የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡ፦ማቴ 16:13-16፣ ኤፌ 2:20፣ ራዕይ 22:6፣ ሉቃስ 2:36-38፣ የሐዋ 21:9፣ ኤፌ 6:10-18።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡“የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፣
አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፣ አሰራርም ልዩ ነው፣ ሁሉን
በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 12:4-6)።
አንድ አባት መኪናውን ሲነዳ (ሲያሽከረክር) አጠገቡ ተቀምጦ የነበረው
ልጁ የአባቱን መኪና የሚመስሉትን መኪናዎች ለመለየት በአጠገባቸው
የሚያልፉትን መኪናዎች ይመለከት ነበር። ከዚያ አባቱ ወደ አንድ መኪና
እያመለከተ በመደነቅ” ተመልከት ልጄ፣ ያ መኪና የመጀመሪያ መኪናዬን ይመስላል”
አለ። ከቤት ሲደርሱ አባትየው የመጀመሪያ መኪናውና የአሁኑ መኪና ባለቤት
መመሪያ (manual) አውጥቶ የሁለቱን መኪናዎች ልዩነትና ተመሳሳይነት ለልጁ
አሳየው። ነገር ግን የመኪናዎቹን ኢንጂን (ሞተር) ሲያስተያይ ተመሳሳይ ነበሩ። ብዙ
ለውጦች ቢኖሩም ሞተሩ ግን ያው ነበር።
እግዚአብሔር በብሉይና በአዲስ ኪዳን በኩል ተናገረ። የመልእክቶቻቸው
መደጋገፍና መጣጣም ምክንያቱ መንፈስ ቅዱስ--የመለኮታዊው መገለጥ ምንጩ
ወይም “ሞተሩ” ያው ስለሆነ ነው። መንፈስ ቅዱስ በትንቢት ስጦታ አማካይነት
ሁልጊዜ እውነተኛ ነቢያትን ያስታጥቃል (ኃይል ሰጣቸው)። የዕብራውያን መጽሃፍ
በግልጽ እንደሚያስረዳው እርሱ ክርስቶስን ብመልእክቱ ማዕከል (እንብርት)
ያስቀምጠዋል (ዕብራውያን 1:13)።
በዚህ ሳምንት የትንቢትን ስጦታ በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንመለከታለን። ነቢያት
ያደረጉትን፣ እንደ ነቢያት ሆነው እነማን እንደሰሩና፣ ነቢያትን ከሐዋርያት ጋር
እናነፃጽራለን። የሃሰተኛ ነቢያትን አደገኛነትንም እንመለከታለን።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለጥቅምት 14 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
ሙሴ እንዲህ ሲል ተነበየ፣ “አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል፣ ከወንድሞችህም እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልና፣ እርሱንም ታደምጣለህ” (ዘዳ 18:15)። ያ ነቢይ ማን ነው? የእግዚአብሔር ቃል ራሱ ግልጽ አድርጎታል። ወደ ኢየሱስ ወደ እራሱ እያመለከተ ነው። “ሙሴም ለአባቶች ‘ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሳኝ ከወንድሞቻችሁ ያስነሳላችኋል በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት’ አለ” (የሐዋ 3:22፣ዮሐ 6:14ንም ይመልከቱ)። የኢየሱስ የነቢይነት ሚና ምን ነበር? ኢየሱስ ይህን ጥያቄ እንዴት መለሰ? (ማቴ 16:13-16፣ማር 8:27-29፣ሉቃ 9:18-20)።
የብሉይ ኪዳን ነቢያት ሁሉ ያመላከቱት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መሲሁ ነበር።
በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ የመሲሐዊ ትንቢቶቻቸው ፍጻሜ መሆኑ ተገለጸ። በሉቃስ
24:13-15 ላይ መሲሐውያን ነቢያት የተናገሩለት እርሱ ራሱ መሆኑን መሰከረ።
እንዲያውም በዮሐንስ 1:1-5 ስለ ቃሉ የተሰጠው መግለጫ ለማንኛውም ሰብዓዊ
ፍጡር ወይም ለሰብዓዊ ነቢይ አይመጥንም (አይገጥምምም)። ቃሉ ፈጣሪ መሆኑ
ተገልጧል፦ “ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ ከሆነውም አንዳች እንኳን ያለ እርሱ አልሆነም”(ዮሐ
1:3)። ይህ ማለት የተፈጠረውን ሁሉ፣ 93 ቢሊዮን የብርሃን ዓመታት (light years)
ስፋት እንዳለው የሚገመተውን አለማትን በሙሉ ፈጠረ ማለት ነው።
በዘፍጥረት 1 ላይ “እግዚአብሔርም አለ” በሚለው በእያንዳንዱ ንግግር
ኢየሱስ ሲናገር እንሰማለን። “ብርሃን ይሁን” ያለው(ዘፍ 1:3) እርሱ እራሱ የዓለም
ብርሃን ነው (ዮሐ 1:4)። ከዚህ የተነሳ በመዳን ዕቅድ መሠረት የምድርን ጨለማ
ገፈፈ (ዮሐ 1:4-5)።
የእግዚአብሔር ትንቢታዊ ቃላት የታመኑና እውነቶች ናቸው። ለሚሰማቸው
ሁሉ “ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ በጨለማ
ስፍራ የሚያበራ ብርሃን” ናቸው (2ኛ ጴጥሮስ 2:19)። “የንጋት ኮከብ” የሆነው ኢየሱስ
እስኪመጣ ድረስ ትንቢት ለዚህ የጨለማና የኃጢአት ምድር ማብራቱን ይቀጥላል።
የዚያ ትንቢታዊ ብርሃን ምንጭ የሆነው የዘላለሙን መንግስት ያመጣል።
እስከዚያ ድረስ ግን ክርስቶስ በህይወቱ፣ በሞቱና በትንሣኤው አማካኝነት
የዘላለም ህይወትን ተስፋ አረጋግጦልናል። ጥያቄው ግን የእኛ ለመቀበል የሚኖርን
ፈቃደኝነት ብቻ ነው።
ፈጣሪው ኢየሱስ(ዮሐ 1:1-3) ኃጢአትዎትን ለማስተሰረይ በመስቀል ላይ
መሞቱን ያሰላስሉ። ይህ አስገራሚ ክስተት(እውነት) እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን
ፍቅር እውነተኛነት ምን ያህል ያስረዳል?
ፈጣሪው ኢየሱስ (ዮሐ 1:1-3) ኃጢአትን ለማስተሰረይ በመስቀል ላይ
መሞቱን ያሰላስሉ። ይህ አስገራሚ ክስተት እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን
ፍቅር እውነተኝነት ምን ያህል ያስረዳል?
አዲስ ኪዳን የነቢያትንና የሐዋርያትን ስራ ያወሳል። ሐዋርያት ተብሎ
የተተረጎመው የግሪኩ ቃል “አፖስትሎስ” “መልክተኞች” ወይም “ከእግዚአብሔር
የተላኩ” ማለት ነው። “ሐዋርያት” የሚለው ቃል በወንጌሎች በሙሉ ወደ አስራ
ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ያመለክታል። የቀረው አዲስ ኪዳንም ይህን ሃሳብ ይደግፋል።
እንዲያውም ከመጀመሪያዎቹ የክርስቶስ ተከታዮች መካከል ያልሆኑትን ሌሎች
ግለሰቦችንም ያከትታል።
ጳውሎስ በደብዳቤዎቹ (በመልእክቶቹ) ውስጥ ራሱን አስራ ሁለት ጊዜ ሐዋርያ
ብሎ ይጠራል። በሮሜ 1:1-2 ላይ ለሐዋርያነት መጠራቱን በመግለጽ የስብከቱን
መልዕክቶች ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ጋር ያያዝቸዋል። ጳውሎስ ራሱን ለአህዛብ
ሐዋርያ ነኝ ብሎ ይጠራል (1ኛ ቆሮንቶስ 1:1)።
ከቤተሰባዊ ዘርፍ ከአባት ወደ ልጅ ሲወርድ ሲዋረድ እንደሚያገለግሉት ካህናት
ሳይሆን እግዚአብሔር እንደ ፈቀደ ነቢያትንና ሐዋርያትን መረጠ። የጳውሎስን
ሐዋርያነት ሌሎች ሲጠራጠሩ” በእግዚአብሔር ፍቃድ” መመረጡን ተሟገተ (ሮሜ
11:13፣1ኛ ቆሮ 9:1-2)።
ጳውሎስ አገልግሎቱን የቀጠለው የቤተ ክርስቲያኗ መሰረት በሆነው በክርስቶስ
ስራ ላይ መሆኑን ይናገራል (ኤፌ 2:20)። እግዚአብሔር ስለገለጠላቸው፣ ሐዋርያትም
የነቢያትን ያህል የራዕይ መገለጥ አላቸው (ኤፌ 3:1-5)።
በ2ኛ ጴጥሮስ 3:1-2 ላይ ከርሱ በፊት የመጡት ነቢያት ቃላታቸው አስፈላጊ
መሆናቸውን ከጠቀሰ በኋላ ሐዋርያት ተመሳሳይ ስልጣን እንዳላቸው ይናገራል።
በእነዚህ ጥቅሶች የብሉይና የአዲስ ኪዳን ጊዜያት ተጠቅሰዋል። ነቢያት የብሉይ
ኪዳን ዘመናት ሐዋርያት ደግሞ የአዲስ ኪዳን ጊዜያት መልክተኞች ቢመስሉም፣ ነገር
ግን ሐዋርያት ያልሆኑ የትንቢት ስጦታ የተቀበሉና ትንቢት የተናገሩ ሌሎች ግለሰቦች
ነበሩ። የትንቢት ስጦታ በአዲስ ኪዳን ለሐዋርያት ብቻ የተወሰነ አልነበረም። ነቢያት
ሁሉም ሐዋርያት አልነበሩም (የሐዋ 15:22)።
ኤፌሶን 2:20 እና ኤፌሶን 3:5ን ያንብቡ። ሐዋርያትና ነቢያት ከክርስቶስ
እና ከቤተ ክርስቲያኗ ጋር በተገናኘ እንዴት ይሰራሉ?
ሐዋርያት በአዲስ ኪዳን ውስጥ የፃፉትን ስናነብ የፃፉት ሁሉ ክርስቶስን ማእከል
ያደረገ ነው። ባንድም ሆነ በሌላ በኩል ያተኮሩት በሕይወቱ፣ በሞቱ፣ በትንሣኤው፣
በሊቀ ካህናት አገልግሎቱና በዳግም ምጽአቱ ላይ ነው።
ስለ ክርስቶስ ህይወትና ስራ የሐዋርያትና የነቢያት ምስክርነት
የተመዘገበበት ስልጣናዊ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ታዲያ
ስለ ኢየሱስና ስለ መሞቱ ለማመናችን ከማንም በላይ ስልጣን ያለው
መረጃ ለመሆኑ ምን አይነት ማስተዋል ይሰጠናል?
የአዲስ ኪዳን ነቢያት ተግባሮች (ሚና ሚና) የሚከተሉት ጥቅሶች የአዲስ ኪዳን ነቢያት ስለሚጫወቱት ሚና ምን ይነግሩናል? 1ኛ ቆሮ 14:3፣ ኤፌ 4:11-13፣ ራዕይ 22:6
እነዚህ ጥቅሶች ጠቃሚ ቢሆኑም የአዲስ ኪዳን ነቢያት የተጫወቱትን ሚና ሙሉ
በሙሉ አያስረዱም። እነርሱ የሰሩት አብዛኛው ስራ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የሰሩትን
ስራ ያንጸባረቃል። ስለዚህ ትንቢታዊ ስጦታ ቀጣይነት እንዳለው ያሳያል።
ትንቢት መናገር ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አንዱ መሆኑ በ1ኛ ቆሮንቶስ 12:10
ላይ ተወስቷል። በክርስቶስ አካል ምሳሌ ውስጥ ነቢያት ከሐርዋርያት በኋላ የተጠቀሱ
ሲሆን እነርሱም ደግሞ ከእግዚ አብሔር ራዕይ የተቀበሉ ናቸው (1ኛ ቆሮ 12:27፣28)።
1ኛ ቆሮንቶስ 14:3 አንዲህ ይላል” ትንቢት የሚናገር ግን ለማነጽ እና ለመምክር፣
ለማጽናናትም ለሰው ይናገራል” (1ኛ ቆሮ 12)
ኤፌሶን 4:11-13ም በ1ኛ ቆሮንቶስ 12 ላይ እንደተገለጸው ተመሳሳይ የመንፈስ ቅዱስ
ስጦታ ጥርቅሞችን ዘግቧል። ነቢያት ከሐዋርያት፣ ከወንጌል ሰባኪዎች፣ ከእረኞችና
ከአስተማሪዎች ጋር ተደምረው ተወስተዋል (ኤፌ 4:11)። እነዚህ ግለሰቦች ያሉት
“ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት ሙሉ
ሰውም ወደ መሆን የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ
ቅዱስን አገልግሎትን ለመስራትና ለክርስቶስ አካል ህንፃ ፍፁማን ይሆኑ ዘንድ”
ነው(ኤፌ 4:12፣13)። በዚህ ቦታና በሌላም ስፍራ እንደምናየው የመልእክታቸው
ማዕከል ኢየሱስ ነው።
የሐዋርያት ስራ ይሁዳ እና ሲላስ ስለተባሉ ሁለት ነቢያት ይናገራል (ሁለቱም
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መጽሐፍ አልጻፉም)” ይሁዳና ሲላስም “ነቢያት ነበሩና
ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኗቸው (የሐዋ 15:32)። ነቢያት አንዳንድ
ጊዜ ማስጠንቀቂያ እንዲያውም ብርቱ ማስጠንቀቂያ ቢናገሩም፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ
እንደ አስፈላጊነቱ የማደፋፈሪያ ወይም የማጽናኛ መልዕክት ያስተላለፋሉ። እነዚህ
ተስፋና ማበረታቻ ያዘሉ ቃላት ተስፋ ለቆረጡ ሰዎች ብርታት ይሰጣሉ። ተቀባዮቹም
በምስጋና መንፈስ ይቀበሏቸዋል።
የማደፋፈር ስራ ትንቢትን በመናገር አውድም ተወስቷል (1ኛ ቆሮ 14:31)።
በስደትና በመክራ ጊዜ የትንቢት ስጦታ የመበረታታትና የተስፋ ምንጭ የሆነበት ጊዜ
ነበር።
በራእይ 22:6 ላይ ኢየሱስ “የነቢያት መናፍስት ጌታ አምላክ” ተብሎ የተገለጸ
ሲሆን “ቃሎቹ የታመኑና እውነተኛ ናቸው።” የእግዚአብሔር አገልጋዮች
እግዚአብሔርን ወክለው ሲናገሩ ከእነርሱ የሚወጣው ማንኛውም ነገር “የታመነና
እውነተኛ” ይሆናል። ብዙ የሚታመን ነገር በሌለበት ዓለም የጌታ መላእክት
የተናገሩትን ማመን እንችላለን። በተለይም የመጨረሻና የበላይ ባለስልጣን በሆነው
በቃሉ ማመን እንችላለን።
ሴቶች ነቢያትና ወጣት ተባባሪ እረኞች (ፓስተሮች ፓስተሮች) የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፦ ሉቃ 2:36-38፣የሐዋ 21:9። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ሴት ነቢያት ምን ይነግሩናል?
በብሉይ ኪዳን ጊዜ እግዚአብሔር ወንዶችንም ሴቶችንም መልዕክተኞቹ አድርጎ
ጠርቷቸዋል። በአዲስ ኪዳን ጊዜም ቢሆን ሴቶች ነቢያት እንደነበሩ በቂ መረጃ አለ።
በአዲስ ኪዳን “ነቢይት” ተብላ ስትጠራ የመጀመሪያዋ ሀና ነበረች። በሙሉ ጊዜዋ
ለአገልግሎት የተሰለፈች ነበረች። “በፆምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች.....
እግዚአብሔርን አመሰገነች፣ ስለ እርሱም ትናገር ነበር”(ሉቃ 2:37፣38)።
የሐዋሪያት ሥራ 21:8-9 ፊሊጵስ “ትንቢት የሚናገሩ አራት ድንግል ሴቶች ልጆች
ነበሩት” ይላል። እንደ አሲቢዮስ ያሉ የአዲስ ኪዳን ታሪክ አጥኚዎች እነዚህ ሴቶች
የት እንደኖሩና እንደተቀበሩ የሚናገሩ ጽሑፎችን ኋላ አግኝተዋል። ያም ሆነ ይህ
እያየን ያለነው ሴቶች፣ ያውም ወጣት ሴቶች ነቢያት እንደነበሩ ነው። ምን ትንቢት
እንደተነበዩ ወይም ለምን ያህል ጊዜ እንዳገለገሉ በትክክል የምናውቀው ነገር የለም።
ነገር ግን ስለ እነዚህ ትንቢታዊ ስጦታ ስለነበራቸው ወጣት ሴቶች የምናውቀው ነገር
ቢኖር፣ ትንቢታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለመመዝገቡን ነው። እንደ ሌሎች
በርካታ ነቢያት ሁሉ እውነተኛ ነቢያት ሆነው ሳለ ቃሎቻቸውና ጽሑፎቻቸው
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተካተቱ ቀኖናዊ ያልሆኑ ነቢያት ናችው።
ከሴቶች ነቢያት ሌላ ወጣት አገልጋዮች ከሐዋርያት ጋር ተባብረው ይሰሩ ነበር።
ለምሳሌ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን በእምነት እውነተኛ ልጄ የሆነ ይለዋል (1ኛ ጢሞ
1:2፣1ኛ ጢሞ 4:12ንም ይመልከቱ)። ጳውሎስ የአገልጋይነትን መሰረታዊ ስራዎች
ለጢሞቴዎስ አስተማረው። ስለ መጠራቱ እንዲህ ይላል፦ “ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፣
አስቀድሞ ስለ አንተ እንደተነገረው ትንቢት፣ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ
ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለው” (1ኛ ጢሞ 1:18)።
በቲቶ 1:4 ላይ ጳውሎስ ቲቶን “በሃይማኖት ህብረት እውነተኛ ልጄ” ብሎ
ያስተዋውቀዋል። ጳውሎስ ቲቶን አስቸጋሪ ምእመናን በነበሩባት በቀርጤስ ቤተ
ክርስቲያን መሪዎችን እንዲሾም ኃላፊነት ሰጠው። ይህን ከባድ ኃላፊነት እንዴት
እንደሚወጣው መንፈሳዊ ምክር ለገሰው። ከዚያ እንዲህ ሲል ምክሩን ደመደም፦”ይህን
በሙሉ ስልጣን ተናገርና ምከር ገስጽም፣ ማንም አይናቅህ”(ቲቶ 2:15)።
ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ወንድ፣ ሴት፣ ሁላችንም በእግዚአብሔር ስራ
ልንሳተፍ እንችላለን። የእርስዎስ ሚና ምንድነው? እንዴት በበለጠ
ሊሳተፉ ይችላሉ?
ማቴዎስ 24:23ና 24ን ያንብቡ። እዚህ ላይ ኢየሱስ ስለ ምን እያስጠነቀቀን ነው? ይህን ማስጠንቀቂያ አጥብቀን መቀበል ያለብን ለምንድን ነው?
ኢየሱስ ራሱ ከዚህ በላይ ግልጽ ሊሆን አይችልም። “ሐሰተኞች ክርስቶሶችና
ሐሰተኞች ነቢያት ይነሳሉና ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ
ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” (ማቴ 24:24)። “ታላቅ ምልክትና ድንቅ” ማሳየት
ከቻሉ የሚያስጠነቅቀን ነገር አሳማኝ መሆን አለበት። ምንም ያህል አሳማኝ ቢሆኑም
ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ትይንቶች ሁሉ ከእግዚአብሔር የመጡ ናቸው ማለት
አይደለም። ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ጠላቶች አሉን። ጳውሎስ እንደሚያስጠነቅቀን
“መጋደላችን ከደምና ከስጋ ጋር አይደለምና፣ ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህም
ጨለማ ዓለም ገዥዎች ጋር በሰማያዊውም ስፍራ ካለ ከክፉ መንፈሳዊያን ሠራዊት ጋር
ነው እንጂ” (ኤፌ 6:12)። እነዚህ ኃይላትም በሐሰተኛ ነቢያት አማካኝነት ስራቸውን
ይሠራሉ።
እንደ እውነቱ ከሆነ ሀሰተኛ ነቢያት አዲስ ነገር አይደሉም። አዲስ ኪዳን ሀሰተኛ
ነቢያት በብሉይ ኪዳን ጊዜ እንደነበሩ ይጠቅሳል (ሉቃ 6:26)። በአዲስ ኪዳን ውስጥ
ሐሰተኛ ነቢያት “የበግ ለምድ ለብሰው በሚመጡ ተክሎዎች” ተመስለዋል (ማቴ
7:15)። እነርሱን “በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ” ተብለናል (ማቴ 7:16)።
ዋና ስራቸው ማታለል ነው (ማቴ 7:17-20)። ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ሲል አወጀ፦
“ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሳሉ” (ማቴ 24:11)። “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ
ያስታሉ”(ማቴ 24:24)። ማርቆስ 14:22ን እና 1ኛ ዮሐ 4:1ን ይመልከቱ።
እንደ ኤፌሶን 6:10-18 አባባል ከማንኛውም መታለል እራሳችንን
እንዴት ልንከላከል እንችላለን?
በእምነት መኖር፣ “ወገብን በእውነት መታጠቅ፣ የጽድቅንም ጥሩር መልበስ፣”
በጸሎት አማካይነት በመንፈስ ቅዱስ ተከቦ በቃሉ ጸንቶ ከመቆም በተጓዳኝ
“በእውነት” መታጠቅ--እነዚህ ነገሮች ከእውነት አስተምህሮና ከመንፈሳዊ መሰረታችን
እንዳንፈናቀል ልናደርጋቸው የሚገቡን ነገሮች ናቸው።
ምድራችንን ካጥለቀለቀው አታላይነት ራስዎን ለመጠበቅ (ለመከላከል)
ምን ማድረግ ይችላሉ?
አስቀድመን እንደተማርነው እግዚአብሔር ነቢያትን አስፈላጊ ለሆኑ ስራዎች
በሆነ ጊዜ ጠርቷቸዋል። ዋናው ስራቸው እግዚአብሔርን ከሰዎች ጋር ማስተዋወቅ
እና ከእርሱ ጋር ታማኝነት ያለው ግንኙነት እንዲኖራቸው ማድረግ ነው። የኤለን ጂ
ዋይትም ዋናው መመሪያዋ ይሄው ነበር። አገልግሎቷ ሁለት ዋና ስራ ነበረው። ሰዎችን
ወደ ኢየሱስ መምራትና ቃሉ ወደሆነው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ማመላከት ነበር።
ኤለን ጂ ዋይት ዘመኗን ሁሉ ለክርስቶስ የጋለ ፍቅር ነበራት። የእግዚአብሔርን
ፍቅር ለሰዎች ማካፈል ትወድ ነበር። አምስት ክፍል ያለው ታዋቂው “የዘመናት
ትግል/ግጭት” የተባለው መጽሀፏ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” በሚል ሐረግ ጀምሮ “
እግዚአብሔር ፍቅር ነው” በሚል ሐረግ ይደመድማል። ምናልባት ከመጽሃፎቿ ሁሉ
በበለጠ ተወዳጅ በሆነው “ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ” በተባለው መጽሃፏ
እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “በጸጋ ማደጋችን፣ ደስታችንና ጠቃሚነታችን--ሁሉም
ከክርስቶስ ጋር ባለን ህብረት ላይ ይደገፋል። በጸጋ የምናድገው ከእርሱ ጋር በየሰአቱና
በየቀኑ በምናደርገው ግንኙነት ነው። የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ እርሱ ነው።” ወደ
ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ ገፅ 69።
በ1890ዎቹ “የዘመናት ምኞትን” እየጻፈች ሳለ በማስታወሻዋ እንዲህ ሰትል
ጽፋለች፦ “ስለ ክርስቶስ ሕይወት ሲጽፍ እጅግ በጣም ተመስጬ ነበር። መተንፈስ
እንደሚገባኝ መተንፈስ ረሳሁ። ክርስቶስ በምድራችን ሳለ የደረሰበትን ስቃይ ሳሰብ
የተሰማኝን ኃይለኛ ስሜት መቋቋም አቃተኝ።” —Manuscript 70, 1897. ኤለን ጂ
ዋይት ስለ ኢየሱስ መናገር ትወድ ነበር።
የኤለን ጂ ዋይት አገልግሎት ሁለተኛው ትኩረቷ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር። የራሷን
ጽሑፍ “ወደ ትልቁ ብርሃን”--ወደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚመራ “ትንሽ ብርሃን” ነው
ብላ ትጠራ ነበር (Selected Messages, book 3, p. 29)። እግዚአብሔር የፍቅር
ባህርዩንና የድነት ዕቅዱን ወደገለጸበት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሄዱ ሰዎችን ሁልጊዜ
ታደፋፍር ነበር። አስቀድማ በአገልግሎቷ እንዲህ በማለት አስቀምጣለች፦”ውድ
አንባቢ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ እምነትህና ልምምድህ ደንብ እንድታደርግ
ሀሳብ እሰጥሃለሁ።” --Selected Messages, book 3, p. 30.
ከብዙ ዓመታት በኋላ እንዲህ ስትል ጻፈች፦”እግዚአብሔር መጽሃፍ ቅዱሳችሁን
እንድታጠኑ ይፈልጋል። ቃሉን ሊተካ የሚችል ሌላ ብርሃን የለም። ቃሉ ሲበላና
ሲታኘክ የነፍስ የህይወት ደም ነው። ያኔ ጨለማን እንደሚያበራ ብርሃን መልካም
ስራ ይታያል።” —Letter 130, 1901።
የነቢይነት ስጦታን ተቀብለናል የሚሉ ሁሉ “ክርስቶስ ያስተማረውን ማስተማር
አለባቸው። እርሱ በአካል ተገኝቶ የተናገረውን ብቻ ሳይሆን በነቢያትና በብሉይ ኪዳን
አስተማሪዎች በኩል የተናገረውንም ማስተማር አለባቸው። ሰብአዊ አስተምህሮ
ተቀባይነት የለውም” በማለት ኤለን ዋይት ጻፈች።(የዘመናት ምኞት ገጽ 826)።
ኤለን ጂ ዋይት ኢየሱስንና የእግዚአብሔርን ቃል የክርስትና ልምምድዋ ማዕከል
አደረገች። በሚመጣው ዓርብ ስለ ራእይና ስለ መንፈስ ቅዱስ መሪነት ያላትን ሀሳብ
እንመለከታለን።