ ማስጠንቀቁ
ስለ እግዚአብሔር የፍቅር ባህርይ ምን ያሳያል?
መልዕክቱን ማጥፋት፦ ክፍል 2
ሰብዓውያን ስለ ትንቢት ስጦታ የሚኖራቸው መልስ (አቀባበል) ይለያያል።
ሙሴን በተመለከተ፣ የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት ሲሞክሩ
የሀገሩን ሰዎች ስለፈሩ በሙሴና በአሮን ላይ በግልጽ አመፁ። ከብዙ አመታት በኋላ
ንጉስ ኢዮአቄም የእግዚአብሔርን የትንቢት ቃል የሚጠፋ መስሎት መልዕክቱን
አቃጠለ።
እነዚህ ክስተቶች በምንም መንገድ ያልተለመዱ ሁኔታዎች አይደሉም። የጥንት
የእስራኤልና የይሁዳ ታሪክ አብዛኛውን ጊዜ ነቢያትን ባለመቀበል የታወቀ ነው።
2ኛ ዜና መጻሕፍት 36:15ና 16ን ያንብቡ። የይሁዳ ሕዝብ እግዚአብሔር
በነቢያቱ በኩል ለተላከላቸው መልዕክቶች ምላሻቸው ምን ነበር? ታዲያ
እግዚአብሔር ለዚህ ባህርያቸው ምን ምላሽ ሰጠ?
የኤርምያስ ትንቢታዊ አገልግሎት የአምስት ነገስታትን ዘመነ መንግስት
ያካትታል። በናቡከደነጾር የሚመራው የባቢሎን መንግስት ከእስራኤል በር ደረሰ።
ሴዴቅያስ የተባለ የ21 ዓመት ወጣት ሲነግስ የኤርምያስ ትንቢት ሊፈፀም ተቃርቦ ነበር
(2ኛ ዜና 36:11)። መጽሐፍ ቅዱስ “በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤
በእግዚአብሔርም አፍ በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊት ራሱን አላዋረደም” ይላል
(2ኛ ዜና መጻሕፍት 36:12)
የኤርምያስ ትንቢታዊ ስጦታ እንዴት እንደተገለጸ ልብ ይሏል። በእግዚአብሔር
አፍ እንደ ተናገረ ተቆጠረ። ነገር ግን ሴዴቅያስ ራሱን በነቢዩ ፊት አላዋረደም።
ኤርምያስ እንደ ማንም ሰው ኃጢአተኛ ቢሆንም በእግዚአብሔር ስም የሚናገር
የእግዚአብሔር ወኪል ነበር።
ኤርምያስ የዚህን አይነት ሚና ከተጫወቱት ከብዙዎች መካከል አንዱ ነበር።
“ወደ ንስሃ እንዲመጡ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ”(2ኛ ጴጥሮስ 3:9) ለብዙ ምዕተ-
አመታት እግዚአብሔር ነቢያትን ወደ ህዝቡ ሲልክ ኖሯል (ዘፀአት 3:15፣ መዝሙር
105:26፣ ሚልክያስ 3:1፣ ኢሳያስ 6:8፣25:4፣ ማቴዎስ 11:13፣ ሉቃስ 11:49፣ ወዘተ)።
የጥንት የእስራኤልና የይሁዳ ታሪክ በዘመናት ሁሉ የኖሩትን ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉ
ህዝብ፣ ንስሃ የሚገቡ ከሆነ ብቻ፣ በድነት ተሰፋዎች ለመድረስ እግዚአብሔር ያደረገው
የማያቋርጥ ጥረት ታሪክ ነው።
በይሁዳ ታሪክ መጨረሻ ላይ በኤርምያስ በኩል የመጣላቸውን የምሪትና
የማጽናኛ መልዕክት ያስተናገዱት በትህትና፣ በመናዘዝና በእምነት ሳይሆን በማፌዝ፣
በመሳለቅ እና በንቀት ነበር።
በእግዚአብሔር መልክተኞች ላይ ቀለዱ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ናቁ፣
እንዲሁም በነቢያቱ ላይ ተሳለቁባቸው። መቼም እኛ ብንሆን ዛሬ
እንደዚያ አናደርግ ይሆን?
ባለፈው ጊዜ ሌሎች ሰዎች ያደረጉትን ሲያዩ እኔ ብሆን እንዲህ አላደርግም ነበር! ብለው ያውቃሉ? በእውነት ለራሳችን ሀቀኛ እንሁን ካልን ሌሎች ያደረጉትን ያነኑ ነገር ባናደርግም ተመሳሳይ ስህተት በመድገም ተመሳሳይ የሆነ ባህርይ እናሳያለን። ይህን የምናደርገው ስህተታችንን ለማየት ፈቃደኛ ባለመሆን ዓይናችንን ጨፍነን ነው። ኢየሱስ “አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ” ባለ ጊዜ የተናገረው መርህ ይህ ነበር (ማቴዎስ 7:5)። ማቴዎስ 23:30-35ን ያንብቡ። ኢየሱስ ከዚህ ላይ ምን አይነት የምጎረብጥ ግን አስፈላጊ የሆነ መልዕክት እያስተላለፈ ነው? ከቃላቱ እኛ መውሰድ የሚያስፈልገን ማስጠንቀቂያ ምን ሊሆን ይችላል?
እነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ ፈሪሳውያን ያደረጉትን ድርጊት በእውነት አልወደደውም
የሚል ስሜት ይፈጥራሉ፤ ለዚህ ምክንያቱ በግትርነት ለመለወጥ ፈቃደኛ
ባለመሆናቸው ግብዝነታቸው በመባባሱ ነው። የፈሪሳዊያን ሀይማኖት ኢየሱስን
አንገፍግፎታል። በአጥንት በተሞሉና በኖራ በተለሰኑ መቃብሮች የተመሰለው
በተንዘረፋፋ ልብሳቸው አጊጠው የሚያስተምሩት የፈሪሳውያን የግብዝነት ትምህርት
ኢየሱስ ሰልችቶታል (ማቴዎስ 23:27፣28)። ኢየሱስ እየደጋገመ ኃጢአታቸውን
ቢያሳያቸውም ሃጥያታቸውን ተናዝዘው ንስሐ መግባት አልፈልጉም።
ታዲያ እነዚህን ሰዎች በተመለከተ ኢየሱስ “ግብዞች” ማለቱ አያስገርምም። ጥቅሱ
እንዲህ በማለት ይነበባል፦”ወዮላችሁ እናንተ ግብዞች፣ ጻፎችና ፈሪሳዊያን።”(ማቴዎስ
23:14፣15፣23፣25፣27ን ይመልከቱ)።
ኑሮአቸው የሚያሳየው የሚናገሩትን በተግባራቸው የማያሳዩ መሆኑን ነው። ስለ
ነቢያት የነበራቸው አስተያየትም ይህን ይመስላል። የነቢያትን መቃብሮች በማስጌጥ
ነቢያቱን ያከበሩ ይመስላቸዋል። ነገር ግን የነቢያትን መልእክቶች ተቀብለው
ሃጥያታቸውን ተናዝዘው ንስሐ መግባትን በጭራሽ አልሞከሩም። የነቢያትን ኃይልና
ዝና ፈለጉ። መልዕክታቸውን ግን ናቁ። መቃብራቸውንና ሐውልታቸውን በማስጌጥ
እኛ ብንሆን የእግዚአብሔርን ነቢያት አንገድልም ነበር እያሉ ነው። በዚያን ጊዜ ግን
ከነቢያት ሁሉ የበለጠውን መሲሁን እራሱን ለመግደል ይዶልቱ ነበር።
የፈሪሳውያንን አድራጎት እኛ እራሳችን እንደማንደግም በመርህ ደረጃ
እንዴት እርግጠኛ መሆን እንችላለን? ይህም ማለት በውጭ ሃይማኖተኞች
እየመሰልን በውስጣችን አመጽ፣ ስስትና ጥላቻ የተሞላን እንዳንሆን
መጠንቀቅ ያለብን እንዴት ነው?
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ እነዚህ ዘገባዎች ሁሉ ምንም ያህል አስቀያሚና አሳዛኝ ቢሆኑም የተዘገቡበት በቂ ምክንያት አለ። ይሄውም በጌታ ላይ ካመጽን ምን ሊደርስብን እንደሚችል እኛን ለማስጠንቀቅ መሆኑን እንድንማር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 10:6-12ን ያንብቡ። እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ አነጋገር እግዚአብሔር ነቢያት የጻፉትን እንዲጽፉ ያነሳሳው ለምንድነው?
ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የጥንት እስራኤልንና አሁን ኢየሱስን
አምላካችንና አዳኛችን አድርገን የተቀበልን እኛ አካሏ የሆንነውን ቤተ ክርስቲያን
በማገናኘት ያለፈውንና የአሁኑን ጊዜ በቀጥታ ያገናኛቸዋል (ገላትያ 6:14-16)።
ሰብአዊ ዘር ባለፈው ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ልምምድ፣ መጥፎም
ሆነ መልካም፣ ችላ መባል እንደሌለበት ጳውሎስ በግልጽ ይናገራል። እንዲያውም
አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም በምሳሌ ለይቶ አስቀምጧል። “እነዚህም ክፉ ነገር
ተመኙ፣ እኛ ደግሞ እንዳንመኝ ይህ ምሳሌ ሆነልን” (1ኛ ቆሮንቶስ 10:6)። በሌላ
አነጋገር ያለፈው ወደፊት የሚመጣውን ያመለክታል። ያለፈው አሁን እየሆነ ላለውና
ለወደፊት ለሚሆነው አውድ ነው።
ከዚህ የተነሳ ያለፈው ትውልድ የፈጸመውን ስህተት እንድንፈጽም አልተተወንም፤
በቅዱሳት መጻሕፍትና በነቢያቱ በኩል የላከልንን ማስጠንቀቂያ መልእክቶች ከሰማን
እንዳለፉት ትውልዶች እንደማንጠፋ እግዚአብሔር ያረጋግጥልናል። “ከሰማን፣
ከተማርንና ከታዘዘን ህይወታችን የተደላደለ እና የበለፀጋ ይሆናል”(2ኛ ዜና
20:20)። አንዳንዶች መንፈሳዊ ብልጽግናን እንኳን የሚተረጉሙት ያማሩ ቤቶችን፣
መኪናዎችን፣ ልብስና ሌላም ቁሳዊ ጥቅሞችን እንደማግኘት ነው። እግዚአብሔር
ፍላጎታችንን ሁሉ እንደሚያሟላ ተስፋ በመስጠት በሌላ ነገሮች ከመበልፀጋችን ጋር
ነፍሳችንም እንድትበለፅግ ይፈልጋል (3ኛ ዮሐንስ 2)። ነገር ግን ዘላቂ የሆነ የእውነት
መንፈሳዊ ሙላትና የክርስትና ህይወት የሚገኘው የእግዚአብሔርን መልእክቶች
በመታዘዝ ብቻ ነው።
እግዚአብሔር ሲናገር ነገር አያንዛዛም (አያስረዝምም)። ከተናገረ ቃላቱ ዘላለማዊ
ናቸው። ኃይላቸውና ውጤት አስገኝነታቸው ለዘላለም ነው (ኢሳያስ 40:8)።
የተሰጡት “የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን” እኛን ለማስጠንቀቅ (ለመገሰጽ) ነው
(1ኛ ቆሮንቶስ 10:11)። ያን ጊዜ እውነት ከሆኑ ታዲያ ዛሬ ለእኛ ምን ያህል የበለጠ
አግባብነት አላቸው?
በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ አመጻና ስለ አለማመን የተጻፉ ዘገባዎችን ሲያነቡ
እርስዎም ያንኑ እንዳይደግሙ የሚረደዎ ምን አይነት ትምህርቶች
ማግኘት ይችላሉ?
የኤለን ጂ ዋይት የልጅ ልጅና የቀድሞ የኤለን ጂ ዋይት ባለ አደራዎች ዳይሬክተር
የነበረው አርተር ዋይት አያቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ራእዮችንና ትንቢታዊ ህልሞችን
እንደተቀበለች ይናገራል። ራእዮቹ ከጥቂት ደቂቃዎች እስከ ብዙ ሰዓታት ርዝመት
የነበራቸው ሲሆን አንዳንዴም ራዕዩን ስታይ ያዩ ብዙ ምስክሮች ነበሩ። አንዳንዴም
የሚጠራጠሯት ሰዎች ሳይቀሩ በሰዎች ፊት ራዕይ ባየችባችው ጊዜያቶች ሊመረምሩአት
ዕድል አግኝተው ነበር።
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት ሁሉ ኤለን ጂ ዋይትም በራዕይ ላይ እያለች
ከሰብአዊ ልምምድ ውጭ የሆነ ኃይል ተለማምዳለች። በ1868 ዓ.ም ጄምስ ዋይት
በራዕይ ሳለች ያሳያችውን ሁኔታ በዝርዝር ይገልጸዋል። “በዙሪያዋ የሚካሄደውን ነገር
ሁሉ አታስተውልም ነበር (ልብ አትልም ነበር)፤ አትተነፍስም፣ ጡንጫዎቿ “የገረሩ”
እና መገጣጠሚያዎቿም “የማይንቀሳቀሱ” ነበር። እንቅስቃሴዋ “ነጻና ደስ የሚል”
ነበር። አይኖቿ ተገልጠው ነበር። ከራዕይ ስትወጣ ለተወሰነ ጊዜ ማየት ያቅታታል።
የማየት ችሎታዋ ግን አይጎዳም። ራእዮቹ ሳይጠበቅ የሚከሰቱ ስለነበር እና ኤለን ጂ
ዋይት ራሷ ስለማታውቅ መች እንደሚመጡና ምን ያህል ርዝመት እንደሚኖራቸው
ማንም መቆጣጠር አይችልም ነበር (ጄምስ ዋይት Life Incidents pp 271-274)።
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ሰዎች ለመልዕክቱ የነበራቸው
አስተያየት የተለያየ ነበር። አንዳንዶች የእግዚአብሔርን ምክር ሲቀበሉ ሌሎች
ደግሞ ችላ አሉት። ኤለን ጂ ዋይት እንዲህ ብላለች፦ “እግዚአብሔር ህዝቡን
እንድገስጽ ልኮኛል። በላዬ ይህንን ከባድ ቀንበር ሲያሸክመኝ ሕዝቡ መልዕክቱን ስለ
መቀበል አለመቀበላቸው እነርሱን ተጠያቂ ያደርጋቸዋል። ይህን መራራ ኃላፊነት
ራሴ አልመረጥሁም። ስራው በሰዎች ዘንድ መወደድን አያስገኝልኝም። በአዳኙ
ስምና ብርታት የሚችለውን ያህል አደርጋለሁ። ሰዎች ቢቀበሉም ባይቀበሉም
አስጠነቅቃለሁ፣ እመክራለሁ፣ እገስፃለው፣ አደፋፍራለሁ። ስራዬ ራሴን ማስደሰት
ሳይሆን ስራ የሰጠኝን የሰማይ አባቴን ማስደሰት ነው።” (Testimonies to the
church vol 4 pp 231፣232)።
የሚገርመው ነገር አብዛኞቹ ትንቢታዊ መልዕክቶቹን መቀበል ያልፈለጉት
ባለማመናቸው ወይም ከኤለን ጂ ዋይት ጋር ባለመስማማት ነው እንጂ በስነ መለኮታዊ
(theological) ምክንያት አልነበረም። ኤለን ጂ ዋይት መልእክቱን ያልተቀበሉትን
ሰዎች በበጎ ፈቃድ ተመለከተቻቸው። እንዲያውም ሰዎቹ “በትዕግስት እና
በወንድማማች ፍቅር መታየት አለባቸው። ራሳቸው መርምርው መቀበል አለመቀበሉ
የራሳቸው ውሳኔ ነው” አለች።
ኤለን ጂ ዋይት የትንቢታዊ ስጦታዋ ትክክለኛ ማረጋገጫ እግዚአብሔር
የሰጣት መልዕክቶች ራሳቸው ናቸው ብላ ታምናለች። ሰዎች በቅን ልብ እውነቱን
ቢመረምሩ ስጦታዋ እውነተኛና ሀቀኛ መሆኑን ይረዳሉ ብላ ታምናለች። የተሻለ
ማስተዋል እንዲያገኙ ጌታ እንደሚመራቸውም ታምናለች። “እምነታችንን በእውነት
እንድንመዝን እግዚአብሔር በቂ መረጃ ሰጥቶናል” ትላለች። (Testimonies to the
church vol 4 page 231)