የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ዘጸአት



3ኛ ሩብ ዓመት 2025


ነሐሴ 24 - 30

10ኛ ትምህርት

Aug 30 - Sep 5




ቃል ኪዳኑና ንድፉ



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ: ዘጸ. 24:1–18፤ 1ኛ ቆሮ. 11:23–29፤ ዘሌ. 10:1፣ 2፤ ሕዝ. 36:26–28፤ ዘጸ. 25:1–9፤ ዘጸ. 31:1–18።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ሙሴም መጣ ለሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ ሥርዓቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፦እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን ብለው መለሱ” (ዘጸ. 24:3)።

ፈጣሪያቸውና አዳኛቸው የሆነው አምላክ ከሕዝቡ ጋር ለመኖርና በመከካከላቸው ለማደር ፈለገ። ከእርሱ ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዲኖረን ፈጠረን። ሆኖም ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነት ሊመሰረት የሚችለው በጊዜና በጥረት እስከሆነ ድረስ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረን አምዳዊ ግንኙት ሊፈጠር የሚችለውም በተመሳሳይ መንገድ ነው። ይህ ከፍ ከፍ የሚያደርግና በእድገት የተሞላ ልምምድ ነው፣ ነገር ግን ይህ ሊሆን የሚችለው ከእርሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ስንችል ብቻ ነው። በተግባራዊ አገላለጽ ይህ ማለት ቃሉን ማጥናት (እግዚአብሔር ሲናገረን)፣ መጸለይ (ልባችንን ለእግዚአብሔር መክፈት)፣ እና ስለ ክርስቶስ ሞት፣ ትንሣኤና መመለስ ለሌሎች መመስከር (በእግዚአብሔር ተልዕኮ መካፈል) ማለት ነው።

እግዚአብሔር ሲባርከን ለሌሎች የበረከት መተላለፊያ መስመሮች እንሆናለን።

ትኩረታችን መሆን ያለበት በራሳችን ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ነው (ዕብ. 12:1፣ 2)። ከእርሱ ጋር ስንገናኝ እግዚአብሔር የእርሱን ትምህርቶች እንድንከተል፣ ማለትም ቃሉን እንድንታዘዝ ኃይል ይሰጠናል።

በመጨረሻው ትውልድ የሚኖሩ የክርስቶስ ተከታዮች “የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስ እምነት ያላቸው” (ራዕይ. 14:12) ተብለው መገለጻቸው አያስደንቅም። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

በርግጥ ቀላል ነው፤ እግዚአብሔርን እንወደዋለን፤ ከዚህ ፍቅር የተነሣ ደግሞ እንታዘዘዋለን። *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለጳጉሜ 1 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ

ነሐሴ 25
Aug 31

መጽሐፉና ደሙ


ዘጸ. 24:1–8ን ያንብቡ። የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብና ደምን መርጨት በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ያለውን ቃል ኪዳን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ረገድ ምን ሚና ይጫወታሉ?



በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸው እግዚአብሔር የግንኙነት አምላክ ነው። ለአምላካችን አስፈላጊው ነገር ዕቃ ወይም አጀንዳ ሳይሆን ሰው ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር ለሰዎች ትኩረት ይሰጣል። የእርሱ ተግባራት ቀዳሚ ዓላማ ከሰብአዊ ዘር ጋር የግል ግንኙነት መፍጠር ነው። “ፍቅር” የሆነው አምላክ የግንኙነት ጉዳይ ግድ ሊለው ይገባል። ያለ ግንኙነት እንዴት ፍቅር ሊኖር ይችላል?

ኢየሱስ እንዲህ አለ፡-“ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ” (ዮሐንስ 12:32)። ለእግዚአብሔር ግድ የሚለው የእኛ የሥነ-ምግባር ባህሪይ፣ ትክክለኛ አስተምህሮ ወይም የትክክለኛ እርምጃዎች ስብስብ ብቻ ሳይሆን ከሁሉ በላይ ከእኛ ጋር የቀረበ ግላዊ ግንኙነት መፍጠር ነው። ሁለቱ የፍጥረት ተቋማት (ዘፍጥረት 1–2) የሚናገሩት ስለ ግንኙነት ነው። የመጀመሪያው ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረውን አምዳዊ ግንኙነት (ሰንበት) የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛው በሰዎች መካከል የሚኖረውን አግድማዊ ግንኙነት (ጋብቻ) የሚገልጽ ነው።

በሲና ቃል ኪዳኑን ማጽደቁ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር እንዲኖረው የፈለገውን ግንኙነት ለማጠንከር ነበር። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሕዝቡ እግዚአብሔር በሚፈልግብን ነገር ሁሉ እንታዘዘዋለን በማለት ሁለት ጊዜ በጩኸት ቃል ኪዳናቸውን አጽንተው ነበር። “እግዚአብሔር ያለውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን” ብለው አወጁ። ይህን ያሉት ከልባቸው ቢሆንም ደካማነታቸውን፣ አቅመ-ቢስነታቸውንና ኃይል የለሽነታቸውን አላወቁም ነበር። እሥራኤል የእግዚአብሔርን መመሪያዎች መከተል የሚችሉት በክርስቶስ መልካም ተግባር ብቻ እንደሆነ ለማሳየት በመጽሐፉ ላይ ደም ተረጭቶ ነበር።

ሰብአዊ ተፈጥሮአችን ተሰባሪ፣ ደካማ እና ሙሉ በሙሉ ኃጢአተኛ መሆኑን መቀበል አንፈልግም። በውርስ ያገኘነው ወደ ክፉ የማዘንበል ሁኔታ አለ። መልካም ማድረግ እንድንችል ከራሳችን ውጭ ከሆነ ኃይል ዕርዳታ ማግኘት አለብን። ይህ እርዳታ የሚመጣው ከላይ፣ ከእግዚአብሔር ጸጋ ኃይል፣ ከቃሉ እና ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። ይህን ሁሉ ማግኘት እየቻልን እንኳን ክፉ በቀላሉ ወደ እኛ ይመጣል። አይደለም?

ከእግዚአብሔር ጋር የቀረበ ግንኙነት መፍጠር ያኔ በሲና ለነበሩ ሰዎች አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ ዛሬም ለእኛ አስፈላጊ የሚሆነው ከዚህ የተነሣ ነው። “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን" (ዘጸ. 24:3)።

እናንተም ተመሳሳይ ነገር ተናገግራችሁ ሳይሆንላችሁ የቀረው ስንት ጊዜ ነው? ለዚህ ብቸኛው መፍትሄ ምንድር ነው?

ነሐሴ 26
Sep 1

እግዚአብሔርን መመልከት


ዘጸ. 24:9–18ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ለእሥራኤል ልጆች የተሰጣቸው አስደናቂ ልምምድ ምን ነበር?



ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን እንደገና ከመሰረቱ በኋላ ሙሴ በድጋሚ ወደ ሲና ተራራ ወጣ። በዚህ ወደ ተራራው የመውጣት ጅምር ላይ ሙሴ ብቻውን አልነበረም። 73 የእሥራኤል መሪዎች አጅበውት ነበር።

ለመሪዎቹ ይህ ልምምድ ከሁሉ ከፍ ያለ ልምምድ ነበር፡- እግዚአብሔርን (የመለኮትን መገለጥ) አዩ፣ በዚህ አስደናቂ እውነታ ላይ ጥቅሱ ሁለት ጊዜ አጽንዖት ይሰጣል። መሪዎቹ አብረው በመብላት ከእግዚአብሔር ጋር ቃል የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ኪዳንን የሚያትሙበት ጊዜም ነበር። ይህ ትልቅ የምግብ ግብዣ ሲሆን ጋባዡ (አስተናጋጁ) የእስራኤል አምላክ ነበር። እግዚአብሔር እነዚህን መሪዎች እጅግ አክብሮአቸው ነበር።

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን በመካከለኛው ምሥራቅ (እስከተወሰነ ደረጃ ዛሬም) አብሮ መብላት ከፍ ያለ ልምምድ፣ ትልቅ ክብር፣ እና ልዩ እድል ነበር። ይቅርታን ይሰጣል፣ የወዳጅነት ግንኙነትንም ይፈጥራል። ለእርስ በርስ መቆምንና በችግርና በመከራ ጊዜ አብሮ መሆንን ያሳያል። አብረው በመብላታቸው በቃላት ባይገልጹትም በአንዳቸው ላይ የሆነ ነገር ቢከሰት ሌላኛው ግለሰብ መጥቶ የመርዳት ግዴታ እንዳለበት ለእርስ በርሳቸው ቃል እየተገባቡ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግብዣን አለመቀበል እጅግ አስከፊ ከሆኑ ስድቦች መካከል አንዱ ነው። ይህ መረዳት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢአተኞች ጋር ስለበላ እጅግ የተነቀፈበትን ታሪክ እንድንረዳ ይረዳናል (ሉቃስ 5:30)። አማኞች የጌታን እራት ሥነ-ሥርዓት በሚፈጽሙበት ጊዜ እንደ እነርሱ ኃጢአተኞች ከሆኑ አማኞች ጋር የቀረበ ግንኙነት ይፈጥራሉ።

ይህን ሥርዓት ስንፈጽም በኢየሱስ ያገኘነውን ይቅርታና ድነት በተግባር እናሳያለን (ማቴ. 26:26–30፣ ማርቆስ 14:22–25፣ 1ኛ ቆሮ. 11:23–29ን ይመልከቱ)።

በሚያሳዝን ሁኔታ ከሙሴ ጋር ወደ ተራራው ከወጡ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ኃጢአት በመስራት ሕይወታቸውን አጡ (ዘሌ. 10:1፣ 2፣ 9 ይመልከቱ)። ይህን የመሰለ ጥልቅ ልምምድ ከእግዚአብሔር ጋር ቢኖራቸውም ልምምዱ አልለወጣቸውም ነበር። እውነትን መያዝና የቅዱስ ዕድሎች ባለቤት መሆን ማለት ወዲያውኑ መለወጥ ላለመሆኑ ይህ እንዴት ያለ ኃይለኛ ትምህርት ነው። እነዚህ ሰዎች ይህንን ልምምድ አግኝተው ኋላ የፈጸሙትን አሳዛኝ ተግባር ለመፈጸም የመጨረሻዎቹ ሰዎች መሆን ነበረባቸው። እጅግ ከመታደላቸው በተጨማሪ የአሮን ልጆች በሆኑ በእነዚህ ሰዎች ታሪክ ላይ ጊዜ ወስደው ያሰላስሉ። እኛም እንደ አድቬንቲስትነታችን፣ ከተሰጠን ብርሃን የተነሣ የታደልን ስለሆንን ይህ እንዴት ያለ ማስጠንቀቂያ ሊሰጠን ይገባል?

ነሐሴ 27
Sep 2

ለመታዘዝ ኃይል


ሕዝቅኤል 36:26–28ን ያንብቡ። በሕይወታችን መታዘዝ የምንችለው እንዴት ነው?



እሥራኤላውያን በሶስት አጋጣሚዎች እግዚአብሔርን እንደሚታዘዙ በግለት ተናግረው ነበር (ዘጸ. 19:8፤ ዘጸ. 24:3፣ 7)። ሰዎች ደካማ፣ ጎስቋላ፣ ተሰባሪና ኃጢአተኛ መሆናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ቢያስተምርም መታዘዝ አስፈላጊ ነው። ይህን በተመለከተ ኢያሱ አድማጮቹን እንዲህ በማለት አስታወሳቸው፡- “እግዚአብሔርን ማምለክ (ማገልገል) አትችሉም” (ኢያሱ 24:19)። ይህ አሳዛኝ እውነት በጥንቶቹ እሥራኤላውያን ታሪክ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሕዝቦቹ ታሪክ የተገለጠ ነው።

ታዲያ እግዚአብሔርን በታማኝነት መከተል የምንችለው እንዴት ነው? መልካሙ ዜና እግዚአብሔር የሚያዘውን ነገር እንድንፈጽም ኃይል ይሰጠናል። በውስጣችን የሌለው እርዳታ ከውጭ በመምጣት እግዚአብሔር የሚፈልግብንን ነገር ማድረግ እንድንችል ያደርገናል። ይህ የእርሱ ሥራ ነው።

በሕዝቅኤል 36፡26ና 27 ላይ ባለው ሥነ መለኮታዊ ማጠቃለያው እምብርት ውስጥ ነቢዩ ሕዝቅኤል ይህንን ነጥብ ግልጽ ያደርገዋል። የልብ ቀዶ ጥገና ማድረግ የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ይህን የሚያደርገው የድንጋይ ልባችንን አስወግዶ ገር በሆነ የስጋ ልብ በመተካት ነው።

እግዚአብሔርን ለመከተል መወሰን እንችላለን፣ ይህ የእኛ ሚና ነው።

ቀስ በቀስ ራሳችንን ለእርሱ አሳልፈን ለመስጠት መምረጥ አለብን። ይህ የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔርን ለማምለክ አስበንበት ያደረግነውን ምርጫ እንኳን ለመፈጸም ኃይል ስለሌለን ነው። ነገር ግን ድክመታችንን ለእግዚአብሔር ስንሰጥ እርሱ ያበረታናል። ጳውሎስ እንዲህ ይላል:- “ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና” (2ኛ ቆሮ 12:10)። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

በሕዝቅኤል 36፡24-30 ላይ ያለውን መለኮታዊ “እኔ”ን ልብ ይበሉ። እግዚአብሔር ሕጉን በጥንቃቄ እንድትጠብቁ ይሰበስባችኋል፣ ያነጻችኋል፣ ያንቀሳቅሳችኋል፣ ይሰጣችኋል፣ ያስቀምጣችኋል፣ ያነሳሳችኋልም።

ራሱን ከእናንተ ጋር ስለሚያመሳስል ከእርሱ ጋር የቀረበ ግንኙነት ከፈጠራችሁ የእርሱ ሥራ የእናንተ ሥራ ይሆናል። በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ያለው አንድነት ውጤታማ፣ ኃይለኛ እና ሕያው ይሆናል።

በድጋሚ ይህ ንባብ አጽንዖት የሚሰጠው በእግዚአብሔር አድራጊነት ላይ ነው። አዲሱ ኪንግ ጄምስ እትም እንዲህ ይነበባል፡- “መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ” (ሕዝ. 36:27)። እግዚአብሔር እንዲታዘዙት ሕዝቡን ያዝና እንዲተገብሩት ኃይልን ይሰጣል። እግዚአብሔር ከሕዝቡ የሚፈልግባቸውን ነገር እንዲያደርጉት ሁልጊዜ ይረዳቸዋል። ጽድቅና ድነት የእግዚአብሔር ሥጦታዎች እንደሆኑ ሁሉ (ፊልጽ. 2:13) መታዘዝም የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው (የእኛ መልካም አፈጻጸም ወይም ስኬት አይደለም)። መታዘዝ የሚያስችለንን ኃይል ሊሰጠን ቃል እስከተገባልን ድረስ በኃጢአት መውደቅ የሚቀልለን ለምንድር ነው?

ነሐሴ 28
Sep 3

በሕዝቡ መካከል


እግዚአብሔር በተለያዩ ዘዴዎች ሕዝቡን ሲያስተምር የነበረ ሲሆን ከእነዚህ ዘዴዎች አንዱ በቤተ መቅደስ አማካይነት ነበር። አገልግሎቶቹ በሙሉ ወደ ኢየሱስ የሚያመለክቱ ሲሆኑ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የሚፈጸመው የድነት ዕቅድ ማሳያ ትምህርቶች ነበሩ። ዘጸ. 25:1–9ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የታዩት ምን ወሳኝ፣ ተግባራዊ እና ሥነ-መለኮታዊ እውነቶች ናቸው?



ምንም እንኳን እግዚአብሔር እሥራኤላውያንን እየመራ የነበረ እና ቅርባቸው ቢሆንም ሙሴ ቤተ መቅደስን እንዲገነባ እንዲህ በማለት መመሪያ ሰጠው፡- “በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ” (ዘጸ. 25:8)። እግዚአብሔር በእርግጥ ከእነርሱ ጋር መሆኑን ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ ሊያሳያቸው ፈለገ። ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ስህተት ቢሰሩም አልተዋቸውም ነበር። “በኋላ እንደገና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ስላገኙ” (Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 343)፣ መለኮታዊ ትዕዛዝ ተሰጣቸውና ቤተ መቅደሱን የመገንባቱ ሂደት ተጀመረ።

እግዚአብሔር ከሰማየ ሰማያት ትልቅ ስለሆነ እና ሰማያት ሊይዙት ስለማይችሉ ሰው በሰራው ቤተ መቅደሶችና ሕንጻዎች እንደማይኖር መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጣል (የሐዋ. ሥራ 7:47–50)። ጳውሎስ አቴና በነበረው አርዮስፋጎስ በሚባል ቦታ እንዲህ ብሏል፡- “ ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም” (የሐዋ. ሥራ 17:24)። ደግሞ ንጉሡ ሰለሞን እንዲህ አለ:- “ በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!” (1ኛ ነገሥት 8:27)። ቤተ መቅዱሱ እግዚአብሔር መገኘቱን ለእነርሱ የሚገልጥበት ቦታ ነበር።

እሥራኤላውያን ቤተ መቅደሱን ለመገንባት የፈቃድ ሥጦታ ማምጣት ነበረባቸው። ወርቅን፣ ብርን፣ ነሃስን፣ የግራር እንጨትን፣ ልዩ ልዩ ውብ ልብሶችን፣ የወይራ ዘይትን እና ቅመማ ቅመሞችን ጨምሮ የከበሩና ውድ ስጦታዎችን መስጠት ነበረባቸው።

በዘጸአት 25:10–27:21 ላይ ስለ ቤተ መቅደሱና ስለ አገልግሎቶቹ ብዙ ዝርዝሮች ተሰጥተውናል። እግዚአብሔር ለሙሴ የቃል ኪዳኑን ታቦት፣ የሕብስት ጠረጴዛን፣ መቅረዙን፣ መሰዊያዎቹን፣ መጋረጃዎቹን፣ ቀለማቱንና ልኬቶችን ጨምሮ ቤተ መቅደሱን እንዴት መገንባትና ማስጌጥ እንዳለበት የሚገልጹ ልዩ መመሪያዎችን የያዘ ንድፍ ሰጠው።

ሙሴ እግዚአብሔር ባሳየው ምሳሌ መሰረት (ዘጸ. 25:9፣ 40፤ ዘጸ. 26:30) የሰማያዊው ቤተ መቅደስ ነጸብራቅ የሆነውን ቤተ መቅደስ መገንባት ነበረበት (ዕብ. 8:1፣ 2፤ ዕብ. 9:11)። ምድራዊው ቤተ መቅደስ እስከ ኢየሱስ ሞትና ምድራዊውን ቤተ መቅደስ ዋጋ ቢስና ከንቱ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ባደረገው በሰማያዊው ቤተ መቅደስ እስከሚያደርገው አገልግሎት ድረስ ወሳኝ ሥራ ሰርቷል። ይህም እውነት ክርስቶስ በሞተ ጊዜ ከቅድስተ ቅዱሳን ፊት የነበረው መጋረጃ በመቀደዱ ተመስሏል (ማቴ. 27:51፣ ማርቆስ 15:38)።

ነሐሴ 29
Sep 4

በእግዚአብሔር መንፈስ የተሞላ


ለቤተ መቅደስ አገልግሎቶች የሚደረገውን ዝግጅት በተመለከተ በእያንዳንዱ ዝርዝር ላይ እግዚአብሔር ለሙሴ መመሪያ ሰጠው። ካህናት የክህነት ልብስ ሊኖራቸው ይገባ ነበር፣ ነገር ግን ሊቀ ካህኑ የእሥራኤልን ልጆች ስሞች የያዘ የተለየ ኤፉድ ይለብስ ነበር። ደግሞም ኡሪምን እና ቱሚምን የያዘውንና በልቡ ላይ መሆን ያለበትን የደረት ኪስ ይለብስ ነበር (ዘጸ. 28)። ሁሉም ካህናት መቀደስ ነበረባቸው (ዘጸ. 29)። ሌሎች በጥንቃቄ መዘጋጀት የነበረባቸው ነገሮች የእጣን መሰዊያ፣ መታጠቢያ ሳህን፣ የቅብዓት ዘይት እና ዕጣን ነበሩ (ዘጸ. 30)። ዘጸ. 31:1–18ን ያንብቡ። የቤተ መቅደሱ ዝርዝሮችና ተዛማጅነት ያላቸው አገልግሎቶች ሁሉ እንዲዘጋጁና ውብና ተገቢ በሆነ መንገድ እንዲገነቡ እግዚአብሔር ምን የተለየ ድጋፍ ሰጠ?



በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔር አንድን ግለሰብ በመንፈስ እንደሚሞላ ይነበባል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ባስልኤል በቤተ መቅደሱ ላይ በብልሃት እንዲሰራ ኃይል ተሰጥቶታል። ይፈለግ በነበረው የእጅ ሙያ በአዳዲስ ክህሎቶች፣ መረዳትና እውቀት ተሞልቶ ነበር፤ ይህ ማለት እግዚአብሔር እነዚህን ችሎታዎች አስታጥቆት ነበር ማለት ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ይህን ሥራ እንዲረዱ እግዚአብሔር ለኤልያብና ለሌሎች ብዙ የእጅ ባለሙያዎች ተመሳሳይ የሆነ መንፈስ ሰጥቷቸው ነበር።

በዚህ ሁሉ የፈጠራ ሥራ መካከል እግዚአብሔር እንዲቀድሳቸው በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ምልክት እንዲሆን የእግዚአብሔር ሰንበት ቀርቧል። ይህ ማለት አራተኛውን ትዕዛዝ መጠበቅ ከቅድስና ጋር ግንኙነት አለው ማለት ነው። ኋላ ሕዝቅኤል እንዲህ በማለት አቅርቧል፡- “ የምቀድሳቸውም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ምልክት ይሆኑ ዘንድ ሰንበታቴን ሰጠኋቸው” (ሕዝ. 20:12)።

ሰንበት እግዚአብሔር ፈጣሪያችን (ዘፍ. 2:2፣ 3)፣ አዳኛችንና አምላካችን (ዘዳ. 5:15፤ ማርቆስ 2:27፣ 28) የመሆኑ ማስታወሻ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ የመሆኑ ማስታወሻም ነው። በመገኘቱ ሰዎችን ይለውጣል፤ ሰዎች በመንፈሱና በቃሉ አማካኝነት አፍቃሪ፣ ቸር፣ ከራስ ወዳድነት የጸዳ እና ይቅር ባይ ባህርይ ለማንጸባረቅ ያድጋሉ።

እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው የመጨረሻው ስጦታ አሥርቱ ትዕዛዛት ነበር (ዘጸ. 31:18)። አሥርቱ ትዕዛዛት የተጻፉባቸውን የድንጋይ ጽላቶች ጽፎ የሰጠው እግዚአብሔር ራሱ ነበር (ዘጸ. 31:18፣ ዘዳ. 9:9– 11)። እነዚህ ጽላቶች በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ከስርየት መክደኛው ሥር ባለው የቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ መቀመጥ ነበረባቸው (ዘጸ. 25:21)። “የስርየት መቀመጫ” የሚለው ሀረግ የመጣው ከዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ማስተሰረይ” ማለት ነው። ታዲያ ይህ “የስርየት መቀመጫ” በእግዚአብሔር ሕግ ላይ የሚቀመጠው ለምንድር ነው? በዚህ ጭብጥ ውስጥ ምን ተስፋ ማየት አለብን?

ነሐሴ 30
Sep 5


ተጨማሪ ሀሳብ


“ቤተ መቅደሱና አገልግሎቱ” የሚለውን ርዕስ ኤለን ጂ ኋይት ከጻፈችው አባቶችና ነቢያት ከሚል መጽሐፍ ገጽ 343– 353ን ያንብቡ።

ቤተ መቅደሱ ለኃጢአታቸው ለተናዘዙ የእግዚአብሔር ሕዝብ ኃጢአቶች ሥርየት የሚፈጸምበት ልዩ ስፍራ ነበር። በርግጥም መላው የድነት ዕቅድ የተገለጠበትና የእሥራኤል ልጆች በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ ለእነርሱም በተወሰነ ደረጃ ዕቅዱ የተገለጠበት ቦታ ነበር። ጽድቅ፣ ቅድስናና ፍርድ ሁሉ በዚህ ቦታ ተስተምረዋል። እያንዳንዱ የእንስሳ መስዋዕት ወደ ኢየሱስ ሞት፣ የኃጢአት ይቅርታና በመጨረሻም የኃጢአትን መፋቅ ያመለክት ነበር። ከመስዋዕቶቹ ጎን ለጎን ደግሞ የጽድቅ መስፈርት የሆነው የእግዚአብሔር ሕግ መገኘት ነበር። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

“በታቦቱ ውስጥ የተቀመጠው የእግዚአብሔር ሕግ የጽድቅና የፍርድ ትልቁ ደንብ ነበር። ሕጉ በሕግ ተላላፊው ላይ ሞትን ያውጅ ነበር፣ ነገር ግን ከሕጉ በላይ የእግዚአብሔር መገኘት የሚገለጥበት የስርየት መክደኛ ነበር፤ በዚህ ቦታ በስርየቱ ሥራ ለተናዛዥ ኃጢአተኛ ምህረት ይሰጠዋል።

ስለዚህ በቤተ መቅደስ አገልግሎት የተወከለው ክርስቶስ ለድነታችን በሰራው ሥራ ‘ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ’ መዝሙር 85:10።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 349.


የመወያያ ጥያቄዎች




1. “እግዚአብሔር እንዳደርግ የሚነግረኝን ነገር ሁሉ አደርጋለሁ” “እግዚአብሔር እንዳደርግ የሚነግረኝን ነገር ሁሉ አደርጋለሁ” ያሉት ስንት ጊዜ ነው? በጥረቶችዎ ምን ያህል ስኬታማ ነዎት?

2. ሙሴ በሲና ተራራ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ለ40 ቀናት በነበረው ቆይታ ሙሴ በሲና ተራራ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ለ40 ቀናት በነበረው ቆይታ መጨረሻ ላይ እሥራኤላውያን የእርሱን ሰንበት መጠበቅ እንዳለባቸው አጽንዖት ሰጥቷል። ለዚህ ምክንያቱ የሚቀድሳቸው ጌታ ስለመሆኑ በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል ምልክት ስለሚሆን ነበር። ሰንበትን በመጠበቅ ውስጥ ቅድስና እና መቀደስ ምን ሚና ይጫወታሉ?

3. ጌታ “በመካከላቸው ያድር ዘንድ” ቤተ መቅደስ እንዲሰሩለት ፈለገ። ጌታ “በመካከላቸው ያድር ዘንድ” ቤተ መቅደስ እንዲሰሩለት ፈለገ። ይህ ቦታ ለእሥራኤላውያን የድነት ማዕከል መሆኑ እንዴት የሚማርክ ነው። እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል ያደረውና የድነት ዕቅድ በምሳሌና በጥላ የተሰራው በዚህ ቤተ መቅደስ ነበር። ይህ ለድነታችን በእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ስለ መደገፋችን ምን ይነግረናል?

4. በደም አማካይነት ኃጢአቶቻቸው በሙሉ የእግዚአብሔር ቤት በደም አማካይነት ኃጢአቶቻቸው በሙሉ የእግዚአብሔር ቤት ወደሆነው ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣሉ ማለት ምን ማለት ነው? ይህ አስደናቂ እውነት፣ በድንግዝግዝም ቢሆን፣ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያደረገልንን እና አሁን በሰማያዊ ቤተ መቅደስ እያደረገልን ያለውን ነገር የሚያንጸባርቀው እንዴት ነው?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL