የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ: ዘጸ. 21:1–32፣ ዘጸ. 22:16–23:33፣ 2ኛ ነገሥ. 19:35፣ ማቴ. 5:38–48፣ ሮሜ 12:19፣ ማቴ. 16:27.
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እግዚአብሔር ሙሴን አለው፦ ለእስራኤል ልጆች
እንዲህ በል፦ እኔ ከሰማይ እንደ ተናገርኋችሁ እናንተ አይታችኋል።
በአጠገቤ ምንም አታድርጉ፤ የብር አማልክት የወርቅም አማልክት
ለእናንተ አታድርጉ” (ዘጸ. 20:22፣ 23)።
እግዚአብሔር ሕዝቡ በዙሪያቸው ካሉ ሕዝቦች የተለዩ እንዲሆኑ
ፈለገ። በእርሱ አመራርና ሥልጣን ሥር የሚኖሩና ራሳቸውን ቀድሰው
የሰጡ የእምነት ማህበረሰብ እንዲሆኑ ፈለገ። ሁሉም የሕጉ ተገዢዎች
ይሆናሉ። መሳፍንት ሕግ አስፈጻሚዎች ሆነው ሲሾሙ ካህናት ደግሞ የሕግ
አስተማሪዎች ይሆናሉ። ወላጆችም ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።
በማንኛውም ባህል ሕጎች ሕግ አውጪው እንዲፈጸሙ የሚፈልጋቸውን
ነገሮች፣ ግቦች፣ ዓላማ እና ባህርይ ይገልጣሉ። ለምሳሌ ፈርዖን እያንዳንዱ
ዕብራዊ ወንድ ልጅ እንዲገደል ትዕዛዝ በሰጠ ጊዜ ሕጉ የእርሱን ማንነት
ማለትም ከፉ መሆኑን ገለጸ። ከዚህ በተቃራኒ ንጉሡ በግዛቱ ውስጥ ያለ
እያንዳንዱ ዕድሜው 18 ዓመት የሆነው ልጅ ነጻ የሆነ ከፍተኛ የትምህርት
ዕድል ይሰጠዋል የሚል ሕግ ቢያወጣ ብዙዎች ይህን ድርጊቱን የልግስና እና
አገሪቱ እንድትበለጽግ ያለው ምኞት ማስረጃ አድርገው ይመለከታሉ።
የእግዚአብሔር ሕግ እርሱን ማለትም መልካምነቱን፣ ፍቅሩን እሴቶቹን፣
ጽድቁን እና ክፉ እንዳይሰለጥን መቆጣጠሩን ያሳያል። ሕጉ ፍጹምና ቅዱስ
እንደሆነ ሁሉ እግዚአብሔርም ፍጹምና ቅዱስ ነው። ለተትረፈረፈው ፍጥረት
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ቦታ እየፈጠረ ሳለ ሕጉ ከአደጋዎችና ከመቅሰፍቶች ለመጠበቅ ይረዳል።
የእርሱ የሕግ ሥርዓቱ መሰረቱ ለእግዚአብሔር፣ ለእርስ በርስና ለሕይወት
አክብሮት መስጠት ነው።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሐሴ 24 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ
እግዚአብሔር በሲና ሕጉን ሲሰጥ ሕዝቡ ከእርሱ ጋር ባላቸው
ግንኙነት እንዴት ቅዱስ ሕይወት መኖር እንደሚችሉ መሰረት ጣለ። ነገር ግን
የሕጉ መርሆዎች በዕለት ተዕለት ሕይወት መተግበር ነበረባቸው። ስለዚህ
እግዚአብሔር “የቃል ኪዳን ደንብ” የሚባሉ ተጨማሪ ሕጎችን ሰጠ። እነዚህን
ሕጎች መጠበቅና በትክክል መተግበር የመሳፍንት ሀላፊነት ነበር።
“በባርነትና በአረማዊነት የታወሩና የተዋረዱ የሕዝቡ አእምሮዎች
ሰፋ ያሉ የእግዚአብሔርን አሥርቱን ትዕዛዛት መርሆዎች በሙላት ለማድነቅ
ዝግጁ አልነበሩም። የአሥርቱ ትዕዛዛት ግዴታዎች ሙሉ በሙሉ ተስተውለውና
ተተግብረው ቢሆን ኖሮ የአሥርቱን ትዕዛዛት መርሆዎች የሚያብራሩና
የሚተገብሩ ተጨማሪ ሕግጋት ይሰጡ ነበር። እነዚህ ሕግጋት ወሰን የለሽ
በሆነው ጥበብና ፍትሃዊነት ስለተዋቀሩና ሹማምንቱ በእነርሱ መሰረት
ፍርድ ስለሚሰጡ ፍርዶች ተብለዋል። ከአሥርቱ ትዕዛዛት በተቃራኒ፣ ለሕዝቡ
እንዲነግር ለታዘዘው ለሙሴ በግሉ (ለብቻው) ተሰጥተዋል።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 310.
ዘጸ. 21:1–32ን ያንብቡ። የዕብራውያን ባሪያዎችን፣ ነፍስ መግደልን እና
አካላዊ ጉዳትን በተመለከተ ምን የተለዩ መመሪያዎች ተሰጥተው ነበር?
የቃል ኪዳን ደንብ በብዙ ምዕራፎች ውስጥ ተገልጾአል (ዘጸ.
21:1–23:19)። እነዚህ ሁሉ ደንቦችና ሕጎች የተሰጡት የክፋት ናዳን
ለማቆምና ሥርዓት ያለውን ማህበረሰብ ለመገንባት ነበር።
የባሪያ ሕጎች የተለዩ ስለነበሩ ከዘመናዊውና በመካከለኛው
ዘመን ከነበረው አረመኔያዊና ክፉ የባርነት ልምምድ ጋር መምታታት
የለባቸውም። እንደ እውነቱ ከሆነ ዕብራውያን ባሪያዎች ዋጋ የሚሰጣቸውና
ጥበቃ የሚደረግላቸው ነበሩ። በዘመናዊውና በመካከለኛው ዘመን በነበሩ
ማህበረሰቦች ውስጥ አገልጋዮችና ባሪያዎች የገዢዎቻቸው ንብረት ስለነበሩ
ገዢዎቻቸው በእነርሱ ላይ የፈለጉትን ነገር ሁሉ ማድረግ ይችሉ ነበር። ከዚህ
በተቃራኒ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሕጎች ነገሮችን በተለየ ሁኔታ ተቆጣጥረዋል።
አገልጋይነት ለስድስት አመት ብቻ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን (ዘጸ. 21:1፣
2፤ ኤር. 34:8–22)፣ በሰባተኛው አመት ባሪያዎች በሙሉ፣ ራሳቸው
ከጌቶቻቸው ጋር ለመሆን ካልፈለጉ በቀር፣ ነጻ ይወጡ ነበር። ደግሞ ጌቶቻቸው
በሰንበት ቀናት እንዲያርፉ በማድረግ (ዘጸ. 20:9፣ 10) መሰረታዊ
ፍላጎቶቻቸውን ያሟሉላቸው ነበር።
በአብዛኛው የዓለም ክፍል ክፉ የሆነ ተቋማዊ የባርነት ልምምድ ቢወገድም፣
አንዳንድ መርሆዎቹ አሁንም እየተተገበሩ ያሉባቸው መንገዶች ምንድር ናቸው?
እነዚህን መርሆዎች ለመዋጋት በራሳችን ውስን ክበብ ምን ማድረግ እንችላለን?
እግዚአብሔር በምህረቱ የንብረት መብቶችን በተመለከተ በተለያዩ ሁኔታዎች ሰዎች ከሰዎች ጋር እንዴት መስራት እንዳለባቸው መሳፍንትን አስተማራቸው። አንድ ኮርማ በሬ በጎረቤት በሬ ላይ ጉዳት ካደረሰ፣ ሰዎች የቤት እንስሳን ሰርቀው ቢሸጡ፣ ከብቶች የሌላ ሰው ግጦሽ ውስጥ ወይም የወይን ቦታ ገብተው ቢግጡ፣ አንድ ግለሰብ የተዋሰው ነገር ቢሰረቅበት ወይም የተከራዩት እንስሳ ቢጎዳ ወይም ቢሞት ምን መደረግ እንዳለበት የሚያመለክቱ በርካታ ጥናቶች ተዘርዝረዋል (ዘጸ. 21:33–22:15)። ዘጸ. 22:16–23:9ን ያንብቡ። በእነዚህ ህግጋት ውስጥ የተነሱ ጉዳዮች ምንድር ናቸው? የተነሱትስ እንዴት ነው?
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የእግዚአብሔር ሕግጋት የተለያዩ ጉዳዮችን አካትተዋል። ሰዎችን
መናቅን ወይም ማዋረድን የሚቃወሙ ልዩ ደንቦች ነበሩ። ምንም ዓይነት
ብዝበዛ እንዲፈጸም አልፈለገም ነበር። እግዚአብሔር በምህረቱ ኃጢአተኛ
የሆኑ የሰብአዊ ልብ ዝንባሌዎችን በማረም የሰዎችን ተፈጥሮአዊ ዝንባሌዎች
ይገድባል። ማህበረሰብ ከአደጋ መጠበቅ፣ ክፋት መጥፋት እና ጥሩ የሆኑ
የእርስ በርስ ግንኙነቶች መጎልበት ነበረባቸው። ሁሉም ተግባሮች ለፍትህና
ፍቅር መገዛት ነበረባቸው።
ዘጸ. 23:10–19ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ የተነሱት ወሳኝ (ጠቃሚ)
ጉዳዮች ምንድር ናቸው?
ሰንበትና በዓላት አምልኮን የሚመለከቱ ስለነበር በድነት ታሪክ ውስጥ
ያሉ ወሳኝ ክስተቶችን የሚያስታውሱ ነበሩ። አምልኮ ለሁሉም ሌሎች ተግባራት
ስነ-መለኮታዊ መሰረት ስለነበር በጥንቃቄ ቁጥጥር ይደረግበት ነበር። ሰንበት
የተቋቋመው በፍጥረት ጊዜ ስለነበር (ዘፍ. 2:2፣ 3፤ ዘጸ. 20:8–
11)፣ ከእሥራኤል ነጻ መውጣትና ድነት ጋር በመገናኘት (ዘዳ. 5:12–
15)፣ ኃይለኛ በሆነ መንገድ እግዚአብሔርን እንደ ፈጣሪያችን፣ አዳኛችንና
ጌታችን ወደማምለክ ያመለክታል (ማርቆስ 2:27፣ 28)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ እሥራኤላውያን በየዓመቱ ማክበር የነበረባቸው
ሶስት ወሳኝ በዓላት ነበሩ፡-(1) ፋሲካ ወይም ያልቦካ ቂጣ የሚበላበት
በዓል ሲሆን የሚከበረውም በፀደይ ወራት (በአብዛኛው ከመጋቢት አጋማሽ
እስከ ሚያዝያ አጋማሽ ድረስ) ነበር። (2) ጴንጤቆስጤ ወይም የመከር
በዓል (ወይም የሳምንታት በዓል) ሲሆን የሚከበረው የመጀመሪያው በዓል
ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ ስለሆነ የሚጀምረው ከ50 ቀናት በኋላ
ነበር። (3) የዳስ በዓል ወይም በበልግ ጊዜ እህል የመሰብሰብ በዓል ሲሆን
(በተለምዶ ከመስከረም አጋማሽ እስከ ጥቅምት አጋማሽ ባለው ጊዜ ይከበር
ነበር (ደግሞ ዘጸ. 34:18–26፣ ዘሌ. 23:4–44፣ ዘሁ 28:16–
29:40፣ ዘዳ. 16:1–16ን ይመልከቱ)።
ዘጸ. 23:20–33ን ያንብቡ።እግዚአብሔር የተስፋይቱን ምድር አሸንፈው እንዲወስዱ ምን ዘዴዎችን መጠቀም ፈለገ?
እሥራኤላውያን አዲሱን ግዛት ለመያዝ እንዲዋጉ የእግዚአብሔር ዕቅድ
አልነበረም፤ እርሱ የፈለገው እንዲሰጣቸው ነበር። አስቀድሞ ለአብርሃም፣
ለይስሐቅና ለያዕቆብ ቃል ተገብቶላቸው ስለነበር የእግዚአብሔር ዕቅድ
እሥራኤላውያን ከእርሱ እንደተሰጣቸው ልዩ ስጦታ እንዲቀበሉት ነበር።
የተስፋይቱን ምድር እንዴት እንደሚወርሱ የሚያሳይ ሞዴል (ምሳሌ)
ቀይ ባህርን በተሻገሩ ጊዜ ታይቶ ነበር። እግዚአብሔር ለሕዝቡ በመዋጋት
እነርሱን ለመግደል እያቀዱ በነበሩት ላይ ሙሉ ድል ሰጣቸው (ዘጸ. 14:13፣
14)። ግብጻውያን የተሸነፉት እግዚአብሔር ተዓምራዊ በሆነ ሁኔታ ጣልቃ
ስለገባ ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ የአሶራውያን ንጉሥ በነበረው በሰናክሬብ
ዘመን እጅግ ግዙፍ የነበረውን በደንብ የታጠቀና የሰለጠነ የአሦራውያንን
ጦር እሥራኤላውያን መዋጋት ሳያስፈልጋቸው እግዚአብሔር ድል አደረገ።
እግዚአብሔር ለንጉሥ ሕዝቅያስ ድል የሰጠው እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ
አማካይነት የተናገረውን በማመኑ ነበር (2ኛ ነገሥ. 19:35፣ ኢሳ 37:36)።
ቃል የተገበላቸው የተስፋይቱ ምድር ለዘሩ ወዲያውኑ እንደማትሰጥ፣
ነገር ግን ከ400 ዓመታት በኋላ ተስፋው ተፈጻሚ እንደሚሆን እግዚአብሔር
ለአብርሃም ነግሮት ነበር (ዘፍ. 15:13–16)። ለምን? ምክንያቱ
በከነዓን ምድር ካሉ ኗሪዎች ክፋት ጋር የተገናኘ ነበር። እግዚአብሔር ለእነዚያ
ሰዎች በምህረቱ እየሰራ ሲሆን እንዲናዘዙ ሌላ የንስሃ ጊዜ ሰጣቸው። ነገር
ግን በእግዚብሔርና በእሴቶቹ ላይ ማመጻቸውን ቀጠሉ፤ የእነዚህ ሕዝቦች
ኃጢአት በተፈጸመ ጊዜ የእነርሱን ግዛት ለዕብራውያን አዲስ መኖሪያ አድርጎ
ሊሰጥ እግዚአብሔር ዝግጁ ነበር።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ከዚህ በተጨማሪ፣ በምድሪቱ የሚኖሩ ሕዝቦችን በሁለት ያልተለመዱ
ግን እጅግ ውጤታማ በሆኑ መንገዶች እሥራኤላውያን ወደ ምድሪቱ
ከመግባታቸው በፊት እንደሚያስወጣ ቃል ገባ፡- (1) ኃጢአተኛ በሆኑ
ሕዝቦች ላይ ሽብርና ፍርሃት በመላክ እና (2) ሕዝቡን በሚያባርሩ ተርቦች
አማካይነት ነበር። እሥራኤላውያን ወደ አዲሱ ግዛት ከመድረሳቸው በፊት
ጠላቶቻቸው ቦታውን ለቅቀው በመውጣት “ጀርባቸውን አዙረው ይሸሻሉ”
(ዘጸ. 23:27፣ 28)።
የተስፋይቱን ምድር በመውረስ ሂዳት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው
የእግዚአብሔር መልአክ ነው። እሥራኤልን የመራው፣ ግዛቶችን ድል ያደረገው
እና እሥራኤልን ከጥቃት የተከላከለው ይህ መልእክተኛ ክርስቶስ ነበር። በቀን
ጊዜ የደመና አምድና በሌሊት ጊዜ የእሳት አምድ ሆኖ ይመራቸው የነበረው
እርሱ ነበር። መለኮታዊ ሥልጣን ስለነበረው እሥራኤላውያን ትከረት ሰጥተው
ሊሰሙት ይገባ ነበር (ዘጸ. 23:21)። የእግዚአብሔርን ፈቃድ አለመቀበልና
በእርሱ አመራር አለማመን የሚያደርጉትን ጉዞ ያወሳስብባቸዋል።
አህዛቦች መንገዳቸውን እንዲለውጡ እግዚአብሔር ብዙ ዓመታትን የመስጠቱ
ሀሳብ ስለ እግዚአብሔር ፀጋ ምን ያስተምረናል? ፀጋን መቀበል እምቢ
ለሚሉት ስላሉ ገደቦችስ ምን ያስተምረናል?
ማቴ. 5:38–48ን ያንብቡ። ኢየሱስ ለበቀል ሕግ ትርጉም የሰጠው እንዴት ነበር? እኛ ዛሬ መተግበር ያለብን እንዴት ነው?
በተራራው ስብከት ኢየሱስ ሕዝቡ በደንብ የሚያውቁአቸውን
ጥቅሶች ከብሉይ ኪዳን ጠቀሰ። ነገር ግን ለብዙ መቶ ዓመታት እነዚህ ሕግጋት
ከተሰጡበት ዓላማ ከራቁትና በወቅቱ የነበሩ መምህራን ከሚሰጡት ትርጉም
ተቃራኒ የሆነ ነገር ይናገሩ ነበር።: ይህ ማለት የሰው ወግ የእግዚአብሔርን
ቃል አላማ የደበቀ ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ አጋጣሚዎች (የሰንበትን ደንቦችና
እነዚህ ደንቦች በሰንበት ሕግ ላይ ስላመጡት ነገሮች ያስቡ) የተሰጡበትን
አላማና ትርጉምም አዛብቶ ነበር። ኢየሱስ በተናገራቸው ቃላት የእነዚህን
ሕጎች የመጀመሪያ ትርጉም እየመለሰ ነበር።
በተራራው ስብከት የአድማጮቹን አእምሮ ወደ ጥቅሶቹ የቀደመው
ዓላማና ትርጉም በማመልከት ኢየሱስ ከእነዚህ የተሳሳቱ ትርጎሞች መካከል
አንዳንዶቹን ለማረም እየሞከረ ነበር።
ዘጸ. 21:24 ላይ “ዓይን ለዓይን፣ ጥርስ ለጥርስ” የሚለው ጥቅስ
በማቴዎስ 5:38 ላይ (“ለቀደሙት እንዲህ እንደተባለ ሰምታችኋል . . . እኔ
ግን እላችኋለሁ”) በማለት የተጠቀሰ ሲሆን የበቀል ሕግ (lex talionis)
የሚለውን የሚያመለክት ነበር። ይህ ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሌሎች
ቦታዎችም ጥቅም ላይ ውሏል (ዘሌ. 24:20፣ ዘዳ. 19:21)።
የዚህ ሕግ የመጀመሪያው ዓላማ ማንኛውንም ግላዊ በቀል ለመቃወም
ነበር። ደም እንዲፈስ የሚያደርግ ጠብን ወይም አስቀድሞ ምርመራ ሳይደረግ
የሚፈጸም በቀልን ለማቆም ነበር። ዳኞች የደረሰውን ጉዳት ይመረምሩና ተገቢ የሆነ
የገንዘብ ካሣ ይወሰናል ወይም ይከፈላል። ይህ ይደረግ የነበረው “ሕግ መፈጸም
ያለበትን ተግባር ሰዎች በራሳቸው እንዳይፈጽሙ” ለመከልከል ነበር። ፍትህ
መስፈን አለበት፣ ነገር ግን ይህ መደረግ ያለበት በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት ነው።
እነዚህን ማህበራዊ ሕጎች ለሙሴ የሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ የዚህን
ሕግ ዓላማ ያውቅ ነበር፤ ስለዚህ መጀመሪያ በተሰጠው ዓላማ መሰረት
ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል። ከዚህ በስተጀርባ ያለው
ሀሳብ ፍትህና እርቅ በማምጣት ሰላምን መመለስ ነበር።
በአንድ መልኩ ፍትህ የበቀል ዓይነትን ያመለክታል ብሎ ሰው ሊከራከር
ይችላል። የእነዚህ ሕጎች ተገቢ ትግበራ በፍትህና በበቀል መካከል ትክክለኛ
ሚዛን ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረት ይመስላል።
አንድ ቀን ፍትህ እንደሚመጣ ማወቃችን ዛሬ በዓለም የምናየውን ኢ-ፍትሃዊነት
ሁሉ በአግባቡ እንድንይዝ ሊረዳን የሚገባው እንዴት ነው?
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
“ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና” (ሮሜ 12:19፤ ደግሞ ዘዳ. 32:35ን ይመልከቱ)። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የሚገኙት ተስፋና ትዕዛዝ ምንድር ናቸው? ግንኙነታቸውስ ምን ያህል የቀረበ ነው?
በጥንቱ የእሥራኤላውያን ዘመን የተጓደለውን ፍትህ ጌታ እስኪመልስ
ድረስ የዳኞቹ ሥራ ሕጉን መተግበርና ጥፋት ወይም ጉዳት ሲደርስ ሕጉን ተፈጻሚ
ማድረግ ነበር። ነገር ግን መጀመሪያ ጭብጦቹን ማግኘት ያስፈልጋቸው ነበር።
ችግሩ ግን በክርስቶስ ዘመን የነበሩ የሕግ መምህራን ይህን ሕግ ለግላዊ በቀል
መንገድ በሚከፍት ሁኔታ ሥራ ላይ አውለውት ነበር። ይህ ከመደረጉ የተነሣ
መርሁ ከአውዱ ውጭ ስለሆነ የመጀመሪያው ዓላማ ጠፍቶ ነበር። ከዚህ የተነሣ
ሕግ የሚከለክለውን ነገር ትክክል እንደሆነ አድርጎ መከላከል ይታይ ነበር።
ማቴ. 6:4፣ 6፤ ማቴ.16:27፤ ሉቃስ 6:23፤ እና 2ኛ ጢሞ. 4:8ን
ያንብቡ። ኢየሱስ የሽልማትና የቅጣት መርሆዎችን እንዴት ይመለከት እንደነበር
እነዚህ ጥቅሶች ምን ይነግሩናል?
ኢየሱስ የሽልማትና የቅጣት ሕጎች ተቃዋሚ አልነበረም። ፍትህ
የመርህ ጉዳይ ሲሆን የሕይወት ወሳኝ ክፍል ነው። ነገር ግን ማንም ሰው
የፈራጅን፣ የዳኛን እና “ሕግ ፈጻሚን” ሚና ለራሱ መውሰድ የለበትም።
ፍትህን ማዛባት ለእኛ ምንኛ ቀላል ነው! ለደረሰው ጉዳት ዋጋ መክፈል
የእኛ ተግባር አይደለም። የሆነ ክፋት መፍትሄ ሊሰጠው የሚገባ ከሆነ መደረግ
ያለበት በፍርድ ቤት ሲሆን ይህ ደግሞ የዳኞች ሥራ ነው።
በዚህ አውድ “በሰማይ ያለው አባታችን ፍጹም እንደሆነ” እኛም
ፍጹማን እንድንሆን ኢየሱስ ይነግረናል። ራስ ወዳድነት የሌለበት ፍቅር
የእግዚአብሔር ዋንኛው ባህርይ ነው። ተከታዮቹ ጠላቶቻቸውን እንዴት
መውደድና ለሚያሳድዱአቸው እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው ያስተምራቸዋል።
እውነተኛ ፍጽምና መውደድ፣ ይቅርታ ማድረግ እና ለማይገባቸው እንኳን
ምህረት ማድረግ ነው (ሉቃስ 6:36)። የእግዚአብሔርን ባህሪይ ማንጸባረቅ
ማለት ይህ መርህና እርሱ የሚያስከትላቸው ድርጊቶች ማለት ነው።
በታዘዝነው መሰረት ከዕለት ዕለት ማፍቀርን መማር የምንችልባቸው መንገዶች ምንድር ናቸው? ይህ ሁልጊዜ ለራስ መሞትን የሚያካትተው ለምንድር ነው?
አባቶችና ነቢያት ከሚለው የኤለን ጂ ኋይት መጽሐፍ
“ለእሥራኤል የተሰጠው ሕግ” የሚለውን ከፍል ከገጽ 310–314 ላይ ያንብቡ።
በጠላታችን ግዛት ስለምንኖር እርሱ ባዘጋጃቸው ስልታዊ በሆኑ
የማታለያ ዘዴዎች በተጨባጭ ሕይወት ጉዳት ማስተናገዳችን አያስደንቅም።
ከኃጢአትና ከምንኖርበት በኃጢአት የተሞላ የወደቀ ዓለም የተነሣ ከእኛ
መካከል ሕመምና ስቃይ ያልደረሰበት ማን ነው? እንደ አለመታደል ሆኖ ይህ
ሁኔታ ዛሬ የሕይወት አካል ሆኗል። ነገር ግን በዚህ ውስጥ ማለፍ እንድንችል
እግዚአብሔር ኃይል ይሰጠናል።
“ክቡር አዳኝ በሚያስፈልገን ጊዜ እርዳታ ይልክልናል። ወደ
ሰማይ የሚመራው መንገድ በእርሱ ዱካዎች ተቀድሷል። እግሮቻችንን
የሚያቆስለው እያንዳንዱ እሾክ የእርሱን እግሮች አቁስሏል። እንድንሸከመው
የተጠራነውን እያንዳንዱን መስቀል ከእኛ በፊት እርሱ ተሸክሞታል።
ጌታ ነፍስን ለሰላም ለማዘጋጀት ግጭቶችን ይፈቅዳል። የመከራው ጊዜ
ለእግዚአብሔር ሕዝብ አስፈሪ ሁኔታ ነው፤ ነገር ግን እያንዳንዱ እውነተኛ
አማኝ ወደ ላይ የሚመለከትበት እና የቃል ኪዳኑ ቀስተ ደመና ሲከበው
በእምነት የሚያይበት ጊዜ ነው።”—Ellen G. White፣ The
Great Controversy፣ p. 633.
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
1. ሰዎች በዘመናት ሁሉ እግዚአብሔር እነዚያን አህዛቦች
ሰዎች በዘመናት ሁሉ እግዚአብሔር እነዚያን አህዛቦች
ከምድራቸው ያባረረበትንና አንዳንዴም ከምድር ገጽ ጨርሶ
ያጠፋቸውን እውነታ ለመረዳት ሲታገሉ ኖረዋል። በርግጥ
የሚረብሽ ነገር ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር ፍትህንም
ማሳየት እንዳለበት መረዳታችን በእነዚህ ክስተቶች ውስጥ እንኳን
የእርሱ ፍትህ ብቻ ሳይሆን ፍቅሩም እንደተገለጠ እንድንታመን
ሊረዳን የሚገባው እንዴት ነው?
2. ኢየሱስ “ስለዚህ በሰማይ ያለው አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ
ኢየሱስ “ስለዚህ በሰማይ ያለው አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ
እናንተም ፍጹማን ሁኑ” (ማቴ. 5:48) ያላቸው ቃላት
ጠላቶቻችንን፣ እኛን የሚጠሉንን ጨምሮ ሌሎችን ስለመውደድ
የሚናገር እውነታ ስለመሆኑ ያስቡ። ኢየሱስ ከእነዚህ ሌሎች
ትዕዛዛት በኋላ ይህንን ትዕዛዝ ያስከተለው ለምንድር ነው?
በዚህ ቦታ “ፍጹም” ስለመሆን ብቻ ሳይሆን “በሰማይ ያለው
አባት ፍጹም” እንደሆነ ፍጹማን ስለመሆን ምን እየነገረን ነው?
3. ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ እግዚአብሔር ሕግና ስለ ተግባሮቹ
ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ እግዚአብሔር ሕግና ስለ ተግባሮቹ
አዎንታዊና ስሜትን ከፍ የሚያደርግ አመለካከት ነበረው። ሆኖም
ሕግን በተሳሳተ መልኩ መጠቀምን ይቃወም ነበር። “ከጸጋ በታች
እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁም” ያለው አባባል ምን ማለት
ነው(ሮሜ 6:14፣ )? ሕግን በስህተት የምንጠቀምባቸው
መንገዶች ምንድር ናቸው?
4. በፍትህና በበቀል መካከል ያለው ልዩነት ምንድር ነው? ሙሉ
በፍትህና በበቀል መካከል ያለው ልዩነት ምንድር ነው? ሙሉ
በሙሉ የተለያዩ ጽንሰ ሀሳቦች ናቸው ወይስ ተመሳሳይ የሆነ ሀሳብ
የተለያዩ መገለጫዎች ናቸው? ለፍትህ ያለን ፍላጎት የበቀል
ፍላጎት እንዳልሆነ እንዴት እናውቃለን?