የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዘፍ. 3፡17-24 ፣ዘዳ.
6:3፣ ኢያሱ 13:1-7፣ ዕብ. 12:28፣ ዘሌ. 25:1-5፣ 8-13፣ ሕዝቅኤል 37:14፣ 25።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እናንተ በተስፋ የምትኖሩ እስረኞች ወደ
ምሽጎቻችሁ ተመለሱ፤ አሁንም ቢሆን ሁለት እጥፍ አድርጌ
እንደምመልስላችሁ እናገራለሁ” (ዘካርያስ 9፡12)።
መጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 13-21 ለእስራኤል ነገዶች የተመደበውን
መሬት የሚገልጹ ረዣዥም መልክአ ምድራዊ የድንበር
ምልክቶችን የያዙ ናቸው። ለዚህ ዘመን አንባቢ እነዚህ ዝርዝሮች
ፋይዳ የሌላቸው ሊመስሉ ቢችሉም ዛሬ ለኛ ጠቃሚ በሆነው ስለ ተስፋይቱ
ምድር ባለን ስነ-መለኮታዊ ግንዛቤ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በእነዚህ ተጨባጭ
ዝርዝሮች፣ እግዚአብሔር ምድሪቱ ሕልም እንዳልሆነች እስራኤላውያንን
ሊያስተምራቸው ፈልጎ ነበር። በጣም በሚጨበጥ፣ በሚለካ መልኩ ቃል
ተገብቶላቸው ነበር። ነገር ግን በዚያ የተስፋ ቃል ላይ የተግባር እርምጃን
በመራመድ ተስፋውን እውን ማድረግ ነበረባቸው።
ማለትም አዎ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ለመፈጸም
ምድርን ርስት አድርጎ ሊሰጣቸው ተዛጋጅቷል። “እነሆ፥ ምድሪቱን
በፊታችሁ አድርጌአለሁ ግቡ፥ እግዚአብሔር ለእነርሱ ከእነርሱም በኋላ
ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም
የማለላቸውንም ምድር ውረሱ።” (ዘዳ. 1:8)። ነገር ግን፣ እነሱም የሚጫወቱት
ሚና ነበራቸው።
በዚህ ሳምንት ከተስፋይቱ ምድር ጋር የተያያዙ አንዳንድ ሥነ-
መለኮታዊ ፅንሰ-ሀሳቦችን እና በኢየሱስ ውስጥ የሚገኙትን የተስፋ ቃሎች
ሁሉ የራሳቸው ለማድረግ ለሚፈልጉ ሰዎች ያላቸውን መንፈሳዊ አንድምታ
እንመለከታለን።
ለህዳር 20 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ዘፍጥረት 2፡15 እና ዘፍጥረት 3፡17-24ን ያንብቡ። የመጀመሪያዎቹ ጥንዶች የሚኖሩበትን ቦታ በተመለከተ የውድቀቱ ውጤት ምን ነበር?
እግዚአብሔር በፍጥረት ጊዜ አዳምንና ሔዋንን በተትረፈረፈና ውበት
ባለው ፍጹም አካባቢ አስቀምጧቸው ነበር። የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት
ሁሉንም ሥጋዊ ፍላጎቶቻቸውን ሊያሟላላቸው በሚችል ውብ የመኖሪያ ቦታ
ላይ ፈጣሪያቸውን ያገኙ ነበር። ከተነገረው ከእግዚአብሔር ቃል በተጨማሪ፣
ኤደን ገነት ስለ እግዚአብሔር ባህሪ እና እሱ ስላሰበላቸው ሕይወት ጉልህ ግንዛቤ
ያገኙበት የመማሪያ ማዕከል ነበረ። ስለዚህ፣ ከፈጣሪያቸው ጋር የነበረውን
በመተማመን ላይ የተመሠረተውን ግንኙነት ባቋረጡ ጊዜ፣ ከኤደን ገነት ጋር
ያላቸው ግንኙነትም እንዲሁ ተለወጠ፣ እናም የተቋረጠ ግንኙነት ምልክት ሆኖ
የአትክልት ስፍራውን መልቀቅ ነበረባቸው። እግዚአብሔር የሰጣቸውን ግዛት
አጡ። ስለዚህ፣ ኤደን ገነት የተትረፈረፈ ህይወት ምልክት ሆነ፣ እና በተስፋይቱ
ምድር ሃሳብ ላይ ንድፈ-ሀሳቦቹን እንደገና እንመረምራቸዋለን።
የኃይማኖት አባቶች የምድሪቱን ተስፋ የተቀበሉት እንዴት ነበር? (ዘፍ. 13:14-
15፣ ዘፍ. 26:3፣ 24፣ ዘፍ. 28:13ን ይመልከቱ።) ለእኛ እንደ አድቬንቲስትነታችን
የተስፋ ቃላቱ ወራሾች ሆነን መኖር ማለት ምን ማለት ነው (ዕብ. 6:11-15)?
አብርሃም እግዚአብሔር ባሳየው ምድር እንደገባ፣ ምድሪቱ በእምነት
ለእርሱና ለዘሩ የተስፋው ቃል ምድር ሆነች። ለ400 ዓመታትም የቃል
ኪዳን ምድር ሆና ቆየች። የሃይማኖት አባቶች የመሬቱ ባለቤት አልነበሩም።
ለልጆቻቸው ርስት አድርገው ሊሰጡ በሚችሉበት መንገድ የእነርሱ
አልነበረም። ይልቁንም ዔድን ገነት የእርሱ እንደነበረች ያችም ምድር
የእግዚአብሔር ነበረች። አዳምና ሔዋን በመጀመሪያ በኤደን ገነት እንዲገኙ
ምንም አስተዋጽዖ እንዳላደረጉ፣ እስራኤልም ምድሪቱ ለነርሱ እንድትገባቸው
ምንም ያዋጡት ነገር የለም። የተስፋይቱ ምድር በእርሱ ተነሳሽነት ላይ
የተመሰረተች የእግዚአብሔር ስጦታ ነበረች። እስራኤል በምድሪቱ ላይ
ምንም የተፈጥሮ መብት አልነበራትም ወይም የምድሪቱ ባለቤትነት ይገባኛል
የምትልበት መሠረት አልነበራትም (ዘዳ. 9፡4-6)። ሕዝቡ ሊይዟት የሚችሉት
በእግዚአብሔር ቸርነት(ፀጋ) ብቻ ነበር።
የእምነት አባቶች የተስፋው ቃላት እስኪፈጸሙ ድረስ ወራሾች ነበሩ።
እኛ እንደ ክርስቶስ ተከታዮች “በእምነትና በትዕግሥት የተስፋውን ቃል
የሚወርሱትን ከመሰልን” (ዕብ. 6፡12) የሚፈጸሙትን የሚሻሉ ተስፋዎችን
ወርሰናል (ዕብ. 8፡6)።
ዘጸአት 3:8፣ ዘሌዋውያን 20:22፣ ዘሌዋውያን 25:23፣ ዘኍልቍ 13:27፣ ዘዳግም 4:1፣ 25-26፣ ዘዳግም 6:3፣ እና መዝሙረ ዳዊት 24:1 በእግዚአብሔር፣ በእስራኤልና በተስፋይቱ ምድር መካከል ምን ልዩ ዝምድና ነበረ?
በመሠረታዊ ደረጃ መሬት ለአንድ ሕዝብ አካላዊ ማንነትን ይሰጣል።
ብሔረሰቡን በአንድ ቦታ በማስቀመጥ የብሔረሰቡን ሥራ እና አኗኗር
ይወስናል። ባሮች የዘር ግንድ የሌላቸው እና ከየትኛውም ቦታ ጋር የማይዛመዱ
ሲሆኑ ሌላን ሰው በሥራቸው ውጤት ማስደሰት ይጠበቅባቸው ነበር። የመሬት
ባለቤት መሆን ማለት ነፃነት ማግኘት ማለት ነው። የተመረጡት ሰዎች ማንነት
በምድሪቱ ውስጥ ከሚኖሩበት ቦታ ጋር በጥብቅ የተያያዘ ነበር።
በእግዚአብሔር፣ በእስራኤል እና በምድሪቱ መካከል ልዩ ግንኙነት
ነበር። እስራኤላውያን ምድሪቱን ከእግዚአብሔር የተቀበሉት በስጦታ
እንጂ በማይሻር መብት አልነበረም። የተመረጡት ሰዎች ከያህዌ ጋር የቃል
ኪዳን ግንኙነት እስካላቸው ድረስ እና የቃል ኪዳኑን ትእዛዛት እስካከበሩ
ድረስ መሬቱን ሊይዙ ይችላሉ። በሌላ አነጋገር ምድሩንና በረከቶቿን ያለ
እግዚአብሔር በረከት ማግኘት አይችሉም ነበር።
በተመሳሳይም ምድሪቱ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን በተሻለ
መንገድ እንዲረዱበት እንደ መነፅር አገልግላለች። በምድሪቱ ውስጥ መኖር
ሁልጊዜ ታማኝ፣ ተስፋ ሰጪ እና ታማኝ አምላክን ያስታውሳቸው ነበር።
ምድርም እስራኤልም የሕልውናቸው መነሻና መሠረት ከሆነው ከእግዚአብሔር
ተነሳሽነት በቀር አይኖሩም ነበር። እስራኤላውያን በግብፅ በነበሩበት ወቅት
የአባይ ወንዝ እና የመስኖ ሥራ ከጠንካራ ሥራ ጋር ተዳምሮ ለዕለት ተዕለት
ኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ሰብል ማስገኘት ችሏል። ከነዓን ግን የተለየ ነበር።
አዝመራቸው እንዲበዛ በዝናብ ላይ የተመሰረቱ ሲሆን አየሩን መቆጣጠር
የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነበር። ስለዚህ ምድሪቱ እስራኤላውያን
በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን የማያቋርጥ ጥገኝነት አስታውሳለች።
እስራኤላውያን ምድሪቱን ከእግዚአብሔር በስጦታ ቢቀበሉም፣
በዋናነት እግዚአብሔር ራሱ ባለቤቷ ነበር። እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ባለቤት
እንደመሆኑ (መዝ. 24፡1) ምድሪቱን ለእስራኤል የመመደብ ወይም የመውሰድ
መብት አለው። እግዚአብሔር የምድሪቱ ባለቤት ከሆነ፣ እስራኤላውያን
እና፣ በአጠቃላይ፣ ሁሉም ሰዎች እንግዶች እና መጻተኞች ናቸው፣ ወይም፣
በዘመናዊ ቃላት፣ ሁላችንም በእርሱ ምድር የምንኖር የእግዚአብሔር የረጅም
ጊዜ እንግዶች ነን።
በ1ኛ ጴጥሮስ 2፡11 እና ዕብራውያን 11፡9-13 መሠረት፣ ቀያሽ እና ፈጣሪዋ ራሱ
እግዚአብሔር የሆነችውን ከተማ እየጠበቁ እንደ እንግዳና መጻተኛ መኖር
ማለት በግል ለእናንተ ምን ማለት ነው?
ኢያሱ 13:1-7ን ያንብቡ። የከነዓን ምድር የእግዚአብሔር ስጦታ ብትሆንም ምድሪቱን ከመያዝ ጋር ከመጡ ተግዳሮቶች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ነበሩ?
እስራኤላውያን ለብዙ መቶ ዓመታት በባርነት ይኖሩ ስለነበር
የውትድርና ችሎታቸው ምድሪቱን ለመቆጣጠር በቂ አልነበረም። የግብፃውያን
ጌቶቻቸው፣ የተዋጣለት እና የታጠቀ ሠራዊታቸው እንኳን ምድሪቱን በዘላቂነት
ሊቆጣጠሩት የማይችሉት ነበር። በቅጥር የተከበቡት ከተማዎች የማይበገሩ
ስለነበሩ ግብፃውያን ከነዓንን በሙላት አሸንፈው አያውቁም። አሁን የቀድሞ
ባሪያዎችን የያዘ ሕዝብ የቀድሞ ጌቶቻቸው ሊቆጣጠሩ ያልቻሉትን ምድር
እንዲቆጣጠር ተነገረው። መሬቱን መውረስ ካለባቸው፣ በራሳቸው ጥረት
ሳይሆን በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ሊሆን የሚችል ነበር።
መጽሐፈ ኢያሱ ከምዕራፍ 13-21 ምድሪቱ ለተለያዩ የእስራኤል ነገዶች
እንደተከፋፈለች ይናገራል። ይህ ድልድል ለእስራኤል የተከፋፈለውን ብቻ
ሳይሆን በዚያ ግዛት ውስጥ ምን ያህል ያልተያዘ ምድር እንዳለም ይነግራል።
እስራኤላውያን አምላክ ርስት አድርጎ በሰጣቸው ምድር በሰላም መኖር
ይችላሉ። በእግዚአብሔር ባለቤትነት ስር ባለችው ምድር ትክክለኛ እና ህጋዊ
ተከራዮች ነበሩ። ሆኖም የእግዚአብሔር ተነሳሽነት በሰዎች ምላሽ መረጋገጥ
አለበት። የመጽሐፉ የመጀመሪያ አጋማሽ እግዚአብሔር ከነዓናውያንን
በማባረር ምድሪቱን እንዴት እንደ ሰጣቸው የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛው
አጋማሽ እስራኤል መሬቱ ላይ በመስፈር እንዴት ምድሪቱን እንደ ወሰደች
ዘግቧል።
ይህ የመውረስ ውስብስብነት የመዳናችንን ሁኔታ ያሳያል። ከእስራኤል
ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ መዳናችንን ለማግኘት ምንም ነገር ማድረግ
አንችልም (ኤፌ. 2፡8፣ 9)። ለእስራኤላውያን ከእርሱ ጋር ባላቸው የቃል ኪዳን
ዝምድና ላይ በመመስረት ምድሪቱ የእግዚአብሔር ስጦታ እንደነበረች ሁሉ
ድነት ስጦታ ነው። በእርግጥም በሥራቸው ላይ የተመሰረተ አልነበረም (ዘዳ.
9፡5ን ይመልከቱ)።
ሆኖም፣ እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ስጦታ እንዲደሰቱ፣ በምድሪቱ
ውስጥ ከመኖር ጋር የተያያዙ ሁሉንም ኃላፊነቶች መወጣት እንደነበረባቸው
ሁሉ እኛም የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች የመሆንን መስፈርቶች በፍቅር
በመታዘዝ የመቀደስን ሂደት ልናልፍ ይገባናል። ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ
ባይሆንም ምድሪቱ በጸጋ ለነርሱ መሰጠቷና የእኛ በጸጋ መዳን መካከል ያለው
ትይዩነት በቂ ነው። አስደናቂ ስጦታ ተሰጥቶናል ነገርግን ካልተጠነቀቅን
ልናጣው የምንችለው ነገር ነው።
በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች ልክ የተስፋይቱን ምድር እንደመያዝ የሆኑ
ተመሳሳይ ፈተናዎች የሚያጋጥሟቸው እንዴት ነው? (ፊል. 2:12፣ ዕብ. 12፡28
ይመልከቱ)።
ምድሪቱ እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ የእስራኤል ሕልውና ማዕከል ስለነበረች ሙሉ በሙሉ ልትከፋፈል አልቻለችም። የጥቂት መሪ ልሂቃኖች ይዞታ እንዳይሆን በነገድ፣ በጎሳ እና በቤተሰብ መከፋፈል ነበረበት (ዘኍ. 34፡13-18)። ዘሌዋውያን 25:1-5፣ 8-13ን ያንብቡ። የሰባተኛ ዓመት ዕረፍት እና የኢዮቤልዩ ዓመት ዓላማ ምን ነበር?
ዜጐች ምድራቸውን እያጡ የፈርዖን አገልጋይ ከሚሆኑባት ግብፅ
በተቃራኒ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ያለው ዓላማ ለዘላለም መብት
አልባ እንዳይሆኑ ነበር። መጀመሪያ ከተሰጠው ዘር እና ቤተሰብ ውጭ ማንም
የመሬቱ ባለቤት ሊሆን አይችልም። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እንደ እግዚአብሔር
እቅድ፣ ምድሪቱ በጥሬው ፈጽሞ ልትሸጥ አትችልም፡ ልትከራይም የምትችለው
እስከሚቀጥለው ኢዮቤልዩ ድረስ ባሉት ዓመታት በተቀመጠው ዋጋ መሠረት
ብቻ ነው። ስለዚህ፣ የአባቶቹን መሬት “ለመሸጥ” የተገደደ ሰው ዘመዶች
ከኢዮቤልዩ በፊት እንኳን የመቤዠት ግዴታ ነበረባቸው (ዘሌ. 25፡25)።
የምድሪቱ ክፍፍል ወደ እግዚአብሔር ልብ ውስጥ የሚገቡበት
መስኮት ሆነ። እንደ ሰማያዊ አባታችን፣ ልጆቹ ለሌላቸው ለጋስ እንዲሆኑ እና
መሬቶቻቸው በየሰባተኛው ዓመት ለነርሱ እንዲመግብ ይፈልጋል። ሰባተኛው
ዓመት የሰንበት ትእዛዝን መርህ በሰፊው ይተገብራል። የመሬት ባለቤትነቱ
ለታታሪው ከመስጠት እና ከማበረታታት በተጨማሪ የገንዘብ ችግር
ለሚገጥማቸው ሰዎች አክብሮት እና ደግነት እንዲደረግላቸው ይጠይቃል።
የመሬት ባለቤትነት ሕግ እያንዳንዱ እስራኤላዊ ከውርስ ወይም በራስ
ጥፋት ከሚመጡ ጨቋኝ ሁኔታዎች ነፃ የመውጣትና በሕይወታቸው ውስጥ
አዲስ ጅምር እንዲፈጠር ዕድል ሰጥቷቸዋል።
በመሰረቱ፣ ይህ የወንጌል ዋና አላማ ነው፡ በሀብታምና በድሀ፣ በአሰሪና
በሰራተኛ፣ ብዙ በተጠቀመ እና አነስተኛ ጥቅም ባገኘ መካከል ያለውን ልዩነት
ለማጥፋት፣ የእግዚአብሔር ፀጋ ሙሉ በሙሉ እንደሚያስፈልገን በመገንዘብ
ሁላችንንም እኩል ያደርገናል።
እንደ አለመታደል ሆኖ፣ እስራኤል እግዚአብሔር ያስቀመጠውን
መመሪያ ሳትጠብቅ ቀረች፡ እናም ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ፣ ካልታዘዙ
ምድሪቱ እንደሚወረስባችው የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ተፈጽሟል (2ዜና. 36፡
20-21)።
የእስራኤላውያን የመሬት ክፍፍልና የሰንበት መሠረታዊ ሥርዓቶች በአምላክ
ፊት ሁላችንም እኩል መሆናችንን የሚያስታውሱን እንዴት ነው? ብዙ
ማህበረሰቦችን እያስጨነቀ ያለውን የአግበስባሽነት አዙሪት “አይሆንም”
እንድንል ሰንበት ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?
ኤርምያስ 24:6፣ ኤርምያስ 31:16፣ ሕዝቅኤል 11:17፣ ሕዝቅኤል 28:25፣ እና ሕዝቅኤል 37:14፣ 25 እግዚአብሔር የእስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር መመለስን በተመለከተ የገባው ቃል ምን ነበር? ፍጻሜውን ያገኘውስ እንዴት ነበር?
እስራኤላውያን በባቢሎን ግዞት ወቅት ዘር አልባ የመሆንን አሳዛኝ
እውነታ ብቻ ሳይሆን ከአምላክ ጋር የነበራቸው ምድሪቱን በመውረስ ላይ
ብቻ የማይገደበውን ግንኙነትም አጡ። እስራኤላውያኑ ኃጢአታቸውን
ሲናዘዙ፣ ንስሐ ገብተው፣ በፍጹም ልባቸው ጌታን ሲፈልጉ፣ እግዚአብሔር
እንደገና የገባውን ቃል ፈጸመ፡ እናም የመልሶ ማቋቋም ምልክት እንዲሆን
ወደ አገራቸው መለሳቸው። ይህም ማለት በምድሪቱ ላይ ሳይሆኑ እንኳን
አምላካቸው ነበር።
ነገር ግን፣ እስራኤል ምድሪቱን ለዘላለም እንደሚወርሱ የተገባው
ቃል ቅድመ ሁኔታ እንደነበረው (ዘዳ. 28:63- 64፣ ኢያሱ 23:13፣ 15፣ 1
ነገ. 9:7፣ 2 ነገሥት 17:23፣ ኤር. 12:10-12)፣ ከምርኮ በኋላም እስራኤልን
መልሶ ለማቋቋምና ምድሪቱ እንደምትበለጽግ የተገባው ቃል እንዲሁ ነበር።
በተመሳሳይ፣ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ወደፊት የዳዊት ዘር የሆነው ንጉሥ
የሚያመጣውን ተሃድሶ ጠቁመዋል (ኢሳ. 9:6-7፣ ዘካ. 9:9፣ 16)። ይህ ተስፋ
የተፈጸመው በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት፣ ሞት እና ትንሣኤ ነው፤ በእርሱም
ለጥንቷ እስራኤል የተገቡት ተስፋዎች ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ።
በአዲስ ኪዳን የተስፋይቱ ምድር በቀጥታ ባትጠቀስም የእግዚአብሔር
ተስፋዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንደተፈጸሙ ተነግሮናል (2ቆሮ. 1፡20፣
ሮሜ. 15፡8)። ስለዚህ፣ በክርስቶስ ብርሃን፣ ምድሪቱ እንደገና ትተረጎማለች፣
እናም እግዚአብሔር ለታማኝ ህዝቡ እዚህ ፣ አሁን (ኤፌ. 2፡6) እና በኋላም
ሊሰጣቸው ያቀደው መንፈሳዊ በረከቶች ምልክት ሆነች።
በምድሪቱ ላይ ያለው የዕረፍት፣ የመትረፈረፍ እና ደህንነት መለኮታዊ
ተስፋ ዋነኛ ፍጻሜ የሚሆነው ከኃጢአትና ከሚያስከትላቸው መዘዞች ነፃ
በወጣች በአዲሲቱ ምድር ላይ ነው። ከዚህ አንጻር፣ እንደ ክርስቲያኖች፣
ተስፋችን ክርስቶስ ተመልሶ እንደሚመጣ በገባው የተስፋ ቃል ላይ የተመሰረተ
ነው፣ እናም በሰማይ ከ1,000 ዓመታት ቆይታ በኋላ፣ ዘላለማዊ መንግሥቱን
በምድር ላይ በአዲስ መልክ ያቋቁማል። ይህ ስለ መሬቱ የተሰጡ ተስፋዎች
ሁሉ ዋነኛ ፍጻሜ ይሆናል።
ዮሐንስ 14፡1-3፣ ቲቶ 2፡13 እና ራዕይ 21፡1-3ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች
ውስጥ ምን ዋነኛ ተስፋ እናገኛለን? የኢየሱስ ሞትስ ለዚህ ተስፋ ፍጻሜ ዋስትና
የሚሰጠው ለምንድን ነው?
ታላቁ ተጋድሎ ከሚለው መጽሐፍ ውስጥ “ጦርነቱ
አብቅቷል” የሚል ርዕስ ያለውን ምዕራፍ ያንብቡ።
“በከተማይቱ ደጅ በገባን ጊዜ ለዘለአለም እንድናለን:: ያኔ ለዘላለም
ስለዳንን ልንደሰት እንችላለን:: እስከዚያ ድረስ ግን የሐዋርያውን ትእዛዝ
ልንጠብቅ እና “ወደ ዕረፍቱ ለመግባት የተስፋው ቃል ሲቀር ማንኛችንም
ብንሆን ምንም የሚጎድለን እንዳይመስለን መፍራት አለብን” (ዕብ. 4: 1). ወደ
ከነዓን መግባታቸው የእስራኤልን ልጆች ወደ ተስፋይቱ ምድር ወደ ወይን
እርሻዎች እና ወደ ወይራ ዛፎች አላመጣቸውም, እነሱ በእውነት የራሳቸው
ሊያደርጉት የሚችሉት በመምራት ፣ ቅድመ ሁኔታዎችን በማክበር ፣ በአምላክ
ላይ ህያው እምነት በማሳየት እና ለራሳቸው የገባውን ቃል በማስማማት
ነው።”—ኤለን ጂ ዋይት
“በመጽሐፍ ቅዱስ የዳኑ ርስት ‘ሀገር’ ተብሏል ዕብራውያን 11፡14-
16 በዚያ ሰማያዊ እረኛ መንጋውን ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ ይመራል
የሕይወትም ዛፍ በየወሩ ፍሬውን ይሰጣል የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ አገልግሎት
የሚውሉ እንደ ብርሌ የሚያበሩ ፈሳሾች በአጠገባቸውም ለእግዚአብሔር
መንገድ የሚውለበለቡ ዛፎችን ይዘረጋል። የተንጣለሉ ሜዳዎች ወደ ውበት
ኮረብቶች ያመጡታል፣ እና የእግዚአብሔር ተራሮች ከፍ ያሉ ከፍታ ቦታዎች
ላይ፣ ከህያዋን ጅረቶች አጠገብ፣ የአምላክ ሕዝቦች፣ ረጅም ፒልግሪሞች እና
ተቅበዝባዦች መኖሪያ ያገኛሉ።”—The Great Controversy, ገጽ. 675.
1. ስለ ተስፋይቱ ምድር በዮሐንስ 10፡10 ላይ ክርስቶስ ለተከታዮቹ የገባውን
ስለ ተስፋይቱ ምድር በዮሐንስ 10፡10 ላይ ክርስቶስ ለተከታዮቹ የገባውን
የተትረፈረፈ ሕይወት ምልክት እንደሆነ አስብ። በተትረፈረፈ ምድር
ውስጥ የመኖር ጥቅሞች የመዳንን በረከቶች የሚገልጹት እንዴት ነው?
2. የምድር ዜጋ መሆን እና የተወሰነ የአኗኗር ዘይቤ በመምራት መካከል
የምድር ዜጋ መሆን እና የተወሰነ የአኗኗር ዘይቤ በመምራት መካከል
ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? አንዱ ሌላውን የሚነካው እንዴት ነው?
የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች መሆን አንዳንድ እንድምታዎች ምንድን
ናቸው?
3. ሰዎች እንደመሆናችን መጠን በሌሎች ተስፋዎች እና አንዳንዴም ለራሳችን
ሰዎች እንደመሆናችን መጠን በሌሎች ተስፋዎች እና አንዳንዴም ለራሳችን
በገባናቸው ተስፋዎች እናዝናለን። በአምላክ ተስፋዎች መተማመን
የምትችለው ለምንድን ነው?
4. የአዲሲቱ ምድር ተስፋ በእርግጥም ሆነ በተጨባጭ መንገድ የወደፊት
የአዲሲቱ ምድር ተስፋ በእርግጥም ሆነ በተጨባጭ መንገድ የወደፊት
ሕይወታችን አካል ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?