የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡ። ኢዮኤል 2፡27-32፣ የሐዋ 2፡1-21፣ ኤፌ 4፡11-14፣ ራዕይ 12፡17፣ ራዕይ 19፡10፣ የሐዋ 2፡36-42።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡”ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ
ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት
ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም
ራእይ ያያሉ፤ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ
መንፈሴን አፈስሳለሁ” (ኢዮኤል 2፡28፣ 29)።
በሆነ የመንግስት ሕግ “የፀሐይ ግባት ደንብ” የሚል ሐረግ አለ። ይህ የህግ
ስያሜ ከፀሐይ መግባት ጋር ግንኙነት የለውም። የአንድ ሕግ ህጋዊነት
የሚያበቃበትን ጊዜ የሚወስን ህጋዊ አባባል ነው። መንግታት የዚህ አይነት
ሐረግ የሚያስቀምጡባቸው የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖራቸው ይችላል። ለምሳሌ አገር
አቀፋዊ ችግሮች ሲፈጠሩ የዜጎችን መብት ለማቀብ ሊሆን ይችላል። በአንዳንድ
አጋጣሚዎች እነዚህን ህጎች የዜጎችን መብት ለመመለስ ይጠቀሙባቸዋል።
በጥንት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለህዝቡ የትንቢትን ስጦታ ሲሰጥ እግዚአብሔር
“የፀሐይ ግባት” ሕግ አስቀምጦ ነበር? ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት ስጦታ መስራቱን
የሚያቆምበት ጊዜ ይኖራል? ባለፈው ሳምንት እግዚአብሔር በወሰኝ ጊዜያት በነቢያት
አማካይነት ለሕዝቡ እንደተናገረ ተምረናል። በዚህ ሳምንት ደግሞ የትንቢት ስጦታ
በመጨረሻ ጊዜ የሚጫወተውን ሚና እናያለን። የኢየሱስ ዳግም ምፃት እየቀረብ
ሲሄድ የትንቢት ስጦታ ስለሚኖረው ሚናም እንመረምራለን።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለታኅሳስ 10 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
ኢዮኤል 2፡28-32ን ያንብቡ። እግዚአብሔር በመጨረሻዎች ቀናት ምን ለማድረግ ተስፋ ሰጠ?
ከክርስቶስ ልደት በፊት በሰባተኛው ምዕተ-አመት (BC) የኖረው ኢዮኤል ወደ
ፊት ስለሚሆኑት ክስተቶች ወሳኝ እይታ ይሰጣል። ይህን ስናነብ እራሱ ስለኖርበት
ጊዜ ነው ወይስ ወደፊት ስለሚመጣው የሩቅ ጊዜ ነው ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን።
የስነ መለኮት ምሁራን ሁለት አይነት ትንቢቶች አሉ ይላሉ--መደበኛና ምሳሌያዊ።
መደበኛ ትንቢት የእውነት ሕዝቦች ይናገራል፣ የእውነት ቁጥሮችንና ስሞችንም
ይጠቀማል (ለምሳሌ ኤርምያስ 25፡1-11ን ያንብቡ።) በአንጻሩ ደግሞ ምሳሌያዊ
ትንቢት በከፍተኛ ደረጃ ምሳሌያዊ ቋንቋን ይጠቀማል፣ ዘመናትን ለማመልከት
ምሳሌያዊ ቁጥሮችን ይጠቀማል፣ አብዛኛውን ጊዜ ዓለም አቀፋዊ ምልክቶችንም
ይጠቅሳል። ሰማያዊ አካላትንም ይጠቅሳል (ዳንኤል 7ን ይመልከቱ)። አንዳንዴ
ሁለቱ ሲጠምሩ እናያለን (ለምሳሌ ማቴ 24ን ይመልከቱ)።
ኢዮኤል 2፡28-31ስ? ይህ ምንባብ የምሳሌያዊ ትንቢት ክፍል ይመስላል።
የትንቢቱ ፍጻሜ በነብዩ እድሜ ወይም ከእርሱ በኋላ በቅርቡ የሚደርስ አይመስልም።
በተቃራኒው ፍጻሜውን ለወደፊቱ መጠባበቅ አለብን። አውዱንና የጊዜውን ክልል
ልብ ይበሉ። “ታላቁና የሚያስፈራው ቀን ሳይመጣ”(ኢዮ 2፡31)። ይህ የትኛው ቀን
ነው? የኢየሱስ የመጀመሪያው ወይስ ሁለተኛው ምፃት? ወይስ ሁለቱም?
በኢዩኤል ትንቢት በፀሐይና በጨረቃ ስለሚሆኑ ምልክቶች ተወስተው ስናይ
በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ተወስተው እናገኛለን። በታወቀው የመጨረሻ
ጊዜ ንግግሩ (ማቴ 24፡29) ደቀ መዛሙርቱን ሲያነጋግር ስለ ፀሐይ፣ ጨረቃና
ከዋክብት ምልክቶች ተናግሯል። ባለ ራዕዩ ዮሐንስም ስለነዚሁ ምልክቶች ይናገራል
(ራዕይ 6፡12,13)። ኢየሱስም ሆነ ዮሐንስ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በፊት ስለሚሆኑት
ምልክቶች ይናገራሉ።
ስለዚህ ተመሳሳይ ወደሆኑ ምልክቶች የሚያመለክተው የኢዮኤል ትንቢት
በመጨረሻ ዘመን ላይ የሆን ተፅዕኖ አለው ማለት እንችላለን። “በላይ በሰማይ
ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ። ታላቁና
የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም
ይለወጣል” (ኢዮኤል 2፡30-31)
በትንቢቱ መሰረት ስለተፈጸሙት ክስተቶች ያስቡ። ያለፉት መፈጸማቸው
እንደ ኢየሱስ ዳግም ምጽዓት ያሉ ለወደፊት የተነገሩትና ገና ያልተፈጸሙት
እንደሚፈፀሙ ምን ያህል መተማመኛ ይሰጠናል?
የሐዋ 2፡1-21ን ያንብቡ። የክርስቶስን የመጀመርያ መምጣት አስመልክቶ ሲናገር ጴጥሮስ ለምን ኢዮኤልን ጠቀሰ? በዚህ ንባብ ትንቢት ምን ሚና ይጫወታል?
በእነዚህ የአዲስ ኪዳን ጥቅሶች ውስጥ ከብሉይ ኪዳን ከተጠቀሱት ረዥም
ጥቅሶች መካከል አንዱን እናገኛለን። ጴጥሮስ ያቀረባቸውን መከራከሪያዎች ስናነብ
“ጴጥሮስ ሆይ፣ ስለ ምልክቶቹስ? ስለ እርሱ አልተናገርህም” ልንለው እንችላለን።
ምናልባት ጴጥሮስ “ምልክቶቹ ተፈጽመዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት ኢየሱስ በመስቀል
ላይ ሲሰቀል ፀሐይ ለሦስት ሰዓት ጨልማ ነበር” ሊል ይችላል (ማር 15፡33)።
ለጴጥሮስ አሳማኝ መከራከሪያ የነበረው ነገር ምናልባት ዛሬ መረጃነቱ ላያሳምን
ይችላል። የኢዮኤልን ትንቢት የተሟላ ፍጻሜ እንጠባበቃለን። ለመፍትሄው ዋናው
ቁልፍ ነገር የኢዮኤል ጥቅስ እራሱ ነው። በኢዮኤል 2፡23 ላይ የፊተኛውና የኋለኛው
ዝናብ ይላል። የሐዋርያት ሥራ 2 የመጀመሪያው ዝናብ መውረድ ነው። የመጨረሻው
የትንቢቱ ፍጻሜ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በፊት የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ነው።
ሰዎች ብዙ ጊዜ ትንቢትን ለወደፊት የሚሆነውን መናገር (መተንበይ) ነው
ይላሉ። ይህ ስህተት አይደለም፣ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት ሰዎችን ወደ
ንሰሃም ጠርተዋል። ጴጥሮስ ሲናገር እኮ በሕዝብ መካከል ከነበሩት አንዳንዶች
አምነው ነበር።
“ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ፥ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት፦
ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉአቸው” (ሐዋርያት 2፡37)።
ታዲያ የጴጥሮስ መልስ ምን ነበር? “ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም
ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም
ስጦታ ትቀበላላችሁ። የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ
እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው” (ሐዋርያት 2፡38,39)።
መጥምቁ ዮሐንስም እንደ ነቢይ ሰዎችን ወደ ንስሃ ጠርቷል። የኢየሱስን
የመጀመሪያ መምጣት ከማወጁም በላይ “መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ
ግቡ”(ማቴ 3፡2) እያለ ከሀጥያታቸው ንስሃ እንዲገቡ ሰበከ።
ስለዚህ የኢዮኤል 2 የመጨረሻ ፍጻሜው ወደፊት ነው (ገና ነው)። ኢዮኤልና
ጴጥሮስ እንዳደረጉት ሁሉ የመጨረሻ ቀን ነቢያትም ህዝብን ወደ ንስሀ ይጠራሉ፣
ወደ ኢየሱስ ያመለክቱአቸዋል፣ የመጨረሻው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ምሪት
ይሰጣሉ።
እነዚህን ከሰው ኃይል ውጪ የሆኑ ነገሮች ሲመለከቱ ሰዎቹ የሆነ
ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው ብለው አሰቡ። ሰዎች የሰከሩ መሰላቸው
(ሰካራሞች በድንገት የሌሎች አገሮችን ቋንቋዎችን እየተናገሩ ነው ማለት
ነው?) መልሳቸው ምንም ያህል ከእውነት የራቀ ቢሆንም አንዳንድ ሰዎች
ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑትን ክስተቶች ተፈጥሯዊ ለማስመሰል የሚሞክሩት
ለምን ይሆን?
የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በሚገባ እንድትሰራና አገልግሎቷን በትክክል
እንድታበረክት እግዚአብሔር የተለያዩ ስጦታዎችን ሰጥቷታል። በአዲስ ኪዳን
በርካታ የመንፈሳዊ ስጦታዎች ዝርዝሮች እናገኛለን።

ኤፌሶን 4፡11-14ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ እነዚህን
ስጦታዎችን ለምን ሰጠ? የትንቢት ስጦታ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ
ያለውን ዕቅድ በተግባር ለመዋል እንዴት ይረዳል?
የመንፈሳዊ ስጦታዎች ሁሉ ዓላማቸው ቤተ ክርስቲያንን ለመግንባትና ወንጌልን
ለማወጅ ነው። ጳውሎስ በአራቱም ዘገባዎች ውስጥ የትንቢት ስጦታን አካትቷል
(ምናልባት “ነቢያት” የሚለውን ቃል በተዘዋዋሪ መጥቀሱ ሊሆን ይሆናል)። ሌሎች
ስጦታዎች የተጠቀሱት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ስለዚህ የትንቢት ስጦታ እጅግ አስፈላጊ
ከሆኑ ስጦታዎች አንዱ ነው ብለን መደምደም እንችላለን። ተደጋግሞ ሲወሳ ስናይ
ምን አልባት ወሳኝ ከሆኑት የመንፈስ ስጦታዎች አንዱ ነው ለማለት እንደፋፈራለን።
ስለ ነቢያት አንዳንድ አጠቃላይ የሆኑ ባህሪያትን እስቲ እንመልከት።
1.
ነቢያት በእግዚአብሔር የተጠሩ ናቸው (1ኛ ነገስት 19፡16፣19-21ን እና ኢሳያስ
6ን ይመልከቱ)። አብዛኛውን ጊዜ የተገቡ/ብቁ እንዳልሆኑ እየተሰማቸው
ሀላፊነቱን ለመቀበል ያመነታሉ፣ ነገር ግን ይታዘዛሉ።
2. እግዚአብሔር በህልም፣ በራእይና በድምጽ ይናገራቸዋል። አንዳንዴ የወደፊቱን
ክስተቶች ይገልጥላቸዋል። በሌላ ጊዜ ደግሞ የመንግስታትን ወይም የህዝብን
ወቅታዊ ሁኔታ ያሳያቸዋል (ዳንኤል 2ን ይመልከቱ)።
3. ቅዱሳት መጻሕፍት አካላዊ ሁኔታዎችን ይገልጣሉ፦ ነቢያቱ አካላቸው
ብርታታቸውን ሊያጡ ወይም መተንፈስ ሊያቆሙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ደግሞ
በአዲስ ኃይል ሊሞሉ ይችላሉ (ዳን 10፡8-10፣ 18,19)።
4. ነቢያት መልዕክቶቻቸውን በተለያየ ዘዴ ያስተላልፋሉ-- በቃል (የሐዋ 21፡10-
12)፣ በትይንት (ሕዝ 4)፣ ወይም በደብዳቤዎች (ራዕይ 2 እና 3)። አንዳንድ
ነቢያት የፀሐፊዎችን እርዳታ ተጠቅመዋል (ኤርምያስ 36:1-4ን ይመልከቱ)።
5. የአንድ ነቢይ መልእክት ካለፉት ነቢያት ጋር መስማማት አለበት። ምክንያቱም
እግዚአብሔር ራሱን አይቃረንም (አይቃወምም) (ኢሳ 8፡20)።
6. የነብዩ መልዕክት ይዘትና የነቢዩ የግል ሕይወት ተጽእኖ መነሻው መለኮታዊ
መሆኑን ይመሰክራል (ማቴ 7፡15-20)።
7. ሰይጣን ምንጊዜም መለኮታዊ የሆነውን ነገር፣ ትንቢታዊ ስጦታ ሳይቀር፣
መኮረጅ (ማስመሰል) ይሞክራል። በመጨረሻው ዘመን ሐሰተኛ ነቢያት
ይነሳሉ (ማቴ 24፡24, 2ኛ ጴጥ 2፡1)።
ራዕይ 12 ከሰማይ ሲጸነስ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ዘመን ያለውን የታላቁን ተጋድሎ ታሪክ በሰፊው ዘግቦታል። ራዕይ 12፡17ን ያንብቡ። “የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር” ምንድር ነው? ራዕይ 19፡10ን ከራዕይ 22፡8ና9 ጋር ያስተያዩ።
ራዕይ 12፡17 ላይ በመጨረሻ ዘመን የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ሁለት የመለያ
ባህሪያት ተወስተዋል። ቤተ ክርስቲያኗ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ትጠብቃለች።
“የኢየሱስም ምስክር” አላት። ይህ ምስክር ምንድነው?
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “የኢየሱስ ምስክር” ማለት እኛ እንደ
አማኞች ኢየሱስን መቀበልና በተልዕኮኦቻችንና በስብከታችን እርሱን ለሌሎች
ማስተዋወቅ ነው ይላሉ (ራዕይ 19፡10ን ይመልከቱ)። ሌላ ትርጉሞች ደግሞ ለየት
ያለ ትርጉም ይሰጡታል። ኢየሱስ ራሱ ለቤተ ክርስቲያኑ ይመሰክራል ይላሉ (ራዕይ
19፡10ን ይመልከቱ፦ “ኢየሱስ የገለጠው እውነት”--ምስክርነቱን የሚያስተላልፈው
ኢየሱስ ነው)። እንደ እውነቱ ከሆነ የግሪኩ ግልባጭ በሁለቱም በኩል የሚያስኬድ
ይመስላል። ታዲያ ዮሐንስ ምን ማለቱ ነው?
ሁለቱን የመለያ ምልክቶች ስናስተያይ ተመሳሳይነታቸውን በግልጽ ማየት
እንችላለን (በግሪኩ ግልባጭ ከመጽሐፍ ቅዱስ በበለጠ ግልፅ ሆኖ ይታያል)።
“የእግዚአብሔር ትእዛዝ” ምንጩ እግዚአብሔር መሆኑ ግልጽ ነው። “የኢየሱስ
ምስክር” ደግሞ ምንጩ ኢየሱስ ነው። ስለዚህ የሚመሰክረው ኢየሱስ ነው።
እውነተኛዋን ቤተ ክርስቲያን ለይቶ ያውቃል። የሚለያት እንዴት ነው? በትንቢት
ስጦታ አማካኝነት። መልሶቹ በራዕይ 19፡10ና በራዕይ 22፡9 ላይ ይገኛሉ። “የኢየሱስ
ምስክር” ከትንቢት መንፈስ ጋር ይስማማል። ዮሐንስ ራሱ ነቢይ ስለሆነ “የየሱስን
ምስክር” ይወክላል። ነቢይ ሕዝቡን ንስሃ እንዲገቡ የሚጎሰጎስ፣ የሚያደፋፍር ወይም
የወደፊቱን የሚተነቢይ የተለየ መልዕክት የያዘ በእግዚአብሔር የተመረጠ ሰው ነው።
ራዕይ 12፡17 ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያኑን እንድትታወቅ የሚያደርጋት በትንቢት
ስጦታ አማካኝነት መሆኑን ይነግረናል። ይህ ማለት በብሉይ ኪዳን ጊዜ እግዚአብሔር
ነቢያትን እንደላከ እና ለቀደመችው ቤተ ክርስቲያንም ዮሐንስን እንደላከ ሁሉ በምድር
የመጨረሻ ዘመንም ነቢያትን ያስነሳል ማለት ነው።
የኤለን ጂ ዋይት አገልግሎት “የትንቢት መንፈስ” መስራት ምሳሌ
መሆኑን የሚያሳይ ምን መረጃ አለዎት (ራዕይ 19:10)?
ዛሬ አብዛኞቹ የእምነት ሰዎች ለጥንቶቹ ይመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት እውቅናን ሊሰጡ ይችላሉ። ነገር ግን በዘመናችን ነቢያት እንደሚነሱ ያምኑ ይሆን? በኢዮኤል 2፡28-31 ላይ የተሰጠው በፍጻሜ ዘመን እንደሚሆን የተነገረው አስገራሚ የትንቢት ተስፋ ከታመነበት ምን ይመስል ይሆን? የሐዋርያት ሥራ 2፡36-42ን ያንብቡ። በጴንጤቆስጤ ጊዜ ጴጥሮስ የሰበከው ስብከት ዋና መልዕክት ምን ነበር? የጉባኤው/የእድማጮቹ መልስ ምን ነበር?
በ31 ዓም በጴንጤቆስጤ ቀን የመንፈስ ቅዱስ መውረድ በመጨረሻ ዘመን የመንፈስ
ቅዱስ ሲወርድ ሊሆን የሚችለውን ቁልጭ አድርጎ በግልጽ የሚያሳይ ምስል ሲሆን
ክስተቱ ከዚያ በላቀ ሁኔታ ይፈጸማል። ጴንጤቆስጤ የሚታወቀው ኢየሱስን ከፍ
ከፍ በማድረ፣ ንስሐ በመግባትና የእግዚአብሔርን መልዕክት ለማዳረስ ፈቃደኛ የሆኑ
እና የታጠቁ ሰዎችን በማፍራት ነው። በክርስቶስ ላይ ያተኮረው የጴጥሮስ መልዕክት
ምንጩ የመንፈስ ቅዱስ ሃይል ነበር። ታዲያ ሶስት ሺህ ሰዎች ንስሀ እንዲገቡና
እንዲጠመቁ አደረገ። ይህ “የፊተኛው ዝናብ” በረከት የተባረከ ዘር ተከለ። የተባበረችው
ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ፍቅር ከመስበኳም በላይ ዳግም ምጽአቱን አበሰረች።
“የፊተኛው ዝናብ ዘሩን ለማብቀል ወረደ። የኋለኛው ዝናብ ደግሞ መከሩ
እንዲያፈራ (እንዲደርስ) ለማድረግ ይወርዳል” (ኤለን ጂ ዋይት ታላቁ ተጋድሎ
ገጽ 611)። በሌላ አነጋገር ዘመናዊ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ በጴንጤቆስጤ ጊዜ
የተገለጠውን የፊተኛውን ዝናብ ይመስላል።
በኢዮኤል 2፡28-31 እንደተመለከትነው በመጨረሻ ዘመን የሚመጣው
ትንቢታዊ ስጦታ ለሽማግሌዎች እና ለወጣቶች፣ ለወንዶችና ለሴቶች ክፍት ይሆናል።
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሚመርጣቸው አማካኝነት ይናገራል። መንፈስ ቅዱስ
የዘመኑ መጨረሻ መልዕክተኛን ሲመርጥ መልእክቱ ወይም መልዕክቷ ኢየሱስን
ከፍ ከፍ ያደርጋል። ሰዎችን ወደ ንሰሃ ይመራል። ሰዎች የእግዚአብሔርን ተልዕኮ
እንዲፈጽሙ ያደርጋል። እነዚህ ሶስት ቁም ነገሮች የኤለን ጂ ዋይት ትንቢታዊ
አገልግሎት ዋና አቋም ናቸው። እድሜ ልኳን በንግግሯና በፅሁፎቿ ኢየሱስንና
ቃሉን ከፍ ከፍ አድርጋለች። 7ኛ ቀን አድቬንቲስቶችንና ሌሎችንም ንስሃ እንዲገቡ
አስተምራለች (ሰብካለች)። ሁሉም የጠፉትን ለማዳን የእግዚአብሔርን ተልዕኮ
እንዲያደርሱ አደፋፍራለች።
በኤለን ጂ ዋይት አገልግሎት አማካኝነት የተቀበሉትን ግሩም ስጦታ ምን
ያህል ተጠቅመውበታል?
በኤፌሶን 4 ላይ የመንፈሳዊ ስጦታዎች ዋና አላማ አማኞች የእግዚአብሔርን
ተልዕኮ እንዲያደርሱ መሆኑን ጳውሎስ ይናገራል። የኤለን ጂ ዋይት ትንቢታዊ
አገልግሎት ይህንኑ መልዕክት ያስተጋባል። መልእክቷ አማኞች ከእግዚአብሔር
ጋር ጥልቅ ግንኙነት እንዲኖራቸው እና የተቀበሉትን ፍቅር ለሌሎች እንዲያካፍሉ
ረድቷቸዋል።
ክርስቲያን እንደሆኑ ስለሚናገሩ ሰዎች እንዲህ ብላ ጽፋለች፦ “ክርስቲያን ነን
ከሚሉ ሰዎች ሁሉ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ክርስቶስን በዓለም ፊት ከፍ ከፍ
በማድረግ ረገድ ግንባር ቀደም መሆን አለባቸው። የሦስተኛውን መልአክ መልዕክት
ማወጅ የሰንበትን እውነታ እንድናውጅ ይጠይቃል። ይህ እውነት ከሌሎች እውነቶች
ጋር ተጨምሮ ይታወጃል። ነገር ግን ዋናው የትኩረታችን ማዕከል የሆነው ኢየሱስ
ክርስቶስ መተው የለበትም። ምህረትና እውነት የሚገናኙት አና ጽድቅና ሰላም
የሚሳሳሙት በክርስቶስ መስቀል ላይ ነው። ኃጢአተኛው ቀራኒዮን እንዲመለከት
መመራት አለበት። በህጻን እምነት የጌታን ምህረት ሊቀበል ይገባዋል። ጽድቁን
ተቀብሎ በምህረቱ ማመን ይገባዋል።” Gospel workers page 156,157
በተጨማሪም እያንዳንዱ አማኝ የተልዕኮው ተሳታፊ እንዲሆን ተጠርቷል
ትላለች። “የቤተ ክርስቲያናችን አባላት በበለጠ ጥረት እንዲያደርጉ እግዚአብሔር
ይፈልጋል” ትላለች። (Evangelism page 113)
“በእግዚአብሔር ስራ ቦዘኔዎች ሊኖሩ አይገባም። የተለያዩ ሰዎች የሰዎች
አጥማጆች ሆነው ይሰለፉ። ሰዎችን ከጠፋው ዓለም እያወጡ አዳኝ ወደ ሆነው ፍጹም
የክርስቶስ ፍቅር ያስገቡ” (evangelism page 115)። ኤለን ጂ ዋይት ራስዋ በ1880ዎቹ
በአውሮፓ፣ በ1890ዎቹ ደግሞ በአውስትራሊያ ሚስዮናዊ ሆና አገልግላለች።
ሰይጣንን በመጨረሻው ዘመን በሚኖሩ የእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ በጣም
የሚቆጣው በግላቸው ለእግዚአብሔር ራሳቸውን ቀድሰው እንዲሰጡና ለተልዕኮ
ሲጠሩ ነው (ራዕይ 12፡7)። እነዚህ የመጨረሻው ዘመን መልዕክት፣ ትንቢታዊ ምሪትና
መረዳት ያላቸው የኢየሱስ ተከታዮች ናቸው። “እግዚአብሔር በአከባቢያችንና
በዙሪያችን ያሉ አደጋዎችን በመግለጥ እንዲህ ብሏል፦ ´በትንቢት መንፈስ ውክልና
አማካይነት ዓለምን ምርኮኛ የሚያደርጉ ማታለያዎችን በመግለጥ ለሕዝቡ እንዲህ
በማለት ተናግሯል፥- ለህዝቡም “ወደ ቀኝ ወደ ግራም አትበል መንገዱ ይህች ናት
በእርስዋም ሂድ” (ኢሳ 30፡2)። ታላቁ ተጋድሎ የሰይጣንን አታላይነት በግልጥ
ያሳያል።” Ellen G Whites manuscript 31,1890።
ሰዎች ህይወታቸውን ለኢየሱስ ሲሰጥ ሰይጣን ይበሳጫል። የእግዚአብሔርን
ትንቢታዊ ድምጽ ለማስተባበል የማያደርገው ነገር የለም። የኤለን ጂ ዋይትን
ትንቢታዊ ስጦታ ለማስተባበል ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ “ጥቅመ ቢስ” ነው
በማለት ነው። የጻፈችው ባለፈው ዘመን ስለሆነ መልዕክቷ ለዘመናችን አይጠቅምም
የሚሉ ሰዎችን ያስነሳል። ሌላው የሚጠቀምበት ዘዴ ደግሞ ነቢይነቷን በማጠራጠርና
ሐሰተኛ ነቢይ ናት በማለት ነው። ዋናው መሳርያ ግን ያሁኑ ትውልድ ጽሑፎቿን
እንዳያነቡ ማድረግ ነው።