የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘጸ. 3:14፣ ዘፍ. 17:1–6፣ ዘፍ. 41:45፣ ዳን. 1:7፣ ዘፍ. 15:7–18፣ ዘፍ. 17:1–14፣ ራእ. 14:6-7።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሰርታለሁ፤ በዚህም ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ፡፡” (ዘፍ. 17፡7)፡፡
ስ
ንቶቻችን ነን በልጅነታችን ክፉኛ የታመምን እና ያን የምናስታውስ? መላው
አካላችን ባተኮሰበት በዚያ የማይነጋ የሚመስል ረጅም ሌሊት ላመል ያህል
ሸለብ ካደረገን እንቅልፍ ብንን ስንል፣ ከአልጋችን አጠገብ ወንበር ላይ ቁጭ
ያለችውን እናታችንን ወይም አባታችንን በደብዛዛው ብርሃን ውስጥ እንመለከታለን።
ከላይ በምሣሌ ከቀረበው በተመሳሳይ ከጥፋት ውሃ አንስቶ ለአያሌ ምዕተ ዓመታት
በግብረገባዊው ጽልመት ቁልቁል እየወረደች የምትገኘው በኃጢአት የታወከች ዓለም
ከተኛችበት አልጋ አጠገብ እነሆ እግዚአብሔር ተቀምጧል። በዚህ ምክንያት--ስለ
ራሱ ተጨባጭ ዕውቀት በአደራ የሚሰጠውን እና የደኅንነት ባለቤት የሚያደርገውን
ሕዝብ የሚያቋቁምበትን ዕቅድ በማውጣት ታማኝ አገልጋዩን አብርሃምን ጠራው።
ስለሆነም እግዚአብሔር ከአብርሃም እና ከትውልዱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት፤
ሰብዓዊውን ፍጡር ከኃጢአት ውጤት ለመታደግ የሚያስችል በዝርዝር የተቀመጠ
መለኮታዊ ዕቅድ አወጣ። ጌታ የፈጠራትን ዓለም በዚህ አስጨናቂ ወቅት ብቻዋን
የመተው ሀሳብ አልነበረውም። በዚህ ሣምንት ተጨማሪ የቃል ኪዳን ተስፋዎችን
እየገለጥን እንመለከታለን።
ሣምንቱን በጨረፍታ፡ የእግዚአብሔር ስም ማን ነው? የስሙ ፍቺ
ምንድን ነው? እግዚአብሔር ራሱን ለአብርሃም ለመግለጽ የተጠቀመባቸው ስሞች
አንደምታቸው ምን ነበር? ራሱን ለመግለጽ የተጠቀማቸው ስሞች የትኞቹ ናቸው?
እግዚአብሔር አብራም የሚለውን ስያሜ ለምን ወደ አብርሃም ቀየረው? ስሞች
አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? ከቃል ኪዳኑ ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ወይም
ግዴታዎች ምንድን ናቸው?
“ይህችን ምድር ላወርስህ፣ ከከለዳውያን ምድር፣ ከዑር ያወጣሁህ
እግዚአብሔር እኔ ነኝ” (ዘፍ. 15፡7)።
ስሞች አንዳንዴ እንደ ንግድ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንድ የስም ባህሪዎች
ከአእምሮአችን ጋር በቅርበት የተሳሰሩ ከመሆናቸው የተነሣ ስሙን እንደ ሰማን
ወዲያውኑ ባህሪያቱን እናስታውሳለን። ለምሣሌ የሚከተሉትን ስሞች ሲሰሙ ምን
ዓይነት ባሕሪያት ወደ አእምሮዎ ይመጣሉ፡ አልበርት አንስታይን፣ ማርቲን ሉተር
ኪንግ ጄ.አር.፣ ጋንዲ ወይም ዶርቃ? እነዚህ እያንዳንዳቸው ከተለያዩ ባህሪዎች እና
ጽንሰ ሀሳቦች ጋር የተቆራኙ ናቸው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን፤ የቅርብ ምሥራቅ አገር ሕዝቦች ለስም ፍቺ ትልቅ ቦታ
ይሰጡ ነበር። ዕብራውያኑ ሁሌም ስለ ስም ሲያስቡ፤ ስያሜው የተሰጠውን ሰው
ግላዊ ባህሪያት ያመላክታል ወይም ያወጣውን ሰው ሀሳብና ስሜት ያሳያል ወይም
ደግሞ ያ ስም በወጣበት ወቅት የተስተዋሉ ክስተቶችን ይጠቁማል ብለው ያስባሉ።–
The SDA Bible Commentary, vol. 1, p. 523.
እግዚአብሔር በመጀመሪያ ከአብራም ጋር የቃል ኪዳን ግንኙነት ሲመሰርት ራሱን
ለዚህ አበው ያስተዋወቀው YHWH (በመጽሐፍ ቅዱስ ጌታ በሚል የቀረበ [ዘፍ.
15:7] እና ያህዌ ተብሎ የተነበበ) ብሎ ነው። ስለዚህ ዘፍ. 15፡7 ቃል በቃል ሲነበብ
“ይህችን ምድር ላወርስህ፣ ከከለዳውያን ምድር፣ ከዑር ያወጣሁህ ያህዌ (YHWH)
እኔ ነኝ” የሚል ይሆናል።
ያህዌ የተሰኘው ስም በብሉይ ኪዳን 6,828 ጊዜ ቢጠቀስም በተወሰነ መልኩ
ምስጢራዊ በሆነ ሁኔታ ተሸፍኗል። በዕብራውያኑ ስዋሰው ሃያህ ማለትም
“የመሆን” ግሥ ቅርጽ የተቀመጠው ይኸው ስያሜ፡ “ዘላለማዊ”፣ “ሕያው”፣ “ራሱን
ችሎ የሚኖር” ወይም “ለዘላለም የሚኖር” የሚል ፍቺ አለው። በዚህ መጠሪያ
አጽንኦት የተሰጣቸው መለኮታዊ ባሕሪያት በራስ ሕያው ሆኖ መኖር እና ታማኝነት
ይመስላሉ። ከአምላኪዎቻቸው ምናብ ባሻገር አንዳችም ሕልውና ካልነበራቸው
ከአረማውያን አማልክት በተቃራኒ ጌታን ሕያው አምላክ እና የሕይወት ምንጭ
አድርገው ያመላክታሉ።
እግዚአብሔር ራሱ ዘፀ. 3:14 ላይ የያህዌን ትርጉም ሲገልጽ “እኔ ያለሁና የምኖር
ነኝ” ይላል። እርሱ በቀድሞው፣ በአሁኑ እና በወደፊቱ ላይ ገዢ መሆኑን ፍቺው
ከመጠቆሙ በተጨማሪ የእግዚአብሔርን ያለ ገደብ ሕያው ሆኖ የመኖር ሁኔታ
ይገልጻል።
ከዚህ በተጨማሪ ያህዌ የእግዚአብሔር የግል ስም ነው። አብርሃምን ከኡር
በማውጣቱ ተለይቶ የታወቀው ያህዌ የተሰኘው መታወቂያ ስም--በዘፍ. 12፡
1-3 ከዚሁ አበው ጋር ለየተገባው አምላካዊ ኪዳንም እንዲሁ ማጣቀሻ ሆኖ
ቀርቧል። አብርሃም የእግዚአብሔርን ስም ያውቅ ዘንድ የጌታ ፍላጎት ነበር።
ያ ስም የእርሱን ማንነት፣ ግላዊ ተፈጥሮ እና ባሕሪያዊ ገጽታዎች በግልጽ
የሚያሳይ እንደመሆኑ፤ እኛም ከዚህ ዕውቀት በእርሱ ተስፋዎች ላይ መደገፍ
መማር እንችላለን (መዝ. 9፡10፣ 91፡14)። ያህዌ ስለ ተሰኘው ስም ሲያስቡ
ወይም ሲሰሙ ወዲያውኑ ወደ አእምሮዎ የሚመጡ ባሕሪያት የትኞቹ
ናቸው? ፍቅር፣ ደግነት እና እንክብካቤ ወይስ ፍርሃት፣ ጥብቅነትና ተግሳጽ?
የሱስ ስለ ተሰኘው ስም ሲያስቡ ወዲያውኑ ወደ አእምሮዎ የሚመጡ
እሳቤዎችስ?
“አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ
አለው፤ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ” (ዘፍ. 17፡1)
ያህዌ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ለአብርሃም ተገልጦለት ነበር (ዘፍ. 12:1፣ 7፣ ዘፍ.
13:14፣ ዘፍ. 15:1፣ 7፣ 18)። አሁን ደግሞ ከላይ በቀረበው ጥቅስ መሠረት ያህዌ
ለአብርሃም እንደገና፤ ራሱን እንደ “ኤልሻዳይ (ሁሉን ቻይ)” አምላክ የገለጠ ሲሆን፤
ይህ መጠሪያ ጥቅም ላይ የዋለው በዘፍጥረት መጽሐፍ እና በመጽሐፈ ኢዮብ ብቻ
ነው። “ኤልሻዳይ” በተሰኘው ስም የምናገኘው ኤል--በሴማውያን ዘንድ መሰረታዊ
የእግዚአብሔር መጠሪያ ስም ነው። ምንም እንኳ ለ“ሻዳይ” ትክክለኛ ፍቺ ሙሉ
ለሙሉ እርጠኛ መሆን ባይቻልም “ሁሉን ቻይ” የሚለው ትርጉም በጣም ትክክለኛ
ይመስላል (ያስተያዩ፡ ኢሳ. 13፡6 እና ኢዮኤል 1፡15)። በዚህ ስም አጠቃቀም ረገድ
ወሳኙ ሀሳብ የእግዚአብሔርን ኃያልነት ከሰው ልጆች ደካማነትና ተሰባሪነት ጋር
ለማነጻጸር ይመስላል።
ማንኛውንም ነገር ከፍ ባለ ዐውድ ለማስቀመጥ የሚረዱትን እነዚህን ጥቅሶች
ያንብቡ፡ ዘፍ. 17፡1-6። ጌታ በዚህ ወቅት ሁሉን ቻይነቱንና ኃያልነቱን አጥብቆ
ለአብርሃም ሊያሳስብ የፈለገው ለምንድን ነው? አብርሃም በእግዚአብሔር ሁሉን
ቻይነትና ኃያልነት ለመታመን ስለሚያስፈልገው ነገር ጌታ ምን እያለው ነበር? በተለይ
ቁጥር ስድስትን ይመልከቱ።
“እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ አለው ‘እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤
ነቀፋም አይኑርብህ፤ በእኔና በአንተ መካከል የተመሠረተውን ኪዳን አጸናለሁ፤
ዘርህንም እጅግ አበዛለሁ።… የብዙ ሕዝቦች አባት ትሆናለህ።… የብዙ ሕዝቦች አባት
አድርጌሃለሁና። ዘርህን እጅግ አበዛለሁ።’ ” ይህ ተመሳሳይ ስም በዘፍ. 28፡3 ላይም
እንዲሁ የሚገኝ ሲሆን “ሁሉን ማድረግ የሚችል ይባርክህ፤ ብዙ ሕዝብ እስክትሆን
ድረስ ልጆች አፍራ፤ ዘርህን ያብዛው” ይላል።
በተመሳሳይ በዘፍ. 35፡11፣ ዘፍ. 43፡14 እና ዘፍ. 49፡25 የቀረቡ የ “ኤልሻዳይ”
የተስፋ ቃሎች የእግዚአብሔርን ለጋስነት ያመለክታሉ። ኤል--የሥልጣንና ኃይል
ባለቤትነቱን እንዲሁም ሻዳይ--ፍጻሜ የሌለው ሀብት ባለቤትነቱን፤ ይኸውም
በእምነት እና በመታዘዝ ይህን ለሚሹ ሁሉ ለመስጠት ፈቃደኛ አምላክ መሆኑን
ያሳያል።
ጽጌረዳ--ከማንኛውም ስም ጋር ቢጠራ፣ ያን ስም በመልካም መአዛ ሽታ
የሞላ ያደርገዋል ይባላል። ሆኖም የጌታ ስም “ደካማው አምላክ” ቢሆን
ኖሮ ምን ያህል መጽናኛና ተስፋ ይኖሮት ነበር? ለዛሬ ጥናት የቀረበውን
ጥቅስ ይመልከቱ። “ሁሉን ቻይ” አምላክ የሚለውን ስም በሌሎች ስሞች
ይተኩ። ጌታ በዚህ መንገድ ራሱን ለእኛ ቢያቀርብ፤ ሁኔታው በእምነትዎ እና
በእርሱ ላይ በሚኖሮት መታመን ላይ ምን ሊያስከትል ይችላል? በተመሳሳይ
“ኤልሻዳይ” የሚለው ስም እንዴት ምቾት ይሰጠናል?
የእግዚአብሔር ስሞች ከመንፈሳዊ እና ሥነ መለኮታዊ አንደምታዎች ጋር ቢመጡም፤
እግዚአብሔር በሚል ብቻ አያበቁም። በጥንቱ ቅርብ ምሥራቅ ክፍለ ዓለም የነበሩ
ሕዝቦች ስም፣ ብዙውን ጊዜ ለእኛ እንደሚመስለን ትርጉም በማይሰጥ መንገድ
የሚወጡ አልነበሩም። ዛሬ ሜሪ ወይም ሱዚ ብሎ ሴት ልጅን መጥራት ብዙ ለውጥ
የለውም። ለጥንት ሴማውያን ግን የሰው ስሞች ብርቱ መንፈሳዊ አንደምታ ነበራቸው።
ሁሉም የሴማውያን ስሞች ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ፤ ብዙውን ጊዜ በወላጆች በኩል
የሚቀርብ መልካም ምኞት ወይም የምስጋና መግለጫ ያካተተ ሀረግ ወይም አጭር
ዓረፍተ ነገር ያካትታሉ። ለምሳሌ፡ ዳንኤል “እግዚአብሔር ፈራጅ ነው” የሚል ፍቺ
ያለው ሲሆን፤ ኢዮኤል “ያህዌ አምላክ ነው” ወይም ናታን “የእግዚአብሔር ስጦታ”
የሚል ፍቺ አላቸው።
ከስሞች ጋር ተያያዥነት ያላቸው አንደምታዎች መኖራቸውን ተከትሎ፤ ብዙውን
ጊዜ ስሞች በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ የተከሰተን ሥር ነቀል ለውጥና ሁናቴን
ለማንጸባረቅ ሲባል ይቀየራሉ።
የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ ምን ዓይነት ሁናቴዎች ይናገራሉ? በእነዚህ
ሁናቴዎች ስሞች ለምን ተቀየሩ?
1. ዘፍ. 32:28______________________________________________________
2. ዘፍ. 41:45______________________________________________________
3. ዳን. 1:7________________________________________________________
በአንድ በኩል ዓለም በሰለጠነበት በዚህ ዘመን ያለ አእምሮም ቢሆን አንድ ሰው
የሚጠራበት ስም ትርጉም አዘል የመሆኑን አስፈላጊነት ለማስተዋል የሚቸገር
አይሆንም። የስም ፍቺዎች አንዳንዴ ረቂቅ የሆኑ ወይም ያልሆኑ ውጤቶች
ሊያስከትሉ ይችላሉ። አንድ ሰው በተደጋጋሚ “ደደብ” ወይም “አስቀያሚ” ከተባለና
እነዚህን መጠሪያዎች ብዙዎች የሚጠቀሙ ከሆነ--ውሎ አድሮ ስሞቹ ግለሰቡ ራሱን
በሚያይበት መነጽር ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። በተመሳሳይ ለሰዎች የተወሰኑ
ስሞችን በማውጣት ወይም ስማቸውን በመቀየር ራሳቸውን በሚመለከቱተበት
ሁናቴ ላይ ተጽእኖ ማድረግ እና የሚሰጡትን አጸፋ ማበረታታት ይቻላል።
ይህንን ከግምት በማስገባት፤ እግዚአብሔር አብራምን ወደ አብርሃም መለወጥ
የፈለገበትን ምክንያት ለመረዳት ያን ያህል ከባድ አይሆንም። አብራም፡ “አባት ከፍ
ከፍ አለ” የሚል ፍቺ ያለው ሲሆን፤ አብርሃም ደግሞ “የብዙዎች አባት” ማለት
ነው። “ ‘ዘርህን እጅግ አበዛለሁ፤ ብዙ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ ነገሥታትም ከአንተ
ይወጣሉ” (ዘፍ. 17፡6) በሚል የቀረበውን የቃል ኪዳን ተስፋ ሲመለከቱ፣ የተደረገው
የስም ለውጥ የተሻለ ትርጉም ይሰጣል። ምናልባት አብርሃም በቃል ኪዳኑ ተስፋ
ላይ እምነት እንዲጥል ለመርዳት (መካን ከነበረች አሮጊት ሚስቱ ጋር ለነበረ የ99
ዓመት አዛውንት) የተደረገ አምላካዊ መንገድ ሊሆን ይችላል። በአጭሩ፣ አብርሃም
በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ ያለው እምነት ይጨምር ዘንድ እግዚአብሔር ያደረገው
ነገር ነው።
ከላይ በቀረቡት ሁለት ጥቅሶች እግዚአብሔር ለአብርሃም ከገባው ቃል ኪዳን
የመጀመሪያው ደረጃ (ሦስት ናቸው) ተገልጧል። እግዚአብሔር ወደ አብርሃም
ቀርቦ ትእዛዝ ከሰጠው በኋላ ቃል ገባለት። ጌታ ወደ አብርሃም መቅረቡ--በቸርነት
የተሞላው አምላክ አብርሃምን በዓይነቱ ልዩ ለሆነው የጸጋ ኪዳን የመጀመሪያው ዋንኛ
አካል አድርጎ የመረጠው መሆኑን ይገልጻል። ትእዛዙ ሙሉ ለሙሉ በእግዚአብሔር
ላይ የመታመን ፈተናን ያካትታል (ዕብ. 11፡8)። የተስፋ ቃሉ (ዘፍ. 12፡1-3፣7) ምንም
እንኳ በተለይ ለአብርሃም ትውልድ የተሰጠ ቢሆንም፤ ውሎ አድሮ መላውን ሰብዓዊ
ዘር የሚያካትት ነበር (ዘፍ. 12፡3፣ ገላ. 3፡6-9)።
እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር የገባው ሁለተኛው ደረጃ ኪዳን በዘፍ.
15፡7-18 ቀርቦአል። በመጀመሪያው ደረጃ የታዩትን አንዳንድ
ተመሳሳይ እርምጃዎች በየትኛው ጥቅሶች እናገኛቸዋለን?
የእግዚአብሔር ወደ ሰው መቅረብ? ቁጥር? _______________________________
ሰብዓዊው ፍጡር እንዲታዘዝ የቀረበ ጥሪ? ቁጥር?_______________________
መለኮታዊ የተስፋ ቃል? ቁጥር ?_______________________________________
በደረጃ ሁለት በቀረበው ከበድ ያለ ሥርዓታዊ ትዕይንት ውስጥ ጌታ ለአብርሃም
በመገለጥ--ሁለት ቦታ በተከፈለውና እያንዳንዱ ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ ሆኖ
በጥንቃቄ በተደረደረው የእንስሳት ሥጋ መካከል አለፈ። እነዚህን ሦስት እንስሳት
ካረዳቸው በኋላ እያንዳንዳቸውን ሁለት ቦታ ከፈለ። በመካከላቸው ክፍተት
በመተው--እያንዳንዱን ወገን በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጠ። ዋኖሷና ርግቧ ግን
ተገደሉ እንጂ ለሁለት አልከፈላቸውም ነበር። ወደ ቃል ኪዳኑ የሚገቡ በተከፈሉት
መካከል ተራምደው ማለፍ የነበረባው ሲሆን፤ ይህም ድንጋጌዎቹን ለዘላለም
ለመታዘዝ የመስማማታቸው የተቀደሰ ቃለ መሃላ ተምሳሌት ነው።
በሦስተኛው እና በመጨረሻው ደረጃ ላይ ምን እንደተከሰተ ይግለጹ (ገላ. 17፡
1-14)።
አብርሃም የሚለው ስም ትርጉም--እግዚአብሔር ሁሉንም ህዝቦች ለማዳን ባለው
ፍላጎት እና እቅድ ዙሪያ አጽንኦት ይሰጣል። “ብዙ ሕዝብም አደርግሃለሁ” የሚለው
ሃረግ አይሁዶችንና አሕዛብን ያጠቃልላል። አዲስ ኪዳን እውነተኛ የአብርሃም ዘሮች-የአብርሃም እምነት ያላቸው እና ቃል በተገባው መሲህ መልካም ሥራ የሚታመኑ
መሆናቸውን ግልጽ በሆነ ቋንቋ ይናገራል። (ገላ. 3፡7፣ 29)። ስለሆነም የጌታ ዕቅድ
ወደ ኋላ እስከ አብርሃም ዘመን ተጉዞ፣ የየትኛውንም አገር ሕዝቦች በተቻለው መጠን
ማዳን ነበር። እነሆ ዛሬም ከዚህ የተለየ ነገር የለም።
የመጀመሪያውን መልአክ መልእክት ያንብቡ፡ ራእ. 14፡6-7።
መልአኩ በሚናገረውና በአብርሃም ቃል ኪዳን ውስጥ በተከናወነው
መካከል ምን ዓይነት ተመሳሳይ ነገሮች ማግኘት ይችላሉ? ጉዳዮቹን
የሚያመሳስሏቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
“‘ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ
ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቦቹን እንዲያዝ መርጬዋለሁ፤ ይኸውም
እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ሁሉ እንዲፈጸም ነው።’ ” (ዘፍ. 18:19)።
እስካሁን እንደ ተመለከትነው፣ ቃል ኪዳኑ--ሁሌም እኛ ለራሳችን ማድረግ
የማንችለው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለእኛ የሚያደርግልን የጸጋ ቃል ኪዳን ነው።
ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን ውስጥ አንዳችም ከዚህ የተለየ ነገር የለም።
ለዓለም በሚደረገው የደኅንነት እቅድ እወጃ አብርሃም ድርሻ ይኖረው ዘንድ፤ ከጸጋው
ብዛት እግዚአብሔር መሣሪያው አድርጎ መርጦታል። ሆኖም፤ የእግዚአብሔር
የቃል ኪዳኑ ተስፋዎች ፍጻሜ፤ አብርሃም ጽድቅን ለማድረግ እና እርሱን በእምነት
ለመታዘዝ ከሚኖረው ፈቃደኝነት ጋር የተቆራኘ ነበር። በአብርሃም በኩል ይጠበቅ
የነበረው ያ መታዘዝ ባይኖር--እግዚአብሔር ሊጠቀምበት ባልቻለ ነበር።
ዘፍ. 18፡19--ጸጋ እና ሕግ እንዴት እንደሚዛመዱ በጉልህ ያሳየናል። ጥቅሱ፡
አውቀዋለሁ፤ የሚል አንደምታ ባለው የጸጋ አነጋገር ይጀምርና--አብርሃም ጌታን
የሚታዘዝ፣ ቤተሰቡም ጭምር እርሱን እንዲታዘዙ የሚያደርግ ሰው መሆኑን የሚገልጽ
ተጨባጭ እውነታ ይከተላል። እምነት ከሥራ ጋር መቆራኘቱ የግድ እንደመሆኑ፤
እነዚህ ሁለቱ በዚህ ስፍራ የጠበቀ ህብረት ፈጥረው ይታያሉ (ያዕ. 2፡17)።
በዘፍ. 18፡19 የቀረበውን መልእክት በተለይም የመጨረሻውን ሀረግ ልብ ይበሉ።
ስለ አብርሃም ታዛዥነት ምን እያለ ነው? ምንም እንኳ መታዘዝ መዳኛ መንገድ
ባይሆንም፣ በዚህ ስፍራ አጽንኦት የተሰጠው ነገር ምንድን ነው? በዚህ ጥቅስ መሠረት
መታዘዝ በሌለበት ሁኔታ ቃል ኪዳኑ ፍጻሜ ማግኘት ይችላል? መልስዎን ያብራሩ።
የተወሰኑ ሁናቴዎች በተጠቃሚዎቹ እስካልተሟሉ ድረስ የቃል ኪዳኑ በረከቶች
ተካፋይ ወይም ተጠቃሚ መሆን አይቻልም። ምንም እንኳ ቃል ኪዳኑን ለማቋቋም
ቅድመ ሁናቴዎች ባያስፈልጉም--የፍቅር፣ የእምነት እና የመታዘዝ ምላሽ መሆን
ነበረባቸው። በሰብዓዊው ፍጡር እና በእግዚአብሔር መካከል ላለው ግንኙነት
መገለጫ መሆን ነበረባቸው። መታዘዝ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የገባውን ቃል ኪዳን
የሚፈጽምበት መንገድ ነበር። በአንጻሩ አለመታዘዝ ቃል ኪዳን ማፍረስ ሲሆን፤ ይህ
ደግሞ ለተመሰረተው ግንኙነት ታማኝ አለመሆን ነው።
እርስዎ ከጌታ ጋር ባሎት የግንኙነት ተሞክሮ መታዘዝ ለምን አስፈላጊ
እንደሆነ መመልከት ይችላሉ? አለመታዘዝ የቃል ኪዳን ተስፋዎች
ፍጻሜ እንዳያገኙ ያደረገበትን ክስተት ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከገዛ
ተሞክሮዎ በምሳሌ ማቅረብ ይችላሉ? እንዲያ ከሆነ፤ ምንድን ናቸው?
ከሁሉም በላይ--መፍትሔው ምንድን ነው?
Read Ellen G. White, “The Call of Abraham,” pp. 125–
131, in Patriarchs and Prophets; “Jew and Gentile,” pp. 188–200, in The
Acts of the Apostles.
ቀስተ ደመናው እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳን የመግባቱ ምልክት ነው።
እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር የገባው የቃል ኪዳን ምልክት ምን እንደነበረ ለማወቅ
ዘፍ. 17፡10 ያንብቡ። መገረዝ “(1) የአብርሃምን ዘር ከአሕዛብ ለመለየት፡--ኤፌ. 2፡
11፣ (2) የይሖዋን ቃል ኪዳን መታሰቢያ ለማቆየት፡--ዘፍ. 17፡11፣ (3) ሥነ ምግባራዊ
ንጽህና የመኮትኮት ሥራን ለማበረታታት፡--ዘዳ. 10፡16፣ (4) ጽድቅ በእምነትን
ለመወከል፡--ሮሜ 4፡11፣ (5) የልብ መገረዝ ምሣሌ እንዲሆን፡--ሮሜ 2፡29 እና
(6) የወደፊቱን የክርስትና ጥምቀት ሥርዓት ለማሳየት፡--ቆለ. 2፡11-12 የተደነገገ
ነበር።”—The SDA Bible Commentary, vol. 1, pp. 322, 323.
ቀስተ ደመና እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ምልክት ሆኖ
የሚቆይ ሲሆን፤ መገረዝ ግን በምልክትነት አይዘልቅም። በሐዋርያው ጳውሎስ
መልእክት መሰረት አብርሃም ከእግዚአብሔር በእምነት ላገኘው ጽድቅ መገረዝን
በምልክትነት ተቀበለ (ሮሜ 4፡11)። ሆኖም ለተከታዮቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ አያሌ
ዘመናት መገረዝ ሕጉን በመታዘዝ የሚገኝ ደኅንነት አመላካች ሆኖ ብቅ አለ። በአዲስ
ኪዳን ዘመን መገረዝ ቀድሞ የነበረውን ትርጉም አጥቷል። በምትኩ አብይ የሆነው
መሰረታዊ ነገር ወደ መታዘዝና የተለወጠ ሕይወት የሚመራው በየሱስ ክርስቶስ ላይ
የሚኖር እምነት ነው። ገላ. 5፡6፣ ገላ. 6፡15፣ 1ቆሮ. 7፡18-19።
1. በእምነት እና በሥራ መካከል ስላለው ግንኙነት ተወያዩ። አንዱ ያለ
ሌላው ሊኖር ይችላል? ካልሆነ ለምን?
2.“አሁን ድረስ በርካቶች እንደ አብርሃም ዓይነት ፈተና ይሰጣቸዋል።
እነዚህ ወገኖች የእግዚአብሔርን ድምፅ በቀጥታ ከሰማይ ባይሰሙም ነገር
ግን በቃሉ አስተምህሮና በቸርነቱ መስመሮች ጣልቃ እየገባ ይጠራቸዋል።
ሐብትና ክብር የሚያስገኝላቸውን ሥራቸውን እንዲተዉ፣ ተስማሚ እና
አትራፊ ድርጅቶቻቸውን እንዲለቁ እና ከቤተሰባቸው እንዲነጠሉ፣
ወደ ራስን መካድ፣ መከራ እና መስዋዕት መስመር እንዲገቡ ሊጠየቁ
ይችላሉ። እግዚአብሔር እነርሱ እንዲሠሩ ያዘጋጀው ሥራ አለ፤ ነገር
ግን ምቾት ያለው ሕይወት፣ የጓደኞች እና የቤተሰብ ተጽእኖ ሥራው
እንዲሳካ የሚያስፈልጉ ወሳኝ ግብአቶች እንዳይጐለብቱ ያደርጋል።
እግዚአብሔር ሲጠራቸው ከሰብዓዊው ፍጡር ተጽእኖ እና እገዛ ውጪ
ሆነው የእርሱ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እንዲሰማቸውና በእርሱ
ላይ ብቻ እንዲተማመኑ በማድረግ ራሱን ሊገልጥላቸው ይችላል። የኑሮ
እቅዶችን እንዲሁም የተለመዱ ቤተሰባዊና ማኅበራዊ ግንኙነቶችን
በእግዚአብሔር ጥሪ ምክንያት ለመተው የተዘጋጀ ማን ነው?”—Ellen G. White, Patriarchs and Prophets, pp. 126, 127.
ከዚህ ጥሪ ጋር ተመሳሳይነት ባላቸውና እርስዎ በሚያውቋቸው የቅርብ
ክስተቶች ላይ ተወያዩ።
ማጠቃለያ፡ አብርሃም ከእግዚአብሔር ጋር የተለየ ግንኙነት ይመሠርት
ዘንድ ጌታ ጥሪ አቀረበለት። ጥሪው አምላካዊውን የደኅንነት ዕቅድ ለዓለም
የሚገልጥ ነበር።