የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ዘጸአት



3ኛ ሩብ ዓመት 2025


ጳጉሜ 1 - መስከረም 2

11ኛ ትምህርት

Sep 6 - 12




ክህደት (ከእምነት መለየት) እና ምልጃ



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ: ዘጸ. 32:1–6፤ መዝ. 115:4–8፤ ኢሳ. 44:9፣ 10፤ ሮሜ 1:22–27፤ ዘጸ. 32:7–32፤ ኢሳ. 53:4.


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፦ ወዮ! እኒህ ሕዝብ ታላቅ ኃጢአት ሠርተዋል፥ ለራሳቸውም የወርቅ አማልክት አድርገዋል፤ አሁን ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ አለ” (ዘጸ. 32:31፣ 32)።

ሙሴ ከእሥራኤል መንደር ተለይቶ የነበረው ለ40 ቀናት ብቻ ነበር። በዚህ ጊዜ ምን ሆነ? የእግዚአብሔር ሕዝብ ከእርሱ በመለየት ሰው የሰራውን ጣዖት፣ የወርቅ ጥጃ አመለኩ። እጅግ ኃይለኛ ከሆኑ ምልክቶች፣ ልምምዶችና ተዓምራቶች በኋላ ይህን ነገር እንዴት ማድረግ ቻሉ?

ብዙ መልሶች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ምናልባትም በሁሉም ውስጥ የተወሰነ እውነት ሊኖር ይችላል። ሕዝቡ በርግጥም እግዚአብሔር ማን እንደሆነ አላስተዋሉም ማለት ነው? ወይም ከእርሱ ጋር የነበሯቸው ኃይለኛ ልምምዶች በሥጋዊና ኃጢአተኛ ፍላጎቶች ተጋርደዋል ማለት ነው? እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ነገር ከማድነቅ ይልቅ ሁሉንም ነገር እንዲሁ እንደሆነላቸው አድርገው ተቀብለውታል ማለት ነው? መረዳታቸው በየዕለቱ ተግባራት ወይም በኃጢአተኛ አስተሳሰብ ደመና ተጋርዶ ተበላሽቷል ማለት ነው? እግዚአብሔር ላደረገላቸው የምህረት ተግባራት አመስጋኞች አይደሉም ማለት ነው? እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ኃይለኛ ነገሮች በፍጥነት ረስተውታል ማለት ነው (መዝ. 106:13፣ 21–23)? ወይስ ለሁሉም ጥፋት ተጠያቂ የሚሆነው ደካማ የሆነው የአሮን አመራር ነው? “ እግዚአብሔርም አሮንን እጅግ ተቆጥቶ ሊያጠፋው ነበር” (ዘዳ. 9:20። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

ለዚህ አስከፊ ክህደት ምክንያቶቹ ምንም ቢሆኑ፣ ስለ ሰው ኃጢአተኝነት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ኃጢአተኛ ለሆኑ ሰዎች ስላለው በጸጋ የተሞላ ፍቅሩ ከዚህ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለመስከረም 3/2018 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ

ጳጉሜ 2
Sep 7

ያልተሳካለት (ደካማ) አመራር


እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ጊዜ እንዲያሳልፍ ሙሴን ጠራው። አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ለሙሴ አጭር ጊዜ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ለእሥራኤላውያን እጅግ ረዥም ጊዜ መሰላቸው። የሚታየው መሪያቸው በመካከላቸው የለም።

ከዚህ የተነሳ ግራ ተጋቡ፣ ትዕግስት አጡ፣ ፍርሃት ያዛቸው፣ የደህንነት ስሜትም አጡ። የሚመራቸው የሚታይ አምላክ እንዲኖራቸው ፈለጉ፤ ጣዖት አምላኪ በነበረችው ግብጽ በኖሩበት ዘመን ሁሉ ያዩአቸው “አማልክት” እንዲመሩአቸው ፈለጉ። ዘጸ. 32:1–6ን ያንብቡ። የአሮን አመራር እንዲህ በሚያስገርም ሁኔታ ያልተሳካለት (ደካማ) አመራር ሊሆን የቻለው እንዴት ነው?



አሮን በዚህ አጋጣሚ መቆም አቃተው። አጋጣሚውን ተጠቅሞ ትክክል የሆነ ነገር ማድረግ ሳይችል ቀረ። በእግዚአብሔር ከመታመን ይልቅ የብዙሃንን ፊት በመፍራት ተልፈሰፈሰ። ሕዝቡም እንዲህ በማለት የማይታሰብ ነገር ጠየቁት፡- “ ተነሥተህ በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን” (ዘጸ. 32:1)፣ እርሱም በሀሳባቸው ተስማማ።

ጠዖቱን እንዲሰራላቸው ሕዝቡ በፈቃዳቸው ወርቅ ሰጡት፤ አሮንም እነርሱን ማስቆም አለመቻል ብቻ ሳይሆን ወርቅ እንዲሰጡ ጠየቃቸው። ከዚያ በኋላ ይህን የውሸት አምላክ በመስራት ሥራ ላይ ተሳተፈ። በኋላም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፡- “እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አላቸው” (ዘጸ. 32:4)። እጅግ ኃጢአተኛ፣ ክፉና አርቆ ማየት የማይችል ሆነ። ጣዖት ሰርተው ከግብጽ ያወጣቸው ይህ ጣዖት እንደሆነ ተናገሩ፡ ፤ ኃጢአተኛ ፍላጎቶች አስተሳሰባችንን እና ተግባሮቻችንን እንዲህ የሚያዛቡ መሆናቸው አያስደንቅም? ሰዎች ሰብአዊ ፈጠራቸውን በማክበራቸው በሂደት ሰብአዊነታቸውና ቅንነታቸው (ሀቀኝነታቸው) ዝቅ አለ።

“እንደዚህ ዓይነቱ አስቸጋሪ ሁኔታ ጽናት፣ ቆራጥነትና የማይናወጥ ድፍረት ያለውን እና በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ከማግኘት፣ ከራስ ደህንነት ወይም በሕይወት ከመኖር ይልቅ የእግዚአብሔርን ክብር ከፍ የሚያደርግ ሰው ይፈልጋል። ነገር ግን አሁን ያለው የእሥራኤል መሪ ይህ ባህሪይ አልነበረውም።

አሮን ደካማ በመሆን ከሕዝቡ ጋር ምሬት አቀረበ፤ በዚህ ወሳኝ ቅጽበት የእርሱ ማወላወል (ማቅማማት) እና አይነ-አፋርነት ሕዝቡ የበለጠውን በሀሳባቸው እንዲገፉበት አደረጋቸው። ሕውከቱ ጨመረ። እውርና ምክንያታዊ ያልሆነ ኃይለኛ ስሜት ሕዝቡን የተቆጣጠረው መሰለ። ከእግዚአብሔር ጋር ለገቡት ቃል ኪዳን ታማኝ ሆነው የቆሙ ጥቂቶች ነበሩ። ነገር ግን አብዛኛው ሕዝብ ክህደትን ተቀላቀሉ። አሮን ለራሱ ደህንነት በመፍራት ለእግዚአብሔር ክብር ጸንቶ ከመቆም ይልቅ ለሕዝቡ ጥያቄ ተሸነፈ።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ pp. 316፣ 317. መሪ የሆነ አሮን እንዲህ ደካማ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? አሮን የራሱን አስከፊ ተግባራት ትክክል እንደሆኑ ለማረጋገጥ የፈለገባቸው መንገዶች ምንድር ናቸው?

ጳጉሜ 3
Sep 8

ጣዖት አምልኮና ክፋት


ዘጸ. 32:6ን ያንብቡ። ጣዖት አምልኮአቸው በፍጥነት ወዴት መራቸው? ዘጸ. 32:6ን ያንብቡ። ጣዖት አምልኮአቸው በፍጥነት ወዴት መራቸው? (ደግሞ መዝ. 115:4–8፤ መዝ. 135:15–18፤ ኢሳ 44:9፣ 10ን ይመልከቱ።)



የወርቅ ጥጃው አፒስ የሚባለውን የግብጻውያን የበሬ ኮርማ አምላክ ወይም ሃጾር የሚባለውን የላም አምላክ ይመስላል። ይህ የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ትዕዛዛት በጭፍን መተላለፍ ነው (ዘጸ. 20:3–6)። ከሕያው እግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት በግልጽ ስለጣሱ ይህ ጥሰት ሳይቀጣ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት አይቀርም። እሥራኤላውያን ፈጣሪያቸውን በማምለክ ፋንታ ማየት፣ መስማት፣ ማሽተት፣ መናገር፣ መጠንቀቅ፣ ማፍቀር ወይም መምራት የማይችላውን የራሳቸውን የፈጠራ ሥራ አመለኩ።

የፍጥረት ሥርዓት ተገልብጧል፡- በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠራቸውን በመረዳት ፋንታ በበቂ ሁኔታ መጥፎ የሆነውን የራሳቸውን ምስል እንኳን ሳይሰሩ በእንስሳ አምሳል አምላክ ሰሩ። ማገልገል የፈለጉት አምላክ ይህ ነበር። ከዚህ የተነሣ በእግዚአብሔር ላይ ከፍተኛ የሆነ ኃጢአት ሰርተዋል (ኢሳ 31:7፤ ኢሳ 42:17)። የወርቅ ጥጃው ክህደት በሮሜ 1፡22-24 ላይ የተጻፈውን ነገር የሚያንጸባርቀው በምን መንገዶች ነው?



ጣዖት አምልኮ እግዚአብሔር እግዚአብሔር መሆኑንና ሰው ሰው መሆኑን የሚገልጸውን ሥነ-መለኮታዊ መረዳት አይቀበልም። ጣዖት አምልኮ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለውን ልዩነት ያጠፋና (መክብብ 5:2) ከእርሱ ጋር ያለውን ግንኙነት ያቋርጣል። ጣዖት አምልኮ ጭፍንና ግልጽ ቢሆን ወይም በልብ ውስጥ የተሰወረ ነገር ቢሆን ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በፍጥነት በማቋረጥ በሞራል መሰላል ላይ ቁልቁል እንድንወርድ ያደርጋል።

ጥቅሱ በቀጣዩ ቀን ስላደረጉት ነገር መናገሩ አያስደንቅም፡- ለጣዖቱ መስዋዕቶችን ካቀረቡ በኋላ መብላት፣ መጠጣትና መጨፈር ጀመሩ፤ ኤለን ጂ ኋይት ሁኔታውን ስትገልጽ “በግብጽ ይደረግ የነበረው የጣዖት አምልኮ ግብዣ ኩረጃ ነበር” ትላለች።—Patriarchs and Prophets፣ p. 320.

ሰዎች የራሳቸውን ጣዖቶች በመስራት ረገድ መጥቀዋል። የራሳቸውን አማልክት መፍጠራቸው መጥፎ ሆኖ ሳለ የሚከፋው ደግሞ ወደ እነርሱ በመሄድ ማምለካቸው ነው። ፈጣሪ በሂደት ወደ ግብረገብ ዝቅጠት በሚመሩ ነገሮች ተተክቷል። ዛሬ ሰዎች ከፈጣሪ ይልቅ ፍጥረትን የሚያመልኩባቸው መንገዶች ምንድር ናቸው?

ጳጉሜ 4
Sep 9

ራሳቸውን ማበላሸት (ማርከስ)


ዘጸ. 32:7፣ 8ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ሙሴን ወደ እሥራኤል ሰፈር ተመልሶ እንዲሄድ ለምን ላከው?



እሥራኤላውያን ወደ ጣዖት በመመለሳቸው ከግብጽ ባርነት ነጻ ካወጣቸው ከእውነተኛ አምላክ ራሳቸውን የማፋታት ሂደት ላይ ነበሩ። ሕዝቡ ሀውልቱ ከግብጽ እንዳወጣቸው በመናገራቸው ጌታ “ራሳቸውን አርክሰዋል” (ዘጸ. 32:7)—በማለት ጥፋቱን ወደ ራሳቸው መልሷል። እግዚአብሔር ከነገራቸው ነገር ጋር እንዴት ያለ መቃረን ነው (ዘጸ. 20:2)! ይህ የእግዚአብሔርን መገኘትና ኃይለኛ ሥራዎች መካድ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።

አስተሳሰባቸውና ስሜቶቻቸው ተዛብተው ሙሉ በሙሉ ተበላሽተዋል።

ከሕዝቅኤል እንደምንረዳው የእግዚአብሔር ሕዝብ መከራ ሁሉ እምብርቱ ጣዖት አምልኮ ሲሆን ሌሎች ኃጢአቶች ሁሉ የሚፈልቁት ከዚያ ነው (ለምሳሌ፡- ሕዝ. 8:1–18፣ ሕዝ. 20:1–44፣ ሕዝ. 22:1–12ን ይመልከቱ)። የጥንት አማኞች የተለያዩ ሰው ሰራሽ ጣዖቶችን በማምለካቸው እና ሞኞችና ለመታረም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ብዙ ጊዜ እንደነቃለን። እኛ የዚህን ዓይነት ነገር በፍጹም እንደማንፈጽም እርግጠኛ ሆነን እንናገራለን። እኛ በርግጥ ከጣዖታት ነጻ ነን ወይ? የዛሬዎቹ ጣዖታት የተለያየ ቅርጽና መልክ ሊኖራቸው ይችላል፣ ነገር ግን ተመሳሳይ የሆነ የመሳብ ኃይል ይኖራቸዋል።

ጣዖት እግዚአብሔርን የሚተካ ነገር ሲሆን፣ ምንም እንኳን ትክክል አለመሆኑን ብናውቅም፣ ብዙ ጊዜ ደግመን ደጋግመን እናመልካለን።

አስተሳሰባችንን፣ ፍቅራችንን፣ ጊዜያችንን እና አእምሮአችንን እግዚአብሔር ከሚይዘው አብልጦ ይይዛል። አስተሳሰባችንን እንኳን ባሪያው ማድረግ ይችላል። በርግጥ የምንመለከተውን ስለምንሆን ከምናመልከው “አምላክ” በላይ ከፍ ማለት አንችልም። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የሕይወትዎ ማዕክል እግዚአብሔር ካልሆነ የእርሱን ቦታ ሌሎች አማልክቶች ይሞላሉ። የእግዚአብሔርን ሕያው መገኘት ካልተደሰትንበትና ካላሳደግን ሕይወታችንን ለሆነ ነገር ወይም ለሆነ ሰው ለይተን እንሰጣለን።

በክርስቶስ ቦታ የምንተካው ነገር የተለያዩ ገጽታዎች ሊኖረው ይችላል፡ - ኩራት፣ ራስን ማዕከል ማድረግ፣ ገንዘብ፣ ሥልጣን፣ ወሲብ፣ ምግብ፣ ቴሌቪዥን፣ አደንዛዥ እጽ፣ አስካሪ መጠጥ፣ የረከሱ አስተሳሰቦች፣ እርቃን የሚያሳዩ ምስሎች፣ መደሰቻዎች፣ ሥራ፣ ስፖርት፣ ቤተሰብ፣ ቪዲዮ ጨዋታዎች፣ ፊልሞች፣ ዕቃ መግዛት፣ ሀሳቦች፣ ፖለቲካ፣ ሙዚቃ፣ የሥልጣን ደረጃ፣ ማዕረግ፣ የትምህርት ውጤቶች እና ወዘተ። ዝረርዝሩ ማብቂያ የለውም።

በዚህ ረገድ እጅግ የመፍጠርና የመፈልሰፍ ችሎታ አለን። ማንኛውንም መልካም፣ ቆንጆ (ውብ) እና ትርጉም ያለው ነገር ወደ ጣኦት መቀየር እንችላለን። ጣዖት አምልኮ ማንነታችንን፣ የአስተሳሰብ መንገዳችንን፣ ፍቅራችንን እና ማህበራዊ ሕይወታችንን ስለሚለውጥ እጅግ አደገኛ ነው። ማንነታችንን በመለወጥ ትክክለኛ የሆኑ ግላዊ ግንኙነቶቻችንን ባዶና ትርጉም የለሽ ወደሆኑ ግንኙነቶች ስለሚለውጥ በመጨረሻ ሊያድነን አይችልም።

ጳጉሜ 5
Sep 10

የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ


ዘጸ. 32:9–29ን ያንብቡ። እግዚአብሔር እሥራኤልን አጠፋለሁ ባለ ጊዜ የሙሴ ምላሽ ምን ነበር?



ሙሴ ገና በሲና ተራራ ላይ እያለ እግዚአብሔር አመጸኞችን አጥፍቶ የሙሴን ዝርያ ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርግ ተናገረ። ነገር ግን ሙሴ ይፈልግ የነበረው ያ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ እሥራኤላውያን የሙሴ ሕዝብ ሳይሆኑ የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆናቸውን በመናገር እግዚአብሔርን ተማጸነ።

ከግብጽ ያወጣቸው ሙሴ ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ ኃይለኛ ሥራ በመስራት ነበር። ከዚህ የተነሣ ሙሴ አስቀድሞ እግዚአብሔር ለአባቶች በገባላቸው ተስፋ ላይ አጽንዖት በመስጠት ተማጽእኖውን አቀረበ። ሙሴ በትክክል በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እንደ አማላጅ እየሰራ ነበር። “እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ አመጣለሁ ያለውን ክፋት ራርቶላቸው ከተወ” (ዘጸ. 32:14) በኋላ ሙሴ ወደ እነርሱ ተመለሰ።

በዘጸ. 34:29፣ 30 ላይ እንደተገለጸው ከእግዚአብሔር ጋር ስለተነጋገረ ፊቱ አንጸባረቀ ከሚለው ሌላ የተመዘገበ ነገር የለም። ምናልባት ፊቱ ቁጣውን አንጸባርቆ ሊሆን ይችላል።

“እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃውንም ዘፈኑንም ባየ ጊዜ ቍጣው ተቃጠለ፥ ጽላቶቹንም ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበራቸው” (ዘጸ. 32:19)። አሥርቱን ትዕዛዛት የያዙ ጽላቶችን መስበር በውስጡ የያዛቸውን ነገሮች የመጣስ ውጫዊ ምልክት ነበር። ስለዚህ ነገር እግዚአብሔር ሙሴን ገሰጸው፣ ነገር ግን “ የሰበራቸውን የፊተኞቹን ጽላቶች” (ዘዳ. 10:2) ለመተካት ሌላ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጠርቦ እንዲያመጣ አዘዘው። ትዕዛዛቱን እንደገና የሚጽፈው እግዚአብሔር ራሱ ነበር።

አሮን ለሕዝቡ ጥያቄ በመሸነፉ ሙሴ እጅግ ተቆጣው፡- “ሙሴም አሮንን፦ ይህን ታላቅ ኃጢአት ታመጣበት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደረገህ? አለው” (ዘጸ. 32:21)። አሮን ለፈጸመው ኃጢአት በተለያዩ መንገዶች ሰበብ ለመስጠት የሞከረ ሲሆን የሚከተሉትን ምክንያቶች አቅርቧል፡- (1) ይህን እንዲያደርግ የገፋፉት ሌሎች ሰዎች እንደሆኑ፣ እና (2) ይህ የሆነው በአስማት እንደሆነ ተናገረ:- “ በእሳትም ላይ ጣልሁት [ወርቁን] ፥ ይህም ጥጃ ወጣ!’ ” (ዘጸ. 32:24)። ሁኔታውን የከፋ ያደረገው አሮን ራሱ ከሙሴና ከ70ዎቹ ሽማግሌዎች ጋር ወደ ተራራው መውጣትን ጨምሮ ብዙ ዕድሎች የተሰጡት በመሆኑ በእግዚአብሔር እጅግ የተከበረ ሰው መሆኑ ነበር (ዘጸ. 24:1)።

እንዴት ያለ አሳዛኝ ምጸት ነው! ተአምር እንደተፈጸመ በመናገር አሮን ወንድሙን ለማታለል ፈለገ (አንድ ኃጢአት እንዴት ወደ ሌላ ኃጢአት እንደሚመራ ልብ ይበሉ፣ በዚህ አጋጣሚ ጣዖት አምልኮ ወደ መዋሸት)።

ነገር ግን ሙሴ የሕዝቡን ሁኔታ ስለተመለከተ አልተታለለም። አሉታዊ መዘዞች የማይቀሩ ስለሆኑ ሙሴ በአፋጣኝ አመጹን ማቆም ነበረበት። ይህ ታሪክ ስለ ምልጃ ጸሎት ኃይል ምን ሊያስተምረን ይገባል? እርስዎ አሁን ለማን መጸለይ አለብዎት? የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

መስከረም 1
Sep 11

ምልጃ


ዘጸ. 32:30–32ን ያንብቡ። ሙሴ ለኃጢአተኞች ባደረገው የምልጃ ጸሎት ምን ያህል ርቀት መሄድ ነበረበት?



ከአመጸኝነታቸው የተነሣ በእሥራኤላውያን መኖሪያ አካባቢ የብዙ ሰዎችን ሞት ጨምሮ አሰቃቂ ነገሮች ተከስተዋል (ዘጸ. 32:28)። በቀጣዩ ቀን ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፡- “እናንተ ታላቅ ኃጢአት ሠርታችኋል፤ አሁንም ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ፤ ምናልባት ኃጢአታችሁን አስተሰርይላችኋለሁ አላቸው” (ዘጸ. 32:30)።

“ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፦ ወዮ! እኒህ ሕዝብ ታላቅ ኃጢአት ሠርተዋል፥ ለራሳቸውም የወርቅ አማልክት አድርገዋል፤ አሁን ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ አለ” (ዘጸ. 32:31፣ 32)።

ሙሴ የክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ መታየቱ አያስደንቅም! ለኃጢአተኞች የምልጃ ጸሎት ስላቀረበና ለእነርሱ የራሱን ሕይወት ለመስጠት ፈቃደኛ ስለሆነ ክርስቶስ ለሁላችንም የሚያደርገውን ነገር በእርግጠኝነት አንጸባርቋል።

ለተላላፊዎች እንዴት ያለ ምሳሌ መሆን የሚችል ርኅራኄ ነው! ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ መሰጠቱንና ለሕዝቡ ያለውን የመስዋዕትነት ፍቅር አሳይቷል።

ሙሴ በዚህ ጊዜ በተራራው ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ለምን ያህል ጊዜ እንደቆየ የዘጸአት መጽሐፍ አይናገርም፣ ነገር ግን በዚህ ጊዜ በሲና ተራራ ላይ ለ40 ቀናት እንደቆየ የዘዳግም መጽሐፍ ይገልጻል (ዘዳ. 9:18ን ይመልከቱ)።

ዘጸ. 32:32 ላይ “ይቅር በላቸው” ተብሎ የተተረጎመው ቃል መሰረታዊ ትርጉሙ ልክ በኢሳይያስ 53፡4 ላይ ስለ ኢየሱስ እንደተገለጸው “ማዘል” ወይም “መሸከም” ከሚል ግሥ የመጣ ነው፡- “እርሱ ሀዘናችንን (ሕመማችንን) ተሸከመ።” ዘጸ. 32:32፣ “ይቅር በላቸው” የተባለውና ኢሳይያስ 53:4 ላይ “ተሸከመ” የተባለው ተመሳሳይ ግሥ ነው። የድነትና የይቅርታ ሂደት እና እኛን ማዳን እግዚአብሔርን ስላስከፈለው ዋጋ እንዴት ያለ ኃይለኛ መረዳት ነው።

በርግጥ ሙሴ የሕዝቡን ኃጢአት “እንዲሸከም” እግዚአብሔር እየጠየቀው ነበር። በሺዎች ከሚቆጠሩ አመታት በኋላ በመስቀል ላይ ያደረገው ይህንኑ ነበር። ዘጸአት 32፡32 የምትክ ስርየትን ሀሳብ ብቻ የሚያሳይ ሳይሆን ምትክ የሚሆነው ማን እንደሆነም ያሳያል፤ ያውም እግዚአብሔር ራሱ ነው።

ይህ ጥቅስ ይቅርታ እንዴት እንደሚመጣ ያሳያል። እግዚአብሔር በክርስቶስ ኃጢአታችንን ተሸከመ። ይህም ይቅርታ የምናገኝበት ብቸኛው መንገድ ነው። ይህ እንዴት ያለ የድነት ዕቅድ መግለጫ እና እግዚአብሔር እኛን ለማዳን የከፈለውን ዋጋ ለራሳችንና ለመላው ዓላማት የሚያሳይ ነገር ነው። ሙሴ እግዚአብሔር እራሱ የሕዝቡን ኃጢአት እንዲሸከም የጠየቀ ሲሆን በመጨረሻም በኢየሱስ ይህን አድርጓል። በዚህ አስደናቂ እውነት ዙሪያ አእምሮአችን ሙሉ በሙሉ እንዲያዝ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ይህ እግዚአብሔር ለወደቀው ሰብአዊ ዘር ስላለው ፍቅር ምን ይነግረናል?

መስከረም 2
Sep 12


ተጨማሪ ሀሳብ


የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት ከሚለው የኤለን ጂ ኋይት መጽሐፍ “የጣዖት አምልኮ በሲና” የሚለውን ርዕስ ገጽ 315–327 ላይ ያንብቡ።

የዚህ ሳምንት ትምህርት እግዚአብሔር በአማኞች ውስጥ በሚሰራው ሥራ ላይ የሚደረገውን ልዩ ትኩረት ያቀርባል። እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ “ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ይችላል” (ኤፌ. 3:20)። በራሳችን ላይ ትኩረት ማድረግና የግል ፍላጎቶቻችንን ማሟላት ወደ ጣዖት አምልኮ ስለሚመራን ይህን ማድረግ የለብንም። ከዚህ ይልቅ ትኩረታችን በእግዚአብሔርና በኃይሉ ላይ መሆን አለበት። ይህም ወደ አዲስና የድል ኑሮ የሚመራንን ብርታት ይሰጣል (ፊልጽ. 4:13፤ ይሁዳ 1:24፣ 25)። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

“በኃጢአት ላይ ፍርድ ስለሚሰጥ ፍትህ ከሚጠይቀው የሚያንስ ምንም ነገር አትውደዱ። እግዚአብሔር የህዝቡ ጠባቂና ሉአላዊ አምላክ ነው። በአመጽ የሚጸኑትን ሌሎችን ወደ ጥፋት ሊመሩ ስለሚችሉ ይቆርጣቸዋል። እግዚአብሔር የቃየልን ሕይወት ከሞት በማዳኑ ለዩኒቨርስ ኃጢአት ሳይቀጣ እንዲቀጥል የመፍቀድ ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል አሳየ። በሕይወቱና በትምህርቶቹ በዘሮቹ ላይ ያሳደረው ተጽእኖ መላውን ዓለም በውኃ እንዲጠፋ ወደጠየቀው እርኩሰት መራ። …ሰዎች ረዥም ዕድሜ በኖሩ መጠን የበለጠውን እየረከሱ ሄዱ።

በሲና በተፈጸመው ክህደትም የሆነው ይኸው ነው። በኃጢአት ላይ አፋጣኝ ቅጣት ካልተሰጠ በቀር ተመሳሳይ ውጤቶች በድጋሚ ይታያሉ።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 325.


የመወያያ ጥያቄዎች




1. በሰኞ ትምህርት መጨረሻ ላይ ባለው ጥያቄ ላይ አብልጠው በሰኞ ትምህርት መጨረሻ ላይ ባለው ጥያቄ ላይ አብልጠው ትኩረት ያድርጉ። ከፈጣሪ በተቃራኒ ፍጥረትን ማምለክ የምንችልባቸው መንገዶች ምንድር ናቸው? ለምሳሌ፣ ተፈጥሮን ሳናመልክ ወይም ጣዖት ሳናደርግ የምድር ጥሩ መጋቢዎች ለመሆንና አካባቢን ለመጠበቅ መሻት የምንችለው እንዴት ነው?

2. አንድ ሰው የሁኔታውን አስከፊነት መለየት የሚችለው ድርጊቱ አንድ ሰው የሁኔታውን አስከፊነት መለየት የሚችለው ድርጊቱ በሚያስከትላቸው መዘዞችና ውጤቶቹ ወይም ለክስተቱ በተሰጠው ምላሽ አሳሳቢነት ነው። በትዕቢት መናዘዝን እምቢ ባሉት እና በእግዚአብሔርና በትምህርቱ ላይ ማመጻቸውን በቀጠሉት ላይ ሙሴ የሞት ቅጣት እንዲፈጸምባቸው ያዘዘው ለምንድር ነበር?

3. የምትክ ስርየት ብቸኛው ትክክለኛ የስርየት ሞዴል የሆነው የምትክ ስርየት ብቸኛው ትክክለኛ የስርየት ሞዴል የሆነው ለምንድር ነው? ወንጌል የሚያስተምረውን የምትክ መሰረት የሚክድ ወይም የሚያቃልል የስርየት ንድፈ ሀሳብ አስከፊ ስነ-መለኮታዊ ስህተት የሆነው ለምንድር ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 2:24ን ያንብቡ። ኢየሱስ ምትካችን የመሆኑን ሀሳብ በኃይል የሚገልጠው እንዴት ነው?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL