የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ማቴ. 4:1–11፣ ዘዳ. 8:3፣ ሐዋ. 10:34፣ ገላ. 3:1–14፣ ሐዋ. 7:37፣ ዕብ. 10:28–31።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ ‘ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም” ’” (ማቴ.4፡4)።
አ
ዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳን መልእክቶች የተሞላ መጽሐፍ ነው። በሌላ
አነጋገር በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት አዲስ ኪዳንን የከተቡ ጸሐፊዎች፣
በተመሳሳይ መንፈስ ብሉይ ኪዳንን የጻፉ ወገኖችን መልእክት እንደ
ሥልጣን ምንጭ በመጥቀስ ጥቅም ላይ አውለዋል። የሱስ ራሱ፡ “ተጽፎአል”
(ማቴ. 4፡4) ሲል የተናገረ ሲሆን፣ ፍቺው “በብሉይ ኪዳን ተጽፎአል”
እንደ ማለት ነው። ደግሞም፡ “መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ” (ማር.
14፡49) ብሎ ተናግሯል። እዚህ ላይ መጻሕፍት--የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
መሆናቸውን ልብ ይሏል።
እንዲሁም የሱስ ኤማሁስ ወደሚባለው መንደር
በሚወስደው መንገድ ላይ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት በተገናኛቸው ጊዜ፣
ታምራዊ በሆነ መንገድ ራሱን አልገለጠላቸውም ነበር። ይልቁንም “ከሙሴና
ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ እርሱ የተጻፈውን አስረዳቸው”
(ሉቃ. 24፡27)።
የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በቀጥታ ከብሉይ ኪዳን መልእክቶች ወስደው
በትምህርተ ጥቅስ በማስቀመጥ ወይም ታሪኮችን ብሎም ትንቢቶችን በመጥቀስ
የብሉይ ኪዳንን ሐሳብ ለማጠንከሪያነት፣ አልፎ ተርፎም ትክክለኝነቱን
ለማሳየት ተጠቅመውበታል።
ብዙውን ጊዜ ተደጋግመው ከተጠቀሱ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መካከል
ኦሪት ዘዳግም (መዝሙር እና ኢሳያስን ጨምሮ) ይገኝበታል። ማቴዎስ፣
ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ ዮሐንስ፣ ሮሜ፣ ገላትያ፣ ቆሮንቶስ 1 እና 2፣
ዕብራውያን፣ ሁለቱ ወደ ጢሞቴዎስ መልእክቶች፣ ቲቶ፣ ራእይ--እነዚህ ሁሉ
መለስ ብለው የዘዳግም መጽሐፍን ይጠቅሳሉ።
በዚህ ሳምንት ከእነዚህ ማስረጃዎች ውስጥ ጥቂቶቹን በመመልከት፤
በውስጣቸው ልናገኝ የምንችለውን እውነት፣ ወቅታዊ እውነት ለማየት
እንሞክራለን።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 4፡1-11። የሱስ በምድረ በዳ ሰይጣን ላቀረበለት ፈተናዎች ምላሽ የሰጠው እንዴት ነበር? ከእርሱ መልስ የምናገኘው ጠቃሚ ትምህርት ምንድን ነው?
የሱስ ከሰይጣን ጋር አልተከራከረም ወይም ሙግት ውስጥ አልገባም።
ይልቁንም “ሕያውና የሚሠራ… በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ
ስለታም” (ዕብ. 4፡12) ከሆነው ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቀሰለት። እናም
ለእያንዳንዱ የቀረበለት ፈተና የጠቀሰው ቃል የተወሰደው ከኦሪት ዘዳግም
ነበር። በወቅቱ በምድረ በዳ የነበረው የሱስ፤ ለእስራኤላውያን በምድረ በዳ
የተሰጣቸውን ጥቅሶች መጥቀሱ ምንኛ አስደሳች ነው!
የሱስ ለመጀመሪያው ፈተና የጠቀሰው--ዘዳ. 8፡3 ነበር። እስራኤላውያን
በምድረ በዳ በነበሩባቸው በእነዚያ ሁሉ ዘመናት ጌታ መና ከሰማይ ማውረድን
ጨምሮ እንዴት የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ያሟላ እንደ ነበር ሙሴ ለጥንት
እስራኤላውያን በዝርዝር እየነገራቸው ነበር። ጌታ በእነዚያ ባለፉባቸው ሁሉም
ዓይነት የመጥራት ሂደቶች ውስጥ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ሊያስተምራቸው
ይፈልግ ነበር። ከእነዚያ ትምህርቶች መካከል፡ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ
በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም”--እግዚአብሔር
ለአካላችሁ ምግብ እንደጣቸው ሁሉ መንፈሳዊ ምግብም ይቸራችኋል።
አንድ
ሰው የመጀመሪያውን ብቻ ወስዶ ሁለተኛውን መተው አይችልም። የሱስ
የእንጀራውን ሀሳብ--ወደ ዘዳግም መጽሐፍ ለመሸጋገር፣ ሰይጣንን ለመገሰጽና
በየሱስ ላይ ለማስረጽ የሞከረውን ጥርጣሬ ለመገሰጽ ተጠቅሞበታል።
በሁለተኛው ፈተና የሱስ ወደ ዘዳ. 6፡16 የሚያመራ ሲሆን፤ ይህም--ሕዝቡ
በማሳህ ስላደረገው አመጽ ሙሴ እስራኤላውያንን ያስታወሰበት ክስተት ነው።
(በተጨማሪ፡ ዘፀ. 17፡1-7 የሚለውን ይመልከቱ)።
“ ‘በማሳህ እንዳደረጋችሁት አምላክችሁን እግዚአብሔርን አትፈታተኑት።’
” ጌታ ቀድሞውንም ቢሆን የሚያስፈልጋቸውን ለማሟላት አቅሙም ሆነ
ፈቃደኝነቱ እንዳለው ያሳያቸው ቢሆንም፤ ነገር ግን ችግር በገጠማቸው ቁጥር
“ ‘እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?’” (ዘፀ. 17፡7) እያሉ ይጮኹ
ነበር። እንግዲህ የሱስ ሰይጣንን ለመገሰጽ ከእግዚአብሔር ቃል የወሰደው
ከዚያ ታሪክ ላይ ነበር።
በሦስተኛው ፈተና ወቅት--ክርስቶስ እንዲሰግድለትና እንዲያመልከው
ሰይጣን ፈለገ። ማንነቱንና የፈለገውን ነገር እርቃኑን ያወጣ ምን ዓይነት ከንቱ
ልፍለፋ ነው! የሱስ ከእርሱ ጋር ከመሟገት ይልቅ ይገስጸውና እንደገና ፊቱን
ወደ እግዚአብሔር ቃል በመመለስ፤ ሕዝቡ አምላካዊውን መንገድ ስቶ ሌሎች
አማልክት እንዳያመልክ ጌታ በዘዳግም መጽሐፍ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ
ይናገራል፡ “ ‘እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱን ብቻ አገልግል’ ” (ዘዳ. 6፡13)።
ማለትም--እርሱን እና እርሱን ብቻ።
የየሱስን ባህሪ ይበልጥ በሙላት እያንጸባረቅን እንደ እርሱ
ፈተናን መቋቋም እንችል ዘንድ፣ ከአምላካዊው ቃል ጥናታችን
በሕይወታችን የበለጠ ኃይል ማግኘትን መማር የምንችለው
እንዴት ነው?
በዘዳ. 10 ሙሴ (እንደገና) የእስራኤልን ታሪክ ዘርዝሮ በመንገር፣ ሕዝቡ ታማኝ ይሆን ዘንድ ለመምከርና ለመገሰጽ እነዚህን ታሪኮች ሲጠቀም ይስተዋላል። ከዚህ ግሳጼ ጎን ለጎን ሌላም ነገር ይናገራል። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 10፡17-19። በዚህ ስፍራ ለሕዝቡ የቀረበው ወሳኝ መልእክት ምንድን ነው? ይህ መልእክት ለዛሬዋ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አግባብነት ያለው ለምንድን ነው?
“አድልዎ የማያደርግ” የተሰኙት ቃላት ከዕብራይስጥ የተወሰዱት “ፊት
አያበላልጥም” በሚል ቃል በቃል ትርጉም ሲሆን--አንዱን ከፍ ሌላውን
ደግሞ ዝቅ አድርጎ አያይም የሚል ፍቺ አላቸው። ይህ ጥቅም ላይ የዋለበት
ምክንያት--ዳኛ ወይም ንጉሥ በችሎት ፊት የቀረበውን ሰው (ከፍ ያለ ስብዕና
ያለው ወይም ተራ እና ጎስቋላ) ተመልክቶ ብይን ከሚሰጥበት ሕጋዊ ሁኔታ
ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይታመናል። ይህን አስመልክቶ በዘዳግም የምናገኘው
መልእክት፣ ጌታ ብርቱና ኃያል አምላክ ቢሆንም ነገር ግን ሰዎችን በዚህ መልኩ
አይዳኝም የሚል አንደምታ አለው። ሰዎች በየትኛውም ዓይነት ማሕበራዊ
ደረጃ ላይ ሊገኙ ቢችሉም እንኳ እርሱ ለእያንዳንዱ ፍትሐዊ ነው። ይህ
እውነት እጅግ የተናቀውን የማኅበረሰብ ክፍል እንዴት ወርዶ እንዳስተናገደ
በታየበት በየሱስ ሕይወት ተገልጧል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሐዋ. 10፡34፣ ሮሜ 2፡11፣ ገላ. 2፡6፣ ኤፌ.
6፡9፣ ቆላ. 3፡25፣ 1ጴጥ. 1፡17። እነዚህ ጥቅሶች በዘዳ. 10፡17
የቀረበውን ሀሳብ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችሉን እንዴት ነው?
በእነዚህ በእያንዳዳቸው ጥቅሶች ውስጥ ያሉ ሁኔታዎች የቱንም ያህል
ቢለያዩም እንኳ (ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ--ጌቶች የባሮቻቸውን አያያዝ
አስመልክቶ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ይናገራል። በሮሜ መልእክቱ
ደግሞ ድነትንና ኩነኔን አስመልክቶ ሲናገር በአይሁድ እና በአሕዛብ መካከል
ልዩነት አለመኖሩን ይጠቅሳል) ሁሉም በዘዳግም ወደ ቀረበው--እግዚአብሔር
“ፊት አያበላልጥም” ወደሚለው ጽንሰ ሀሳብ ያመራሉ። “የአማልክት አምላክ፣
የጌቶች ጌታ፣ ታላቅ አምላክ፣ ኃያልና የሚያስፈራ” የሆነው እርሱ ይህን
የማያደርግ ከሆነ፣ እኛም በእርግጠኝነት ማድረግ አይኖርብንም።
በተለይ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ በተጠቀመበት መንገድ የወንጌልን
ራእይ ማየት እንችላለን፡ እኛ ሁላችንም የቱንም ያህል በተለያየ ማኅበራዊ
ሁኔታ ልንገኝ ብንችልም፣ ነገር ግን እያንዳንዳችን ውደቀት የደረሰብንና
የእግዚአብሔር ማዳን የሚያስፈልገን ሰብዓዊ ፍጡራን ነን። መልካሙ
የምሥራች--በየትኛውም ማሕበራዊ ወይም ኤኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ ብንገኝም
በየሱስ ክርስቶስ የደኅንነት ስጦታ ተሰጥቶናል።
እርስዎ በገሀድም ባይሆን ምን ያህል “ፊት የማበላለጥ” ተግባር
ይፈጽማሉ? መስቀሉ እንዲህ ዓይነቱ ተግባር በእርግጥም ኃጢአት
መሆኑን የሚያሳየን ለምንድን ነው?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ገላ. 3፡1-14። ጳውሎስ ለእኛ ዘመን ገጣሚ በሆነው በዚህ መልእክት ምን እያለን ነው? ዘዳ. 27፡26 እና ዘዳ. 21፡22-23 ሀሳቡን ለማስተላለፍ የተጠቀመበት መንገድ ምን ይመስላል?
ሕጉን ማለትም አሥሩን ትእዛዛት ላለመጠበቅ፤ በክርስትና እምነት ይህ
መልእክት እንደ ሰበብ ሲጠቀስ መመልከት የተለመደ ነው። የሰንበትን ትእዛዝ
መጠበቅ ከሌሎቹ ዘጠኙ ጋር የሚጋጭና እንደ ሕጋውያን የሚያስቆጥር
ይመስል--ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ከሚናገረው ሕጋውያን የመሆን መግለጫ
ጋር በማያያዝ፣ አራተኛውን ትእዛዝ ላለመጠበቅ እንደ ምክንያት ጥቅም ላይ
መዋሉ እሙን ነው።
ሆኖም ጳውሎስ ሕጉን በመጻረር እየተናገረ አልነበረም። እንደውም
የሰንበትን ሕግ ስለ ማፍረስ የቀረበ አንድም አባባል በዚህ መልእክት ውስጥ
አናገኝም። የዚህ ቁልፍ ሀሳብ በገላ. 3፡10 መገኘት ይችላል። “ሕግን በመጠበቅ
የሚተማመኑ ሁሉ ከእርግማን በታች ናቸው” (ገላ. 3፡10) ይልና በዘዳ. 27፡
26 የቀረበውን ይጠቅሳል። ጉዳዩ ለሕግ መታዘዝ ሳይሆን “ሕግን በመጠበቅ
መተማመን” ከመሆኑ አኳያ--እንደ እኛ ላሉት ለወደቁ ፍጥረታት ቀላል
አለመሆኑ እውነት ነው።
የጳውሎስ ነጥብ፡ የዳንነው ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን ስለ አኛ መሥዋእት
በሆነልንና በእምነት በተቆጠረልን የክርስቶስ ሞት ነው--የሚል ነው። እዚህ
ላይ አጽንኦት የሚሰጠው ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስላደረገልን ነገር ነው።
ይህን ነጥብ ለማጉላት እንደገና ወደ ዘዳግም መጽሐፍ የሚመለስ ሲሆን፤
በዚህ ወቅት የሚጠቅሰው ዘዳ.21፡23 ነው። እንደ የሱስ ሁሉ የብሉይ ኪዳን
መጻሕፍት ሥልጣን እንዳላቸው በሚያሳይ መልኩ “ተጽፎአል” የሚለው
ጳውሎስ፣ በመቀጠል ለጥፋቱ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ለሌሎች መቀጣጫ
እንዲሆን በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ከሚገደል ሰው ጋር በተያያዘ ከቀረበ ጥቅስ
በመውሰድ ያሰፈረውን ሀሳብ እንመለከታለን።
ሆኖም ጳውሎስ ይህን ሀሳብ ጥቅም ላይ ያዋለው ክርስቶስ በእኛ ምትክ
የሞተውን ሞት ለማሳየት ነው፡ “ክርስቶስ ለእኛ እርግማን ሆነ” በዚህም
የሕጉን እርግማን ተጋፈጠ። ይህ ሁሉም ሰብዓዊ ፍጡር ሕጉን መጣሱን
ተከትሎ የሚጋፈጠው ሞት ነው። የወንጌል የምሥራች እንደሚነግረን የእኛ
ሊሆን ይገባ የነበረው ርግማን የእርሱ ሆነ፡ “ይኸውም በእምነት የመንፈስን
ተስፋ እንድንቀበል ነው” (ገላ. 3፡14)።
“በኃጢአት የወደቀውን ሰብዓዊ ዘር ከሕጉ እርግማን በመዋጀት ዳግመኛ
ከሰማይ ጋር ህብረት እንዲኖረው ሊያደርግ ይችል የነበረው አንዱ ክርስቶስ
ብቻ ነበር። ክርስቶስ እንደ በደለኛ ተቆጥሮ የኃጢአትን ውርደት መቀበል
ነበረበት። ለቅዱሱ አምላክ በእጅጉ አጸያፊ የሆነው ኃጢአት--አብን ከወልድ
የግድ መለየት ነበረበት።”--የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት፡ ገጽ 59።
ለፈጸሟቸው ጥፋቶች ሁሉ ትክክለኛውን ቅጣት ቢቀበሉ ምን
ሊደርስቦት እንደሚችል ያስቡ። ሆኖም የበደልዎን ቅጣት ክርስቶስ
በመሸከሙ እርስዎ ያን መቀበል አያስፈልጎትም። ታዲያ ለዚህ
መሥዋእነትነቱ ምላሽዎ ምን ሊሆን ይገባል?
እስራኤላውያን በዙሪያቸው የነበሩ አጎራባች ሕዝቦችን አረማዊ ልምምዶች እንዳይከተሉ ጌታ በተደጋጋሚ አስጠንቅቋቸዋል። እንደውም በተቃራኒው ምስክር መሆን ነበረባቸው (ዘዳ. 4፡6–8)። ሙሴ በዘዳ. 18፡9-14 እንደገና ስለ ሌሎች የአረማውያን “ርኩሰት” (ዘዳ. 18፡12 [1962 ትርጉም]) ይናገራል። በዚያው ዐውደ ሀሳብ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ነውር ዐልባ ሁን” (ዘዳ. 18፡13) ሲል ይነግራቸዋል። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 18፡15-19። እዚህ ላይ ሙሴ ምን እያላቸው ነው? ይህን ሀሳብ ከሚከተሉት ጥቅሶች ጋር ያስተያዩ፡ ሐዋ. 3፡22 እና ሐዋ. 7፡37። ጴጥሮስ እና እስጢፋኖስ ዘዳ. 18፡18 ጥቅም ላይ ያዋሉት እንዴት ነበር?
ሙሴ በሲና የተደረገውን ቃል ኪዳን በመጥቀስ ሲናገር፤ አምላካዊው ሕግ
በተገለጠበት ወቅት (ዘፀ. 20፡18-21) ሙሴ በእነርሱና በእግዚአብሔር
መካከል አማላጅ እንዲሆን የእስራኤል ልጆች ፈልገው እንደ ነበር ያወሳል።
እንግዲህ በዚህ ጊዜ ነበር ጌታ እንደ እርሱ ያለ ነቢይ እንደሚያስነሳላቸው
ለሕዝቡ ከአንዴም ሁለቴ (ዘዳ. 18፡15፣18) የነገራቸው። ይህ ነቢይ እንደ ሙሴ
ከሌሎች ነገሮች በተጓዳኝ በሕዝቡና በጌታ መካከል አማላጅ ይሆናል።
ከብዙ ምዕተ ዓመታት በኋላ ጴጥሮስ እንዲሁም እስጢፋኖስ ይህንኑ ጥቅስ
ለየሱስ በማመሳከሪያነት ሲጠቅሱት ይታያሉ። ለጴጥሮስ--የሱስ “በቅዱሳን
ነቢያቱ” (ሐዋ. 3፡21) የተነገረው ሁሉ ፍጻሜ ነው፤ ስለዚህ መሪዎች እርሱንም
ሆነ ከአንደበቱ የሚወጡትን ቃላት መታዘዝ ይኖርባቸዋል። ማለትም ጴጥሮስ
አይሁዶች የሚያውቁትን ይህን ጥቅስ ተጠቅሞ በቀጥታ ለየሱስ በማዋል
የሚጠቀምበት ሲሆን፤ መልእክቱ በእርሱ ላይ ስላደረጉት ነገር ንስሐ መግባት
እንደሚያስፈልጋቸው አጽንኦት ይሰጣል (ሐዋ. 3፡19)።
በቀጣይ፣ እስጢፋኖስ በሐዋ. 7፡37 ከጴጥሮስ ለየት ባለ ዐውድ ስለ የሱስ
ሲያውጅ፣ ወደ ኋላ ተጉዞ ወደ እርሱ ያመላክት የነበረውን ያን ዝነኛ የተስፋ
ቃል ይጠቅሳል። ሙሴ በታሪክ ከነበረው ሚና እና አይሁዶችን ከመምራቱ
አኳያ የሱስን አስቀድሞ ገልጾታል። ይኸውም ጴጥሮስ እንዳደረገው ሁሉ
የሱስ የትንቢቱ መጨረሻ መሆኑንና እርሱን ሊያደምጡ እንደሚገባ ለሕዝቡ
ለማሳየት ይጥር ነበር። እስጢፋኖስ ይናገረው ከነበረ በተቃራኒ “ ‘በሙሴና
በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲሰነዝር ሰምተናል’ ” (ሐዋ. 6፡11) ብለው
ቢከሱትም፣ እርሱ ግን የሱስ--እግዚአብሔር በሙሴ በኩል የተናገረው ትንቢት
ቀጥተኛ ፍጻሜ መሆኑን በመግለጽ መሲህነቱን ዐውጇል።
የሱስ በጠቅላላው የመጽሐፍ ቅዱስ አስኳል መሆኑን ጥቅሶቹ
እንዴት ያሳዩናል? አምላካዊው ቃል ላይ ያለን ማስተዋል ሙሉ
በሙሉ ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ መሆን ያለበት ለምንድን ነው?
የዕብራውያን መጽሐፍ ካለው ጥልቀትና ንዑስነት አኳያ፣ በየሱስ ለሚያምኑ
አይሁዶች፣ በብዙ መልኩ የተሰጠ አንድ ረጅም ልባዊ ምክር ነበር። ይህ ልባዊ
ምክር፡ ለጌታ ታማኝ ሁኑ!--ሲል የሚበረታታቸው ነበር።
በእርግጥ ይህ ታማኝነት መመንጨት የሚኖርበት ማንነቱ፣ ባህሪውና
መልካምነቱ እጅግ ኃያል በሆነ መንገድ በክርስቶስ መስቀል በተገለጸጠ
ለእግዚአብሔር አምላክ ከሚኖረን ፍቅር ነው። ይሁን እንጂ አንዳንዴ የሰው
ልጆች ውድቀት ሊያስከትል የሚችለውን አስከፊ መዘዝ መዘንጋት የለባቸውም።
ማለትም፣ የሱስ የኃጢአታችንን ዋጋ በመክፈል ለእኛ ያደረገልንን ነገር
የማንቀበል ከሆነ፤ ያንን ቅጣት በራሳችን መክፈል እንደሚኖርብን ማስታወስ
የሚኖርብን ሲሆን፣ ይህም “ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት” ነው (ማቴ. 22፡13)።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዕብ. 10፡28-31። ጳውሎስ ምን እያለ ነው?
ይህ በተመሳሳይ ለእኛም ገቢራዊ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
ጳውሎስ የአይሁድ አማኞች ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው እንዲጸኑ
ለማበረታታት፣ ቀደም ባለው ዘመን በዘዳግም መጽሐፍ የቀረበውን፣ ለአይሁድ
አማኞች የተሰጠ ልባዊ ምክር ሲጠቅስ መመልከት ያስደስታል። ጳውሎስ
አንድ ሞት ይገባዋል የተባለ ሰው ፍርዱ ተግባራዊ የሚደረግበት ቢያንስ ሁለት
ሰዎች ከመሰከሩበት ብቻ እንደሆነ የሚገልጸውን ዘዳ. 17፡6 ይጠቅሳል።
ነገር ግን ጳውሎስ ይህን የጠቀሰው--ታማኝ አለመሆን በአሮጌው ኪዳን
መሠረት ለሞት ሊዳርግ የሚችል ከሆነ፣ በአዲስ ኪዳን ያለውን ውጤት ደግሞ
ምን ያህል ጽኑ እንደሆነ ለማሳየት ነው፡ “ታዲያ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፣
የተቀደሰበትን የኪዳኑንም ደም እንደ ተራ ነገር የቆጠረ፣ የጸጋንም መንፈስ
ያክፋፋ እንደ ምን ያለ የባሰ ቅጣት ይገባው ይመስላችኋል?” (ዕብ. 10:29)።
በሌላ አነጋገር እናንተ ከእነርሱ የበለጠ ብርሃንና የላቀ እውነት ስላላችሁ
የአግዚአብሔር ልጅ ስለ ኃጢአታችሁ የከፈለውን መሥዋእትነት አበጥራችሁ
ታውቃላችሁ፤ ስለዚህ የምትሰናከሉ ከሆነ በእናንተ ላይ የሚደርሰው ኩነኔ
ከእነርሱ የሚበልጥ ይሆናል--የሚል ነው።
ከዚያም ጳውሎስ ይህን የሙግት ሀሳቡን ለመደገፍ ወደ ዘዳ. 32፡35 መለስ
ይላል። በክርስቶስ ስለ ተሰጣቸውና ስለ ተዘጋጀላቸው ታላቅ ስጦታ ያላቸውን
ዕውቀት ከግምት ውስጥ በማስገባት “ ‘በቀል የእኔ ነው’ ” ሲል የተናገረው ጌታ
ስለ ክህደታቸው እና ታማኝ አለመሆናቸው በሕዝቡ ላይ “ፍርድ” ይሰጣል።
ደግሞስ እነዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በሙላት የተገለጠላቸው የአዲስ ኪዳን
አይሁዶች ያላቸው ነገሮች ያልነበራቸው--እነዚያ የብሉይ ኪዳን አባቶቻቸው
ላይ ፍርድ ሰጥቶ አልነበር? በመሆኑም ጳውሎስ ለማስጠንቀቂያው አጽንኦት
ስጡ እያለ ነበር።
በፍርድ ወቅት ብቸኛው ተስፋችን ምንድን ነው (ሮሜ 8፡1)?
ብሉይ ኪዳን ራሱን እንደሚጠቅስ ሁሉ (ለምሳሌ አንዳንድ
ነቢያት ከአምስቱ የሙሴ መጻሕፍት እንደሚጠቅሱት) አዲስ ኪዳንም ብሉይ
ከዳንን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ይጠቅሳል። መዝሙር፣ ኢሳይያስ እና
ዘዳግም በብዛት ከሚጠቀሱ መጻሕፍት መካከል ይመደባሉ። በተደጋጋሚ
እንደሚስተዋለው የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በቀደሙት ዘመናት ከዕብራይስጥ
ወደ ግሪክኛ የተተረጎመውንና “ግሪክ ብሉይ ኪዳን” (LXX) ተብሎ
የሚጠራውን ቅጂ ይጠቅሳሉ። ቶራ ወይም ፔንታቴክ በመባል የሚታወቁት
የመጀመሪያዎቹ አምስቱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የተተረጎሙት ከክርስቶስ
ልደት በፊት ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ሲሆን፤ የተቀሩት የብሉይ
ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በፊት ሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን
አካባቢ ተተርጉመዋል።
በመንፈስ አነሳሽነት አዲስ ኪዳንን የጻፉ ሰዎች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን
እንዴት እንደተጠቀሙባቸው አስመልክቶ ማንም ቢሆን ብዙ ትምህርት
መቅሰም ይችላል። ከእነዚህ ከምንማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱና
የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በዚህ ዘመን ካሉት የመጽሐፍ ቅዱስ
ምሁራን በተለየ ስለ ብሉይ ኪዳን ትክክለኛነት ወይም ሥልጣን አንዳችም
ጥያቄ አለማንሣታቸው ነው። ለምሳሌ በጽሑፎቻቸው ስለ አዳምና ሔዋን
ፍጥረት፣ ውድቀት፣ የጥፋት ውሃ፣ የአብርሃም መጠራት--የብሉይ ኪዳን
ታሪኮች ያነሷቸው አንዳችም ጥርጣሬዎች አልነበሩም። እነዚህን ነገሮች
የሚጠይቅ “ምሑር” የሰው ልጅ ጥርጣሬ ብቻ እንደመሆኑ በሰባተኛው ቀን
የዳግም ምጽአቱ ተጠባባቂዎች ልብና አእምሮ ውስጥ ቦታ ሊኖረው አይገባም።
1.እንደ ሰባተኛ ቀን የዳግም ምጽአቱ ተጠባባቂ ሕዝብ የተሰጠንን
ብርሃን ከግምት ማስገባታችን፤ ለተሰጡን እውነቶች ታማኝ
እንድንሆን ስለ ወደቀበን ታላቅ ኃላፊነት ምን ሊያስተምረን
ይገባል?
2.ጥቅሶቹን በድጋሚ ያንብቡ፡ ዘዳ. 18፡9-14። የዛሬዎቹ
ዘመናዊ በጌታ ላይ የሚሠሩ “ርኩሰት”ተግባራት መገለጫዎች
ምንድን ናቸው? እነዚህን ነገሮች ከእኛ ስለ ማራቃችን እንዴት
እርግጠኞች መሆን እንችላለን?
3.ዩኒቨርስ አቀፍ የሆነውን የክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት
አንደምታ የሚያስተውሉ ሕዝቦች ሁሉ “ፊት ማበላለጥ” ፈጽሞ
የማያደርጉት ለምንድን ነው (የሰኞን ትምህርት ይመልከቱ)? ይህን
የማድረግ ዝንባሌ በውስጣችን መኖሩን መመልከት የምንችለው
እንዴት ነው? (መቼም የተወሰነ አዝማሚያም ቢሆን በውስጣችን
ሊኖር አይችልም ብለን በመካድ ራሳችንን አንሸነግልም--አይደል?)
መስቀሉ እና መስቀሉን ብቻ ከፊታችን ማስቀደማችን ከዚህ
የተሳሳተ አመለካከት እንዴት ሊፈውሰን ይችላል?