የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ኢያሱ 5:13-15፣ ኢሳ.
37:16፣ ራእይ 12:7-9፣ ዘዳ. 32:17፣ ዘጸ. 14:13-14፣ ኢያሱ 6፡15-20።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና
እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያ በፊት
ከዚያም በኋላ አልነበረም።” (ኢያሱ 10፡14)
የመጽሐፈ ኢያሱን ገፆች ስናነብ፣ በእግዚአብሔር ትእዛዝ፣ በእግዚአብሔር
ስም እና በእግዚአብሔር ረዳትነት የተካሄዱትን ኃይለኛ ወታደራዊ
ዘመቻዎች እናገኛለን። ከከነዓን ወረራ ጀርባ እግዚአብሔር እንዳለ
የሚገልፀው ኃሳብ በኢያሱ መጽሐፍ ውስጥ ሰፍኗል፤ ይህ ደግሞ በተራኪው
ቃላት (ኢያሱ 10:10-11)፣ በራሱ በእግዚአብሔር ቃላት (ኢያሱ 6:2፣ ኢያሱ
8:1)፣ በኢያሱ ቃላት (ኢያሱ 4:23-24፣ ኢያሱ 8፡7)፣ በረዓብ ቃላት (ኢያሱ
2:10)፣ በሰላዮቹ (ኢያሱ 2፡24)፣ እና በህዝቡ ቃላት (ኢያሱ 24፡18) ተደጋግሞ
ተነግሯል። የነዚህ ኃይለኛ ግጭቶች አነሳሽ እግዚአብሔር ራሱ መሆኑን
ይናገራል።
ይህ እውነታ የማይቀሩ ጥያቄዎችን ያስነሳል። በብሉይ ኪዳን ዘመን
እግዚአብሔር በመረጣቸው ሰዎች እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች መፈፀማቸውን
እንዴት እናስተውላቸው? የብሉይ ኪዳንን ተአማኒነት፣ ሥልጣንና ታሪካዊነት
ወደጎን ሳናደርግ “ተዋጊ” የሆነ አምላክን ከፍቅር ባህሪው ጋር ማስታረቅ
የምንችለው እንዴት ነው?
በዚህ እና በሚቀጥለው ሳምንት፣ በመጽሐፈ ኢያሱ እና በሌሎች
ቦታዎች ላይ በመለኮት የታዘዙ ጦርነቶች ላይ ያለውን አስቸጋሪ ጥያቄ
እንመረምራለን።
ለጥቅምት 15 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ኢያሱ 5:13-15ን ያንብቡ። ይህ ጽሁፍ ስለ ከነዓን ድል የኋላ ታሪክ ምን ይላል?
እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግሮ የጠላትን ምድር ረገጠ። የኢያሪኮ ግንብ
በፊታቸው ቆሟል፤ በሮቿም በጥብቅ ተዘግተዋል (ኢያሱ 6፡1)። በዚህ ጊዜ
ህዝቡ የትኛውንም የትግል ስልት አያውቁም። ከሁሉም በላይ የሚያስጨንቀው
ደግሞ እስራኤል ረጅም ከበባን ለመቋቋም እና የተመሸገች ከተማን ለመያዝ
በእጃቸው የነበረው የጦር መሣሪያ ወንጭፍ፣ ጦር እና ቀስቶች ብቻ ነበሩ።
ኢያሱ የእንግዳውን ማንነት በተመለከተ ያነሳቸው ጥያቄዎች
“አይደለሁም” የሚል ግልጽ ያልሆነ መልስ አግኝተዋል። የእንግዳው መልስ
በኢያሱ ወደተገለፁት ምድቦች (ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን) ለመግባት
ፈቃደኛ አለመሆኑን ያሳያል። በሌላ አነጋገር የመጨረሻው ጥያቄ እሱ ከኢያሱ
ጎን ነው ወይ አይደለም ሳይሆን ኢያሱ ከእንግዳው ጎን ነው ወይ? የሚለው
ይሆናል።
ኢያሱ 5:14-15ን ከ2 ነገሥት 6:8-17፣ ነህምያ 9:6 እና ኢሳይያስ 37:16 ጋር
ያነፃፅሩ። ስለ እግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ማንነት ምን ተማራችሁ?
በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ”
የሚለው አገላለጽ ልዩ ቢሆንም “አዛዥ” እና “ሠራዊት” የሚሉት ቃላት ጥምረት
ሁልጊዜ የሚያመለክተው ወታደራዊ መሪን ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ
“ሠራዊት” የሚለው ቃል ወታደሮችን፣ መላእክትን ወይም የሰማይ አካላትን
ሊያመለክት ይችላል።
በሥጋ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ክርስቶስ ለኢያሱ የተገለጠለት
እንደ አጋር ወይም እንደ የእስራኤል ሠራዊት አዛዥ ሳይሆን የብዙ የማይታዩ
እና ኢያሱ ከከነዓናውያን ጋር ካለው ጦርነት በበለጠ ታላቅ ጦርነት ውስጥ
የሚሳተፉ ቅዱሳን መላእክት ሠራዊት አዛዥ ሆኖ ነው። የኢያሱ መልስ ስለ
አዛዡ ማንነት ያለውን ግንዛቤ በግልፅ ያሳያል። እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር
እኩል ነው፣ ኢያሱም አክብሮቱንና አምልኮውን ለመግለፅ በፊቱ ሰገደ(ኢያሱ
5፡14፣ ዘፍ. 17፡3፣ 2 ሳሙ. 9፡6፣ 2 ዜና. 20፡18)። ኢያሱም የሠራዊት አምላክ
ራሱ የተሳተፈበት እጅግ ታላቅ የሆነ ግጭት ውስጣዊ አካል ለሆነ ወታደራዊ
ዘመቻ የውጊያ ስልቱን ለመቀበል ተዘጋጀ።
“የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ” ሕዝቡን ለመከላከል እየተንቀሳቀሰ እንዳለ
ማወቃችን ምን ማጽናኛ ይሰጠናል?
ማወቃችን ምን ማጽናኛ ይሰጠናል?
ኢያሱ ጦርነቱ የአንድ ትልቅ ግጭት አካል እንደሆነ ተረድቷል። እግዚአብሔር ራሱ ስለሚዋጋበት ጦርነት ምን ያህል እናውቃለን? ራእይ 12:7-9ን ፣ ኢሳ. 14፡ 12-14፣ ሕዝ. 28፡11-19፣ እና ዳን. 10፡12-14ን ያንብቡ።
አምላክ አጽናፈ ዓለም የመምረጥ ነፃነት በሰጣቸው ፍጥረታት
እንዲሞላ አድርጓል፤ ይህ ደግሞ መውደድ እንዲችሉ ቅድመ ሁኔታ ነበር።
በእግዚአብሔር ፈቃድ መሰረት ለመስራት ወይም ለመቃወም መምረጥ
ይችላሉ። ከኃያላን መላእክት አንዱ የሆነው ሉሲፈር በእግዚአብሔር ላይ
ዐመፀ፣ ብዙ መላእክትንም ከእርሱ ጋር ወሰደ።
አንዳንድ ተንታኞች የኢሳይያስ 14ቱን ትንቢት በባቢሎን ንጉሥ
የሕዝቅኤል 28ቱን ትንቢት በጢሮስ ገዥ ብቻ ለመገደብ ቢሞክሩም ኢሳይያስና
ሕዝቅኤል በሰማይ የተካሄደውን ግጭት አመላክተዋል። በመጽሐፍ ቅዱሳዊው
ጽሑፍ ውስጥ ከምድራዊው ከፍ ያለ እውነታን የሚያመለክቱ ግልጽ ጠቋሚዎች
አሉ። የባቢሎን ንጉሥ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ በሰማይ እንዳለ ሆኖ ነው
የተገለጠው (ኢሳ. 14:12-13)፣ የጢሮስ ንጉሥ ደግሞ በእግዚአብሔር ቅዱስ
ተራራ ላይ በኤደን እንደ ጠባቂ ኪሩብ ሆኖ ነው የተገለፀው (ሕዝ. 28፡12-15)።
ስለ ባቢሎንና ስለ ጢሮስ ነገሥታት ይህ ሁሉ እውነት አይደለም።
ስለ ምድራዊ ነገሥታትም ነቀፋ የሌለባቸውና “ፍፁም ውበትን
የተላበሱ” ነበሩ ማለት አይቻልም። ስለዚህ፣ እነዚህ ገፀ-ባሕርያት ከባቢሎን
እና ከጢሮስ መንግሥታት ባሻገር ያመለክታሉ።
ኢሳይያስ ከቅርብ ታሪካዊ አውድ በላይ ትርጉም ያለው “ምሳሌን”
(በዕብራይስጡ ማሻል) ነው እየተናገረ ያለው። በዚህ ሁኔታ የባቢሎን ንጉሥ
የአመፅ፣ በራስ ብቃት የመታበይ እና የኩራት ምሳሌ ሆኗል። በተመሳሳይም
ሕዝቅኤል በጢሮስ ገዥ (ሕዝ. 28:2) እና በጢሮስ ንጉሥ (ሕዝ. 28:11-12)
መካከል ያለውን ልዩነት አሳይቷል፤ በዚያም ገዢው በምድራዊው ዓለም ንቁ
ሆኖ በሰማያዊው ውስጥ የሚሠራው ንጉሥ ምሳሌ ሆኗል።
በዳንኤል 10፡12-14 መሠረት፣ እነዚህ ዓመፀኛ ሰማያዊ ፍጥረታት
የእግዚአብሔር ዓላማዎች በምድር ላይ እንዳይፈጸሙ እንቅፋት ሆነዋል።
በመለኮት ፍቃድ የተነሳሱትን የእስራኤል ጦርነቶች መረዳት ያለብን በዚህ
የሰማይ እና የምድር ግንኙነት አንጻር ነው። ጦርነቶቹ በእግዚአብሔር እና
በሰይጣን፣ በመልካም እና በክፉ መካከል ያለው ታላቅ ግጭት ምድራዊ
መገለጫዎች እንደሆኑ ልንገነዘብ ይገባናል—ሁሉም በመጨረሻው በወደቀው
ዓለም ውስጥ የእግዚአብሔርን ፍትህ እና ፍቅር ወደነበረበት የመመለስ ዓላማ
ያነገቡ ናቸው።
በዙሪያችን ባለው ዓለም እና በግል ሕይወታችን ውስጥ፣ በመልካም እና
በክፉ መካከል ያለውን ዓለምዓቀፍ ጦርነት እውነታ የምናይባቸው መንገዶች
ምንድናቸው?
ዘጸአት 2:23-25፣ ዘጸአት 12:12-13፣ እና ዘጸአት 15:3-11ን ያንብቡ።
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ማለት ምን ማለት ነው?
እስራኤላውያን በግብፅ በቆዩበት ረጅም ጊዜ የአባቶቻቸውን እውነተኛ
አምላክ ረስተውታል። በምድረ በዳ ያደረጓቸው ብዙ የጉዞ ትዕይንቶች
እንደሚያሳዩት፣ ስለ አብርሃም፣ ይስሐቅ እና ያዕቆብ አምላክ ያላቸው እውቀት
ፈዝዞ ከአረማዊያን የወሰዷቸውን ግብዓቶች በሃይማኖታዊ ልምምዳቸው
ውስጥ ደባልቀው ነበር (ከዘፀ. 32፡1-4 ጋር ያነፃፅሩ)። በግብፃውያን ጭቆና ወደ
እግዚአብሔር ጮኹ (ዘጸ. 2፡23-25)፣ እናም በትክክለኛው ጊዜ፣ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ጣልቃ ገባ።
ሆኖም በዘፀአት የመጀመሪያዎቹ 12 ምዕራፎች ላይ የተገለፀው ግጭት
በሙሴና በፈርዖን መካከል ከነበረው ቀላል የሥልጣን ሽኩቻ የበለጠ ነበር።
በጥንታዊው የምስራቃዊ ጦርነት ርዕዮተ ዓለም መሠረት፣ በሕዝቦች መካከል
የሚነሱ ግጭቶች በዋናነት በአማልክት መካከል እየተካሄዱ እንዳሉ ግጭቶች
ይወሰዱ ነበር። በዘጸአት 12፡12 ላይ እግዚአብሔር ፍርድን ያወረደው በፈርዖን
ላይ ብቻ ሳይሆን ከግብፅ ጨቋኝ ኃይል እና ኢፍትሐዊ ስርዓት ጀርባ በቆሙት
አማልክቶች፣ ኃያላን አጋንንት (ዘሌ. 17፡7፣ ዘዳ. 32፡17) ላይም ጭምር ነበር።
በዋናነት፣ እግዚአብሔር ከኃጢአት ጋር እየተዋጋ ነው፤ ይህንንም
ግጭት ለዘላለም እየታገሰ አይቆይም (መዝ. 24:8፣ ራዕ. 19:11፣ ራዕ. 20:1-
4፣14)። ሁሉም የወደቁት መላእክት፣ እንዲሁም ሊድኑ በማይችሉበት ሁኔታ
ራሳቸውን ከኃጢአት ጋር ያጣመሩ የሰው ልጆች ይጠፋሉ። ከዚህ አንጻር
በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ የሚደረጉ ጦርነቶች ገና የመጀመሪያ ደረጃ እንደሆኑ
ሊገነዘቡት ይገባል፤ ይህም በመስቀሉ ጡዘቱ ላይ ይደርስና በመጨረሻው
ፍርድ መጨረሻ ላይ የእግዚአብሔር ፍትህ እና አፍቃሪነቱ በዓለም ሁሉ
ሲረጋገጥ ይጠናቀቃል።
የከነዓናውያንን አጠቃላይ የጥፋት ጽንሰ-ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው
የዓለም አተያይ ማለትም እግዚአብሔር በአጽናፈ ሰማይ ውስጥ ካሉ የክፋት
ሠራዊት ጋር እያካሄደ ካለው ግጭት አንፃር ልንረዳው ይገባናል። በዋናነት
አደጋ ላይ የሚወድቁት የእግዚአብሔር ተቀባይነት እና ባህሪው ናቸው (ሮሜ
3፡4፣ ራእ. 15፡3)።
ኃጢአት በሰው ልጅ ሕልውና ውስጥ ስለገባ ማንም ሰው በገለልተኝነት
መቆም አይችልም። አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ወይም ከክፉው ጎን
መቆም አለበት። ስለዚህ ይህን በአእምሯችን ይዘን የከነዓናውያን መጥፋት
የመጨረሻው ፍርድ ቅምሻ ተደርጎ መወሰድ አለበት።
ታላቁ ተጋድሎ ከአንዱ ወገን ጋር ብቻ መሆንን ይፈቅዳል። ከየትኛው ወገን
እንደሆንን የምናውቀው እንዴት ነው?
በዘፀአት 14:13-14፣25 መሠረት አምላክ እስራኤላውያን በጦርነት ውስጥ ሲሳተፉ መልካም ዕቅዱ ምን ነበር?
በዚያ በችግር ጊዜ፣ የእስራኤል ሕዝብ በሥጋዊ ችግር ውስጥ
በተጋረጠበት ወቅት፣ “ሙሴም ለሕዝቡ፡- አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን
ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን
የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም
ዝም ትላላችሁ አላቸው።” እንደ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ትረካ፣ ግብፃውያን
ራሳቸው እንኳ ይህን እውነታ ተረድተውታል፡- “እግዚአብሔር በግብፃውያን
ላይ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ አሉ” (ዘጸ. 14፡25)።
ረዳት ለሌላቸው እና በውትድርና ክህሎት ላልሰለጠኑት እስራኤላውያን፣
የእግዚአብሔር ተአምራዊ ጣልቃገብነት በተደጋጋሚ ተከስቷል። ዘፀአት፣
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ወክሎ ጣልቃ የመግባቱ ምሳሌ ነው። በዚህ
ቦታ ጦርነቱን ያህዌ የሚዋጋው ብቻ ሳይሆን እስራኤላውያኑም ሳይዋጉ
መቆም ይጠበቅባቸዋል (ዘጸ. 14፡14)። እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ተነሳሽነቱ
የርሱ ነው። ስልቱን የሚቀይሰው እርሱ ነው፤ እንዴት እንደሚከናወን ይገልፃል፤
ዘመቻውን ያካሂዳል። ያህዌ ለእስራኤል የማይዋጋ ከሆነ ስኬታማ የመሆን
እድል የላቸውም።
ኤለን ጂ ኋይት ይህንን ስታብራራ እግዚአብሔር “የተስፋውን ምድር
ለርሱ በመገዛት እና በመታዘዝ እንጂ በጦርነት እንዲያገኙ እቅዱ አልነበረም።”
Ellen G. White, The Signs of the Times, September 2, 1888 ልክ
ከግብፅ ሲያወጣቸው እንዳደረገው እግዚአብሔር የነርሱን ውጊያ ሊዋጋ ነው።
ከእነርሱ የሚጠበቀው ዝም ብለው መቆም እና የእርሱን ታላቅ ጣልቃገብነት
መመስከር ብቻ ነበር።
ታሪክ እንደሚያሳየው እስራኤል በእግዚአብሔር ላይ በቂ እምነት
በነበራት ጊዜ ሁሉ መዋጋት አላስፈለጋቸውም ነበር (2ኛ ነገሥት 19፣ 2 ዜና
32፣ ኢሳይያስ 37)።
በእግዚአብሔር ትክክለኛ እቅድ፣ እስራኤል ለራሳቸው መዋጋት
አይጠበቅባቸውም ነበር። እግዚአብሔር ከከነዓናውያን ጋር በተደረገው
ጦርነት እንዲካፈሉ የፈቀደላቸው ከግብፅ ከወጡ በኋላ ባሳዩት አለማመን
ምክንያት ነው። በተመሳሳይም ከግብፅ በወጡበት ጊዜ በግብፃውያን ላይ
አንድም ጎራዴ ማንሳት አላስፈለጋቸውም፤ ከነዓንንም ለመውረር መዋጋት
አይጠበቅባቸውም ነበር (ዘዳ. 7፡17-19)።
“የእስራኤል ልጆች በጌታ ላይ ባያጉረመርሙ ኖሮ ጠላቶቻቸው ከእነርሱ
ጋር እንዲዋጉ ጌታ አይፈቅድም ነበር።”— Ellen G. White, The Story of
Redemption፣ ገጽ. 134. ዛሬስ በጌታ ላይ ማጉረምረም በሕይወታችን ላይ
ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል?
ዘጸአት 17፡7-13 እና ኢያሱ 6፡15-20 ያንብቡ። በእነዚህ ሁለት የጦርነት ትረካዎች መካከል ምን ተመሳሳይነት አለ? እንዴትስ ይለያያሉ?
እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋጉት
በዘፀአት 17 ላይ ሲሆን ያም እስራኤላውያን ራሳቸውን ከአማሌቃውያን
ሲከላከሉ ነበር። እስራኤላውያን ግብፃውያንን በማሰቃየትም ሆነ
እስራኤላውያንን ወደ ነፃነት በመምራት ረገድ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይ
ኃይል አይተዋል። እግዚአብሔር ለእስራኤል ያለው የመጀመሪያ እቅድ ከሌሎች
ሕዝቦች ጋር መዋጋትን እንደማያጠቃልል አይተናል (ዘጸ. 23፡28፣ ዘጸ. 33፡2)።
ነገር ግን እስራኤላውያን ከግብፅ ነፃ ከወጡ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በመንገዱ
ላይ ማጉረምረም ጀመሩ (ዘፀ. 17: 3)፤ በመካከላቸው ያለውን የእግዚአብሔርን
መገኘት እንኳ ይጠራጠሩ ነበር። አማሌቅ ከእስራኤል ጋር ሊዋጋ የመጣው
በዚህ ጊዜ ነበር። ይህም በአጋጣሚ አልነበረም። እግዚአብሔር እስራኤላውያን
እሱን እንደገና መታመንን ይማሩ ዘንድ አማሌቃውያን እንዲያጠቋቸው
ፈቀደላቸው።
መርሆዎቹን ሳይጥስ፣ እግዚአብሔር ህዝቡ ወደሚገኝበት ደረጃ
ይወርዳል፣ በቀጣይነትም ወደ ትክክለኛው እቅድ ማለትም በመለኮታዊ
መገኘት ሙሉ በሙሉ ወደ መተማመን ይጠራቸዋል። በእርግጥም የጦርነት
ሕግ (ዘዳግም 20) የተሰጠው ከ40 ዓመታት የምድረ በዳ ጉዞ በኋላ ነበር፤
ይህም በእስራኤል አለማመን የተነሳ የሆነ ነው። አዲስ ሁኔታዎች አዳዲስ
ስልቶችን ፈለጉ፤ እና እግዚአብሔር እስራኤል ከነዓናውያንን ሙሉ በሙሉ
እንዲያጠፉ የጠየቀው በዚያን ጊዜ ነበር (ዘዳ. 20፡16-18)።
ጦርነት ለእስራኤል አስፈላጊ ከመሆኑ እውነታ በተጨማሪ ለይሖዋ
ያላቸውን ታማኝነት የሚያረጋግጡበት መለያ ሆነ። እግዚአብሔር ተስፋ
አልቆረጠባቸውም ነገር ግን በእርሱ ላይ ሙሉ ጥገኝነትን በመለማመድ
ኃይሉን እንዲመሰክሩ ፈቀደላቸው።
እስራኤላውያን መሬቱን ለመውረስ ያደረጉት ተሳትፎ በኢያሱ መጽሐፍ
መደምደሚያ ላይ በግልጽ ይታያል። በዚህ ቦታ ከነዓናውያን ከእስራኤላውያን
ጋር ሲዋጉ እንደነበር ተጽፏል (ኢያሱ 24፡11)። የኢያሪኮ ግንብ መፍረስ
የመለኮታዊ ተአምር ውጤት ቢሆንም እስራኤላውያን በጦርነቱ ንቁ ተሳትፎ
ማድረግና የከተማዋን ነዋሪዎች ተጋድሎ መቋቋም ነበረባቸው።
የእስራኤል በትጥቅ ትግል ውስጥ መሳተፍ በያህዌ እርዳታ ላይ ያለ
ምንም ቅድመ ሁኔታ መተማመንን የማዳበር መንገድ ሆነ። የእያንዳንዱ
ጦርነት ውጤት በዋናነት በጌታ እጅ እንደሆነ እና በጦርነቱ ውጤት ላይ
ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችለው ጌታ የሰጣቸውን ተስፋዎች ማመናቸው ወይም
አለማመናቸው እንደሆነ ጌታ ሁልጊዜ ያስታውሳቸው ነበር(ኢያሱ 7:12-13፤
ኢያሱ 10:8)። ምርጫው የራሳቸው ነበር።
የኃይማኖት አባቶች እና ነቢያት ከሚለው
መጽሐፍ ውስጥ “የኢያሪኮ ውድቀት” የሚል ርዕስ ያለውን ምዕራፍ ያንብቡ።
በዩኒቨርስ ውስጥ በእግዚአብሔር ሥልጣን ላይ አመፅ በተነሣ ጊዜ፣
ወይ እግዚአብሔር የማይለወጥ እና ዘላለማዊ መሆኑን አቁሞ የአጽናፈ ዓለም
መሪነቱን ለአመጸኛው ፍጡር ይሰጣል ካልሆነም ቅዱስ፣ ጻድቅ፣ አፍቃሪ እና
መሐሪ የሆነ አባት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛውን ምስል ያቀርባል፤
በዚህ ሁኔታ፣ በክፉ ኃይሎች እና በእርሱ ኃይል መካከል ያለው ግጭት
የማይቀር ሆነ።
ከዓመፀኛ የጠፈር ኃይሎች ጋር የተቆራኙ የፖለቲካ ወይም የማህበራዊ
ኃይሎች በያህዌ ላይ ተመሳሳይ የሆነ የአመፀኝነት አመለካከት ሲያሳዩ እርሱ
የአጽናፈ ዓለም ሉዓላዊ ጌታ እንደመሆኑ ጣልቃ ገባ። ያህዌ እንደ ተዋጊ
የሚለው መነሻ ሃሳብ በመልካም እና በክፉ መካከል ያለውን አለም አቀፋዊ
ግጭት የሚያስቆመው የመጨረሻ ድል ቅድመ-ምሳሌ ይሆናል፣ (ራዕ. 20፡
8-10)። ከዚህም በላይ፣ የእስራኤል ጦርነቶች በመስታወት እንደሚታዩት
የአለም ዓቀፋዊውን ግጭት በጥቂቱ የሚያንፀባርቁ ብቻ ሳይሆኑ የዚያው
ግጭት አካልና የእግዚአብሔርን የፍጻሜ ጊዜ ፍርድ የሚያሳዩን ናቸው።
“እግዚአብሔር መሪያቸው እንዲሆን በፈቀዱለት ጊዜ ወደ ምድሪቱ
የመግባት ልዩ መብትና ኃላፊነት ሰጥቷቸው ነበር፣ ነገር ግን ሆን ብለው ቸል
በማለታቸው ፍቃዱ ተነፈገ…። መሬቱን ትእዛዛቱ በጥብቅ በመታዘዝ እንጂ
በጦርነት እንዲወርሱ ዓላማው አልነበረም።” ኤለን ጂ. ኋይት፣ የኃይማኖት
አባቶች እና ነቢያት ገፅ 392.
1. የዓለም ዓቀፋዊው ጦርነት የኋላ ታሪክ እስራኤል ወደ ጦርነት እንድትሄድ
የዓለም ዓቀፋዊው ጦርነት የኋላ ታሪክ እስራኤል ወደ ጦርነት እንድትሄድ
የሚያዘውን ጌታ በተሻለ ለመረዳት የሚረዳን እንዴት ነው?
2. በክፍል ውስጥ ስለ ታላቁ ተጋድሎ እውነታ እና በዙሪያችን ባለው
በክፍል ውስጥ ስለ ታላቁ ተጋድሎ እውነታ እና በዙሪያችን ባለው
ዓለም ውስጥ እንዴት እንደሚታይ የሚያወሳውን የሰኞ ክፍል ጥያቄ
ይወያዩበት። በዚህ ተጋድሎ ውስጥ የእኛ ሚና ምንድን ነው? እሱን
ለመፈጸም የምንፈልገውስ እንዴት ነው?
3. በመንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ ቀጥ ብለን መቆምን እና ጌታ እንዲዋጋልን
በመንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ ቀጥ ብለን መቆምን እና ጌታ እንዲዋጋልን
መጠበቅ የሚለውን መርህ ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
4. ብዙ ጊዜ በውይይታችንና በቤተክርስትያን ውስጥ በሚያጋጥሙን የኃሳብ
ብዙ ጊዜ በውይይታችንና በቤተክርስትያን ውስጥ በሚያጋጥሙን የኃሳብ
አለመግባባቶች በኛ ጎራ ማን እንዳለ ማወቅ እንፈልጋለን። በኢያሱ 5፡13-
15 መሠረት ከዚህ አንፃር አመለካከታችንን መቀየር የምንችለው እንዴት ነው?