የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተለውን ጥቅስ ያንብቡ፡- ቆላ. 4:7-15።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር
ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና” (1 ተሰ. 5፡18)።
በዚህ ሳምንት ጳውሎስ ለቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን የጻፈውን መልእክት (ደብዳቤ)
የመጨረሻ ክፍል እናጠናለን። ስለ ጳውሎስ የሥራ አጋሮች የበለጠ እንማራለን።
የሐዋርያት ሥራ ጳውሎስ በመጀመሪያ ከበርናባስ ቀጥሎም ከሲላስ ጋር ይሠራ
እንደነበር ያሳየናል። ከዚያም የሐዋርያት ሥራ ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን መልካሙን
የምሥራች (ወንጌል) ለማካፈል ባደረጋቸው ሦስት ጉዞዎች ላይ ማብራሪያ ይሰጠናል።
በዚህ ሳምንት ጳውሎስ ወንጌልን ለመስበክ ስለነበረው እቅድ እንመለከታለን።
የጳውሎስ እቅድ በሮም ግዛት ስር በነበሩ ወሳኝ ከተሞች ውስጥ ስለ ኢየሱስ ወንጌል
መስበክ ነበር። በተጨማሪም ጳውሎስ ሰዎች የወንጌል አገልጋይ እንዲሆኑ ለማሠልጠን
ፈልጎ ነበር። ጳውሎስ እነዚህን አገልጋዮች እሱ በአካል ወዳልጎበኛቸው (ወዳልደረሰባቸው)
ከተሞች ላካቸው። ከእነዚህ ቦታዎች መካከል ቆላስይስ፣ ሎዶቅያና ኢያራ ይገኙበታል።
ጳውሎስ በሚሄድበት ቦታ ሁሉ፣ ሰዎችን ሁልጊዜ ከአብያተ ክርስቲያናት ጋር
ያገናኛቸው ነበር። ጳውሎስ አይሁዶችና አይሁዳውያን ያልሆኑ፣ ወንዶችና ሴቶች፣
እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን አባላት ከአገልጋዮች ጋር አብረው መሥራት እንዳለባቸው
ተረድቶ ነበር። ከእነዚህ አገልጋዮች መካከል ቲኪቆስ፣ አርስጥሮኮስ፣ ኢዮስጦስ፣
ኤጳፍራ፣ ሉቃስና ንምፉ ይገኙበታል።
ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክት የመጨረሻ ክፍል ላይ፣ ለሎዶቅያ
ሰዎችም መልእክት ጽፎ እንደነበር እንረዳለን። ይህ መልእክት ጠፍቷል። ጳውሎስ
በመጨረሻዎቹ ጥቅሶች ውስጥ ብዙ መረጃዎችን አስቀምጧል። በተጨማሪም ለአክሪጳ
አንዳንድ ምክሮችን አካቷል። ጳውሎስ አብያተ ክርስቲያናት ጠንካራ እንዲሆኑ
የሚችለውን ሁሉ አድርጓል።
*የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።
ትምህርቶች (ቆላ. 4:7-9)
ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን መልካሙን የምሥራች (ወንጌል) ስለ ማካፈል
ከጳውሎስ ብዙ እንማራለን። ጳውሎስ 13,400 ማይል (21,565 ኪሎ ሜትር) ያህል
ተጉዟል። ይህ መረጃ አስደናቂ ነው ምክንያቱም ጳውሎስ አብዛኛውን ጉዞ ያደርግ
የነበረው በእግር ነበር! አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጳውሎስ ታስሮ ነበር።
ጳውሎስ ቆሮንቶስንና ኤፌሶንን ጨምሮ በከተሞች ብዙ ጊዜ አሳልፏል። እነዚህም
ከተሞች የንግድ ማዕከሎች ነበሩ። ጳውሎስ አገልጋዮችን ከእነዚህ ማዕከላት ወደ ትንንሽ
ከተሞች ይልክ ነበር። እነዚህ አገልጋዮች ደግሞ በትንንሽ ከተሞች ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ
ሰዎች የኢየሱስን ወንጌል ይሰብኩ ነበር። በተጨማሪም ጳውሎስ የመሠረታቸውን
አብያተ ክርስቲያናት ይጎበኝ ነበር። ጳውሎስ በእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ
የነበሩትን አዳዲስ ክርስቲያኖች በእምነታቸው እንዲበረቱ ለማድረግ ፈልጎ ነበር።
ጳውሎስ ራሱ በአካል አብያተ ክርስቲያቱን መጎብኘት ሳይችል ሲቀር፣ ደብዳቤዎችን
ይልክላቸው ነበር። በዚህ መንገድ የቤተ ክርስቲያን አባላት እርሱ እንደሚያስባቸውና
እንደሚጠነቀቅላቸው ያውቁ ነበር።
ቆላ. 4:7-9ን ያንብቡ። ከኤፌ. 6፡21 ጋር ያስተያዩ። ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች
ስለ ቲኪቆስ የተናገረው ምንድነው? ጳውሎስ ቲኪቆስንና አናሲሞስን ወደ ቆላስይስ
የላከበት ምክንያት ምን ነበር?
ቲኪቆስና አናሲሞስ ለቆላስይስ ሰዎች ምን ዜና እንደነገሯቸው አናውቅም።
ጳውሎስ ከጻፈው መልእክት ተነስተን፣ ዜናው ተስፋን ይሰጣቸው ዘንድ የታለመ
መሆኑን መናገር እንችላለን (ቆላ. 4፡7-9)። ቲኪቆስና አናሲሞስ ጳውሎስ በእስር ቤት
ስለነበረው ቆይታ ተርከውላቸው ይሆናል። ይህ በጳውሎስና በአብያተ ክርስቲያናት
መካከል የነበረው የመልእክት ልውውጥ አስፈላጊ ነበር። የጳውሎስ ደብዳቤዎች የቤተ
ክርስቲያን አባላትን አንድ ለማድረግ ያግዙ ነበር።
ቲኪቆስ ማለት “እድለኛ “ ማለት ነው። ጳውሎስ ቲኪቆስን ያምነው ነበር።
ጳውሎስ ቲኪቆስ ታማኝ ሰባኪና አገልጋይ እንደነበረ ተናግሯል። ጳውሎስ ወደ
ኢየሩሳሌም በሚያደርገው ጉዞ አብረውት እንዲሄዱ እሱንና ከእስያ አንድ ሌላ ሰው
መርጦ ነበር (ሐዋ. 20፡4)። ጳውሎስና እነዚህ ሁለት ሰዎች በከተማው ለነበሩ ምስኪን
ክርስቲያኖች ስጦታ አምጥተውላቸው ነበር። ቲኪቆስ ጳውሎስ በሮም በድጋሚ
በታሰረበት ወቅት አብሮት ነበር። ከዚያም ጳውሎስ ቲኪቆስን በኤፌሶን የነበረችውን ቤተ
ክርስቲያን እንዲረዳት ወደዚያ ላከው (2 ጢሞ. 4፡12)። በተጨማሪም ጳውሎስ ቲኪቆስን
በቀርጤስ ወደነበረው ወደ ቲቶ ሊልከው አስቦ ነበር (ቲቶ 3፡12)። አናሲሞስም ከቲኪቆስ
ጋር አብሮ ወደ ቆላስይስ ተጓዘ። አናሲሞስ ክርስቲያን የሆነው በሮም ከጳውሎስ ጋር
ከተገናኘ በኋላ ነበር (1ኛ ትምህርትን ያንብቡ)። ጳውሎስ አናሲሞስም ታማኝ ክርስቲያን
እንደነበረ ተናግሯል። በተጨማሪም ጳውሎስ በቆላስይስ ስለሚኖሩት ክርስቲያኖች
ሕይወት ለማወቅ ፈልጎ ነበር። ቤተ ክርስቲያኗም በቀላሉ አንድ ሰው መልእክት አስይዛ
ወደ ጳውሎስ መላክ ትችል ነበር። በዚህ መንገድ ጳውሎስ ለክርስቲያኖች የነበረውን
ፍቅር በመግለጽ፣ በኢየሱስ ላይ የነበራቸው እምነት እንዲያድግ ረድቷቸዋል።
ዛሬ ግንኙነታችን እንዳይቋረጥ የሚረዱን ኢንተርኔት፣ ስልኮችና ኮምፒውተሮች አሉን። ስለዚህ ያኔ ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያን አባላትን ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኖቻቸው በላይ ትልቅ ለሆነ ነገር አካል እንደሆኑ እንዲሰማቸው እንዴት እንደረዳቸው በአእምሯችን ለመገመት ልንቸገር እንችላለን። ጳውሎስ አገልጋዮችን ወደ አብያተ ክርስቲያናት ይልክ ነበር። አገልጋዮቹም ከጳውሎስ ዜና ይዘው ይሄዱ ነበር። ከዚያም በኋላ ከአብያተ ክርስቲያናት ደግሞ ለጳውሎስ ዜና ይዘው ይመለሱ ነበር (ቆላ. 4፡7-9)። ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያን አባላት እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነት ቀጣይነት እንዲኖረው ያበረታታቸው የነበረው በሌሎች በምን መንገዶች ነው? ጳውሎስ ምን አይነት ሰላምታ ነበር የላከላቸው? እነዚህ ሰላምታዎችስ ምን መልዕክት ይዘው ነበር? ቆላ. 4:10, 11ን ያንብቡ።
በእነዚህ ሰላምታዎች ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያን አባላት እርስ በርስ የማይቋረጥ
ግንኙነት እንዲኖራቸው ረድቷቸዋል። ጳውሎስ ስለሥራ አጋሮቹ መረጃ ያካፍላቸዋል።
ከእነዚህ ጥቅሶች ማርቆስ የበርናባስ የወንድሙ ልጅ እንደሆነ እንረዳለን። ምናልባት
ማርቆስ ወደ ቆላስይስ ሄዶ ሊሆን ይችላል። ጳውሎስም የማርቆስ ጉዞ የተሳካ እንዲሆን
ሁኔታዎችን ያመቻቻል። አርስጥሮኮስ ከጳውሎስ ጋር ታስሮ ነበር። ሁለቱም የኢየሱስ
ወታደሮች ነበሩ። የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር እንደ ልብስ ለብሰው ነበር (ኤፌ. 6:10,
11)። ጳውሎስና አርስጥሮኮስ ሰዎች ከሰይጣን ኃይል እንዲያመልጡ ለመርዳት አብረው
ይሠሩ ነበር። ከዚያም እነዚህን ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲያገለግሉ
ያስተምሯቸው ነበር (2 ጢሞ. 2፡1–4ን ያንብቡ)። ጳውሎስ ኢዮስጦስንም ያመሰግነዋል።
ኢዮስጦስ የእግዚአብሔር ሠራተኛ እንደሆነ ሊታመኑበት የሚገባ ሰው ነበር። ኢዮስጦስ
የኢየሱስን ወንጌል ሊያካፍላቸው እንደሚችል እምነት ሊጥሉበት ይችሉ ነበር።
እንዲሁም ጳውሎስ አርስጥሮኮስ፣ ማርቆስና ኢዮስጦስ አይሁዳዊ ክርስቲያኖች
እንደሆኑ ይናገራል። ከዚያም ጳውሎስ አይሁዳዊ ስላልሆኑት ሦስት ክርስቲያኖች
ኤጳፍራ፣ ሉቃስና ዴማስ ይናገራል (ቆላ. 4፡12–14)። አይሁዊ በሆኑና ባልሆኑ
ክርስቲያኖች መካከል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንዳንድ ችግሮች ነበሩ። ሆኖም
ጳውሎስ እነዚህ አይሁዳዊ የሆኑና ያልሆኑ ሰዎች በሰላምና በአንድነት አብረው ይሠሩ
እንደነበር ያሳየናል። በተጨማሪም ብዙ አይሁዳዊ ክርስቲያኖች በሥራው ከእርሱ ጋር
ስላልተባበሩ ጳውሎስ አዝኖ ነበር። በዚህ ጊዜ ዮሐንስ ማርቆስ ከጳውሎስ ጋር ነበር።
ከጥቂት ዓመታት በፊት፣ ጳውሎስና በርናባስ ወንጌልን ለመስበክ ባደረጉት የመጀመሪያ
ጉዟቸው ላይ ዮሐንስ ማርቆስ ትቷቸው ሄዶ ነበር (ሐዋ. 13፡13)። አሁን ግን ጳውሎስ
ዮሐንስ ማርቆስን በጣም ያምነው ነበር። በኋላ ላይ ዮሐንስ ማርቆስ ለጳውሎስ ተስፋ
ሰጠው (ሐዋ. 15፡36-40)።
ሰይጣን በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰላም እንዳይኖር ይሰራል። ቤተ
ክርስቲያናችን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገች ስትሄድ፣ በብዙ መልኩ ለውጥ ይታይባታል።
በእነዚህ ለውጦች ስታልፍ፣ ሰይጣን ቤተ ክርስቲያንን በመዋጋት ሁላችንንም በሚጎዳ
መልኩ ሰላምና አንድነቷን ለማደፍረስ ይሞክራል።
የጳውሎስ ህይወትም ሆነ ለእግዚአብሔር የሚሠራው ሥራ እቅድ እንደነበረው ያሳያል (ፊል. 3፡13, 14ን ያንብቡ)። የጳውሎስ የሥራ አጋሮችና የኢየሱስ ተከታዮችም ተመሳሳይ እቅድ ነበራቸው። በሮም ግዛትም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የኢየሱስን ወንጌል በፍጥነት ለማሰራጨት አቅደው ነበር (ቆላ. 1፡23)። እኛም ዛሬ በተመሳሳይ ግለትና ኃይል ልንሰራ ይገባል። ቆላ. 4:12, 13ን ያንብቡ። በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ስለ ምን አይነት እቅድ እናነባለን? ጳውሎስ ይህንን እቅድ እንዴት አድርጎ ፈጸመው?
ቀደም ባለው ትምህርት ላይ እንዳየነው፣ ኤጳፍራ ወንጌልን ለመስበክ ወደ ቆላስይስ
ሳይሄድ አልቀረም። እንዲሁም በአቅራቢያው ወደሚገኙት የሎዶቅያና የኢያራ ከተሞች
ተጉዞ ሊሆን ይችላል (1ኛ ትምህርትን ያንብቡ)። በእርግጠኝነት የኤጳፍራ ሰላምታና ጸሎት
በእነዚህ ከተሞች የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት በተስፋ ሞልቷቸዋል። ጳውሎስ ለአብያተ
ክርስቲያናቱ ኤጳፍራ እንደ ክርስቲያን በእምነታቸው እንዲያድጉ እንደሚጸልይላቸው
ይነግራቸዋል። ኤጳፍራም “በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ
እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል” (ቆላ. 4፡12)። በቀላሉ እንዲስተዋል
ተደርጎ በተጻፈው የእንግሊዝኛው ትርጉም “እግዚአብሔር እንድታደርጉት የሚፈልገውን
ሁሉ ሙሉ በሙሉ እንድትረዱት ይጸልያል” ይላል (ቆላ. 4፡12)። የዚህን ጸሎት የተለያዩ
ክፍሎች በጥንቃቄ እንመልከታቸው።
•“እንድትጠነክሩ”፡- ቃሉ ጸንቶ መቆምንና በእምነታችን አለመናወጥን ያሳያል።
ይህንን ማድረግ የምንችለው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን ስናውቅና የኢየሱስን
ወንጌል ስንተማመን ብቻ ነው (ቆላ. 1፡23)። ጳውሎስ ከሰይጣን ጋር ስለሚደረገው
ተጋድሎና ስለ ማታለያዎቹ ለመናገር “ቁሙ” የሚለውን ቃል ብዙ ጊዜ
ተጠቅሞበታል (ኤፌ. 6፡11)። የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር እንደ ልብስ መልበስ
አለብን። ያን ጊዜ ዲያብሎስንና የክፉ መላእክት ሠራዊቱን ተቋቁመን መቆም
እንችላለን (ኤፌ. 6፡10–18፣ ከ2 ጢሞ. 2፡19 ጋር ያስተያዩ)።
•“ፍጹማን ሊያደርጋችሁ”፡- “ፍጹም” የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ቅዱስ ፍቅር
ማለት ነው። ይህ ፍቅር እኛን ለማዳን ሲል ኢየሱስን በመስቀል እንዲሰቀል
አደረገው (ማቴ. 5፡44, 48)።
•“ሙሉ በሙሉ መረዳት”፡- “ሙሉ በሙሉ” የሚለው ቃል እግዚአብሔር አንድን
ነገር ሙሉ በሙሉ እንድናውቅ እንደሚፈልግ ያሳየናል። አብርሃም እግዚአብሔር
የገባውን ቃል እንደሚፈጽመው ሙሉ እምነት ነበረው (ሮሜ 4፡21)። ጳውሎስ
ወንጌልን በሙላት እንዲሰብክ ጌታ አበረታው (2 ጢሞ. 4፡17)።
•“እግዚአብሔር እንድታደርጉ የሚፈልገውን ሁሉ”፡- “ሁሉ” የሚለው ቃል
ጳውሎስና ኤጳፍራ የቆላስይስ ሰዎች እግዚአብሔር ለሕይወታቸው ያለውን እቅድ
ሁሉ እንዲያውቁ እንደሚፈልጉ ያሳያል። ያን ጊዜ እግዚአብሔርን ያከብሩታል፣
በሁሉም ነገር ያስደስቱታል (ቆላ. 1: 9, 10)።
ቆላ. 4:14, 15ን እና 2 ጢሞ. 4:10, 11ን ያንብቡ። ሉቃስ ከዴማስ የሚለየው እንዴት ነው? የተለየ የሆነውስ ለምንድን ነው?
ዮሐንስ “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድ
የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም” ይለናል (1 ዮሐ. 2:15)። ሉቃስ ለኢየሱስ የነበረው
ፍቅር፣ እስከ ጳውሎስ የሕይወት ፍጻሜ ድረስ፣ ለጳውሎስ ታማኝ እንዲሆን አድርጎታል።
ዴማስ ግን እንደዚህ አልነበረም። ዴማስ በላይ በሰማይ ያለውን ከመውደድ ይልቅ፣
የዚህን ዓለም ነገሮች አብልጦ ይወድ ነበር።
የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ። ኢየሱስ ዳግም እስኪመጣ ስንጠብቅ ሳለ፣ እነዚህ
ጥቅሶች ምን ምክር ይሰጡናል?
1. ማር. 13፡32-37
2. ቲቶ 2፡11-14
3. 2 ጴጥ. 3፡10-14
ኢየሱስም ሆነ ተከታዮቹ እንድንተጋና እንድንጠነቀቅ ደጋግመው ያስጠነቅቁናል።
ኢየሱስ ተመልሶ ስለሚመጣ፣ ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን አለብን። ከተዘጋጀን፣ ምጻቱ ድንገት
አይደርስብንም። የሚያሳዝነው ግን ብዙዎች ልክ ኢየሱስን ይከተሉት እንደነበሩት ሰዎች
ይሆናሉ። ኢየሱስ እንዲተጉና እንዲጸልዩ ነግሯቸዋል (ማር. 14፡38)። ሆኖም ብዙ ሰዎች
ዝግጁ ይሆኑ ዘንድ፣ እግዚአብሔር እንዲያደርጉ የሚጠይቃቸውን አይተገብሩትም።
የልባችሁ ትኩረት ምን ላይ ነው? ለዚህ ጥያቄ የምንሰጠው ምላሽ ለዳግም ምጽአቱ
ዝግጁ እንደሆንን ወይም እንዳልሆንን ይነግረናል። ሁለት ጌቶችን ማገልገል አንችልም።
ኢየሱስን ወይም ሰይጣንን መምረጥ አለብን።
ኢየሱስ ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን በሰጠው መልእክት፣ ዝግጁ እንሆን ዘንድ ምን
ማድረግ እንዳለብን ይነግረናል (ራዕ. 3፡14-22)። በመጀመሪያ ኃጢአታችንን መናዘዝ
አለብን። በሁለተኛ ደረጃ ልባችንን ለኢየሱስ መክፈት አለብን። ኢየሱስ ሕይወታችንን
ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠረው ልንፈቅድለት ይገባል። በሦስተኛ ደረጃ እምነትና ፍቅር
እንዲሰጠን ኢየሱስን መጠየቅ አለብን። ይህ እምነትና ፍቅር በእሳት እንደነጠረ ወርቅ
ነው። ወርቅን በከፍተኛ ሙቀት ስታቀልጡት፣ ቆሻሻዎቹ ሁሉ ይወገዳሉ። ከዚያም
ወርቁ ንጹህ ይሆናል። እሳት በህይወታችን የሚያጋጥሙንን መከራዎችና ፈተናዎች
ሁሉ ያመለክታል። እነዚህ ፈተናዎች ከኃጢአት ጋር የምናደርገውን ተጋድሎ ለማሸነፍና
ኃጢአትን ከልባችን ለማስወገድ ይረዱናል።
ቆላ. 4:16-18ን ያንብቡ፤ ከቆላ. 2: 1-3 ጋር ያነጻጽሩ። ኢየሱስ በራዕ. 3፡
14-22 ለሎዶቅያ የሰጣትን መልዕክት ያሰላስሉ (የትናንቱንም ጥናት ያንብቡ)።
ጳውሎስ ለቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን የጻፈው ደብዳቤ ለሎዶቅያ ሰዎችም እንዲነበብ
ጠይቋል። የጳውሎስ ምክር ለሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት ጠቃሚ የሆነው ለምን ነበር?
በእግዚአብሔር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ፣ ተመሳሳይ ችግሮች በተደጋጋሚ
ይከሰታሉ። ነቢያት እስራኤላውያንን የሐሰት አማልክትን እንዳያመልኩ
አስጠንቅቀዋቸው ነበር። ነቢያት የተለዩ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ነበሩ። ነቢያት
ለእስራኤላውያን የምህረት ደጅ ሳይዘጋ በፊት ኃጢአታቸውን እንዲናዘዙና የሐሰት
አማልክቶቻቸውን እንዲተዉ ነግረዋቸው ነበር። ኢሳይያስ ሕዝቡን እግዚአብሔርን
ይቅርታ እንዲጠይቁ ነግሯቸው ነበር (ኢሳ. 1፡21፣ ኢሳ 1፡16-20)። መጥምቁ ዮሐንስም
ሆነ ኢየሱስ እስራኤላውያንን ኃጢአት መሥራታቸውን እንዲተዉና እግዚአብሔርን
እንዲያገለግሉ ጠይቀዋቸዋል (ማቴ. 3:2, 8–10፣ ማቴ. 4:17፣ ማቴ. 12:33–37)።
የኢየሱስ ተከታዮችም ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልእክት ሰብከው ነበር (ሐዋ. 2: 38፣
ሐዋ. 3: 19፣ ሐዋ. 17: 30፣ 2 ቆሮ. 7: 9, 10)።
ኢሳ. 60፡1–3ን ከራዕ. 18፡1–4 ጋር፣ እንዲሁም ኢሳ. 62:1–5ን ከራዕ.
19:7, 8 ጋር ያነጻጽሩ። በሁለቱ መጻሕፍት ውስጥ ባሉት መልእክቶች መካከል ምን
ተመሳሳይ ነገሮች አሉ?
እግዚአብሔር ሐጢአትን በማጥፋት ሰማይንና ምድርን አንድ ያደርጋል። ነገር
ግን በመልካምና በክፉ መካከል በሚደረገው በታላቁ ተጋድሎ ምክንያት እግዚአብሔር
ይህንን ሥራ በተለያዩ ክፍሎች ያከናውነዋል፡-
1. መስቀሉ፡- በቀራንዮ ላይ ሰይጣን ቅዱሳን መላእክት ለእርሱ የነበራቸውን
እንጥፍጣፊ ፍቅር አጥቷል (ዮሐ. 12፡31)።
2. ኢየሱስ በሰማይ ለእኛ የሚሠራው ሥራ፡- ኢየሱስ በሰማይ ሊቀ ካህናችን ሆኖ
ያገለግላል። ኢየሱስ ለእኛ ረድኤትን ይቀበል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይቀርባል።
“በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን
ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ” ይላል (ዕብ. 13:21)።
3. 1,000 ዓመታት በሰማይ፡- ከዳግም ምጽአቱ በኋላ 1,000 ዓመታትን በሰማይ
እናሳልፋለን። በዚያን ጊዜ፣ ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር የፍርድ ሥራ ለጥያቄዎቻችን
ሁሉ መልስ ይሰጠናል። ከዚያም ኃጢአትና ኃጢአተኞች ሁሉ በዘላለም የእሳት ባሕር
ውስጥ ተቃጥለው ይጠፋሉ። ይህ እሳት መላውን ምድር ያነጻዋል (ራዕ. 21፡8)።
4. የኃጢአት መጨረሻ፡- ኃጢአት ከተወገደ በኋላ፣ እግዚአብሔር በመጨረሻ
ሰማይንና ምድርን በማስታረቅ አንድ ያደርጋቸዋል።
“ህይወታችንን ለኢየሱስ ስናስረክብ፣ በምድር ላይ እንደ
ጸና ግንብ ያደርገናል። ይህ ግንብ በእርሱ እንጂ በሌላ በማንም ቁጥጥር ስር አይደለም።
በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ግን የእግዚአብሔር ተቃዋሚ ናቸው። ህይወታችንን ሙሉ
በሙሉ ለኢየሱስ ስናስረክብ፣ ሰይጣን ሊያጠፋን አይችልም። ስለዚህ ኢየሱስ ሙሉ
በሙሉ እንዲቆጣጠረን መፍቀድ አለብን። ይህችን ምድር ሁለት ሃይሎች ይገዟታል።
ከሁለቱ አንዱን ለማገልገል መምረጥ አለብን። ሰይጣንን ለማገልገል ላንመርጥ
እንችላለን። ሆኖም በእሱ ቁጥጥር ስር እንወድቃለን። ይህም የሚሆነው ኢየሱስን
ለማገልገል ባለመምረጣችን ነው። ከእግዚአብሔርና ከመላእክቱ ጋር ካልተባበርን፣
ሰይጣን ልባችንን ተቆጣጥሮ ማደሪያው ያደርገዋል። ኢየሱስ በልባችን ውስጥ መኖር
አለበት። ከክፋት ጋር በምናደርገው ተጋድሎ ብቸኛው ደህንነታችን የርሱ ህይወት
በልቦናችን ውስጥ መኖሩ ነው። ኢየሱስ ደግሞ በልባችን ውስጥ የሚኖረው፣ ቅዱስና
ታዛዥ በሆነው ህይወቱ ላይ እምነት ሲኖረን ነው። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት
ሊኖረን ይገባል። ይህ ሕያው ግንኙነት፣ ከእኔነትና ከኃጢአት ጋር በምናደርገው ተጋድሎ
ብቸኛው ተስፋችን ነው። ለተወሰነ ጊዜ ብዙ መጥፎ ልማዶችን እንተው ይሆናል።
ለጥቂት ጊዜ ሰይጣንንም እንተወው ይሆናል። ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ህያው
ግንኙነት ከሌለን፣ ሰይጣን መልሶ ይቆጣጠረናል። በየሰከንዷ ልባችንን ሙሉ በሙሉ
ለርሱ ስንሰጥ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ይኖረናል። ስለዚህ ከኢየሱስ ጋር የግል
ግንኙነት ሊኖረን ይገባል። ሁልጊዜ ያለማቋረጥ ከእርሱ ጋር ልንነጋገር ይገባል። ካልሆነ
ግን ሰይጣን ሕይወታችንን ይቆጣጠረዋል፤ በመጨረሻም ፈቃዱን እናደርጋለን።”—
ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 324።
1. ከላይ ያለውን ከኤለን ጂ. ዋይት መጽሐፍ የተወሰደውን ጽሑፍ እንደገና ያንብቡ።
ከላይ ያለውን ከኤለን ጂ. ዋይት መጽሐፍ የተወሰደውን ጽሑፍ እንደገና ያንብቡ።
በመልካም እና በክፉ መካከል ባለው ታላቁ ተጋድሎ ውስጥ ያሉት ሁለት ወገኖች ብቻ
ናቸው። ኢየሱስን ካልመረጥን፣ ከሰይጣን ጎን ነን (ሉቃ. 11፡23)። ይህንን ሃሳብ
ላንወደው እንችላለን። ሆኖም እኛ እንድንወደውና እንድንቀበለው፣ እግዚአብሔር
እውነትን በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረግ አይጠበቅበትም። ይህ
የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ልባችሁንና ፈቃዳችሁን ለኢየሱስ ማስረከብ እንዳለባችሁ
ምን ይነግራችኋል? ይህን ማድረግስ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
2. ራዕ. 14:14–16ን ያንብቡ። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ፣ እግዚአብሔር
ራዕ. 14:14–16ን ያንብቡ። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ፣ እግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስን በቤተ ክርስቲያን ላይ አፈሰሰው። መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ቤተ
ክርስቲያን እንድታድግ አደረገ። ይህ የመጀመሪያው ዝናብ ይባላል። በመጨረሻው
ዘመንም እግዚአብሔር መንፈሱን (የኋለኛውን ዝናብ) በቤተ ክርስቲያን ላይ
እንደገና ያፈሰዋል። መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን የእግዚአብሔርን ሥራ በምድር
ላይ እንድታጠናቅቅ ይረዳታል። ራዕ. 14:12 ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት
የሚያሳየን እንዴት ነው?
ማሳሰቢያ
ድርጅቱ