የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ሕዝ. 16:8፣ ዘዳ. 28:1፣ 15፣ ኤር. 11:8፣ ዘፍ. 6:5፣ ዮሐ. 10:27-28፣ ገላ. 3:26–29፣ ሮሜ 4:16, 17።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ለራሱ የለያችሁ ሕዝብ ናችሁ፡፡” (1ጴጥ. 2፡9)፡፡
በ
አንዲት ትንሽዬ ከተማ የጌጣ ጌጥ መሸጫ መደብር መስኮት ላይ የተለጠፈ
የግድግዳ ሰዓት ለሦስት እሩብ ጉዳይ ሲል መሥራት አቆመ። አብዛኛው
የከተማ ነዋሪ ጊዜውን የሚለካው ይህን ብቸኛ ሰዓት በመጠቀም ነበር።
በዚህ የተለየ ማለዳ ነጋዴዎች እና ሴቶች ወደ መስኮቱ መልከት ሲያደርጉ ገና ለሦስት
እሩብ ጉዳይ እንደሚል አስተዋሉ። ወደ ትምህርት ቤት ይሄዱ የነበሩ ታዳጊዎች
አሁንም ወዲህ ወዲያ የሚሉበት ጊዜ በማግኘታቸው ተገረሙ። በዚያ የጌጣጌጥ
መሸጫ መስኮት ላይ በተሠቀለና መሥራት ባቆመ አነስተኛ ሰዓት የተነሣ ብዙ ሰዎች
ዘገዩ።”—C. L. Paddock, God’s Minutes (Nashville, TN: Southern Publishing Association, 1965), p. 244, adapted
የጥንቷን እስራኤል ውድቀት ውክልና በእጅጉ ትክክለኛ ነበር። ጌታ እስራኤልን
“በአሕዛብ መካከል” (ሕዝ. 5፡5) ምቹ (ስትራቴጂክ) በሆኑ አህጉሮች (አፍሪካ፣
አውሮፓ እና እስያ) መካከል አስቀመጣት። እነዚህ ሕዝቦች ለዓለም መንፈሳዊ
“ሰዓት” መሆን ነበረባቸው።
እስራኤል ግን በጌጣጌጥ መደብሩ መስኮት ላይ እንደተሰቀለው ሰዓት አገልግሎት
መስጠት አቆመች።
ሆኖም ውድቀቱ አጠቃላይ ባለመሆኑ፤ እንደዛሬው ሁሉ
እግዚአብሔር ያኔም ታማኝ ትሩፋን ነበሩት። የያዝነው ሣምንት ጥናታችን የራሳችንን
ጨምሮ በእያንዳንዱ ዘመን የእግዚአብሔር እውነተኛ እስራኤል ማንነትና ሚና ላይ
ያተኩራል።
ሣምንቱን በጨረፍታ፡ ጌታ ለእስራኤል የገባው ቃል ኪዳን ምን ነበር?
አብረዋቸው የነበሩ ሁኔታዎች ምን ነበሩ? ሕዝቡ ምን ያህል ለቃል ኪዳኖቹ ተገዝቶ
ነበር? ባለመታዘዛቸው ምን ተከሰተ?
“አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ስለ ሆንህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር
የራሱ ሕዝብ፣ ርስትም እንድትሆንለት በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ
መረጠህ።” (ዘዳ. 7፡6)
ነገሩ ያን ያህል ግርታ የሚፈጥር አይደለም። ጌታ ዕብራውያንን በምድር ላይ
ልዩ ወኪሉ ወይም ርስቱ አድርጎ መርጧቸው ነበር። ምርጫው ሙሉ በሙሉ
በእግዚአብሔር የተደረገና የእርሱ የጸጋው መገለጫ መሆኑ፤ እዚህ ላይ ሊታወስ
የሚገባ ሌላው ወሳኝ ነጥብ ነው። ይህ ጸጋ ለዚህ ሕዝብ እንዲገባ የሚያደርግ አንዳች
ነገር በእነርሱ ውስጥ አልነበረም። ሊኖርም አይችልም--ምክንያቱም ጸጋ የተሰጠው
ለማይገባቸው ሁሉ ነው።
ጥቅሱን ያንብቡ፡ ሕዝ. 16፡8። ጌታ እስራኤልን የመረጠበትን መንገድ
ጥቅሱ እንዴት ሊያብራራ ይችላል?
“እስራኤል በያህዌ የተመረጠችው ለምን ነበር? ያ በእርግጥ የማይመረመር ነበር።
አገሪቱ ታላቅ ባህል ወይም ሌሎችን የሚመስጥ ኃይል ያልነበራት የአነስተኛ ሕዝቦች
ስብስብ ነበረች። ለእንዲህ ያለው መመረጥ እምነት እንዲጣልባት የሚያደርግ ምንም
ዓይነት የተለየ ግላዊ ብቃት አልነበራትም። ምርጫው የእግዚአብሔር አምላክ ብቻ
ተግባር ነበር… የዚያ ምርጫ ዋነኛው መንስኤ በመለኮታዊ ፍቅር ምስጢር ውስጥ
ነበር። እውነታውን ስንመለከት እግዚአብሔር እስራኤልን ወዷል፣ መምርጧል
እንዲሁም ለአባቶች የገባውን ቃል አክብሯል።… ያህዌ ለእርሷ ባለው ፍቅር የተነሣ
ተመርጣለች። የያህዌ ኃይል በተገለጸበት ሁኔታ ከግብፅ የባርነት ቀንበር አርነት
ወጥታለች። እነዚህን ታላላቅ እውነቶች አንዴ እንኳ ማስተዋል ከቻለች በእርግጥ
ቅዱስ እና ልዩ ሐብት ያካበተች ሕዝብ እንደ ነበረች ትገነዘባለች።””—J. A. Thompson, Deuteronomy (London: Inter-Varsity Press, 1974), pp. 130, 131.
በመለኮት ዕቅድ መሠረት እስራኤላውያን የንጉሥ እና የካህን ዘር መሆን
ነበረባቸው። ክፉ በሆነው ዓለም--ነገሥታት፣ ሥነ ምግባራዊ እና መንፈሳዊ በመሆን
በኃጢአት ግዛት ላይ ድል መቀዳጀት ነበረባቸው (ራእ. 20፡6)። እንደ ካህንነታቸው
በጸሎት፣ በምስጋና እና በመሥዋዕት ወደ ጌታ መቅረብ ነበረባቸው። በአሕዛብ
እና በእግዚአብሔር መካከል አማላጅ እንደ መሆናቸው--መምህራን፣ ሰባኪዎች
እና ነቢያት ሆነው ማገልገል ነበረባቸው። በቅድስና የተሞላ አኗኗር ምሳሌ እና
የሰማያዊው እውነተኛ ኃይማኖት ደጋፊ መሆን ከእነርሱ ይጠበቅ ነበር።
በዛሬው ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እስራኤላውያን “በምድር
ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ …” በላይ መሆን እንደነበረባቸው ጌታ
የተናገረውን ሀረግ ይመልከቱ። አምላካዊው ቃል ስለ ትህትና መልካም
ምግባርነት እና ስለ መታበይ አደገኛነት ያስተማረውን ከግምት ውስጥ
በማስገባት የጥቅሱ ፍቺ ምንድን ነው ብለው ያስባሉ? እነዚህ ሕዝቦች
ከሰው ሁሉ በላይ የሚሆኑት በምን ዓይነት መንገድ ነበር? እንደ ቤተ
ክርስቲያን እኛም ይህን ጽንሰ ሀሳብ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብን
ይሆን? እንዴት?
የእግዚአብሔር ሕዝቦች የሆኑት እስራኤላውያን የተስፋይቱን ምድር እንደሚወርሱ
መጀመሪያ ለአብርሃም የተስፋ ቃል የተሰጠ ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ይኸው ቃል
ለይስሐቅ እና ለያዕቆብ ተደግሟል። ዮሴፍ በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ የተናገራቸው
ቃላት ይህንኑ የተስፋ ቃል የደገመ ነበር (ዘፍ. 50፡24)። የአብርሃም ዘር ምድሪቱን
የሚወርሰው ከ “አራት መቶ ዓመታት” በኋላ መሆኑን እግዚአብሔር አስታውቆት
ነበር (ዘፍ. 15፡13፣16)። የተስፋው ቃል ፍጸሜ ማግኘት የጀመረው በሙሴ እና
በኢያሱ ዘመን ነበር። ሙሴ እንዲህ ሲል መለኮታዊውን ትእዛዝ በድጋሚ ተናግሯል፡
“ ‘ “እነሆ፤ ይህችን ምድር ሰጥቻችኋለሁ፤ ገብታችሁ ውረሱ” ’ ” (ዘዳ. 1፡8)።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 28፡1፣ 15። እነዚህ ቃላት ምን ይዘዋል?
በአጭሩ፤ የተስፋው ምድር የቃል ኪዳኑ አካል እንደመሆኑ ይሰጣቸዋል።
ኪዳን በውስጡ ግዴታዎችን ይይዛል። ከዚህ አኳያ የእስራኤል
ግዴታዎች ምን ነበሩ?
የዘዳግም 28 የመጀመሪያ ክፍል እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከተከተሉ
የሚያገኟቸውን በረከቶች ይዘረዝራል። ሌላኛው የምዕራፉ ክፍል ደግሞ ይህን
ከማድረግ ከተሰናከሉ የሚደርስባውን እርግማን ያስቀምጣል። እነዚህ እርግማኖች
“በአጠቃላይ፤ ምንም እንኳ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም፣ የኃጢአት መጠንና ስፋት
እንዲያድግና የራሱ መጥፎ ውጤት እንዲሠራ አድርገዋል። ‘ሥጋዊ ምኞትን
ለማርካት የሚዘራ፤ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል’ (ገላ. 6፡8)።
የፈለገው ደረጃ ላይ
እስኪደርስ መፍሰሱን እንደማያቆም--በራሱ እንዲጓዝ እንደ ተተወ ወራጅ ውሃ፣
መሥራት እስኪሳነው ከመገስገገስ እንደማይገታ የተተወ ሰዓት፤ በራሱ እንዲያድግ
እንደ ተተወውና ተገቢውን የፍሬ መጠን ማፍራት እንደማይችለው ዛፍ፤ በተመሳሳይ
ኃጢአትም አጥብቆ የሚሻው ደረጃ አለ ‘የዚያ ነገር ውጤት ሞት ነው’ (ሮሜ 6፡
21)። ”–The Pulpit Commentary: Deuteronomy, H. D. M. Spence and
Joseph S. Exell, eds. (Peabody, MA: Hendrickson Publishers, 1890), vol.
3, p. 439.
ምንም እንኳ ምድሪቱን በመውረስ ዙሪያ እነዚያ ሁሉ የተስፋ ቃሎች ቢሰጡም፤
ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተሰጡ ግን አልነበሩም። የቃል ኪዳኑ አካል ሆነው ነበር
የመጡት። እስራኤል በእርሷ በኩል የሚጠበቀውን ድርድር ማሟላት ነበረባት፤
ያለበለዚያ ግን የተስፋ ቃሎቹ ሊሻሩ ይችላሉ። የማይታዘዙ ከሆነ ምድሪቱ ከእነርሱ
እንደምትወሰድ ጌታ ከአንድ ጊዜ በላይ በግልጽ አስቀጧል። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘሌዋ.
26፡27-33። ጌታ በዚህ ጉዳይ እንዴት ከዚህ የበለጠ ግልጽ ሊሆን እንደሚችል
መገመት ያዳግታል።
እኛ እንደ ክርስቲያን ሰማያዊውን እና አዲሲቱን ምድር እንደምንወርስ የተሰጠውን
የተስፋ ቃል በጉጉት እንጠባበቃለን። ምድራዊዋ የተስፋይቱ ምድር ለዕብራውያኑ
ቃል እንደ ተገባች ሁሉ ለእኛም ቃል ተገብቶልናል። ልዩነቱ፣ እኛ አንዴ እዚያ
ከገባን በኋላ ዳግም ልናጣው የምንችልበት ሁኔታ ፈጽሞ አለመኖሩ ነው (ዳን.
7፡18)። በተመሳሳይ እኛም እዚያ ለመግባት የሚፈለጉብን ሁናቴዎች
መኖራቸው እሙን ነው። የእነዚህን ሁናቴዎች ምንነት በተለይ ከጽድቅ
በእምነት ዐውደ ሀሳብ አኳያ እንዴት እናስተውላቸዋለን?
“እነርሱ ግን የክፉ ልባቸውን እልከኝነት ተከተሉ እንጂ አልታዘዙኝም፤ ጆሮአቸውንም
ወደ እኔ አላዘነበሉም፤ ስለዚህ እንዲከተሉት አዝዤአቸው ያላደረጉትን የዚህን ኪዳን
ርግማን ሁሉ አመጣሁባቸው።” (ኤር. 11፡8)።
ከላይ የቀረበውን ጥቅስ ልብ ብለው ይመልከቱ። ጌታ “የዚህን ኪዳን ርግማን ሁሉ”
እንደሚያመጣባቸው ይናገራል። እንግዲያውስ እየተናገረ ያለው አጉል ስለሆነ ነገር
ነው! ምንም እንኳ ቃል ኪዳኑ መልካም ብቻ እንደሆነ አድርጎ የማሰብ ዝንባሌ
ቢኖረንም የጀርባ ገጽታም አለው። ይህ መርኅ ከኖኅ ጋር በነበረው ሁናቴ ታይቷል።
እግዚአብሔር ኖኅን ከጥፋት የማዳን ድንቅ ነገር ያደረገለት ሲሆን፤ ኖኅ ደግሞ
የአምላካዊውን ጸጋ በረከቶች ለመቀበል መታዘዝ ነበረበት። ያን ባያደርግ ኖሮ የቃል
ኪዳኑ ሌላኛው ገጽታ ተከትሎ መምጣቱ አይቀርም ነበር።
ከላይ የቀረቡትን ጥቅሶች ከጥፋት ውሃ አስቀድሞ የነበረውን ሁናቴ
ከሚጠቁመን ዘፍ. 6፡5 ጋር ያስተያዩ። ምን ያመሳስላቸዋል? የልባችንን
ሀሳብ መቆጣጠር ለእኛ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስመልክቶ
ጥቅሶቹ ምን ያስተምሩናል?
እንደ አለመታደል ሆኖ አብዛኛው የእስራኤል ታሪክ ክፍል ተደጋጋሚ የክህደት
ሁናቴዎች እና መለኮታዊ ፍርዶች--ንስሐ እና የመታዘዝ ወቅቶች የተፈራረቁበት
ነበር። እስራኤላውያን የተስፋይቱን ምድር በስፋት መቆጣጠር የቻሉት ለአጭር ጊዜ
ብቻ ሲሆን፤ ይኸውም በዳዊት እና በሰለሞን ዘመን ነበር።
የእስራኤልን ክህደት አስመልክቶ በኤርምያስ የተጻፉትን የሚከተሉትን ጥቅሶች
ይመልከቱ፡ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፣ እርሷም ሄዳ ሌላ ሰው ብታገባ፣ ወደ እርሷ
ይመለሳልን? ምድሪቱስ ፈጽማ አትረክስምን? አንቺ ግን ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር
አመንዝረሻል፤ ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽን? ይላል እግዚአብሔር።
…የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሚስት፣ ስታታልሉኝ ኖራችኋል፤
ይላል እግዚአብሔር።” (ኤር. 3፡1፣ 20)።
ይህ ቀደም ሲል የተዳሰሰን ነገር ይጠቅሳል፡ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መግባት
የሚፈልገው ቃል ኪዳን በንግድ ሰዎች መካከል የሚደረግ ዓይነት ውል አይደለም።
ቃል ኪዳናዊው ግንኙነት እንደ ጽኑ እና የተቀደሰ ጋብቻ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ
መሆኑን ተከትሎ እነሆ ጌታ ይህን ምሳሌ ተጠቀመ።
ዋናው ነጥብ--የእስራኤል ክህደት ሥረ መሰረቱ አለመታዘዝ ሳይሆን፤ ከጌታ
ጋር የተቋረጠ ግላዊ ግንኙነት ነበር። ይህ የግንኙነት መቋረጥ በመጨረሻ ቅጣት
አስከተለባቸው።
ግላዊ የግንኙነት ሁኔታ ለክርስትና ህይወት እጅግ ወሳኝ የሆነው ለምንድን
ነው? ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ትክክል ካልሆነ ወደ ኃጢአት
እና አለመታዘዝ ያዘነበልን የምንሆነው ለምንድን ነው? “ከእግዚአብሔር
ጋር ጥልቅና በፍቅር የተሞላ ግንኙነት ማጎልበት የምችለው እንዴት
ነው” ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቆት ምን ይመልሱለታል?
በእስራኤላውያን ላይ ክህደት፣ መለኮታዊ ፍርድ እና ንስሐ ቢፈራረቁም
እንኳ በሚከተሉት ጥቅሶች ምን ዓይነት ተስፋዎች ቀርበዋል?
ኢሳ. 4:3___________________________________________________________
ሚክ. 4:6, 7_______________________________________________________
ሰፎን. 3፡12-13_____________________________________________________
ምንም እንኳ እግዚአብሔር ለጥንት እስራኤላውያን የነበረው ዕቅድ ባለመታዘዝ
ቢበላሽም፤ ሁኔታው ፍጹም ተስፋ አስቆራጭ ግን አልነበረም። በአረሞች መካከል
አሁንም ጥቂት አበቦች ይፈኩ ነበር። ብዙዎቹ የብሉይ ኪዳን ነቢያት እንደ ተወዳጅ
አበባ እግዚአብሔር በእቅፉ ስለሚሰበስባቸው ስለነዚህ ትሩፋን ተናግረዋል።
የታመኑ ትሩፋንን የመፍጠርና የማዳን አምላካዊ ዓላማው፤ ለመላው እስራኤላውያን
ከነበረው ጋር አንድ ዓይነት የነበረ ሲሆን፤ ይኸውም በመለኮት እንደ ሾማቸው
መሣሪያዎቹ “ ‘በሕዝቦች መካከል’ ” (ኢሳ. 66፡19) ክብሩን እንዲናገሩ ነበር። በዚህ
መሠረት ሌሎች ሕዝቦች “ለንጉሡ ለእግዚአብሔር ጸባኦት ለመስገድ” (ዘካ. 14፡16)
ታማኞቹን ወገኖች ይቀላቀላሉ። በመሆኑም ሁናቴዎች የቱንም ያህል አጉል ገጽታ
ሊኖራቸው ቢችልና በእግዚአብሔር የተመረጡ ሕዝቦች መሃል ክህደት ቢኖርም፤
የራሳቸውን ጥሪ እና ምርጫ በትክክል ያረጋገጡ አንዳንድ ታማኝ ወገኖች አሉት
(2ጴጥ. 1፡10)።
በአጭሩ፤ በአጠቃላይ በአገሪቱ የደረሱ ውድቀቶች የቱንም ያህል
ቢሆኑም፤ በተቻላቸው መጠን ቃል ኪዳኑን እስከ መጨረሻ ለመጠበቅ የሞከሩ ነበሩ
(1ነገሥ. 19፡14-18)። ምንም እንኳ እነዚህ ወገኖች በአጠቃላይ ከሕዝባቸው ጋር
ሥቃይ ቢደርስባቸውም (ከምድራቸው መሰደድና በግዞት መውደቅ) ውሎ አድሮ
የመጨረሻው የተስፋ ቃል፤ ይኸውም ዘላለማዊ ህይወት የእነርሱ ይሆናል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዮሐ. 10፡27-28። የሱስ ምን እያለ ነው? እርሱ
የተናገራቸውን ቃላት እና ቃላቶቹ የያዙትን ተስፋ በጥንቷ እስራኤል
በነበረው የክህደት ሁናቴ ላይ ይተግብሩ። እነዚህ ቃላት የታመኑ ትሩፋን
መኖራቸውን ለማስረዳት እንዴት ይረዳሉ?
ከጥቂት ዓመታት በፊት አንዲት ወጣት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኗ ባየችው
ኃጢአት፣ ክህደት እና ግብዝነት ተስፋ በመቁረጧ የክርስትና እምነቷን
ሙሉ በሙሉ ተወች። ሁሉንም ነገር ለመተው እንደ ሰበብ በመጠቀም
“እነዚያ ሰዎች በእውነት ክርስቲያኖች አልነበሩም” ስትል ተናገረች።
በዛሬው ጥናት መርኅዎች መሠረት የወጣቷ ሰበብ ለምን በጣም አንካሳ
ሆነ?
የጥንቷ እስራኤል ስህተቶች እና ውድቀቶቹ የቱንም ያህል የከፉ ቢሆኑም ጌታ እርሱን
የሚያገለግሉ ታማኞችን የመፍጠር እቅዱን አልጨረሰም ነበር። እንደ እውነቱ ከሆነ
ብሉይ ኪዳን--ጌታ መንፈሳዊቷን እስራኤል የሚፈጥርበትን፣ ይኸውም ወንጌልን
ለዓለም የመስበክ ሥራ ይዘው ወደፊት የሚገሰግሱ ታማኝ አይሁዶች እና አሕዛብ
አማኝ ወገኖችን አሻግሮ ወደፊት ተመልክቷል። ወደ ጥንታዊት ቤተክርስቲያን
እንኳን በደህና መጡ።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ገላ. 3፡26-29።
1. ጳውሎስ በቁ. 29 ላይ ስለ ምን ዓይነት ተስፋ እየተናገረ ነው?
2. አንድን ሰው የእነዚህ ተስፋዎች ወራሽ የሚያደርገው ቁልፍ ነገር ምንድነው?
(ገላ. 3፡ 26)
3. ጳውሎስ የፆታ፣ የብሔር እና የማኅበራዊ ልዩነቶችን የሚያፈራርሰው
ለምንድን ነው?
4. “በክርስቶስ አንድ” መሆን ምን ማለት ነው?
5. ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 4:16- 17። ጥቅሶቹ ጳውሎስ በገላ. 3፡26-29
የሚናገረውን ማስተዋል እንድንችል እንዴት ይረዱናል?
ክርስቶስ የአብርሃም ልጅ እንደመሆኑ በልዩ ሁኔታ የቃል ኪዳኑ ተስፋዎች ወራሽ
ሆነ። በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር ዝምድና በመፍጠር በእርሱ አማካይነት ለአብርሃም
የተሰጡት ተስፋዎች ላይ የመሳተፍ መብት እናገኛለን። ስለዚህ እግዚአብሔር
ለአብርሃም የሰጣቸው ተስፋዎች በሙሉ በክርስቶስ የተገኙ እንደመሆናቸው፤
ተስፋዎቹ የእኛ የሚሆኑት ከብሔራችን፣ ከዘራችን፣ ወይም ከፆታችን ውጪ
እግዚአብሔር በእምነት በሰጠን ተስፋ ነው።
“ለአብርሃም እና ለዘሮቹ የተሰጠው ስጦታ የከነዓንን ምድር ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ
ምድርን የሚሸፍን ነበር። ሐዋርያው እንዲህ ይላል ‘እርሱ የዓለም ወራሽ እንዲሆን
አብርሃም እና ዘሩ ተስፋን የተቀበሉት በሕግ በኩል አልነበረም። ነገር ግን በእምነት
ከሆነው ጽድቅ ነው።’ (ሮሜ 4፡13)። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚያስተምረው
ለአብርሃም የተገቡት የተስፋ ቃሎች የሚፈጸሙት በክርስቶስ በኩል እንደሆነ ነው።
‘የክርስቶስ ከሆናችሁ እናንተ የአብርሃም ዘር ናችሁ፤ እንደ
ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።
’ ‘እንዲሁም በሰማይ ለማይጠፋ ለማይበላሽና
ለማይለወጥ ርስት እንደገና ወለደን’ (ገላ. 3፡29፣ 1ኛ ጴጥ. 1፡4)። ምድርም ከኃጢአት
እርኩሰት ነጻ ሆነች። (የዘመናት ምኞት ገጽ 187-188)። ይህ የተስፋ ቃል ፍጻሜ
የሚያገኘው ቅዱሳን በአዲሲቱ ምድር ከክርስቶስ ጋር ከዘላለም እስከ ዘላለም ሲኖሩ
ነው። (ዳን. 7፡27)።
Read Ellen G. White, “The Vineyard of the Lord,” pp.
15–22; “Hope for the Heathen,” pp. 367–378; and “The House of Israel,”
pp. 703–721, in Prophets and Kings.
“በብሔር፣ በዘር ወይም በማሕበራዊ ደረጃ የሚደረግ ልዩነት በእግዚአብሔር ዘንድ
እውቅና አልተቸረውም። እርሱ የሰው ዘር ሁሉ ፈጣሪ ነው። ሰው ሁሉ በአምላካዊው
የፍጥረት ሥራ የመጣው ከአንድ ቤተሰብ ሲሆን፤ በመቤዠት ሁሉም አንድ ናቸው።
እያንዳንዱ ነፍስ ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ መገናኘት ይችል ዘንድ ክርስቶስ
እያንዳንዱን የመለያየት ግድግዳ ሊያፈራርስና እያንዳንዱን የቤተ መቅደስ ክፍል
ወለል አድርጎ ሊከፍት መጣ።
ፍቅሩ በጣም ሰፊ፣ ጥልቅ፣ ሙሉ እና በሁሉም ቦታ
ዘልቆ የሚገባ በመሆኑ፤ በሰይጣን ማሳቻዎች የተታለሉትን ከተጽእኖው አውጥቶ
በአምላካዊው የተስፋ ቃል ቀስተ ደመና በተከበበው የእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ
ያኖራቸዋል። በክርስቶስ--አይሁድ፣ ግሪክ፣ ባሪያ ወይም ነፃ የሚባል ሰው የለም።”—
Ellen G. White, Prophets and Kings, pp. 369, 370.
ጴጥሮስ በቤተ ክርስቲያን ሥራ ላይ ያዋላቸውን አራት መጠሪያ ማዕረጎች ለመገንዘብ
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 1ጴጥ. 2፡9-10። ከእነዚህ ማዕረጎች አብዛኞቹ እስራኤልን
አስመልክቶ በሚከተሉት የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች ተንጸባርቀዋል፡ ዘፀ. 19፡6 እና ኢሳ.
43፡20። እነዚህ እያንዳንዳቸው መጠሪያ ማዕረጎች ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር
ጋር ስላላት ግንኙነት ምን ዓይነት አጽንኦት ይሰጣሉ? (ለአብነት ያህል፡ “የተመረጠ
ትውልድ” የሚለው ማዕረግ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን መምረጡን እና ለእርሷ
ስላለው በአምላካዊ ዕቅድ የተበጀ ፍጻሜ አጽንኦት ይሰጣል።)
1.በጥንቷ እስራኤል ካህናት መሲሑን የሚያመላክት የእንስሳት
መሥዋእት ያቀርቡ ነበር። የቤተ ክርስቲያን አባላት የንጉሥ ካህን
እንደመሆናቸው ምን ዓይነት “መሥዋእቶች” ማቅረብ ይኖርባቸዋል?
(1ጴጥ. 2፡5)
2.እስራኤል ቅዱስ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ከዓለም እንድትለይ
አደረጋት። ሆኖም እነዚህ ሕዝቦች የደኅንነትን እውነቶች ለዓለም
ማካፈል ነበረባቸው። ይህ ለዛሬዋ ቤተ ክርስቲያንም ይሠራል። ከዓለም
እየተለዩ በተመሳሳይ ወንጌልን ለዓለም ማካፈል የሚቻልበት አቋም
ላይ መገኘት የሚቻለው እንዴት ነው? የእስራኤል ተሞክሮ እና የየሱስ
ምሣሌ ለዚህ ጥያቄ መልስ እንድንሰጥ እንዴት ይረዳናል?
3.እግዚአብሔር ሁሌም ቢሆን ትሩፋን ሕዝቦች ነበሩት። ኤልያስን እና
በእርሱ ዘመን የነበሩትን ትሩፋን ያስቡ (1ነገሥ. 19፣ በተለይ ቁ. 18
ይመልከቱ)። ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ካሉ የቤተ ክርስቲያን አባላት ይልቅ
በዓለማዊ ሕዝቦች መሃል ለእግዚአብሔር እውነተኛ መሆን ብዙውን
ጊዜ የሚቀለው ለምንድን ነው?
ማጠቃለያ፡ የእግዚአብሔር እውነተኛ እስራኤል (ከመስቀሉ በፊትም
ሆነ ኋላ) ከእርሱ ጋር በመንፈሳዊ የኪዳን ግንኙነት የሚኖር የእምነት
እስራኤል ነው። የእርሱ ተወካዮች ሆነው የሚሠሩ እንዲህ ያሉ ሰዎች፤
አምላካዊውን አዳኝ የወንጌል ጸጋ ለዓለም ያደርሳሉ።