የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተለውን ጥቅስ ያንብቡ፡- ቆላ. 3:1-14።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ
የሆነውን ፍቅርን ልበሱት” (ቆላ. 3: 14)።
“ሰማያዊ የሆኑ ነገሮችን አብዝታችሁ አትመኙ። ይህን ብታደርጉ ግን ከዚህ ምድር
ለሆነው ለማንኛውም ነገር አትጠቅሙም” የሚለውን አባባል ታውቁታላችሁ?
በእርግጥ አባባሉ የተወሰነ እውነታ አለው። ነገር ግን ጳውሎስ በቆላስይስ 3
ላይ አንድ ጠቃሚ ሀሳብ ያስተምረናል፡- ምድራዊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ የምንፈልግ ከሆነ፣
ለጌታ ምንም አንጠቅምም። ጳውሎስ ለዕለት ተዕለት ሕይወታችን ጠቃሚ መርሆዎችን
ያስተምረናል። እነዚህ መርሆዎች ከሰማይ የተላኩ ናቸው። እነዚህን መርሆዎች ማስተዋል
የሚችሉት ከኢየሱስ ጋር ከሙታን የተነሡ ሰዎች ብቻ ናቸው (ቆላ. 3፡1)። የጳውሎስ ምክር
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለንን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉንም ግንኙነታችንን ለማሻሻል
ይረዳናል። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች
ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም
መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን
ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና” (ማቴ. 5:44, 45)።
ጠላቶቻችንን መውደድ? ይህንን ማድረግ በጣም ከባድ ነውን? አዎን ሰብዓዊ ሰዎች ለሆነው
ለእኛ ይከብደናል። በእውነት ለእግዚአብሔር ከመኖራችን በፊት፣ ለራሳችን (ለእኔነታችን)
መሞት አለብን። ስለዚህ ስለ ሰማይ አሁን ከምናስበው በላይ ማሰላሰል አለብን። ያኔ የሰማዩ
አባታችን በዚህ ምድር ላይ መልካም እናደርግ ዘንድ ሊጠቀምብን ይችላል።
በዚህ ሳምንት ከኢየሱስ ጋር መኖር ነገሮችን አሁንም ሆነ ወደፊት እንዴት
ማሻሻል እንደሚችል እንማራለን።
*የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።
ጳውሎስ እንደ ክርስቲያን ሊኖረን ይገባል ያለው ምንድነው? እነዚህን ነገሮች ማድረጋችን፣ ሰማያዊ የሆኑትን ነገሮች ይበልጥ እንድንፈልግ የሚረዱን እንዴት ነው? ጳውሎስ የተናገረውን እንዲናገር ያደረገው ምክንያት ምን ይመስላችኋል? ቆላ. 3፡ 1-4ን ያንብቡ።
በቆላስይስ 3 ላይ ጳውሎስ በሰማይ ስላሉት ነገሮች ይናገራል። “እንግዲህ
ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ
ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ሞታችኋልና፥
ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና። ሕይወታችሁ የሆነ
ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ”
(ቆላ. 3፡1-4)።
በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የሚሆኑትን ብዙ ነገሮች መግለጽ አንችልም።
ክርስቲያኖች በእርግጥ “የሚሞቱት” እና በኢየሱስ ወደሚገኘው አዲስ ሕይወት
”የሚነሱት” እንዴት ነው? አካላቸው እንደ ቀድሞው ሆኖ፣ እውነተኛ የሞትና ህይወት
ልምምድ ሳይኖራቸው ይህ ለውጥ እንዴት ሊከሰት ይችላል? ያለ መንፈስ ቅዱስ
እርዳታ፣ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ወይም መንፈሳዊ ልምምዶችን ለማስተዋል
እንቸገራለን። እግዚአብሔር የሰጠንን የአዲስ ልብ ተስፋ ከተቀበልን ግን ከኢየሱስ
ጋር መነሳት ማለት ምን እንደሆነ ይገባናል። አንድ መዝሙር፡- “እርሱ ህያው እንደሆነ
እንዴት እንደማውቅ ብትጠይቁኝ፣ በልቤ ውስጥ ስለሚኖር ነው” ይላል።
ጳውሎስ ክርስቲያኖችን በቆላ. 3፡1-4 ላይ ያለውን ያዘዘበት አንድ አስፈላጊ
ምክንያት አለ። መንፈሳዊ ሕይወታችን በየዕለቱ መታደስ እንዳለበት ያውቃል (2 ቆሮ.
4፡16ን ያንብቡ)። እንደገና ኃጢአት በመሥራት ልንጠፋ እንችላለን! በዚህ ሕይወት
ከኃጢአት ፈተና ፈጽሞ ነፃ አይደለንም።
ስለዚህ “በላይ በሰማይ ያለውን ለመሻት” እና ያንኑ ለመኖር በየቀኑ መምረጥ
አለብን (ቆላ. 3፡1)። አዲሱ “ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር
ተሰውሮአልና” ይላል (ቆላ. 3፡3)። ሆኖም ሰዎች ክርስቲያኖች መሆናችንን የሚያውቁት
የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ውስጥ መኖሩን ስናሳያቸው ነው።
በአብዛኛው የሚያስቡት ስለ ሰማይ ነው ወይስ ስለ ምድራዊው ሕይወት? ስለ
ምድራዊው ሕይወት ነው ካሉ፣ ይህንን እንዴት ሊለውጡት ይችላሉ?
ቆላ. 3:5, 6ን እና ሮሜ 6:1–7ን ያንብቡ። ለእኔነትና ለሃጢያት የምንሞተው እንዴት ነው? በህይወታችን ክፉ ነገሮች መፈለግን እንዴት ልንተው እንችላለን? በተጨማሪም “በላይ ያለውን በመሻት” ለመኖር የምንችለው እንዴት ነው? (ቆላ. 3: 1)
በመጀመሪያ ከኢየሱስ ጋር መንፈሳዊ ሞትን መሞት አለብን። ከዚያም
በህይወታችን ክፉ ነገሮች መፈለግን ልንተው ይገባል። ሥጋችንና አእምሯችን ለእኛ
የማይበጁ ብዙ ነገሮችን ይፈልጉ ይሆናል። ስለዚህ ለእነዚያም ኃጢአቶች መሞት
ያስፈልገናል። ክፉ ነገሮችን ሁሉ ከህይወታችን ማስወገድ ይኖርብናል።
ከዚህ ትእዛዝ ጋር በተያያዘ ግን ሁለት ነገሮችን መረዳት አለብን። በመጀመሪያ
በቆላ. 3፡1 ላይ እንደምንመለከተው ከክርስቶስ ጋር ከተነሣን፣ በኢየሱስ ሕያዋን መሆን
አለብን። በእርሱ አዲስ ሕይወት መኖር አለብን። ሁለተኛ በቆላ. 3፡5 ላይ ያለው ትዕዛዝ
የሚፈጸመው በጌታ ሕያዋን ስለሆንን ነው። ክፉ ነገሮችን ከህይወታችን ማስወገድ
የምንችለው፣ የኢየሱስ ህይወት ስላለን ነው። ኃጢአትንና ክፋትን ከአእምሯችንና
ከሕይወታችን ለማስወገድ ኃይልን ይሰጠናል። “በእነዚህም ጠንቅ የእግዚአብሔር ቍጣ
በማይታዘዙ ልጆች ላይ ይመጣል” (ቆላ. 3: 6)።
መጽሐፍ ቅዱስ “የእግዚአብሔር ቁጣ” የሚለውን ሐረግ በሮሜ 1፡18 ላይ
በድጋሚ ይጠቀመዋል፡- “እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና
በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና”። “ስለዚህ እርስ
በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ
ሰጣቸው” (ሮሜ 1:24)። በእነዚህ ኃጢአቶች ምክንያት “ታላቁ የቁጣው ቀን ይመጣል”
(ራእ. 6:17)። ከዚያም “በእነዚህም ጠንቅ የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች
ላይ ይመጣል” (ቆላ. 3፡6)። በሮሜ 1፡18 ላይ ጳውሎስ ስለ “ሰዎች ኃጢአትና ዓመጽ”
ይናገራል (ሮሜ 1፡18)። “ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው” (ሮሜ 1፡24)።
እነዚህ ሰዎች በሥጋቸው የሚያደርጓቸው ያልተገቡ ነገሮች ምንድናቸው? “ስለዚህ
እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው
የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ
ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው
ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት
በራሳቸው ተቀበሉ” (ሮሜ 1:26, 27)። እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉት የፈጠራቸውን
አምላክ በመቃወማቸው ነው።
ቆላ. 3:6-11ን ያንብቡ። በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ የጳውሎስ መልእክት ምንድነው?
በቆላ. 3፡8 ላይ ያለው ቃል፣ ታላቅ ስለሆነው ከሞት ወደ ሕይወት ስለመለወጥ
ይናገራል። “እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ” (ቆላ. 3፡5)። “አሁን
ግን እናንተ ደግሞ ቍጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም
ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ” ይላል (ቆላ. 3: 8)። ሁሉም ቁጣ መጥፎ አይደለም።
እግዚአብሔር በኃጢአት ላይ ይቆጣል፤ ኢየሱስም እንዲሁ (ማር. 3:5፣ ራእ. 6:16)።
የእግዚአብሔር ቁጣ ግን ቅዱስ ነው። ሰዎች ስለሆንን፣ መጽሐፍ ቅዱስ “ተቆጡ
ኃጢአትንም አታድርጉ” በማለት ያስጠነቅቀናል (ኤፌ. 4፡26)። ለዚህም ነው ያዕቆብ
“ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም
የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና” ብሎ
የተናገረው (ያዕ. 1:19, 20)። አሮጌውን የኃጢአት ሕይወታችንን ትተነዋል (ቆላ. 3፡9)።
ስለዚህ አንዳችን ለሌላችን መዋሸት የለብንም (ከዘሌ. 19:11, 18 ጋር ያስተያዩ)።
ጳውሎስ ስለ አሮጌው ሰው ወይም ስለ አሮጌው ሕይወት ይናገራል። ያ ምን ማለት ነው?
ያስ ከአዲሱ ሕይወት ጋር እንዴት ይነጻጸራል? ሮሜ 6፡6ን እና ኤፌ. 4፡22–24ን
ያንብቡ።
ለእኔነት ስንሞት፣ እግዚአብሔር አዲስ ሕይወት ይሰጠናል። በልባችን ውስጥ
ሕጉን “ይጽፈዋል”። ያም ማለት እግዚአብሔር በልባችን ውስጥ ላለው ለሕጉ ፍቅር
እንዲኖረን ያደርገናል (2 ቆሮ. 3፡4-18)። እንድንታዘዘውም ኃይል ይሰጠናል።
እነዚህ ምሳሌአዊ አገላለጾች የኢየሱስ ስንሆን፣ እርሱ ሕይወታችንን አዲስ
እንደሚያደርገው እንድንገነዘብ ይረዱናል (2 ቆሮ. 5፡17)። “የፈጠረውንም ምሳሌ
እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል” (ቆላ.
3:10)። “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው” (ቆላ. 1፡15)። ኢየሱስ ክርስቶስ
እግዚአብሔር ማን እንደ ሆነ በሙላት ያሳየናል። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ስለ ኢየሱስ
ያስተምረናል። ኢየሱስን ስናውቀው፣ እርሱን “እንመስል ዘንድ” ይለውጠናል (2 ቆሮ.
3፡18)። ከዚያም ፍጹም የሆነውን ውበቱንና ፍቅሩን የበለጠ እናሳያለን (2 ቆሮ. 2፡18)።
የኢየሱስ ስንሆን፣ ሀብታም ሆንን ድሃ፣ አይሁዳዊ ሆንን አልሆንን ልዩነት አያመጣም።
ሁላችንም የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች እንሆናለን (ቆላ. 3፡11)።
የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንዴት መኖር አለባቸው? ቆላ. 3፡12-14ን ያንብቡ።
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር እስራኤልን የተለየ ሕዝቡ አድርጎ መርጦት
ነበር። እግዚአብሔር እስራኤልን እርሱ ማን እንደሆነ ለሰዎች እንዲያሳዩ ፈልጎ
ነበር። በተመሳሳይ መልኩ፣ ኢየሱስ ክርስቲያኖችን የራሱ የተለዩ ህዝቦች እንዲሆኑ
መርጧቸዋል (ቆላ. 3፡12)። አዲስ ሕይወት እንዲኖሩ ይጋብዛቸዋል። ሆኖም ሁሉም
ክርስቲያኖች ይህንን ግብዣ አይቀበሉትም። ኢየሱስ እንደሚናገረው “የተጠሩ ብዙዎች፥
የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው” (ማቴ. 22:14፣ ከማቴ. 24: 22, 24, 31 ጋር ያስተያዩ)።
ጳውሎስም ልክ እንደ ኢየሱስ ስለ ተመረጡ የእግዚአብሔር ህዝቦች ይናገራል (ሮሜ 8፡
33፣ 2 ጢሞ. 2፡10)። እግዚአብሔር ህዝቡን ይወዳቸዋል፤ ይቀድሳቸውማል (ዘዳ. 7፡
6-8)። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእርሱ የተለዬ ሥራ እንዲሰሩ ይሰጣቸዋል። ጴጥሮስ
“የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ ናችሁ” ብሏል (1 ጴጥ. 2፡9)።
ይህንንም የምናደርገው አሁን በምንኖረው ህይወት ሁኔታ ነው።
ጳውሎስ ምን ማድረግ እንዳለብን ይዘረዝራል:- “እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር
ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥
ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ። እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥
ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ። ክርስቶስ ይቅር
እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ። በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ
የሆነውን ፍቅርን ልበሱት” (ቆላ. 3፡12-14)። እነዚህን ነገሮች ማድረግ የምንችለው፣
ልባችን ከኢየሱስ ጋር ከተቆራኘ ብቻ ነው። ጳውሎስ እንድናደርግ የሚጠይቀን ነገሮች፣
ኢየሱስ ለእኛ የሚያደርግልን ነገሮች ናቸው። ስለዚህ እርስ በርሳችን መዋደድና ይቅር
መባባል አለብን። እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር፣ ሌሎችን በእውነት እንድንወድ
አቅም ይሰጠናል (1 ዮሐ. 4:11, 12)።
ጳውሎስ እንደተናገረው ስንኖር፣ ለሌሎች ሰዎች በረከት እንሆናለን።
ደስተኞችም እንሆናለን። ብዙ ሰዎች ፍቅርና አክብሮት የሚያሳዩን ስንወዳቸው ነው።
እግዚአብሔር እኛን በፍቅሩና በይቅርታው መሙላቱን ይቀጥላል (ማቴ. 5፡7፣ ማቴ.
6፡14)። የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሌሎች ሰዎች ስናሳይ፣ ለእርሱ ምስጋናንና ክብርን
እንሰጣለን። ሌሎች ሰዎች የእኛን ምሳሌ ሲመለከቱ፣ ኢየሱስን ለመከተል ሊመርጡ
ይችላሉ። “ራስ ወዳድነት የሌለበት ሕይወት ኃይል አለው። የእግዚአብሔርን ፍቅር
የሚያሳይ አፍቃሪ ክርስቲያን፣ ስለ ኢየሱስ የሚናገረው ወንጌል እውን መሆኑን ከምንም
ነገር በላይ ያረጋግጣል።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የፈውስ አገልግሎት፣ ገጽ 470።
ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰላምና አንድነት እንዲኖር ይፈልጋል (ቆላ.
3)። አስቀድመን ስለ እግዚአብሔር ሰላም ተመልክተናል (7ኛ ትምህርትን ያንብቡ)።
የኢየሱስ ሰላም ልባችንን መቆጣጠር ይኖርበታል። ይህም ሊሆን የሚችለው ኢየሱስ
ሕይወታችንን ከተቆጣጠረ ብቻ ነው።
ኢየሱስ ሕይወታችንን እንዲቆጣጠር ፈቃድ የሚሰጠው ምንድነው? በኢየሱስ ባገኘነው
አዲስ ሕይወት መዝሙር ምን ድርሻ አለው? ቆላ. 3:16, 17ን ያንብቡ።
ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ” ይላል (ቆላ. 3፡16)።
ኢየሱስ በልባችን ውስጥ መኖር ይፈልጋል። ይህም የሚሆነው የእግዚአብሔርን
ጥበብ እናውቅ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ነው። ሙዚቃም (መዝሙርም) ስለ
እግዚአብሔር እንድናውቅ በመርዳት ረገድ ትልቅ ድርሻ አለው (ቆላ. 3፡16)። ሆኖም
ማንኛውም ሙዚቃ አይደለም። ጳውሎስ ስለ ሙዚቃ ለመናገር በቆላ. 3፡16 እና
በኤፌ. 5፡19 ላይ በጣም ጥንቃቄ የተሞላበት ቃል ይጠቀማል። “በመዝሙርና በዝማሬ
በመንፈሳዊም ቅኔ” መዘመር አለብን (ቆላ. 3፡16፣ በተጨማሪም ኤፌ. 5፡19ን ያንብቡ)።
እነዚህ መዝሙሮች እግዚአብሔር የሚቀበላቸው ሙዚቃዎች (ዜማዎች) ናቸው።
መዝሙር ዝማሬ ወይም ግጥም ነው። የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ የሚባለው
በብሉይ ኪዳን የነበሩ የመዝሙሮችና የግጥሞች ስብስብ ነው። ዝማሬዎች ክርስቲያኖች
የዘመሯቸው የአዲስ ኪዳን መዝሙሮች ሊሆኑ ይችላሉ። መንፈሳዊ ቅኔዎች ደግሞ
ስለ መንፈሳዊ ሕይወት ወይም ስለ ቤተ ክርስቲያን ሕይወት የሚቀርቡ የምስጋና
መዝሙሮች ሊሆኑ ይችላሉ። የመዝሙሮቹ ቃላት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት
ያስተምራሉ። መዝሙሮች ሰዎችን እንደ ክርስቲያኖች እንዴት መኖር እንዳለባቸው
ያስተምራሉ። ባለፉት ጥቂት መቶ ዓመታት ውስጥ ብዙ ውብ ዝማሬዎች ተጽፈዋል።
እነዚህ ዝማሬዎች ድንቅ የተስፋ መልእክት አላቸው። ልባችንን ከፍ ያደርጉታል።
እርግጥ ነው ሙዚቃ ኃይል አለው። ዳዊት በገናውን ሲደረድር፣ ንጉሥ ሳኦል ጥሩ ስሜት
ይሰማው ነበር (1 ሳሙ. 16፡23)። ጥናቶች እንደሚያሳዩት አንዳንድ የሙዚቃ ዓይነቶች
ፈውስን የሚያመጡ ሊሆኑ ይችላሉ። ሙዚቃ ሰላም እንዲሰማን ሊያደርገን ይችላል።
በተጨማሪም ሙዚቃ አእምሮን የበለጠ በግልፅ እንዲያስብ ሊረዳው ይችላል።
እንዲሁም ሙዚቃ ዘና እንድንልና ህመምን እንድናሸንፍ ይረዳናል። ሙዚቃ ከሰዎች ጋር
ያለንን ግንኙነት ሊያሻሽለው ይችላል። ሙዚቃ መልካም ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል።
ግን ሀሳባችንንና ስሜታችንን ሊለውጥ እንደሚችል ሁላችንም ልንስማማ እንችላለን።
ትክክለኛ ሙዚቃ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበን ይችላል።
“እግዚአብሔር አብን በእርሱ (በኢየሱስ) እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ
የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት” (ቆላ. 3፡17)። አሁን በህይወትዎ
ይህንን እንዴት ይተገብሩታል? ካልሆነስ እንዴት ሊለወጡ ይችላሉ? በጌታ ስም ሊያደርጉት
የሚችሉት ነገር ካልሆነ፣ አሁን እያደረጉት ያሉት ግን ማቆም ያለብዎት ነገር ምንድነው?
“የእግዚአብሔር መንፈስ አእምሮአችንንና ልባችንን
ሲቆጣጠር፣ አዲስ ዝማሬ እንዘምራለን። እግዚአብሔር የሰጠንን ተስፋ እንደሚፈጽምልን
እንረዳለን። እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል፣ ከእኛም ያስወግደዋል። ከዚህ
በፊት ስለሠራነው ኃጢአት፣ የእግዚአብሔርንም ሕግ ስለ ተላለፍን፣ እናዝናለን።
በኢየሱስም እናምናለን። እርሱ እኛን ያነጻን ዘንድ ሞተ። ‘እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን
ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ
ከመጠን ይልቅ በለጠ’ (ሮሜ 5፡21)። ከኢየሱስ የተነሳ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን።
“የተቀደሰ ሕይወት ለመኖር ኃይል ያስፈልገናል። ያለዚያ ስለ ምድራዊ
ሕይወታችን እንጂ ስለ ሰማዩ መንግሥት ብዙም አናስብም። . . .
“ክርስቲያኖች እግዚአብሔር እንዲሆኑ የሚፈልገውን ለመሆን ጥረት ማድረግ
አለባቸው። ቢሳሳቱ ግን መተከዝ የለባቸውም። እግዚአብሔር ሊያነጻንና ሊቀድሰን ቃል
ገብቶልናል። ፍቅሩንና ይቅርታውን ይሰጠናል። እኛን ይረዳን ዘንድ የኢየሱስን ኃይል
እንደሚሰጠን ቃል ገብቷቶልናል። ኢየሱስ ንጹህና ቅዱስ ለመሆን የሚያስፈልገንን ኃይል
ሁሉ ይሰጠናል። ሕይወት ሁሉ የሚጀምረው በኢየሱስ ነው። . . . ኢየሱስ ይረዳናል፤
ረድኤትንም ከሰማይ ይልክልናል። ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ በምናደርገው ጥረት ሁሉ፣
ሕያው የሆነ ኃይሉን እናገኛለን።”—ኤለን ጂ ዋይት፣ የሐዋርያት ሥራ፣ ገጽ 476–478።
1. ጳውሎስ “ሰው በእምነት ይጸድቃል” ይላል (ሮሜ 3፡28) ። ይህንን ተስፋ
ጳውሎስ “ሰው በእምነት ይጸድቃል” ይላል (ሮሜ 3፡28) ። ይህንን ተስፋ
በተመለከተ ልምምድዎ ምን ይመስላል? ይህ አስደናቂ ተስፋ ሕይወትዎን እንዴት
ነው የለወጠው? ይህ ተስፋ በኢየሱስ አዲስ ሕይወት መኖር የሚለው ሀሳብ ምን
እንደሆነ ለማስተዋል የሚረዳዎት እንዴት ነው?
2. በሰማይ ያሉትን ነገሮች አብዝቶ መሻት ማለት ለእርስዎ ምን ማለት ነው? በዚህ
በሰማይ ያሉትን ነገሮች አብዝቶ መሻት ማለት ለእርስዎ ምን ማለት ነው? በዚህ
ምድር ላይ መልካም ነገርን ከማድረግ ይልቅ በሰማይ ያሉትን ነገሮች መፈለግ
ይበልጣልን? መልስዎን ያስረዱ።
3. ህይወትዎ የሌሎችን ሰዎች ህይወት፣ ለመልካምም ሆነ ለመጥፎ፣ እንዴት
ህይወትዎ የሌሎችን ሰዎች ህይወት፣ ለመልካምም ሆነ ለመጥፎ፣ እንዴት
እንደሚለውጥ ያስቡ። እንደ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወታችንስ ምን
ይመስላል? የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን በዙሪያችን ያለውን ማኅበረሰብ ወደ ተሻለ
ህይወት እንዴት ልትለውጠው ትችላለች?
4. ቆላ. 3:11ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ እንደ ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ሊኖረን
ቆላ. 3:11ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ እንደ ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ሊኖረን
ስለሚገባው ሰላምና አንድነት ምን ይነግረናል?