ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡--መዝ. 33:6–9፣ ማቴ. 19:16–22፣ 1ጴጥ. 1:18፣ ዕብ. 2:14-15፣ ዘፀ. 9:14፣ መዝ. 50:10፡፡
የሳምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ - “ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው፤ ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው፡፡ ” (ፊልጵ. 2፡9-11)
እግዚአብሔር ስለ ገንዘብና ቁሳዊው ነገር ከልክ ባለፈ ስለ ማሰላሰል ሃሳቡን ለመግለጽ ቃሉን አያባክንም፡፡ ምንም እንኳ በሉቃስ ወንጌል የተጠቀሰው ሀብታሙ ሰው በጌታ የተባረከና አብልጦ ያከማቸ ቢሆንም ነገር ግን ክርስቶስ ስለዚህ ንፉግ ሀብታም ሰው የተናገራቸው ቃላት እግዚአብሔርን መፍራት እንዳለብን ያሳዩናል፡፡ “ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊወስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው፡፡ ስለዚህ ለራሱ ሀብት የሚያከማች፣ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሀብታም ያልሆነ ሰው መጨረሻው ይኸው ነው፡፡”
ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንዲሉ እግዚአብሔርን ማገልገልና ገንዘብን ማገልገል በጋራ የሚያገናኛቸው አንዳች ነገር የለም፡፡ መንታ ህይወት ለመኖር መሞከር ውሎ አድሮ መዘዝ እንደማያጣው ሁሉ፤ እነዚህን ሁለቱን በጋራ አስኬዳለሁ ብሎ ማሰብ ከቁም ቅዠት የዘለለ አይሆንም፡፡ ምናልባት ሌሎችን ብሎም ራሳችንን ጭምር እናታልል ይሆናል፤ ነገር ግን አንድ ቀን ለዚህ ሁሉ ምላሽ ለመስጠት በፊቱ የምንቀርበውን እግዚአብሔርን ማሞኘት አንችልም፡፡ ምርጫ ልናደርግ የግድ ነው፡፡ በሁለት ልብ እያመነታን ምክንያቶችን እየደረደርን ከዛሬ ነገ እያልን ብራችንን አንቀን የምንይዝ ከሆነ፤ ፍቅረ ንዋይ በነፍሳችን ይጠቀምብናል፡፡ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እምነት ሊኖረን የግድ ነው፡፡
ትኩረታችንን አብልጠን በእግዚአብሔር ማንነት ላይ በማኖር እርሱ ለእኛ ያደረገልንንና የበጎነቱ ባለዕዳ መሆናችንን ማሰባችን ውሳኔያችንን በእጅጉ ሊያቀልልን ይችላል፡፡
የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 1:1፣ መዝ. 33:6–9፣ ኢሳ. 45:11-12፣ ኤር. 51:15፣ ዮሐ. 1:3፡፡ ጥቅሶቹ ስለ ቁሳዊው ዓለም መልካምነት ምን ይነግሩናል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“ሰማያትን የዘረጋውና የምድርንም መሰረት የጣለው ክርስቶስ ነበር፡፡ ዓለማትን በጠፈር ላይ ያንጠለጠለውና የሜዳ አበቦችንም የቀረጸ የእርሱ እጅ ነበር፡፡ ‘ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ’ ‘ባሕር የእርሱ ናት፤ እጁም አበጀ’ (መዝ. 65፡6፣ 95፡5)፡፡ ምድርን በውበት ያስጌጣትና አየሩንም በዜማ የሞላው እርሱ ነበር፡፡ በምድር፣ በአየርና በሰማይ ላይ ባሉ ነገሮች ሁሉ የአብን የፍቅር መልእክት ጻፈ፡፡” የዘመናት ምኞት ገጽ 10 (አማርኛው ትርጉም)፡፡
ቁሳዊ ነገሮች በራሳቸው ክፉ አይደሉም፡፡ አንዳንድ የኃይማኖት ተቋሞች መንፈሳዊው ነገር ብቻ መልካም እንደሆነ በማስተማር፤ ቁሳዊው አካልም ሆነ ዓለም በራሱ መጥፎ ወይም ክፉ ነው ሲሉ ቢደመጡም፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ለቁሳዊው
ዓለም ዋጋ ይሰጣል፡፡
ለነገሩ ቁሳዊውን ዓለም ማን ፈጠረው? የሱስ ራሱ አይደለምን? ታዲያ እንዴት አድርጎ ነው ክፉ የሚሆነው? በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም የእግዚአብሔር ስጦታዎች የታለመላቸውን ጤነኛ ባህሪ ለውጠው የክፉው መጠቀሚያ መሣሪያ ቢሆኑም ነገር ግን ኋለኛው ክስተት የቀደመውን ስጦታ ክፉ አያሰኘውም፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም የፈጠራቸው ነገሮች ላይ ጉዳት እንዳናደርስ ወይም ከጤነኛ ተፈጥሮአቸው እንዳናወጣቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስጠነቅቀናል፡፡ እግዚአብሔር ቁሳዊውን ዓለም በመፍጠር ሕዝቦቹ ምድር በምታፈራው ፍሬ ደስ እንዲሰኙና ይህች ዓለም ባሏት ነገሮች ሁሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፈለገ፡፡ “ከዚያም አንተ፣ ሌዋዊውና በመካከልህ የሚኖረው መጻተኛ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተና ለቤትህ በሰጠው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ይበላችሁ” (ዘዳ. 26፡11፣ ዘዳ. 14፡26)፡፡ የሱስ የዚህ ዓለም ፈጣሪ ሲሆን (ዮሐ. 1፡1-3) ምድር ደግሞ የአምላካዊው ንድፍ ጥሩ ማሳያ ምሳሌ ናት፡፡ የእርሱ የመፍጠር ችሎታ በራሱ በሕይወትም ሆነ በምድር ነዋሪዎች ላይ የተለየ አመለካከት እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡ ቁሳዊ ነገሮች ስላላቸው ዋጋ ጠንቅቆ የሚያውቀው ይህ ጌታ ስለ እኛ ጥቅም--ብሎም ደስታና ፍስሐ ሲል አበረከተልን፡፡ ደግሞም ሰብዓዊው ዘር አብልጦ ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሰጥ ታልመው ጥቅም ላይ የዋሉትን አምላካዊ ትሩፋቶች ከተፈጥሮአቸው ውጪ ሲጠቀምባቸው ወይም ዳግም እንዳያንሰራሩ አድርጎ ሲያወድማቸው እርሱ ያውቃል፡፡
ይህች በእግዚአብሔር የተፈጠረች ዓለም የያዘችውን የተትረፈረፈ ቸርነት ይመልከቱ፡፡ ኃጢአት ካደረሰባት መጠነ ሰፊ ውድመት በኋላም እንኳ የተትረፈረፈውን መልካም ተፈጥሮ ማየት ይቻላል፡፡ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሥራ የሆነው ይህ ዓለም በውስጡ የያዘው መልካምነት ስለ አበጃጀው ጌታ በጎነት ምን ይነግረናል?
እንደ ክርስቲያንነታችን የሱስ ፍጹም ሰው፣ ፍጹም አምላክ መሆኑን እናምናለን፡፡ ይህ የመለኮትና የሰብዓዊ ፍጹም ውህደት አሁንም ሆነ ለዘላለም ለዚህች ምድር በእጅጉ የሚያስፈልጋትን ጠንቅቆ የሚያውቅና ለእርሷ ያለው ሃሳብ የተለየ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ፍጹም መለኮት፣ ፍጹም ሰው ተፈጥሮ እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ማስተዋል አለመቻላችን እውነታውን ዋጋ ሊያሳጣው አይችልም፡፡
“የአንዱ አምላክ በሶስት ባህሪ መገለጥና የየሱስ ፍጹም መለኮትና ፍጹም ሰው ባህሪ የመውሰድ ምስጢር… እነዚህ ሁለቱ ከሰብዓዊው ልብም ሆነ እሳቤ የመጠቁ እጹብ ድንቅ ክስተቶች ናቸው፡፡” —J. I. Packer, Knowing God (Downers Grove, Illinois: InterVarsity Press, 1973), p. 53.
የሱስ ወደዚህ ምድር ከመጣባቸው ምክንያቶች አንዱ እግዚአብሔር ምን ያህል እያንዳንዳችንን የሚወድና የሚጠነቀቅልን አምላክ መሆኑን ለማሳየት ነበር፡፡ አንዳንዶች እንደሚያምኑት እግዚአብሔር እጅግ ርቆ የሚኖር ቀዝቃዛ አምላክ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሱስ የሰማያዊ አባታችንን እውነተኛ ጸባይ ገለጠልን፡፡ ይህም ሆኖ ሰይጣን ሰብዓዊውን ፍጡር ከእግዚአብሔር ለመለየት ሞክሯል፡፡ የአምላካዊውን ትክክለኛ ባህሪ አዛብቶ በማቅረብ ስለ እኛ ግድ የማይለው አምላክ አድርጎ ለመሳል ጥረት አድርጎአል፡፡ ተጨባጩን የእግዚአብሔር መልካምነትና ጸጋ ከማወቅና ከመለማመድ እንድንገታ ለማድረግ የሚችለውን ሁሉ ተጠቅሞአል፡፡ ሰይጣን አፈንጋጩን አፍቅሮተ ቁስ በማዘናጊያነት ጥቅም ላይ ማዋሉ ዕቅዱን በጥሩ ሁኔታ ለማሳካት አስችሎታል፡፡
ይህን ጥቅስ ያንብቡ--ማቴ. 19፡16-22፡፡ ሰይጣን እኛን ከጌታ ለማራቅ ለብልጭልጩ ግዑዝ ያለንን ፍቅር እንዴት መጠቀም እንደሚችል ታሪኩ ምን ይነግረናል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ይህን ጎልማሳ ሀብታም ያናግር የነበረው ሰብዓዊውን ሥጋ የለበሰው ራሱ እግዚአብሔር እንደ ነበር ልብ ይሏል፡፡ የሱስ ከማንኛውም ሰው ወጣ ያለ ስብዕና የተላበሰ ሰው እንደነበር ጎልማሳው በእርግጠኝነት አውቆአል፡፡ ታዲያ በመቀጠል የተከሰተው ምን ነበር? ጎልማሳው በፊቱ ከቆመው ከራሱ ከእግዚአብሔር አምላክ ይልቅ ባፈራው መጠነ ሰፊ ሀብት ላይ ብርቱ ፍቅር እንዲኖረው ፈቀደ፡፡ ለዚህ ዓለምና ለአላፊው ነገር የነበረው ብርቱ ፍቅር ልቡን በማሳወሩ ቢያዝንም-አዘኔታው ጥልቅ ባለመሆኑ ትክክለኛውን ነገር እንዲያደርግ አላስቻለውም፡፡ ጎልማሳው ዘላለማዊውን ህይወት በሚያልፈው በዚህ ዓለም ፍቅር በመለወጡ አዘነ እንጂ ምድራዊን ሀብት አጣለሁ ብሎ አልተከፋም ነበር፡፡ ሀብታም ሆንን ወይም ደኻ ከዚህ ዓለም ነገሮች ጋር ያለን ግንኙነት አግባብ ያለው ለመሆኑ እርግጠኞች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
ብድር ወይም ዕዳ ሰማያዊ መርኅ አይደለም፡፡ ሆኖም አዳምና ሔዋን ኃጢአት በመሥራታቸው የተጣሰው ሕግ ሞት አስከተለ፡፡ በዚህም ሰብዓዊው ዘር የመለኮታዊው ፍትሕ ባለ ዕዳ ሆነ፡፡ እኛ ሁላችን ፍጹም ዕዳችንን መክፈል የማንችልና በመንፈሳዊ ኪሳራ ብቻ የምንቀሳቀስ ሆንን፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር የደኅንነትን ዕቅድ ሐሳብ ማቅረቡን ተከትሎ የሱስ ለእኛ “ዋስ” ሆነ (ዕብ. 7፡22)፡፡ እስከ ዛሬ ከታሠሩት ውሎች ሁሉ እጅግ ብርቱው በክርስቶስ አዳኝ ማንነት የተገለጠው ነው፡፡ በመለኮት የተጠየቀውን የፍትሕ ዕዳ መክፈል የሚችለው በመሥዋዕትነት የቀረበው የእርሱ ህይወት ብቻ ሆነ፡፡ በዚህም የሱስ የኃጢአትን ዕዳ በመስቀል ላይ በመክፈል የፍትሕ እና የምህረት ባለ ውለታችን ሆነ፡፡ ለሰብዓዊው ፍጡር ዕዳ በቤዛነት የተከፈለው ይህ ግዙፍ የክፍያ መጠን በዩኒቨርስ ታሪክ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አይታወቅም (ኤፌ. 5፡2)፡፡
“እግዚአብሔር አምላክ ሰማያዊውን መዝገብ አንጠፍጥፎ ያለውን ሁሉ ይኸውም ክርስቶስን በመስጠትና በክርስቶስ የሰማይ ባለቤት በማድረግ የእያንዳንዱን ሰብዓዊ ፍጡር ይሁንታ፣ ፍቅር፣ ልብና ነፍስ ገዛ፡፡” —Ellen G. White, Christ’s Object
Lessons, p. 326.
በመቀጠል የቀረቡትን ጥቅሶች በጥንቃቄ ካነበቡ በኋላ ክርስቶስ ከምን ከምን እንዳዳነን ዘርዝረው ለማስቀመጥ ይሞክሩ፡፡ ቆለ. 1:13፣ 1ተሰ. 1:10፣ 1ጴጥ. 1:18፣
ዕብ. 2:14-15፣ ገላ. 3:13፣ ራእ. 1:5፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በዮሐ. 19፡30 ቴትለስታይ በሚል ጥቅም ላይ የዋለው የግሪክ ቃል ከማንኛውም ቃል ይልቅ እጅግ ጠቃሚና ብርቱ ነው፡፡ ቃሉ “ተፈጸመ” የሚል ፍቺ ያለው ሲሆን፤ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተናገረው የመጨረሻ ቃል ነው፡፡ የክርስቶስ የመጨረሻው እስትንፋስ እወጃ ወደ ምድር የመጣበት ተልዕኮ ክንዋኔ ማግኘቱንና ዕዳችን ሙሉ ለሙሉ መከፈሉን የሚያበስር ነበር፡፡ ቃሉ ከአንደበቱ የወጣው እንደው በተስፋ ቢስ ስሜት ሳይሆን--ጠፍቶ ለነበረው ዓለም ቤዛነቱን በሚያውጅ ድምፀት ነበር፡፡ የክርስቶስ ከሁለት ሺ ዓመታት በፊት በመስቀል ላይ ለዓለም ቤዛ መሆን ትናንትን ጨምሮ ለዛሬ እንዲሁም ለነገ ብሩህ ተስፋ ፈንጥቆአል፡፡ የሱስ ኃጢአትን፣ ሞትንና የዲያብሎስን ሥራ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሥረ መሰረቱ ለመገርሰስ ህይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ሰጠ፡፡ ምንም እንኳ ይህ ሁሉ በጎነት የማይገባን ቢሆንም ነገር ግን እንደ ባለጸግነቱ መጠን እነሆ በእርሱ ቤዛነት ተዋጀን (ኤፌ. 1፡7)፡፡ አስደናቂውን የደኅንነት ታሪክ በጨረፍታ መመልከት-አረማመዳችንን የተቀደሰ ማድረግ ነው፡፡ የክርስቶስ ቤዛነት ልብ የሚማርከው የእግዚአብሔር ገጽታ ነው፡፡ እኛን መዋጀት የእርሱ ተቀዳሚ ፍላጎት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለሰብዓዊው ዘር ያለውን ሀሳብ፤ በተለይም ከእኛ ጋር ላለው ግንኙነት ምን ያህል ዋጋ እንደሚሰጥ ያሳያል፡፡ ክርስቶስ ዕዳችንን ከፍሎ ሕጉ የሚጠይቀውን ፍትሕ ካሰፈነ በኋላ ትኩረቱን ምላሻችን ላይ አድርጓል፡፡ እርስዎ ላደረጉት ክፉ ነገር ይጠብቅዎ የነበረውን ቅጣት--እርሱ አንድም ሳይቀር ሙሉ ለሙሉ ከፍሎልዎታል፡፡ ታዲያ ለዚህ በጎነት ምላሽዎ ምንድን ነው? (ኢዮብ.
42:5-6)፡፡
እግዚአብሔር ከፈርዖን ጋር ባደረገው ግጥሚያ እንዲህ ሲል ተናገረ “አለዚያ በአንተ፣ በሹማምቶችህና በሕዝብህ ላይ የመቅሰፍቴን መዓት ሁሉ አሁን አወርድብሃለሁ፤ ይኸውም በምድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ ማንም እንደሌለ ታውቅ
ዘንድ ነው፡፡” (ዘፀ. 9፡14)፡፡ ጌታ “በምድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ ማንም እንደሌለ” ሲል ምን ማለቱ ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“ውሱን በሆነው ሰብዓዊ አእምሮ የማይወሰነውን አምላክ ጸባይ ወይም ሥራ ማስተዋል የማይሆን ነገር ነው፡፡ ንቁ፣ ስል እና ላቅ ያለ አስተሳሰብ ባላቸው የተማሩ ሰዎች አእምሮ--ቅዱሱ አምላክ ምስጢር እንደሆነ ሊኖር የግድ ነው፡፡” —Ellen G.
White, Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 698, 699.
እግዚአብሔር እርሱን የሚመስል አቻ የለውም (1ነገሥ. 8፡60)፡፡ እርሱ እኛ ልናስተውል በማንችለው መልኩ ያስባል፣ ያስታውሳል፣ እንዲሁም ያደርጋል፡፡ የቱንም ያህል ከገዛ አምሳላችን ጋር ልናመሳስለው ጥረት ብናደርግ እግዚአብሔር ግን ያው ሁሌም እግዚአብሔር እንደሆነ ይኖራል፡፡ የእያንዳንዱን ሰው በዓይነቱ ልዩና ከሌላው የማይገጥም ሰብዓዊ አእምሮ፣ የፊት ገጽታና ባህሪ አበጥሮ ከሚያውቀው አምላክ “ከእርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ” (1ነገሥ. 8፡60) አምላካዊው ቃል ይነግረናል፡፡ ደግሞም እርሱ ፈጣሪ ነው፤ እናም እንደ ፈጣሪነቱ እርሱ ከፍጥረት ሥራው ልዩ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከፍጥረት ሥራው የተለየ ስለመሆኑ የሚከተሉት ጥቅሶች ምን
ይነግሩናል? 1ሳሙ. 2:2፣ መዝ. 86:8፣ Iሳሙ. 55:8-9፣ ኤር. 10:10፣ ቲቶ1:2፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
እግዚአብሔር አምላክን ስንመለከት፣ ባለጸግነቱን ስናይና ሥራዎቹን ለመቃኘት ስንሞክር በእርግጥ እርሱ ተወዳዳሪ የሌለው አስደናቂ አምላክ መሆኑን ለመረዳት አንቸገርም፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን ስለ ሰብዓዊው ፍቅርና መውደድ ሲል ራሱን
“ውድድር” ውስጥ በመክተት ሲገልጽ ይስተዋላል፡፡ ምናልባት እርሱ “ቀናተኛ” አምላክ ነኝ ያለበት ምክንያት ይኸው ይሆናል (ዘፀ. 34፡14)፡፡ እግዚአብሔር ለሰዎች ነፃ አስተሳሰብ ሰጥቶ የፈጠረበት ምክንያት እርሱን ወይም ከእርሱ ውጪ የመረጡትን እንዲያመልኩ ምርጫ እንዲኖራቸው ነው፡፡ የመላው ዩኒቨርስ ፈጣሪና ባለቤት የሆነውን፣ ሰብዓዊውን ዘር በአምሳሉ የፈጠረውንና በብቸኝነት አምልኮ የሚገባውን ጌታ ከማገልገል በተቃራኒ ሌሎች አማልክትን መምረጥ--በብዙ መልኩ እየታየ የኖረና ያለ የሰው ልጅ መሰረታዊ ችግር ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር እየተፎካከረ ያስቸገረዎ ነገር ካለ ምንድን ነው?
በእግዚአብሔር የተፈጠርንና በእርሱ የተዋጀን እንደመሆናችን ያው የእርሱ ነን፡፡ ደግሞም እኛ ብቻ ሳንሆን ያፈራነውም ንብረት የእርሱ ነው፡፡ እኛ ከገዛ ምርጫችን ውጪ በራሳችን ምንም የለንም፡፡ ነገር ግን ዓለማዊው መርኅ ራሳችንን የሀብታችን ባለቤት አድርጎ በተቃራኒ ያስተምራል፡፡ ነገር ግን ይህ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቃል ከሚያስተምረው በተቃራኒ የምድራዊ ሀብታቸው የመጨረሻው ባለቤት እንደሆኑ አድርገው
እንዲያስቡ የተቀናበረ ማታለያ ነው፡፡
የሁሉም ነገር ባለቤት እግዚአብሔር እንጂ እኛ አይደለንም (ኢዮብ 38፡4-11)፡፡ የተስፋው ምድር ለእስራኤሎች ቃል እንደተገባው እኛም እንግዶችና ጭሰኞች ነን፡፡ ቀጣይዋ እስትንፋሳችን ሳትቀር በእግዚአብሔር ላይ ጥገኛ ናት (ሐዋ. 17፡25)፡፡ እኛ የራሳችን ነው ብለን የምናስበው የእርሱ ነው፡፡ የእርሱ መጋቢዎች እንደመሆናችን ተጨባጩንም ሆነ ተጨባጭ ያልሆነውን ንብረት ለእግዚአብሔር ክብር
ልናስተዳደር የተገባ ነው፡፡
በጥቅሶቹ መሰረት የእግዚአብሔር የሆኑትን ንብረቶች ዘርዝረው ለማስቀመጥ ይሞክሩ ዘዳ. 10:14፣ መዝ. 50:10፣ 104:16፣ ሕዝ. 18:4፣ ሐጌ. 2:8፣ 1ቆሮ. 6:19, 20፡፡ በሀብትነት የያዝናቸውን ነገሮች እንዴት ልንመለከት እንደሚገባ አስመልክቶ ጥቅሶቹ ምን ይነግሩናል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“ሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ነው፡፡ ሰዎች የእግዚአብሔርን ባለቤትነት ችላ ይሉ ይሆናል፡፡ እርሱ በለጋስነት በረከቱን ሲያፈስላቸው ስጦታዎቹን ለገዛ ራሳቸው ራስ ወዳድ ፍላጎት ማርኪያነት ሊጠቀሙ ቢችሉም፤ ነገር ግን ስለ መጋቢነታቸው ምላሽ
እንዲሰጡ ይጠራሉ፡፡” —Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 9, p. 246.
የእግዚአብሔር ባለቤትነትና በአደራ የተቀበልነው የመጋቢነት ግንኙነት እኛን ለሰማይ ገጣሚ አድርጎ በማዘጋጀት ለሌሎች ጥቅምና በረከት ያስገኛል፡፡ ነገር ግን ታማኝ ያልሆኑ መጋቢዎች ባለቤቱ የገዛ ንብረቱን መጠቀም እንዳይችል ይገድባሉ፡፡ በትናንቱ ጥናታችን እንደተመለከትነው እግዚአብሔር ፈቃዱን እንድናደርግ አያስገድደንም፡፡ እርሱ እኛን ከፈጠረ በኋላ እርሱን ወክለን ዳግም እስኪገለጥ በዚህ ዓለም የምናስተዳድረው ሀብት ንብረት ሰጥቶናል፡፡ በእጃችን ባለው ንብረት ላይ የምንወስነው ውሳኔ ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ያንጸባርቃል፡፡ ነገሩን በእውነት ከተመለከቱት እርስዎ ባለቤት ከሆኑባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱም የእርስዎ አይደለም፡፡ ሁሉም የእግዚአብሔር ስለ መሆኑ እስቲ አሰብ ያደርጉ፡፡ ሁኔታው ከንብረትዎ ጋር ሊኖርዎት ስለሚገባው ዝምድና ምን ሊነግርዎ ይችላል?
መጋቢነት የተሰኘውን ጽንሰ ሀሳብ እንደምናስተውለው ኃላፊነቱ የተጀመረው እግዚአብሔር ውብ የሆነውን የኤደን አትክልት ስፍራ ለአዳምና ለሔዋን መኖሪያቸው አድርጎ እንዲንከባከቡና እንዲጠብቁ በሰጣቸው ጊዜ ነበር (ዘፍ. 2፡15)፡፡ እነዚህ ጥንዶች በዚህ ፍጹም ስፍራ የሚገኘውን የአትክልት ቦታ ምቹ አድርገው ማሳመር የነበረባቸው ሲሆን ኃላፊነቱ ደግሞ ከአቅማቸው በላይ አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር ለአዲሱ ሥራ ተገቢውን ሹመት በመስጠት የኃላፊነታቸውን ድርሻ በአግባቡ አስተምሯቸዋል፡፡ ኤደንን መንከባከብ ትርጉም ያለው ህይወት ከመስጠቱ ባሻገር ለአዲሱ ቤተሰብ ደስታ የሚያመጣ ነበር፡፡
በዘፍ. 1፡26፣28 “ሥልጣን ይኑራቸው” በሚል ጥቅም ላይ የዋለው የዕብራውያን ቃል “ቁጥጥር ማድረግና ማስተዳደር” የሚል ፍቺ አለው፡፡ አባባሉ በጭካኔና በማንቀጥቀጥ መግዛት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፍጥረታት በደግነት መንከባከብ የሚል አውድ አለው፡፡ ይህ ኃላፊነት ዛሬም አለ እንጂ አላበቃም፡፡ አዳምና ሔዋን ይኖሩበት በነበረው በዚያ ቅዱስ ድባብ እግዚአብሔር የሁሉም ነገር ባለቤት፤ እነርሱ ደግሞ የንብረቱ አስተዳዳሪዎችና መጋቢዎች መሆናቸውን መማር ነበረባቸው፡፡ ገና ከመጀመሪያው አዳምና ሔዋን የማስተዳደሩን ኃላፊነት በመውሰድ ለእርሱ ያላቸውን ታማኝነት እንዲያሳዩ እንጂ ባለቤቶች እንዲሆኑ አምላካዊው እቅድ አልነበረም፡፡ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ
ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት ማሳየት ከእነርሱ ይጠበቅ ነበር፡፡
“አዳምና ሔዋን የኤደንን የአትክልት ስፍራ እንዲንከባከቡ ተሰጣቸው፡፡ እንዲያለሙና እንዲጠብቁ ኃላፊነቱን ወሰዱ፡፡ እነርሱ በሥራቸው ደስተኞች ነበሩ፡፡ አእምሮአቸው፣ ልባቸውና ፈቃዳቸው ፍጹም ስምሙ ነበር፡፡ በሥራ መድከምም ሆነ ልፋት አያውቁም፡፡ ጊዜና ሰዓታቸው በጠቃሚ የሥራ እንቅስቃሴ ብሎም እጅግ በቀረበ የእርስ በርስ ግንኙነት የተሞላ ነበር፡፡ የሚሠሩት ሥራ በእጅጉ አስደሳች ነበር፡፡ እግዚአብሔር አብ እና እግዚአብሔር ወልድ ይጎበኟቸውና ያናግሯቸው ነበር፡፡ ፍጹም ነጻነት የተሰጣቸው የእነዚህ ጥንዶች. . . መኖሪያ የነበረው ኤደን ባለቤት እግዚአብሔር ነበር፡፡ እነርሱም ከእርሱ በታች ሆነው ያስተዳድሩት ነበር፡፡”—Ellen G. White, Manuscript Releases, vol. 10, p. 327.