የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡ። ዘፀ 4፥10-16፣ ሉቃ 8፥22-25፣ ዮሐ 3፥1-10፣ የሐዋ 16፥25-34፣ 1ኛ ቆሮ 5፥1-5፣ ሉቃ 7፥28።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡”የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥
ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም
ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና
አሳብ ይመረምራል” (ዕብራውያን 4፡12)።
በህዳር ወር 1989 ዓም በኮሙኒከት ምስራቅ ጀርመን ጉንተር ስቻቦዊስኪ
በቴሌቪዥን ያስተላለፈው ቀጥታ ንግግር ለበርሊን ግንብ መውደቅ
ዋዜማ ሆነ። የምስራቅ ጀርመን ዜና ማሰራጫዎች ወኪል ሆኖ ሲናገር
ማስታወቂያውን በትክክል አላስተላለፈም ነበር። የምስራቅ ጀርመን ነዋሪዎች
አስቸጋሪና አስፈላጊ የሆነውን ተገቢ ቪዛ ካገኙ በኋላ ምዕራብ አውሮፓን መጎብኘት
ይችላሉ በማለት ፋንታ እንዲሁ በደፈናው የምስራቅ ጀርመን ነዋሪዎች ምዕራብ
አውሮፓን መጎብኘት ይችላሉ አለ። አንድ ጋዜጠኛ የፖሊሲ ለውጡ መቼ ይጀምራል
ብሎ ሲጠይቀው ስቻቦዊስኪ “እኔ እንደማውቀው ከሆነ ከአሁን ጀምሮ ምንም
ሳይዘገይ” አለ። ታዲያ ህዝቡ ይህን ሲሰማ መንግስት ባሳወቀው መሰረት ወደ ድንበሩ
ኬላ በመጉረፍ ለማለፍ ፈለገ።
ሰዎች ለተቋማትና ለሀገራት እንዲናገሩ ይወከላሉ። ለእግዚአብሔር የሚናገሩትስ?
በዚህ ሳምንት ነቢያት ምን አይነት ስልጣን እንዳላቸው እንመረምራለን። መጽሐፍ
ያልፃፉት ነቢያት እንደነ ናታን እና እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት፣ ኤለን ጂ ዋይት
ሳትቀር ምን ስልጣን አላቸው?
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለህዳር 26 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
አንድ ሰው እርስዎን ወክሎ እንዲናገር ከመፍቀድዎ በፊት ሰውየው የታመነ መሆኑን ማረጋገጥ አያስፈልግም? ሀሳብዎን በደንብ የተረዳ እና በታማኝነት የሚያስተላልፍ መሆን አለበት። ዘፀ 2፥11-15 እና ዘፀ 3፥1-3፣10-13 ያንብቡ። ሙሴ በበግ እረኝነት ያሳለፈው ጊዜ የእግዚአብሔር አፈ ንጉሥ (ቃል አቃባይ) ለመሆን እንዴት ረዳው?
ሙሴ ከዕድሜው የመጀመሪያዎቹን አርባ አመታት ግብጽ ሊሰጥ የሚችለውን ሁሉ ከፍተኛ ትምህርት በመማር አሳለፈ። ነገር ግን ያ ሁሉ ትምህርት የእግዚአብሔር መልእክተኛ ለመሆን አላዘጋጀውም። ነገር ግን የዓለም አወናባጅነት በሌለበት ምድረ በዳ ቀጣዩን የእድሜውን አርባ አመታት በበግ ጠባቂነት ማሳለፍ ነበረበት። ልዑል ሳለ የተማረውን መርሳት ነበረበት። እስራኤላውያንን ነፃ ለማውጣት ከመሰለፉ በፊት ወክሎ ከሚናገርለት አምላኩ ጋር በሚገባ መተዋወቅ ነበረበት። ዘፀ 4፥10-16ን ያንብቡ። በእግዚአብሔር እና በሙሴ መካከል የተደረገውን ውይይት ስናነብ ነቢያት እንዴት እንደሚጠሩ እና እንዴት እንደሚሰሩ ምን እንማራለን?
ሙሴ እግዚአብሔርን ሲወክል አሮን ደግሞ የሙሴ ቃል አቃባይ ሆኖ እንዲሰራ
ታዘዘ (ዘፀ 4፥16 እና ዘፀ 7፥1 ይመለከቱ)። እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን እንዳደረገው
ሁሉ ነቢያቱ እርሱ የሰጣቸውን መልዕክት በትክክል እንዲያስተላልፉ ይረዳቸዋል።
ሙሴ ባለፈው ጊዜ እንዳልተሳካለት ያውቃል። ከወገኖቹ ከእስራኤላውያን
ጋር በነበረው ግንኙነት ስልጣኑ ተቀባይነት እንዳላገኘ ያስታውሳል (ዘፀ 2፥14)።
እግዚአብሔር የሙሴን ማመንታት አስተዋለ። ፍርሃቱን በትዕግስት አስተዋለለት።
ሰበብ የሚሆኑ ምክንያቶች ሁሉ ተወግደው ነበር፣ ነገር ግን ከዚያ በኋላም ሙሴ
ጥሪውን ለመቀበል አልፈልገም። ፍርሃቱ ወደ አለማመን መራው። ሲያመነታ
እግዚአብሔር ሊጠቀምበት ያለውን ኃይል ተጠራጠረ። ከዚያ በኋላ ተጠራጣሪውን
ነቢይ በስራ ላይ ለማሰለፍ እግዚአብሔር የማያዳግም ትእዛዝ ሰጠው (ዘፀ 3፥14-17)።
ነቢይ ላይሆኑ ይችላሉ። ታዲያ እድሜ ልክዎን በሙሉ እግዚአብሔር
ምን እንዲያደርጉለት ጠርቶዎታል? ለዚህ መጠራት (ጥሪ) እራስዎን
እንዴት ሊያዘጋጁ ይችላሉ?
የኢየሱስ ስልጣን ምንጩ ምንድር ነው? የዚህ ሥልጣንስ መረጃ ምንድን ነው? ማቴ 21፥23-27ን እና ዮሐ 17፥2ን ይመልከቱ።
ኢየሱስ ሲያስተምር ካህናቱ ይህን ስልጣን ከየት እንዳገኘው ማወቅ ፈለጉ። ኢየሱስ ከትምህርት ቤቶቻቸው መካከል ከአንዱ አልተመረቀም። ከመምህራን ማሰልጠኛዎች ገብቶ አልሰለጠነም። በቀጥታ ጥያቄያቸውን በመመለስ ፋንታ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ የማይጠራጠር ስልጣን በመጠየቅ ጠያቂዎቹን ወደ መልሱ አመላከታቸው። ጥያቄውን ባለመመለሳቸው ለመጥምቁ ዮሐንስ እንዲያስተምር ስልጣን የሰጠውን የእግዚአብሔር ኃይል የካዱ ብቻ ሳይሆን እንደ ዮሐንስ በእግዚአብሔር የተላከውን ኢየሱስንም ካዱ። የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ ኢየሱስ ስልጣን ምን ይነግሩናል? ማቴ 7፥28ና 29፤ ማር 1፥21-27፤ ሉቃ 8፥22-25፤ ሉቃ 9፥1፤ ዮሐ 5፥25-27 እና ዮሐ 7፥38።
ኢየሱስ የሰው ፈጣሪና (ዮሐ 1፥3) አዳኝ ስለሆነ (ሮሜ 3፥24) ስልጣን ሁሉ
የእርሱ ነው። እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በምድራዊ አገልግሎቱ ጊዜ ኢየሱስ
የነበረውን መለኮታዊነት ማንም ሊያስመስለው ወይም በራሱ ሊያመነጨው
አይችልም። ስልጣን እንዳለው ሆኖ ስላስተማረ የኢየሱስ ማስተማር አድማጮቹን
አስገረማቸው (ማቴ 7፥29)።
የኢየሱስን ከሰው ያልመነጭ ማስተማር ወንጌሎቹ በሙሉ ዘግበውታል። ኢየሱስ
ኃጢአትን ይቀር አለ (ማር 2፥10፣11)። አጋንንትን አስወጣ (ማር 3፥15)። የሰዎችን
ሀሳብም አወቀ (አነበበ) (ዮሐ 2፥24,25)። ሙታንን አስነሣ፣ የዘላለም ህይወትን ተስፋ
ሰጠ (ዮሐ 10፥28)። መድሃኒታችን ሆኖ በዚህ ምድር ሳለ ኢየሱስ ከአብ የተሰጠውን
ስልጣኑን ከስራ ላይ አዋለ (ዮሐ 17፥2)። ምን ጊዜም በአብ ላይ ተማመነ፣ ከእርሱም
ጋር ተባበረ (ዮሐ 5፥19)። ብዙ ጊዜ ስለ እርሱ የሚመሰክረውን ቃል ይጠቅስ ነበር።
እርሱ ሙሉ ስልጣን ነበረው። ስልጣኑንም ለደቀ መዛሙርቱ ማስተላለፍ ይችል
ነበር (ማር 6፥7)። የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ምስክርነቱ በተነገረባቸው ነቢያት
አማካይነት ተገለጠ (ራዕይ 19፥10)።
ኢየሱስ የሚያስፈልገውን መረጃ ቢሰጥም አንዳንድ ሰዎች ክርስቶስን
አልተቀበሉትም። ልናምን የሚያስችሉን ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም
ካለማመን ወጥመድ ውስጥ እንዳንገባ እንዴት መጠንቀቅ ያስፈልገናል?
መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከእግዚአብሔር የተገለጠ ትንቢታዊ
ራዕይ ነው። የህይወትን አብይ ጥያቄዎች ከመመለሱም በላይ እግዚአብሔር ራሱን
ለሰው ዘር ሁሉ የገለጠበት የተለየ መሳሪያ ነው። የሰው ዘርን ህልውና (የመኖር)
ምክንያት፣ የእግዚአብሔርን ባህሪና ፍቃድ እና ለህይወታችን ያለውን ዕቅድ ከቃሉ
እንማራለን። መጽሃፍ ቅዱስ የእውነት ወርቃዊ መለኪያ ነው። የህይወትን ትክክለኛ
ምርጫ እንድናደርግ የሚመራን ስልጣን ነው። የክርስቲያናዊ አስተሳሰብ መሰረት ነው።
ለተገለጠው እውነት ሁሉ ምንጭ ነው። የክርስቲያን እምነትና ተግባር መመሪያ ነው።
የእግዚአብሔርን ቃል መቀበል ወይም አለመቀበል ስለምንችል አለመቀበላችንን
ለማሳየት እንደ ንጉሱ ኢዮአቄም መጽሀፍ ቅዱሳችንን ማቃጠል አያስፈልገንም (ኤር
36፥22-27ን ይመልከቱ)። እናምናለን እያልን ቃሉን ችላ ማለት የማቃጠል ያህል
ችግር ነው።
የእግዚአብሔርን ቃል ሲናገኝና ስንቀበል እንደ ንጉስ ኢዮሲያስ እንለወጥና
ሌሎችንም ወደ እግዚአብሔር እንመራለን (2ኛ ነገስት 22፥10-13ን ይመልከቱ)።
በአሁኑ ወቅት ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡት ስህተት ለመፈለግና ለማሾፍ
ነው። አንዳንዶች ደግሞ ከዘመናዊ ባህል ጋር አይስማማም (አይገጥምም) ይላሉ (
ብዙ ጊዜ አይስማማም፣ ሊስማማም አይገባውም)። አንዳንዶች ደግሞ ከዘመናዊው
“ሳይንሳዊ” ወይም ባህላዊ ዝንባሌ ጋር ስለሚቃረን ያፌዙበታል።
በክርስትና እንኳን ለግል መንፈሳዊ እድገትና ተሃድሶ በመጠቀም ፋንታ ብዙዎች
የሆነ ስነ መለኮታዊ አስተያየትን ለመደገፍ ይጠቀሙበታል። ሌሎች ደግሞ በዕለታዊ
ሕይወታቸው ላይ ምንምታሪካዊ ወይም ተግባራዊ ስልጣን እንዳይኖረው አድርገው
ይተረጉሙታል።
ከሁሉም ቀላሉና ምናልባትም የተለመደው የመጽሐፍ ቅዱስን ስልጣንን
ያለመቀበል ዘዴ መጽሐፍ ቅዱስን ችላ ማለትና ጊዜ ወስዶ በማንበብ እውነቱን
በህይወት ላይ አለማዋል ነው።
በቃል ብቻ የተላለፈው የእግዚአብሔር ቃል በሚከተሉት ክስተቶች ላይ
ምን አይነት ውጤት አስገኘ? (ኤር 38፥1-4ን፣ ዮሐ 3፥1-10ን፣ የሐዋ
16፥25-34ን ይመልከቱ)።
በጥንት ጊዜ የጽህፈት መሳሪያዎች በብዛት የማይገኙና ዋጋቸውም ውድ ነበር።
በተጨማሪም ብዙ ሰዎች ማንበብ አይችሉም ነበር። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል
ነቢያቱ በቃል ማሰማታቸው አስፈላጊ ነበር።
በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በፅሁፍም ሆነ በቃል የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል
ኃጢአትን ለመግለጥና ተሃድሶና መለወጥን ለማምጣት ወደ ሰዎች ልብ ሰርጾ መግባት
ይችላል። ቃሉ ወደ ንስሐ መግባትና ወደ መታዘዝ ይመራናል (የሐዋ 5፥29ን እና ዕብ
4፥12ን ይመልከቱ)። በተሻለ ሁኔታ ማወቅ ያለባቸው ብዙ ሰዎች የማይቀበሉት ከዚህ
የተነሳ ነው። ህይወታቸውን እንዲቆጣጠር አይፈልጉም።
ሆሴዕ 12፥14 በግልጽ እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔርም በነቢይ እጅ እስራኤልን
ከግብጽ አወጣ፥ በነቢይም እጅ ጠበቀው።” ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነቢያት ስራዎች
መካከል ዋናዎቹ ህዝቡን መምራትና መጠበቅ ነበር።
እንደ መሳፍንት 4፥4-8፣ 2ኛ ዜና 20፥14-17፣ ዘፀ 12፥1-3፣ ዘዳ 1፥9-16 ያሉ
ጥቅሶችን ስናነብ ነቢያት የእግዚአብሔርን የአመራር ዘዴ ለሕዝቡ በመግለጥ በጣም
ወሳኝ እንደነበሩ እንመለከታለን። በጦርነትና በችግር ጊዜ በዲቦራና በኢያኤል
አማካይነት እንዳደረገው ሁሉ ለህዝቡ እና ለመሪዎቹ አመራር፣ ማደፋፈሪያና ተስፋ
ለመስጠት ነቢያት ታላቅ ሚናዎችን ተጫውተዋል። የዓመት በዓልን አከባበርና
አምልኮን በተመለከተም ደግሞ ነቢያት መመሪያ ይሰጡ ነበር (ዘፀ 12፥1-3)። በሌላ
ጊዜም እግዚአብሔር የሕዝብ አስተዳደርን በሚመለከት ለነቢያት ተናግሯል። ባጭሩ
እግዚአብሔር በነቢያቱ በኩል መመሪያ ያልሰጠበት የእስራኤላውያን የኑሮ ክፍል
አልነበረም።
ትንቢታዊ ስጦታ የቀደምት ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንን ድርጅትና
አመራር የረዳባቸው አንዳንድ ክፍሎች ምን ነበሩ? የሐዋ 6፥1-7፣ 1ኛ
ቆሮ 5፥1-5፣ 1ኛ ቆሮ 7፥10-16፣ ቲቶ 1፥5።
አዲስ ተቋም (ድርጅት) ያለ ምንም መመሪያ ጽሑፍ ወይም ያለ መሪ መጀመር
እንዴት ከባድ እንደሚሆን ሊገምቱ ይችላሉ። የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን
የገጠማት ችግር ይሄን ይመስል ነበር። ክርስቶስ ወደ ሰማይ ስላረገ ከደቀ መዛሙርቱ
ጋር አልነበረም። “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ አስተምሩ”
የሚል ግልጽ የሆነ መመሪያ ሰጥቷቸው ሄደ (ማር 16፥15)። አስራ ሁለቱ ሐዋርያት
ቢመረጡም ስራቸውን ለመጀመር ግልጽ የሆነ ድርጅታዊ መዋቅር አልነበረም።
ቀደምቷ ቤተ ክርስቲያን እንድ የቤተ ክርስቲያን ድርጅት፣ የተልዕኮ መዋቅር፣
የማንነት አስፈላጊነትና በመካከላቸው ክህደትንና ኢ-ግብረገባዊነትን እንደመኮነን ያሉ
በርካታ ተግዳሮቶችን ተጋፍጣ ነበር። በትክክል ሲታይ፣ በቀደምት ቤተ ክርስቲያን
ውስጥ ይሰራ የነበረው የትንቢት ስጦታ ቤተ ክርስቲያኗን በመጠበቅና በመከላከል
ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል (የሐዋ። 13:1,2)። ቤተ ክርስቲያን እንድትደራጅና
በተልዕኮዋ ወደ ፊት እንድትንቀሳቀስ የትንቢት ስጦታ ባያግዛት ኖሮ ቀደምት ቤተ
ክርስቲያን እንዴት እንደጀመረች ማሰብ በርግጥ ከባድ ነው።
አንዳንድ ሰዎች “የተደራጀ ሃይማኖትን” በጥርጣሬ አይን ይመለከቱታል።
ችግሮች ቢኖሩም የተደራጀ ሃይማኖት አካል መሆን ምን ጥቅሞችን
ያስገኛል? ከራስዎ ትልቅ የሆነ ነገር አካል በመሆንዎ ምን ሊሰጡና
ሊቀበሉ ይችላሉ?
1ኛ ዜና 29፥29ንና 2ኛ ዜና 9፥29ን ያንብቡ። እነዚህን ሁለት ምንባቦች ሲያነቡ ስለ አንዳንዶቹ ነቢያት ምን ተገነዘቡ?
እንደ ናታን፣ ጋድ፣ አሂያ ና ኦዶ የመሳሰሉት ነቢያት ነቢይነታቸው ቢታመንበትም መጽሐፎቻቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም። 1ኛ ነገስት 11፥29-39ንና ሉቃ 7፥28ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላልተካተቱት ነቢያት ስልጣን ምን ያስተምሩናል?
የአንዳንድ ነቢያት መልዕክቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተካትተው ሳለ የአንዳንዶቹ
እንዳይከተቱ እግዚአብሔር ለምን እንደፈቀደ ባናውቅም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
ያልተካተቱ ነቢያትም በመንፈስ ቅዱስ የተነሳሱ መሆናቸውን እናውቃለን። መንፈሳዊ
ስጦታዎች፣ የትንቢት ስጦታንም ጨምሮ፣ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እንደሚቀጥሉ
መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ከመጽሐፍ ቅዱስ በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
ያልተካተቱ ነቢያት እንደሚነሱም መጽሐፍ ቅዱስ ይተነብያል። የሚነሱትም “ሁላችን
የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ
መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን
አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ለማድረግ” ነው (ኤፌሶን
4፥12-13)። “ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ” በፊትም ይኖራሉ
(ኢዩኤል 2፥31)።
ዳዊት ዝሙት ከፈጸመና ነፍስ ከገደለ በኋላ እግዚአብሔር ነብዩን ናታንን በመላክ
ተጋፈጠው (2ኛ ሳሙኤል 12፥7-14)። ዳዊት የነቢዩን ስልጣን አልተጠራጠረም።
የነቢዩ ትንቢት የናታን ትንቢት ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይካተትም በመንፈስ
ቅዱስ የተነሳሳ መሆኑ አላጠራጠረም። መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ በኋላ የተነሱ ነቢያት፣
ኤለን ጂ ዋይትን ጨምሮ፣ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ስልጣን እንደተሰጣቸው ያምናሉ።
መልእክታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ መስፈርት መፈተን ያለበት ሲሆን መልእክቶቹ
የአስተምህሮና የእምነት ምንጭ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን አይተኩም።
ኤለን ጂ ዋይት እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱሳችሁን
እንድታጠኑ ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስን የሚተካ ሌላ ተጨማሪ ብርሃን አልሰጠም።
ይህ ብርሃን ግራ የተጋቡ አእምሮዎችን በደንብ ከተበላና ከተዋሃደ የነፍስ የሕይወት
ደም ወደ ሆነው ወደ ቃሉ ለመምራት የተሰጠ ብርሃን ነው።” (selected messages,
book 3, page 29)።
እግዚአብሔር ለመልክተኛነት የመረጣቸው ነቢያት በስልጣን እና አገባብነት
ባለው ሁኔታ ይናገሩናል። መጽሐፋቸው የመጽሐፍ ቅዱስ አካል የሆነ ነቢያት አሉ።
ጽሑፋቸው የመጽሐፍ ቅዱስ አካል ያልሆነ ነቢያት ደግሞ አሉ (እነዚህ ነቢያት
ከአዲስ ኪዳን በኋላ የመጡ ናቸው)። ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ የተነሳሱ ሲሆኑ
መልእክታቸውም መለኮታዊ ማህተም አለበት።
ኤለን ጂ ዋይት ከመጽሐፍ ቅዱስ በኋላ ከተነሱትና በመጽሐፍ ቅዱስ ካልተካተቱት
ነቢያት መካከል ነች። 7ኛ ቀን አድቬንቲስቶች ጽሑፎቿን የመጽሐፍ ቅዱስ ጭማሪ
ናቸው ብለው አያምኑም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እኩል ናቸውም አይሉም። ጽህፎቿ
ግን በስልጣን የሚናገሩና ጠቃሚዎች ናቸው። ኤለን ጂ ዋይት ራሷ እንዲህ ትላለች፦
“በእነዚህ በምጽፋቸው ደብዳቤዎችና በማስተላልፋቸው ምስክርነቶች ጌታ
የገለጠልኝን ለእናንተ አስተላልፋለሁ (አቀርባለሁ)። በወረቀት ላይ የራሴን ሀሳቦች
በመግለጽ አንድ ጽሑፉ እንኳን አልጽፍም። እግዚአብሔር በራዕይ በፊቴ የከፈተልኝ
ነገሮች ናቸው--ከከበረ ዙፋኑ እየበሩ ያሉ ከቡር የብርሃን ጮራዎች ናቸው። (Select-
ed Messages, Book 1, page 29)።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሁሉ ኤለን ጂ ዋይትም የኃጢአትን መኖር
እርግጠኝነትና ኢየሱስ ብቸኛው የዘላለም ህይወት ተስፋ መሆኑን ትናገራለች። ይህም
ተስፋ በሀይማኖት (በእምነት) ለሚሹት ሁሉ በነፃ የሚሰጥ ጸጋ መሆኑን የምታበስር
ሲሆን ይህ ሌላኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ሀይለኛ ርዕሰ ጉዳይ ነው።
በመልእክቷ (እግዚአብሔር ባቀበላት መልዕክት ማለት ይሻላል) ሉሲፈር ከሰማይ
ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ በክፉ እና በመልካም መካከል ያለውንና የሚቀጥለውን ተጋድሎ
ታብራራለች። በመጨረሻ ኃጢአት፣ ሰይጣንና ተከታዮቹ እንደሚደመሰሱም በግልጽ
ትናገራለች። የኤለን ጂ ዋይት ጽሑፎች በመጨረሻ ዘመን የሚሆነውን የመጽሐፍ
ቅዱስ ትንቢት ያብራራሉ። ለምሳሌ፣ የመንግስትና የሃይማኖት ተቋማትን ውህደት
(መቀላቀል) ትቃወማለች። የሃይማኖት ነፃነትን አስፈላጊነት በጥብቅ ታሳስባለች። ስለ
ግብረ ገብ መበላሸትም ታስጠነቅቃለች። የእግዚአብሔር ህግ አስፈላጊነቱን አጉልታ
ትናገራለች። የአውሬውን ምልክት ማወቃችን በእርሷ ጽሑፎች ላይ የተመሠረተ
አይደለም። ቢሆንም ጽሑፎቿ ስለ መጨረሻዎቹ ክስተቶች ድንቅ የሆነ ማስተዋል
እንዲኖረን ይረዱናል።
በክርስቲያናዊ አኗኗር ላይም ተጨባጭ ምስክሮችን ትለግሳለች። ስለ
መንፈሳዊነት፣ ስለ ጤና፣ ስለ ስነ-ትምህርት፣ ስለ የቤተሰብ ኑሮ፣ ስለ ልጅ አስተዳደግ፣
ስለ ግብረ-ገባዊ ኑሮና በሌሎች ነገሮችም ላይ ያስተላኣለፈቻቸው መልእክቶች
ብዙዎች የአኗኗር ዘይቤአቸውን እንዲቀይሩ በማድረግ በተለያዩ ደረጃዎች ጥሩ
ሕይወትን እንዲለማመዱ ረድቷቸዋል።
የኤለን ጂ ዋይት ጽሑፎች በመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ አይገኙም፣ ነገር ግን
በምድር የመጨረሻ ታሪክ ዘመን የሚኖሩ አማኞችን እንድትመራ እግዚአብሔር
ተጠቅሞባታል። ጽሑፎቿ አሁንም በትንቢታዊ ስልጣንና አግባብነት ይናገራሉ።