
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ኢሳ. 2፡2-3፣ ዕብ. 1፡ 1-4፣ ዘፀ. 24፡16-17፣ ኢሳ. 44፡24፣ ዕብ. 1፡10፣ ሉቃስ 1፡31-32፣ ዕብ. 1፡5።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።” ዕብራውያን 1፡2-3
አ
ዳምና ሔዋን ኃጢያት ከሰሩ በኋላ ወዲያው እግዚአብሔር ስለ አንድ
ዘር ተስፋ ሰጠ፤ያም ልጅ ከጠላት ነጻ የሚያወጣቸው፤ያጡትን ውርስ
የሚያስመልስላቸውና የተፈጠሩበትን አላማ መፈጸም የሚያስችላቸው
ነው(ዘፍ.3፡15)። ይህ ልጅ የነርሱን ቦታ በመውሰድ እነርሱን በመወከልና
በመዋጀት በመጨረሻ ዘንዶውን ያጠፋዋል።
አዳምና ሔዋን መጀመሪያ ተስፋውን ሲሰሙ ቶሎ ይፈጸማል ብለው ጠበቁ።
የመጀመሪያ ወንድ ልጃቸውን ሲወልዱ ነጻ አውጪው ነው በሚል ተስፋ
በደስታ ተቀበሉት። ነገር ግን የተስፋው ፍጻሜ ዘገየ።
ኤለን ጂ.ኋይት፤የዘመናት
ምኞት፤ገጽ.31። ጥቂት ቆይቶ ተስፋው ለአብርሃም ተረጋገጠለት። ዘር
እንደሚሰጠው በርሱም አማካኝነት የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደሚባረኩ
እግዚአብሔር ማለለት(ዘፍ.22፡16-18፤ገላ.3፡16)። እግዚአብሔር ለዳዊትም
እንደዚሁ አደረገ። የርሱን ልጅ አንደራሱ አድርጎ እንደሚያሳድገውና ልጁም
በምድር ነገስታት ሁሉ በጽድቅ የሚገዛ እንደሚሆን እግዚአብሔር ቃል
ገባለት(2 ሳሙ.7፡12-14፤መዝ.89፡27-29)።አዳም ይሁን ሔዋን፤አብራሃም
ይሁን ዳዊት ቤዛ የሚሆነው ልጅ ራሱ እግዚአብሔር ይሆናል ብለው ግን
አልጠበቁም።
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለጥር 7 ሰንበት ይዘጋጁ።
የዕብራውያን መልዕክት የመጀመሪያው አንቀጽ እንደሚነግረን ጳውሎስ “በመጨረሻዎቹ ቀናት” እየኖረ እንዳለ ያምን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ የሚገልጹና የተለያየ ትርጉም ያላቸውን ሁለት አይነት አገላለጾችን ይጠቀማል። ነብያቱ በዘመኑ ፍጻሜ እና በኋለኛው ዘመን የሚሉትን አገላለጾች በመጠቀም በአጠቃላይ ስለደወፊቱ ይናገራሉ (ለምሳሌ ዘዳ.4፡30-31፤ኤር.23፡ 20) ዳንኤል ደግሞ በተለይ ስለምድር ታሪክ የመጨረሻ ቀናት ለመግለጽ የፍጻሜ ዘመን የሚል ሌላ አገላለጽን ይጠቀማል(ዳን.8፡17፤ዳን.12፡4) ። ዘሁልቅ 24፡14-19ንና ኢሳያስ 2፡2-3ን ያንብቡ። እግዚአብሔር በኋለኛው ዘመን ለህዝቡ ሊያደርግ ቃል የገባው ነገር ምንድነው?
ብዙ የብሉይ ኪዳን ነብያት በኋለኛው ዘመን እግዚአብሔር ንጉስን አስነስቶ
ያ ንጉስ ደግሞ የህዝቡን ጠላት የሚያጠፋና ህዝቦችን ወደ እስራኤል
የሚስብ (ኢሳ. 2፡2-3፤ዘሁ. 24፡14-19) እንዲሆን ተንብየዋል። ጳውሎስ
እነዚህን ትንቢቶች በየሱስ በኩል እንደተፈጸሙ ይናገራል።ሰይጣን አሸነፈና
ህዝቦችን ሁሉ ወደራሱ ሳለ (ቆላ. 2፡15፣ ዮሐ.12፡32) ከዚህ አንጻር ኢየሱስ
የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃላት ስለፈጸማቸው የኋለኛው ዘመን ጀምሯል
ማለት እንችላለን።
መንፈሳዊ አባቶቻችን የሞቱት በእምነት ነበር።ተስፋዎቻቸውን ከርቀት
አይተው ተሳለሟቸው ነገር ግን አልተቀበሏቸውም። እኛ ደግሞ በሌላ መልኩ
የተስፋ ቃላቱ በኢየሱስ መፈጸማቸውን ተመልክተናል።
ለጥቂት ደቂቃዎች ስለ እግዚአብሔር ተስፋዎችና ስለ ኢየሱስ እናስብ። አብ
ልጆቹን ከሞት እንደሚያስነሳ ቃል ገብቷል(1ተሰ. 4፡15-16)። መልካሙ ዜና
የልጆቹን ትንሳኤ በኢየሱስ ትንሳኤ አማካኝነት ማስጀመሩ ነው(1 ቆሮ.15፡
20፤ማቴ.27፡51-53)። አብ ስለ አዲስ ፍጥረት ተስፋን ሰጥቷል(ኢሳ 65፡17)።
ያንን ተስፋ ደግሞ በኛ ውስጥ አዲስ መንፈሳዊ ህይወትን በመፍጠር ጀምሮታል
(2 ቆሮ.5፡17፣ ገላ.6፡15)። የርሱን የመጨረሻ መንግስት እንደሚያቋቁም
ተስፋን ሰጥቶ ነበር(ዳን.2፡44) ያንን መንግስት ደግሞ እኛን ከሰይጣን ኋይል
ነጻ በማውጣትና ኢየሱስን ጌታችን በማድረግ አስጀመረው(ማቴ.12፡28-30፣
ሉቃ.10፡18-20)። ሆኖም ይህ ገና መጀመሪያው ብቻ ነው። አብ በክርስቶስ
የመጀመሪያ ምጻት ያስጀመረውን በሁለተኛው ምጻት ወደ ፍጻሜ ያመጣዋል።
ከዚህ በፊት የተፈጸሙ ተስፋዎችን ይመልከቱ። ባልተፈጸሙት
የተስፋ ቃላት ላይ በርሱ እንድንተማመን የሚረዱን እንዴት ነው?
ዕብራውያን 1፡1-4ን ያንብቡ። የዚህ ጥቅስ ዋነኛ ኃሳብ ምንድነው?
ዕብራውያን 1፡1-4 በኦሪጅናል ግሪኩ የተፃፈ ብቸኛ ዓረፍተ ነገር ሲሆን
ከስነፅሁፋዊ ውበቱ አንፃር በመላው አዲስ ኪዳን እጅግ ውብ የሆነ ነው ተብሎ
ይነገራል። ዋና ነጥቡ ደግሞ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ በኩል ተናግሮናል
የሚለው ነው።
ከክ.ል. በኋላ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ አይሁዶች
የእግዚአብሔርን ቃል ከሰሙ ቆይተዋል። የመጨረሻው የተፃፈው
የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ በነቢዩ ሚልክያስ እንዲሁም በእዝራና በነህምያ
አገልግሎት ከአራት መቶ ዓመታት በፊት ነበር። አሁን ግን በኢየሱስ በኩል
እግዚአብሔር እንደገና እየተናገራቸው ነበር።
በኢየሱስ በኩል የሆነው የእግዚአብሔር መገለጥ ግን በነቢያቱ በኩል ከሆነው
ይበልጣል ምክንያቱም ኢየሱስ የመገለጥ ታላቁ መንገድ ስለሆነ ነው። እሱ
ሰማይንና ምድርን የፈጠረውና ዓለማትን የሚገዛው ራሱ እግዚአብሔር ነው።
ለጳውሎስ የክርስቶስ አምላክነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አልነበረም፤ የታወቀ
ነገር ነበር።
በተጨማሪም ለጳውሎስ ብሉይ ኪዳንም የእግዚአብሔር ቃል ነበር። ያኔ ሲናገር
የነበረው አምላክ ዛሬም መናገሩን ቀጥሏል። ብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔርን
ፈቃድ እውነተኛ እውቀት ገልጧል።
ሆኖም ሙሉ በሙሉ መረዳት የሚቻለው ልጁ ወደዚህ ምድር ሲመጣ ብቻ
ነው። በፀሐፊው አእምሮ ልክ የሚገጣጠም ምስል መያዣ ላይ ያለው ምስል
ለእያንዳንዱ ተገጣጣሚ አካል ትክክለኛውን ቦታ እንደሚያስቀምጥ ሁሉ
የብሉይ ኪዳንን ጥልቀት ማስተዋል የሚቻለው አብ በልጁ በገለጠው ውስጥ
ነው። ኢየሱስ አብዛኛውን የብሉይ ኪዳን ክፍል ወደ ብርሃን አምጥቶታል።
ኢየሱስ የመጣው ወኪላችንና አዳኛችን ለመሆን ነው። በጦርነቱ ውስጥ የኛን
ቦታ ወስዶ ዘንዶውን አሸነፈልን። ልክ እንደዚያው በዕብራውያን መልዕክት
ኢየሱስ የአማኞች “መሪ” ወይም ቀዳሚና ጀማሪ ነው(ዕብ. 2፡10፣ ዕብ. 6፡
20)።
ለኛ ይዋጋል እንዲሁም በኛ ፋንታ ይቆማል። ይህ ማለት ደግሞ እግዚአብሔር
አብ ለወኪላችን ኢየሱስ ያደረገውን ሁሉ ለኛም ማድረግ ይፈልጋል። ኢየሱስን
በቀኙ ከፍ እንዲል ያደረገው እርሱ በዙፋኑ ላይ ከርሱ ጋር አብሮ መቀመጥ
ይፈልጋል(ራዕይ 3፡21)። በኢየሱስ ውስጥ እግዚአብሔር ለኛ ያለው መልዕክት
ኢየሱስ የተናገረውን ብቻ ሳይሆን ለኛ ምድራዊና ዘላለማዊ ትርፍ ሲል በርሱ
ውስጥ አብ ያደረገውንም የሚጨምር ነው።
ኢየሱስ- እግዚአብሔር ወደዚህ ምድር የመምጣቱን ትርጉም
ያሰላስሉ። ይህ እውነት እጅግ ብዙ ተስፋን የሚሰጠን እንዴት
ነው?
ዕብራውያን 1፡ 2-4ን ያንብቡ። ይህ ቦታ ስለ ኢየሱስ ምን ትምህርቶችን ይሰጠናል?
በዚህ ክፍል “እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥” (ዕብ. 1፡3) በሚለው ላይ እናተኩራለን። ዘፀ. 24፡16-17፣ መዝሙር 4፡6፣ መዝሙር 36፡9 እና መዝሙር 89፡15ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች የእግዚአብሔር ክብር ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት የሚረዱን እንዴት ነው?
በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ክብር ማለት በህዝቡ መካከል በሚታይ መልኩ
ሲገኝ ማለት ነው (ዘፀ. 16፡7፣ ዘፀ. 24፡16-17፣ ዘሌ. 9፡23፣ ዘሁ. 14፡10)። ይህ
መገኘት በአብዛኛው የሚገናኘው ከብርሃን ወይም ከነፀብራቅ ጋር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ክብር ለመግለፅ
ወደዚህ ዓለም የመጣ ብርሃን ነው(ዕብ. 1፡3፣ ዮሐንስ 1፡6-9፣ 14-18፣ 2ኛ
ቆሮ. 4፡6)። ለምሳሌ በመለወጥ ተራራ ኢየሱስ የተገለፀበትን ሁኔታ እናስብ።
“በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ
ሆነ።” (ማቴ. 17፡2)።
ልክ ፀሐይ በብርሃኗ ነፀብራቅ ብቻ ልትታወቅ እንደምትችል እግዚአብሔር
አብም የሚታወቀው በኢየሱስ በኩል ነው። እንደምናስተውለው ሁለቱም
አንድ ናቸው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ክብር ራሱ ብርሃን ስለሆነ በአብና
በወልድ መካከል ልክ በብርሃንና በነፀብራቁ መካከል ልዩነት እንደሌለ ሁሉ
ልዩነት የለውም።
የዕብራውያን መልዕክትም ኢየሱስ የአባቱ ባህሪ “ትክክለኛ መገለጫ” ነው
ይላል(ዕብ. 1፡3)። የአነጋገሩ ዋና ነጥብ በአብና በወልድ ባህሪና ህልውና
መካከል ፍፁም መመሳሰል አለ የሚለው ነው። ሰብዓዊ ዘሮች የርሱን አምሳል
ይዘናል እንጂ እኛው ራሳችን አምላክ እንዳልሆንን እናስታውስ (ዘፍ. 1፡26)።
ወልድ ግን ከአባቱ ጋር በሁሉም አንድ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ “እኔን ያየ አብን
አየ” (ዮሐንስ 14፡9) ማለቱ አይገርምም።
ኢየሱስ የአብን ባህሪና ክብር ለኛ መግለጡ የምስራች የሆነው
ለምንድነው? ኢየሱስ ስለ አብ ማንነት ምን ነገረን?
የዕብራውያን መልዕክት እግዚአብሔር ዓለምን በኢየሱስ እንደፈጠረና በርሱ ኃይልም ዓለም ፀንታ እንደቆመች ያረጋግጣል። ኢሳያስ 44፡24ን፣ ኢሳያስ 45፡18ንና ነህምያ 9፡6ን ያንብቡ። በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ብቻውን ዓለምን እንደፈጠረና እሱ ብቻ አምላክ እንደሆነ የሚናገረውን በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ዓለማትን በኢየሱስ ፈጠረ ከሚለው ጋር እንዴት እናስታርቀዋለን?
አንዳንዶች ኢየሱስ እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረበት መሳሪያ እንደነበር
ያስባሉ። ያ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም በመጀመሪያ ለጳውሎስ ኢየሱስ
ዓለምን የፈጠረ ጌታ እንጂ ረዳት አልነበረም። ዕብራውያን 1፡10 ላይ
እንደሚናገረው ኢየሱስ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ ጌታ መሆኑን እንዲሁም
በመዝሙር 102፡25-27 ላይ ለያህዌ የተጠቀመውን መገለጫ ተጠቅሟል።
በሁለተኛ ደረጃ ዕብራውያን 2፡10 እንደሚናገረው ዓለማት ሁሉ የተፈጠሩት
በአብ ነው ይላል። (በዕብራውያን 1፡2 ላይ ለኢየሱስ የተጠቀመውን ተመሳሳይ
አገላለፅ በመጠቀም ማለት ነው)። አብም ፈጥሯል ኢየሱስም ፈጥሯል (ዕብ.
1፡2፣ 10፣ ዕብ. 2፡10)። በዐላማና በተግባር በዓብና በወልድ መካከል ፍፁም
ስምምነት አለ። የስላሴ ሚስጥር አንዱ ክፍል ይህ ነው።
ኢየሱስም ፈጥሯል፣ አብም ፈጥሯል፤ ነገር ግን አንድ ብቻ ፈጣሪ አለ፤ እርሱም
አምላክ ነው ማለትም ኢየሱስ አምላክ ነው።
በተጨማሪም ዕብራውያን 4፡13 ደግሞ ኢየሱስ ዳኛ እንደሆነም ይናገራል።
ለመግዛትና ለመዳኘት ያለውን ስልጣን ያገኘው ሁሉንም የፈጠረና አሁንም
እያኖረ ያለ አምላክ ስለሆነ ነው (ኢሳ. 44፡24-28)።
ዕብራውያን 1፡3 እና ቆላስያስ 1፡17 ኢየሱስ ዓለምን አፅንቶ እንዳቆመ
ያረጋግጡልናል። ይህ ደግፎ ማቆም መምራትን ወይም ማስተዳደርን የሚገልፅ
ነው። ፌሮን (ማቆየት፣ መደገፍ) የሚለው የግሪኩ ቃል ጀልባን የሚገፋን ንፋስ
(የሐዋ. ሥራ 27፡15፣17) ወይም ነቢያቱን የሚመራውን አምላክ (2 ጴጥ. 1፡21)
ለመግለፅ ጥቅም ላይ ውሏል። ስለዚህ ኢየሱስ እኛን መፍጠር ብቻ ሳይሆን
ደግፎ ያቆየን እርሱ ነው ማለት ነው። እያንዳንዷ እስትንፋስ፣ እያንዳንዷ የልብ
ምት፣ የመኖራችን እያንዳንዷ ቅፅበት የፍጥረታት መኖር መሠረት በሆነው
በኢየሱስ ውስጥ የሚገኝ ነው።
ሐዋ. ሥራ 17፡28ን ያንብቡ። ስለ ኢየሱስና እርሱ ስላለው ኃይል
ለኛ ምን ይነግረናል? ያው ኢየሱስ ደግሞ ለኃጢአታችን ሲል
በመስቀል ላይ የመሞቱን አንደምታ ደግሞ እናስብ። ይህ እውነት
ስለጌታችን ራስን የካደ ፍቅር ምን ያስተምረናል?
ዕብራውያን 1፡5 አብ ለኢየሱስ የተናገራቸውን ቃላት እንዲህ ብሎ ያስቀምጠዋል፡- “አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ”። ለኢየሱስ “ወለድኩህ” ሲባል ምን ማለት ነው? ይህስ መቼ ተፈጸመ? ይህ ብዙዎች እንደሚያምኑት ኢየሱስ ቀደም ብሎ በእግዚአብሔር ተፈጥሯል የሚለውን አያሳይም? ዕብራውያን 1፡5ን፤2 ሳሙ.7፡17-14ን፤ መዝ. 2፡7ንና ሉቃስ 1፡31-32ን ያንብቡ። ለዳዊት የተገባውን የትኛውን ተስፋ ነው ጳውሎስ ለየሱስ የተጠቀመው?
ኢየሱስ ተወለደ የተባለው እንደ ዳዊት ልጅ ተስፋ እንደተገባው ገዢ
በእግዚአብሔር መቆጠሩን ለመግለጽ ነው። ለንጉስ መለኮታዊ አባት መሆን
የሚለው ጽንሰ ኃሳብ በግሪኮ-ሮማንና በምስራቁ ዓለም የታወቀ ኃሳብ ነው።
ገዢው መሬቱን ለመግዛት ሙሉ መብትና ኃይልን ይሰጠዋል።
እግዚአብሔር ለዳዊት ልጁ በህዝቦች ሁሉ ላይ እውነተኛ ገዢ እንደሚሆን
ቃል ገብቶለታል የዳዊትን እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ እንደሚወስደው ይናገራል።
በዚህ ሂደት ውስጥ ዳዊታዊው ንጉስ የእግዚአብሔር ወራሽና ስልጣን ተቀባይ
ይሆናል። እግዚአብሔር ጠላቶቹን ይረታለትና ህዝቡን የርሱ ውርስ አድርጎ
ይሰጠዋል(መዝ. 89፡27፤መዝ. 2፡7-8)።
በሮሜ 1፡3-4 እና በሐዋ.ሥራ 13፡32-33 ኢየሱስ በይፋ እንደ እግዚአብሔር
ልጅ ተገልጧል። የሲየሱስ ጥምቀትና የመልኩ መለወጥ እግዚአብሔር እርሱን
ልጄ ብሎ የጠራባቸው ክስተቶች ናቸው(ማቴ. 3፡17፤ማቴ.17፡5)።
ሆኖም እንደ አዲስ ኪዳን ገለጻ ኢየሱስ ከሞት ሲነሳና በእግዚአብሔር
ቀኝ ሲቀመጥ “ኃያል የእግዚአብሔር ልጅ” ሆኗል። በዚህ ቅጽበት ነበር
እግዚአብሔር ለዳዊት ልጅ የራሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚሆንና ግዛቱም
ለዘላለም እንደሚሆን የተገባለት ቃል የተፈጸመው። (2 ሳሙ. 7፡12-14)
ስለዚህ ቄሳር(የሮም ምሳሌ) የእግዚአብሔር ልጅ ያልነበረ ገዢ ነበር። ኢየሱስ
ግን ነበር። የኢየሱስ መወለድ በህዝብ ላይ ገዢ የመሆን መጀመሪያ እንጂ እርሱ
ሁሌም ስለነበረ መኖር የጀመረበት አይደለም። ኢየሱስ ያልነበረበት ጊዜ የለም
ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ ነው።
እንደውም ዕብራውያን 7፡3 ላይ ኢየሱስ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም
ይላል ምክንያቱም እርሱ ዘላለማዊ ስለሆነ ነው(ዕብ.13፡8)። ስለዚህ ኢየሱስ
የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ሲባል ስለ አምላክነቱ ሳይሆን እርሱ የኪዳናት
ሁሉ ፍጻሜ ስለሆነ በድነት ዕቅድ ውስጥ ስላለው ሚና ጅማሮ እየተናገረ ነው።
ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ወደዚህ ምድር
መምጣቱ የተለያዩ ተግባራትን በአንድ ጊዜ የፈፀመ ነው። በመጀመሪያ
የእግዚአብሔር መለኮታዊ ልጅ ኢየሱስ አብን ለኛ ለመግለፅ(ለመተረክ) መጣ።
በተግባሩና በንግግሩ አብ ምን አይነት አምላክ እንደሆነና እርሱን መታመንና
መታዘዝ ስላለብን ምክንያት አሳየን።
ደግሞም ኢየሱስ ጠላትን አሸንፎ ዓለምን የሚገዛው ተስፋ የተሰጠው የዳዊት፣
የአብርሃምና የአዳም የተስፋው ልጅ ሆኖ መጣ። ስለዚህ ኢየሱስ የአዳምን
ቦታ ወስዶ የሰብዓዊ ዘር ራስ በመሆን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን
የመጀመሪያ ዓላማ ለመፈፀም መጣ (ዘፍ. 1፡26-28፣ መዝ. 8፡3-8)።
“በዮርዳኖስ ስለ ኢየሱስ የተነገሩት ቃላት “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ
ይህ ነው” ሰብዓዊ ዘርን ሁሉ የጠቀለለ ነው። እግዚአብሔር ለኢየሱስ ሲናገር
እንደወኪላችን ነበር። በብዙ ኃጢአታችንና ድክመታችን የማትረቡ ተብለን
አልተጣልንም።
“በውድ ልጁ አማካኝነት ተቀባይነት አግኝተናል” ኤፌ. 1፡6 በክርስቶስ ላይ
ያረፈው ክብር እግዚአብሔር ለኛ ያለው ፍቅር መያዣ ነው። . . . ሰማይ
ተከፍቶ በአዳኛችን ላይ የበራው ብርሃን እኛ ፈተናን ለመጋፈጥ ስንፀልይ በኛ
ላይ ያርፋል። ያ ለኢየሱስ የተናገረው ድምፅ ለእያንዳንዱ አማኝ “በእርሱ
ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” ይላል።” ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት
ምኞት፣ ገፅ 113
1. የኢየሱስን ቃላትና ተግባራት መረዳት እግዚአብሔር አብን
ለመረዳት እንደሚረዳ ተምረናል። ስለ ኢየሱስ የተሻለ መረዳት
ከአብ ጋር ያለንን ግንኙነት እንዲያድግ የሚያደርገው እንዴት
ነው?
2. እግዚአብሔር ለእየሱስ የተናገረውንና ለርሱ ያደረገውን ለኛ
መናገርና ማድረግ እንደሚፈልግ ተምረናል። ይህ እኛ ከሌሎች
ጋር እንዴት መኖር እንዳለብን ምን ይነግረናል?
3. ስለ ኢየሱስ ዘላለማዊ አምላክነት አስፈላጊነት ጊዜ ወስደው
ያስቡ። የተሰቀለው ኢየሱስ በአንድ ወቅት በሆነ መልኩ ልክ
እንደ እኛ ተፈጥሯል ብለን ብናምን ምን ይጎድላል? ያንን ደግሞ
ዘላለማዊ አምላክ ሆኖ ራሱ መጥቶ በመስቀል ሞተልን ከሚለው
ኃሳብ ጋር ያነፃፅሩት። በሁለቱ ኃሳቦች መካከል ያለው ትልቅ
ልዩነት ምንድነው
4. በሰንበት ትምህርት ክፍላችሁ ለእግዚአብሔር ክብር ስለ
መስጠት ተወያዩ። ዮሐንስ ራዕይ 14፡7ን ያንብቡ። ለእግዚአብሔር
ክብር መስጠት የሶስቱ መላዕክት መልዕክት ወቅታዊ እውነት
አንድ አካል የሚሆነው እንዴት ነው?