የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ኢሳ. 13፣ ኢሳ. 13:2–22፣ ኢሳ. 14፣ ኢሳ. 24–27።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡- “ ‘እነሆ አምላካችን ይህ ነው፤ በእርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በእርሱ ታመንን፤ በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ’ ” (ኢሳ. 25፡9)።
አ
ገልጋዩ በመታበይና ኩራት ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ለምዕመኑ ስብከት አቀረበ።
መልእክቱን በጥሞና ከሰሙት መካከል አንዲት ሴት ከፕሮግራሙ ፍጻሜ
በኋላ ወደ እርሱ በማምራት በከፍተኛ የአእምሮ ሰላም ማጣት ውስጥ እንደምትገኝ
ነገረችው። ታላቅ ያለችውን ኃጢአት መናዘዝ እንደምትፈልግም ገለጸችለት። አገልጋዩ
ኃጢአቱ ምን እንደሆነ ጠየቃት።
“እርሷም ስትመልስ፤ ‘ከጥቂት ቀናት በፊት ለአንድ ሰዓት ያህል ውበቴን እያደነቅኩ
መስታወት ፊት ቁጭ ብዬ ነበር።’
“ ‘ኦ፤ ያ የኩራት ኃጢአት ሳይሆን--ልቦለድ ኃጢአት ነው!’”—C. E. Macartney,
compiled by Paul Lee Tan, p. 1100.
ኃጢአት ኃያል በነበረው መልአክ ልብ ውስጥ ከተወለደ አንስቶ ኩራት የተጨባጩን
እውነት ወሰን አላከበረም (በመላእክትም ሆነ በሰዎች)። ይህ ችግር የመንፈሳዊ
ኩራት ማደሪያ የሆኑ ሰዎችን ያህል በየትኛውም ስፍራ ከፍቶ አልታየም።
ከሌሎች ነጥቦች በተጓዳኝ፤ በዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ስለ ሁለቱ
የቀደሙ ኃጢአቶች ማለትም ስለ ኩራትና ራስን ከፍ የማድረግ አባዜ አጀማመርና
አመጣጥ እንመረምራለን።
ኢሳ. 13፡1--ኢሳይያስን የመልእክቱ ደራሲ አድርጎ በሚያስቀምጥ ርዕስ ይጀምራል (ኢሳ. 1፡1፣ 2፡1)። እንዲሁም ነቢዩ መጽሐፉን በአዲስ ክፍል የሚጀምር ይመስላል። ከምዕ. 13-21--ያሉት ደግሞ በተለያዩ ሕዝቦች ላይ የቀረቡ የፍርድ ትንቢቶችን ይዘዋል። እስቲ እንመልከታቸው፡ እነዚህ በሕዝቦች ለምንድነው? ላይ የተነገሩ ትንቢቶች በባቢሎን የሚጀምሩት
እግዚአብሔር በኢሳይያስ ዘመን ታላቅ አደጋ ሆኖ በተደቀነው አሦር ላይ አስቀድሞ
የሰጠው ፍርድ በኢሳ. 10፡5-34 ቀርቦአል። ኢሳ. ምዕ. 13-23--ጌታ አሦርን ለማፍረስ
የነበረውን ዕቅድ በተደጋጋሚ በአጭሩ ሲያቀርብ፤ ከምዕ. 13-23 ደግሞ በአብዛኛው ስለ
ሌላው አስጊ ቁልፍ አገር ባቢሎን ይናገራል።
ከጥንት ጀምሮ አብሯት በኖረ የበለጸገ ባህላዊ፣ ኃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ቅርስ ባለቤትነት
የምትታወቀው ባቢሎን፤ ኋላ ላይ ይሁዳን ድል አድርጋ በግዞት ያኖረች ልዕለ ኃያል
ሆና ብቅ አለች። ነገር ግን ከኢሳይያስ ዘመን ሰብዓዊ አመለካከት አኳያ፤ ባቢሎንን
በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ አስጊ ኃይል አድርጎ ማሰብ አዳጋች ነበር። በአብዛኛው
የኢሳይያስ አገልግሎት ዘመን አሦር በባቢሎን ላይ የበላይነት ነበራት።
ከክርስቶስ ልደት
በፊት 728 አንስቶ ቴልጌልቴልፌልሶር 3ኛ ባቢሎንን በቁጥጥሩ ስር አውሎና ራሱን
በፑሉ (2ነገሥ. 15፡19፣ 1ዜና 5፡26) ስርወ መንግሥት እግር ተክቶ የባቢሎን ንጉሥ ብሎ
በመሰየም ዙፋኑ ላይ ከተቀመጠበት ጊዜ አንስቶ የአሦር ነገሥታት ባቢሎንን በተደጋጋሚ
በቁጥጥራቸው ስር አውለዋል (ከክ.ል.በ. 710፣ 702፣ 689 እና 648)። ሆኖም ውሎ
አድሮ ባቢሎን የይሁዳን አገረ መንግሥት የምታጠፋና የቀጠናው ልዕለ ኃያል ትሆናለች።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ኢሳ. ምዕ. 12። ቋንቋው ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ ልብ
ይበሉ። አፍቃሪ የሆነው አምላክ እንደነዚህ ዓይነቶቹን ነገሮች ለምን አደረገ?
ወይም ለምን እንዲሆኑ ፈቀደ? በዚህ መሀል አንዳንድ ንጹሃን የሥቃይ ጦስ
ሰለባ መሆናቸው እሙን አልነበር? (ኢሳ. 13፡6)።
እንዲህ ያለውን አምላካዊ
እርምጃ እንዴት እናስተውለዋለን? እግዚአብሔርን በኃጢአት እና በክፉው
ላይ ስለሚነድ ቁጣው የሚገልጹት እነዚህ ጥቅሶችም ሆኑ ሌሎች--ስለ ኃጢአት
እና ክፉው ልዩ ተፈጥሮ ምን ሊነግሩን ይገባል? በፍቅር የተሞላው አምላክ
ብቸኛ የነበረውን ይህን መንገድ ብቻ ተጠቅሞ ምላሽ የሰጠበት እውነታ፤
ኃጢአት ምን ያህል የከፋ ነገር እንደሆነ ለእኛ ለማሳየት በቂ ማስረጃ መሆን
አይችልም? እነዚህን ማስጠንቀቂያዎች በኢሳያስ በኩል የተናገረው--ይቅር
ያለ፣ የፈወሰ፣ ለኃጢአተኞች ጥሪ ያቀረበና ንስሐ እንዲገቡ የተማጸነ ያው
የሱስ መሆኑን ማስታወስ ይኖርብናል።
አፍቃሪ የሆነውን የእግዚአብሔር
ባሕርይ ገጽታ በግልዎ እንዴት ተረዱት? ይህንን ጥያቄ ራስዎን ይጠይቁ-ይህ ቁጣ በእውነት ከፍቅሩ የመነጨ ሊሆን አይችልም? ከሆነ፣ እንዴት?
ወይም ከሌላ አቅጣጫ፤ ይኸውም ራሱ የሱስ የዓለምን ኃጢአት ከመሸከሙ፣
በአገሪቱ ኃጢአት ምክንያት እነዚያ “ንጹሃን” ከደረሰባቸው መከራ የበለጠ፣
እንደውም በምድር ከኖረ ማንኛውም ሰው የላቀ ሥቃይ ከተቀበለበት ከመስቀሉ
አኳያ ይመልከቱት። ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተቀበለው መከራ እነዚህን
አስቸጋሪ ጥያቄዎች ለመመለስ እንዴት ይረዳል?
ከክርስቶስ ልደት በፊት 626 ካልዲያን ናቦፖላዛር ራሱን የባቢሎን ንጉሥ አድርጎ በመሰየም አዲሱን የባቢሎናውያንን ሥርወ መንግሥት በመጀመርና በአሦር ሽንፈት ላይ ተሳትፎ በማድረግ (ከምድያ ጋር) የባቢሎንን ክብር ወደ ቀድሞው መለሰ። ይሁዳን ድል አድርጎ በግዞት ያኖረው ንጉሥ የእርሱ ልጅ ናቡከደነጾር 2ኛ ነበር። በመጨረሻ የባቢሎን ከተማ እንዴት አበቃላት? ዳን. 5
ፋርሳዊው ቂሮስ ከክርስቶስ ልደት በፊት 539 ላይ ባቢሎንን የሜዶንና ፋርስ ግዛት
አድርጎ ሲማርክ (ዳን. 5) ከተማዋ ነፃነቷን ለዘላለም አጣች። በ482 ንጉሥ ጠረክሲስ
1ኛ በፋርስ አገዛዝ ላይ የተነሳውን የባቢሎን አመጽ ጨካኝ ኃይል ተጠቅሞ ጸጥ
አደረገ። ዋና አማልክታቸው የሆነውን የሜሮዳክ ሀውልት ከመገርሰሱ በተጨማሪ
አንዳንድ ምሽጎችንና ቤተ አምልኮዎችን አውድሞአል።
ታላቁ እስክንድር ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያደርግ ባቢሎንን በ 331 ከፋርሳውያን
እጅ ወሰደ። ባቢሎንን ምሥራቃዊ ርዕሰ መዲና የማድረግ በአጭር የተቀጨ
ህልም የነበረው ቢሆንም፤ ከተማዋ ለቀጣይ ምዕተ ዓመታት ቁልቁል ከመውረድ
ባለፈ አላንሰራራችም። ሮማዊው ሴፕቲመስ ሴቨረስ ከክርስቶስ ልደት በፊት 198
ላይ ባቢሎንን ሲያገኛት ሙሉ ለሙሉ ባድማ ሆና ነበር። ስለዚህ ታላቂቱ ከተማ
ባድማ ወይም ሰው የማይኖርባት መሆኗን ተከትሎ አከተመላት። ዛሬ ኢራቃውያን
በዚህ ጥንታዊው ግዛት አንዳንድ መንደሮች ቢኖሩም፤ ከተማዋን እንደሚገባው
አልገነቧትም።
በኢሳ. 13 ላይ የተገለጸው የባቢሎን ጥፋት በባቢሎን የተጨቆኑ የያዕቆብን
ትውልዶች ነፃ ያወጣል (ኢሳ. 14፡1-3)። በ539 የባቢሎን በቂሮስ እጅ መውደቅ፤
ለዚህ ክንውን መንስኤ የሆነው ክስተት እንዲመጣ ያደረገ ነበር። ምንም እንኳን
ከተማዋን ባያጠፋትም ይህ የባቢሎን የመጨረሻ መጀመሪያ ነበር። በመሆኑም ከዚህ
በኋላ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ስጋት ሆና አታውቅም።
ኢሳ. 13 የባቢሎንን ውድቀት የመለኮታዊ ፍርድ ገጽታ ሰጥቶ ያቀርባል። ከተማዋን
በቁጥጥራቸው ስር ያዋሉ ተዋጊዎች የእግዚአብሔር ወኪሎች ሆነው ቀርበዋል (ኢሳ.
13፡2-5):: የፍርድ ጊዜ “የእግዚአብሔር ቀን” (ኢሳ. 13፡6፣9) ተብሎ ተጠርቷል።
አምላካዊው ቁጣ እጅግ ብርቱ ከመሆኑ የተነሳ ከዋክብትን፣ ፀሐይን፣ ጨረቃን፣
ሰማያትንና ምድርን ያቃውሳል (ኢሳ. 13፡10፣ 13)።
በመሳፍ. ምዕ. 5 የጌታን ግስጋሴ ከምድር መናወጥ፣ ከሰማይ ዝናብ ማዝነብና
ከደመናዎች ውሃ ማፍሰስ ጋር የተገለጸበትን የዲቦራ እና የባራክ መዝሙር ያስተያዩ
(መሳ. 5፡4)። ከዋክብትን ጨምሮ የተፈጥሮ አካላት የባዕድ አገር ጨቋኞችን
እንደሚዋጉ መሳ. 5፡20-21 ያመለክታል።
በባቢሎን ክብር ከፍታ የሚኖር እነዚህን በኢሳ. 13 በተለይ ደግሞ
ኢሳ. 13፡19-22 የቀረበውን መልእክት ሊያነብ እንደሚችል መገመት
ይቻላል። እንዴት ተሞኝተው የማይሆን አድርገው አሰቡ! ገና ፍጻሜ
ያላገኘ ማንኛውም ትንቢት ለእኛ ዛሬ የማይሆን ነገር ነው? እነርሱ
ለምን እንደማይሆን አድርገው አሰቡ እንላለን--እኛስ?
የእግዚአብሔር ሕዝብ ነፃ የወጣበትን (ኢሳ. 14፡1-3) የባቢሎን ውድቀት (ኢሳ. 13) ተከትሎ፤ ኢሳ. 14፡4-23 በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዘይቤያዊ የዘለፋ ቃል ይሰነዝራል (በተጨማሪ፡ ሚክ. 2፡4፣ ዕንባ. 2፡6)። የሞቱ ነገሥታት ወደ እነርሱ ግዛት ለመጡ አዳዲሶቹ ባልደረቦቻቸው ሰላምታ የሚያቀርቡበት ይህ ብሎች ከታች የተነጠፉበትና ትሎች የተደረቡበት (ኢሳ. 14፡11) አባባል ቃል በቃል የሚወሰድ ሳይሆን ቅኔያዊ ነው። እንደ ሌሎች ነገሥታት ሁሉ የታበየው ንጉሥ በፊቱ እንደሚዋረድ ጌታ የገለጸበት መንገድ እንጂ የሞቱ ሰዎች ስለ ሚገኙበት ሁኔታ የተሰጠ ሀተታ አይደለም። በኢሳ. 14፡12-14 የቀረበው መልእክት እንዴት ለባቢሎን ንጉሥ ገጣሚ ይሆናል?
የባቢሎን ነገሥታት ለራሳቸው ከፍ ያለ ግምት በመስጠታቸው ችግር አልደረሰባቸውም
(ዳን. 4፣5)። ነገር ግን “እንደ ልዑል” (ኢሳ. 14፡14) ለመሆን መመኘት በጣም ከተወጠረ
ራስ ወዳድነትም ይልቃል። ነገሥታቱ ከአማልክቱ ጋር ጥብቅ ትስስር እንዳላቸው
ቢነገርም፤ ከተለማማጭነት የዘለሉ አልነበሩም። በባቢሎናውያን አዲስ ዓመት፣
አምስተኛው ቀን ላይ በየዓመቱ በሚውል ክብረ በዓል፤ ንጉሡ ንግሥናው ዳግም
ይጸናለት ዘንድ ወደ ሜሮዳክ ጣኦት (ሀውልት) ከመቅረቡ አስቀድሞ ንጉሣዊ አርማውን
እንዲያወልቅ ይጠየቅ ነበር። ደካማ የተባለውን እንኳ አማልክት ለማስወገድ መሞከር
እንደ እብደት ወይም ራስን እንደ ማጥፋት ይቆጠር ነበር።
በኢሳ. 14 ከቀረበው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሰማይን የመዳፈር ትዕቢት በከተማዋ ገዢ
መፈጸሙን ሕዝ. 28 ያስነብበናል። በዚህ ስፍራ የቀረበው መግለጫም እንዲሁ
ከምድራዊ ንጉሥ ባሻገር አልፎ የሚሄድና የእግዚአብሔርን ብርቱ ትኩረት የሚያሳይ
ነው፡ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ ክፋት እስከ ተገኘበት ድረስ ነቀፌታ ያልነበረበት፣
በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ጠባቂ ኪሩብ ሆኖ ተቀብቶ የኖረውና በዔደን የአትክልት
ቦታ የነበረው በትዕቢት የተሞላ ገዥ ወደ ምድር መጣሉንና በመጨረሻም በእሳት
ተቃጥሎ ዐመድ እንደሚሆን ይገልጻል (ሕዝ. 28፡12-18)። እንዲህ ያለውን ዘይቤያዊ
የአነጋገር ስልት ለየትኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ማዋል ትርጉም አይሰጥም። ነገር ግን ራእ.
12፡7-9 “ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው፣ ዓለምን ሁሉ የሚያስተው” ከሰማይ የተጣለው
መልአክ መሆኑን ይነግረናል (ራእ. 12፡9)። ሰይጣን በዔደን ሔዋንን ያሳተ ነው (አፍ.
3)።
በትዕቢት የተወጠረው ሰይጣን ምናባዊ ዓለም ውስጥ ነበረ፡ “እኔ አምላክ ነኝ፤ በአምላክ
ዙፋን ላይ በባሕሮችም ልብ ተቀምጫለሁ አልህ… አንተ ሰው (ሟች) እንጂ አምላክ
አይደለህም” (ሕዝ. 28፡2)። ሟች መሆኑ አምላክ አለመሆኑን ያረጋግጣል። ሰይጣን ወደ
እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጥሎ ይወገዳል (ራእ. 20፡10) ዳግመኛ ዩኒቨርስን አይጎዳም።
ጥቅሶቹን ያነጻጽሩ፡ ኢሳ. 14፡13-14፣ ማቴ. 11፡29፣ ዮሐ. 13፡5፣
ፊልጵ. 2፡5-8። ንጽጽሩ ከሰይጣን በተቃራኒ ስለሚገኘው የእግዚአብሔር
ባሕሪ ምን ይነግረናል? ጌታ--ትዕቢትን፣ እብሪትን እና ራስን የማመጻደቅ
አባዜን እንዴት እንደሚመለከት ንጽጽሩ ምን ይነግረናል?
በኢሳ. ምዕ. 14 “አንተ የንጋት ልጅ (ሉሲፈር)፣ አጥቢያ ኮከብ” (ኢሳ. 14፡12) በሚል
በሰይጣን ላይ የቀረበው መሳለቂያ፤ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ከተፌዘው ጋር ኅብር
ፈጥሮአል። ለምን? ህጻኑ ገና እንደተወለደ ሊያስወግደው የሞከረው ዘንዶ ሰይጣን
መሆኑ ከተገለጸበት (ራእ. 12፡9) ጥቅስ ጋር ያስተያዩ (ራእ. 12፡1-9)። በራእ. 12፡5
በግልጽ የተመለከተው ህጻን ክርስቶስ ነው። ነገር ግን የሱስን ገና በህጻንነቱ ሊገድለው
የሞከረው ንጉሥ ሄሮድስ ነበር (ማቴ. 2)። ሰይጣን የሚሠራው በሰብዓዊ ወኪሎች
አማካይነት እንደ መሆኑ፤ ዘንዶው ሰይጣን እና በሄሮድስ የተወከለው የሮም ኃይል ነው።
በተመሳሳይ ከባቢሎን ንጉሥ እና ከጢሮስ ልዑል ጀርባ ይሠራ የነበረው ኃይል ሰይጣን
ነበር።
ኋላ ላይ “ባቢሎን” ሮምን (1ጴጥ. 5፡13) እና የክፉ ኃይልን ለማመልከት
በራእይ መጽሐፍ ለምን ተጠቀሰ (ራእ. 14:8፣ 16:19፣ ራእ. 17:5፣ ራእ.
18:2፣ 10፣ 21)?
ቃል በቃል እንደቀረበው ባቢሎን ሁሉ፤ ሮም እና በራእይ መጽሐፍ የቀረበው “ባቢሎን”
የእግዚአብሔርን ሕዝቦች የሚጨቁኑ የታበዩና ምህረት የለሽ ጨካኝ ኃይላት ናቸው።
ለዚህ እንደ ማስረጃ ራእ. 17፡6 ብንመለከት፡ “በቅዱሳን ደም ሰክራ” ነበር ይለናል።
በእግዚአብሔር ላይ አመጹ የሚለው ጽንሰ ሀሳብ የሚያመለክተው ራሷን “ባቢሎንን”
ነው። በባቢሎናውያን ቋንቋ ባብ ኢሊ ወይም “የአምላክ ደጃፍ”--ወደ መለኮታዊው
ግዛት መድረሻ ቦታን ያመለክታል። ከአምላካዊው ተጠያቂነት ነጻ ወደሚያደርጋቸው
መለኮታዊ ከፍታ በራሳቸው ኃይል መውጣት ይችሉ ዘንድ፤ ሰዎች የባቤልን (ባቢሎን)
ግንብ መገንባታቸውን ከሚያሳየው ዘፍ. ምዕ. 11 ጋር ያሰተያዩ።
ያዕቆብ ሰማይንና ምድርን ያገናኘውን መሰላል በሕልሙ አይቶ ከእንቅልፉ ሲነቃ፡ “ይህስ
ሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ የሰማይ ደጅ ነው” (ዘፍ. 28፡17) ብሎ
ነበር። እዚህ ላይ “የእግዚአብሔር ቤት” ወደ መለኮታዊው ግዛት መድረሻ የሆነው
“የሰማይ ደጅ” መሆኑን ልብ ይሏል። ያዕቆብ ቦታውን “ቤቴል” ማለትም “የአምላክ ቤት”
ብሎ ሰየመው።
የቤቴሉ “የሰማይ ደጅ” እና የባቢሎኑ “የአምላክ ደጃፍ” ተቃራኒ መንገዶች ነበሩ።
ሰማያዊ ጥንስስ የሆነው የያዕቆብ መሰላል የተገለጸው ከላይ ከእግዚአብሔር ነበር። ነገር
ግን የባቢሎን ልቀው የሚታዩ ግንቦቿና የፒራሚድ ቅርጽ የነበራቸው ቤተ አምልኮዎቿ
ከምድር ሽቅብ የተገነቡት በሰብዓዊ ፍጡሮች ነበር። እነዚህ ተቃራኒ መንገዶች ሁለቱን
የማይስማሙ የደኅንነት መንገዶች ይወክላሉ--መለኮታዊው ውጥን ጸጋ እና ሰብዓዊው
ሥራ። ሁሉም እውነተኛ ኃይማኖት የተመሠረተው ትሁት በሆነው የቤቴል ተምሳሌት
ነው፡ “በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና” (ኤፌ. 2፡8-9)።
ሕግ ጠብቆ ለመዳን የሚደረግ
እሳቤን ጨምሮ ሁሉም ዓይነት ሐሰተኛ “ኃይማኖት” እና “ዓለማዊነት” በታበየው
ባቢሎን ምሳሌ ላይ የተመሰረተ ነው። ሁለቱን አመለካከቶች ለማነጻጸር ይረዳ ዘንድ
የሱስ ስለ ፈሪሳዊው እና ቀረጥ ሰብሳቢው በምሳሌ የተናገረውን ይመልከቱ (ሉቃ. 18፡
9-14)።
ታዋቂው ካናዳዊ ድምጻዊና የሙዚቃ ግጥም ጸሐፊ ሊዎናርድ ኮህን፤ በጃፓን
ዜን ገዳም ጥቂት ዓመታት ካሳለፈ በኋላ “እኔ የዳንኩ ሰው አይደለሁም”
ሲል በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ተናግሮአል። ከዛሬው ጥናት አኳያ የዚህ ሰው
ችግር ምን ይመስሎታል? ስለ ድነት ምን ማወቅ አስፈልጎት ነበር?
በተናጥል ስለ አገራት የተነገሩ ትንቢቶችን ተከትሎ--ኢሳ. ምዕ. 13-23 እንዲሁም 24-27
የእግዚአብሔር ሕዝብ ጠላቶች በዓለማቀፍ ደረጃ ስለ ደረሰባቸው አስደናቂ ሽንፈት እና
ሕዝቡ ስላገኘው ነጻነትና ደኅንነት ይገልጻሉ።
ኢሳይያስ ስለ ምድር ባድማ መሆን የሰጠው መግለጫ (ኢሳ. 24)፤ ዮሐንስ
የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ተከትሎ ገቢራዊ ስለሚሆኑት የአንድ ሺ ዓመት
ክስተቶች ከሰጠው መግለጫ ጋር ተመሳሳይ የሆነው ለምንድን ነው--(ራእ. 20)?
በኢሳ. ምዕ. 13-14 እንደተጠቀሰው፤ የነባራዊው ባቢሎን ገጽታዎች ለኋለኞቹ ኃይላት
በመዋል፤ “የባቢሎን ንጉሥ” ከበስተ ጀርባ ሆኖ በሚዘውረው በራሱ በሰይጣን ወጣኝነት
ከሰብዓዊ ገዢዎች ጋር የሚኖረውን ውህደት ይወክላል። ስለዚህ ባቢሎን ወደቀች
በሚል የቀረበው መልእክት (ኢሳ. 21፡9) በቀጣይም ይደገምና (ራእ. 14፡8፣ ራእ. 18፡
2) ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በኋላ ሰይጣን ለመጨረሻ ጊዜ ይደመሰሳል (ራእ. 20፡
10) ። ነባራዊዋ ባቢሎን የተደመሰሰችው “በጌታ ቀን” (ኢሳ. 13፡6፣9) ፍርድ እንደ ነበር
ሁሉ ሌላዋ በሂደት ያለችው “ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን” (ኢዮ. 2፡31፣
ሚልክ. 4፡5፣ ሶፎ. 1፡7) ሲመጣ የምትጠፋ ይሆናል።
በተመሳሳይ ነቢዩ በኢሳ. 24 ትንቢቱ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና
በኢየሩሳሌም፣ በሽማግሌዎቹም ፊት በክብሩ ይነግሣል፣ ጨረቃ ትሸማቀቃለች፣
ፀሐይም ታፍራለች” ኢሳ. 24፡23) የተሰኘውን በሚያውቅበት ሁኔታ ላይ ደርሶ እንደ
ነበር እንመለከታለን። ኢሳይያስ የተመለከተውን ራእይ ገጣሚነቱን እርሱ ያውቃት
ለነበረችው የሩሳሌም አድርጎ ቢያስብም፤ ነገር ግን ጉዳዩ በትክክል ፍጻሜ የሚያገኘው
በአዲሲቱ የሩሳሌም እንደሚሆን የራእይ መጽሐፍ ያብራራል፡ “የእግዚአብሔር
ክብር ብርሃን ስለሚሰጣትና በጉም መብራቷ ስለሆነ፣ ከተማዋ ፀሐይ ወይም ጨረቃ
እንዲያበሩላት አያስፈልጋትም (ራእ. 21፡23)።
እግዚአብሔር በእርግጥ ኃጥአንን ያጠፋል?
እግዚአብሔር ኃጥአንን ማጥፋቱን እንግዳ የሆነ “ተግባር” በሚል ኢሳ. 28፡21
ይገልጸዋል። እግዚአብሔር ይህን ማድረግ የማይፈልግ አምላክ ከመሆኑ አኳያ ለእርሱ
እንግዳ ነገር ቢሆንም፤ ነገር ግን በተጨባጭ ገቢራዊ የሚሆን ጉዳይ ነው። ኃጢአት ራስን
የማጥፋት ዘሮች በውስጡ መሸከሙ እሙን ነው (ያዕ. 1፡15)። በሕይወትና ሞት ላይ
የመጨረሻ ውሳኔ ያለው እግዚአብሔር እንደመሆኑ፤ የመጨረሻውን ጥፋት--ጊዜ፣ ቦታ
እና ሁኔታ እርሱ ይወስናል (ራእ. 20)። ከዚህ ውጪ መንስዔና ውጤት--ተፈጥሮአዊ
ሂደቱን ተከትሎ እንዲሄድ በመፍቀድ በስተመጨረሻ የኃጢአት እርግማን የማይሠራ
ሆኖ እንዲያበቃለት ያደርጋል፤ የሚል የሙግት ሀሳብ ማንሳት ትርጉም የለውም።
በኢሳ. 24 እስከ 27 የምናየው ነገር በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
ተንጸባርቆ ይገኛል። ምንም እንኳ ዛሬ የቱንም ያህል ሥቃይ፣ ህመም እና ሰቆቃ
ቢኖርም፤ በስተመጨረሻ እግዚአብሔር እና አምላካዊው በጎነት በክፉ ላይ ባለ
ድል ይሆናል። እኛ እራሳችን--የዚያ የመጨረሻ ድል አካል ለመሆን የምንፈልግ
ከሆነ ማድረግ ያለብን ብቸኛው ነገር ምንድን ነው? ምሳ. 3፡5-7፣ ሮሜ 10፡9።
“ነገሩ እንዴት ነው? የሚል ጥያቄ ይነሣል። መዳን የምናገኘው
በሁኔታዎች ነው? ፈጽሞ በሁኔታዎች አይደለም--ወደ ክርስቶስ በመምጣት እንጂ።
ወደ ክርስቶስ የምንመጣ ከሆነ ታዲያ ሁኔታው ምንድ ነው? የተሰቀለውንና ከሞት
የተነሣውን የሚቤዥ አዳኝ ደም አምኖ በመቀበል ያን በቅድስና አጥብቆ መያዝ።
ያን ስናደርግ የጽድቅ ሥራ እንሠራለን። ነገር ግን እግዚአብሔር ለኃጢአተኛው ጥሪ
ሲያቀርብለትና ሲጋብዘው እንዲያሟላ የሚጠየቀው ሁናቴ የለም። ክርስቶስ ባቀረበው
ግብዣ መሰረት ይስበዋል። ኃጢአተኛው ይመጣል፤ ከዚያም ያን በቀራኒዮ መስቀል ላይ
ከፍ ያለ ክርስቶስ ሲመለከት፤ ከዚህ የሚልቅ ፍቅር የለም ሲል እግዚአብሔር አእምሮውን
ይነካዋል።”—Ellen G. White, Manuscript Releases, vol. 6, p. 32.
1.ከላይ የቀረበውን የኤለን ጂ. ኋይት መልእክት ከረቡዕ ጥናት ዐውድ ያንብቡ።
ምን እየነገረችን ነው? በጽሑፏ የቀረቡትን ሁለቱን የክርስትና ህይወት ጉዞ
አላባዎች ማለትም እምነት እና ሥራ ይመልከቱ። በሁለቱ መካከል ያለውን
ልዩነት በአቀራረቧ የምታሳይበት መንገድ ምን ይመስላል?
2.ትዕቢት እና እብሪት አደገኛ ኃጢአት የሆኑበት ምክንያቱ ምንድን ነው?
እነርሱን ማስወገድ አስቸጋሪ የሆነው ለምንድን ነው? ሰዎችን በሚያስፈልጓቸው
ነገሮች ማሳወር የሚችል ተፈጥሮ ስላላቸው ይሆን? ለነገሩ በትዕቢት የተሞላ
ሰው ደህና እንደ ሆነ አድርጎ ስለ ራሱ ያስባል። ታዲያ ደህና ነኝ ብሎ
የሚያስብ ሰው መለወጥ ለምን ያስፈልገዋል? በመስቀሉ እና መስቀሉ
በሚወክለው ላይ በማረፍ (ሰው የሚድንበት ብቸኛው መንገድ) በትዕቢት እና
እብሪት ላይ ብርቱ ፈውስ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
3.ኢሳይያስ ለሌሎች ሕዝቦች ተስፋ ስለ መኖሩ ተመልክቶ ነበር? ኢሳ. 25፡
3፣ 6፣ ኢሳ. 26፡9 ያስተያዩ፡ ራእ. 19፡9)
ማጠቃለያ፡ አሦርን ተከትሎ ባቢሎን ይሁዳን በቁጥጥሩ ስር እንደሚያውል ኢሳይያስ
ተመልክቶ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ የእግዚአብሔርን ሚና ለመጫወት በሚሞክሩ
ሰብዓዊ የእግዚአብሔር ጠላቶች አማካይነት የሚሠሩ ልዕለ ሰብዓዊ ተፈጥሮ
ያላቸው የዚህ ጨለማ ዓለም ገዦች (ኤፌ. 6፡12) ቢኖሩም፤ ጌታ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቶ
በጭንቀት ውስጥ ለምትገኘው ምድራችን ዘላለማዊ ሰላም ያስገኛል።