የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዳንኤል 4፣ 2 ነገስት 5:1-19፣ ዮሐንስ 3:1-12፣ ዮሐንስ 7:43-52፣ ማቴ. 19:16-22፣ ዮሐንስ 19፡38-42።
መግቢያ ጥቅስ፡- “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅ
መዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?” (ማቴዎስ 16:26)።
መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው ከብዙ ዓመታት በፊት ቢሆንም እግዚአብሔር ግን
ለዓለማችን የእውነትን መገለጥ አሳየበት። እና ከገለጣቸው ብዙ እውነቶች
መካከል አንዱ የሰው ተፈጥሮ ነው። በሰባተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ያለ
አይሁዳዊም ሆነ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ላይ ያለ ብራዚላዊ ሰው መሠረታቸው
አንድ ነው፡ መለኮታዊ ጸጋ የሚያስፈልጋቸው ኃጢአተኞች።
ይህ ደግሞ ሀብታም እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን (ኃያላንን) ያካትታል። በተለይም
ሀብትን፣ ዝናንና ሥልጣንን ከማሳደዳቸው አንፃር እንዲሁም ብዙ ጊዜ (ሁልጊዜም
ባይሆን) አቅመ ደካሞችን ከመጨቆናቸው አንፃር በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበሩ
ሀብታሞችና ኃያላን በዘመናችን ካሉት ሀብታሞችና ኃያላን አይለዩም። እንዲህም ቢሆኑ
እግዚአብሔር ለደካሞችና ለችግረኞች እንደሚያስብ ሁሉ ለሀብታሞችና ለኃያላን
መዳንም ያስባል። መጽሐፍ ቅዱስ ኃያላንና ሀብታም የሆኑ ሰዎችን ለአሕዛብ በረከት
እንዲሆኑ እግዚአብሔር እንዴት እንደተጠቀመባቸው የሚገልጹ አንዳንድ ምሳሌዎችን
ይዘረዝራል፦ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ኢዮብ፣ ሰሎሞን እና ዮሴፍ በስም ሊጠቀሱ የሚችሉ
ምሳሌዎች ናቸው።
በዚህ ሳምንት ለሀብታሞች እና ኃያላን ያለውን የእግዚአብሔር ተልዕኮ
እንመረምራለን። እግዚአብሔር ከእነዚህ ሰዎች መካከል የተወሰኑትን እንዴት እንደደረሰ
እና ለእነሱም ዛሬ ምስክር እንዲሆኑ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችን እንዴት እየጠራ እና
እያዘጋጀ እንደሆነ እያየን አብረን እንጓዝ።
*ለህዳር 22 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስትነታችን፣ “ያልተገደበ ስርየት” ተብሎ
በሚታወቀው ነገር እናምናለን። ይህ ማለት ከአንዳንድ ክርስቲያኖች በተቃራኒ የክርስቶስ
ሞት ለሰው ልጆች ሁሉ እንጂ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለድነት የወሰነው ልዩ ቡድን
እንደሌለ እናምናለን። አምላክ “ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ
ስለሚፈልግ” (1 ጢሞ. 2:4) “ለኃጢአታችን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ
ኃጢአት” (1ኛ ዮሐንስ 2፡2) ኢየሱስ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። ሁሉም ሰው
በምላሹ እርሱን የመረጠው ባይሆንም እንኳ "ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የተመረጠው’
(ኤፌ. 1:4) ለዚህ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አምላክ የደረሳቸውን ሁሉንም ዓይነት
ሰዎች የሚገልጹ ዘገባዎችን የምናገኘውም ለዚህ ነው።
ዳንኤል 4ን ያንብቡ። እዚህ ላይ ንጉሱ ምን አጋጠመው? ይህ ምዕራፍ
በአለማችን ላይ ሀያል ወደሆነው ሰው መዳን እንደመጣ የሚነግረን
እንዴት ነው?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ኃያላን ሆነው የማያምኑትን እንዴት
አድርጎ እንደሚደርስ የሚያሳየው አስደናቂ ምሳሌ የንጉሥ ናቡከደነፆር ታሪክ ነው።
የአምላክ ፍርድ በእሱ ላይ የተፈጸመው ከአንዳንድ የእስራኤል ነገሥታት ጋር በሚመሳሰል
መንገድ ነው (ለምሳሌ 2 ዜና 32:25-26፣1 ነገሥት 14:21-31፤ 1ኛ ሳሙኤል 28 ይመልከቱ)።
ወደ አእምሮው ተመልሶ ለፈጣሪው ምላሽ የሰጠው ናቡከደነፆር መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ትረካ እግዚአብሔር ለሀብታሞችና ለኃያላን እንዲሁም ለደካሞችና ለችግረኞች
ጭምር እንደሚያስብ ያሳያል። በቁጥር 37 ላይ በምድር ላይ በወቅቱ እጅግ ኃያል የነበረው
ሰው እንዲህ ሲል አወጀ “አሁንም እኔ ናቡከደነፆር የሰማይን ንጉሥ አመሰግናለሁ፥
ታላቅም አደርገዋለሁ፥ አከብረውማለሁ። ሥራው ሁሉ እውነት፥ መንገዱም ፍርድ
ነውና፥ በትዕቢትም የሚሄዱትን ያዋርድ ዘንድ ይችላልና።” (ዳን. 4፡37)። በእኛ መካከል
ያሉ ሟች ሀብታሞች፣ ኃያላን እና ትዕቢተኞች ሁሉ ይህንን እውነት ምነው ቢረዱ!
ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? በመጀመሪያ፣ እግዚአብሔር የማያምኑትን ኃያላን
ለመድረስ እንደ ዳንኤል ያሉ ቁርጠኛ አማኞችን እንደ ድልድይ ይጠቀማል። ሁለተኛ፣
የማያምኑ ኃያላንን ለመድረስ አምላክ በምስክርነት ሂደት ውስጥ በቀጥታ ሊሳተፍ
ይችላል። ናቡከደነፆር በትዕቢቱና በእብሪቱ ምክንያት በእግዚአብሔር ተዋረደ። እናም
ምንም እንኳን ይህ በጣም አስደናቂ ታሪክ ቢሆንም እግዚአብሔር ሀብታም፣ ኃያላን እና
ትዕቢተኞችን ዝቅ ማድረግ የሚችልባቸው ሌሎች ብዙ መንገዶችም አሉ።
በዓለም የመመዘኛ ደረጃዎች ሀብታምና ኃያላን ባንሆን እንኳ ይህ ንጉሥ
ያሳየውን ዓይነት ትዕቢት ለማስወገድ መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው?
ትዕቢተኛ መሆን እኛ ከምናስበው በላይ ቀላል የሆነው ለምንድን ነው?
አስተዳደግ፣ ሀብት፣ ዘር እና ደረጃ ሳይለይ ክርስቶስ ለሁሉም ሞቷል።
እግዚአብሔር በዓለም ውስጥ ያሉ ክርስቲያን ያልሆኑ ኃያላንን በወንጌሉ እየደረሳቸው
ሲሆን እንደተሰጣቸው ብርሃን እንዲኖሩ ይጠብቅባቸዋል (Ellen G. White, The Acts
of Apostles, p. 416)።
2 ነገሥት 5:1-19ን ያንብቡ። ሰዎችን በወንጌሉ ስለመድረስ ከዚህ
ታሪክ ምን ልንማር እንችላለን?
በ2ኛ ነገሥት 5፡17-19፣ ንዕማን በእግዚአብሔር ከለምጽ ከዳነ በኋላ ሁለት
ያልተለመዱ ጥያቄዎችን አቀረበ። በመጀመሪያ፣ ሕያው አምላክን ለማምለክ ሁለት
በቅሎ ሊሸከመው የሚችል አፈር ከእስራኤል ወደ ሶርያ ለመውሰድ ጠየቀ። “እኔ
ባሪያህ የሚቃጠለውን መባ ወይም መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር እንጂ ለሌላ አማልክት
አላቀርብምና” (2ኛ ነገሥት 5፡17) ብሏል። ሁለተኛ፣ ንዕማን የራሱን ሀገር ንጉስ አማልክት
ባያመልክም ከንጉሱ ጋር ለመስገድ ፍቃድ ጠየቀ።
አሁን ንዕማን የብቸኛው እውነተኛ አምላክ አማኝ ሆኗል። ሆኖም አሁንም
አረማዊ እምነቶች ነበሩት። ከእስራኤል አፈር መወሰዱ ፈጣሪ አምላክን ሙሉ በሙሉ
እንዳልተረዳው ያሳያል። በእሱ የዓለም አተያይ እግዚአብሔር እንደቀድሞ አማልክቶቹ
ሁሉ የአንድ አካባቢ አምላክ ስለሆነ አፈሩን መውሰድ እንዳለበት አስቦ ሊሆን ይችላል፤
ወይም በእስራኤል አፈር መሠዊያ መሥራት ፈልጎ ይሆን? ያም ሆነ ይህ በአምላክ ላይ
ያለው እምነት ከቀድሞ እምነቱ ጋር ተደባልቆ ነበር። የንዕማን ታሪክ ዛሬ ወደ ክርስቶስ
የሚመጡትን ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች አውድ ይገልፃል። ከንዕማን ታሪክ የምንማረው
ለነገሮች ያለን እይታ እስኪለወጥ ጊዜ እንደሚወስድ ነው።
ሁለተኛው ጥያቄ የበለጠ አሳሳቢ ነበር። ንዕማን ከንጉሱ ጋር ለመስገድ ፍቃድ
ጠይቆ አምላክን ይቅር እንዲለው ለምን ጠየቀ? ነቢዩ “በሰላም ሂድ” (2ኛ ነገሥት 5፡19)
በማለት መመለሱ ፍንጭ ይሰጣል። ንዕማን በሶርያውያን ዘንድ ኃያል ሰው እንደመሆኑ
መጠን ለአዲሱ እምነቱ ተግዳሮት የሆኑ ሥራዎችን ማከናወን ነበረበት። አዲስ አማኞች፣
በተለይም ከሌላ እምነት የመጡ፣ ወደ እምነት ከመምጣታቸው በፊት ያለፈው
ህይወታቸው የሚጠይቃቸውን ባህላዊ እና ማህበራዊ መስፈርቶችን ማሟላት
ንዕማን ከነለምፁ ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌለበትን አገሩን ትቶ ቢመጣም
ተፈውሶና የፈጣሪ አምላክ ደቀ መዝሙር ሆኖ መመለሱን አንርሳ። ጉዞውን የጀመረው
ገና አሁን ነው። ለማደግ ጊዜ ያስፈልገዋል።
በተለይ ክርስቲያን ካልሆነ አስተዳደግ ወይም ባሕል የመጡትን በተመለከተ
እነዚህን ሰዎች ቶሎ ላለመግፋት ከዚህ ታሪክ ምን ትምህርት እናገኛለን?
ኒቆዲሞስ የተማረ ሰው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ “የአይሁድ አለቃ” ብሎ
ይገልጸዋል (ዮሐንስ 3፡1)። ኢየሱስም “የእስራኤል መምህር” ብሎ ጠርቶታል (ዮሐንስ
3፡10)። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ ግንዛቤ ነበረው፤ ጌታውን የሚራብም መንፈሳዊ ረሃብ
ነበረው። ከሰዎች እይታ አንጻር የእግዚአብሔር ተከታይ መስሎ ይታያል። ትእዛዛቱን
ሁሉ ጠብቋል፣ እናም በአይሁድ ዘንድ የተከበረ መሪ ነበር። እሱ ኃያል እና ሀብታም
ነበር። እነዚህ መገለጫዎች ብዙዎች በእግዚአብሔር የተባረከን ሰው የሚገልፁባቸው
ናቸው። የሆነ ሆኖ፣ ይህ የውጪ ገጽታ ብቻ ነበር።
ዮሐንስ 3:1-12ን ያንብቡ። ይህ ታሪክ ስለ ኒቆዲሞስ መንፈሳዊ ፍላጎቶችና
ኢየሱስ እንዴት አድርጎ ጥያቄዎቹን እንደመለሰለት ምን ያሳየናል?
ኒቆዲሞስ ወደ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ በወቅቱ ከአማኝ ይጠበቅ የነበረውን ውጫዊ
መለኪያ ያሟላ ነበር። እግዚአብሔር ግን የልቡን አውቋል። በተመሳሳይ መንገድ፣
እግዚአብሔር የኋላ ታሪካቸው ምንም ይሁን ምን የሁሉንም ሀብታሞች እና ኃያላን ልብ እና
ፍላጎቶች ያውቃል። ኒቆዲሞስ ወደ ኢየሱስ የመጣው የኢየሱስ ትምህርቶች አሳምነውት
ነው። ትምክህቱ ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ እንደሆነ በግልፅ ከመመስከር ቢከለከለውም
ያ ሌሊት ለዘለአለም እንዲለወጥ አደረገው። ኢየሱስ ከእግዚአብሔር እንደተላከ ካመነ
በኋላም እንኳ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ መሆኑን በግልጽ አልተናገረም።
ዮሐንስ 7፡43–52 እና ዮሐንስ 19፡39ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ
ኒቆዲሞስ እና ኢየሱስ ምን ይነግሩናል?
በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ኒቆዲሞስ በኢየሱስ አስተምህሮ ከፍተኛ ተጽዕኖ
እንደተፈጠረበት ማየት እንችላለን። ኢየሱስ በሕይወት እያለ ሊጠብቀው እና ኢየሱስ
ከሞተ በኋላ ሊያከብረው ፈለገ። ታላቅ እውቀት እና ጥበብ ያለው ሰው ቢሆንም እንኳን
ልክ እንደኛው አዳኝ ያስፈልገው የነበረውን ኒቆዲሞስን ኢየሱስ በወንጌሉ ስለመድረሱ
አያጠያይቅም።
"እውነት ስላለን" (አዎ አለን) የዚህ እውነት እውቀት ብቻውን ለመዳን
በቂ ነው ብሎ ከማሰብ ወጥመድ ማምለጥ ያለብን ለምንድነው? ለመዳን
የሚያስፈልገው ብዙ እውቀት ያላቸው እንዲሁም ስለ ሶስቱ መላእክት
መልእክትም ጭምር በደንብ የሚያውቁ ሆነው የሚጠፉ ስንት ነፍሳት
ይኖሩ ይሆን?
ማቴዎስ 19:16-22ን ያንብቡ። ከኒቆዲሞስ በተቃራኒ ኢየሱስን ካለተቀበለው ከዚህ ሰው ታሪክ ምን ትምህርት እናገኛለን?
ኢየሱስ ከሀብታሙ ወጣት ገዥ ጋር ያደረገው ግንኙነት የሀብት ወጥመድ ምን ያህል
አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ያሳያል። እነዚህን ቃላት ይመልከቱ፡- “ዳግመኛም እላችኋለሁ፥
ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።”
(ማቴ. 19:24)። ይህ በእርግጥ ባለጠጎች መዳን አይችሉም ማለት አይደለም፤ ነገር ግን እነዚህ
ሰዎች ካልተጠነቀቁ ሀብታቸው በእውነት የመዳን እንቅፋት ሊሆን ይችላል።
በመጨረሻ ሀብታሞችም ሆኑ ድሆች አንድ አይነት እጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል-
መቃብር። ይህም ማለት ባለጠጎች እንደማንኛውም ሰው መዳን ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው።
ገንዘብ የሚገዛው ምንም ነገር ይሁን ምን ከሞት ነፃ መሆንን መግዛት አይችልም። ከዛ ነፃ
መሆን የሚቻለው በኢየሱስ በኩል በነጻ የተሠጠንን ስጦታ በእምነት ስንቀበል ብቻ ነው።
"ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ። በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል” (ዮሐ. 11፡25)።
ሉቃስ 19:1-10ን ያንብቡ። ስለ ሀብታሙ ወጣት ገዥ ከተፃፈው በተለየ
በዚህ ታሪክ ውስጥ ልዩነቱን የፈጠረው ነገር ምንድን ነው?
በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ወጣቱ ባለጠጋ ያልሰጠውን ምላሽ ዘኪዮስ መለሰ። ልብ
ይበሉ፣ ኢየሱስ ለሀብታሙ ወጣት ገዥ እንዳለው ለዘኬዎስ ያለውን ሸጦ ለድሆች
እንዲሰጥ አልነገረውም። ኢየሱስ ያንን የተናገረው ባለጠጋው ገዥ ምን ያህል ከገንዘቡ
ጋር እንደተቆራኘ ስላወቀ ነው። በአንጻሩ ግን ኢየሱስ በቤቱ በነበረበት ጊዜ የተነገረውን
ሁሉ ባናውቅም ዘኬዎስ በኢየሱስ ልቡ ስለተነካ በሕይወቱ ውስጥ በተለይም ከሀብቱ
ጋር በተያያዘ አንዳንድ ለውጦችን ማድረግ እንዳለበት ተገነዘበ።
“ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?
ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?” (ማቴ. 16፡) እነዚህ ቃላት
ለሁላችንም ምን የሚነግሩን ነገር አለ?
ኢየሱስ ከኃያላን ጋር እንዴት ጓደኝነት መመሥረት እንዳለበት ያውቅ ነበር።
በብዙዎቹ ዘንድ የተደነቀ እና የተከበረ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜም በብዙዎች ዘንድ
የተናቀም ነበር። ለእርዳታ ወደ ኢየሱስ የመጡት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኛቸው
ኃያላን ሰዎች ሁሉ እርሱ እንደሚያስብላቸው ተገንዝበዋል። በተጨማሪም፣ ብዙ
ሀብታምና ኃያላን በግልጽ ወደ ኢየሱስ አልመጡም፤ ኢየሱስ በእውነት የእግዚአብሔር
ልጅ መሆኑን እስኪያረጋግጡ ድረስ ጠበቁ። የኒቆዲሞስ እና የአርማትያው ዮሴፍ ሁኔታ
ይህ ነበር።
ማቴዎስ 27፡57-60ን ያንብቡ (በተጨማሪም ማርቆስ 15፡43-47፤ ሉቃስ
23፡50-53፣ እና ዮሐንስ 19፡38-42ን ይመልከቱ)። ይህ ታሪክ ጌታ
በእርሱ በጎ ተጽዕኖ የተነካን አንድ ሀብታም እንዴት እንደተጠቀመበት
ምን ይነግረናል?
እስከዚህ ታሪክ ድረስ ስለ አርማትያው ዮሴፍ ምንም አልሰማንም። በድንገት
ይህ ባለጸጋ ወደ ታሪኩ ገብቶ አንድ ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ምክንያት ሆነ። እግዚአብሔር
ባለጠጎችን ለዓላማው ተጠቅሞባቸዋል እና ይህንን ማድረጉንም ይቀጥላል። ስለዚህ
እነርሱን ለመድረስም ተልዕኮ ሊኖረን ይገባል።
ከኃያላን ሰዎች ጋር ጓደኝነት ለመመሥረት ከየት መጀመር እንዳለብን መረዳት
ራሱ በጣም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። በአጠቃላይ እነሱን መከታተል አይመከርም፤
እነሱ ራሳቸው ወደ እናንተ ይምጡ። ኢየሱስም ይህንን ነበር ያደረገው፤ ከእግዚአብሔር
ዘንድ ስለሆነው መልእክቱ፣ ፈውሱና ኃይሉ ምስክር ሆኑ። ከትዕይንቱ በስተጀርባ እርሱ
በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምነው ነበር።
ኃያላን ሰዎች በብዙ ምክንያቶች ከእውነተኛ አገልግሎት ጋር አጋር ለመሆን
ይፈልጋሉ። የሰዎችን ሕይወት ወደ መልካም እየለወጠ ባለ ነገር ውስጥ መሳተፍ
ይፈልጋሉ። ይህ ህይወታቸውን ሊለውጥ እንደሚችል የሚያውቁበት አንዱ መንገድ
ነው። ሀብታሞች እና ኃያላን ፍላጎቶቻቸውን በይፋ ሳይገልጹ የሚያስፈልጋቸውን
እርዳታ እንዲያገኙ የሚያስችል ስውር መንገድን ይሰጣቸዋል።
ሁለተኛው ምዕራፍ ሀብታሞች እና ኃያላን ሰዎች በእግዚአብሔር አገልግሎት
ውስጥ አካል ሆነው እንዲታቀፉ ጥርጊያ መንገዱን ማስፋት መቻል ነው። በማህበረሰብዎ
ውስጥ በሀብታሞች እና በሀያላን ህይወት ላይ ለመሥራት ይችሉ ዘንድ ትንሽ ጊዜ
ይውሰዱ።
ግድድሮሽ፡- በስልጣን ቦታ ላይ ያለ፣ አማኝ ያልሆነ፣ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊያገኙት
የሚችሉትን ሰው ወደ ዕለታዊ የጸሎት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩት።
ከፍ ያለ ግድድሮሽ፡- በስልጣን ቦታ ላይ ላለ ሰው— ምንም እንኳን ምናልባት
በጭራሽ ተገናኝታችሁ የማታውቁ ቢሆንም— ለዚያ ሰው እየጸለዩለት እንደሆነ
በደብዳቤ ወይንም በኢሜል አድራሻው ያሳውቁት።
Read Ellen G. White, “Ministry to the Rich,” The Minis-
try of Healing, pp. 209–216; “Captive Maid Shows Concern for Naaman,”
Reflecting Christ, p. 337.
የኢየሱስ ፍቅር በዓለም ላይ ላሉ ሀብታም እና ኃያላን ሰዎች ለድሆች ተመሳሳይ
ነው። የሞተው ለመኳንንት ለድሆችም ነው። ኢየሱስ ልባቸውን ለመንካት ከሁሉ
የተሻለውን መንገድ ያውቅ ነበር። “ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ
ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል” (ማር 10፡25) በማለት አስጠንቅቆናል። በዚህ
ሳምንት ኃያላን እና ባለጸጎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ስለመድረስ ተነጋግረናል።
ምንም እንኳን በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ሀብታቸው በሚሰጣቸው "ደህንነት" ምክንያት
ላያውቁ ቢችሉም እንደማንኛውም ሰው መዳን ያስፈልጋቸዋል።
“ቸል ለተባሉ ድሆች ያለብንን ግዴታ በተመለከተ ብዙ ተብሏል። ቸል
ለተባሉ ሀብታም ሰዎችስ የተወሰነ ትኩረት መሰጠት የለበትም? ብዙዎች እንደዚህ
አይነቶቹን ተስፋ ቢስ አድርገው ይመለከቷቸዋል። . . . በሺዎች የሚቆጠሩ ባለጸጎች
ማስጠንቀቂያው ሳይደርሳቸው ወደ መቃብራቸው ገብተዋል። ነገር ግን ግድየለሾች
ቢመስሉም ከሀብታሞች መካከል ብዙዎቹ የነፍስ ሸክሞች ያለባቸው ናቸው።”—Ellen
G. White፣ The Ministry of Healing, p. 210.
1. ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ሀብታሞችንና ድሆችን ሲያገለግል
ሳለ የነበረውን የመደብ ልዩነት አፍርሷል። እኛ አድቬንቲስቶች በሁሉም
ማህበረሰቦቻችን ውስጥ ስር የሰደደውን ይህን ጉዳይ ማለትም በሀብታሞች እና
በድሆች መካከል ያለውን ልዩነት እንዴት ልንሠራበት ይገባናል?
2. ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “በእሾህ መካከል የተዘራውም ቃሉን የሚሰማ
ነው፣የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፣ የማያፈራም
ይሆናል።” (ማቴ. 13፡ 22) ኢየሱስ “የሀብት ማታለል” ሲል ምን ማለቱ
ይመስላችኋል? በሀብት ለመታለል የግድ ሀብታም መሆን የሌለብን ለምንድን ነው?
3. ክፍልዎ ውስጥ፣ እውነትን ማወቅ ብቻ መዳን ማለት ስላለመሆኑ እውነታ
በማክሰኞው ጥናት መጨረሻ ላይ የተጠየቀው ጥያቄ ላይ ተወያዩ። እነዚህን ለይተን
ማስቀመጥ ያለብን ለምንድነው? የሚያድነን እውነትን ማወቅ ብቻ ካልሆነ ታድያ
የሚያድነን ምንድነው?
4. ዘኪዎስ ኢየሱስን ሲቀበል ሀብታሙ ወጣት ገዥ ኢየሱስን ያልተቀበለበት ሌላ
ምን ምክንያት ሊኖር ይችል ይሆን?