የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ኤፌ. 3:1፣ 2 ቆሮ. 4:7–12፣ ሐዋ. 9:16፣ ፊልሞና 1:15, 16፣ ፊል. 1፡1-3
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ
እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ” (ፊል.4፡4)።
አንድ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቄስ ባልሠራው ወንጀል ተያዘ። ቄሱ ለሁለት
አመታት ያህል ታሰረ። በመጀመሪያ ላይ ቄሱ አዝኖና ግራ ተጋብቶ ነበር።
እግዚአብሔር ይህ ክፉ ነገር እንዲደርስበት ለምን ፈቀደ? እግዚአብሔር
ለእሱ አይጠነቀቅለትም እንዴ? ብዙም ሳይቆይ እግዚአብሔር ቄሱን ሰዎችን ለማዳን
ወደ እስር ቤት እንደላከው ተረዳ! እስረኞቹ ቄሱ ማን እንደሆነ ሲያውቁ፣ እንዲሰብክ
ጠየቁት። ስለዚህ ቄሱ ስለ ኢየሱስ መልካሙን የምስራች ሰበከላቸው። በተጨማሪም
ቄሱ ለእስረኞቹ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስረዱ መጽሔቶችን ሰጣቸው። እስረኞቹን
አጥምቆ የጌታን እራት ሰጣቸው። ቄሱም እንዲህ አለ፡- “አንዳንድ ጊዜ በእስር ቤት
ውስጥ መስራት አስቸጋሪ ነበር። ሆኖም ግን በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ጌታ የሰዎችን
ህይወት ሲለውጥ ሳይ ደስ አለኝ። እግዚአብሔርም ጸሎቴን ሲመልስ አየሁ።”
ጳውሎስና ሲላስም ባልሠሩት ወንጀል ተከሰው ነበር። እነሱም ወደ እስር ቤት
ተወረወሩ። የወኅኒውም ኃላፊ “እግራቸውን በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው” (ሐዋ.
16:24)። በእስር ቤት እያለ፣ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ እና በቆላስይስ ከተሞች ላሉ የቤተ
ክርስቲያን አባላት ደብዳቤ ጻፈላቸው (ፊል. 1፡7ን እና ቆላ. 4፡3 ያንብቡ)።
በዚህ ሳምንት፣ ጳውሎስ በእስር ላይ በነበረ ጊዜ ያጋጠመውን እንመለከታለን።
ጳውሎስ በእስር ቤት ሆኖ መሰቃየቱ፣ እግዚአብሔር ለህይወቱ ያለውን እቅድ ለማየት
ረድቶታል። የጳውሎስ ምሳሌ በአስቸጋሪ ጊዜያትም እግዚአብሔርን እንዴት ማገልገል
እንዳለብን ያስተምረናል።
*የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።
ጳውሎስ በፊልጵስዩስና በቆላስይስ ለሚኖሩ ሰዎች ደብዳቤ ጻፈላቸው። ጳውሎስ
በእስር ቤት ሆኖ ስለጻፋቸው፣ መልዕክቶቹ የወኅኒ ደብዳቤዎች ተብለው ይጠራሉ።
በተጨማሪም ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች እና ለፊልሞና በእስር ቤት እያለ ደብዳቤ ጽፎላቸዋል።
አብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊህቃን፣ ጳውሎስ የፊልጵስዩስን እና የቆላስይስን መልዕክቶች
በሮም ሳለ ከ60-62 ዓ.ም አካባቢ እንደጻፋቸው ያምናሉ (ሐዋ. 28፡16ን ያንብቡ)።
ኤፌ. 3፡1ን እና ፊልሞና 1ን ያንብቡ። ጳውሎስ ስለ እስር ቤት ቆይታው ምን ተናገረ?
ጳውሎስ ኢየሱስን ለማገልገል ሕይወቱን ሁሉ ሰጠ። እግዚአብሔር ለጳውሎስ
ያለው እቅድ እስረኛ መሆንን የሚጨምር ከሆነ፣ ጳውሎስ ለዚያም ዝግጁ ነበር።
ጳውሎስ ለምን እንደታሰረ ምክንያቱን ሲነግረን፡- “ስለ ወንጌልም በሰንሰለት መልእክተኛ
ሆንሁ” ይለናል (ኤፌ. 6:20)። ጳውሎስ ከመታሰሩ በፊት፣ ወደ ተለያዩ ቦታዎች እየተጓዘ
ይሰብክ ነበር። አብያተ ክርስቲያናትን ይመሰርት እና ለእግዚአብሔርም ሥራ ሠራተኞችን
ያሰለጥን ነበር። ምናልባት ጳውሎስ “ለምን ታሰርሁ? ነጻ ብሆን ኖሮ ለእግዚአብሔር
እጅግ ብዙ አገለግል ነበር!” ብሎ አስቦ ሊሆን ይችላል። በኋላም ጳውሎስ ለሁለተኛ ጊዜ
ወደ እስር ቤት ገባ። በዚያም እያለ 2ኛ ጢሞቴዎስን ጻፈ። ስለዚህ ጳውሎስ በእስር ቤት
ሆኖ ቢያንስ አምስት የአዲስ ኪዳን ደብዳቤዎችን ጽፏል።
ጳውሎስ እስረኛ የነበረበትን ከተማ ስም አልነገረንም። አንዳንድ የመጽሐፍ
ቅዱስ ሊህቃን ጳውሎስ በኤፌሶን ወይም በቂሳርያ እስረኛ እንደነበረ ይናገራሉ። ነገር
ግን ጳውሎስ በኤፌሶን ታስሮ እንደነበረ የሚያረጋግጥ ምንም አይነት የመጽሐፍ ቅዱስ
ማስረጃ የለም። ጳውሎስ በቂሳርያ እስረኛ ነበር? አዎን፣ ቢሆንም ጳውሎስ መጀመሪያ ወደ
ቂሳርያ በሄደበት ወቅት አደጋ ላይ አልነበረም። በኋላ ግን ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች
ሲጽፍላቸው፣ ህይዎቱ በእርግጥ አደጋ ውስጥ ነበር (ፊል. 1፡20ንና ፊል. 2፡17ን ያንብቡ)።
ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች የጻፈው ደብዳቤ፣ የት ታስሮ እንደነበር ፍንጭ
ይሰጠናል። በመጀመሪያ ጳውሎስ ልዩ ስለነበረ ቤተ መንግሥት ይናገራል። ይህ ቤተ
መንግስት የአካባቢው ገዥ መኖሪያ ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ወደ እየሩሳሌም ቤተ
መንግሥት ተወስዶ ጲላጦስ ፈርዶበት ነበር (ማቴ. 27፡27፣ ዮሐ. 18፡33)። ጳውሎስ እስረኛ
ሆኖ በተላከበት በቂሣርያም ልዩ ቤተ መንግሥት ነበረ (ሐዋ. 23፡35)። ነገር ግን ጳውሎስ
‘ልዩ ቤተ መንግስት’ የሚሉትን ቃላት ለቦታ ስያሜ አልተጠቀመባቸውም። ጳውሎስ
እነዚህን ቃላት ሰዎች ለማለት ይጠቀምባቸዋል። ስለ ኢየሱስ የተማሩ 9,000 የሚሆኑ
የሮም ጠባቂዎችን ያመለክታል (ፊል. 1፡13)። እነዚህ ወታደሮች ከሮማውያን ሠራዊት
ውስጥ በጣም ጀግና ተዋጊዎች ነበሩ። እነሱ የሮምን ንጉሥ እና እስረኞችን ይጠብቁ ነበር።
ሁለተኛ ጳውሎስ “በንጉሡ ቤት ከሚኖሩ ክርስቲያኖች” ሰላምታ ልኮላቸዋል (ፊል. 4፡22)።
ስለዚህ ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች መልዕክቱን በጻፈ ጊዜ በሮም እስረኛ ነበር ማለት ነው።
ጳውሎስ በቤተ መንግስት ውስጥ ከሚኖሩ እና ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ግንኙነት ነበረው።
ጳውሎስ በመቄዶንያ ሳለ ብዙ ጊዜ ታስሮ እንደነበር ተናግሯል (2 ቆሮ. 6:5፣
2 ቆሮ. 11:23፣ 2 ቆሮ. 7:5)። ለመጀመሪያ ጊዜ የታሰረው በፊልጵስዩስ ነበር (ሐዋ. 16፡
16-24)። በኋላም በኢየሩሳሌም ለጥቂት ጊዜ ታስሮ ነበር። ከዚያም በቂሣርያ ወኅኒ ቤት
እንዲታሰር ተላከ።
በሌላ ቦታ፣ ጳውሎስ ‘በሰንሰለት ስለ መታሰሩ’ ተናግሯል (ፊልሞና 1:10, 13)።
ጳውሎስ በሮም እስረኛ በነበረበት ጊዜ ይኖር የነበረው በቤት ውስጥ ነበር። እዚያ እያለ
ከወታደር ጋር በሰንሰለት ታስሮ ነበር። ይህ ወታደር በሮማውያን ጦር ውስጥ ምርጥ ተዋጊ
ከሆኑት ልዩ ወታደሮች አንዱ ነበር። በ300ዎቹ ዓ.ም ኢግኔሼየስ የሚባል ክርስቲያንም ከአንድ
የሮም ወታደር ጋር በሰንሰለት ታስሮ ነበር። ኢግኔሼየስ የወታደሮቹን ባህሪይ አስመልክቶ
ሲናገር “እንደ ዱር አራዊት ይሆኑ ነበር። ሰዎች መልካም ሲሆኑላቸው ደግሞ ከእንሰሳም
የከፋ ባህሪይ ያሳዩ ነበር” በማለት ተናግሯል።— Michael W. Holmes, editor, The Ap-
ostolic Fathers (Grand Rapids, MI: Baker Academic, 2007), page 231, adapted
ጳውሎስ በአስቸጋሪ ጊዜያት ሲሠቃይ እንዲበረታ የረዳው ምን ነበር? 2 ቆሮ. 4፡
7-12ን ያንብቡ።
ጊዜው ሲከፋ ጳውሎስ ሁልጊዜ ተስፋና እምነት ነበረው። ተስፋውና እምነቱ
እንዲጸና አበረቱት። ሰይጣን ጳውሎስ እንዲሰቃይና ተስፋ እንዲቆርጥ የሚችለውን ሁሉ
አደረገ። ጳውሎስ ግን እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር እንደሆነ ያውቅ ነበር።
ጳውሎስ በአስቸጋሪ ጊዜያት እንዲጸና የረዱት መንፈሳዊ በረከቶች ምንድን ናቸው? 2
ቆሮ. 6፡3-7ን ያንብቡ።
ብዙ ጊዜ ያለፍንባቸውን ድክመቶቻችንን እንመለከታለን። ደካማ መሆናችንን
እናውቃለን። በዙሪያችን የሚሆኑትን አስከፊ ነገሮች እየተመለከትን ተስፋ እንቆርጣለን።
በእነዚህ ጊዜያት፣ እግዚአብሔር ይሳካልን ዘንድ የሰጠንን ስጦታዎች ሁሉ ማስታወስ
አለብን። እግዚአብሔር ከሰጠን ስጦታዎች መካከል ዋነኛው መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ሰዎች ስህተት እንድንማር ይረዳናል። በተጨማሪም መጽሐፍ
ቅዱስ ሰዎች ከክፉ ጋር የነበራቸውን ተጋድሎ እንዴት ድል እንዳደረጉት ያስተምረናል።
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስንም ይሰጠናል። መንፈስ ቅዱስ “የአዳኛችንን ዓይነት
ህይወት እንድንኖር ይረዳናል። መንፈሱ ልባችንን ንጹህና ቅዱስ ያደርገዋል። መንፈሱ
በልባችን ውስጥ እግዚአብሔርን እንድንመስል ይረዳናል። በልባችን ውስጥ ካለው
ከማንኛውም ኃጢአትና ክፋት ጋር በምናደርገው ተጋድሎ እናሸንፍ ዘንድ ኢየሱስ
መንፈሱን ሰጠን። መንፈሱ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ሕይወቱና በፍቅሩ
እንድትሞላ ይረዳታል።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 671።
በሁለተኛው ዙር የጳውሎስ የስብከት ጉዞ ወቅት፣ ጢሞቴዎስ የጳውሎስን
ቡድን ተቀላቀለ። ብዙም ሳይቆዩ፣ መንፈስ ቅዱስ እነ ጳውሎስን ትንሿን እስያ
(አናቶሊያን) እንዳይሻገሩ ከለከላቸው (ሐዋ. 16፡6)። ትንሿ እስያ የዛሬዋ ቱርክ ናት።
በዚያ ሌሊት ጳውሎስ ሕልም አየ። በሕልሙም ጳውሎስ “አንድ የመቄዶንያ ሰው ወደ
መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው” አየ (ሐዋ. 16፡6)። ወዲያው ጳውሎስና
ጓደኞቹ ከጢሮአዳ ተነስተው በመርከብ ተጓዙ። የጳውሎስ ቡድን ሲላስን፣ ጢሞቴዎስን
እና ሉቃስን ያካተተ ነበር። ሉቃስ ከእነርሱ ጋር የተቀላቀለው በጢሮአዳ ነበር (ሐዋ. 16፡
11)። ጳውሎስና የቡድኑ አባላት የኤጂያን ባህርን አቋርጠው በአውሮፓ ወደምትገኘው
ናጱሌ ደረሱ። ግን እዚያ አልሰበኩም። ከዚያም ቡድኑ ወደ ፊልጵስዩስ ሄደ። ፊልጵስዩስ
በመቄዶንያ ወሳኝ ከተማ ነበረች (ሐዋ.16: 12)። በተጨማሪም ፊልጵስዩስ በሮም
መንግሥት ውስጥ በጣም ከተከበሩ ከተሞች አንዷ ነበረች። የፊልጵስዩስ ዜጎች፣
በጣሊያን ይኖሩ እንደነበሩት ሮማውያን፣ መምረጥና የመሬት ባለቤት መሆን ይችሉ
ነበር። በተጨማሪም የፊልጵስዩስ ሰዎች የተወሰኑ የግብር አይነቶችን አይከፍሉም ነበር።
በፊልጵስዩስ ከተማ የተወለደ ማንኛውም ሰው የሮም ዜጋ ነበር። ፊልጵስዩስ ሮምን
ከምሥራቁ ጋር በሚያገናኘው በቪያ ኤግናቲያ መንገድ ላይ ወሳኝ ማረፊያ ቦታ ነበረች።
ስለዚህ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን መመስረት ፈለገ። በዚህ ከተማ ውስጥ
ያለች ቤተ ክርስቲያን ለጳውሎስና ለቡድኑ አባላት በአቅራቢያው ላሉት ሌሎች ከተሞች
መልካሙን የምሥራች ለማካፈል ትረዳቸዋለች። ከእነዚህ ከተሞች መካከል አንዳንዶቹ
አምፊጶል፣ አጶሎንያ፣ ተሰሎንቄ እና ቤርያ ናቸው (ሐዋ. 17:1, 10ን ያንብቡ)።
በጳውሎስ ዘመን የፊልጵስዩስ ሰዎች የላቲን ቋንቋ ይናገሩ ነበር። ነገር ግን ሕዝቡ
በገበያ ቦታና በፊልጵስዩስ ዙሪያ ባሉ ከተሞች የግሪክ ቋንቋ ይናገሩ ነበር። ጳውሎስና
ጓደኞቹ ከሰዎች ጋር ይጸልዩ ዘንድ በወንዝ ዳር እንዴት እንደተገናኙ ሉቃስ ይነግረናል።
በዚያም ልድያ እና በቤቷ ውስጥ ይኖሩና ይሠሩ የነበሩ ሰዎች ክርስቲያኖች ሆኑ (ሐዋ. 16፡
13-15)። ልድያ ቀይ ሐር የምትሸጥ ነጋዴ ነበረች። ልድያም የጳውሎስን ሥራ ለመደገፍ
ገንዘቧን ትጠቀምበት ነበር። ጳውሎስና ሲላስ በፊልጵስዩስ በቆዩበት ወቅት፣ በወኅኒ
ቤት ታስረው ነበር። የእስር ቤት ቆይታቸው ደግሞ፣ የእስር ቤቱን ጠባቂ ክርስቲያን
እንዲሆን አድርጎታል። እሱ ብቻ ሳይሆን፣ የቤተሰቡም አባላት ሁሉ ክርስቲያኖች ሆኑ!
ፊልጵስዩስ ለቤተ ክርስቲያን ወሳኝ ከተማ ነበረች። በፊልጵስዩስ የተመሰረተችው ቤተ
ክርስቲያን፣ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በአውሮፓ መልካሙን ምሥራች እንዲሰብኩ
ረድታቸዋለች። በእርግጥ ጳውሎስ እና ጓደኞቹ በእምነታቸው ምክንያት በፊልጵስዩስ
መከራን ተቀብለዋል። ነገር ግን እግዚአብሔር የእኛን ስቃይ የሰዎችን ልቦና በወንጌል
ለመንካት ሊጠቀመው ይችላል።
ሐዋ. 9:16ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ የጳውሎስን መከራ ለማስተዋል እንዴት ይረዳናል?
ጥቅሱ እኛንስ እንዴት ያደፋፍረናል?
መጽሐፍ ቅዱስ ጳውሎስ የቆላስይስን ከተማ እንደጎበኘ አይናገርም። ነገር ግን
ኤጳፍራ በዚያ ይኖር እንደነበር እናውቃለን (ቆላ. 4፡12)። ኤጳፍራም በቆላስይስ ስለ
ኢየሱስ መልካሙን ምሥራች ያካፈለ የመጀመሪያው ሰው ነበር (ቆላ. 1፡7)። ኤጳፍራ
እንዴት ክርስቲያን ሊሆን ቻለ? መልሱን በእርግጠኝነት አናውቀውም። ምናልባት
ኤጳፍራ ክርስቲያን የሆነው፣ ጳውሎስ በአቅራቢያው በኤፌሶን ሳለ በ50ዎቹ አጋማሽ
ላይ ሊሆን ይችላል። በጳውሎስ አገልግሎት ምክንያት፣ “በእስያ የኖሩት ሁሉ አይሁድም
የግሪክ ሰዎችም የጌታን ቃል ሰምተዋል” (ሐዋ. 19፡10፣ ከሐዋ. 20፡31 ጋር ያነጻጽሩ)።
የዮሐንስ ራእይም የኢየሱስ ተከታዮች መልካሙን የምሥራች በእስያ ላሉ ሁሉ
እንዳካፈሉ ይነግረናል (ራእይ 1:4)። ለስኬታቸው ምክንያቱ ምን ነበር? የጳውሎስ
ስብከት ነበር። ሰዎች የጳውሎስን መልእክት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሙት በኤፌሶን ነበር።
ኤፌሶን በትንሿ እስያ ውስጥ ወሳኝ ከተማ እና ትልቅ የባህር ወደብ ነበረች። ኤጳፍራ
ጳውሎስ በኤፌሶን ሲሰብክ ሰማ። ኤጳፍራም ከጳውሎስ የሥራ አጋሮች አንዱ ሆነ።
ከዚያም ኤጳፍራ ወደ ቤቱ ወደ ቆላስይስ ተመልሶ መልካሙን የምስራች በዚያ አካፈለ።
የቆላስይስ ከተማ ከሎዶቅያ በስተደቡብ ምስራቅ በ15 ኪ.ሜ ርቀት ትገኛለች።
የከርሰ ምድር ተመራማሪዎች አሁን በቆላስይስ መቆፈር ጀምረዋል። ስለዚህ በዚህ ጊዜ
ስለ ከተማዋ ብዙ ነገሮችን አናውቅም። እስከ 10,000 የሚደርሱ አይሁዶች በዚያ የአገሪቱ
ክፍል ይኖሩ እንደነበር እናውቃለን። በቆላስይስ ይገበያዩባቸው የነበሩት ሳንቲሞች
በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ብዙ አማልክትን ያመልኩ እንደነበር ያሳያሉ። ስለዚህ ክርስቲያኖች
በቆላስይስ መልካሙን የምሥራች ለሌሎች ለመናገር ተቸግረው ነበር። በተጨማሪም
ክርስቲያኖች በዚያች ከተማ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው ለመኖር ተቸግረው ነበር።
ፊልሞና በቆላስይስ ይኖር የነበረ ሌላኛው ክርስቲያን ነበር። ምናልባት ፊልሞና ከኤጳፍራ
ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ክርስቲያን ሆኖ ሊሆን ይችላል።
ፊልሞና 1:15, 16ን ያንብቡ። በተጨማሪም ቆላ. 4:9ን ያንብቡ። ጳውሎስ
ፊልሞናን ለአናሲሞስ ምን እንዲያደርግለት ጠየቀው?
የሮም ሕግ ጳውሎስ አናሲሞስን ወደ ፊልሞና መልሶ መላክ እንዳለበት
ይደነግጋል። አናሲሞስ ባሪያ ነበር። ሆኖም ጳውሎስ ፊልሞናን፣ ለአናሲሞስ እንዲራራለት
ጠየቀው። በተጨማሪም ፊልሞና አናሲሞስን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሙ እንደሆነ
አድርጎ እንዲቆጥረው ጠየቀው (ፊልሞና 1፡16)።
በእርግጥ የባርያ ስርዓት ክፉ ነው። ጳውሎስ አናሲሞስ አርነት እንዲወጣ እንዲፈቅድለት
ለፊልሞና ቢነግረው እንመኝ ነበር። (በአሜሪካ የባርያ ስርዓት ወቅት፣ ኤለን ጂ. ዋይት
ለሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች፣ የኮብላይ ባሪያ ህግን እንዳይታዘዙ ተናግራለች። ይህ
ህግ ሰዎች የኮበለሉ ባሪያዎችን ወደ ጌታቸው እንዲመልሱ ያዝዛል።) ታዲያ ጳውሎስ
ለፊልሞና የሰጠውን ምክር እንዴት ልንረዳው ይገባል?
ፊል. 1:1-3ን እና ቆላ. 1:1, 2ን ያንብቡ። መጽሐፍ ቅዱስ በፊልጵስዩስ እና በቆላስይስ ስላሉት አብያተ ክርስቲያናት ምን ይነግረናል? ለምንድነው ይህ መረጃ በጣም አስፈላጊ የሆነው?
ጳውሎስ ብዙ ጊዜ በመልእክቶቹ ክርስቲያኖችን ቅዱሳን ብሎ ሰላምታ
ያቀርብላቸዋል፤ ምክንያቱም በጥምቀት ቤተ ክርስቲያንን ተቀላቅለዋልና። ጥምቀት
ከአሮጌ ኑሯቸው ተላቀው የተለዩ የእግዚአብሔር ሕዝቦች መሆናቸውን ያሳያል። በብሉይ
ኪዳንም እግዚአብሔር እስራኤላውያንን የተለዩ ሕዝቦች እንዲሆኑ መርጧቸዋል።
እግዚአብሔር ወንድ እስራኤላዊያንን ምልክት ይሆን ዘንድ እንዲገረዙ አዘዛቸው።
መገረዝ ማለት የወንድ ብልት ሸለፈትን መቁረጥ ማለት ነው። ይህ ምልክት እስራኤላውያን
ከአህዛብ ተለይተው የእግዚአብሔር መሆናቸውን ያሳያል። እግዚአብሔር እስራኤልን
የተለዬ ርስቱ አደረገው። እስራኤላውያንም ቅዱስ ህዝብ እንዲሆኑለት ፈለገ (ዘጸ. 19:5,
6ን ከ1 ጴጥ. 2:9, 10 ጋር ያስተያዩ)። በተመሳሳይም እግዚአብሔር ክርስቲያኖችን ቅዱሳን
እንዲሆኑ ይፈልጋል። ጥምቀት የእግዚአብሔር መሆናችንን ያሳያል።
ጳውሎስ በመልእክቶቹ ላይ በፊልጵስዩስ እና በቆላስይስ ለሚገኙ ክርስቲያኖች
ያቀረበውን ሰላምታ እናስተያይ። ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ላሉ “ሽማግሌዎችና ዲያቆናት”
ደብዳቤ ጽፎላቸዋል (ፊል. 1፡1)። እንዲሁም ጳውሎስ በቆላስይስ ለሚኖሩ “በክርስቶስ
ቅዱሳንና ታማኝ ለሆኑ ወንድሞች” ጽፏል (ቆላ. 1፡2)። አዲስ ኪዳን ስለ “ታማኝ
ወንድሞች” ሲናገር፣ እነዚህ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለእግዚአብሔር የተለየ ሥራ
እንደሚሠሩ እንረዳለን (ኤፌ. 6፡21ን፣ ቆላ. 4፡7ን እና 1 ጴጥ. 5፡12 ያንብቡ)። ስለዚህ
ጳውሎስ እየተናገረ ያለው በፊልጵስዩስ እና በቆላስይስ ላሉ የቤተ ክርስቲያን አባላት እና
መሪዎች ነው። በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ እነዚህ መሪዎች በቤተክርስቲያን
ውስጥ ስለሚያከናውኑት ሥራ እንማራለን (1 ጢሞ. 3፡1-12ን እና ቲቶ 1፡5-9 ያንብቡ)።
እነዚህ የተለያዩ ሚናዎች፣ አመራር ከመጀመሪያው ጀምሮ ለእግዚአብሔር ቤተ
ክርስቲያን አስፈላጊ እንደነበረ እንድናስተውል ይረዱናል።
ጳውሎስ ጢሞቴዎስን፣ ኤጳፍራን እና ሌሎች ክርስቲያኖችን የአጥቢያ አብያተ
ክርስቲያናት መሪዎች እንዲሆኑ አሠልጥኗቸዋል። ጳውሎስ መሪዎችን ማሠልጠን
አስፈላጊ ሥራ እንደሆነ ያስብ ነበር። እነዚህ መሪዎች ጳውሎስ በከተሞች ውስጥ
መልካሙን የምሥራች እንዲሰብክ ረድተውታል። ጳውሎስ ወንጌልን ለማካፈል እና ለቤተ
ክርስቲያን አመራር እቅድ ነበረው። የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ፈር ቀዳጆችም ይህንን
እቅድ ተከትለዋል። ጳውሎስ በፊልጵስዩስ እና በቆላስይስ ላሉት አብያተ ክርስቲያናት
መልክት ከመጻፉ ከረጅም ጊዜ በፊት፣ በኢየሩሳሌም የነበረችው ቤተ ክርስቲያንም
ይህንን እቅድ ተግብራው ነበር (ሐዋ. 6፡1-6ን እና ሐዋ. 11፡30ን ያንብቡ)። የኢየሩሳሌም
ቤተ ክርስቲያን “ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ሊከተሉት የሚገባቸው የአመራር አርአያ
ነበረች።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የሐዋርያት ሥራ፣ ገጽ 91።
“እግዚአብሔር የመረጣችሁ እንድትድኑ ነው። ሊቀድሳችሁም
ይፈልጋል። በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ያላችሁ እምነት ቅዱሳን ያደርጋችኋል። ስለዚህ
ጽኑ።... እግዚአብሔርን የምትታዘዙ ከሆነ፣ ሰዎች በእምነታችሁ ምክንያት ያሳድዷችኋል።
ሰዎች ሲበድሏችሁ ተቆጥታችሁ መልሳችሁ አትበድሏቸው። በኢየሱስ ጽኑ። ሌሎች
ስለ እናንት ስለሚናገሩት ነገር አትጨነቁ። ሊያደርጉ የሚፈልጉትንም ነገር እንዳያደርጉ
ለመከልከል አትሞክሩ። ልባችሁን ከትዕቢት ሁሉ ባዶ አድርጉ። ሥራችሁን በሙሉ
ሃይላችሁ ሥሩ። ተስፋ አትቁረጡ። በጌታ ታመኑ። ሥራችሁ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
በዚህ ህይወት የዚህን ጥያቄ ምላሽ በፍፁም አታውቁትም ይሆናል። ነገር ግን ህይወታችሁ
ምን ያህል ዋጋ እንዳለው አሁኑኑ ማወቅ ትችላላችሁ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እናንተን
ለማዳን ልጁን ሰጥቷልና። ይህም እጅግ የከበራችሁ (ውድ) መሆናችሁን ያሳያል።
“እያንዳንዱ እውነተኛ ክርስቲያን አስቸጋሪ ጊዜያት ይገጥሙታል። ሰይጣን
በልባችሁ ውስጥ ኢየሱስን እንዳትመስሉ ይገዳደራችኋል። ነገር ግን ወደ መስቀሉ
ተመልከቱ። ወደ መስቀሉ ስትመለከቱ፣ አሸናፊ ትሆናላችሁ። ኢየሱስ ‘አልለቅህም
ከቶም አልተውህም’ ብሎ ይህንን ተስፋ ሰቶናል (ዕብ. 13: 5)። በተጨማሪም ‘እነሆ እኔ
እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ብሎናል (ማቴ. 28:20) ።” —ኤለን
ጂ. ዋይት፣ የወጣቱ አስተማሪ፣ ህዳር 9, 1899።
1. ጳውሎስ ብዙ ጊዜ ምንም የሰራው ስህተት ሳይኖር ወደ እስር ቤት ተወርውሯል።
ጳውሎስ ብዙ ጊዜ ምንም የሰራው ስህተት ሳይኖር ወደ እስር ቤት ተወርውሯል።
ሌሎች ሰዎች ለእናንተ ፍትሃዊ ሳይሆኑ ሲቀሩ ወይም ክፉ ሲያደርጉባችሁ ምን
ይሰማችኋል? በእንደዚህ አይነት አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ስታልፉ፣ የትኞቹ
የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋዎች ያበረቷችኋል?
2. ተርቱሊያን በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር። ሮማውያን ክርስቲያኖችን ሲጎዱአቸውና
ተርቱሊያን በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር። ሮማውያን ክርስቲያኖችን ሲጎዱአቸውና
ሲገድሉአቸው፣ ተርቱሊያን “በገደላችሁን ቁጥር እንዲሁ እንበዛለን፤ ደማችን ዘር
ነውና” አላቸው። ሆኖም ያኔም ሆነ አሁን በክርስቲያኖች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት፣
ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮዋን እንዳትፈጽም እንቅፋት ሆኗል። በእምነታቸው ምክንያት
መከራ የሚደርስባቸውን ክርስቲያኖች ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን?
3. ጳውሎስ ምን ያህል እንደተሰቃየ ያስቡ። አሁን የዚህን ሳምንት መሪ ጥቅስ ያንብቡ።
ጳውሎስ ምን ያህል እንደተሰቃየ ያስቡ። አሁን የዚህን ሳምንት መሪ ጥቅስ ያንብቡ።
“ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ” (ፊል. 4: 4) ማለት ምን ማለት ነው? እንዴትስ
ደስተኛ መሆን እንችላለን? የምትወዱት ሰው ቢታመም ወይም ቢሞትስ? ወይም
ሥራችሁን ብታጡስ? ወይም በከባድ ህመም ውስጥ ብትሆኑስ? እንደ ክርስቲያን፣
ሁልጊዜ ደስተኛ እንሆን ዘንድ ምክንያታችን ምንድን ነው?