የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 3:6፣ ዘፍ. 6:5፣ 11፣ ዘፍ. 6:18፣ ዘፍ. 9:12–17፣ ኢሳ. 4:3፣ ራእ. 12:17።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ ““ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አገኘ” (ዘፍ. 6፡ 8)፡፡
ረ
ቂቅ ተህዋሲያን (ባክቴርያ) በጣም አነስተኛ እንደ መሆናቸው እነርሱን
ከአጉሊ መነጽር ውጪ መመልከት አይቻልም። አንድ የተለመደ ባለ ክብ
ቅርጽ ረቂቅ ተህዋሲ፣ አንድ ሺ ጊዜ ከጎላ በኋላም እንኳ ከእርሳስ ነጥብ
በላይ መታየት አይችልም። ረቂቅ ተህዋሲያኑ ለዕድገት ምቹ ሁኔታዎች ማለትም በቂ
ሙቀት፣ እርጥበት እና ምግብ ካገኙ እጅግ ፈጣን በሆነ ፍጥነት ይራባሉ። ለምሣሌ
አንዳንድ ረቂቅ ተህዋስያን በቀላል ክፍፍል የሚራቡ ሲሆን፤ በዚህም አንድ የጎለመሰ
ባክቴርያ በቀላሉ ወደ ሁለት ሴቴ ጓል ይከፋፈላል። መከፋፈል በየሰዓቱ ሲከሰት አንድ
ባክቴርየም በ24 ሰዓት ውስጥ ከ18 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ባክቴሪያዎችን ማምረት
ይችላል። በ48 ሰዓታት ውስጥ ደግሞ በመቶ ቢልዮን የሚቆጠሩ ባክቴርያዎች
ይፈጠራሉ።
ይህ በተፈጥሮአዊው ዓለም እየተስተዋለ ያለው በዓይን የማይታይ የባክቴርያ ባህሪ፤
ከውድቀት በኋላ የተከሰተውን የክፉውን ፈጣን ዕድገት ያሣያል። ጥልቅ የማሰብ
ችሎታ፣ የተሟላ ጤንነትና ረዥም ዕድሜ የተቸራቸው እነዚህ ብርቱ ፍጡራን
እግዚአብሔርን በመተው፤ ሁሉም ዓይነት እርክስና ቀጣይነት ይኖረው ዘንድ በዚህ
ብርቅዬ አቅምና ጉልበታቸው ምንዝር ፈጸሙ። ባክቴሪያዎች በፀሐይ ብርሃን፣
በኬሚካሎች ወይም በከፍተኛ የሙቀት መጠን ሊጠፉ ቢችሉም፣ እግዚአብሔር
ይህንን የተንሰራፋ አመፃ ምድርን ከዳር እስከ ዳር ባጥለቀለቀ የጥፋት ውሃ ለመፈተሽ
መረጠ።
ሣምንቱን በጨረፍታ፡ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ምን አደረሰ? የኖኅ
ባህሪያት ምን ይመስላሉ? ከኖኅ ጋር በተገባው ቃል ኪዳን ምን ዓይነት መሠረታዊ
ነገሮች ተካተው ነበር? “ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋር” በሚል በቀረበው በዚህ
በ3ኛው ትምህርት፤ እግዚአብሔር ከጥፋት ውሃ በፊት ከኖኅ ጋር በገባው ቃል
ኪዳን ጸጋው የተገለጠባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው? እግዚአብሔር ከጥፋት
ውሃ በኋላ ከሰው ልጆች ጋር የገባው ኪዳን ለእኛ ስላለው ዩኒቨርስ አቀፍ ፍቅር ምን
ያስተምረናል?
በአምላካዊው የፍጥረት ሥራ መጨረሻ የተሰጠው መለኮታዊ አስተያየት ሁሉም
“እጅግ መልካም ነበረ” በሚል እንደ ቀረበ እንመለከታለን (ዘፍ. 1 31)። ከዚያ
ኃጢአት ገባና የንድፉ አቅጣጫ ተለወጠ። ነገሮች ከእንግዲህ “እጅግ መልካም”
መሆናቸው አከተመ። አምላካዊው በሥርዓት የሚጓዝ የፍጥረት ሥራ በኃጢአት እና
ያን ተከትሎ በመጡ አጸያፊ ውጤቶች ተበላሸ። ዐመጻ በኖኅ ዘመን አስከፊ ደረጃ
ላይ ደርሶ ነበር። ክፉው ሰብዓዊውን ዘር ፈጀው። ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ሰፋ
ያለ ዝርዝር ባይሰጠንም፤ የተስተዋለው መተላለፍ እና ዐመጻ--አፍቃሪ፣ ታጋሽ እና
ይቅር ባይ የሆነው አምላክ እንኳ ሊታገሰው የማይችለው ነበር (የኃይማኖት አባቶች
እና ነቢያት፡ ገጽ 92-94)።
ለመሆኑ ነገሮች እንዴት እንዲህ በፍጥነት የከፉ ሊሆኑ ቻሉ? መልሱን ማግኘት
ምናአልባት ያን ያህል ከባድ ላይሆን ይችላል። ዛሬ ወደ ገዛ ራሳቸው ኃጢአት
እየተመለከቱ፡ ነገሮች እንዴት እንዲህ በፍጥነት የከፉ ሆኑ? የሚል ተመሳሳይ ጥያቄ
የማይጠይቁ ስንቶች ናቸው?
ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥቅሶች ይመልከቱ። ያነሱትን ነጥቦች ይጻፉ። የማያቋርጠውን
የኃጢአት መስፋፋትና መፋጠን ያስተውሉ።
1. ዘፍ. 3:6_________________________________________________________
2. ዘፍ. 3:11–13____________________________________________________
3. ዘፍ. 4:5_________________________________________________________
4. ዘፍ. 4:8_________________________________________________________
5. ዘፍ. 4:19________________________________________________________
6. ዘፍ. 4:23________________________________________________________
7. ዘፍ. 6:2_________________________________________________________
8. ዘፍ. 6:5፣ 11_____________________________________________________
ዘፍ. 6፡5 እና 11 እንደው ከምንም አልመጡም። ከእነርሱ አስቀድሞ ራሱን የቻለ
ታሪክ ነበረ። ይህ አስከፊ ውጤት መንስዔ ነበረው። ኃጢአት ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየተባባሰና እየከፋ መሄዱን ተያያዘው። ኃጢአት እንዲህ ዓይነት አዝማሚያ አለው።
ኃጢአት በስለት ስንቆረጥና ስንቆስል በአካላችን የተገነባው ፈጣን ሂደት ፈውስ
እንደሚያመጣልን ዓይነት ሽረት አያገኝም። በተቃራኒው ኃጢአት ችላ የሚባል ከሆነ
ወደ ጥፋት እና ሞት እስኪያደርስ፣ በላይ በላይ እየጨመረ ከመሄድ በቀር ፈጽሞ
መቆሚያ የለውም። አንድ ሰው ያ መርኅ እንዴት ይሠራ እንደ ነበር ለማየት ሕይወት
ከጥፋት ውሃ አስቀድሞ ምን ይመስል እንደ ነበር የግድ ማሰላሰል አይኖርበትም።
ምክንያቱም ዛሬም፣ በጉልህ በዙሪያችን አለ።
እግዚአብሔር ኃጢአትን ቢጠላ አያስደንቅም። ይዋል ይደር እንጂ፣ ኃጢአት
የሚወገድ መሆኑም እንዲሁ አያስደንቅም። ጻድቅና አፍቃሪ የሆነው አምላክ ከዚህ
ውጪ ሌላ ምንም ማድረግ አይችልም።
ምንም እንኳ እርሱ ኃጢአትን ለማስወገድ ቢፈልግም፣ ኃጢአተኞችን
ማዳን ይፈልጋል። ይህ በእርግጥ መልካም የምሥራች ነው። ቃል ኪዳኑ
የሚያወሳውም ይኸው ነው።
ከጥፋት ውሃ በፊት ስለ ነበረው ዓለም ክፋት ከሚገልጹ መልእክቶች መሃል፤ ኖኅ
የተባለ ሰው በዙሪያው ከነበሩ በተቃራኒ ቆሞ ይታያል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እርሱ
የሚጠቅሳቸውን በዓይነታቸው ልዩ የሆኑ ሦስት ነጥቦች ከላይ በቀረበው ጥቅስ
ይመልከቱ። እነዚህ እያንዳዳቸው ነጥቦች ምን ይላሉ ብለው ያስባሉ?
1.“ጻድቅ” ሰው ነበር፡ ________________________________________________
2.“ከበደል የራቀ” ነበር፡ ______________________________________________
3.“አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ” _______________________________
ኖኅ ከጌታ ጋር ሕያው ግንኙነት የመሠረተ ሰው እንደ ነበር አያጠያይቅም። እርሱ
ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ የሚሠራ፣ እርሱን የሚያዳምጥ፣ የሚታዘዝና የሚታመን
ዓይነት ሰው ነበር። ጌታ ዓላማዎቹን ለማስፈጸም እርሱን መጠቀም የቻለበት ምክንያት
እና ጴጥሮስ በአዲስ ኪዳን “የጽድቅ ሰባኪ” (2ጴጥ. 2፡5) ብሎ የጠራው ለዚህ ነው።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 6፡8። ጥቅሱ በኖኅ እና በጌታ መካከል
የነበረውን ግንኙነት እንድናስተውል እንዴት ይረዳናል?
በምሕረት የተሞላ፣ በበጎ ምግባር ያልተገኘ አምላካዊ ሞገስ፣ ለማይገባቸው
ኃጢአተኞች የተደረገ--የሚሉ አንደምታዎች ያሉት ጸጋ የተሰኘው ቃል ለመጀመሪያ
ጊዜ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጠቀሰው በዚህ ስፍራ ሲሆን፤ ከአዲስ ኪዳን
ማጣቀሻዎች ጋር ተመሳሳይ ፍቺ አለው። ኖኅ “ከበደል የራቀ” እና “ጻድቅ” ሰው
ቢሆንም፤ አምላካዊው ሞገስ የማይገባው ኃጢአተኛ መሆኑን ግን ማስተዋል
ይኖርብናል። ከዚህ አንጻር ኖህ ጌታን ለመከተል ከልብ ከሚፈልግ ከማንኛውም ሰው
አይለይም።
እንደ ሌሎቻችን ሁሉ ኖኅ የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳስፈለገው በማስተዋል፤
ወደ ገዛ ሕይወትዎ ይመልከቱና ራስዎን እንዲህ ብለው ይጠይቁ--እኔ እንደ
ኖኅ “ጻድቅ”፣ ከበደል የራቅኩ እና አካሄዴን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረግኩ
ሰው ነኝ? ለማንኛውም አቋሞዎ ምክንያቶችዎን ይጻፉ። ፈቃደኛ ከሆኑ
ለሰንበት ትምህርት ጥናት ቡድንዎ ያካፍሉ።
“‘ካንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እመሠርታለሁ። አንተና ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና
የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋር ወደ መርከቧ ትገባላችሁ’ ” (ዘፍ. 6:18)።
በዚህ አንድ ጥቅስ ውስጥ እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ያደረገው የመጽሐፍ
ቅዱሳዊ ኪዳን መሠረታዊ አላባዎች አሉን፡ እነሆ እግዚአብሔር እና ሰብዓዊው
ፍጡር ውል ገቡ። ነገሩ ቀላል ነው። ገና በመጀመሪያ ዐይን ከሚያርፍበት ነገር የላቁ
ባሕሪዎች አሉ። ሲጀመር፣ በሰው በኩል መታዘዝ የሚባል መሰረታዊ ጉዳይ እንደ
መኖሩ፤ ኖኅ ቤተሰቡን ይዞ ወደ መርከቢቱ እንዲገባ በእግዚአብሔር ተነግሮታል።
እርሱና ቤተሰቡ እንዲፈጽሙት የሚጠበቅባቸው የበኩላቸው ድርሻ የነበረ ሲሆን፤
ያን ባያደርጉ ግን ቃል ኪዳኑ ይፈርሳል።
የቃል ኪዳኑ ተጠቃሚዎች እነርሱ
እንደመሆናቸው--ኪዳኑ ከፈረሰ ውሎ አድሮ ተጎጂዎቹ እነርሱ ራሳቸው ይሆናሉ።
ሆኖም፤ ኖኅ እምቢ ብሎ ለኪዳኑ ባይገዛ ወይም እሺ ካለ በኋላ ሀሳቡን ቢቀይር፤
የእርሱም ሆነ የቤተሰቡ የመጨረሻ ውጤት ምን ሊሆን ይችል ነበር?
እግዚአብሔር ያ “የእኔ ቃል ኪዳን ነው ይላል። አባባሉ ስለ ቃል ኪዳኑ
መሠረታዊ ባሕሪይ ምን ይነግረናል? ጌታ “ቃል ኪዳናችን” ብሎ
ቢጠራው፤ ስለ ቃል ኪዳኑ በሚኖረን ግንዛቤ ላይ ምን ዓይነት ልዩነት
ሊያመጣ ይችላል?
ይህ ሁኔታ በዓይነቱ ልዩ ቢሆንም መሠረታዊው የአምላክ እና ሰው መስተጋብር
በኪዳኑ ቀርቦ እንመለከታለን። ከኖኅ ጋር “ኪዳኔን” እመሠርታለሁ በማለት-እግዚአብሔር እዚህ ላይ በድጋሚ አምላካዊውን ጸጋ ገልጦ ያሳያል። በዚህም የሰውን
ልጆች--ኃጢአታቸው ካስከተለባቸው ውጤት ለማዳን ተቀዳሚውን ተነሳሽነት
ለመውሰድ ያለውን ፈቃደኝነት ያሳየናል። በአጭሩ የዚህ ቃል ኪዳን የሽርክና አጋሮች
የእኩል ማንነት ኅብረት እንዳላቸው ተደርጎ መታየት የለበትም። እግዚአብሔር
ከቃል ኪዳኑ “ይጠቀማል” ልንል ብንችልም፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው ከሰው ልጆች
እሳቤ አጅግ በየተለየ መልኩ ነው። ለወደዳቸው እና የዘላለም ሕይወት ባለቤት
ላደረጋቸው--ለዚህ ጌታ፤ ይህ ቀላል እርካታ የሚሰጠው አይሆንም (ኢሳ. 53፡
11)። ሆኖም እኛ በሌላው ጫፍ ካለነው ጋር በተመሳሳይ መንገድ የኪዳኑ ተጠቃሚ
ይሆናል ለማለት ግን አይደለም።
ለምሳሌ፡ አንድ ሰው በመርከብ እየተጓዘ እያለ ማዕበሉ ክፉኛ በሚያጓራበት ባሕር
ውስጥ ተንሸራትቶ ይወድቃል። በመርከቧ ላይ ያለ አንድ ሰው ህይወቱን ሊያተርፍለት
የሚችል ጀልባ ቁልቁል እንደሚወረውርለት ይነግረዋል። ሆኖም ውላቸው ይሰምር
ዘንድ በሌላኛው ጫፍ ያለው፣ ይህ የባህሩ ወጀብ ክፉኛ እያላታመው የሚገኝ
ሰው የሚላክለትን ሕይወት አድን ቁስ አፈፍ አድርጎ ለመያዝ “የተስማማ” መሆኑን
መግለጽ ይኖርበታል። ይህ--በእግዚአብሔር እና በሰው ልጆች መካከል ያለው ቃል
ኪዳን ምን ማለት እንደሆነ በብዙ መንገዶች የሚያሳይ ይሆናል።
ምሳሌው በቃል ኪዳኑ ውስጥ ያለውን የጸጋ ጽንሰ ሀሳብ ማስተዋል
እንዲችሉ ምን ያህል ረድቶታል? ዛሬም ቢሆን--ከእግዚአብሔር ጋር
ያሎት ግንኙነት በምን ላይ መመስረት እንዳለበት አስመልክቶ ይህ
እንዴት ሊረዳዎ ይችላል?
“እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ በእኔና በእናንተ መካከል፣ ከእናንተም ጋር ሁሉ
ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋር፣ የማደርገው የኪዳኑ
ምልክት ይህ ነው፤ ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር
መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል።” (ዘፍ. 9፡12-13)።
ከቀስተ ደመናው ይልቅ ጥቂት ተፈጥሮአዊ ክስተቶች የላቀ ውበት አላቸው።
ወደ ሰማይ ደጃፍ እየጠቀሱ፣ ምስጢራዊ በሆነ መንገድ ከአምላክ ጋር ግንኙነት
መፍጠሪያ ሰማያዊ ደጃፍ በመሰሉት፣ በእነዚያ የደጋን ቅርጽ የተላበሱ ከአጥናፍ እስከ
አጥናፍ የተዘረጉ አስገራሚ የብርሃን ጸዳሎች በልጅነቱ ያልተደመመ፣ ክስተቶቹንስ
የማያስታውስ ማን ነው? በጎልማሳነታችንም እንኳ ቢሆን፣ እነዚያ በደመናዎች
ውስጥ ፈንጥቀው የፈኩ አስደማሚ ሕብረ ቀለማት ትንፋሾቻችንን ሰቅዘው
ያላስደመሙን እንኖር ይሆን? ከዚህ አኳያ ቀስተ ደመና ዛሬም ቢሆን--ከፖለቲካ
እስከ አምልኮ ድርጅቶች፣ ከሙዚቃ ባንድ እስከ የጉዞ ወኪሎች--አያሌ ተቋማትን
ሲወክል መመልከት እምብዛም ላያስገርም ይችላል። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው
እነዚያ ውብ የቀለም ሕብሮች ዛሬም ቀልባችንን ይገዛሉ። እግዚአብሔር ሊያመለክት
የፈለገው ነገር ቢኖር ይኸው ነው።
ጌታ ቀስተ ደመና ምልክት እንደሚሆን የተናገረው ለምንድን ነው?
ዘፍ. 9፡12-17።
ጌታ ቀስተ ደመናን እርሱ ከሰዎች ጋር ለገባው “ኪዳን” ምልክት አድርጎ
እንደሚጠቀምበት ተናግሯል (ዘፍ፣ 9፡15)። ምንም እንኳ ይህ ኪዳን ጥቅም ላይ
የዋለበት መንገድ ከሌሎቹ ለየት ቢልም፤ እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ቃሉን ሲጠቀም
መመልከት ደስ ያሰኛል። እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ወይም በሲና ተራራ ላይ
ከገባው ኪዳን በተቃራኒ--በቃል ኪዳኑ ተጠቃሚ በሆኑት በኩል (በኖኅም ቢሆን)
ተወስኖ የተቀመጠ አስገዳጅ ሁናቴ የለም። በዚህ ስፍራ የቀረቡት አምላካዊ ቃላት
እንደሚያመለክቱት ኪዳን የገባው “ ‘ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር’ ” (ዘፍ. 9:15)
“ ‘ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋር’ ” (ዘፍ. 9፡12) ነው። ሰው ጌታን ለመታዘዝ
ቢመርጥ ወይም ባይመርጥ፣ የእግዚአብሔር ቃላት ሁሉን ገዥ የሆኑ ዩኒቨርስ አቀፍ
ባሕሪ የተላበሱ ናቸው። በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ስለሚኖረው ግንኙነት
ሲወሳ፤ ይህ ኪዳን በሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከሚቀርበው የቃል ኪዳን
ጽንሰ ሀሳብ አኳያ ጥቅም ላይ አልወዋለም።
ይህ ቃል ኪዳን የእግዚአብሔርን ጸጋ በምን መልኩ ይገልጻል? የቃል
ኪዳኑ ጠንሳሽ ማን ነው? ወሳኝ የሆነው ደጋፊና ረዳትስ? ምንም እንኳ
በዚህ ስፍራ እንደተገለጸው ኪዳኑ በእኛ በኩል የተወሰኑ ግንዴታዎችን
ይዞ ባይመጣም፤ (በእግዚአብሔር በኩል ዓለምን ፈጽሞ በጎርፍ ላያጠፋ
መሆኑ እሙን ቢሆንም) ስለ ቀስተ ደመናው ተምሳሌት ያለን ዕውቀት
ጌታን በመታዘዝ እንድንኖር እንዴት ተጽእኖ ያሳድርናል? በአጭሩ
ወደ ሰማይ አሻቅበን ቀስተ ደመናን ስናይ በተዘዋዋሪ በእኛ በኩል
የተቀመጡ ግዴታዎች ይኖሩ ይሆን? ቀስተ ደመናው የመጣበትን
አጠቃላይ ሁኔታ እና ከዚያ ዘገባ የምንወስደውን ትምህርት አስቡ።
“ሕይወት ያላቸው ፍጡራን ሁሉ ከምድር ገጽ ጠፉ፤ ሰዎችና እንስሳት በምድር ላይ
የሚሳቡ ፍጡራንና የሰማይ ወፎች ከምድር ላይ ጠፉ፤ ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቧ
ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ።” (ዘፍ. 7፡23)።
አንድ ሰው “ተረፉ” የተሰኘውን ቃል ጽንሰ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ስፍራ እንደ
ተጠቀሰ ሊያስተውል ይችላል።
“ ‘እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ በታላቅ መድኃኒትም
አድናቸሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ’ ” (ዘፍ. 45፡7 /1954 ትርጉም)
“በጽዮን የተቀሩት፣ በኢየሩሳሌምም የተረፉት፣ በኢየሩሳሌም በሕይወት
ከተመዘገቡት ሁሉ ጋር ቅዱሳት ተብለው ይጠራሉ” (ኢሳ. 4፡3)።
“በዚያን ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ… ይሰበስባል”
(ኢሳ. 11፡11)። እነዚህ ቃላት በዘፍ. 7፡23 ከቀረበው ቃል ጋር የተሳሰሩ ናቸው።
ዘፍ. 7፡23 እና ሌሎች ምሳሌዎችን ይመልከቱ። በዚህ ስፍራ የቀረበውን የትሩፋን
ወይም ቅሬታ ጽንሰ ሀሳብ እንዴት ያስተውሉታል? ወደ ትሩፋንነት የመሩ
አካባቢያዊ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው? ቃል ኪዳኑ ከትሩፋን ጽንሰ ሀሳብ ጋር
እንዴት ይጣጣማል?
በውሃ ጥፋት ወቅት የምድር ፈጣሪ የዓለም ፈራጅ ሆነ። በመላዋ ምድር ላይ ሊሰጥ
የተቃረበው ፍርድ ሰውን ጨምሮ ማንኛውንም ሕይወት ያለውን ፍጥረት የሚያጠፋ
ይሆን? ካልሆነ የሚተርፉት እነማን ይሆናሉ? ትሩፋኖቹ እነማን ናቸው? የሚሉ
ጥያቄዎችን አስነስቶ ነበር።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ትሩፋኑ ኖኅ እና ቤተሰቡ ነበሩ። ሆኖም የኖኅ መዳን እግዚአብሔር
ከገባው ቃል ኪዳን ጋር የተሳሰረ ነበር (ዘፍ. 6፡18)--በምኅረት እና በጸጋ በተሞላው
አምላክ በተጠነሰሰውና ፍጻሜ ባገኘው ቃል ኪዳን። ምንም እንኳ የእነርሱ ትብብር
አስፈላጊ የነበረ ቢሆንም፤ የተረፉት እግዚአብሔር ባደረገላቸው ነገር ብቻ ነው።
የኖኅ ቃል ኪዳን ግዴታዎች የቱንም ዓይነት ቢሆኑ እና በየትኛውም የታማኝነት
መስፈርት ቢፈጽማቸውም--ብቸኛ ተስፋው የእግዚአብሔር ምኅረት ነበር።
በመጨረሻዎቹ ጊዜያቶች ገቢራዊ በሚሆኑ ክስተቶች ላይ ባለን መረዳት
መሰረት እግዚአብሔር ትሩፋን ሕዝቦች ይኖሩታል (ራእ. 12፡17)።
ታዲያ እኛም የትሩፋኑ አካል ሆነን መዘጋጀት እንድንችል የሚረዱን
ምን ዓይነት ተመሳሳይ ነጥቦች ከኖኅ ታሪክ መገብየት እንችላለን?
የኃይማኖት አባቶች እና ነቢያት መጽሐፍ አማርኛ ትርጉም፡
“የጥፋት ውሃ” ገጽ 92-108 “ከጥፋት ውሃ በኋላ” ገጽ 109-116
“ግዙፍ ተፈጥሮአዊ ክስተት የሆነው ቀስተ ደመና እግዚአብሔር ምድርን ዳግመኛ
በጎርፍ እንደማያጠፋት ለተሰጠው ቃል ተስማሚ ምልክት ነበር። ከውሃ ጥፋት
በኋላ የምድር አየር ንብረት ሁኔታ ፍጹም የተለየ ስለሚሆን ዝናብ ቀደም ሲል አፈሩን
የሚያረጥበውን ጤዛ ተክቶ አብዛኛውን የዓለም ክፍል የሚሸፍን ሆነ።
በየጊዜው
ዝናብ መዝነብ በጀመረ ቁጥር የሚስተዋለውን የሰዎች ፍርሃት የሚያስወግድ አንድ
ነገር አስፈልጎ ነበር። መንፈሳዊ አእምሮ እግዚአብሔር ራሱን ተፈጥሮአዊ በሆነ
ያልተለመደ ዓይነት ክስተት የገለጠበትን መንገድ መመልከት ይችላል (ሮሜ 1፡20)።
ስለዚህ ዝናብ በረከት እንጂ ዩኒቨርስ አቀፍ ጥፋት እንደማይመጣ ቀስተ ደመና
ለአማኙ ማስረጃ ነው።”—The SDA Bible Commentary, vol. 1, p. 265.
1.በእነዚያ ቀናት ዓለም በሕያው ፍጡራን ተሞላች፣ ሰዎች ተባዙ፣ ምድር
እንደ ዱር ኮርማ አጓራች፣ ከፍ ብሎ የሚተጋባ የብዙዎች የልፍለፋ ድምፅ
ታላቁን አምላክ ቀሰቀሰው። ኢንሊል የተሰኘው ይህ አምላክ ከልክ በላይ
የሚሰማውን የጩኸት ድምፅ አስመልክቶ በጉባዔ ለተቀመጡት አማልክት
እንዲህ አላቸው ‘በባቤል የተነሣ እንቅልፍ መተኛት የማይታሰብ ሆኗል።
የሰዎችን ሁካታ ከዚህ በላይ መቋቋም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።’
ስለዚህ አማልክቱ ሰውን ለማጥፋት ተስማሙ።”—“The Story of the
Flood” in The Epic of Gilgamesh, trans. N. K. Sanders
(London: The Penguin Group, 1972), p. 108. ይህን የውሃ ጥፋት
ምክንያት በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠቀሰው ምክንያት ጋር ያነጻጽሩ።
2.ኖኅ በእርሱ ትውልድ ላይ ሊመጣ ያለውን የእግዚአብሔር ፍርድ
ለሕዝቡ ከማስጠንቀቅ በላይ ሠርቷል። የማስጠንቀቂያው ዓላማ ሰዎች
ወደ ህሊናቸው ተመልሰው መዳን እንደሚያስፈልጋቸው እንዲገነዘቡ ነበር።
በአጠቃላይ የመዳን እውነቶች ተቀባይነት ያጡት ለምን ነበር? ብዙዎች
የሚድኑበትን አምላካዊ ዕቅድ እንዳይቀበሉ እንቅፋት የሚሆኑባቸውን
አንዳንድ ነገሮች በመዘርዘር ተወያዩባቸው። ዮሐ. 3፡19፣ 7፡47-48፣
12፡42-43፣ ያዕ. 4፡4።
ማጠቃለያ፡ እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር የገባቸው ቃል ኪዳኖች በመጽሐፍ
ቅዱስ ግልጽ መወያያ ሆነው ሲቀርቡ የመጀመሪያዎቹ መሆናቸውን በዚህ
ሣምንት ጥናታችን አስተውለናል። ለሰብዓዊው ቤተሰብ ያለውን ደግነት እና
እነርሱን የማዳን የግንኙነት ውል ውስጥ የመግባት ምኞቱን ያመለክታሉ።
እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ዳግም አጽንቷል። እናም በዘመኑ
ከተንሰራፋው ክህደት ጋሻ ሆኖ የጠበቀው፣ በስተመጨረሻ እርሱንና ቤተሰቡን
ከአውዳሚው የጥፋት ውሃ ያዳነው ለእግዚአብሔር የነበረው ቁርጠኝነት
ነው።
“በደመናዎች ውስጥ ያለው ይህ ምልክት (ቀስተ ደመናው) ለሰዎች የተገለጠ
መለኮታዊ ምኅረት እና መልካምነት እንደ መሆኑ፣ የሁሉንም እምነት
የሚያጸና እና እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ እንዲጥሉ የሚያደርግ ነው።
ምንም እንኳ እግዚአብሔር በጥፋት ውሃ ምድርን ለማጥፋት ቢገፋፋም፤
አሁንም ምሕረቱ ምድርን እንደከበበ ነው።”—Ellen G. White, The Story
of Redemption, p. 71.