የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ፊል. 1:3-18፣ ቆላ. 1:3-12
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ
ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና።”
(ፊል. 1:6)
ጳውሎስ መልእክቶቹን የሚጀምረው በሰላምታ እና በምስጋና ነው።
“ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይሁን።
ስለ እናንተ ስንጸልይ፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን
ሁልጊዜ እናመሰግናለን” (ቆላ. 1: 2, 3)።
እኛም ልናመሰግንበት የሚገባን ብዙ ነገር አለን። እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ
እናመሰግነዋለን። በሰማይ ያሉ መላእክት ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሳ ያለንን
አስደናቂ ልምምድ አይረዱትም። እግዚአብሔርን ስለሰጠን ሰላም፣ ተስፋና ፍቅር
እናመሰግነዋለን። ሰዎች ለሚያደርጉልን ነገር አመስጋኞች መሆናችንን እንገልጻለን።
እኛም ለምናደርጋቸው ነገሮች አመስጋኞች እንደሚሆኑ ተስፋ እናደርጋለን። ወላጆች
ልጆቻቸው እግዚአብሔርን እንዲወዱት ይጸልያሉ። በተጨማሪም ወላጆች ልጆቻቸው
ደስተኛ ይሆኑ ዘንድ ላደረጉላቸው ነገር ሁሉ አንድ ቀን አመስጋኝ እንደሚሆኑ
ተስፋ ያደርጋሉ። በዚህ ሳምንት፣ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ እና በቆላስይስ ላሉ አብያተ
ክርስቲያናት በጻፋቸው ደብዳቤዎች ላይ ያሉትን የመክፈቻ ቃላት እናጠናለን። እነዚህ
ቃላት በምስጋና እና በጸሎት የተሞሉ ናቸው። እነዚህ ቃላት የኛን የጸሎት ህይወት
እንዲያበረቱት ምኞቴ ነው።
*የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።
ፊል. 1:3-8ን አንብበው የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይመልሱ። ጳውሎስ የሚያመሰግንበት ምክንያት ምንድን ነው? በፊልጵስዩስ ላሉ ክርስቲያኖች ተስፋ ይሰጣቸው ዘንድ ምን ተናገረ? እርሱ የተናገራቸው ቃላት ዛሬም ለእኛ በጣም አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው?
ጳውሎስ እስረኛ ነበር። የታሰረውም በፊልጵስዩስ ከነበሩት ክርስቲያኖች በጣም
ርቆ ነበር። ቢሆንም ጳውሎስ እጅግ ይጠነቀቅላቸው ነበር። በፊልጵስዩስ የነበረችነውን
ቤተ ክርስቲያን የመሰረታት ጳውሎስ ነበር። ስለዚህ የጳውሎስ ልብ በዚያ በነበሩት
ክርስቲያኖች ፍቅር የተሞላ ነበር። ለዚህም ነው “በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ሁላችሁን
እንዴት እንድናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው” ብሎ የተናገራቸው (ፊል. 1: 8)።
ጳውሎስ ስለ እነርሱ እግዚአብሔርን ያመሰግናል። የጳውሎስ የምስጋና ጸሎት፣ ኢየሱስ
በሰማይ ስለኛ የሚሠራውን ሥራ እንድናስተውል ይረዳናል። ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን ነው።
በብሉይ ኪዳን የቤተ መቅደስ አገልግሎት፣ ሊቀ ካህኑ የደረት ኪስ ይደርብ
ነበር። በዚህ የደረት ኪስ ላይ 12 የዕንቁ ድንጋዮች ነበሩበት። ለ12ቱ የእስራኤል ነገዶች፣
ለእያንዳንዳቸው ስማቸው የተጻፈበት አንድ የዕንቁ ድንጋይ ነበራቸው። ስለዚህ ሊቀ
ካህኑ የደረት ኪሱን ሲለብስ፣ ስማቸውን “በልቡ ውስጥ” ከመሸከም ጋር ተመሳሳይ ነበር
(ዘጸ. 28፡29)። ከዚያም ስለ እነሱ ረድኤትን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ይቀርብ ነበር።
የእኛ ሊቀ ካህን የሆነው ኢየሱስም የህዝቡን ስም በልቡ ተሸክሞታል። ከዚያም ለእኛ
ረድኤትን ይቀበል ዘንድ ወደ አብ ይቀርባል። በፊል. 1፡3 ላይ፣ ጳውሎስ “ባሰብኋችሁ ጊዜ
ሁሉ አምላኬን አመሰግናለሁ” ይላል። ይህ ጥቅስ ጳውሎስ ከፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች
ጋር የነበረውን የጠበቀ ወዳጅነት ያሳየናል። ጳውሎስ የኢየሱስን መከራ እንደ ተካፈለ
ሁሉ (ፊል. 3፡10)፣ የፊልጵስዩስ ሰዎችም ከጳውሎስ ጋር መከራን ተቀብለዋል።
በተጨማሪም የፊልጵስዩስ ሰዎች የጳውሎስን አገልግሎት ደግፈዋል (ፊል. 4፡14, 15)።
እርሱም ካመናችሁበት “ከፊተኛው ቀን እስከ ዛሬ ድረስ ወንጌልን በመስበክ አብራችሁ
ሠርታችኋል” ይላቸዋል (ፊል. 1፡5)። ለዚህም ነው ጳውሎስ ስለ እነርሱ እግዚአብሔርን
የሚያመሰግነው። ደግሞም “በደስታ” ይጸልይላቸው ነበር (ፊል. 1፡4)።
ጳውሎስ በወኅኒ በመታሰሩ አይተክዝም ነበር። የእስር ቤት ልምምዱን፣
እግዚአብሔርን የሚያመሰግንበት ጊዜ እንደነበር ተናግሯል። ጳውሎስ እስረኛ ሆኖ
እንኳን፣ በወኅኒ ቤት ስለ ኢየሱስ መልካሙን የምሥራች ይናገር ነበር። በተጨማሪም
ጳውሎስ መልካሙ የምሥራች የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መሆኑን አረጋግጧል። ጳውሎስ
ባጭር ጊዜ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ያውቅ ነበር። ሆኖም እርሱን ይበልጥ ያስጨንቀው
የነበረው ከእስር ቤት መውጣቱ ሳይሆን፣ ወታደሮቹንና በወኅኒ ቤት ይጎበኙት
የነበሩትን ሰዎች ማዳን ነበር። ጳውሎስን በሕይወት መኖሩ ወይም መሞቱ አላሳሰበውም
ነበር። እግዚአብሔር በእርሱ በሚታመኑት ሁሉ ላይ የጀመረውን “መልካሙን ሥራ”
እንደሚፈጽመው ያምን ነበር (ፊል. 1፡6)።
በፊል. 1፡9-11 ያለውን የጳውሎስን ጸሎት ያንብቡ። ጳውሎስ የጸለየው ስለ ምንድን ነው? እግዚአብሔርን የለመነባቸው ትልልቅ ነገሮች ምንድናቸው? መልስዎ ስለ ጸሎት ምን ይነግርዎታል?
የጳውሎስ ጸሎት በግሪክ ቋንቋ 43 ቃላት ናቸው። ነገር ግን በእነዚህ ጥቂት ቃላት
ውስጥ ምኞቱንና ፍላጎቱን ሁሉ አጠቃሏል። ጳውሎስ ስለ ፍቅር፣ እውቀት፣ ማስተዋል፣
ሐቀኝነት፣ ንጹህና የዋህ ልቦና እንዲሁም የተቀደሰ ህይወት ለመኖር ስለሚያስፈልጋቸው
ኃይል ይጸልያል። ጸሎቱ ለመላው ቤተ ክርስቲያን እና ስለ ስኬቷ እንጂ ለራሱ አልነበረም።
ጳውሎስ ስለ ጸለየባቸው አንዳንድ ነገሮች በጥልቀት እንመልከት፡-
1. ፍቅር፡- ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን የበለጠ አፍቃሪ እንድትሆን ብቻ አይጸልይም፤
ጥቢብም እንድትሆን እንጂ። ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ማስተዋል
እንዲኖራት ይፈልግ ነበር። ይህንን ማስተዋል ማግኘት የምንችለው ከእግዚአብሔር
ጋር ግንኙነት ካለን ብቻ ነው። እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ በማጥናት እውቀትን
እናገኛለን (ኤፌ. 1:17ን፣ ኤፌ. 4:13ን እና 1 ጢሞ. 2:4ን ያንብቡ)።
2. እውቀት እና ማስተዋል፡-
እውቀት እና ማስተዋል፡- እውቀትና ማስተዋል ሲኖረን ትክክለኛውን ነገር ስህተት
ከሆነው ለይተን ለማወቅ እንችላለን። ትክክለኛውን ነገር ስንመርጥ ደግሞ፣ የተቀደሰ
ልብ እና ንጹህ አእምሮ ይኖረናል (ፊል. 1፡10)።
3. ሐቀኝነት፡- በግሪክ ቋንቋ ሐቀኛ መሆን የሚለው ቃል “በፀሐይ ብርሃን መፈረድ”
ማለት ነው። ይህም ባህሪያችን ቅዱስ መሆን እንዳለበት ያሳየናል። “ክርስቲያኖች
የሚያደርጉት ነገር ሁሉ እንደ ፀሐይ ብርሃን ግልጽ መሆን አለበት።”—ኤለን ጂ.
ዋይት፣ ክርስቶስን ማንጸባረቅ፣ ገጽ 71። ይህ ጥቅስ ትክክለኛ ትርጉሙ ምንድን ነው?
ተንኮለኛ መሆን ወይም ምንም ነገር በድብቅ ማድረግ የለብንም። ሕይወታችንና
ድርጊታችን ግልጽ እና ሐቀኛ መሆን አለበት። ስለዚህ በጓዳችን አንድ ነገር ብለን፣
ከዚያም በአደባባይ ሌላ ነገር ማድረግ የለብንም። የግል ህይወታችንና በህዝብ ፊት
የምንኖረው ኑሮ መመሳሰል አለበት።
4. ንጹህና ቅን ልቦና፡- ሰው በኢየሱስ ለማመን እንዲያዳግተው የሚያደርግ
ማንኛውንም ነገር መናገርም ሆነ ማድረግ የለብንም።
5. የተቀደሰ ሕይወት የመኖር ኃይል፡- ያለ ኢየሱስ የተቀደሰ ሕይወት መኖር አንችልም።
ጳውሎስ ስለዚህ ሃሳብ ሰፋ ባለ መልኩ ለሮሜ እና ለገላትያ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ
ላይ ተናግሯል። በፊልጵስዩስ 3 ላይም ስለዚህ ጉዳይ ጽፏል።
ኢየሱስ እስኪመጣ ድረስ ፍቅራችን “ከፊት ይልቅ እያደገ” ሊሄድ የሚችለው እንዴት
ነው (ፊል. 1፡9)? ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለክርስቲያን ሕይወት አስፈላጊ
የሆነው ለምንድነው? 1 ቆሮ. 13፡1-8ን ያንብቡ።
የፊልጵስዩስ ሰዎች ጳውሎስ እንደታሰረ ሲሰሙ አዘኑ። ይህ ዜና ለምን
እንዳሳዘናቸው መረዳት እንችላለን። አሁን የጳውሎስ አገልግሎት ተገድቦ ነበር።
መጓዝም ሆነ መስበክ አይችልም ነበር። ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን ለሕዝቡ ለማስተማር
የአይሁድን አብያተ ክርስቲያናት መጎብኘት አይችልም ነበር። ጳውሎስ አብያተ
ክርስቲያናትን መመስረት አይችልም ነበር። የፊልጵስዩስ ሰዎች ጳውሎስን እንዲጎበኘውና
እንዲያበረታታው አፍሮዲጡን ላኩት።
ጳውሎስ እስር ቤት በመሆኑ ምን ተሰማው? ስለ ገጠመኙ ከነበረው ሃሳብና ስሜት ምን
ትምህርት እናገኛለን? መልሶቹን ለማግኘት ፊል. 1:12-18ን ያንብቡ።
ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች የላከላቸው መልእክት ሳያስገርማቸው አይቀርም።
የጳውሎስ መንፈሳዊ ግንዛቤ በእስር ቤት ያሳለፈውን ጊዜ እንደ በረከት እንዲቆጥረው
ረድቶታል። ወኅኒ የጳውሎስን አገልግሎት በጭራሽ አላቆመውም ነበር። ለዚህ ነው
ጳውሎስ “ይህ የደረሰብኝ መከራ በእውነት ወንጌልን ብዙ ሰዎች እንዲያውቁት
ረድቷቸዋል” የሚለው (ፊል. 1:12)። ጳውሎስ እሱን የሚጠብቁ የሮም ወታደሮች
የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተመልክቶ ነበር። ጳውሎስ በእስር
ቤት መሆኑ ሌሎች ሰዎችን ለጌታ ተግተው እንዲሠሩ እንዳበረታታቸው ተረድቷል።
የሚያሳዝነው አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጳውሎስ ስለታሰረ የበለጠ
ታዋቂ የሚሆኑና ሥልጣን የሚኖራቸው መስሏው ነበር። ጳውሎስ ስለተገለለ፣ እነዚህ
መሪዎች ሕዝቡ ለስብከታቸው የበለጠ ትኩረት እንደሚሰጥ አስበው ነበር። የራስ
ወዳድነት ምሳሌ መሆናቸው እጅግ ያሳዝናል። ይባስ ብሎ እነዚህ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን
አባላት ነበሩ! ከጳውሎስ አስቀድሞ ኤርምያስ እንዲህ ሲል አስጠንቅቆን ነበር:- “የሰው
ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?” (ኤር. 17:9)።
በእርግጥ ሁሉም ሰው ክፉ አልነበረም። እንዲያውም አንዳንድ ክርስቲያኖች ጌታን
አብዝተው ያገለግሉ ነበር። እነዚህ አገልጋዮች ጳውሎስን በጣም ይወዱት ስለነበር፣
በእምነቱ ምክንያት የደረሰበት መከራ በኢየሱስ የበለጠ እንዲታመኑ አድርጓቸው ነበር።
አሁን፣ አስቀድመው ለመሄድ ይፈሩ ወደ ነበሩባቸው ቦታዎች ሄዱ። በፊት ለመናገርም
ሆነ ለመስበክ ይፈሩ ነበር። አሁን ግን ፍርሃት አይሰማቸውም ነበር። በእነዚህ ደፋር
ሠራተኞች ምክንያት፣ ብዙ ሰዎች ኢየሱስንና መልካሙን የምሥራች ተቀበሉ።
ከዚህ በፊት ያጋጠሟችሁና እምነታችሁን ያጠነከሩ አንዳንድ መጥፎ ገጠመኞች ምንድን
ናቸው? እነዚህ ገጠመኞች እንድታድጉ የረዷችሁ እንዴት ነው? በእግዚአብሔርም
የበለጠ እንድትታመኑ የረዷችሁስ እንዴት ነው?
ጳውሎስ ከቆላስይስ ሰዎች ጋር የነበረው ግንኙነት ከፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች ጋር ከነበረው ግንኙነት የተለየ ነበር። ጳውሎስ የቆላስይስ ሰዎችን ፊት ለፊት በአካል ካልተገናኙት ውስጥ ይመድባቸዋል (ቆላ. 2፡1)። ልክ እንደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ሁሉ፣ ጳውሎስ በቆላስይስ ለነበሩት ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ሁልጊዜም ይጸልይላቸው ነበር። ጳውሎስ እግዚአብሔርን የሚያመሰግንባቸው ሦስት ነገሮች ምንድናቸው? ቆላ. 1፡ 4-8ን ያንብቡ።
ጳውሎስ ስለ ሦስት ቅዱስ ተግባራት ወይም መልካም ባሕርያት ይናገራል፡-
እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር። በሌሎች መልእክቶቹም ስለ እነዚህ ሦስት ነገሮች ተናግሯል
(1 ቆሮ. 13፡13ን፣ 1 ተሰ. 1፡3ን እና 1 ተሰ. 5፡8 ያንብቡ)። ስለ እነዚህ ነገሮች የቆላስይስ
ሰዎችን እንደማያመሰግን አስተውለዋል? የእነዚህ ሥጦታዎች ምንጭ አምላክ ስለሆነ፣
ጳውሎስ በሰማያት ያለውን አባቱን አመሰገነ። ያዕቆብ “በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት
ሁሉ ከላይ ናቸው” ይላል (ያዕ. 1፡17)። እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ስንመለከት፣
በኢየሱስ እናምናለን (ኤፌ. 2፡4-8)። በኢየሱስ ስናምን ደግሞ፣ እግዚአብሔር ልባችንን
በሰማያዊ ተስፋ ይሞላዋል። ጴጥሮስ ተስፋ እግዚአብሔር ለልጆቹ ከሚሰጣቸው
በረከቶች አንዱ ነው ይላል። “ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥
ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት … ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል” (1 ጴጥ. 1: 4)።
በተጨማሪም ጳውሎስ ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሆነ፣ መልካሙን የምሥራች
ልንተማመንበት እንደምንችል ተናግሯል። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው (2
ቆሮ. 6፡7ን እና 2 ጢሞ. 2፡15ን ያንብቡ)። መጽሐፍ ቅዱስ በእርሱ በሚያምኑ ሰዎች
ሕይወት ውስጥ ይሠራል (1 ተሰ. 2፡13)። ጌታ እንዲህ ይላል፡- “ቃሌ የምሻውን ያደርጋል፣
የላክሁትንም ይፈጽማል” (ኢሳ. 55፡11)። የኢየሱስ ተከታዮች ምሥራቹን በሚሰብኩበት
ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ የሰዎችን ልብ ይነካል። ህይወታቸውም ተለውጦ መልካም ይሆናል፤
ምክንያቱም ወንጌሉ “የሕይወት ቃል” ነውና (ፊል. 2፡16)። ወንጌሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ
ወደ ብዙ ቦታዎች ደርሷል። ኢየሱስ ከሞተ ከ30 ዓመታት በኋላ፣ ጳውሎስ ወንጌሉ
“ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ ተሰብኳል” ብሎ ተናግሯል (ቆላ. 1:23)።
ሮማውያን የሰሯቸው መንገዶች ጉዞንና ተግባቦትን ቀላልና ፈጣን አድርገውት ነበር።
ነገር ግን ለወንጌል ስርጭቱ ስኬት ዋንኛው ምክንያት የእግዚአብሔር ፍቅር ኃይል ነው።
የእግዚአብሔር ፍቅር አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ይሰጠን ዘንድ በወንጌሉ አማካኝነት
ይሰራል (ያዕ. 1፡18፣ 1 ጴጥ. 1፡23፣ 2 ቆሮ. 5፡17)።
በቆላ. 1፡9-12 ያለውን የጳውሎስን ጸሎት ያንብቡ። ጳውሎስ እግዚአብሔር ለቆላስይስ ሰዎች ምን እንዲያደርግላቸው ነው የጠየቀው?
ጳውሎስ የቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን “የእግዚአብሔርን ፍቃድ በማወቅ”
እንድትሞላ ጸልዮአል። ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ያውቁ ዘንድ “ጥበብ
እና መንፈሳዊ ማስተዋል” እንዲሰጣቸው አምላክን ይለምናል (ቆላ. 1፡9)። ጥበብ
የሚገኘው እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ በመተማመን ነው። እኛ ደግሞ እግዚአብሔር
የሚፈልገውን ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን አለብን (ዮሐ. 7፡17)። በምናውቀውና በራሳችን
ማስተዋል ልንደገፍ አይገባም (ምሳ. 3፡5)። ሰዎች ብዙ ጊዜ “እግዚአብሔር ለእኔ ያለው
እቅድ ምንድን ነው?” ብለው ይጠይቃሉ። እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያለውን እቅድ
ከአራት አስፈላጊ ነገሮች እንማራለን፡-
1. መጽሐፍ ቅዱስ:- እግዚአብሔር ከሰጠን የጥበብ ስጦታዎች ሁሉ የላቀው መጽሐፍ
ቅዱስ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን ለሕይወታችን ያለውን ዕቅድ ለማወቅ
ከመጽሐፍ ቅዱስ መጀመር አለብን።
2. የትንቢት መንፈስ:- እግዚአብሔር የትንቢት መንፈስንም ሰቶናል። የትንቢት መንፈስ
ተብለው የተሰየሙት የኤለን ጂ. ዋይት ጽሑፎች ናቸው። ጽሑፎቿ በመጨረሻው
ዘመን ለሚኖሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የጥበብ ምንጭ ናቸው። ንጉሥ ኢዮሣፍጥ
ለእስራኤላውያን “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤
በነቢያቱም እመኑ፥ ነገሩም ይሰላላችኋል አላቸው” (2 ዜና 20:20)።
3. ከእግዚአብሔር የተሰጡ ልምምዶች:-
ከእግዚአብሔር የተሰጡ ልምምዶች:- ነገሮች እንዲሆኑ ወይም እንዳይሆኑ
እግዚአብሔርን በጸሎት ልንጠይቀው እንችላለን (ቆላ. 4፡3)።
4. መንፈስ ቅዱስ:- የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ስናውቅ፣ እርሱ ይመራናል። “ወደ ቀኝም
ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል፣ ጆሮችህ በኋላህ መንገዷ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ
የሚለውን ቃል ይሰማሉ” (ኢሳ. 30፡21)።
ጳውሎስ የቆላስይስ ሰዎች ሕይወት “በነገር ሁሉ ጌታን ደስ የሚያሰኝ” ይሆን
ዘንድ ጸልዮአል (ቆላ. 1፡12)። በእርግጥ ያለ እርሱ እርዳታ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት
የሚችል ማንም የለም። ስለዚህ እግዚአብሔር ይምረናል። ጌታ ለእርሱ እንደሚገባ
እንመላለስ ዘንድ ያዘናል (ኤፌ. 4፡1፣ 1 ተሰ. 2፡12)። ጳውሎስ እንደሚናገረው በኢየሱስ
ጸንተን መኖር አለብን (ቆላ. 2፡6፣ 3፡7፣ 4፡5)። ይህንን ለማድረግ ደግሞ የእግዚአብሔርን
ሕግ መጠበቅ አለብን (ዘጸ. 18፡20)። ይህም የሚሆንልን በመንፈስ እርዳታ ብቻ ነው
(ሕዝ. 36፡27)።
ጳውሎስ የቆላስይስ ሰዎችም ሆነ የእኛ ሕይወት እግዚአብሔርን በሁሉም
መንገድ ደስ የሚያሰኘው ይሆን ዘንድ ይጸልያል። ከዚያም ጳውሎስ ይህንን እንዴት
ማድረግ እንምንችል ይነግረናል:-
(1) ማንኛውንም “በጎ ሥራ ማድረግ”፤ (2) “በእግዚአብሔር እውቀት ማደግ“
(ቆላ. 1:10, 9)፤ (3) በመጨረሻም “አብን በደስታ ማመስገን” ናቸው (ቆላ፣ 1፡12)።
“ብዙ ሰዎች ስለ ወደፊቱ ማቀድ ይቸገራሉ። ስለ
ሕይወታቸው እርግጠኛ አይደሉም። የነገሮችን ፍፃሜ አያውቁም። ስለዚህ ልባቸው
ብዙውን ጊዜ በፍርሃት የተሞላ ነው። ሰላም የላቸውም። ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ
እውነት እናስታውስ - ይህች ምድር ቤታችን አይደለችም። የራሳችንን ሕይወት በእቅድ
ለመምራት ጥበብ የለንም። ይህ የእኛ ጉዳይም አይደለም። ‘አብርሃም የተባለው ርስት
አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ
ሳያውቅ ወጣ’ (ዕብ. 11:8)።
“ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ፣ ለራሱ የሆነ ምንም እቅድ አልነበረውም፤
የእግዚአብሔርን እቅድ ተቀበለ እንጂ። በየቀኑ አብ እቅዶቹን ለኢየሱስ ገለጸለት። እኛም
በተመሳሳይ መንገድ በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ አለብን። ከዚያም ህይወታችን የእሱን
እቅድ ይፈጽማል። ምን ማድረግ እንዳለብን እና የት መሄድ እንዳለብን ይነግረናል።
“ብዙ ሰዎች ለወደፊት ሕይወታቸው ለማቀድ ይሞክራሉ። ነገር ግን
እቅዳቸው ይከሽፋል። እግዚአብሔር እንዲያቅድላችሁ አድርጉ። በልባችሁ እንደ
ህፃናት ሁኑ። ይመራችሁ ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኑ። ‘እርሱ የቅዱሳኑን እግር
ይጠብቃል’፤ ከመሰናክልም ያድናቸዋል (1 ሳሙ. 2: 9)። የእግዚአብሔር ልጆች
የወደፊቱን ማየት ቢችሉ ኖሮ፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ልጆቹን የሚመራቸው፣
እርሱ እንዲመራቸው በሚመርጡት መንገድ ነው። ያኔ የእግዚአብሔርን ውብ
እቅድ ይረዳሉ። ከአምላክ ጋርም አብረው እንደሚሠሩ ያውቃሉ።”—ኤለን ጂ.
ዋይት፣ የፈውስ አገልግሎት፣ ገጽ 478, 479።
1. የምታመሰግኑባቸውን ነገሮች ዘርዝሩ። ከሚያስቡት በላይ አመስጋኝ ሊሆኑ
የምታመሰግኑባቸውን ነገሮች ዘርዝሩ። ከሚያስቡት በላይ አመስጋኝ ሊሆኑ
የሚችሉባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉዎት?
2. ከላይ ያለውን የትንቢት መንፈስ ጽሁፍ የመጨረሻውን ክፍል ያስቡበት። ጥልቅ በሆነ
ከላይ ያለውን የትንቢት መንፈስ ጽሁፍ የመጨረሻውን ክፍል ያስቡበት። ጥልቅ በሆነ
በዚህ መንገድ በእግዚአብሔር መተማመንን እንዴት መማር ይችላሉ?
3. ቆላ. 1: 6, 23ን ያንብቡ። ከዚያም ስለሚቀጥለው ጥቅስ ይናገሩ:-
ቆላ. 1: 6, 23ን ያንብቡ። ከዚያም ስለሚቀጥለው ጥቅስ ይናገሩ:-
“በኃጢአታቸው ምክንያት የቀደሙት እስራኤላውያን ለ40 ዓመታት ወደ ተስፋይቱ
ምድር መግባት አልቻሉም ነበር። እስራኤላውያን የእግዚአብሔር ተቃራኒ ነበሩ።
ተጠራጠሩት፣ አጉረመረሙም። ተመሳሳይ ኃጢአቶች የዘመኑን እስራኤላውያን
ለብዙ ዓመታት ሰማይን እንዳይወርሱ አድርገዋቸዋል። ይህ ችግር በእግዚአብሔር
ስህተት የመጣ አይደለም። የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ሥራዋን ብትሰራ ኖሮ፣
በምድር የሚኖር ሁሉ ከዚህ ጊዜ በፊት የማስጠንቀቂያው መልዕክት ይደርሰው
ነበር። ኢየሱስም በኃይልና በክብር ወደ ምድራችን በመጣ ነበር።”— ኤለን ጂ.
ዋይት፣ የመጨረሻ ቀን ክስተቶች፣ ገጽ 38። ዛሬም ተመሳሳይ በሆኑ ኃጢአቶች
በደለኛ የምንሆነው በየትኞቹ መንገዶች ነው?