የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ 2ነገሥ. 22፣ ነኽ. 9:6፣ ኤር. 7:1–7፣ መዝ. 148:4፣ ኤር. 29:13፣ ሚክ. 6:1–8፣ ዳን. 9:1–19።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ ‘ነገር ግን እዚያም ሆናችሁ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ’ ” (ዘዳ. 4፡29)።
ስ
ለ መጽሐፍ ቅዱስ በተለይም ስለ ብሉይ ኪዳን ከሚያስደንቁ ነገሮች
አንዱ ራሱን በተደጋጋሚ መጥቀሱ ወይም ማንሣቱ ነው። በዚህም
የፊተኞቹ የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች፣ ቀደም ሲል የኋለኞቹ የጻፉትን
እያነሡ ለመልእክቶቻቸው ይጠቀሟቸዋል።
ለምሳሌ መዝ. 81 ወደ ኦሪት ዘፀአት ይመለስና የዐሥርቱን ትእዛዛት መግቢያ
“ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ” (መዝ. 81፡10)
በማለት ቃል በቃል ለማለት በሚያስችል መልኩ ይጠቅሰዋል።
በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት--ኦሪት ዘፍጥረት በተለይ የፍጥረት ታሪክ፡ “ምድርን
ተመለከትሁ፤ እነሆ ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች፤ ሰማያትንም አየሁ፣ ብርሃናቸው
ጠፍቶአል” (ኤር. 4፡23፣ ዘፍ.1፡2) በሚል ተጠቅሶ እንመለከታለን።
የፊተኞቹ የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች ለምሳሌ ነቢያት፣ በቀደመችው እስራኤል
ሕይወት ወሳኝ ሚና የተጫወተውን የኦሪት ዘዳግም መጽሐፍ በተደጋጋሚ
በማጣቀሻነት ይጠቀማሉ። በዚህ ሳምንት መጽሐፉ በኋለኞቹ ጸሐፊዎች
ጥቅም ላይ በዋለበት አካሄድ ዙሪያ ትኩረት እናደርጋለን። የትኞቹን የዘዳግም
ክፍሎች ተጠቅመዋል? ለእኛ ገጣሚነት ያላቸውን ምን ዓይነት ነጥቦች
አንስተዋል?
ኢዮስያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆኖ ሲቀባ ገና የስምንት ዓመት ታዳጊ ወጣት የነበረ ሲሆን፤ በጦር ሜዳ ውጊያ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ለ31 ዓመታት (ከክ.ል.በ. ከ640 – 609) በዙፋኑ ቆይቷል። በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ታሪክ የቀየረ አንድ ነገር ተከሰተ። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 2ነገሥ. 22። ከዚህ ክስተት ምን እንማራለን?
በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ሰፊ ምርምር ያደረጉ ምሑራን “የሕጉ መጽሐፍ”
(2ነገሥ. 22፡8) ለብዙ ዓመታት ከሕዝቡ ጠፍቶ የነበረ የሚመስለው ኦሪት
ዘዳግም ነው--ብለው ከድምዳሜ ከደረሱ ቆይተዋል።
“ኢዮስያስ የዚህ ጥንታዊ መጽሐፍ ማስጠንቀቂያና ምክር ለመጀመሪያ ጊዜ
ሲነበብለት ሲሰማ ልቡ በጣም ተነካ። እግዚአብሔር ለእስራኤል ‘ሕይወትንና
ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን’ (ዘዳ. 30፡19) በግልጽ ማስቀመጡን ከዚህ
በፊት፣ እንዲህ ሙሉ በሙሉ አልተገነዘበም ነበር… መጽሐፉ መታመናቸውን
ሙሉ ለሙሉ በእርሱ ላይ የሚያደርጉትን እግዚአብሔር ሊያድናቸው ፈቃደኛ
መሆኑን የሚገልጽ የተትረፈተፈ ማረጋገጫ ይዟል።
ከግብፅ ባርነት ቀንበር ነጻ
እንዳወጣቸው ሁሉ እነርሱን በተስፋይቱ ምድር ለመትከልና የምድር ሕዝቦች
ቁንጮ አድርጎ ለመሰየም ኃያል በሆነ መንገድ ይሠራል።”—Ellen G. White,
Prophets and Kings, p. 393.
በቀጣዮቹ ምዕራፎች ንጉሥ ኢዮስያስ “ትእዛዞቹን፣ ደንቦቹን፣ ሥርዓቶቹን
በፍጹም ልቡ፣ በፍጹምም ነፍሱ” (2ነገሥ. 23፡3፣ ዘዳ. 4፡29፣ 6፡5፣ 10፡12፣
11፡13) ለመጠበቅ መፈለጉን መመልከት እንችላለን። ይህን ተሐድሶና መንጻት
ተከትሎ ኢዮስያስ “በይሁዳና በኢየሩሳሌም የተገኙትን ሌሎች አስጸያፊ ነገሮች
ሁሉ አስወገደ፤ ይህን ያደረገውም ካህኑ ኬልቅያስ ከእግዚአብሔር መቅደስ
ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈው የሕጉ ቃል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ነው” (2ነገሥ.
23፡24)።
ዘዳግም የእስራኤል አጎራባች ሕዝቦች የሚፈጽሟቸውን ድርጊቶች እንዳይከተሉ
አጽንኦት በሚሰጡ ማስጠንቀቂያዎችና ምክሮች ተሞልቷል። የሰማርያ ጣኦት
አምላኪ ካህናትን ግድያ (2ነገሥ. 23፡20) ጨምሮ--የኢዮስያስ ድርጊትና
እርሱ የፈጸማቸው ነገሮች በሙሉ፣ በአደራ ከተሰጣቸው እውነት ምን ያህል
እንደራቁ ገልጠው የሚያሳዩ ነበሩ። ከእነርሱ እንደሚጠበቀው ማለትም እንደ
ቅዱስ ሕዝብ በጽናት መኖር ሲገባቸው ከጌታ ጋር ያለን ግንኙነት ሰላም ነው
ብለው ራሳቸውን እየሸነገሉ ከዓለም ጋር ተስማሙ።
እንዴት ያለ አደገኛ ማታለያ ነው!
በፍጹም ልባችን እና ነፍሳችን ጌታን በእውነት ማገልገል እንችል
ዘንድ ከገዛ ቤታችንም ሆነ ከቤተ ክርስቲያን ተቋማት በጥንቃቄ
ልናጸዳቸው የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው?
እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር ለነበረው ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በአጠቃላይ “የተመረጠ” ሕዝብነቱ (ዘዳ. 7:6፣ ዘዳ. 14:2. ዘዳ. 18:5) ሕጉ እና ኪዳኑ ማዕከላዊ መሆኑን ዘዳግም በጣም ግልጽ አድርጎ ያስቀምጣል። በአብዛኛው ስለዚህ ሕግ ጽንሰ ሀሳብና እስራኤል ስለ ተመረጠችበት ሁኔታ አጽንዖት የሚሰጥበትን የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘዳ. 10፡12-15። መጽሐፍ ቅዱስ--ሰማየ ሰማያት ሲል ምን ማለቱ ነው? ሙሴ በዚህ ሀረግ ሊያስተላልፍ የፈለገው ነጥብ ምንድን ነው?
“ሰማየ ሰማያት” የሚሉት ቃላት ቢያንስ ከቀረበው ዐውድ ብዙም ግልጽ ፍቺ ባይኖራቸውም፤ ነገር ግን ሙሴ የእግዚአብሔርን ግርማ፣ ኃያልነትና ታላቅነት መጠቆሙ እሙን ነው። በሌላ አነጋገር--ራሱ ሰማይ ብቻ ሳይሆን “ሰማየ ሰማያት” የእርሱ መሆናቸውን ያቀረበበት ይህ መንገድ፤ እግዚአብሔር በሁሉም የፍጥረት ሥራዎች ላይ ያለውን ሉዓላዊ ባህሪ አመልካች ዘይቤያዊ አገላለጽ ሊሆን ይችላል። በዘዳግም መጀመሪያ በሚገኝ ሐረግ ላይ የተመሠረቱትን የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ። በእያንዳንዱ ጉዳይ ለማመላከት የተፈለገው ነጥብ ምንድን ነው? የዘዳግም መጽሐፍ በመልእክቶቹ ላይ ያለውን ተጽእኖ እንዴት እንመለከተዋለን? 1ነገሥ. 8:27__________________________________________________
ነህ. 9:6 _____________________________________________________
መዝ. 148:4 __________________________________________________
በነህ. 9 በተለይ ግልጽ ሆኖ የተቀመጠው፤ እግዚአብሔር ፈጣሪና እርሱ ብቻ
አምልኮ የሚገባው አምላክ ሆኖ የቀረበበት ርዕሰ ነጥብ ነው። እርሱ “ከሰማያት
በላይ ያሉትን ሰማያትና… ሰራዊት ሁሉ” (ነህ. 9፡6) ፈጥሯል። እንዲያውም
ነህ. 9፡3 “ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ አነበቡ” ሲል መናገሩ፣ እንደ ኢዮስያስ
ዘመን ሁሉ፣ ሌዋውያኑም ከጥቂት ጥቅሶች በኋላ ለአምላክ ውዳሴና አምልኮ
በሚቀርብበት ወቅት “ሰማየ ሰማያት” የሚለውን ይህን በቀጥታ ከዘዳግም
የተወሰደ ሐረግ የተጠቀሙበትን ምክንያት ይገልጻል።
እግዚአብሔር የምድር ብቻ ሳይሆን የ “ሰማየ ሰማያት” ፈጣሪ
ጭምር ነው። ከዚያም ይኸው አምላክ ወደ መስቀል አመራ ብሎ
ማሰብ…! እግዚአብሔር ላደረገልን ነገር--አምልኮ ተገቢ ምላሽ
የሆነው ለምንድን ነው?
ከዓመታት በፊት እውነትን የማወቅ ጥልቅ ፍላጎትና እውነት ወዴትም
ቢመራው ለመከተል ቁርጠኛ የሆነ አንድ ኢ-አማኒ ወጣት ነበር። ውሎ አድሮ
እግዚአብሔር አብን እና እግዚአብሔር ወልድን ብቻ ሳይሆን ሰባተኛ ቀን
የዳግም ምጽአቱን መልእክት ጭምር ተቀበለ። አጥብቆ ልቡን የሚነካው ጥቅስ
በኤር. 29፡13 የሚገኝ ሲሆን እንዲህ ይላል፡ “እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፣ በፍጹም
ልባችሁ ከፈለጋችሁኝ ታገኙኛላችሁ።” ከዓመታት በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ
ሲያጠና ይህንኑ ጥቅስ መልሶ ያገኘው ሲሆን፤ አሁን ላይ ጥቅሱን ያገኘው
ቀደም ብሎ ከተጻፈው የኦሪት ዘዳግም መጽሐፍ ነበር። ይህም ኤርሚያስ
ከሙሴ አግኝቶት እንደ ነበር ያሳያል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 4፡23-29። ይህ ለእስራኤል የተሰጠ
የተስፋ ቃል ዐውደ ጽሑፍ ምንድን ነው? ዛሬ ከእኛ ጋር መዛመድ
የሚችለው እንዴት ነው?
ቀደም ሲል እንደተመለከትነው የዘዳግም መጽሐፍ እንደገና የተገኘው በንጉሥ ኢዮስያስ የግዛት ዘመን ሲሆን፣ ኤርምያስ አገልግሎቱን የጀመረው በዚሁ በኢዮስያስ አስተዳደር ወቅት ነበር። ከዚህ አኳያ የዘዳግም መጽሐፍ ሥራዎች ተጽእኖ በኢሳይያስ መልዕክቶች ላይ ቢታዩ ብዙም አያስደንቅም። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ኤር. 7፡1-7። ኤርምያስ ሕዝቡን ምን አድርጉ አለ? መልእክቱ በዘዳግም መጽሐፍ ከተጻፈው ጋር እንዴት ይዛመዳል?
የሕዝቡ በከነዓን ምድር መኖር በሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ እንደ ነበር ሙሴ
አጽንኦት ሰጥቶ ነግሯቸዋል። የማይታዘዙ ከሆነ እግዚአብሔር በመረጠላቸው
ስፍራ ላይ እንደማይኖሩ በዘዳግም መጽሐፍ ተደጋግሞ ቀርቧል። በተለይ
በኤር. 7፡4 የቀረበው ማስጠንቀቂያ፡ አዎ ይህ የእግዚአብሔር መቅደስ ነው፣
እነርሱም የተመረጡ ሕዝቦች ናቸው፤ ነገር ግን የማይታዘዙ ከሆነ አንዱም
ፋይዳ የለውም--የሚል አንደምታ አለው።
ይህ መታዘዛቸው ደግሞ--በመጻተኛው፣ አባቱ በሞተበት ልጅ እንዲሁም
በመበለቲቱ ላይ ተንጸባርቆ መታየት የነበረበት ሲሆን፤ ጽንሰ ሀሳቡ በቀጥታ
ወደ ቀደመው የዘዳግም መጽሐፍ በማምራት አንዳንድ የሕግ አግባብ
ያላቸውን ኪዳናዊ ግዴታዎች መከተልን ያካትታል፡
“ ‘ለመጻተኛው ወይም
አባት ለሌለው ልጅ ፍትሕ አትንፈገው፤ የመበለቲቱንም መደረቢያ መያዣ
አታድርግ’ ” (ዘዳ. 24:17፣ በተጨማሪ--ዘዳ. 24:21፣ 10:18፣ 19፣ 27:19)።
ጥቅሱን ያንብቡ--ኤር. 4፡4 እና ከዘዳ. 30፡6 ጋር ያስተያዩ።
ለሕዝቡ የቀረበው መልእት ምንድን ነው? መርኁ ለዛሬው
የእግዚአብሔርም ሕዝብ በእኩል ሥራ ላይ መዋል የሚችለው
እንዴት ነው?
አብዛኞቹ የነቢያት ጽሑፎች ሕዝቡ ታማኝ ሆኖ እንዲገኝ የሚማጸኑ ናቸው።
ይኸውም በአጠቃላይ ታማኝ መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በተለይ ወደ
ተስፋይቱ ምድር ከመግባታቸው በፊት በድጋሚ እንዲጸና የተደረገውን
ይኸውም በእነርሱ በኩል ላለው ቃል ኪዳን ታማኝ ሆኖ መገኘት ነው።
የዘዳግም መጽሐፍ ያሳየው ይህንኑ ነው፡ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር
የገባውን ቃል ኪዳን እንደገና ስለ ማጽናት። ጌታ አሁን ከአርባ ዓመት መዳከር
በኋላ በእርሱ በኩል የገባውን ቃል ኪዳን ሊፈጽም (ወይም መፈጸም ሊጀምር)
ተቃርቧል። በመሆኑም ሕዝቡም በእነርሱ በኩል የሚጠበቀውን ኪዳን
አጽንተው እንዲገኙ ሙሴ አጥብቆ አስጠንቅቋቸዋል።
እርግጥ ነው አብዛኛው
የነቢያቱ ጽሑፍ መሠረታዊ መልእክት ተመሳሳይ የነበረ ሲሆን፤ በሕዝቡ
በኩል የሚጠበቀውን የቃል ኪዳን ድርሻ ጠብቆ እንዲገኝ የቀረበ ተማዕጽኖ
ይዟል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሚክ. 6፡1-8። ጌታ ለሕዝቡ እየነገረ ያለው
ነገር ምንድን ነው? ከዘዳግም መጽሐፍ ጋር እንዴት ይዛመዳል?
(አሞጽ 5፡24፣ ሆሴዕ 6፡6)።
ሕዝቡ የገባውን ቃል ኪዳን በመጣሱ ምክንያት ጌታ በሕዝቡ ላይ “ክስ”
የመሠረተበትን ወይም የሚያቀርብበትን ይህን “ኪዳናዊ ክስ” በመባል
የሚታወቅ መግለጫ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በእነዚህ ቁጥሮች
ተመልክተዋል። ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ሚክያስ “እግዚአብሔር ከሕዝቡ
ጋር ክርክር አለው” (ሚክ 6፡2) ብሎ የሚናገር ሲሆን፤ “ክርክር” የሚለው
ቃል “ክስ” ወይም “አቤቱታ” የሚል በሕጋዊ መንገድ የሚፈጸም ሙግት ሊሆን
ይችላል። ይህም ጌታ የኪዳኑን ሕጋዊ ገጽታ የያዘ ዘይቤያዊ ክስ በእርሱ ላይ
እየመሠረተ እንደ ነበር ያሳያል።
በተጨማሪ ሚክያስ በቀጥታ ከዘዳግም መጽሐፍ የተዋሰውን ይህን አነጋገር
ልብ ይበሉ፡ “ ‘አሁንም እስራኤል ሆይ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ
የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትፈራው፣
በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ፣ እንድትወደው፣ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም
ነፍስህ እንድታገለግለው፣ መልካም እንዲሆንልህና ዛሬ እኔ የምሰጥህን
ትእዛዞችና ሥርዐቶች እንድትጠብቅ አይደለምን?’ ” (ዘዳ. 10፡12-13)። ሚክያስ
በቀጥታ መጥቀሱን ትቶ የዘዳግምን “የሕጉን ቃላት” ቅንና መሃሪ ስለመሆን
በሚያወሳው “በሕጉ መንፈስ” አቀያይሮ ያቀርባል።
በዚህ ስፍራ እየሆነ የሚመስለው፤ የቱንም ዓይነት ውጫዊ የኃይማኖተኝነትና
እና የቅድስና ገጽታ (ብዛት ያላቸው እንስሳት ማለትም፡ “አንድ ሺህ አውራ በጎች”
በመሥዋዕት ማቅረብ) እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር የገባውን ቃል ኪዳናዊ
ግንኙነት አያመላክትም። ለምሳሌ ሰዎች “ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤
ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤ የሰውን ቤት፣ የባልንጀራን ርስት አታልለው
ይወስዳሉ” (ሚክ. 2፡2) ታዲያ የውጪያዊ ቅድስና ፋይዳው ምንድን ነው?
ሌሎች ሕዝቦች “በእውነቱ ይህ ታላቅ ሕዝብ የቱን ያህል ጥበበኛና አስተዋይ
ነው” (ዘዳ. 4፡6) እንዲሉ በሚያስችል መልኩ እስራኤል ለዓለም ብርሃን
እንድትሆን ትጠበቅ ነበር። ስለዚህ ሰዎችን በፍትሐዊና በምኅረት ዐይን እያዩ
በጥበብና ማስተዋል መመላለስ ነበረባቸው።
በብሉይ ኪዳን ከቀረቡ እጅግ ዝነኛ ጸሎቶች አንዱ በዳን. 9 የሚገኘው የዳንኤል ጸሎት ነው። ዳንኤል ከትንቢተ ኤርምያስ መጽሐፍ ባነበበው መሠረት ሰባ ዓመታት የሚወስደው የእስራኤል ጥፋት (9፡2) ዘመን በቅርቡ ያበቃ ስለ ነበር ዳንኤል ጽኑ ጸሎት ማድረግ ጀመረ። የዳንኤል ጸሎት ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ኑዛዜ ያቀረበበት፣ አጥብቆ ልብን የሚነካና በዕንባ የታጀበ ምልጃና ልመና የነበረ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ለደረሰባቸው መከራ የአምላካዊውን ፍትሐዊነት ያረጋገጠና ዕውቅና የሰጠ ነበር። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዳን. 9፡1-19። ከዘዳግም መጽሐፍ ጋር ቀጥተኛ ተዛማጅነት ያላቸው ምን ዓይነት ጭብጦች በጥቅሶቹ ማግኘት ይችላሉ?
የዳንኤል ጸሎት ሕዝቡ የሚጠበቅበትን የኪዳን ውል አለመጠበቁ
የሚያፈራቸውን ፍሬዎች--ይኸውም በዘዳግም መጽሐፍ የተሰጠውን
ማስጠንቀቂያ ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽ ነው። ዳንኤል ከአንዴም ሁለቴ
መለስ ብሎ ስለ “ሙሴ ሕግ” ጠቅሷል። ይህም የዘዳግም መጽሐፍን ያካተተና
በተለይ በማመሳከሪያነት የጠቀሰ ነው።
ኦሪት ዘዳግም እንደሚናገረው ከምድሪቱ የወጡት (ዘዳ. 4፡27-31፣ ዘዳ. 28)
ባለመታዘዛቸው ነው። ይህ ደግሞ ሙሴ ሊከሰት እንደሚችል አስመልክቶ
በትክክል የተናገረው ነው (ዘዳ. 31፡29)።
እስራኤል “በእውነቱ ይህ ታላቅ
ሕዝብ የቱን ያህል ጥበበኛና አስተዋይ ነው” (ዘዳ. 4፡6) መባል ሲገባው
በእነዚያው ሕዝቦች ፊት “መሣለቂያ” (ዳን. 9፡16) መሆኑ ምን ያህል አሳዛኝ ነው!
በዳንኤል እምባ እና ምልጃዎች ውስጥ ብዙዎች አደጋ ሲከሰት የሚጠይቁት
ዓይነት “ለምን?” የሚል ጥያቄ አልጠየቀም። ለዘዳግም መጽሐፍ ምሥጋና
ይግባውና እነዚህ ሁሉ ነገሮች የተከሰቱት ለምን እንደሆነ በትክክል
ስለሚያውቅ ፈጽሞ አልጠየቀም። በሌላ አነጋገር በሕዝቡ ላይ የደረሰው ክፉ
ነገር ዕጣ ፈንታ ሳይሆን ነገር ግን በትክክል የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ውጤት፣
ማለትም ያለመታዘዛቸው ፍሬ እንደ ነበር የዘዳግም መጽሐፍ ለዳንኤል (እና
ሌሎች ግዞተኞች) በቂ የኋላ ታሪክ ጭብጥ ሰጥቷል።
ይሁን እንጂ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የዳንኤል ጸሎት--እነዚህ ሁኔታዎች
ቢከሰቱም እንኳን ተስፋ መኖሩን ይገልጽ ነበር። ጉዳዩ የቱንም ዓይነት
ገጽታ ቢይዝም እግዚአብሔር ግን አልተዋቸውም ነበር። የዘዳግም መጽሐፍ
የሚገኙበትን ሁኔታ እንዲያስተውሉ አድርጎ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ
ቀድሞ ሁኔታቸው የሚመለሱበትንም አቅጣጫ ይጠቁማል።
ስለ የሱስ ትንቢትና የመስቀል ላይ ሞቱ የሚናገሩትን ጥቅሶች
ያንብቡ፡ ዳን. 9፡24-27። ይህ ትንቢት በእስራኤል ግዞት እና
ወደ ምድራቸው የመመለስ የተስፋ ቃል ዐውድ ለዳንኤል (እና
ለተቀረነው ለእኛ) ለምን ተሰጠ?
“ይህ[ሚክ. 6 1–8] ከብሉይ ኪዳን ታላላቅ ምንባቦች
አንዱ ነው። ልክ እንደ አሞጽ 5፡24 እና ሆሴ. 6፡6 በስምንተኛው መቶ ዓመት
ላይ የነበሩ ነቢያት ያስተላለፉትን መልእክት በምሳሌ ይጠቅሳል። ያሕዌ
በሕዝቡ ላይ ያቀረበውን ክስ ይሰሙ ዘንድ ነቢዩ ለሕዝቡ የሚያቀርበውን ጥሪ
በሚያሣይ ውብ ተምሳሌታዊና ኪዳናዊ ሙግት ጥቅሱ ይጀምራል። ተራሮቹና
ኮረብቶቹ በዚያ ስፍራ ለረጅም ጊዜ የቆዩና እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር
ያለውን ግንኙነት የተመለከቱ እንደመሆናቸው በዳኝነት ተሰይመዋል።
ኪዳኑን አፍርሳችኋል ብሎ እስራኤልን በቀጥታ ከመወንጀል ይልቅ፤ እስራኤል
በእግዚአብሔር ላይ የሚያቀርበው ክስ እንዳለ ይጠይቃል፡ ‘ህዝቤ ሆይ፤
ምን አድርጌሃለሁ? ሸክም የሆንኩብህስ እንዴት ነው?’ አንዳንድ ድኾች
ከሚጋፈጡት ኢፍትሐዊነት አኳያ በጎ ማድረግ ‘ሸክም’ ሊሆንባቸው ይችላል።
አንዳንድ ባለ መሬቶች በአቋራጭ ለመክበር በሚያደርጉት ሩጫ የኪዳኑ ሕጎች
‘ሸክም’ ሊሆኑባቸው ይችላሉ።”—Ralph L. Smith, Word Biblical Commentary, Micah-Malachi, (Grand Rapids, MI: Word Books, 1984),
vol. 32, p. 50.
“ከዚያ በኋላ በተካሄደው የተሃድሶ እንቅስቃሴ ንጉሡ [ኢዮስያስ] የቀረውን
የጣዖት አምልኮ ከእነ ርዝራዡ ለማጥፋት ሙሉ ትኩረቱን አደረገ። የምድሪቱ
ነዋሪዎች በእንጨት እና በድንጋይ ምስል ለተቀረጹ ጣኦቶች በመስገድ
በዙሪያቸው የነበሩ ሕዝቦችን ወግና ልማድ እስከተከተሉ ድረስ፣ እያንዳንዱን
የክፉ ተጽእኖ ማስወገድ ከሰብዓዊው አቅም በላይ ነበር። ነገር ግን ኢዮስያስ
ምድሪቱን የማጽዳት ጥረቱን ገፋበት።”—Ellen G. White, Prophets and
Kings, p. 401.
1.እኛ ሰባተኛ ቀን የዳግም ምጽአቱ ተጠባባቂዎች ካለን ወቅታዊ
መልእክት አኳያ ራሳችንን የጥንቷ እስራኤል በነበረችበት
ቦታ እናስቀምጣለን፡ በዙሪያቸው የነበረው ዓለም ሊሰማው
የሚያስፈልገው እውነት ነበራቸው። ይህ ለእኛ ትልቅ መብትና
ጥቅም ነው። ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነቱ መብት የሚሰጠንን
ኃላፊነት ምን ያህል በብቃት እየተወጣን ይመስሎታል?
2.ራስዎን በዳንኤል ቦታ አስቀምጠው--ግዛታችሁ ጣኦት አምላኪ
በሆኑ አረማውያን መሸነፉንና መወረሩን፣ የአምልኮአችሁ ማዕከላዊ
ስፍራ የሆነው ቤተ መቅደስ መውደሙን ተመልክተዋል እንበል።
ዳንኤል (ወይም ሌላ አይሁድ) በዘዳግም መጽሐፍ ላይ የነበረው
ዕውቀት ምን ያህል እምነቱን ደግፎ ይዞለታል? ይኸውም ምን
እየተከሰተ እንደነበርና ለምን እንደተከሰተ እንዲገነዘብ መጽሐፉ
የረዳው እንዴት ነው? በተመሳሳይ፣ በአጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ
አረዳዳችን ፈታኝ ጊዜያቶችንና ክስተቶችን እንዴት መጋፈጥ
እንደሚኖርብን የሚረዳን በምን መልኩ ነው--ምክንያቱም
የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ከሌለን ሁኔታዎች በእጅጉ ተስፋ
አስቆራጭ ሊሆኑብን ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የእምነታችን
አስኳል ከመሆኑ አኳያ መልሱ ምን ሊያስተምረን ይችላል?
3.በዳን. 9፡24-27 የቀረበውን የ70 ሳምንት ትንቢት ይመልከቱ።
ቃል ኪዳኑ በዚህ ትንቢት ውስጥ ምን ሚና አለው? የቃል ኪዳን
ጽንሰ ሀሳብ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?