
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡-ዘሌ.25፡25-27፣ዕብ.2፡ 14-16፣ዕብ.11፡24-26፣1ቆሮ.15፡50፣ዕብ.5፡8-9፣ዕብ.12፡1-4።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው።” (ዕብ. 2፡14)
ዕ
ብራውያን ምዕራፍ 1 ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር ልጅ፣እንደ
መላዕክት ገዢና እንደ ክብሩ መንጸባረቅና የባህሪዩ ምሳሌ(ዕብ.1፡
3) አድርጎ ይገልጸዋል። በዕብራውያን ምዕራፍ 2 ደግሞ ኢየሱስ
ከመላእክት በታች ተዋርዶ የሰውን ተፈጥሮ እስከነድካሙ እስከ ሞትም ድረስ
የተሸከመ የሰው ልጅ መሆኑን ገልጾልናል።(ዕብ.2፡7)
በዕብራውያን 1 እግዚአብሔር ለኢየሱስ አንተ ልጄ ነህ(ዕብ.1፡5) ብሎት
ነበር። በዕብራውያን 2 ኢየሱስ የሰው ልጆችን ወንድሞቼ ይላቸዋል(ዕብ.2፡
12)።
በዕብራውያን 1 አብ የወልድን መለኮታዊ ሰብዓዊነት (ዕብ.1፡8) ያውጃል።
በዕብራውያን 2 ወልድ ለአባ ታማኝ መሆኑን ያረጋግጣል(ዕብ.2፡13)።
በዕብራውያን 1 ኢየሱስ አምላክ፣ጌታ፣ፈጣሪ፣የሚያኖርና ሉአላዊ ነው።
በዕብራውያን 2 ኢየሱስ የሚራራና ታማኝ ሰው የሆነ ሊቀካህን ነው።
ለማጠቃለል ኢየሱስ ታማኝና መሃሪ ወንድም ሆኖ መገለጹ ዘላለማዊና ፈጣሪ
የሆነው አምላክ የወልድ የመጨረሻ መገለጥ ውስጥ ተገልጿል(ዕብ.1፡1-4)።
ለጥር 14 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትህር ያጥኑ።
ዘሌዋውያን 25፡25-27፣ 47-49ን ያንብቡ። በድህነት ምክንያት ንብረቱን ወይም ነፃነቱን ያጣውን ሰው ሊቤዠው የሚችለው ማነው?
በሙሴ ህግ መሠረት አንድ ሰው እጅግ ድሃ ከመሆኑ የተነሳ ለመኖር ሲል ንብረቱን ወይም ራሱን መሸጥ ቢኖርበት ንብረቱን ወይም ነፃነቱን መልሶ የሚያገኘው የኢዮቤልዩ ዓመት በሆነው በሃምሳኛው ዓመት ነው። የኢዮቤልዩ ዓመት እዳዎች የሚሰረዙበት፣ ንብረቶች የሚመለሱበት እንዲሁም ባሪያዎች ነፃነታቸውን የሚያገኙበት “ታላቁ” የሰንበት ዓመት ነው። ሆኖም ሃምሳ ዓመት መጠበቅ ረዥም ጊዜ ነው። የሙሴ ህግ የቅርብ ዘመዱ የራሱን ንብረት ከፍሎ በእዳ የተያዘው ዘመዱን በፍጥነት መቤዠት(ነፃ ማውጣት) እንዲችል ያዘዘው ለዚያ ነው። ዕብራውያን 2፡14-16ን ያንብቡ። በዚህ ጥቅስ ውስጥ ኢየሱስና እኛ የተገለፅነው እንዴት ነው?
ይህ ጥቅስ እኛን የዲያብሎስ ባሪያ እንደሆንን ኢየሱስ ደግሞ ቤዛችን እንደሆነ
ይገልፃል። አዳም በኃጢአት ሲወድቅ የሰው ልጅ በሰይጣን ኃይል ስር ወደቀ።
በውጤቱም ኃጢአትን የመቋቋም ኃይል የለንም (ሮሜ 7፡14-24)። ከዚህ
የከፋው ደግሞ በመተላለፋችን ምክንያት ልንከፍለው የማንችል የሞት ቅጣት
ተጥሎብናል(ሮሜ 6፡23)። ስለዚህ የነበርንበት ሁኔታ ተስፋ ቢስ ነበር።
ሆኖም ኢየሱስ የኛን ተፈጥሮ ወስዶ ልክ እንደኛ ስጋና ደም ሆነ። የኛ ቅርብ
ዘመድ ሆኖ ተቤዠን። “ወንድሞቼ” ብሎ ሊጠራን አላፈረም (ዕብ. 2፡11)።
የኛን ተፈጥሮ በመውሰዱና እኛን በመዋጀቱ በአስገራሚ ሁኔታ መለኮታዊነቱን
ገለጠ። በብሉይ ኪዳን የእስራኤል እውነተኛው ቤዛ የቅርብ ዘመዳቸው ያህዌ
ነው (መዝ. 19፡14፣ ኢሳ. 41፡14፣ ኢሳ. 43፡14፣ ኢሳ. 44፡22፣ ኤር. 31፡11፣ ሆሴ.
13፡14)።
ክርስቶስ ከእርስዎ ጋር መቅረቡን የበለጠ ጥልቅ በሆነ ሁኔታ
መለማመድ የሚችሉባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው? ይህንን
ልምምድ ማግኘት ለእርስዎ እጅግ ጠቃሚ የሆነው ለምንድነው?
የእብራውያን መልዕክት እንደሚነግረን ኢየሱስ እኛን ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራን አላፈረብንም (ዕብ. 2፡11)። ከአብ ጋር አንድ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ኢየሱስ የርሱ ቤተሰብ አካል አድርጎ አቅፎናል። ይህ አንድነት የዕብራውያን መልዕክት አንባቢዎች በዙሪያቸው ከነበሩት ማህበረሰብ ከደረሰባቸው ይፋዊ ነቀፋ ጋር ይለያያል (ዕብ. 10፡33)። ዕብራውያን 11፡24-26ን ያንብቡ። የሙሴ ውሳኔዎች ኢየሱስ ለኛ ያደረገውን የሚመስሉት በምን መልኩ ነው?
ለሙሴ የፈርኦን የልጅ ልጅ ተብሎ መጠራት ምን ማለት እንደ ሆነ አስባችሁታል? በጊዜው በነበረው ኃያል ግዛት ውስጥ ከፍ ያለ ስፍራ የሚሰጠው ነበር። የእውቀትና የውትድርና ስልጠናን ስለወሰደ እጅግ ማራኪ ሰው ሆነ። እስጢፋኖስ ስለ እርሱ ሲናገር ሙሴ “በቃሉና በሥራው የበረታ ሆነ” (ሐዋ. ሥራ 7፡22) ይላል። ኤለን ኋይትም ሙሴ ከግብጽ ወታደሮች የተመረጠውና ፈርኦን ደግሞ “ልጁ ያሳደገችው ይህ ልጅ እርሱን እንደሚተካው ያስብ ነበር” (የሃይማኖት አባቶችና ነቢያት ገፅ 245)። ሙሴ ግን እነዚህን በረከቶች ሁሉ ትቶ ካልተማሩትና አቅመቢስ ባርያዎች ከሆኑት ከእስራኤላውያን ጋር ለመቆም መረጠ። ማቴዎስ 10፡32-33፣ 2 ጢሞ. 1፡8፣ 12ንና ዕብራውያን 13፡ 12-15ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ከኛ የሚጠይቀው ምንድነው?
ለዕብራውያን መልዕክት አንባቢዎች አስቸጋሪ የነበረው ይህ ነው። ስደትና
መገፋት ካጋጠማቸው በኋላ ብዙዎቹ በኢየሱስ ማፈር ጀመሩ። አንዳንዶቹም
በተግባራቸው ኢየሱስን ከማክበር ይልቅ በግልፅ የማዋረድ አደጋ ውስጥ
ወደቁ (ዕብ. 6፡6)። ስለዚህ ጳውሎስ በተደጋጋሚ በእምነታቸው እንዲፀኑ
ያበረታታቸዋል (ዕብ. 4፡14፣ ዕብ. 10፡23)።
እግዚአብሔር ኢየሱስን እንደ አምላካችንና እንደ ወንድማችን ሊያየው
ይፈልጋል። እዳችንን ስለከፈለ ቤዛችን የሆነ ሲሆን “ልጁ በብዙ
ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቀን የልጁን መልክ
እንድንመስል”(ሮሜ 8፡29) እንዴት መኖር እንዳለብን በማሳየት ወንድማችን
ሆኗል።
እኛን እንደ ወንድምና እህቶቹ ለማቀፍ ኢየሱስ መወሰን
የነበረበትን ውሳኔ ለጥቂት ደቂቃዎች ያስቡ። ኢየሱስ ያደረገው
ሙሴ ካደረገው በላይ ራስን ማዋረድ የሆነው ለምንድነው? ይህ
እግዚአብሔር ለእኛ ስላለው ፍቅር ምን ያስተምረናል?
የዕብራውያን መልዕክት እንደሚነግረን ኢየሱስ የሰውን ተፈጥሮ የለበሰው የእኛ ወኪል ለመሆንና ለኛ መሞት እንዲችል ነው(ዕብ. 2፡9፣ 14-16፣ ዕብ. 10፡ 5-10)። የድነት ዕቅድ መሠረትና የዘላለም ሕይወት የማግኛ ብቸኛ ተስፋችን ይህ ነው። ማቴዎስ 16፡17፣ ገላትያ 1፡16፣ 1 ቆሮ. 15፡50ና ኤፌ. 6፡ 12ን ያንብቡ። “ስጋና ደም” የሚለው አገላለፅ ከሰው ተፈጥሮ ከየትኛው ድክመት ጋር ይገናኛል?
ሥጋና ደም የሚለው አገላለፅ የሰብዓዊ ዘርን ደካማነት (ኤፌ. 6፡12)፣
አለማስተዋል (ማቴ. 16፡17፣ ገላ. 1፡16) እና ሟች መሆን (1 ቆሮ. 15፡50)
የሚገልፅ ነው። የዕብራውያን መልዕክት ኢየሱስ “በሁሉ ነገር” ወንድሞቹን
መሠለ ይላል(ዕብ. 2፡17)። ይህ አገላለፅ ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ሰው ሆኗል
የሚል ትርጉምን ይሰጣል። ኢየሱስ እንዲሁ መምሰል ብቻ ሳይሆን ሰው ሆኖ
ከእኛ እንዳንዱ ሆኖ ነበር።
በተጨማሪም መልዕክቱ ኢየሱስ ኃጢአት ከመሥራት አንፃር ከኛ የተለየ
እንደሆነ ይናገራል። በመጀመሪያ ኢየሱስ ምንም ኃጢአት አላደረገም (ዕብ.
4፡15)። በሁለተኛ ደረጃ ኢየሱስ የነበረው ስብዕና “ቅዱስ፣ ንፁህ፣ በኃጢአት
ያልተበከለ፣ ከኃጢአተኞች የተለየ”(ዕብ. 7፡26) ነበረ።
እኛ ክፉ ተፈጥሮ
ነው ያለን። ለኃጢአት ባሪያ መሆናችን ጥልቅ በሆነው በራሳችን ተፈጥሮ
ውስጥ ይጀምራል። እኛ “ሥጋውያን፣ ከኃጢአት በታች የተሸጥን” ነን (ሮሜ
7፡14-20)። መልካሞቹን ሥራዎቻችንን እንኳን እኔነትና ሌሎች የኃጢአት
መነሻ ምክንያቶቻችን ያበላሹብናል። ሆኖም የኢየሱስ ተፈጥሮ በኃጢአት
አልተበላሸም ነበር። እንደዚህ መሆን ነበረበት። ኢየሱስ እንደኛ “ሥጋዊ
ከኃጢአት በታች የተሸጠ” ቢሆን ኖሮ እርሱም አዳኝ ያስፈልገው ነበር።
በተቃራኒው ኢየሱስ ሊያድነን መጥቶ ለኛ ሲል ራሱን በእግዚአብሔር ፊት
“ነቀፋ የሌለበት” መስዋዕት አድርጎ አቀረበ(ዕብ. 7፡26-28፣ ዕብ. 9፡14)።
ከዚያም ኢየሱስ ለኃጢአታችን እንከን አልባ መስዋዕት ሆኖ በመሞት
የሰይጣንን ኃይል አጥፍቶ ይቅር እንድንባልና ከእግዚአብሔር ጋር እንድንታረቅ
መንገድን ከፈተ (ዕብ. 2፡14-17)። በተጨማሪም በአዲሱ ኪዳን ተስፋ በገባው
መሠረት ህጉን በልባችን በመፃፍ የፅድቅ ህይወት መኖር የምንችልበትን
ኃይል በመስጠት ኢየሱስ የኃጢአትን ኃይል ሰበረ(ዕብ. 8፡10)። ስለዚህ
ኢየሱስ ጠላትን በማሸነፍና እኛን ሙሉ በሙሉ ነፃ በማውጣት “ህያው
የሆነውን አምላክ”(ዕብ. 9፡14) እንድናገለግል አስቻለን። ደግሞም የሰይጣን
የመጨረሻው ጥፋት በመጨረሻው ፍርድ ጊዜ ይሆናል (ራዕይ ዮሐ. 20፡1-3፣
10)።
በኢየሱስ በኩል የድል ተስፋ እያለንም ብዙዎቻችን በኃጢአት
ውስጥ እየተንከባለልን ያለነው ለምንድነው? ምኑ ላይ ነው
የተሳሳትነው? በክርስቶስ ባለን ከፍ ያለ ጥሪ ልክ መኖር የምንችለው
እንዴት ነው?
ዕብራውያን 2፡ 10፣ 17፣ 18ንና ዕብራውያን 5፡8-9ን ያንብቡ። በኢየሱስ ህይወት ውስጥ መከራ ምን ነበር?
ሐዋርያው እንደሚናገረው እግዚአብሔር አብ ኢየሱስን “ፍፁም ያደረገው
በመከራዎች ውስጥ ነው”። ይህ አገላለፅ አስደናቂ ነው። ፀሐፊው ሲናገር
ኢየሱስ “የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ” (ዕብ. 1፡3) ሲሆን በተጨማሪም
ኃጢአት አልባ፣ ነቀፋ የሌለበት፣ ያልረከሰና ቅዱስ ነው (ዕብ. 4፡15፣ ዕብ. 7፡
26-28፣ ዕብ. 9፡14፣ ዕብ. 10፡5-10)። ይህ ማለት ኢየሱስ ምንም አይነት
የግብረገብ እንከን አልነበረበትም ማለት ነው።
ሆኖም የዕብራውያን መልዕክት ኢየሱስ እኛን ማዳን እንዲችል ፍፁም በመሆኛ
ሂደት ውስጥ እንዳለፈ ይናገራል። ኢየሱስ ፍፁም ሆነ ስንል የኛ አዳኝ እንዲሆን
ብቁ ሆነ ማለት ነው።
1.ኢየሱስ በመከራ ውስጥ “ፍፁም የሆነው” የመዳናችን ራስ ለመሆን
ነው (ዕብ. 2፡10)። አብ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲያድነን ኢየሱስ
በመስቀል ላይ በመሞት መስዋዕት መሆን ነበረበት። ኢየሱስ ብቸኛው
ፍፁም የሆነ መስዋዕት ነው። አምላክ እንደመሆኑ ኢየሱስ ፈራጅ ሊሆን
ይችላል፤ ነገር ግን መስዋዕት በመሆኑ ምክንያት ሊያድነንም ይችላል።
2.ኢየሱስ መታዘዝን የተማረው በመከራ ውስጥ ነበር (ዕብ. 5፡
8)። መታዘዝ ለሁለት ነገሮች አስፈላጊ ነበር። በመጀመሪያ መታዘዙ
መስዋዕቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ አስቻለው (ዕብ. 9፡14፣ ዕብ. 10፡
5-10)። በሁለተኛ ደረጃ በመከራ ውስጥ ማለፉ የኛ ምሳሌ እንዲሆን
አስችሎታል (ዕብ. 5፡9)። ኢየሱስ መታዘዝን “የተማረው” ከዚያ በፊት
ተለማምዶት ስለማያውቅ ነው። አምላክ እንደመሆኑ ለማን መታዘዝ
ይኖርበታል? እንደዘላለማዊ ልጅነቱና ከእግዚአብሔር ጋር አንድ
እንደመሆኑ እንዲሁም የዩኒቨርስ ገዢ እንደመሆኑ ሌሎች ነበሩ እርሱን
የሚታዘዙት። ስለዚህ ኢየሱስ ካለመታዘዝ ወደ መታዘዝ ሳይሆን
ከሉዓላዊ ገዢነት ዝቅ ብሎ ወደ መገዛትና ወደመታዘዝ ነው የተሻገረው።
የከበረው የእግዚአብሔር ልጅ ታዛዥ የሰው ልጅ ሆነ።
3.መከራዎች ኢየሱስ የሚራራና ታማኝ ሊቀካህን መሆኑን ገለጡ(ዕብ.
2፡17-18)። መከራዎች ኢየሱስን የበለጠ ሩህሩህ አላደረጉትም።
በተቃራኒው ከመጀመሪያውም እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ ለመሞት
የፈቀደው እርሱ መሃሪ(ሩህሩህ) ስለነበረ ነው(ዕብ. 10፡5-10ን ከሮሜ
5፡7-8 ጋር ያነፃፅሩ)። ሆኖም የኢየሱስ ወንድማዊ ፍቅር የተገለፀው
በመከራዎቹ ውስጥ ነበር።
ኃጢአት አድርጎ የማያውቀው ኢየሱስ መከራን ከተቀበለ እኛም
እንደ ኃጢአተኝነታችን መከራን እንቀበላለን። የህይወትን አሳዛኝ
ገፅታዎች እየተቋቋምን በተለያዩ ታላላቅ መንገዶች ፍቅሩን
በገለፀልን አምላክ ላይ ተስፋንና መተማመንን ማግኘት የምንችለው
እንዴት ነው?
ኢየሱስ የሰውን ተፈጥሮ የወሰደበትና በመካከላችን የኖረበት ምክንያት አርአያችን(ምሳሌያችን) መሆን እንዲችል ነው፤ በእግዚአብሔር ፊት በትክክለኛው መንገድ የመኖር ምሳሌ ሊሆን የሚችል ብቸኛው እርሱ ነው። ዕብራውያን 12፡1-4ን ያንብቡ። እንደ ሐዋርያው አነጋገር የክርስትና ህይወት ሩጫን መሮጥ ያለብን እንዴት ነው?
በዚህ ጥቅስ ሐዋርያው በእምነታቸው ምሳሌ የሆኑ ሰዎች የዘረዘረበት
መደምደሚያ ነው። ይህ ጥቅስ ኢየሱስን “የእምነታችን ጀማሪና ፈፃሚ”
ብሎ ይጠራዋል። አርኬጎስ የሚለው የግሪክ ቃል “ቀዳሚ” ተብሎ ሊተረጎም
ይችላል። ኢየሱስ የሩጫው ቀዳሚ የሆነው ከአማኞች ፊት በመሮጡ ነው።
እንደውም ዕብራውያን 6፡20 ኢየሱስን ከፊት ቀዳሚ ብሎ ይጠራዋል።
“ፈፃሚ” የሚለው ቃል ኢየሱስ በእግዚአብሔር ማመንን እጅግ ንፁህ በሆነው
መንገድ መተግበሩን ያመላክታል። ይህ ጥቅስ ኢየሱስ የኛን ሩጫ በስኬት
መሮጡንና በእምነት መኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነ በፍፅምና ያሳየው
እርሱ መሆኑን ይገልፃል።
ዕብራውያን 2፡13 ላይ “ደግሞም፡- እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም፦
እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች” ይላል። በዚህ ቦታ ኢየሱስ
እምነቱን በእግዚአብሔር ላይ ማድረጉን እየተናገረ ነው። ይህ ጥቅስ የኢሳያስ
8፡17-18ን ኃሳብ ያስተጋባል።
ኢሳያስ እነዚህን ቃላት የተናገረው በሰሜን እስራኤላውያንና በሶርያ የመወረር
ፍርሃት ውስጥ ባለበት ጊዜ ነበር (ኢሳ. 7፡1-2)። የርሱ ማመን የንጉስ አሃዝን
አለማመን ያሳብቃል (ኢሳ. 7፡1-11)። የዳዊት ልጅ(ዘር) እንደመሆኑ ቀድሞውኑ
እንደ ልጁ እንደሚጠነቀቅለት ቃል ገብቶለት ነበር። አሁን እግዚአብሔር
ለአሃዝ የገባውን ቃል በምልክት ሊያረጋግጥለት ፈለገ። ሆኖም ንጉስ አሃዝ
ምልክት መጠየቅ አሻፈረኝ ብሎ ወደ ሶርያውያን ንጉስ ቴልጌልፌልሶር “እኔ
ባሪያህና ልጅህ ነኝ” (2 ነገስት 16፡7) ብሎ መልዕክት ላከበት። እጅግ ያሳዝናል!
አሃዝ የእግዚአብሔር ልጅ ከመሆን ይልቅ የቴልጌልፌልሶር ልጅ መሆንን
መረጠ።
ኢየሱስ ግን በእግዚአብሔርና ጠላቶቹን በእግሩ ስር እንደሚያደርግለት
በገባው ቃል ታመነ (ዕብ. 1፡13፣ ዕብ. 10፡12-13)። እግዚአብሔር ተመሳሳይ
ቃል ለኛ ገብቶልናል፤ ስለዚህ ኢየሱስ እንዳደረገው ልናምነው ይገባናል(ሮሜ
16፡20)።
በየዕለቱ በምንመርጣቸው ምርጫዎች በእግዚአብሔር ላይ
መተማመንን መማር የምንችለውና መተማመናችንን የምናሳየው
እንዴት ነው? ቀጥሎ በህይወትዎ የሚመርጡት ወሳኝ ምርጫ
ምንድነው? ይህ ምርጫዎ በእግዚአብሔር መታመንዎን የሚያሳየው
እንዴት ነው?
ዕብራውያን 2፡13 ኢየሱስ ለአባቱ ስለወንድሞቹ
የሚናገረውን ኃሳብ ይዟል። “እነሆኝ እኔ እግዚአብሔር የሰጠኝም ልጆች” ዕብ.
2፡13 ፓትሪክ ግሬይ ስለዚህ ሲናገር በዚህ ቦታ ኢየሱስ እንደ ወንድሞቹ ጠባቂ
እንደተገለጠ ይናገራል። ቱቴላ ኢምፑቤረም የሚባለው የሮማውያን ስርዓት
በቤቱ ውስጥ አባት ሲሞት “ታናናሾቹ አድገው ኃለፊነት መሸከም እስኪችሉ
ድረስ ለታናናሾቹ እንክብካቤ ለማድረግና ውርሳቸውንም ለመጠበቅ ኃላፊነት
የሚወስደው በአብዛኛው ታላቅ ወንድምየው ነው፤ በዚህም ታላቅ ወንድምየው
በተፈጥሮ ለታናናሾቹ ማድረግ ያለበትን የመጠንቀቅ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።”
የዕብራውያን መልዕክት እኛን እንደ ኢየሱስ ወንድምና እንደ ልጆቹ የገለፀበትን
ምክንያት ይህ ያስረዳል። እንደ ታላቅ ወንድማችን ኢየሱስ ሞግዚታችን፣
ጠባቂያችንና አስተማሪያችን ነው።
“ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቶ ሰብአዊ ስጋን የለበሰውና የሰው ወኪል ሆኖ
የቆመው የሰው ልጅ ከሰይጣን ጋር ባለበት ትግል ከአብና ከወልድ ጋር የጠበቀ
ግንኙነት ካለው እያንዳንዱን የህጉን ጥያቄ ሊታዘዝ እንደሚችል ለማሳየት
ነው።” Ellen G. White, Selected Messages, book 1, p. 253
“በህይወቱና በትምህርቱ ኢየሱስ ከአባቱ የፈለቀውን ራስ ወዳድ ያልሆነ
አገልግሎት በመስጠት ምሳሌ ሆነ። እግዚአብሔር ለራሱ አይኖርም። ዓለምን
በመፍጠርና ሁሉንም ነገር በመደገፍ ሁልጊዜ ሌሎችን እያገለገለ ነው።
“እርሱ
በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም
ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” ማቴ. 5፡45 ይህ አይነቱን አገልግሎት እግዚአብሔር
ለልጁ ሰጥቶታል። ኢየሱስ የሰው ልጆች ራስ እንዲሆን የተሰጠው ማገልገል
ማለት ምን ማለት እንደሆነ ምሳሌ ሆኖ ለማሳየት ነው።” ኤለን ጂ. ኋይት፣
የዘመናት ምኞት፣ ገፅ 649
1.የዕብራውያን መልዕክት እንደሚነግረን ኢየሱስ ወንድማችን
የሆነው እኛን ለማዳን ሲል ነው። እኛን ለማዳን አብ ያደረገውን
ደግሞ እናስብ። ለዚህ አስደናቂ እውነት ጀርባን መስጠት እጅግ
አሳዛኝ ስህተት የሚሆነው ለምንድነው?
2.ኢየሱስ እንደ እኛ “ከኃጢአት በታች ሊሆን የተሸጠ” (ሮሜ 7፡
14) ሆኖ አለመወለዱ ለኛ ምን ይጠቅመናል? ስለ ሙሴ እናስብና
ሙሴ እንደ እስራኤላውያኑ ባርያ አለመሆኑ ለእስራኤላውያኑ
ምን ጠቀማቸው? በትንሹም ቢሆን የሙሴ ታሪክ ኢየሱስ ለኛ
ያደረገውን እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው?
3.በኛ ህይወት ውስጥ መከራ ስላለው ሚና ጊዜ ወስደው ያስቡ።
ምንም እንኳን አንዳንዴ መልካም ውጤት ቢያመጣም መከራ
በራሱ መልካም ነገር እንደሆነ ማሰብ የሌለብን ለምንድነው?