የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡ። ማቴዎስ 5:17-48፣ 1ኛ ቆሮንቶስ
16:20፣ ማቴዎስ 4:1-11፣ ሉቃስ 10:25-28፣44-49።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡“ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ
በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው” (ሉቃስ 24:27)።
ከስቅላቱና ከትንሳኤው በኋላ “እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እንደሆነ
ተስፋ አድርገን ነበር” እያሉ ሲወያዩ ለነበሩ ሁለት ተስፋ ለቆረጡ ደቀ
መዛሙርት ክርስቶስ ተገለጠ (ሉቃስ 24:21)። እነዚህ ደቀ መዛሙርት
መሲህ ከሮማ አገዛዝ አይሁድን ነጻ የሚያወጣቸው መስሏቸው ነበር። ይህ የሀሰት
መሲህን መጠበቅና ይህን ተከትሎ የመጣው ተስፋ መቁረጥ መንስኤው በብሉይ
ኪዳን ስለ መሲሁ የተነገሩ መሲሀዊ ትንቢቶችን ሚዛናዊ ባልሆነ እና በአንድ አቅጣጫ
ማየት ነው።
ክርስቶስ ቃሉን ሰፋ አድርጎ በመተርጎምና በማስተማር የነዚህን ተስፋዬ የቆረጡ
ደቀ መዛሙርት ችግር ፈታላቸው (ሉቃስ 24:25-27)። የክርስቶስ የቃሉ አተረጓጎም
አይኖቻቸውን ገለጠላቸው፣ ልቦቻቸውንም አቃጠለ (ሉቃስ 24:31፣32)። ቆይቶ
ደግሞ ክርስቶስ ቁጥራቸው በርከት ላለ ደቀ መዛሙርት በኢየሩሳሌም ተገለጠላቸው።
“በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው” (ሉቃስ
24:45፣ ሉቃስ 24:33፣ 36፣44-49ን ይመልከቱ)።
እነዚህ ምሳሌዎች ትንቢታዊ ጽሑፎችን በትክክል የማስተዋልን አዎንታዊ
(መልካም) ውጤት ያሳያሉ። ትንቢትን በተሳሳተ መንገድ ማስተዋል መንፈሳዊ
ውድመትን ያስከትላል።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለህዳር 12 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
አብዛኛውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎማችን በግምት ላይ የተመሰረተ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን የተራ ጽሑፎች ጥርቅም ነው ብሎ የሚገመቱ ሰዎች በተለያዩ መጻሕፍት መካከል ምንም ዓይነት ህብረት ሊያዩ አይችሉም። ነገር ግን “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ይጠቅማል” የሚለውን ከተቀበልን መሰረታዊ ህብረቱንና መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ ተርጓሚ መሆኑን ማየት እንችላለን። ማቴዎስ 5:17-48ን ያንብቡ። በዚህ ንባብ ውስጥ የተጠቀሱትን የብሉይ ኪዳን አስተምህሮዎች ኢየሱስ እንዴት አብራራቸው?
ማቴዎስ 5:17-48ን ላይ ላዩን የሚያነብ ሰው ኢየሱስ የብሉይ ኪዳንን
አስተምሮዎችን በራሱ አዲስ አስተምሮዎች የተካ ሊመስለው ይችላል። ነገር ግን
በደንብ በጥንቃቄ ማንበብ ኢየሱስ የብሉይ ኪዳንን ጥልቅ መንፈሳዊ ገጽታዎች
እየገለጠ መሆኑን ግልጽ ያደርጋል። በዚህ መልኩ በኤርምያስ 31:31-33 ላይ በአዲሱ
ቃል ኪዳን የእግዚአብሔር ሕግ በሕዝቡ አእምሮ ውስጥ እንደሚደረግና በልባቸው
እንደሚጻፍ የተገባውን ተስፋ እየፈጸመ ነው። (ከዕብራውያን 8:8-10 እና ዕብራውያን
10:16 ጋር ያነፃፅሩ)።
አንዳንዴ የተነበበው ምንባብ ትርጉም ምንባቡ በተዘገበበት በዚያው መጽሃፍ
ውስጥ ይገኛል። ለምሳሌ የናቡከደነጾርን ህልም በዳንኤል 2 ላይ እናገኛለን (ዳንኤል
2:31-35)። የዚያን ምስጢራዊ ትርጉም ደግሞ በዳንኤል 2:36-45 ላይ አናገኛለን።
እንዲሁም በማቴዎስ 13 ላይ የዘሪውን ምሳሌ እናያለን (ማቴዎስ 13:9)። ትርጉሙ
ደግሞ በዚያው ምዕራፍ ውስጥ አለ (ማቴዎስ 13:18-23)።
አንዳንዴ ደግሞ የአንድ መልዕክት ትርጉም በሌላ ቆይቶ በሚነሳ ነቢይ ይሰጣል።
ለምሳሌ በኤርምያስ 25:11፣12ና በኤርምያስ 29:10 የተነገረው የ70 ዓመት ትንቢት
ፍጻሜው 2ኛ ዜና 36:22፣23 ላይ ተዘግቧል። ሆኖም ብዙ የብሉይ ኪዳን ምሳሌዎች
በክርስቶስ መገለጥ ተፈጽመዋል። ሌሎች የብሉይ ኪዳን ጽሑፎች በአዲስ ኪዳን
ጽሑፎች ተተርጉመዋል።
“ብሉይ ኪዳን የምልክትና የምሳሌ ወንጌል ነው። አዲስ ኪዳን ፍሬ ነገሩ ነው።
ቢሆንም የሁለቱም አስፈላጊነት አይተናነስም፣ አይበላለጥምም።” (selected mes-
sages፣ book 2፣ page 104)። በእርግጥ አዲስ ኪዳን በመንፈስ የተመራ የብሉይ
ኪዳን ተርጓሚ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና ግምታችን እንዳያሳስተን መጠንቀቁ ወሳኝ
የሚሆነው ለምንድር ነው? የሚፈርደን የእግዚአብሔር ቃል ነው እንጂ
እኛ የእግዚአብሔርን ቃል መፍረድ እንደማንችል መገንዘባችን እንዴት
ይጠቅመናል?
ኢሳይያስ 65:17-20ን ያንብቡ። በአዲሲቱ ሰማይና በአዲሲቱ ምድር “ጎልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና” ሲል ምን ማለቱ ነዉ? (ኢሳያስ 65:20)።
ኢሳያስ 65:20ን ከታሪካዊ አውድ ውጭ አድርጎ በአዲሲቱ ሰማይና በአዲሲቱ
ምድር ሞትና ሃጢያተኞች ይኖራሉ ብሎ መተርጎም ይቻላል። ይህ አስተሳሰብ ግን
የሞቱት ፃድቃን ይነሳሉ፣ ሀዘንና ሞት ከዚያ በኋላ አይኖርም የሚለውን በኢሳይያስ
ላይ የተሰጠውን ተስፋ ይጻረራል (ኢሳያስ 26:19፣ ኢሳያስ 25:8፣ ኢሳያስ 65:20)።
ኢሳያስ 65:20 በእርግጥ ምሳሌያዊ ቋንቋ ነው። የ100 ዓመት ጎልማሳ (ልጅ)
የት ይገኛል? ነገር ግን ኢሳያስ 65:17-20ን በታሪካዊ አቀማመጥ ስናነብ ህዝቡ
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ (ቃል ኪዳን) ቢያከብሩ ሊቀበሉ የሚችሉትን በረከት
የሚያመለክት ቅኔያዊ ምሳሌ ነው (ከዘዳግም 28 ጋር ያስታያዩ)። ኢየሱስ በማቴዎስ
24 ላይ በቅርብ የሚሆነውን ክስተት በኋላ ከሚሆነው ክስተት ጋር እንዳነፃፀረ ሁሉ
ኢሳያስ አሁን በምድር ላይ የሚደርሰው በረከት በአዲሲቱ ሰማይና በአዲሲቱ ምድር
ለሚሆነው ቅምሻ መሆኑን ሊያመለክት ነው።
በኢሳይያስ ላይ የሚነገረው አዲስ ፍጥረት ለወደፊት የሚሆን ብቻ አይደለም።
በእግዚአብሔር የሚያስገርም የማዳንና ይቅር ባይነት ተግባር አሁንም ይገኛል።
ጥቅሱ አሁንም ቢሆን በእስራኤል ምድራዊ ኑሮ እግዚአብሔር ሞትን አሸንፏል። ይህ
ሀሳብ የረዥም ዘመን መኖርንና የህፃናትን ሞት ለማቆም የተሰጠውን ተስፋ ያበስራል
(ኢሳያስ 65:20)። ይህ ለወደፊት ለሚሆነው ጥላ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 16:20ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ ለዘመናችንና ለባህላችን ምን
አግባብነት አለው?
በአዲስ ኪዳን ጊዜ በነበረው የግሪክ ባህል ወዳጅ ዘመድ ሲገናኙ በመሳሳም
ሰላምታ መቀያየር የተለመደ ነበር። ስለዚህ ፍቅራዊ የሰላምታ መግለጫ ጳውሎስ
በሮሜ 16:16፣ በ 1ኛ ቆሮንቶስ 16:20፣ በ2ኛ ቆሮንቶስ 13:12 እና 1ኛ ተሰሎንቄ 5:26
ላይ ለክርስቲያኖች ምክሩን ይለግሳል። ከዚህ አውድ ላይ ልንገነዘብ የምንችለው
አማኞችን ሞቅ ባለ የፍቅር ስሜት ሰላም ማለት እና የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል
መሆናቸውን መግለጽ ተገቢ መሆኑን ነው። በአንዳንድ ባህሎች መሳሳም ተቀባይነት
ላይኖረው ይችላል። በእጅ መጨባበጥ፣ መተቃቀፍ ወይም እጅ መንሳት የበለጠ
ተቀባይነት ይኖረዋል። ያም ሆነ ይህ በቤተ ክርስቲያን ስንሰባሰብ ባህሉ በሚፈቅደው
ዓይነት ፍቅራችንን እንድንገላለጽ ጳውሎስ ያደፋፍረናል።
አንድ የታወቀ ሰባኪ ከባድ ችግር ስለ ደረሰበት እና ከችግሩ ለመውጣት
የእግዚአብሔርን ፍቃድ ስለ ጠየቀ አንድ ሰው ታሪክ ይተርካል። ሰውየው መጽሐፍ
ቅዱሱን ገልጦ እንዲያው በአጋጣሚ ወደ አንድ ጥቅስ በጣቱ ይጠቁማል። “ይሁዳም
ሄዶ ራሱን ሰቀለ” ከሚለው ጥቅስ ላይ ጣቱ ያርፋል። ደነገጠና አሁንም እንደ
በፊተኛው አደረገ። አሁን ጣቱ በሉቃስ 10:37 “ኢየሱስም ሂድ አንተም እንዲህ
አድርግ” ከሚለው ላይ ጣቱ ያርፋል። ሁለቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ናቸው።
ግን በአውዳቸው መስተዋል አለባቸው።
በእርግጥ ብዙዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች በስህተት የሚተረጉሙት ከአውዱ
ውጪ በሆነ አመለካከት ሲታዩ ነው። ይህ አይነቱ አቀራረብ ቃሉን ለሰው ሰራሽ
አተረጓጎም ይዳርጋል።
ዘፍጥረት 3:1-5ና ማቴዎስ 4:1-11ን ያንብቡ። ከአውድ ውጪ በማስቀመጥ
ሰይጣን የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት አዛባው?
አንዳንድ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን መልዕክት የሚያማቱት ሆን ብለው ሳይሆን
ከእውቀት ጉድለት የተነሳ ነው። ሌሎች ግን ሰይጣን ከላይ በተጠቀሱት ክስተቶች
እንዳደረገው ሆነ ብለው የእግዚአብሔርን ቃል ያማታሉ። ያም ሆነ ይህ ውጤቱ አንድ
ነው (ያው ነው)። እርሱም ጥፋት ነው። በኤደን ገነት ውስጥ ሰይጣን (ዘፍጥረት 3:1-
5፣ ከሪያል 12:9 ጋራ ያስተያዩ) ወደ ሄዋን የቀረበው ለማወቅ የፈለገ፣ የሰው ቋንቋ
የሚናገር፣ የሚያምር ፍጥረት መስሎ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ከመጀመሪያው
አውድ አስወጥቶ የራሱን ሀሳብ ጨማምሮ አድበስብሶ አቀረበላት።
ኢየሱስ ወደ ምድረ በዳ በመንፈስ ሲወሰድ (ማቴዎስ 4:1-11፣ ሉቃስ 4:1-13)
ሰይጣን “ክርስቶስን ለመፈተንና ለማታለል የብርሃን መልዓክ መስሎ መጣ” (El-
len G white The Adventist review and sabbath herald፣ Dec 18፣1888)።
ከክርስቶስ ጋር ባደረገው ንግግር ሰይጣን መዝሙር 9:11፣12ን በትክክል አልጠቀሰም።
ራሳቸውን ሆን ብለው ለአደጋ የሚያጋልጡ ሰዎችን እግዚአብሔር እንደሚረዳቸው
አስመስሎ አቀረበው።
በኤደን ገነት ውስጥና በምድረ በዳው ላይ በተከሰቱት ክስተቶች እንደታየው ታላቁ
ተጋድሎ የቃሉን የተሳሳተ አተረጓጎም ያካትታል። እነዚህ ሁኔታዎች የእግዚአብሔርን
ቃል በአውዱ መሰረት ለማስተዋል መጣር ምንኛ አስፈላጊ መሆኑን ያረጋግጡልናል።
አስተያየታችን የቱንም ያህል ትክክል ቢሆንም ጥቅሶችን ከአውዳቸው
ውጪ አድርገን ለሌሎች ለማስረዳት ጥረት የማድረግን ፈተና መሸሽ
ያለብን ለምንድን ነው?
ክርስቲያኖች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው ማስተዋል ይገባቸዋል። ሰዎች ሁሉ የድነት መንገድን እንዲያስተውሉ ለማድረግ መጽሐፍ ቅዱስ በበቂ ሁኔታ ግልጽ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አዋቂ ነን የሚሉት ሁሉ ለማስተዋል የሚቸገሩበት ምስጢር አለበት። ቃሉ ቢጠና ቢጠና የማያልቅ እውቀትን ያካተተ የማያልቅ እንቁ ነው። ሉቃስ 10:25-28ን ያንብቡ። አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ አያስፈልገውም ይላሉ። እንዲያ ከሆነ ኢየሱስ ለምን “በህግ የተጻፈው ምንድነው? እንዴትስ ታነባለህ (ትተረጉማለህ)” አለ? (ሉቃስ 10:26)።
የአንድን ጥቅስ ትርጉም ለመረዳት በመጀመሪያ ማድረግ ያለብን ጥቅም ላይ የዋሉ ቃላትን መረዳት ነው። ክዚያም ተዛማጅነት ባለው የስነ-ጽሑፍ አውደና በአጠቃላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ አውድ እንዲሁም ከታሪካዊና ባህላዊ አውድ እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋሉ ለማወቅ እስከምንችል ድረስ መጣር ነው። በመጨረሻም ድምዳሜያችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ሰፊ አስተምህሮዎች ጋር ሙሉ በሙሉ መጣጣም አለባቸው። በአራቱ ወንጌላት እንደተደረገው ሁሉ ትይዩ ጥቅሶችን ማነጻጸር መረዳታችንን ማበልጸግ ይችላል። ማቴዎስ 5:43-48ን ከሉቃስ 6:27-36 ጋር ያነጻጽሩ። የማቴዎስ 5:43- 48 አውድና ትይዩ ጥቅስ፣ ሉቃስ 6:36፣ በማቴዎስ 5:48 ላይ “ፍጹም” የሚለውን ቃል ትርጉም በተሻለ ሁኔታ እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው?
የታማኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ አንዱና ዋና መለያው ከልቡ የሚሰራና
ትሁት መሆኑ ነው። እውነት የማናችንም ንብረት አለመሆኑን ልብ ይሏል፤ ሁላችንም
“በመስታወት በድንግዝግዝ እናያለን።” ምንጊዜም የምናምነው አስተምሮ እውነት
መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልገናል (2ኛ ጢሞቴዎስ 4:1-5)። ልንከተል የሚገባን መመሪያ
ያስተዋልነውን መከተል እና በዚያ ላይ ያላስተዋልነውን ለማስተዋል መጣር ነው።
በሰማይ ዝርዝሩን እስክንማር ድረስ በዚህ ምድር ሳለን ሁሉንም ማወቅ አንችልም።
በፊት ያላስተዋሉትን ነገር ሲገለጥልዎ እንዴት እንደተሰማዎት እስቲ
ያስተውሉ። ታዲያ ያለፈው ልምምድዎ አሁንም ያላስተዋሉትን
እግዚአብሔር ሊገልጥልዎ እንደሚችል ምን ያህል አስተማማኝ
ይሆንልዎታል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን በሁለት ሀሳቦች ላይ ማተኮር አለበት። ይህም የግል መንፈሳዊ ዕድገታችንና ሌሎች የክርስቶስን አዳኝነት እንዲያውቁ ወደ እርሱ መምራት ላይ ነው። ክርስቶስ ስለ እውነተኛ ክርስቲያን እንዲህ ይላል፦ “የእውነት መንፈስ ወደ እውነት ይመራል። ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ይኖራል”(ዮሐንስ 16:13፣ ማቴዎስ 4:4)። የታዘዘውን ሁሉ ለሌሎች ያስተምራል (ማቴዎስ 28:20)። ሉቃስ 4:16-30፣ ሉቃስ 24:25-27፣44-49ን ያንብቡ። ለእነዚህ ጥቅሶች ክርስቶስ ከሰጠው ማብራሪያ ምን መማር እንችላለን?
ኢየሱስ ክርስቶስ “መንገድና እውነት ህይወትም ነበር፣ አሁንም ነው፣ ሁልጊዜም
ይሆናል”(ዮሐንስ 14:6)። ቢሆንም ስብከቱ ጸንቶ የተመሰረተው በቃሉ (በመጸሃፍ
ቅዱስ) ላይ ነበር። ለምሳሌ ማርቆስ 1:14፣15 እንዲህ ይላል፦ “ዮሐንስም አልፎ
ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል እየሰበከና ዘመኑ ተፈጸመ፣
የእግዚአብሔር መንግስት ቀርባለች ንስሐ ግቡ፣ በወንጌል እመኑ እያለ ወደ ገሊላ
መጣ።” ጊዜው በእርግጥ ወደ ዳንኤል 9:24-27 ያመላክታል። በተራራው ስብከት
(ማቴዎስ 5-7) ላይ ዘፍጥረት 20:13ንና 14ን ይጠቅሳል (ማቴዎስ 5:21ና 27)። በሉቃስ
4 ደግሞ ኢሳያስ 61:1 እና 2ን ጠቀሰ። ኢየሱስ በግልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሰባኪ ነበር።
በሌላ ምሳሌ ደግሞ የሐዋርያት ሥራ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ “ወደ እየሩሳሌም
ሊሰግድ መጣ” ይላል (የሐዋርያት ሥራ 8:27)። ይህ ማለት ስለ አይሁድ ሃይማኖት፣
ቢያንስ ስለ አንዳንዱ ስነ ስርዓት ያውቅ ነበር ማለት ነው። እንዲያውም የኢሳይያስ
መጽሐፍ ቅጅ ስለነበረው እያነበበ ነበር። ነገር ግን ኃጢአት ስለሚሸከመው አገልጋይ
የሚያነበውን ትንቢት አላስተዋለውም። ስለዚህ የሚያስረዳው ሰው አስፈለገው።
ይህ ልምምድ አንድ ሁለት ትምህርቶችን ያስተምረናል። በመጀመሪያ ደረጃ
አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስላነበብን ብቻ እናስተውለዋለን ማለት አይደለም።
ሁለተኛ ቃሉን ስናጠና እርስ በርሳችን ልንማማር እንችላለን፣ ይገባናልም። ሦስተኛ
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሌሎች ለማካፈል ሀላፊነት ተጥሎብናል።
ፊልጶስ ኢሳይያስንና ሌሎች የብሉይ ኪዳን መልእክቶችን ስላስረዳው ጃንደረባው
ተጠመቀ (የሐዋርያት ሥራ 8:35-39፣ መዝሙር 51:12 ጋር ያስተያዩ)። እኛም ቃሉን
ለሌሎች የምናስረዳው ለዚያው ዓላማ ነው (ዮሐንስ 17:17ን ይመልከቱ)።
አንዳንዴ ጥቅሶችን ለማስተዋል እርዳታ ቢያስፈልገንም ስለምናምነው
ነገር በአእምሮአችን እርግጠኛ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?
በትክክል ለማስተዋል እና በስራ ላይ ለማዋል የሚረዱ ጥቂት መመሪያዎች እነሆ፦
መጀመሪያ በመጠራጠር ሳይሆን በጸሎት እና በተከፈተ አእምሮ (በበጎ ፈቃድ)
ማንበብ ይጀምሩ። አስተሳሰባችን የምንሰማውን፣ የምናነባውንና የምንመለከተውን
የሚቀባ ሌንስ ወሳኝ ነው። አስተሳሰባችን በመንፈስ ቅዱስ ሊመራ ይገባል። ኤለን ጂ
ዋይት ራስዋ እንዲህ ብላለች፦ “ቃሉን የምትመረምሩ የራሳቸሁን አስተያየት ለመደገፍ
ከሆነ በምንም ሁኔታ እውነቱን አታገኙም። እግዚአብሔር ምን እንደሚል ለማወቅ
ተመራመሩ (አጥኑ)። (የክርስቶስ ምሳሌያዊ ትምህርቶች ገጽ 112፣ በእንግሊዘኛው
ቅጅ)። ስለ እሷ ጽሑፎች ጥናትም ያው ነው።
2ኛ ስለምታነቡት ክፍል አውዱን አትርሱ። አንዳንድ ሰዎች ጽሑፏን ከአውዱ
ውጪ በነጠላ ቃል ወይም በአንድ አንቀጽ ብቻ ሊያስተውሉ ይሞክራሉ። ኤለን ጂ
ዋይት “ጊዜና ቦታ ወሳኝ ነው” ብላለች (selected messages book 1 page 57)።
ይህ አውደን ችላ የማለት አሳዛኙ ልምምድ ለአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባላት ችግር
ፈጥሯል፣ አሁንም ችግር መፍጠሩን ይቀጥላል።
3ኛ በዋናው ሃሳብ ላይ አተኩሩ፣ ያ ክፍል ለማስረዳት የፈለገው ዋና ሃሳብ
ምንድነው? ለምሳሌ በ1894 ኤለን ጂ ዋይት በባትል ክሪክ፣ ሚቺጋን የሚገኙትን
የቤተ ክርስቲያን አባላት ብስክሌቶች ስለገዙ ወቀሰቻቸው። ሃሳቡ እግዚአብሔር
የሰጠንን ገንዘብ ማባከን የለብንም ማለት ነው (በዚያን ጊዜ ብስክሌት ውድ ነበር)።
4ኛ ኤለን ጂ ዋይት በሆነ ርእስ ላይ የጻፈችውን ሁሉ አንብቡ። በአንድ ታሪክ ላይ
የሰጠችውን ተራ የመሰለ አስተያየቷን እንኳ መርምሩ። ኤለን ጂ ዋይት ጽሑፎቿን
አንዳንድ ሰዎች ያለአግባብ ሲጠቀሙ ስታይ እድሜ ልኳን ስታዘን ኖራለች። “የሲስተር
ዋይት መልዕክት ነው እያሉ ሀሳቧን በማጣመም ያላሰበችውንና ያላለችውን ያሰበችና
የተናገረች እያስመሰሉ ያቀርባሉ።” (selected message book 1 page 44)
በመጨረሻ የምታነቡት ኤለን ጂ ዋይት ራሷ ያለችው መሆኑን አረጋግጡ።
አንዳንድ አባባሎች በውሸት የእርሷ አባባሎች ናቸው እየተባሉ ቀርበዋል። የምታነቡት
በእርሷ የተፃፈ መሆኑን ለማረጋገጥ የተጠቀሰበትን መጽሐፍ ማወቅ ያስፈልጋል። ከየት
እንደተጠቀሰ ካወቅን ትክክለኛ መርሆዎችን በመጠቀም እውነተኛነቱን መመርመር
እንችላለን።
በኤለን ጂ ዋይት ትንቢታዊ ጽሑፎች ውስጥ ድንቅ ስጦታዎች ተሰጥተውናል።
በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች በረከት ስለሆኑ ጽሑፎቿን በትክክል (በአግባብ) ማንበብ
በጣም ይጠቅማል። ያለአግባብ መጠቀምና ከስራ ላይ ማዋል በጣም አሳዛኝ ነው።