የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘዳ. 5:22–29፣ ዘዳ. 4:25–31. ዘዳ. 30:1–10፣ ማቴ. 3:1–8፣ ማር. 1:15፣ ሐዋ. 2:37፣ 38
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “‘ነገር ግን እዚያም ሆናችሁ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ’ ” (ዘዳ. 4:29)
ቀ
ላል የሕይወት እውነታ እኛን ሁላችንንም ይከተለናል፡ ሁላችንም
ኃጢአተኞች ነን። አልፎ አልፎ አንዳንድ “ዐዋቂ” ነን ባዮች-ሰብዓዊነት መሠረታዊ ምግባረ ብልሹነት ገጥሞታል በሚለው
የክርስቲያኖች ጽንሰ ሀሳብ ላይ ሲያላዝኑ ቢደመጡም፤ ነገር ግን የዕለቱን ዜና
ቢያጤኑ ወይም የሰብዓዊውን ታሪክ አለፍ አለፍ ብለው ቢቃኙ የዚህ ክርስትና
አስተምህሮ እውነታ በግልጽ ይታያል።
ወይም የተሻለው ቀላል መንገድ ራስን በመስታወት መመልከት ነው።
ለነገሩ የልቡን ውስጠኛ ክፍል በጥልቅ የመመርመር ድፍረቱ ያለው ማንም
ሰው የሮሜ 3፡9-23 እውነትነት ይገነዘባል፡ “ሁሉም ኃጢአት ሠርተዋል፣
የእግዚአብሔም ክብር ጎድሏቸዋል።”
እንደ እውነቱ ከሆነ አብልጦ መልካም የሆነው የምሥራች በቀጣዩ ቁጥር ላይ
ይገኛል፡ “የየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት እንዲያው በጸጋው ጸድቀዋል” (ሮሜ
3፡24)። የዚህ ታላቅ የምሥራች ወሳኝ ክፍል ንስሐ ነው፡ ኃጢአተኝነታችንን
ማመን፣ ስለ በደለኝነታችን ማዘን፣ የእግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና
በመጨረሻም ከኃጢአት መራቅ። እኛ ኃጢአተኞች እንደመሆናችን ንስሐ
የክርስቲያናዊ ሕልውናችን ዋና አካል መሆን አለበት። በዚህ ሳምንት በዘዳግም
በተለገለጸው መሠረት የንስሐን ጽንሰ ሀሳብ እንመለከታለን።
እንደ አብዛኞቹ ቋንቋዎች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ዕብራይስጥም በፈሊጣዊ
አነጋገሮች የተሞላ ነው። አንዳንድ ልዩ ቃላት በተለምዶ ካላቸው ፍቺ ውጪ
ትርጉም ይኖራቸዋል። በብሉይ ኪዳን ከምናገኛቸው ፈሊጣዊ ቃላት መሃል
አንዱ “ሚ-ይትን” ነው። “ሚ”--“ማን?” የሚል ፍቺ ያለው ሲሆን “ይትን”
ደግሞ “ይሰጣል” ማለት ነው። ስለዚህ “ሚ-ይትን”--“ማን ይሰጣል” የሚል
ፍቺ አለው።
ይሁን እንጂ ሐረጉ በብሉይ ኪዳን አንድን ነገር በብርቱ የመፈለግን ጠንካራ
ምኞት ጽንሰ ሀሳብ ይገልጻል።
ለምሳሌ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ ፈተና
በተጋረጠባቸው ጊዜ “‘በግብፅ ሳለን ምነው በእግዚአብሔር እጅ ሞተን
ባረፍነው ኖሮ!’ ” (ዘፀ. 16፡3) ብለው ጮኸው ነበር። “ምነው” የተሰኘው ቃል
የመጣው ከ“ሚ-ይትን” ነው።
በመዝ. 14፡7 ዳዊት “ምነው እስራኤልን የሚያድን ከጽዮን በወጣ!” ሲል
ይደመጣል። በጥቅሱ ጥቅም ላይ የዋለው የዕብራይስጡ ቃል “ኦ” ሳይሆን
“ሚ-ይትን” መሆኑን ልብ ይሏል።
በኢዮ. 6፡8 “ምነው ልመናዬ በተመለሰልኝ” በሚለው ሀረግ ውስጥ “ምነው”
በሚል የቀረበው ቃል የተወሰደው “ሚ-ይትን” ከተሰኘው እንጂ “ኦ” ከሚል
ቃል አይደለም።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 5፡22-29። ትኩረትዎን በተለይ በቁ.
29 ላይ ያድርጉ። “ሚ-ይትን” ከሚለው ቃል ተወስዶ “ምናለ”
በሚል የተተረጎመው ቃል ፍቺው ምንድን ነው?
ጠፈርን የዘረጋ፣ ጊዜን የቀመረ፣ በቃሉ ትእዛዝ ምድራችንን ወደ መኖር
ያመጣ፣ በአዳም ላይ የሕይወት እስትንፋስ እፍ ያለ ፈጣሪ አምላክ--ይህን
በአጠቃላይ ከሰው ልጅ ድክመትና ውሱንነት ጋር የተቆራኘ ሀረግ ይናገራል።
የመምረጥ ነጻነትን በተጨባጭ የሚያሳይ እንዴት ያለ ምሳሌ ነው! በታላቁ
ተቃርኖ ግብግብ መሃል እግዚአብሔር ሊያደርግ የሚችላቸውን ነገሮች
ውሱንነት እዚህ ላይ እንመለከታለን። እርሱ እግዚአብሔር አምላክ ቢሆንም
እንኳ፣ የማንንም የመምረጥ ነጻነት መጋፋት እንደማይችል ይህ የ “ሚ-ይትን”
ቃል አጠቃቀም ይገልጥልናል። ይህን ቢያደርግ ግን፣ የመምረጥ ነጻነት በዚያው
ቅጽበት ያከትምለታል።
እኛ ሰብዓዊ ፍጡራን ኃጢአት የመሥራት ነጻነት እንዳለን ሁሉ፡ ጌታን
መምረጥ፣ ለእርሱ ምሪት ክፍት መሆን፣ ለመንፈሱ ምላሽ መስጠት፣
ለኃጢአታችን ንስሐ መግባትና እርሱን የመከተል ምርጫ የማድረግ ነጻነትም
እንዲሁ አለን። ውሎ አድሮ ምርጫው የእኛና የእኛ ብቻ ሲሆን--በየዕለቱ
ብሎም በየቅጽበቱ ማድረግ ይጠበቅብናል።
በቀጣዮቹ ሰዓታት ወይም ጥቂት ቀናት ሊጋፈጡ የሚችሏቸው
ምርጫዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? ጌታ በሚሰጥዎት ብርታት
ትክክለኛውን ምርጫ መምረጥ ይችሉ ዘንድ ፈቃድዎን
ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠትን እንዴት መማር ይችላሉ?
የእግዚአብሔር አስቀድሞ የማወቅ ችሎታ በመላው የመጽሐፍ ቅዱስ
መልእክቶች በማስረጃ ተጠቅሶ እናገኛለን። የመንግሥታትን መነሣትና
መውደቅ (ዳን. 7) ወይም የግለሰቦች ድርጊት ከመፈጸማቸው በፊት ያውቃል፡
- “ ‘እውነት እልሃለሁ በዛሬዋ ሌሊት ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ
ትክደኛለህ’ ” (ማቴ. 26፡34)። ጌታ ከመጨረሻ እስከ መጀመሪያ ያለውን
ያውቃል። እኛ የመምረጥ ነጻነታችንን ተጠቅመን የቱንም ዓይነት ምርጫ
ብናደርግ፣ የእርሱ ነገሮችን አስቀድሞ የማወቅ ችሎታ በምርጫዎቻችን ላይ
የሚያሳርፈው አንዳችም ተጽእኖ አይኖርም።
ስለዚህ ጌታ የእስራኤልን ልጆች ወደ ተስፋይቱ ምድር ከማምጣቱ በፊት
በምድሪቱ ምን እንደሚያደርጉ ያውቅ ነበር።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 4፡25-28። እስራኤላውያን ቃል ወደ
ተገባላቸው የተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላ ምን እንደሚያደርጉ
ጌታ አስቀድሞ ምን አለ?
ቀደም ባሉት ጥቅሶች በተለይ ጣዖታትን እንዳይሠሩና እንዳያመልኳቸው
ጌታ ነግሯቸዋል (ዘዳ. 4፡15-20)። ሆኖም እነዚያ ሁሉ ማስጠንቀቂያዎች
ቢሰጧቸውም ጣዖት ሠርቶ ማምለክ በትክክል የሚያደርጉት ነገር መሆኑን
የሚከተሉት ጥቅሶች በትክክል ይናገራሉ።
ይህ የተባለው ነገር ወዲያውኑ እንደማይከሰት ሙሴ በግልጽ ማስቀመጡን
ልብ ይበሉ፡ በዘዳ. 4፡25። ካለፉበት ተሞክሮ አኳያ ወዲያውኑ በጣዖት አምልኮ
ሊወድቁ የሚችሉበት ዕድል አልነበረም። ሆኖም ከጊዜ በኋላ፣ ትውልድ አልፎ
ትውልድ ሲተካ፣ ጌታ ያደረገላቸውን “እንዳትረሱ” (ዘዳ. 4፡9) ሲል በትክክል
ቢያስጠነቅቃቸውም እነርሱ ግን ወደ መርሳትና አታድርጉ የተባሉትን ወደ
ማድረግ ሲያዘነብሉ ይታያሉ።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 4፡29-31። በዚህ ልዩ ሁኔታ ጌታ ምን
አደርጋቸዋለሁ አለ?
የእግዚአብሔር ጸጋ አስደናቂ ነው። አሰቃቂ በሆነው ክፉ የጣዖት አምልኮ
ከወደቁና ኃጢአታቸው ያስከተለባቸውን መዘዝ ከተቀበሉ በኋላም እንኳ
ወደ ጌታ ቢመለሱ ይቅር ይላቸዋል፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታም ይመልሳቸዋል።
በአጭሩ ንስሐ ለመግባት ምርጫ ካደረጉ፣ ንስሐቸውን ይቀበላል።
በዘዳ. 4፡30 “ትመለሳለህ” በሚል የተተረጎመው ቃል “እንደገና ትመለሳለህ”
የሚል ጥልቅ ትርጉም አለው። ይኸውም እንደገና ወደ ጌታ መመለሳቸውን
ያሳያል። “ተሹቫህ” የተሰኘው ይኸው ዕብራይስጥ ሥርወ ቃል “ንስሐ” የሚል
ፍቺ አለው።
ንስሐው የቱንም ዓይነት መሠረታዊ ነገር ቢያካትትም፤
ወሳኙ ነገር በኃጢአታችን ከእርሱ ከተለየን በኋላ እንደገና ወደ
እግዚአብሔር መመለሳችን ነው።
በአጠቃላይ በዘዳግም መጽሐፍ አንድ ቁልፍ ጭብጥ ቁልጭ ብሎ
ይታያል፡ ጌታን ብትታዘዙ በረከት ታገኛላችሁ ባትታዘዙ ግን አለመታዘዛችሁ
የሚያስከትለውን መዘዝ ትቀበላላችሁ--የሚል። ይህ ጭብጥ ከአዲስ ኪዳን
ጋር ልዩነት የለውም። “አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው
የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል። ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ
ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን
ሕይወት ያጭዳል (ገላ. 6፡7-8)።
እንደ አለመታደል ሆኖ ሰው ውድቀት ከደረሰበት በኋላ ኃጢአት እንደ
እስትንፋስ ቀላልና ተፈጥሮአዊ መሰለ። “በዛሬው ዕለት የምሰጥህ ትእዛዝ
ይህን ያህል አስቸጋሪ ወይም ከአንተ የራቀች አይደለችም” (ዘዳ. 30፡11) በሚል
እነዚያ ሁሉ ማስጠንቀቂያዎች እና የተስፋ ቃሎች ቢሰጡም-- አብዛኛው
ሕዝብ እግዚአብሔር በትክክል ያስጠነቀቀውን ኃጢአት ተላልፎ ወደቀ።
በዚህን ጊዜም ቢሆን፤ የመምረጥ ነጻነታቸውን ተጠቅመው፣ ንስሐ
ገብተውና እንደገና ተመልሰው የሚመርጡት ከሆነ፣ እግዚአብሔር መልሶ
የራሱ ሊያደርጋቸው ፈቃደኛ ነበር።
ጥቅሶቹን በድጋሚ ያንብቡ፡ ዘዳ. 30፡1-10። እነዚህ ሕዝቦች ያን
ሁሉ ስህተት ከፈጸሙ በኋላም እንኳ ጌታ ምን እንደሚያደርግላቸው
ነው የሚናገረው? ሆኖም፣ እነዚህ አስደናቂ ተስፋዎች ያረፉበት
ቅድመ ሁኔታ ምን ነበር?
የመልእክቱ ጽንሰ ሀሳብ ቀላልና ቀጥተኛ ነው፡ ታማኝነታችሁን ብታጎድሉ
እናንተንም ሆነ ቤተሰባችሁን አስከፊ መዘዝ ይከተላል። ኃጢአት የሚያደርገው
ይህንኑ ነው። ሆኖም፣ በዚያው ቅጽበት ንስሐ የምንገባ ከሆነ፣ ጌታ መልሶ
ወገኑ አድርጎ ተቀብሎ በበረከት ይሞላናል።
ተመሳሳይ የዕብራይስጥ ስርወ ቃል ያለው ተሹቫህ በእነዚህ ጥቅሶች
በተደጋጋሚ ቀርቦ እንመለከታለን፡ “ ‘ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር
ተመልሳችሁ…’ ” (ዘዳ. 30፡2)፣ “ ‘አንተም ተመልሰህ ለእግዚአብሔር
ትታዘዛለህ’ ” (ዘዳ. 30፡8) የሚል ቢሆንም፣ ነገር ግን ቃሉ በተደጋጋሚ
የተተረጎመው “እንደገና የጌታን ድምፅ ትታዘዛለህ” በሚል ነው። በመጨረሻ
በዘዳ. 30፡10 ይህን እናገኛለን--“ ‘አምላክህን እግዚአብሔርን ከታዘዝህና…
በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ስትመለስ
ነው’ ” (ዘዳ. 30፡10)። አሁንም “ስትመለስ” የሚለው ቃል እንደገና መመለስ
የሚል ፍቺ አለው።
በሌላ አነጋገር፣ የገቡትን ቃል ኪዳን ማፍረሳቸውን ተከትሎ ያ ሁሉ
ሲደርስባቸው ጌታ ሙሉ ለሙሉ ከእነርሱ ጋር አልነበረም። ይህ እንዳይሆን
ከፈለጉ እንደገና መመለሳቸውን በንስሐ መግለጥ ይችላሉ።
ምንም እንኳ ጥቅሶቹ በአጠቃላይ ከሕዝቡ ጋር ስለተገባው
ውል ከማውሳታቸው አኳያ ከዛሬው የእኛ ዘመን ጋር የተለያየ
ዐውድ ሊኖራቸው ቢችልም፤ አልፎ አልፎ ከእግዚአብሔር ጋር
የገባነውን ኪዳን ለምንጥስ ለእኛ--የእውነተኛ ንስሐን ተጨባጭ
እውነታ ምን ያህል ያንጸባርቃሉ?
ዘዳ. 30፡1-10 ክህደት ለፈጸሙና ለኃጢአተኞች የቀረበውን አምላካዊ ጸጋ
እና ቸርነት ይገልጣል። እንዳውም እነዚህ ክህደት የፈጸሙና ኃጢአተኞች
በተለየ መንገድ በእግዚአብሔር መባረካቸውን ሲገልጽ፡ “ ‘በምንጠራው ጊዜ
ሁሉ አምላካችን እግዚአብሔር ለእኛ ቅርብ እንደሆነ አማልክቱ የሚቀርቡት
ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማነው?’ ” ይላል። ምንም እንኳ እግዚአብሔር ያን ሁሉ
መልካም ነገር ቢያደርግላቸውም፤ እነርሱም ለኃጢአታቸው ሊያቀርቡ
የሚችሉት አንዳችም ምክንያት ወይም ሰበብ ባይኖራቸውም--ኃጢአት ግን
ሠሩ (ስለዚህ መናገር የሚችል ይኖራል?)
ያም ሆኖ፣ በዚያን ጊዜም ቢሆን—ምን ማለት ነው?
በዘዳ. 30፡1-10 በቀረበው ንስሐ እና እንደገና ወደ እግዚአብሔር
መመለስ (ተሹቫህ) ይዟቸው በነበረው ነገሮች ያተኩሩ። የተጠየቀው
ምን ነበር? እውነተኛ ንስሐ ስለሚያካትት ነገር ዛሬ ያ ምን
ሊያስተምረን ይገባል?
በመጨረሻ ወደ እርሱ ለመመለስና በሙሉ ልባቸው እርሱን ለመታዘዝ
ምርጫ ማድረግ ነበረባቸው። በአንድ በኩል አንገብጋቢው ጉዳይ የልባቸው
ሁኔታ ነበር። ምክንያቱም ልቦቻቸው ከእግዚአብሔር ጋር ቀና ቢሆኑ፣
ድርጊቶቻቸውም ያንኑ ይከተሉ ነበር--ማለትም ታዛዥ ይሆናሉ።
ወደ ጌታ ከተመለሱ፣ ከልባቸው ወደ እርሱ እንደገና ከመጡ፣ በእነርሱ ውስጥ
እንደሚሠራና ልባቸውንም “እንደሚገርዝ” ይህ ድንቅ ተስፋ የተሰጣቸው
ለዚህ ነው። በምርኮ ወድቀውም ወደ እግዚአብሔር የመመለስ ምርጫ
ማድረግ ነበረባቸው። ይህ ሲሆን ወደ ራሱና ወደ ምድሪቱ ይመልሳቸዋል።
ከዚያም በምድሪቱ ሆነው ይባርካቸዋል። ከመባረካቸው ጎን ለጎን ልቦቻቸውን
ይበልጥ ወደ እርሱ የማምጣት ሥራ በእነርሱ ውስጥ የሚሠራ ሲሆን፤
ይኸውም እነርሱና ልጆቻቸው ጌታ አምላካቸውን በፍጹም ልባቸው፣ በፍጹም
ነፍሳቸው፣ በፍጹም ኃይላቸው ይወዱ ዘንድ ነው።
በመጨረሻ ለእግዚአብሔር ሳይዘገዩ ምላሽ በመስጠት (ሐዋ. 5፡31) በእውነት
ለኃጢአታቸው ንስሐ መግባት ነበረባቸው። ምንም እንኳ ከተለየ የታሪክ
ዐውድ ቢቀርብም፣ ኤለን ኋይት የሚከተለውን ጽፋለች፡ “ህዝቡ ያለቀሱት
ኃጢአታቸው በራሳቸው ላይ ሥቃይ ስላመጣባቸው እንጂ ቅዱስ ሕግጋቱን
በመተላለፍ እግዚአብሔርን በማዋረዳቸው አልነበረም። እውነተኛ ንስሐ
ለኃጢአት ከማዘን በላይ ነው። ከክፉ የመመለስ ጽኑ ውሳኔ ነው።” የኃይማኖት
አባቶችና ነቢያት ክፍል፡ 2 ገጽ፡ 211። ይህ በዘዳ. 30፡1-10 የምናየው እውነታ
ነው
ኃጢአታችን ለሚያስከትለው መዘዝ በመጸጸትና (ማንም
የሚያደርገው) ስለ ኃጢአታችን በማዘን መካከል ያለውን ልዩነት
እንዴት ማወቅ እንችላለን? ልዩነቱ ያን ያህል አስፈላጊ የሆነው
ለምንድን ነው?
አዲስ ኪዳን በንስሐ ጽንሰ ሀሳብ የተሞላ መሆኑ እርግጥ ነው። ደግሞስ፣ መጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎቱን የሚጀምረው የንስሐ ጥሪ በማቅረብ አይደል? ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 3፡1-8። “የመመለስ” ጽንሰ ሀሳብ በጥቅሶቹ የቀረበበት መንገድ ምን ይመስላል? በሌላ አነጋገር፣ በዘዳግም መጽሐፍ ይገኝ የነበረውን ጽንሰ ሀሳብ በሚያንጸባርቅ መልኩ ዮሐንስ ምን እንዲያደርጉ እየነገራቸው ነው? ደግሞስ ቃላቱ ለፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን የነበራቸው ልዩ ጠቀሜታ ምን ነበር?
የሱስም ቢሆን አገልግሎቱን የጀመረው የንስሐ ጥሪ በማቅረብ ነበር። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 1፡15። የሱስ ምን አለ? ንስሐን ከወንጌል ጋር ለምን አዛመደው?
ዮሐንስ በተለይ ለኃይማኖት መሪዎች የተናገረውም ሆነ የሱስ በአጠቃላይ
ለሕዝቡ ያቀረበው ጥሪ ሀሳቡ አንድ ነው። እኛ ኃጢአተኞች ነን። ክርስቶስ
የመጣው ኃጢአተኞችን ለማዳን ቢሆንም ስለ ኃጢአታችን ንስሐ ልንገባ
የግድ ይሆናል። ይህ ንስሐ ደግሞ--ክህደት በመፈጸም ወይም በታማኝነት
እየተመላለሱ በኃጢአት መውደቅ ወይም ደግሞ እንደ አዲስ ወደ ጌታ
በመምጣት--ከቀድሞው የኃጢአት መንገድ መመለስን ያካትታል።
ኃጢአተኝነታችንን አምነን መቀበል እና ለበደላችን ንስሐ መግባታችንን
(ስላስከተለው መዘዝ ብቻ አይደለም) ገልጸን ማሳየት ይኖርብናል። እነዚህን
ኃጢአቶች በማስወገድ እና የሱስ በሠራልን የጽድቅ ሥራ ሙሉ በሙሉ
በመመካት፣ የእግዚአብሔርን ድምጽ በመስማት (ዘዳ. 15፡5) ንቁ ውሳኔ
መወሰን ይኖርብናል።
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በዘዳግም መጽሐፍ የተገለጠው
የንስሐ ጽንሰ ሀሳብ በአዲስ ኪዳንም ሲያስተጋባ ይመለከታሉ። ለምሳሌ ሕዝቡ
የሱስን ሰቀላችሁት ብሎ ሲከሳቸው “ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ልባቸው
እጅግ አዘነ፤ ጴጥሮስንና ሌሎቹንም ሐዋርያት፣ ‘ወንድሞች ሆይ፤ ታዲያ ምን
እናድርግ? አሏቸው’ ” (ሐዋ. 2፡37)። ይህ ኃጢአታቸውን መገንዘብ ነው። ስለ
በደላቸው መጸጸት ነው (“ልባቸው እጅግ አዘነ”)፣ አሁን ባሳዘኑት አምላክ ፊት
ሞገስ ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለማወቅ ፈለጉ።
እኛ ሁላችን ኃጢአተኞች ከመሆናችን አኳያ ይህ ከእኛ ሁኔታ ጋር
ተመሳሳይ ነው፡ እግዚአብሔርን ያሳዘኑ ኃጢአተኞች?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሐዋ. 2፡38። ጴጥሮስ ለጥያቄአቸው ምላሽ
የሰጠው እንዴት ነበር? ይህ ትዕይንት ከእውነተኛ ንስሐ በስተጀርባ
ያለውን መርኅ እንዴት ያሳያል?
“በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ በምናደርገው
እያንዳንዱ እርምጃ የንስሐ ሕይወት ይበልጥ ያጠናክረናል። ጌታ ይቅር
ላላቸውና ሕዝቡ አድርጎ ለተቀበላቸው እንዲህ ይላል፡ ‘ከዚያም ክፉ
መንገዳችሁንና የረከሰ ሥራችሁን ታስታውሳላችሁ፤ ስለ ኃጢአታችሁና
ስለ አስጸያፊ ድርጊታችሁ ራሳችሁን ትጠላላችሁ።’ (ሕዝ. 36፡31) አሁንም
እንዲህ ሲል ይናገራል፡ ‘ስለዚህ ከአንቺ ጋር ቃል ኪዳኔን ዐድሳለሁ፤ በዚያ
ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ። ያደረግሽውን ሁሉ ይቅር
ባልሁሽ ጊዜ፣ በደልሽ ትዝ ሲልሽ ታፍሪያለሽ፤ ከውርደትሽም የተነሣ አፍሽን
ከቶ አትከፍቺም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።” (ሕዝ. 16፡62-63)።
ያ ሲሆን
ከንፈሮቻችን ራሳችንን ለማወደስ አይከፈቱም። ብቃታችን በክርስቶስ ብቻ
መሆኑን እናውቃለን። የሐዋርያትን የኃጢአት ኑዛዜ የራሳችን እናደርጋለን።
‘በእኔ፣ ማለትም ኃጢአተኛ በሆነው ተፈጥሮዬ ውስጥ ምንም በጎ ነገር
እንደማይኖር ዐውቃለሁ’ (ሮሜ 7:18)። ‘ነገር ግን ዓለም ለእኔ ከተሰቀለበት፣
እኔም ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር፣
ሌላው ትምክሕት ከእኔ የራቀ ይሁን።’ ገላ. 6:14.”—Ellen G. White,
Christ’s Object Lessons, pp. 160, 161.
“ ‘የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ የሚመራ’ ነው (ሮሜ 2፡4። የወርቅ
ሰንሰለት የሆነው የመለኮታዊ ፍቅር ምሕረት እና ርኅራኄ ወደ እያንዳንዱ አደጋ
ላይ ያለ ነፍስ ይተላለፋል። ጌታ እንዲህ ሲል ያውጃል፡ ‘በዘላለማዊ ፍቅር
ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህም በርኅራኄ ሳብሁሽ።’ ኤር. 31:3.”—Ellen G. White,
Christ’s Object Lessons, p. 202.
1.ምንም እንኳ ንስሐ መግባት ቢኖርብንም፣ ነገር ግን አስመስጋኝ
ሥራ እንደሠራን አድርጎ ከማሰብ ወጥመድ መጠበቅ የምንችለው
እንዴት ነው? በእግዚአብሔር ፊት ቀና ሆነን መታየት የምንችልበት
ብቸኛው መንገድ ምንድን ነው?
2.“አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ኢየሱስ እንደ ተፈረደበት ባየ ጊዜ
ተጸጸተ፤ የወሰደውንም ሠላሳ ጥሬ ብር ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ
ሽማግሌዎች መልሶ በመስጠት፣ ‘ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠቴ
በድያለሁ’ አለ። እነርሱም ‘ታዲያ እኛ ምን አገባን፤ የራስህ ጉዳይ
ነው’ አሉት። ስለዚህ ይሁዳ ብሩን በቤተ መቅደስ ውስጥ ወርውሮ
ወጣ፤ ሄዶም ራሱን ሰቅሎ ሞተ።” (ማቴ. 27፡3-5)። ይሁዳ
በየሱስ ላይ በሠራው ነገር መጸጸቱ ምንም አያጠራጥርም (ራሱን
እስከማጥፋት አድርሶታልና)። የእርሱ ድርጊት እንደ እውነተኛ
ንስሐ የማይቆጠረው ለምንድን ነው?
3.የሰብዓዊው ፍጡር ኃጢአተኝነት ተጨባጭ እውነታ ብሎም
የገዛ ኃጢአተኝነታችን፣ በሌሎች (ላይ እንዳንፈርድ) እንዲሁም
በእግዚአብሔር ፊት ትሁት ሊያደርገን የሚገባው እንዴት ነው?
ኃጢአት የእግዚአብሔርን ልጅ እኛን ለማዳን ሲል እስከ ሞት
ያደረሰው የመሆኑ ተጨባጭ እውነታ፤ ኃጢአት ምን ያህል
አስከፊ እንደሆነ እንዴት ያሳየናል?