የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተለውን ጥቅስ ያንብቡ፡- ቆላ. 1:21-27።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው”
(2 ቆሮ. 5፡21)፡፡
ባለፈው ሳምንት እንዳየነው፣ ጳውሎስ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚቀበለን
ተናግሯል (ቆላ. 1:20)። ኢየሱስ ለኛ በሠራው ሥራ ምክንያት እግዚአብሔር
ይቀበለናል (በ8ኛ ትምህርት ላይ ያለውን የሐሙሱን ጥናት ያንብቡ)። በዚህ
ሳምንት ጳውሎስ ስለዚህ ጉዳይ በተጨማሪ ምን እንደሚል ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው
ደብዳቤ ላይ እናጠናለን።
ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞቱ እግዚአብሔር እኛን እንደገና እንዲቀበለን
አድርጎታል። ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይለየናል። አሁን ግን በልጁ ስናምን በኢየሱስ
ምክንያት እግዚአብሔር ይቀበለናል።
የዚህ ሳምንት መሪ ጥቅስ 2 ቆሮ. 5፡21 ነው። ይህ ጥቅስ ደግሞ ኢየሱስ ስለ
ኃጢአታችን በመሞቱ ምክንያት እግዚአብሔር እንደሚቀበለን የሚናገረውን የመጽሐፍ
ቅዱስን እውነት ያስተምረናል። መስቀሉ የእግዚአብሔርን ፍቅር በድንቅ ሁኔታ የሚገልጽ
ቃል ነው። ሰዎች መልካሙን የምሥራች ሰምተው ኢየሱስን ሲቀበሉ፣ የእግዚአብሔር
ፍቅር ሕይወታቸውን እንደሚለውጥ መስቀሉ ያሳየናል። ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት
ተስፋን ይሰጠናል። በተጨማሪም ጳውሎስ “ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ
ስለ ነበረ ምሥጢር” ይናገራል (ቆላ. 1፡26)። ይህ ምስጢር ምንድን ነው? ይህ ምስጢር
ምን ተጨማሪ ነገርን ያካትታል? ይህ “ምስጢር” ስለ ኢየሱስ ከሚናገረው ከመልካሙ
የምሥራች ጋር የሚገናኘው እንዴት ነው? በዚህ ሳምንት የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ
ለማግኘት እናጠናለን።
*የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።
ቆላ. 1:21, 22ን ያንብቡ። ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ምን እያለ ነው? ከእግዚአብሔር ተለይተን የእርሱ ጠላቶች የነበርን ስለ መሆናችን ሲናገር ምን ማለቱ ነው? የኢየሱስ ሞት ይህንን ሁኔታ ሁሉ የሚለውጠው እንዴት ነው? በተጨማሪም ኤፌ. 5:27ን ያንብቡ።
ጳውሎስ ይኖር የነበረው እና መልዕክቱን የጻፈው ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት
ነው። በልባቸው ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር ከሌለ በስተቀር፣ ሰዎች ክፉ እንደሆኑ
ተረድቷል። ከሁለት ሺህ ዓመታት በኋላ ከጳውሎስ ጋር ማን ሊከራከር ይችላል? አንድ
ሰው ሰዎች ኃጢአተኞች ናቸው የሚለውን የክርስቲያን አስተምህሮ ለመቀበል እምነት
አያስፈልገንም ብሏል። የምሽት ዜናዎችን መመልከት በቂ ነው፣ አይደለም እንዴ?
ምንም እንኳን ክፉ ብንሆን፣ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ፍጹም እቅድ አዘጋጀ።
ነገር ግን የኃጢአትን ችግር ለመፍታት ብቸኛው መንገድ የኢየሱስ መሞት ነበር።
በኤደን ኃጢአት ከሠሩ በኋላ፣ እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ሊፈልጋቸው
ሄደ። አዳምና ሔዋንም ከበደሉ በኋላ ከእግዚአብሔር ተሸሸጉ። አምላክም አዳምን
ጠርቶ “ወዴት ነህ?” አለው (ዘፍ. 3፡9)። ዛሬም እግዚአብሔር እኛን መፈለጉን ቀጥሏል።
እኛ እንደ ጠፉ በጎች ነን። እግዚአብሔር እያንዳንዱን የጠፋውን በግ አንድ በአንድ
ይፈልጋል። በዘፍ. 3፡15 ላይ የእግዚአብሔርን የማዳን እቅድ እናያለን። ይህ ጥቅስ ስለ
ኢየሱስ የተነገረው የወንጌል ተስፋ ነው።
ስለ ኢየሱስ የሚናገረው መልካሙ የምሥራች ሦስት ክፍሎች አሉት። እነዚህ
ሦስት ክፍሎች ለመረዳት ቀላል ናቸው፡-
ክፍል 1፡- እኛ ረዳተ ቢስ ኃጢአተኞች ነን። ኃጢአተኞች በመሆናችን ምክንያት ራሳችንን
ማዳን አንችልም። ስለዚህ ለኛ ኃጢአት ይሞት ዘንድ ኢየሱስ መጣ (ሮሜ 5:6–8ን ያንብቡ)።
ክፍል 2፡- ኢየሱስ የሞተው ለኃጢአታችን መሆኑን መቀበል አለብን። ከዚያም
ኃጢአታችንን ተናዝዘን መጠመቅ አለብን። እነዚህን ነገሮች ስናደርግ፣ ኢየሱስ ይቅር
ይለናል። ከበደለኝነት ስሜትም ነፃ ያደርገናል (ሮሜ 5:9–11ን እና ሮሜ 6:6, 7ን ያንብቡ)።
ክፍል 3፡- ኢየሱስ ካዳነን በኋላ የምንኖረው ሕይወት ከእርሱ ኃይል የተነሣ ነው።
ሕይወታችንን ለእርሱ እናስረክባለን። እርሱም ይለውጠንና አዲስ ልብ ይሰጠናል።
ከዚያም እርሱ በእኛ ውስጥ ይኖራል (2 ቆሮ. 5:17–21ን እና ገላ. 2: 20ን ያንብቡ) ።
እነዚህ ሦስት ክፍሎች በአንድ ጊዜ ወይም በተለያየ ጊዜ ሊፈጸሙ ይችላሉ።
የእያንዳንዱ ሰው ልምምድ የተለያየ ሊሆን ይችላል። ሆኖም የሚያመሳስለን አንድ ነገር አለ -
ሁላችንም ኢየሱስን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለብን። በየማለዳው ህይወታችንን ለኢየሱስ
ስናስረክብ፣ እነዚህን ሶስቱን ክፍሎች እንደገና መለማመድ እንችላለን። ማስታወስ ያለብን
እጅግ አስፈላጊው ነገር መዳናችንን ነው ምክንያቱም ኢየሱስ ለኃጢአታችን ሞቷልና።
ቆላ. 1:23ን ያንብቡ። ጳውሎስ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ለቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን ምን የሚያበረታቱ ቃላትን ጻፈላቸው? እነዚህ ቃላት የጳውሎስን መልዕክት ለሚያነቡ ሰዎች ተስፋ የሚሰጡት እንዴት ነው? በተጨማሪም ቆላ. 2:5ን እና ኤፌ. 3:17ን ያንብቡ።
ጳውሎስ የቆላስይስ ክርስቲያኖችን በእምነታቸው እንዲጸኑ ያበረታታቸዋል።
ጳውሎስ የእምነታቸውን ማረጋገጫ አስቀድሞ ተመልክቷል። በእምነታቸውም ጠንካራ
እና ታማኝ እንደሆኑ ያውቃል (ቆላ. 2፡5)። ደግሞም ተስፋቸው የተመሰረተው በጽናት
በማመናቸው ላይ ነበር። እምነታቸው መጠንከርና ማደግ ነበረበት። በቆላ. 1፡23 ላይ
“መጽናት” የሚለው ቃል ተስፋ አለመቁረጥ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ
ባለመሆን ሰባተኛውን ትእዛዝ የተላለፈችውን ሴት ወደ ኢየሱስ ስላመጧት የአይሁድ
መንፈሳዊ መሪዎች ለመናገር ይህንኑ ቃል ይጠቀማል። የአይሁድ መሪዎች በዚህች
ሴት ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ኢየሱስን መጠየቃቸውን ቀጠሉ (ዮሐ. 8፡7)።
በተጨማሪም ጴጥሮስ ከእስር ቤት ካመለጠ በኋላ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እሱ ለመናገር
“ቀጠለ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል። ሮዳ የተቆለፈውን በር ለጴጥሮስ ሳትከፍትለት፣
እሱ በደጅ እንዳለ ለሁሉም ለመንገር ወደ ውስጥ ሮጣ በሄደች ጊዜ፣ ጴጥሮስ በሩን
ማንኳኳቱን ቀጠለ (ሐዋ. 12፡16)። እንዲሁም ጳውሎስ ጢሞቴዎስን በመጽሐፍ ቅዱስ
እውነት ማመኑን እንዲቀጥል ለማበረታታት “ቀጥል” የሚለውን ቃል ተጠቅሟል (1
ጢሞ. 4:16)። በቆላ. 1፡23 ላይ ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ በእግዚአብሔር በማመን እና
በመታመን እንዲጸኑ (እንዲቀጥሉ) ያበረታታቸዋል።
በሚቀጥለው ሳምንት እንደምናየው፣ ጳውሎስ የቆላስይስ ሰዎች ስለ መልካሙ
የምሥራች የተሳሳቱ ሃሳቦችን እንዲቀበሉ አይፈልግም (ቆላ. 2:8, 20–22ን ያንብቡ)።
ጳውሎስ የቆላስይስ ክርስቲያኖች በእምነት እያደጉ እንዲሄዱ፣ የእግዚአብሔር ቃል
ለሆነው ለመጽሐፍ ቅዱስ ያላቸውም ፍቅር እንዲበረታ ይፈልጋል (ማቴ. 7:25ን፣ ኤፌ.
2:20ን እና ኤፌ. 3:17ን ያንብቡ)። ጳውሎስ የቆላስይስ ሰዎች እንደማይናወጥ ሕንፃ
እንዲሆኑ ይፈልጋል። ያን ጊዜ በወንጌሉ ላይ ያላቸው ተስፋ ምንጊዜም የጸና ይሆናል።
ስለዚህ ጉዳይ ጳውሎስ በ1 ቆሮ. 15፡58 ላይ “ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥
ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥
የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ” ይላል።
በእምነት የመፅናት ልምምድዎ ምን ይመስላል? በፅናት ለመቀጠል መምረጥ አስፈላጊ
የሆነው ለምንድነው? ያለዚያ ምን ይሆናል?
ቆላ. 1:24, 25ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጳውሎስ ለኢየሱስ ስለተቀበለው መከራ ሲናገር ምን ይላል?
ጳውሎስ ለቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን መልእክቱን የጻፈው በሮም ታስሮ እያለ ነው።
በእርግጠኝነት ጳውሎስ በዚህ ጊዜ በስቃይ ውስጥ ነበር። ጳውሎስ እስረኛ ስለነበር እንደ
ቀድሞው ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ መስበክ አልቻለም ነበር (ሐዋ. 20፡20)። ምናልባትም
ይህ ሁኔታ ከመታሰር የበለጠ ጳውሎስን አስጨንቆት ይሆናል። ኢየሱስ ተከታዮቹን
ለእምነታቸው ሲሉ መከራን ሊቀበሉ እንደሚገባቸው አስጠንቅቋቸዋል (ማቴ. 24:9፣ ዮሐ.
16:33)። ነገር ግን እግዚአብሔር ቃል የገባልን በሰማይ ያሉት በረከቶች “የአሁኑን ዘመን
ሥቃይ ምንም እንዳይደለ እንድናስብ” ያደርጉናል (ሮሜ 8፡18)። ስለዚህ ጳውሎስ ለቆላስይስ
ሰዎች ሲል መከራ ስለተቀበለ ደስ አለው። ጳውሎስ ችግሮቹን በደስታ ይቀበላቸው የነበረው
ለቤተክርስቲያን በረከት እንደሚሆኑ ስለሚያውቅ ነው (ቆላ. 1፡24)።
ጳውሎስ በወኅኒ ውስጥ ቢሆንም፣ “የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም!” (2
ጢሞ 2:9)። ጳውሎስ በእስር ቤት እያለ በፊልጵስዩስ እና በኤፌሶን ለሚገኙ አማኞች
እንዲሁም ለፊልሞና ደብዳቤ ጻፈላቸው። ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ፣ 1ኛ ጢሞቴዎስን
እና ቲቶን ጻፈ። እንደገና ለመጨረሻ ጊዜ በሮም ሲታሰር፣ 2ኛ ጢሞቴዎስን ጻፈ። ባጭሩ
ጳውሎስ በእስር ቤት ያሳለፈው ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን ያኔም ሆነ አሁን በረከት ነው፤
ምክንያቱም ሰፊውን የአዲስ ኪዳን ክፍል ጽፏልና። በተጨማሪም የዕብራውያንን
መጽሐፍ የጻፈው በዚህ ጊዜ ይመስለናል።
እኛን ለማዳን የተዘጋጀው የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ፣ የጳውሎስን
እና የሌሎችንም ተሞክሮ ያካትታል። የጳውሎስም ሆነ የሌሎቹ የኢየሱስ ተከታዮች
አገልግሎቶች ሁሉ የእግዚአብሔር እቅድ አካል ነበሩ። በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩት
የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኞችም አገልግሎት፣ የሙሴን ጨምሮ፣ የእቅዱ አካል
ነበሩ (ቆላ. 1፡25፣ 26)። በነገው ትምህርታችን ስለ እግዚአብሔር እቅድ የበለጠ
እንመለከታለን። ለጊዜው ጳውሎስ አገልግሎቱ ከታላቁ እቅድ ውስጥ ትንሹ ክፍል
እንደሆነ ያውቅ እንደነበር ልንረዳ ይገባል። እግዚአብሔር ይህንን እቅድ ያዘጋጀው
ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ በፊት ነው (ማቴ 13፡35፣ ኤፌ. 1፡4)።
ስለ ራስዎ ህይወት ያስቡ። የሚወስኗቸው ትልቅም ሆኑ ትንሽ ውሳኔዎች እኛን ለማዳን
ካለው ከትልቁ ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር እንዴት ይጣጣማሉ? የምንወስነው ውሳኔ
በእርግጥ “ትንሽ” መሆኑን ማወቅ እንችላለን? ትንሹ ውሳኔ ከጊዜ በኋላ የምንረዳው
ትልቅ ውሳኔ እንዴት ሊሆን ይችላል?
ቆላ. 1:26, 27ን ያንብቡ። ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ምስጢር ይናገራል። ይህ ምስጢር ምንድን ነው?
በ1 ቆሮ. 2፡7 ላይም ጳውሎስ ስለ “እግዚአብሔር ምሥጢር” ተናግሯል፡- “ነገር ግን
እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን
የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን” ይላል። እግዚአብሔር እኛን ለማዳን
ያለው እቅድ የእርሱ ሚስጥር ነው። በተጨማሪም ጴጥሮስ ስለ እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ
እውነቶች ሲናገር:- “ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ” ብሏል (1 ጴጥ. 1:12)።
ጳውሎስ ይሰብክ የነበረው መልእክት “ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው ወንጌል” ነበር
(ሮሜ 16:25)። ኢየሱስ ግን ይህንን ምስጢር እንድናስተውል ይረዳናል (2 ቆሮ. 3፡14)።
ስለ እግዚአብሔር ምስጢር የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ። እግዚአብሔር እኛን ለማዳን
ያለውን እቅድ እንድናስተውል እንዴት ይረዱናል?
ኤፌሶን 1፡7-10
ኤፌሶን 3፡3-6
በመጨረሻም ኢየሱስ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ ይጠቀልላል። ያኔ ሁሉም
ነገር በእርሱ ምሉዕ ይሆናል። ኢየሱስ ስለዚህ አንድነት በዮሐንስ 17 ጸልዮአል። ነገር ግን
ኢየሱስ እስኪሞት ድረስ እግዚአብሔር ይህንን አንድነት እንዴት እንደሚያመጣ ማንም
አልተረዳም ነበር።
እግዚአብሔር ኢየሱስን እስኪሰጠን ድረስ እጅግ አድርጎ የወደደን ለምንድነው?
ወደ ሰማይ ከሄድን በኋላ፣ እኛን ያድነን ዘንድ እግዚአብሔር ያዘጋጀውን እቅድ
እናጠናለን። ጥናታችንም ለዘላለም የሚቀጥል ይሆናል። እስከዚያው ድረስ ኢየሱስ
“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው
እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ” እናውቃለን (2 ቆሮ. 5:15)። በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ
እግዚአብሔር ቃል የገባልንን ነገሮች ይወርሳል። እግዚአብሔር በኢየሱስ የገባውን ተስፋ
ለአይሁድም ሆነ አይሁድ ላልሆኑ ሰዎች ይጠብቃል። እግዚአብሔር ሁሉንም አንድ
አካል - ያውም ቤተ ክርስቲያን - ያደርጋቸዋል።
ጳውሎስ “ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ ይኖራል” ብሏል (ቆላ. 1፡27)። እንዴት?
እምነት ሲኖረን፣ ኢየሱስ በልባችን ውስጥ ይኖራል።
ቆላ. 1:28, 29ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጳውሎስ ስለ ምን እየተናገረ ነው?
የጳውሎስ የስብከት ርዕስ ኢየሱስ እና በመስቀል ላይ መሞቱ ነው (1 ቆሮ. 1፡
23)። ኤፌ. 5፡27 ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ለምን እንደሞተ ይነግረናል፡- “እድፈት
ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን
ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ”። ጳውሎስ ፍላጎቱ የሱ
ስብከት “በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ ለማቅረብ” እንዲረዳ ነበር (ቆላ. 1፡
28)። ጳውሎስ ሕዝቡን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትና እንዴት መኖር እንዳለባቸው
ያስተምራቸውና ያስጠነቅቃቸው ነበር (2 ተሰ. 2:15፣ 1 ጢሞ. 4:11፣ 1 ጢሞ. 5:7፣ ቲቶ
1:9)። ጳውሎስ ክርስቲያኖች ኢየሱስን ከተቃወሙት ሊከሰቱ ስለሚችሉት መጥፎ
ነገሮች፣ እንዲሁም ስለ ሐሰተኛ መምህራን አደገኛነት አስጠንቅቋል (ሐዋ. 20፡29–31፣
ሮሜ 16፡17)።
እንደ ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምህሮዎችና ማስጠንቀቂያዎች ስንቀበል
እናድጋለን። በኢየሱስ ማደግ ጠቃሚ ሀሳብ ነው። ወላጆች በልጃቸው የመጀመሪያ
ቃላት እና የመጀመሪያ እርምጃዎች ይደሰታሉ። ልጃቸው ማንበብ ሲማር ደስ ይሰኛሉ ።
ነገር ግን አንድ ሰው ልጁ ከብዙ አመታት በኋላ መራመድ ወይም ማውራት ባይችልስ?
ወላጆች ይጨነቃሉ፣ አይደለም እንዴ? ማደግ የህይወት የተፈጥሮ ዑደት ነው።
በቆላ. 1፡28 ላይ “ፍጹም ወይም ምሉዕ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪኩ ቃል
“ቴሌዮስ” ነው። “ቴሌዮስ” ማለት ፍጹም የሆነ እና በምንም መልኩ ያልተበላሸ ነገር
ማለት ነው። በእምነት እያደግን ስንሄድ፣ የእግዚአብሔርን ህግ የበለጠ እናስተውላለን፤
ከእኛም የሚጠብቅብንን እንዲሁ (መዝ. 119፡96)። የእግዚአብሔር ህግ “የልብንም
ስሜትና አሳብ እንደሚመረምር” እንረዳለን (ዕብ. 4:12)።
ሆኖም መጠንቀቅ አለብን። ለዚህ ነው ጳውሎስ በቆላ. 1፡28 ላይ “እየገሠጽን
ወይም እያስጠነቀቅን” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው። “ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ
አለች፣ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው” (ምሳ. 14: 12)። መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና፣
መንፈስ ቅዱስ ጥበብን ይሰጠናል። የሐሰት አስተምህሮዎች ብዙውን ጊዜ የተወሰነ እውነት
አላቸው። ነገር ግን እነዚህ አስተምህሮዎች መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገረው ላይ ይጨምራሉ
ወይም ይቀንሳሉ (ኢሳ. 8፡20ን ያንብቡ)። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር
ለዘመናችን ገጣሚ መሆኑን መጠራጠር እንጀምራለን። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና
ጠቢባን መሆን አለብን። ያኔ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን ከሐሰት አስተምህሮዎች ለይተን
እናውቃለን።
“በልባችን ውስጥ ምንም የተቀደሰ ነገር የለንም።
የእግዚአብሔርንም ህግ መጠበቅ አንችልም። ነገር ግን ኢየሱስ እኛን የሚያድንበትን
መንገድ አዘጋጀ። . . . ራስህን ለእርሱ መስጠት አለብህ። እርሱን አዳኝህ አድርገህ
ተቀበለው። ያለፈው ህይወትህ በኃጢአት የተሞላ ሊሆን ይችላል። ሆኖም እግዚአብሔር
በኢየሱስ ምክንያት ቅዱስ አድርጎ ይቀበልሃል። እግዚአብሔር እኛን ሲመለከት፣ የኢየሱስን
ቅዱስ ሕይወት ብቻ ነው የሚያየው። እግዚአብሔር እኛን ምንም እንዳልበደልን አድርጎ
ይቀበለናል።” “ከዚህም በላይ ኢየሱስ ልባችንን ይለውጠዋል። በእርሱ ስናምን፣ ኢየሱስ
በልባችን ውስጥ ይኖራል። እምነት ከኢየሱስ ጋር ያለንን ግንኙነት እንድናጸና ይረዳናል።
እኛም ደግሞ ልባችንን ለእርሱ ማስረከባችንን መቀጠል አለብን። ልናገለግለው
እስከመረጥን ድረስ፣ እግዚአብሔር እርሱን ደስ የሚያሰኙትን ነገሮች እናደርግ ዘንድ
በእኛ ውስጥ ይሰራል። . . . “ስለዚህ የምንኮራበት ምንም ምክንያት የለንም። ብቸኛው
ተስፋችን ኢየሱስ ነው። ቅዱስ ህይወቱ ለእኛ የሰጠን ስጦታ ነው። ስጦታውም ልባችንን
ያነጻዋል። ከዚያም መንፈሱ ቅዱሳን እንድንሆን በውስጣችን ይሠራል።”—ኤለን ጂ.
ዋይት፣ ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ፣ ገጽ 62, 63።
“ብዙ ሰዎች ቤተ ክርስቲያናችንን እንደሚለቁ እግዚአብሔር በሚገርም ሁኔታ
አሳየኝ። ክፉ መናፍስትን ይታዘዛሉ፤ አስተምህሮዎቻቸውንም ይቀበላሉ። ጌታ የመጽሐፍ
ቅዱስን እውነት የሚያምን እያንዳንዱ ሰው፣ እውነትን እንዲያስተውል ይፈልጋል።”—
ኤለን ጂ. ዋይት፣ የወንጌል ስርጭት፣ ገጽ 363።
1. መሪ ጥቅሱን እንደገና ያንብቡ። ኢየሱስ ለእኛ ኃጢአት ሆነ ማለት ምን ማለት ነው?
መሪ ጥቅሱን እንደገና ያንብቡ። ኢየሱስ ለእኛ ኃጢአት ሆነ ማለት ምን ማለት ነው?
ይህ ሃሳብ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የኛ ምትክ ሆኖ መሞቱን እንድናስተውል እንዴት
ሊረዳን ይገባል? በተጨማሪም እግዚአብሔር በኢየሱስ ምክንያት ይቀበለናል ማለት
ምን ማለት ነው?
2. ብዙ ክርስቲያኖች “ሰው አንድ ጊዜ ከዳነ ሁልጊዜም የዳነ ነው” በሚለው ሃሳብ
ብዙ ክርስቲያኖች “ሰው አንድ ጊዜ ከዳነ ሁልጊዜም የዳነ ነው” በሚለው ሃሳብ
ያምናሉ። ይህ አስተምህሮ ክርስቲያኖች ኢየሱስን ከተቀበሉ በኋላ ፈጽሞ ሊጠፉ
አይችሉም የሚል ነው። ይህ ሀሳብ ስህተት የሆነው ለምንድነው? ይህ የሐሰት
ትምህርት የሚያምኑበትን ክርስቲያኖች አደጋ ላይ የሚጥላቸው እንዴት ነው?
ይህንን የሐሰት ትምህርት ልንቃወመው ይገባል። ጎን ለጎን ስለ መዳናችን እንዴት
ተስፋ ሊኖረን ይችላል?
3. እምነትዎ ምን ያህል ጠንካራ ነው? ቆላ. 1፡23ን ያንብቡ። የሚያምኑትን ለምን
እምነትዎ ምን ያህል ጠንካራ ነው? ቆላ. 1፡23ን ያንብቡ። የሚያምኑትን ለምን
እንደሚያምኑ በሚገባ ያውቃሉ? የሚያምኑትንስ የበለጠ ለማወቅ ምን ማድረግ
ይችላሉ? በእምነት ጠንካራ መሆን እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?