የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ኢያሱ 21:43–45፣ 2 ጢሞ. 2:11–13፣ ኢያሱ 23፣ ራእይ 14:10፣ 19፣ ዘዳ. 6፡5።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም
ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።” (ኢያሱ 21፡45)
ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጥር 20 ቀን 1961 በበዓለ ሲመታቸው ላይ ለአሜሪካ
ሕዝብ ሲናገሩ ንግግራቸው 1,366 ቃላትን ብቻ የያዘ ነበር። ነገር
ግን በአሜሪካውያኑ አእምሮ ላይ የማይረሳ አሻራ ያስቀመጠ ንግግር
ነበረ። የሀገራቸውን ሕዝቦች ከጥቅማቸው ይልቅ በተሰጣቸው ኃላፊነት ላይ
እንዲያተኩሩ ሲያበረታቱ፣ “በመልካም ሕሊና ያለን ብቸኛው አስተማማኝ
ሽልማታችን፣ ታሪክ የተግባራችን የመጨረሻ ዳኛ ሆኖ፣ የእግዚአብሔርን
በረከቶችና እርዳታዎች እየጠየቅን የምንወዳትን ምድር ለመምራት እንውጣ፡
ነገር ግን በዚህ ምድር የእግዚአብሔር ሥራ በእውነት የኛ መሆን እንዳለበት
እንወቅ” ብለዋል።
እድሜው የገፋው የእስራኤል መሪ ኢያሱ ወደ ህይወቱ መገባደጃ
መቃረቡን ሲያውቅ የሀገሪቱን መሪዎችና እስራኤላውያንን ለማነጋገር ወሰነ
(መጽሐፈ ኢያሱ 23 እና 24)። ኢያሱ 23 በተለይ የሚያተኩረው ስለ ወደፊቱ
እና እግዚአብሔርን እንዴት ማምለክ እንደሚቻል ላይ ነው። ኢያሱ ምዕራፍ 24
የቀደሙትን የእግዚአብሔርን የታማኝነት ተግባራት ይገመግማል፣ ዓላማውም
ማን ብቻ መመለክ እንደሚገባው ውሳኔ እንዲያደርጉ ለመቀስቀስ ነው።
በዚህ ሳምንት፣ የእስራኤልን ድሎች ወደ ኋላ መለስ ብሎ የቃኘበትን
የኢያሱን የመጀመሪያ ንግግር አብረን እናጠናለን፣ በተመሳሳዩ ደግሞ
የእስራኤልን የወደፊት የስኬት ጎዳና እንቃኛለን።
ለታህሳስ 10 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
በኢያሱ 21፡43-45 ላይ መጽሐፉ ስለ እግዚአብሔር ምን አይነት ምስልን ይከስታል? እነዚህ ቃላት ስለ ታሪካዊቷ የተስፋይቱ ምድር ብቻ ሳይሆን ስለ መዳናችንን እውነታ የሚናገሩት እንዴት ነው(2 ጢሞ. 2:11-13)?
እነዚህ ጥቅሶች የመጽሐፉ ጡዘት እና የስነ-መለኮታዊ ትምህርቱ
ማጠቃለያን የያዙ ናቸው። ከመጽሐፉ ዋና መሪ ሃሳቦች አንዱን ያጎላሉ፡- እሱም
የገባውን ቃል የሚጠብቀው እና መሐላውን የሚፈጽመው የያህዌ የቃል ኪዳን
ታማኝነት ነው። ይህ አጭር ክፍል እስከ አሁን ያለውን የመጽሐፉን ይዘት
ጠቅለል አድርጎ ያቀርባል። ኢያሱ 21:43 ምደሪቱን ስለመከፋፈል(መጽሐፈ
ኢያሱ ምዕራፍ 13-21) የሚናገር ሲሆን ኢያሱ 21:44 ደግሞ በጠላቶቻቸው
ላይ ስለተቀዳጁት ድል እና ምድሪቱን ስለመቆጣጠራቸው (መጽሐፈ ኢያሱ
ምዕራፍ 1-12) ይናገራል። ይህ ሁሉ ወደ ኋላ ተመልሶ መናገር በእግዚአብሔር
ታማኝነት መነፅር የሚታይ ነው። እስራኤላውያን አምላክ ለሰጣቸው ቃሉ
ካለው ታማኝነት የተነሳ ካልሆነ በቀር በጠላቶቻቸው ወይም በምድሪቱ ላይ
የተቀዳጁትን ድሎች ርስት አድርገው ሊወስዱ እንደማይችሉ ምንጊዜም
ማስታወስ አለባቸው።
“ምድርን ሁሉ” ሰጠ (ኢያሱ 21:43)፣ “ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው
አሳልፎ ሰጠ” (ኢያሱ 21:44) እና “በማለላቸውም ሁሉ” (ኢያሱ 21:44)
“ሁሉም ተፈጽሟል”፣ “ሁሉ” የሚለው ቃል በሦስት ቁጥሮች ውስጥ ስድስት
ጊዜ ደጋግሞ መጠቀሙ ምድሪቱ የይሖዋ ስጦታ መሆኗን በድጋሚ አጽንዖት
ይሰጣል፤ እና እስራኤል ስለተቀበለችው ርስት ምንም ዓይነት ምስጋና
ልትወስድ አትችልም። ምድሪቱን “ሊሰጥ” የማለው እና ጠላቶቻቸውን
በእጃቸው “የሰጣቸው” ጌታ ነው።
የእስራኤል ስኬቶች ሁሉ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ተነሳሽነት እና
ታማኝነት ብቻ የመጡ ናቸው። ይህም በተመሳሳይ ሁኔታ ስለ መዳናችን
እውነት ነው፡- “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር
ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።”
(ኤፌ. 2:8-9).
በእርግጥም፣ የእግዚአብሔርን ታማኝነት በማጉላት፣ ጳውሎስም
እንዲህ ሲል ጽፏል፡- ቃሉ የታመነ ነው እንዲህ የሚለው፦ ከእርሱ ጋር
ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፤ ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር
ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤ ባናምነው፥ እርሱ
የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።” (2 ጢሞ. 2፡11-13)።
አምላክ የገባቸውን ተስፋዎች በመጠበቅ ረገድ ያለው ታማኝነት ወደፊት
የሚሰጣቸው ተስፋዎች እንደሚፈፀሙ እንድንተማመን የሚረዳን እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 10:13፣ 2 ቆሮ. 1:18-20 ይመልከቱ።)
የሙሉው ክፍል ክቡር መደምደሚያ (ኢያሱ 21፡43-45) እስራኤላውያን እንደታዘዙ ያሳያል። ስኬት በፍፁም በነፃ የሚገኝ አይደለም፤ ሁልጊዜም ለእግዚአብሔር ቃል ከመታዘዝ ጋር የተያያዘ ነው። ስለዚህ፣ ምድሪቱ መከፋፈሏ፣ እግዚአብሔር ለእስራኤል ያለውን ታማኝነት የሚያሳይ ምልክት ከመሆኑ በተጨማሪ (ነህ. 9፡8)፣ በእስራኤል አቋም ላይ የተመሰረተ ውጤት እንዲኖር የሚያስችል ዕድል ይሰጣል። እስራኤል የተገኘውን ነገር ማስጠበቅ ትችል ይሆን? ኢያሱ 23:1-5ን ያንብቡ። የኢያሱ የንግግር መግቢያ ያካተታቸው ዋና ዋና ነጥቦች ምንድን ናቸው?
የኢያሱ ንግግር ከሽማግሌው ተናጋሪ (ሁለት ጊዜ በአጽንዖት ተነግሯል)
እግዚአብሔር የሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈፀም ወደ ታደሙት ተመልካቾች
ይሸጋገራል። ምድሪቱን መውረስ እንዴት እንደተቻለ ገልጿል፡- በአጭሩ ጌታ
ስለ እነርሱ ተዋጋ። ምንም እንኳ፣ እስራኤላውያን ታማኝ ባለመሆናቸውና
ባለማመናቸው ምክንያት ከግብፅ ከወጡ በኋላ ጦርነት ውስጥ ቢገቡም
ምድሪቱን መውረስ የቻሉት በወታደራዊ ኃይላቸው ሳይሆን በእግዚአብሔር
እርዳታ ነው።
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው አሳረፋቸው፤ ነገር ግን
አሁንም መውረስ ያለባቸው አንዳንድ ሀገራት አሉ። ድል ለእስራኤላውያን
የተጠናቀቀ፣ የማይለወጥ እውነታ ሳይሆን በእግዚአብሔር እርዳታ ላይ
በመታመን ከቀጠሉ ምንጊዜም ሊሆን የሚችል ነው።
እስራኤላውያን በኢያሱ መሪነት ከነዓንን ድል ባደረጉበት ሁኔታና በዛሬው
ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች ድል አድራጊ መንፈሳዊ ሕይወት መምራት በሚችሉበት
መንገድ መካከል ምን ተመሳሳይነት አለ? ኢያሱ 23፡10፣ ቆላ. 2፡15፣ 2 ቆሮ. 10፡
3-5፣ ኤፌ. 6፡11-18ን ያንብቡ።
የእስራኤላውያን ድሎች በጥንካሬያቸው እና በስልታቸው ነው
ሊባል አይችልም። በተመሳሳይ፣ በኃጢአት እና በፈተና ላይ ያለው መንፈሳዊ
ድል በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት እና ትንሳኤ ተረጋግጧል፤ ነገር ግን
የእግዚአብሔር ህዝብ ዛሬ ያለማቋረጥ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የድል ህይወት
ለመኖር መታመን አለባቸው።
በፊታችን ብዙ አስደናቂ ተስፋዎች ቢኖሩም አሁንም ኃጢአት መሥራት ቀላል
የሆነብን ለምንድነው?
ኢያሱ በመጽሐፉ መጀመሪያ ላይ የተነገሩትን ተመሳሳይ ቃላት በመጠቀም (ኢያሱ 1:7- 8) በእስራኤል ፊት የሚጠብቀው ተግባር በዋነኝነት ወታደራዊ እንዳልሆነ ተናግሯል። መንፈሳዊ ነው። ያም በኦሪት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከመታዘዝ ጋር የተያያዘ ነው። ኢያሱ እስራኤላውያን በዙሪያቸው ካሉት ህዝቦችጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ጠንካራ አቋም የወሰደው ለምን ይመስላችኋል? (ኢያሱ 23:6- 8፣12፣13)
እስራኤልን የሚያስፈራት የቀሪዎቹ ህዝቦች ጠላትነት ሳይሆን
ወዳጅነታቸው ነበር። የጦር መሣሪያዎቻቸው ለእስራኤል ምንም ዓይነት ፈተና
ላይሆኑ ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ አስተምህሯቸው እና እሴቶቻቸው (ከእስራኤል
ተቃራኒ የሆኑ እሴቶች) ከየትኛውም ወታደራዊ ኃይል የበለጠ ጎጂ ሊሆኑ
ይችላሉ። ኢያሱ ሕዝቡ የተሳተፈበት ግጭት በመጀመሪያ እና በዋነኝነት
መንፈሳዊ መሆኑን መሪዎቹን እንዲያስተውሉ ፈልጓል። ስለዚህ እስራኤል ልዩ
ማንነቷን መጠበቅ አለባት።
የአማልክትን ስም መጥራት፣ በእነርሱ ስም መማል፣ እሱን ማገልገል
ወይም መስገድ የተከለከለው ከጣዖት አምልኮ ጋር ስለተያያዘ ነው። በጥንታዊው
ቅርብ ምስራቅ የአንድ አምላክ ስም መገኘቱንና ኃይሉን ይወክላል። በዕለት
ተዕለት ሰላምታ ወይም የንግድ ልውውጥ የአማልክትን ስም መጥራት ወይም
መጥቀስ ለሥልጣናቸው እውቅና መስጠት እና እስራኤላውያን በችግር ጊዜ
እርዳታቸውን እንዲፈልጉ ማመቻቸት ነው (ከመሳ. 2፡1-3፣ 11-13 ጋር ያነፃፅሩ)።
ከቀሩት ከነዓናውያን ጋር መጋባት የእስራኤልን መንፈሳዊ ንጽሕና
ማጣትን በውስጡ የያዘ ነው። የኢያሱ ማሳሰቢያ ዓላማ የዘር ወይም የጎሳ
ንጽህናን ማራመድ ሳይሆን የእስራኤልን መንፈሳዊ ውድቀት ሊያስከትል
ከሚችለው ጣዖት አምልኮ መራቅ ነው። የሰሎሞን ህይወት የተቀላቀለ ጋብቻ
የሚያስከትለውን አሳዛኝ መንፈሳዊ ውጤት የሚያሳይ ምሳሌ ነው (1 ነገሥት
3፡1፣ 1 ነገሥት 11፡1-8)። በአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ከማያምኑ ጋር የጋብቻ
ግንኙነቶችን እንዳይፈልጉ በግልጽ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል(2ኛ ቆሮ. 6፡
14)፤ ሆኖም ቀደም ብለው ከተከናወኑ ጋብቻዎች አንፃር ጳውሎስ ከማያምን
የትዳር ጓደኛ ጋር መፋታትን አልመከረም፤ ነገር ግን የትዳር ጓደኛን ወደ ጌታ
ማሸነፍን ተስፋ በማድረግ አርአያ የሆነ ክርስቲያናዊ ሕይወት እንዲመሩ
መከራቸው (1 ቆሮ. 7፡12-16)።
ኢያሱ ጎጂ በሆኑ ወዳጅነቶች ላይ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ክርስቲያኑ “ከዓለም”
ጋር ስላለው ዝምድና ወደ ጥያቄ መመራቱ የማይቀር ነው። በዙሪያችን ካለው
ማህበረሰብ ጋር ሚዛናዊ ግንኙነት መፍጠር የምንችለው እንዴት ነው?
ማህበረሰብ ጋር ሚዛናዊ ግንኙነት መፍጠር የምንችለው እንዴት ነው?
በኢያሱ (ኢያሱ. 23:15-16) እና በሌሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የእግዚአብሔርን ቁጣ እና የበቀል ፍትሕ መግለጫዎችን እንዴት ልንረዳቸው ይገባናል? (ዘሁ. 11:33፣ 2 ዜና 36:16፣ ራእይ 14:10፣19፣ ራዕይ 15:1)
እስራኤል የእግዚአብሔርን ቁጣ በምድረ በዳ፣ (ዘኁ. 11፡33፣ ዘኁ. 12፡
9)፣ እንዲሁም በተስፋይቱ ምድር (ኢያሱ 7፡1) ተለማምዶታል። እናም ቃል
ኪዳኑን በማፍረስ የእግዚአብሔርን ቁጣ ማነሳሳት የሚያስከትለውን መዘዝ
ሙሉ በሙሉ ያውቁ ነበር። እነዚህ ጥቅሶች የኢያሱ ንግግር ከባድነት ጡዘትን
ያመለክታሉ። ቀደም ሲል የከነዓናውያንን መጥፋት ለማመልከት ተመሳሳይ ቃል
ተጠቅሞ ስለነበረ ጌታ እስራኤልን ያጠፋቸዋል የሚለውን በዚህ ንግግር ውስጥ
መስማት አስደንጋጭ ነው። የእስራኤልን በረከት በተመለከተ የጌታ የተስፋ
ቃል በታማኝነት እንደተፈፀመ ሁሉ፣ እስራኤላውያን ኪዳኑን ካፈረሱ የቃል
ኪዳኑ እርግማኖች (ዘሌዋውያን 26፣ ዘዳግም 28) መቀበላቸው አይቀሬ ነው።
ከከነዓናውያን መባረር እና ጥፋት አንጻር፣ እነዚህ ጥቅሶች ያህዌ በመጨረሻ
የምድር ሁሉ ፈራጅ መሆኑን በድጋሚ ያሳያሉ። ኃጢአት የሚገኝበት ቦታ ምንም
ይሁን ማን በኃጢአት ላይ ጦርነት ያውጃል። አረማውያን በተመረጠው ሕዝብ
ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ መጠቀሚያ ሲሆኑ ከሆኑት በላይ እስራኤላውያኑ
በቅዱስ ጦርነት ውስጥ ሲሳተፉ አልተቀደሱም፤ ልዩ ጥቅሞችንም አላገኙም ።
ያለፈውን የከበሩ እርግጠኛ መንገዶች የወደፊቱን ለመጋፈጥ መሰረት
አድርጎ መጠቀም የእስራኤል ምርጫ ነበር።
በመጀመሪያ እይታ፣ በእግዚአብሔር ቁጣ ላይ ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ
ትምህርት እግዚአብሔር ፍቅር ነው ከሚለው ማረጋገጫ ጋር የማይጣጣም
ይመስላል (ዮሐንስ 3፡16፣ 1 ዮሐንስ 4፡8)። ሆኖም፣ የእግዚአብሔር ፍቅር
መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ የበለጠ ወሳኝ የሚሆነው በእግዚአብሔር ቁጣ
ብርሃን ነው። በመጀመሪያ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን አፍቃሪ፣ ታጋሽ፣
እና ይቅር ለማለት ዝግጁ አድርጎ ይገልጸዋል (ዘጸ. 34፡6፣ ሚክ. 7፡18)። ነገር
ግን፣ በኃጢአት በተጠቃ ዓለም ዓውድ፣ የጌታ ቁጣ ከኃጢአትና ክፋት ጋር
ሲጋፈጥ የቅድስናውና የጽድቅ ዝንባሌው መገለጫ ነው። ቁጣው በጭራሽ
ስሜታዊ፣ የበቀል፣ ያልተመጣጠነ አይደለም። አዲስ ኪዳን ክርስቶስ ስለ እኛ
ኃጢአት እንደሆነ (2ቆሮ. 5፡21) እና፣ በሞቱም ከእግዚአብሔር ጋር እንደታረቅን
(ሮሜ. 5፡10) ያስተምራል። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቁጣ
አይጋፈጥም (ዮሐ. 3:36፣ ኤፌ. 2:3፣ 1 ተሰ. 1:10)። የእግዚአብሔር ቁጣ
ጽንሰ-ሐሳብ እግዚአብሔርን የሚያቀርበው የዩኒቨርስ ጻድቅ ዳኛ እና ፍትሕን
የሚደግፍ አድርጎ ነው (መዝ. 7፡11፣ መዝ. 50፡6፣ 2ጢሞ. 4፡8)።
እስራኤል የጣዖት አምልኮን ፈተና እና የእግዚአብሔርን ቁጣ የምታስወግድበት ብቸኛው መንገድ የቃል ኪዳኑን “አታድርጉ” በማስታወስ ሳይሆን ለጌታ ንቁ እና የማያቋርጥ ታማኝነት በማዳበር ነው። “መጣበቅ” የሚለው ተመሳሳዩ ግስ፣ ከጌታ ጋር (ዘዳ. 4፡4)፣ በሚስት እና በባል መካከል የሚካሄደውን የጋብቻ ቃል ኪዳን (ዘፍ. 2፡24) ወይም ሩት ለኑኃሚን ያሳየችውን ታማኝነት (ሩት 1፡14) ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል። ኢያሱ ባደረገው ግምገማ መሠረት እንዲህ ያለው ታማኝነት እስራኤላውያንን “እስከ ዛሬ ድረስ” እንደ ሕዝብ ለይቷቸው እንደነበር ልብ ማለት ያስፈልጋል። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ የመሳፍንት መጽሐፍ በሚያሳዝን ሁኔታ እንደሚገልፀው፣ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ በቀጣዮቹ ጊዜያት ተመሳሳይ አባባል እውነት አይሆንም (መሳ. 2:2፣ 7፣ 11፣ መሳ. 3:7፣ 12፣ መሳ. 4:1፣ ወዘተ.) ኢያሱ እስራኤልን አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲወዱ ጠይቋል (ኢያሱ 23፡11፤ ከዘዳ. 6፡5 ጋር ያነፃፅሩ)። ፍቅርን ማስገደድ አይቻልም፤ ያለበለዚያ ፍቅር መሆኑ ያቆማል። ግን ፍቅርን ማዘዝ የሚቻለው እንዴት ነው?
እስራኤላውያን በቃል ኪዳኑ በረከቶች እንዲደሰቱ፣ ለእግዚአብሔር
ታማኝ ሆነው መቆየት ነበረባቸው። የዕብራይስጡ ቃል “ስለ ነፍስህ ስትል
በጣም ተጠንቀቅ” የሚል አጽንዖት ይሰጣል። አሃባ፣ “ፍቅር” የሚለው ቃል
ወዳጃዊ ትስስርን፣ የፆታ ግንኙነትን፣ የእናቶችን ርኅራኄን፣ ፍቅርን እና
ለእግዚአብሔር ታማኝነትን ጨምሮ የተለያዩ የሰዎችን ፍቅር ሊያመለክት ይችላል። ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ራስን ለርሱ አስቦ እንደ መስጠት
ከተረዳን፣ እውነተኛ ተፈጥሮውን ሳይጥስ ሊታዘዝ ይችላል (ከዮሐንስ 13፡34
ጋር ያነፃፅሩ)። እግዚአብሔር ሁልጊዜ ለትእዛዛቱ መታዘዝን በታላቅ ምህረቱና
ፍቅሩ ባደረጋቸው ነገር ላይ በመመስረት ከእርሱ ጋር ከሚኖረን(ካለን)
ግላዊ ግንኙነት ውስጥ እንዲመነጭ ይፈልጋል (ዘፀ. 19፡4 [“ወደ እኔ...
እንዳመጣኋችሁ፣” ዘዳ. 6፡5፣ ከማቴ. 22፡37 ጋር ያነፃፅሩ)።
እግዚአብሔርን የመውደድ ትእዛዝም በሁለቱም በኩል መሆን
ያለበትንና፣ ከሰው ጋር እኩል ያልሆነውን መለኮታዊ ፍቅር ይገልፃል።
እግዚአብሔር ለፍቅሩ ምላሽ ከሚሰጥ እያንዳንዱ ሰው ጋር ወደ ግላዊ
ግንኙነት ለመግባት ይፈልጋል። ስለዚህ የእርሱ ሁለንተናዊ ፍቅር ከኛ የሆነን
ፈቃደኝነት፣ በሁለት በኩል የሆነ የሚገለፅ ፍቅርን የያዘ ነው።
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ አዲስ ትእዛዝ ሰጠ። ይህ ትእዛዝ በተመሳሳይ ጊዜ
አዲስና አሮጌ የሆነው በምን መልኩ ነው? ዮሐንስ 13:34፣ ዮሐንስ 15:17፣ እና 1
ዮሐንስ 3:11; ዘሌ. 19፡18 ጋር ያነፃፅሩ።
የኃይማኖት አባቶች እና ነቢያት ከሚለው መፅሐፍ
“የኢያሱ የመጨረሻ ቃላት” የሚል ርዕስ ያለውን ምዕራፍ ያንብቡ።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለው ፍቅር እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ
በህዝቡ ውስጥ ኃጢአትን እንዳላየ የሚያልፍ እንደሆነ የእግዚአብሔር
ቃል ማስፈራሪያዎች በሥነ ምግባራዊ መንግሥቱ ውስጥ አንድን ዓላማ
የሚያገለግሉ ቢሆንም፣ ቃል በቃል ፈጽሞ ሊፈጸሙ እንደማይችሉ በመናገር
አሳማኝ የሚመስሉ ንድፈ ሐሳቦችን በማስቀመጥ ሰይጣን ብዙዎችን ያታልላል።
ነገር ግን እግዚአብሔር ከፍጡራኑ ጋር ባደረገው ግንኙነት ሁሉ ኃጢአትን
በእውነተኛ ባህሪው በመግለጥ የጽድቅን መርሆች ጠብቋል - ይህም የኃጢአት
ውጤቱ መከራ እና ሞት መሆኑን በማሳየት ነው። የኃጢያት ይቅርታ ያለ ምንም
ቅድመ ሁኔታ ከቶ ሆኖ አያውቅም፣ አይሆንምም። እንዲህ ዓይነቱ ይቅርታ
የእግዚአብሔር መንግሥት መሠረት የሆኑትን የጽድቅ መርሆችን መተውን
ያሳያል። ያልወደቀውን አጽናፈ ሰማይ በድንጋጤ ይሞላል። አምላክ የኃጢአትን
ውጤት በታማኝነት አስቀድሞ ጠቁሟል፣ እና እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች
እውነት ካልሆኑ፣ የገባው ቃል እንደሚፈጸም እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? ያ ፍትህን ወደ ጎን የሚተው በጎነት፣ በጎነት ሳይሆን ድክመት ነው።
“ሕይወት ሰጪ አምላክ ነው። ሕጎቹ ሁሉ ከመጀመሪያ ጀምሮ
ለሕይወት ለመስጠት የተቀረጹ ነበሩ። ነገር ግን ኃጢአት እግዚአብሔር
ባዘጋጀው ሥርዓት ሰብሮ መጣ፣ አለመግባባቶችም ተከተሉ። ኃጢአት እስካለ
ድረስ መከራና ሞት የማይቀር ነገር ነው። ሰው አስከፊውን ውጤት ለማምለጥ
ተስፋ ማድረግ የሚችለው ቤዛችን በእኛ ምትክ የኃጢአትን እርግማን
ስለተሸከመ ብቻ ነው።” የኃይማኖት አባቶች እና ነቢያት፣ ገፅ 522
1. በህይወትዎ ውስጥ የእግዚአብሔር ታማኝነት ማስረጃዎችን ያሰላስሉ።
በህይወትዎ ውስጥ የእግዚአብሔር ታማኝነት ማስረጃዎችን ያሰላስሉ።
እርስዎ የትኞቹን ይጠቅሳሉ? በተመሳሳይ ጊዜ፣ እርስዎ እንዳሰቡት ወይም
እንደጸለዩት ነገሮች ካልሄዱ ወይም የተገባውን ቃል እርስዎ በታማኝነት
እንደታዘዙ ቢያስቡም ጸጥታ ብቻ ሲቸረው ምን ምላሽ ይሰጣሉ?
2. ስለ እግዚአብሔር ቁጣ የሚናገረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ላይ
ስለ እግዚአብሔር ቁጣ የሚናገረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ላይ
ይወያዩ። የጌታን ቁጣ እንደ የምሥራቹ አካል አድርጎ ማቅረብ የሚቻለው
እንዴት ነው?
3. ከዚህ ሳምንት ትምህርት ከማያምኑ ጋር ስለሚመሰረት ጓደኝነት ምን
ከዚህ ሳምንት ትምህርት ከማያምኑ ጋር ስለሚመሰረት ጓደኝነት ምን
መሠረታዊ መርሆዎችን ማግኘት እንችላለን? ከመርሆዎቻችን እና
ከተግባሮቻችን አንጻር ግልጽ የሆኑ ድንበሮችን ማስቀመጣችን እንዳለ
ሆኖ ከሰዎች ጋር ተቀላቅለን እነርሱን ለማገልገል እና ለነርሱ መልካም
ማድረግን ሚዛናዊ ሆነን መፈፀም የምንችለው እንዴት ነው?
4. በፍጹም ልባችን ከጌታ ጋር እንዳንጣበቅ የሚከለክሉን አንዳንድ
በፍጹም ልባችን ከጌታ ጋር እንዳንጣበቅ የሚከለክሉን አንዳንድ
እንቅፋቶች ምንድን ናቸው?