የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዘፍ. 1:26, 27፣ ቆላ. 1:15–18፣ ኤፌ. 1:22።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ
ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም
አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ
ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ
ተፈጥሮአል። እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል”
(ቆላ. 1:15–17)፡፡
በዚህ ሳምንት ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች የጻፈውን መልእክት ማጥናት
እንጀምራለን። ስለ ቆላስይስ ሰዎች በ1ኛ ትምህርት እና 2 ላይ አስቀድመን
በጥቂቱ ተመልክተናል። በ2ኛ ትምህርት የሀሙሱ ጥናት ላይ ጳውሎስ በቆላስይስ
ከተማ ላሉ ክርስቲያኖች ይጸልይ እንደነበር አይተናል (ቆላ. 1፡9-12)። በቁጥር 12 እና
13 ላይ ጳውሎስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ከሰይጣን መንግሥት ጋር ያነጻጽረዋል።
የእግዚአብሔር መንግሥት በብርሃን ሲመሰል የሰይጣን መንግሥት ደግሞ በጨለማ
ተመስሏል። እግዚአብሔር ከሰይጣን ኃይል አድኖናል። የመንግስቱም ዜጎች አድርጎናል።
እግዚአብሔር አብ ስለ ኢየሱስ ሲል ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል (ቆላ. 1፡13, 14)።
ኢየሱስ አምላካችን ነው። እርሱ ፈጠረን። ራሱም ያድነናል። በኢየሱስ
ስናምን፣ እግዚአብሔር ከሰይጣን መንግሥት ያፈልሰናል፤ የሰማይም ዜጎች ያደርገናል።
እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ያደረገልን፣ ኢየሱስ እኛን ለማዳን በሠራው ሥራ ነው።
በዚህ ሳምንት ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልዕክት ውስጥ ስለ ኢየሱስ
የተናገራቸውን አንዳንድ ነገሮች እንመለከታለን። እነዚህ ጥቅሶች በመላው መጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ ስለ ኢየሱስ ከተነገሩት እጅግ ውብ ቃላት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።
*የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።
በመስታወት ወይም በፎቶ ራሳችንን ስንመለከት፣ የእኛን ቅጂ እናያለን። ግን ምስሉ ጠፍጣፋ (ባለ ሁለት ገጽታ) ነው። ሃውልት ከፎቶ የተሻለ ነው። ቀራፂ የአንድን ሰው ሃውልት ከእንጨት ወይም ከድንጋይ ሊቀርጸው ይችላል። ሃውልት ከምስል ይልቅ አንድ ሰው ምን እንደሚመስል የተሻለ እይታ ይሰጠናል። ሆኖም ሃውልት ህያው ከሆነና ከሚተነፍስ ሰው ጋር አንድ አይነት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ሕያው የእግዚአብሔር አምሳያ እንደሆነ ይናገራል። ስለዚህ ኢየሱስ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ በትክክል ያሳየናል። ዘፍ. 1:26, 27ን፣ ዘፍ. 5:3ን፣ 1 ቆሮ. 15:49ን፣ 2 ቆሮ. 3:18ን እና ዕብ. 10፡1ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች እያንዳንዳቸው ስለ ምን ይናገራሉ? ቅጂ ምንድን ነው? አንድ ቅጂ ከዋናው ነገር ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ኢየሱስ የእግዚአብሔር ትክክለኛ ቅጂ የሆነው እንዴት ነው? እንዲሁም ኢየሱስ ከቅጂ በላይ የሆነው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር ሰዎችን የፈጠራቸው እርሱን እንዲመስሉ ነው። አካል አለን።
እናስባለን፣ ስሜት አለን፣ እንወዳለን። ግንኙነት እንዲኖረን እንፈልጋለን። እግዚአብሔር
በዚህ መልኩ ፈጥሮናል ምክንያቱም እኛ የእርሱ አምሳያዎች ነን። ሆኖም እኛ ልክ እንደ
እግዚአብሔር አይደለንም። ስለዚህ እኛ የእርሱ ፍጹም ቅጂ (አምሳያዎች) አይደለንም።
እግዚአብሔርን ማሳየት የምንችለው በከፊል ብቻ ነው። ኢየሱስ ግን የማይታየውን
አምላክ “እንድናየው” ይረዳናል። ኢየሱስ “እኔን ያየ አብን አይቶአል” ብሏል (ዮሐ.
14፡9)። ኢየሱስ “የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ” ነው (ዕብ. 1:3)። ኢየሱስ
እግዚአብሔር የሚያስበውን ይነግረናል። ኢየሱስ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ያሳየናል።
ኢየሱስ አብ ማን እንደሆነ ሊያሳየን የሚችለው ለምንድን ነው? ማቴ. 11:27ን እና
ዮሐ. 1:1, 2, 14, 18ን ያንብቡ።
ኢየሱስ ከአብ ጋር ስላለው ግንኙነት የሚናገርባቸውን ሌሎች መንገዶችን አስተውሉ፡-
•“አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል፣ እኔም ደግሞ እሠራለሁ“ (ዮሐ. 5፡17)።
•“እኔና አብ አንድ ነን“ (ዮሐ. 10፡30)።
•“በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐ. 14፡6)።
እንዲሁም ኢየሱስ ስለ ራሱ ለመናገር የእግዚአብሔርን ስም በተደጋጋሚ
ይጠቀማል። እግዚአብሔር “እኔ እኔ ነኝ” ይላል (ዘጸ. 3፡14ን ያንብቡ)። ኢየሱስ “እኔ የዓለም
ብርሃን ነኝ” ብሏል (ዮሐ. 8፡12)። እንዲሁም “መልካም እረኛ እኔ ነኝ” ይላል (ዮሐ. 10፡11) ።
በተጨማሪም ዮሐ. 10: 14ን፣ ዮሐ. 11: 25ን፣ ዮሐ. 14: 11ን እና ዮሐ. 8: 58ን ያንብቡ።
በአዲስ ኪዳን “በኩር” የሚለው ቃል በአብዛኛው ስለ ኢየሱስ ለመናገር ጥቅም
ላይ ውሏል (ሉቃ. 2፡7፣ ሮሜ 8፡29፣ ዕብ. 1፡6 እና ራዕ. 1፡5ን ያንብቡ)። አሁን “በኩር”
የሚለውን ቃል የምንጠቀመው መጀመሪያ ለተወለደ ወንድ ልጅ ነው። በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ ግን ቃሉ ከሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ አስቀድሞ የተወለደ ወንድ
ልጅ ማለት ላይሆን ይችላል። ለዚህም ምክንያቱ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ልጅ ከአባቱ
ጋር ያለውን ልዩ ግንኙነት ለማስረዳት ቃሉን ስለሚጠቀመው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ
ከታላላቅ ወንድሞቻቸው ይልቅ ኃያል ስለሆኑት ወጣት ወንዶች ልጆች ብዙ ምሳሌዎችን
ይሰጠናል። ከነዚህም ውስጥ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ እና ዮሴፍ ይገኙበታል። ታናሹ ልጅ
ከወንድሞቹ ይልቅ ኃያል ስለ መሆኑ ሌላኛው ምሳሌ ዳዊት ነው። ዳዊት ሰባት ወንድሞች
ነበሩት። ሁሉም የዳዊት ወንድሞች የእሱ ታላላቆች ነበሩ። እግዚአብሔር ግን ዳዊትን
ንጉሥ እንዲሆን መረጠው (1 ሳሙ. 16፡10-13)። ስለዚህ እግዚአብሔር ዳዊትን እንደ
በኩር ልጁ አደረገው፤ ከምድርም ነገሥታት ይልቅ ኃያል አደረገው (መዝ. 89፡27)።
ደግሞም እግዚአብሔር ለሙሴ እስራኤል የበኩር ልጁ እንደሆነ ነገረው (ዘጸ. 4፡22)።
እነዚህ ጥቅሶች “በኩር” የሚለው ቃል ከሌሎች ይልቅ አስፈላጊ እና ኃያል የሆነ ሰው
ማለት እንደሆነ ያሳዩናል።
ቆላ. 1:15–17ን ያንብቡ። ጳውሎስ ኢየሱስ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ
የሚቆጣጠር በኩር እንደሆነ የተናገረባቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ጳውሎስ እግዚአብሔር ሌላ ነገር ከመፍጠሩ በፊት ኢየሱስን እንደፈጠረው
እየተናገረ አይደለም። ጳውሎስ እያለ ያለው ኢየሱስ ሁሉን ለራሱና በራሱ ኃይል
ፈጥሮታል ነው (ቆላ. 1፡16)። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን የፈጠረው
ከኢየሱስ ጋር ነው። በተጨማሪም ኤፌ. 3፡9ን፣ ዮሐ. 1፡1–3ን እና ራዕ. 4፡11ን ያንብቡ።
ጳውሎስ ኢየሱስ ሁሉን ነገር እንደፈጠረ ሲናገር፣ እግዚአብሔር ሰማይንና
ምድርን ፈጠረ ማለቱ ነው። ኢየሱስ የምናየውንና የማናየውን ሁሉ ፈጥሯል። ኢየሱስ
ሁሉንም ነገር በመደገፍ ሥራቸውን እንዲሠሩ ያደርጋል። ኢየሱስ በሁሉም ነገር ላይ
ሥልጣን አለው - በመላእክትም ጭምር (ኤፌ. 3፡10፣ ኤፌ. 6፡12)። ጳውሎስ ኢየሱስ
ሁሉን ከመፍጠሩ በፊት ሕያው እንደነበር ተናግሯል (ቆላ. 1፡17)። ጳውሎስ ኢየሱስ
በኩር ነው ያለበትን ሌላ ምክንያት ሲናገር ሁሉም ነገር በእርሱ ተጋጥሞአል ይላል።
ኢየሱስ ይህንን ሥራ መሥራት የሚችለው እርሱ ስለፈጠረንና ስላዳነን ነው።
እግዚአብሔር ፈጠረን፣ ደግሞም ሞተልን። የእኛ መልካም ሥራ በዚህ ስጦታ ላይ ምን
ሊጨምር ይችላል? ሥራችን ኢየሱስ በመስቀል ለኛ በፈጸመው ነገር ላይ ምን ሊጨምር
ይችላል? ይህ ሃሳብ እጅግ የተሳሳተ የሆነው ለምንድነው?
ኤፌ. 1:22ን እና ቆላ. 2:10ን ያንብቡ። ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ኢየሱስ “ራስ” እንደሆነ ይናገራል። ይህ ቃል ትርጉሙ ምንድነው? ጳውሎስ ኢየሱስ “የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው” ሲል ምን ማለቱ ነው? (ኤፌ. 5:23)
“ራስ” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ታላቅ መሪን ለማመልከት ያገለግላል።
ብሉይም ሆነ አዲስ ኪዳን ይህንን የቃላት ምስል ብዙ ጊዜ ይጠቀማሉ። በሚቀጥሉት
ምሳሌዎች ውስጥ “ራስ” እና “መሪዎች” የሚሉትን ቃላት ልብ ይበሉ፡-
1. ዘጸ. 18፡25፡- “ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ አዋቂዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ
የሺህ አለቆች፥ የመቶም አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የአሥርም አለቆች አድርጎ
ሾማቸው”።
2. ዘኍ. 31፡26፡- “ካህኑ አልዓዛር የማኅበሩም አባቶች አለቆች (ራሶች)”።
3. ዘዳ. 28፡13፡- ቢታዘዙት እግዚአብሔር እስራኤልን “ራስ ያደርጋቸዋል እንጂ ጅራት
አያደርጋቸውም”።
4. ኢሳ. 7፡8፡ “የሶርያ ራስ ደማስቆ ነው፥ የደማስቆም ራስ ረአሶን ነው”።
5. ሆሴ. 1፡11፡- “የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በእንድነት ይሰበሰባሉ፣ ለእነርሱም
አንድ አለቃ ይሾማሉ”።
6. ሚክ. 3:9:- “እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆች ስሙ”።
7. 1 ቆሮ. 11፡3፡- “የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ ነው”።
ስለዚህ ኢየሱስ የቤተ ክርስቲያን ራስ ወይም መሪ ነው። መሪ ስለሆነ ኢየሱስ
ቤተ ክርስቲያንን ይመራታል፤ ያስተምራታል፤ እንድታድግ ይረዳታል። በተጨማሪም
ኢየሱስ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምንና አንድነትን ይሰጣል።
በ1 ቆሮ. 12፡12-27 ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን “በአካል” ይመስላታል። ይህ ምሳሌ
ስለ ቤተ ክርስቲያን ምን ያስተምረናል?
ሰውነት ያለ ራስ መኖር እንደማይችል፣ ቤተክርስቲያንም ያለ ኢየሱስ መኖር
አትችልም። የአካል ክፍል ሲጎዳ ወይም ሲቆረጥ፣ ህይወት ከባድ ሊሆን ይችላል።
ብዙውን ጊዜ አንድን ነገር ካላጣነው በቀር፣ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አናውቀውም።
እግር ወይም ዓይን ማጣት ቢኖርብዎ፣ የትኛውን ይመርጣሉ? መልስዎ እያንዳንዱ አባል
ለቤተ ክርስቲያን ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ምን ይነግርዎታል?
ጳውሎስ ኢየሱስ የእኛ ራስ ወይም መሪ እንደሆነ ይነግረናል። በተጨማሪም ኢየሱስ የሁሉም ነገር “መጀመሪያ” ነው፣ ምክንያቱም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ ፈጥሮአልና። ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ እነዚህ ሁለት ሐሳቦች የተዛመዱት እንዴት ነው? ቆላ. 1:18ን ያንብቡ።
በዕብራይስጥ “ራስ” እና “መጀመሪያ” የሚሉት ቃላት የተዛመዱ ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ “መጀመሪያ” የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው በዘፍ. 1፡
1 ላይ ነው፡- “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” ይላል (ዘፍ. 1፡1)።
ኢየሱስ ይህችን ምድር ይቆጣጠራል። ደግሞም የቤተ ክርስቲያን መሪ ነው።
በግሪክ ቋንቋ “መጀመሪያ” የሚለው ቃል ብዙ ነገሮችን ሊያመለክት ይችላል።
በቆላ. 1፡18 ላይ “መጀመሪያ” የሚለው ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መሰረተ
የሚያመለክት ነው። ለዚህም ነው መሪዋ የሆነው። በተመሳሳይ መልኩ በምድርም ሆነ
በሰማይ ያለው ሕይወት ሁሉ የጀመረው በእርሱ ነው።
ኢየሱስ ከሞት በተነሳ ጊዜ (ሮሜ 6:3, 4)፣ አዲስ ሕይወት ሰጪ ሆነ። የኃጢአት
ዋጋ ሞት ነው። ሆኖም ኢየሱስ ከሞት ጋር የነበረውን ተጋድሎ አሸንፏል። ስለዚህ
አዲስ ሕይወትና አዲስ ልብ ሊሰጠን ሥልጣን (ኃይል) አለው። እነዚህ ሐሳቦች ኢየሱስ
“ከሙታንም በኵር” የሆነው ለምን እንደሆነ እንድንገነዘብ ይረዱናል (ቆላ. 1:18)። እርግጥ
ነው፣ ከሞት የተነሣው የመጀመሪያው ሰው ሙሴ እንጂ ኢየሱስ አይደለም። ዲያብሎስ
ስለ ሙሴ ሥጋ ከኢየሱስ ጋር ተሟግቷል (ይሁ. 1፡9ን ያንብቡ)። ነገር ግን ጳውሎስ አንድ
ወሳኝ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንድናስተውል ለመርዳት ስለ ኢየሱስ ትንሣኤ
ይህን ምሳሌ ተጠቅሟል። ያለ ኢየሱስ ትንሣኤ፣ ከሞት ሊነሳ የሚችል ማንም የለም።
ኢየሱስ በነገር ሁሉ የመጀመሪያውና ዋንኛው ስለ ሆነበት ምክንያት ጳውሎስ
የሰጣቸውን ሁሉንም አመክንዮዎች እንመልከት፡-
1. ኢየሱስ የማይታየው አምላክ ፍጹም ምሳሌ ነው።
2. ኢየሱስ ሁሉንም ነገር ፈጠረ።
3. ኢየሱስ ምንም ነገር ከመፈጠሩ በፊት ሕያው ነበር።
4. ኢየሱስ የቤተ ክርስቲያን መሪ ነው።
5. ኢየሱስ በእርሱ አማካኝነት አዲስ ያደርገናል።
6. ኢየሱስ ከኃጢአትና ከሞት ጋር የተደረገውን ተጋድሎ አሸንፏል። ስለዚህ ኢየሱስ
ህዝቡን ከሞት የማስነሳት ሥልጣን አለው።
7. ኢየሱስ ምድርን ይቆጣጠራል።
ኢየሱስ ሕይወትዎን ይቆጣጠር ዘንድ እግዚአብሔር እንዲለውጣቸው መፍቀድ
ያለብዎት ነገሮች ምንድን ናቸው?
ቆላ. 1:19, 20ን ያንብቡ። መስቀሉ ከእግዚአብሔር ጋር እንድንስማማ የሚረዳን እንዴት ነው?
በቆላ. 1: 19, 20 ላይ ጳውሎስ “እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥
በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ
ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና” ይላል። እግዚአብሔር በኢየሱስ ውስጥ ለማኖር
የመረጠው “ሙላቱ” ምንድን ነው? ዮሐንስ ያስረዳናል። ኢየሱስ “ጸጋንና እውነትንም
ተመልቶ” ነበር (ዮሐ. 1፡14)። ጸጋ የሚለው ቃል ምሕረትን፣ ይቅርታን፣ ፍቅርን እና
ኃጢአትን ድል ማድረግን ያጠቃልላል።
የእግዚአብሔር “ሙላት” ወይም ጸጋ ከፍቅሩ፣ ይቅር ባይነቱ እና ትዕግሥቱ
የበለጠ ብዙ ነገሮችን ያካትታል። የእግዚአብሔር ሙላት (ማንነቱ) አዳዲስ ነገሮችን
የመሥራት ኃይሉንም ይጨምራል። በተጨማሪም እግዚአብሔር አሮጌውን ነገር እንደገና
አዲስ ማድረግ ይችላል። ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔር ጸጋ የእርሱን ጥበብ ያካትታል።
እግዚአብሔር የኃጢአትንና የሞት ችግሮችን ፈቷል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም
ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ
ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐ. 3:16)።
ኢየሱስ መሞት ነበረበት። ያም እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ማዳን የሚችልበት
ብቸኛው መንገድ ነበር። እግዚአብሔር ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ ኢየሱስን በመስቀል
ላይ እንዲሞት ፈቀደ። እግዚአብሔር ይህንን ነገር ያደረገው ለእኛና በሰማይ ላሉት ሁሉ ነው።
ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ፣ እግዚአብሔር በሰማይና በምድር ላሉ ኃጢአተኞች ሁሉ
ያለውን ፍቅር ማረጋገጫ ሰጠ። ለዚህ ነው ጳውሎስ “ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም”
ይመለከቱን ዘንድ እንደ ትዕይንት ሆነናልና ያለው (1 ቆሮ. 4፡9)።
“በሰማይ ያሉ ፍጥረታት ኢየሱስን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ አዩት። ተገረሙ፣
አዘኑም። ... ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ እንደ አመጸ፣ ከሰይጣን ጋር የሚተባበሩ
ሁሉ እንዲሁ ያደርጋሉ። እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ነገር ግን ክብሩ ኃጢአተኞችን
ያጠፋቸዋል። ለኃጢአተኞች እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር እንደሚያቃጥል እሳት ነው።
በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል ያለው ታላቁ ተጋድሎ ሲከሰት፣ መላእክቱ ይህንን
ነገር አልተረዱትም ነበር። …
“ሆኖም በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል ያለው ታላቁ ተጋድሎ ሲያበቃ፣
ሁሉም ሰው ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ይገነዘባል። ከዚያም የእግዚአብሔር
ኃጢአተኞችን የማዳን ዕቅድ ይፈጸማል። በዚያን ጊዜ መላእክትና ሰዎች ሁሉ
የእግዚአብሔርን ፍቅርና ጥበብ ያስተውላሉ።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣
ገጽ 760–764።
“አብ እግዚአብሔር ነው። በዓይናችን ባናየውም በምሕረት፣
በፍቅር እና በይቅርታ የተሞላ ነው። ኢየሱስም አብን ሙሉ በሙሉ ያሳየናል። መጽሐፍ
ቅዱስ ኢየሱስ “የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ” ነው ይላል (ዕብ. 1:3)።
“ኢየሱስ ክርስቶስ ሁልጊዜ ሕያው ነበር፣ እርሱንም የፈጠረው የለም። ሁልጊዜም
የእግዚአብሔር ልጅ ነበር። … ኢየሱስ ሁልጊዜ ሕያው መሆኑን ተናግሯል። እርሱም
ሁልጊዜ ዘላለማዊ ከሆነው አብ ጋር የቅርብ ኅብረት እንደነበረው ይነግረናል። ...
“ኢየሱስ በነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ነው። መጀመሪያም መጨረሻም
የለውም። እርሱ ሁሉን ቻይ ነው። ኢየሱስ ዘላለዊ የሆነ ልጅ ነው። ኢየሱስ ሁልጊዜ
የነበረ፣ ያለና ለዘላለምም የሚኖር ነው። “—ኤለን ጂ. ዋይት፣ በወንጌል መድረስ፣ ገጽ
614, 615።
1. ስለ ኢየሱስና ሁልጊዜም ሕያው ስለ መሆኑ ደጋግመው ያስቡ። ኢየሱስ አምላክ
ስለ ኢየሱስና ሁልጊዜም ሕያው ስለ መሆኑ ደጋግመው ያስቡ። ኢየሱስ አምላክ
ባይሆን ኖሮስ? እርሱ ዘላለማዊ ባይሆን ኖሮስ? እግዚአብሔር አብ ኢየሱስን
ፈጥሮት ቢሆን ኖሮስ? ታዲያ ኢየሱስ ሁልጊዜ ማንነቱ የማይለዋወጥ ባይሆን
ኖሮ፣ ኃጢአተኞችን እንዴት ሊያድናቸው ይችላል? ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ
እንደሆነ የሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
2. ስለ ኢየሱስ፣ ስለ መልካሙ የምሥራች እና እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ለማዳን
ስለ ኢየሱስ፣ ስለ መልካሙ የምሥራች እና እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ለማዳን
ስላለው እቅድ ያስቡ። እነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች እኛን ብቻ የሚመለከቱ ሳይሆኑ፣
የመላእክትንና በሰማይ ያሉ ፍጥረታትን ሕይወት ጭምር የሚነኩ ናቸው። በሰማይ
ያሉ ሁሉ በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል በሚካሄደው ታላቁ ተጋድሎ ውስጥ
ስለሚሆነው ነገር ትኩረት እንደሚሰጡ ሁልጊዜ ማስታወስ ያለብን ለምንድን ነው?
በእርግጥ መስቀል ያስደንቀናል። ሆኖም መላእክቱ እና በሰማይ ያሉ ፍጥረታት
ሁሉ ኢየሱስን ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ በፊት ያውቁታል። ያመልኩትም ነበር።
የፈጠራቸውም እርሱ ነው። ኢየሱስን በመስቀል ላይ ሲመለከቱ፣ መላእክቱ ምን
ያሰቡና የተሰማቸው ይመስላችኋል?
3. አብ እና ወልድ ሁልጊዜ ህያው እንደ ነበሩ ለማያምን ሰው ምን ይነግሩታል? ይህ
አብ እና ወልድ ሁልጊዜ ህያው እንደ ነበሩ ለማያምን ሰው ምን ይነግሩታል? ይህ
ሀሳብ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? በመስቀል ላይ ለአጭር ጊዜ ካልሆነ
በስተቀር፣ አብ እና ወልድ ሁልጊዜ አብረው እንደነበሩ ለአንድ ሰው እንዴት
ያስረዱታል?