የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ሰማይ እና ምድርን ማስታረቅ
በፊልጵስዩስ እና በቆላስይስ ስለ ኢየሱስ መማር



1ኛ ሩብ ዓመት 2026


ጥር 23 - 29

6ኛ ትምህርት

Jan 31 - Feb 6




ያድነን ዘንድ በኢየሱስ ብቻ መታመን



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ፊል. 3:1-6፣ ዮሐ. 9፣ ፊል. 3:9-16።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ” (ፊል. 3:10-11)።

የእግዚአብሔር ፍቅርና ይቅርታ በእርግጥ እንደሚያድናችሁ ታምናላችሁ? አንዳንድ ሰዎች ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለማመን ይቸገራሉ። እነሱን ለማዳን የእግዚአብሔር ምሕረት በቂ እንዳልሆነ ያምናሉ። በእግዚአብሔር የማዳን ስጦታ ላይ የራሳቸውን መልካም ባህሪ ማካተት እንዳለባቸው ያስባሉ። ጳውሎስ በነበረበት ጊዜ አንዳንድ ክርስቲያኖች ለመዳን መገረዝ እንደሚያስፈልጋቸው ያምኑ ነበር። መገረዝ ማለት በወንድ ብልት ጫፍ ላይ ያለውን ሸለፈት መቁረጥ ማለት ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ይህ ድርጊት አይሁዳውያን የእግዚአብሔር መሆናቸውን የሚያሳይ ልዩ ምልክት ነበር። ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ግርዛት በጥምቀት ተተክቷል። ሆኖም አንዳንድ ክርስቲያን የሆኑ አይሁዶች ይህንን ሃሳብ ለመቀበል ተቸግረው ነበር። ለመዳን መገረዝ እንዳለባቸው ያምኑ ነበር። ጳውሎስ ጠንከር ባሉ ቃላት ይህንን የተሳሳተ ሃሳብ በመቃወም ተከራክሯል። እሱ “እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ፣ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ፣ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና” ይላል (ፊል. 3:3)። *የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።

ጥር 24
Feb 1

በጌታ ደስ መሰኘት (ፊል. 3፡1-3)


ፊል. 3:1-3ን ያንብቡ። ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የሰጣቸው ምክሮችና ማስጠንቀቂያዎች ምንድናቸው? ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ተከታዮች ምን ተናገረ? ማስጠንቀቂያዎች ምንድናቸው? ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ተከታዮች ምን ተናገረ?



በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ፣ ጳውሎስ በመልእክቱ ካካተታቸው እጅግ አስፈላጊ ርዕሶች መካከል አንዱ ስለ ሆነው ስለ ደስታ ተናግሯል። ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ ለምን ደስተኛ መሆን እንዳለባቸው ብዙ ምክንያቶችን ይነግራቸዋል። ከሁሉም በላይ በራሳችን ሳይሆን በኢየሱስ መታመን አለብን፡- “እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ የምንመካ፣ በሥጋም የማንታመን ነንና” ይላል (ፊል. 3፡3)። በተጨማሪም ጳውሎስ አንባቢዎቹ እንዲጠነቀቁ ያስጠነቅቃል። ይህ ማስጠንቀቂያ ጠንካራ ሲሆን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሌላ ቦታ አናገኘውም። የፊልጵስዩስ ሰዎች ጳውሎስ እየተናገረ ስለ ነበረው አደጋ ጠንቅቀው ያውቁ ነበር። ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች ስለ ሦስት የተለያዩ ነገሮች እያስጠነቀቃቸው እንዳልሆነ ትረዳላችሁን? ጳውሎስ ስለ አንድ ነገር ሦስት ጊዜ እያስጠነቀቃቸው ነበር።

ማስጠንቀቂያውም ስለ ሐሰት አስተማሪዎች ነበር።

መጽሐፍ ቅዱስ ክፉ እስራኤላውያንን ብዙውን ጊዜ “ውሾች” ሲል ይጠራቸዋል (ፊል. 3:2፤ ከመዝ. 22: 16፣ ኢሳ. 56: 10፣ ማቴ. 7: 6፣ 2 ጴጥ. 2: 21, 22 ጋር ያስተያዩ)።

ሐሰተኛ መምህራን በዚህ ቡድን ውስጥ ተካተዋል። ጳውሎስ እነዚህን ሐሰተኛ አስተማሪዎች ክፉ ሠራተኞች ናቸው ብሎ ይጠራቸዋል። ጳውሎስ የፊልጵስዩስን ሰዎች “ከሐሰተኛ” አስተማሪዎች ተጠበቁ እያለ ያስጠነቅቃቸዋል (ፊል. 3፡2)። ለምን? ምክንያቱም እነዚህ አስተማሪዎች አይሁዳዊ ያልሆኑ ክርስቲያኖች እንዲገረዙ ወይም የአይሁዳዊነት ምልክት በሰውነታቸው እንዲታይ ይፈልጉ ነበር (ፊል. 3፡2)። እነዚህ የአይሁድ አስተማሪዎች አይሁዳዊ ያልሆኑ ክርስቲያኖችን የቤተ ክርስቲያን አባላት ለመሆን እንዲገረዙ ለማስገደድ እንደሞከሩ የጳውሎስ ቃላት ያመለክታሉ። ይህ አስተምህሮ በኢየሩሳሌም ስብሰባ የተወሰነውን ውሳኔ ይቃወም ነበር (የሐዋ. 15ን ያንብቡ)። ጳውሎስ አንባቢዎቹን በኢየሱስ ደስ እንዲላቸው ነገራቸው። ደስታቸው በመከራቸው ያበረታቸው ነበር። በተጨማሪም ደስታ ለሐሰት አስተምህሮዎች ዳርቻ ያበጅላቸው ነበር (ፊል. 3:1፤ ከፊል. 4:4 ጋር ያስተያዩ)።

እግዚአብሔር ደስተኞች እንድንሆን ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ደስታና ሐሴት እንዴት ማግኘት እንደምንችል ያስተምረናል። (1) የእግዚአብሔርን ምሕረት መቀበል አለብን (መዝ. 31፡7)፤ (2) በእግዚአብሔር መታመን አለብን (መዝ. 4:11)፤ (3) የእግዚአብሔርን በረከቶች መቀበል አለብን (መዝ. 9፡14)፤ (4) ሕጉን መታዘዝ አለብን (መዝሙረ ዳዊት 19፡14)፤ (5) ሰንበትን መጠበቅ አለብን (ኢሳ. 58:13, 14)፤ (6) የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ ማመን አለብን (መዝ. 119፡162)፤ በተጨማሪም (7) ልጆቻችን ጌታን እንዲከተሉ ማስተማር አለብን (ምሳ. 23፡24, 25)። ሊደሰቱ የሚችሉባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

ጥር 25
Feb 2

የጳውሎስ የኋላ ታሪክ (ፊል. 3፡4-6)


ብዙ ክርስቲያኖች ኢየሱስን ከመቀበላቸው በፊትና በኋላ ስላለው ሕይወታቸው የሚናገሩት በሁለት ከፍለው ነው። ጳውሎስም በፊልጵስዩስ 3 ላይ ተመሳሳይ ነገር አድርጓል። አንዳንድ ጊዜ ኢየሱስን ያልተቀበሉ ሰዎችም “መልካም ሰዎች” ናቸው እንል ይሆናል። በአብዛኞቹ ሰዎች እይታ፣ እነዚህ ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች ጥሩ ናቸው። ነገር ግን ህይወታቸውን ከእግዚአብሔር ህግ ጋር ስናነጻጽረው፣ ማንም መልካም አይደለም፤ ክርስቲያኖችም እንኳን ቢሆኑ። በፊል. 3፡4-6 ጳውሎስ ስለ ድሮ ህይወቱ ብዙ ነገሮችን ተናግሯል። እነዚህ ነገሮች ልቡን በኩራት ሞልተውት ነበር። እነዚህ ነገሮች ምንድን ናቸው? አሁንም ሆነ በፊት፣ በራስህ ህይወት ውስጥ “መልካም” የምትላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?



ጳውሎስ ሁለት አይነት ሰዎችን ያነጻጽራል፡- ሐሰተኛ አስተማሪዎችን እና አይሁዳዊ ያልሆኑ ክርስቲያኖችን። የሐሰት አስተማሪዎች እውነት ያልሆኑ ነገሮችን ያስተምሩ ነበር።

አይሁዳዊ ያልሆኑ ክርስቲያኖች ኢየሱስ እንደሚያድናቸው ሙሉ በሙሉ ታምነውበታል። የእግዚአብሔርን ይቅርታ ወይም ሞገስ ለማግኘት በራሳቸው መልካም ባህሪ አይታመኑም ነበር (ዕብ. 6፡1ን እና ዕብ. 9፡14ን ያንብቡ፤ ከሮሜ 2፡25-29 ጋር ያስተያዩ)።

የጳውሎስ የኋላ ታሪክ በክብር የተሞላ ነበር። ነገር ግን ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ አንዳቸውም አላዳኑትም ነበር። ይባስ ብለው የጳውሎስን ልብ በትዕቢት ሞሉት።

ለጊዜው ኢየሱስ ምን ያህል እንደሚያስፈልገው ሳያውቅ “ታውሮ” ነበር።

የጳውሎስን የኋላ ታሪክ እንመልከት። በትውልዱ እስራኤላዊ ነበር። ከብንያም ወገን ነበር። በእስራኤል ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት ከተሞች መካከል አንዳንዶቹ የዚህ ወገን ድርሻ ነበሩ። ጳውሎስ የዕብራይስጥን ቋንቋ ያውቅ ነበር። እንዲሁም የታዋቂው መምህር የገማልያል ተማሪ ነበር (ሐዋ. 22:3፣ 26:4, 5)። ጳውሎስ ፈሪሳዊ ወይም የአይሁድ መንፈሳዊ መሪ ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ ስለ ሕጉና እንዴት መጠበቅ እንዳለበት ያውቅ ነበር።

ጳውሎስ ሕጉን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ፣ ለሕጉ ይቀና ነበር። ስለዚህ ክርስቲያኖች የአይሁድን ሕግ ወይም የአኗኗር ዘይቤ አያከብሩም ብሎ በማሰቡ ያሳድዳቸው ነበር።

ከዚያም ጳውሎስ ሕጉ ጥልቅ ትርጉም እንዳለው ተረዳ። ሕጉ ከሱ የሚፈልገው፣ እሱ ሊያደርገው ከሚችለው በላይ ነበር። ያለ ኢየሱስ፣ ጳውሎስ ሕጉን በመተላለፍ ጥፋተኛ መሆኑን ተረድቶ ነበር። ሮሜ 7:7-12ን ከማቴ. 5:21, 22, 27, 28 ጋር ያነጻጽሩ። ኢየሱስም ሆነ ጳውሎስ ስለ ሕጉ ምን ይላሉ? ሕጉ ሳይሆን በኢየሱስ ማመናችን ብቻ ቅዱሳን የሚያደርገን ለምንድነው? (ፊል. 3፡9) ይህንን ጥያቄ በዚህ መንገድ ይመልከቱት፡- ኢየሱስ ልንጠብቀው እንደሚገባ በተናገረው መንገድ ሕጉን ምን ያህል ይጠብቁታል? መልስዎ ኢየሱስ ያድነን ዘንድ እንደሚያስፈልገን ምን ይነግርዎታል?

ጥር 26
Feb 3

ወሳኝ የሆኑ ነገሮች (ዮሐ. 9)


ትናንት እንዳየነው፣ ጳውሎስ ባለፈው ሕይወቱ በብዙ ነገሮች ይመካ ነበር።

ሆኖም እነዚህ ነገሮች ጳውሎስ እምነት እንዳይኖረው እንቅፋት ሆነውበት ነበር። እንዲያውም ጳውሎስ ኢየሱስ እንደሚያስፈልገው እንዳይመለከት “አሳውረውት” ነበር።

ጳውሎስ ኢየሱስን ከተቀበለ በኋላ፣ ነገሮችን በተለየ መንገድ ይመለከታቸው ጀመር። አይሁዳዊ በመሆኑ መታበዩን አቆመ። አሁን የሰማይ ዜጋ በመሆኑ በኩራት ተሞላ።

ኢየሱስ “ከሰማይ የወረደው፣ ስለ ሰማይ ሊነግረን ነው። ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ የተጋረጠብንን መንፈሳዊ አደጋ ያውቃል። እርሱ የመጣው ኃጢአትን ከልባችን ውስጥ በማስወገድ እኛን ሊቀድሰን ነው። ከዚያም በሰማይ በዙፋኑ ላይ ከእርሱ አጠገብ መቀመጥ እንችላለን። ኢየሱስ በዚህ ህይወት የማይጠቅሙ ነገሮችን መውደድ ስላለው አደጋ ያስጠነቅቀናል። እርሱ ስለ ምድራዊ ነገሮች ሳይሆን ስለ ሰማይ እንድናስብ ይረዳናል። እናም አላስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ጊዜአችንን፣ መክሊታችንንና ህይወታችንን እናባክንም።”⎯ ኤለን ጂ. ዋይት፣ የምጻቱ ግምገማ እና የሰንበት አዋጅ፣ ሐምሌ 1, 1890።

በአዲስ ኪዳን ዘመን፣ ጳውሎስ በፍጥነት ታዋቂ ሆነ። ነገር ግን ጳውሎስ ወደ ደማስቆ ሲሄድ፣ ኢየሱስን አየው (ሐዋ. 9)። ኢየሱስ በብሩህ አንጸባራቂ ክብር ተሸፍኖ ነበር። ጳውሎስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ፣ ዓይኑ ታወረ። ዓይኑ በታወረ ጊዜ ነበር ጳውሎስ በመጨረሻ ስለ ኢየሱስ እውነቱን የተረዳው። ዮሐንስ 9 ዓይነ ስውር ስለነበረው እና ከዚያም ኢየሱስን ስላየው ሰው ታሪክ ይነግረናል።

ኢየሱስ ወደዚህ ምድር ለምን እንደ መጣ ሲናገር “የማያዩ እንዲያዩ የሚያዩም እንዲታወሩ እኔ ወደዚህ ዓለም መጣሁ አለ” (ዮሐ. 9:39)። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ኢየሱስ ምን ማለቱ ነው? በሕይወታችን ይህንን አስፈላጊ መርህ መታዘዝ የምንችለው እንዴት ነው?



ከዘላለም ሕይወት ይልቅ አስፈላጊ የሆነ ነገር ምን አለ? ምንም። የሚያሳዝነው ምድራዊ ሐሳቦችና ነገሮች ብዙውን ጊዜ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንዳንመለከት ያሳውሩናል። ከፈቀድንላቸው ምድራዊ ነገሮች ልባችንንና አእምሯችንን ይቆጣጠሩታል (ማቴ. 13:22፣ ሉቃ. 4:5, 6፣ 1 ዮሐ. 2:16)። ስለዚህ ልባችንንና አእምሯችንን በእግዚአብሔር ዓይን ብዙ ዋጋ ባላቸው ነገሮች መሙላት አለብን። እነዚህ ነገሮች ምንድን ናቸው? በልባችን እንደ ኢየሱስ መሆን አለብን። ሰዎችንም ለማዳን ከእግዚአብሔር ጋር መስራት አለብን። ምድራዊ የሆኑ ነገሮች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነትና እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ነገር እንዳናይ “ሊያሳውሩን” ይችላሉ። ዓይኖቻችንን ወሳኝ በሆኑ ነገሮች ላይ እንድናተኩር የሚረዳን ምንድን ነው?

ጥር 27
Feb 4

የኢየሱስ እምነት (ፊል. 3:9)


ወደ ደማስቆ በሚወስደው መንገድ ላይ ጳውሎስ አስደናቂ ነገር አጋጥሞት ነበር።

አሮጌ ሕይወቱን በኢየሱስ በሚገኘው አዲስ ሕይወት ለወጠው። “አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት፣ ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ” (ፊል. 3:8, 9)። ጳውሎስ “በእርሱ እገኝ ዘንድ” እፈልጋለሁ ብሏል። በቀላሉ ሊስተዋል በሚችለው የእንግሊዝኛው ትርጉም ከኢየሱስ ጋር አንድ መሆን እፈልጋለሁ ይላል። ጳውሎስ ምን ማለቱ ይመስልዎታል? በተጨማሪም ኤፌ. 1:4ን፣ 2 ቆሮ. 5:21ን፣ ቆላ. 2:9ን እና ገላ. 2፡20ን ያንብቡ።



ብዙ ሰዎች የጳውሎስን ቃላት ለማብራራት ሞክረዋል። ከሁሉ የተሻለው ማብራሪያ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ይገኛል። በዚህ ደብዳቤ ላይ ጳውሎስ ስለ እግዚአብሔር የማዳን እቅድ ይናገራል። “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው” (ኤፌ. 1፡ 10)። ከመጀመሪያው የእግዚአብሔር እቅድ በሰማይና በምድር ያሉትን ቤተሰቦች አንድ ማድረግ ነው። ጳውሎስ ያ እቅድ እንዴት እንደሚፈጸም ሲገልጽ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው” ይላል (1 ቆሮ. 1:30)።

በክርስቶስ ኢየሱስ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? በክርስቶስ ኢየሱስ ስንሆን፣ ዳግመኛ እንወለዳለን። እግዚአብሔር አስተዋይ ያደርገናል። እርሱ ይቀድሰናል።

ለሰማይም ያዘጋጀናል። በመጨረሻም በዳግም ምጽአቱ፣ ኢየሱስ ሰውነታችንን ይለውጠዋል። ኢየሱስ ሁሉንም ነገር ለእኛና በእኛ ውስጥ ያደርግልናል። ኢየሱስን ወደ ልባችን ስንጋብዘው፣ የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ይኖረናል። ፊል. 3:9ን ያንብቡ። በዚህ ጥቅስ ውስጥ ጳውሎስ ሁለት ነገሮችን አነጻጽሯል። ምንድን ናቸው? ይህንን ሀሳብ ሁልጊዜ ማስታወስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?



ኢየሱስ የሚያድን እምነት ይሰጠናል። በኢየሱስ ከሆንን፣ እርሱ በእኛ ይኖራል (ገላ. 2፡20)፤ እንድንታዘዝም ይረዳናል። በእርሱ ስለምናምን፣ ሕይወትን ይሰጠናል።

ጥር 28
Feb 5

ኢየሱስን ማወቅ (ፊል. 3፡10-16)


ፊል. 3:10-16ን ያንብቡ። ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተናገራቸው አንዳንድ ሃሳቦች ምንድን ናቸው?



ኢየሱስን ከማወቅ የበለጠ አስፈላጊ ነገር እንደሌለ የተረጋገጠ ነው። ኢየሱስን ስናውቀው፣ እርሱ ይቀበለናል (ማቴ. 7፡21-23ን ያንብቡ)። ታዲያ እርሱን እንዴት ልናውቀው እንችላለን? ኢየሱስን የምናውቀው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እርሱ ስለሚነግረን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብና በተገለጠው እውነት ስንኖር ኢየሱስን እናውቀዋለን።

በምድር በነበረ ጊዜ ይከተሉት እንደ ነበሩት፣ ኢየሱስን ፊት ለፊት ልናውቀው አንችልም። ነገር ግን ምን እንደሆኑ ተመልከቱ:- ቃሉን አላስተዋሉትም ነበር። ስለዚህ ቃሉን ለማስተዋልም ሆነ ይመራን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገናል (ዮሐ. 16፡13ን ያንብቡ)። ኢየሱስን የበለጠ ባወቅነው ቁጥር፣ ወደ እርሱ የበለጠ እንጠጋለን። ኢየሱስ ከመንፈሳዊው ሞት እንድንነሳ ይረዳናል (ፊል. 3፡10)። ከዚያም በእርሱ አዲስ ሕይወት እንኖራለን (ሮሜ 6፡4)። በተጨማሪም እርሱ መከራ እንደተቀበለ መከራ ስንቀበል፣ በልባችን ወደ ኢየሱስ የበለጠ እንቀርባለን (ፊል. 3፡10)። እያንዳንዱ ፈተና፣ አስቸጋሪ ጊዜ እና መጥፎ ገጠመኝ ኢየሱስ ለእኛ ሲል የተቀበለውን መከራ እንድናውቅ ይረዳናል።

ከዚያም ኢየሱስን እና እኛን ለማዳን ያለውን እቅድ በተሻለ ሁኔታ እንረዳለን።

ጳውሎስ ከኢየሱስ ጋር ያለንን ልምምድ ከሩጫ ጋር አመሳስሎታል። “በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ወደ መጨረሻው ምልክት እፈጥናለሁ (እሮጣለሁ)” ይላል (ፊል. 3፡14)። የእግዚአብሔርን ስጦታ (ሽልማት) ለመቀበል እሮጣለሁ ነው የሚለው። ኢየሱስ ሞተ፣ ተነሳ፣ ወደ ሰማይም አረገ። በተመሳሳይ መንገድ፣ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሽልማት እንድንቀበል ይጋብዘናል።

እርግጥ ነው ኢየሱስ ሥጋችንን እስኪለውጠው ድረስ፣ ያን ቀን መጠባበቃችንን እንቀጥላለን (ፊል. 3፡21)። ሆኖም እርሱን ስናውቀው፣ በየቀኑ በልባችን እንዲኖር እንጋብዘዋለን። ከዚያም አሁን መሆን የምንችለውን ያህል ኢየሱስን እንመስላለን።

ጳውሎስ ይህንን ልምምድ ከምንም ነገር በላይ ፈልጎት ነበር። እኛም ይህንን ልምምድ ከፈለግነው እንደ ሯጮች መሆን አለብን። ሯጮች ከኋላቸው ማን እንዳለ ወይም ምን ያህል ርቀት እንደሮጡ ትኩረት አይሰጡትም። በሩጫው መጨረሻ ላይ ስለሚጠብቃቸው ሽልማት ነው የሚያስቡት። ስህተቶቻችሁንና ውድቀቶቻችሁን አዘውትራችሁ ወደ ኋላ አለመመልከታችሁ ጥቅሙ ምንድነው? እግዚአብሔር አሁን በኢየሱስ ቃል የገባላችሁን ተስፋ ሁሉ ወደ ፊት መመልከት ያለባችሁ ለምንድን ነው?

ጥር 29
Feb 6


ተጨማሪ ሀሳብ


“ኢየሱስን መምሰል ትፈልጋላችሁ? በልባችሁ እንደርሱ መሆን ትፈልጋላችሁ? ግሩም ክርስቲያን መሆን ከፈለጋችሁ፣ ሁሉንም ነገር ለኢየሱስ ማስረከብ አለባችሁ። የምታደርጉትንም ሁሉ እርሱን ለማክበር ማድረግ አለባችሁ።

ሙሉ ልባችሁን ይፈልገዋል እንጂ ኢየሱስ የተከፈለ (ግማሽ) ልባችሁን አይቀበለውም። ሁሉንም ነገር ለእርሱ ብሎ መተው ማለት ምን ማለት እንደሆነ መማር አለባችሁ።

መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት፣ ምን እንደሚናገር ተማሩ። የሚያስተምራችሁን ታዘዙ። እነዚህን ነገሮች ስታደርጉ፣ ግሩም ክርስቲያን ልትሆኑ ትችላላችሁ። በየዕለቱ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሰራል። እርሱ ቅዱሳንና ፍጹማን ያደርጋችኋል። በመጨረሻው ዘመን የሚሆነውን ታላቁን ፈተና እንድታልፉ ይረዳችኋል። በየቀኑም እያንዳንዱ ክርስቲያን የዚህ አስደናቂ ልምምድ አካል ነው። ስለ ኢየሱስ የሚናገረው ወንጌል ለኃጢአተኞች ምን ሊያደርግላቸው እንደሚችል በሰማይም ሆነ በምድር ላሉ ሁሉ እናሳያለን።” ⎯ኤለን ጂ. ዋይት፣ የሐዋርያት ሥራ፣ ገጽ 483።

“ኢየሱስ ተመልሶ እስኪመጣ ስንጠባበቅ ሳለ፣ ሁሉም ወደ ኢየሱስ እንዲመለከቱ መናገር አለብን። በምድር ላይ ላሉ ሁሉ የእግዚአብሔርን የመጨረሻውን የምሕረት መልዕክት ማስተላለፍ አለብን። ይህም መልዕክት ለሰዎች የእግዚአብሔርን ፍቅር ያሳያል። እንደ እግዚአብሔር ልጆች ሕይወታችን የእግዚአብሔርን ክብር ማሳየት አለበት። የእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት እንዴት እንደሚያድነን እና እንደሚለውጠን ስናሳይ የእግዚአብሔርን ክብር እናንጸባርቃለን።

“ኢየሱስ ብርሃን ነው። ብርሃኑም በምንሰራውና በምንናገረው ነገር ሁሉ ማብራት አለበት። ያኔ ንግግራችንና ተግባራችን የተቀደሰ ይሆናል።”⎯ኤለን ጂ. ዋይት፣ የክርስቶስ ምሳሌያዊ ትምህርቶች፣ ገጽ 415, 416።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. በጌታ ደስ ስለ መሰኘት ደጋግመው ያሰላስሉ። ፍቅሩን፣ የማዳን ኃይሉን እና በጌታ ደስ ስለ መሰኘት ደጋግመው ያሰላስሉ። ፍቅሩን፣ የማዳን ኃይሉን እና እግዚአብሔር የሚያደርግልንን መልካም ነገሮች ማስታወስ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እነዚህ ነገሮች በህይወትዎ በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ሲያልፉ እንዴት ሊረዱዎት ይችላሉ?

2. ያለ እግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት እርሱን መታዘዝ አንችልም። ኢየሱስ ተመልሶ ያለ እግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት እርሱን መታዘዝ አንችልም። ኢየሱስ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ እየተጠባበቅን ሳለ፣ እነዚህ ስጦታዎች እጅግ አስፈላጊ የሆኑት ለምንድነው? በእርግጠኝነት የእኛ መልካም ባህሪ (ሥራ) አያድነንም። ሆኖም ካልታዘዝን በእርግጥ መዳን እንችላለን?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL