የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ዘጸ. 19:1–20:17፣ ራዕይ. 21:3፣ ዘዳ. 5:6–21፣ ያዕቆብ 1:23–25፣ ሮሜ 3:20–24፣ ሮሜ 10:4።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር
ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤
እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ።
ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው” (ዘጸ. 19:4–6)።
እግዚአብሔር እሥራኤላውያንን ከግብጽ ነጻ ካወጣ በኋላ ወዴት መራቸው?
ወደ ተስፋይቱ ምድር ወይስ ሌላ ቦታ? በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ
መልሱ ምንም ያህል ትክክል ቢሆንም በሥነ መለኮታዊ አመለካከት
ስህተት ነው። መልሱን እግዚአብሔር ራሱ እንዲህ በማለት ይመልሰዋል፡- “
በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም
እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል” (ዘጸ. 19:4)። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊው
የስነ-መለኮት መልስ እግዚአብሔር ቅድሚያ የሰጠውና ግቡ ያደረገው ሕዝቡን
ወደ ራሱ ማምጣት መሆኑን ይገልጻል።
ሰብአዊ ፍጡራን ከእግዚአብሔር ሲለዩ እርሱ ይፈልጋቸዋል፣ ወደ ራሱም
ይጠራቸዋል። ለዚህ መሰረታዊ እውነት ጥሩ ሞዴል የሚሆነው አዳምና ሔዋን
ኃጢአት ሰርተውና የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ተላልፈው ከእርሱ በተደበቁ ጊዜ
በኤደን ገነት የሆነው ነገር ነው። እግዚአብሔር ተነሳሽነቱን በመውሰድ “የት
ነህ?” (ዘፍ. 3:9) በማለት ጠራ። እርሱ ሁልጊዜም የመጀመሪያውን
እርምጃ ይወስዳል። ኢየሱስ ይህንን ነገር ልብ በሚነካ ሁኔታ እንዲህ በማለት
ይገልጸዋል፡- “ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም
አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም
ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ” (ማቴ. 11:28፣ 29)።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
እግዚአብሔር ሁላችንንም ይጠራናል፤ ዘላለማዊ መዳረሻችን
በመልሳችን ላይ ይደገፋል።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሐሴ 17 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ
ዘጸ. 19:1–8ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ፣ በሲና ተራራ ሥር፣ እግዚአብሔር ምን ቃል ገባላቸው?
እግዚአብሔር በቅርቡ አሥርቱን ትዕዛዛት (ሕግጋትን) ወደሚሰጥበት ወደ
ሲና ተራራ እሥራኤላውያንን መራቸው። ሙሴ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔርን የተገናኘበት
ቦታ ጀበል ሙሳ እንደሆነ የሚገመት ሲሆን (ከፍታው 7,497 ጫማ ወይም
2,285 ሜትር) (ለምሳሌ ዘጸ. 3:1፣ ዘጸ. 19:2፣ ዘጸ. 24:18) ነው።
ከዓመታት በኋላ ኤልያስ በዚህ ቦታ ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኝቷል (1ኛ መሳፍንት
19:8)። ይህ ተራራ እስራኤላውያንን ከግብጽ እንዲያወጣ እግዚአብሔር ሙሴን
የጠራበት ያው ተራራ ነው (ዘጸ. 3:1፣ 10)። በዚያን ጊዜ ነጻ ከወጡ
እሥራኤላውያን ጋር በዚህ ቦታ እግዚአብሔርን እንደሚያመልክ እግዚአብሔር
ለሙሴ ነገረው። ይህም ይመራቸው የነበረው የአብርሃም፣ የይስሃቅና የያዕቆብ
አምላክ እንደነበር ለሙሴ ምልክት ይሆናል (ዘጸ. 3:12)።
ከሁለት ወር ጉዞ በኋላ እሥራኤላውያን ወደ ሲና ደረሱ (ዘጸ.
19:1)፣ በዚያ ቦታም ለአንድ ዓመት ያህል ቆዩ (ዘጸ. 19:1ን ከዘሁልቁ
10:11፣ 12 ጋር ያነጻጽሩ)። በዚህ አመት ውስጥ በዘጸ. 19–40፣
ዘሌዋውያን 1–27፣ እና ዘሁልቁ 1:1–10:10 ላይ በተገለጸው መሰረት
ብዙ ሕግጋት ተሰጥተዋል። የእሥራኤላውያን በሲና መቆየት በመጀመሪያዎቹ
አምስት የሙሴ መጻሕፍት ውስጥ ያለው ትረካ ማዕከላዊ ጉዳይ ነው።
በአረማዊነትና በጣዖት አምልኮ ያልተሳተፈ ብቸኛው የእግዚአብሔር ምርጥ
ሕዝብ የመሆናቸው መሰረት ያለው እዚህ ነው።
እግዚአብሔር ተነሳሽነቱን በመውሰድ በራሱና በእሥራኤል መካከል
ቃል ኪዳን ፈጸመ። ሕዝቡ ከታዘዙና ከእርሱ ጋር ግንኙነታቸውን ከጠበቁ ለራሱ
የተለየ ንብረት፣ የካህነት መንግሥትና ቅዱስ ሕዝብ ሊያደርጋቸው ቃል ገባ።
ቅዱስ ሕዝብ መሆን ማለት ለእግዚአብሔር መለየትና የእርሱን
ባህርይ ለሌሎች፣ በተለይም በዙሪያቸው ላሉ ሕዝቦች መግለጥ ማለት ነው።
ሌላ ሕዝብን ወደ እግዚአብሔር ለመምራት እና የእርሱን መንገድና ህግጋት
ለማስተማር እንደ ካህናት መንግስት ለመስራትም ተጠርተዋል። እስራኤል
የእግዚአብሔርንና የባህርዩን እውቀት ለዓለም እንዲያበሩ የእርሱ መሣሪያዎች
ሊያደርጋቸው ስለፈለገ የእግዚአብሔር ልዩ ሕዝብ መሆን ነበረባቸው።
ይህ ቃል ኪዳን በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል የተመሰረተ ሕጋዊ
ግንኙነት ነበር። በተለያዩ ጥቅሶች ውስጥ በመጠኑ የሚለያየው አጠቃላይ
የቃል ኪዳን ፎርሙላ “እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፣ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ”
(ዘጸ. 6:7፣ ዘሌ. 26:12፣ ኤር. 24:7፣ ኤር. 31:33፣ ዕብ.
8:10፣ ራዕይ. 21:3ን ይመልከቱ) የሚል ነው።
የእግዚአብሔር “ልዩ ንብረት” መሆንን ያስቡ! ይህ ምን የተለዩ መልካም
ዕድሎችን ያካትታል? እርሷ ምን የተለዩ ሀላፊነቶች አሏት?
ዘጸ. 19:9–25ን ያንብቡ። እሥራኤላውያን አስርቱን ትዕዛዛት እንዲቀበሉ እግዚአብሔር ያዘጋጃቸው እንዴት ነበር?
እሥራኤላውያን በሲና ለሚሰጠው ሕግ ለመዘጋጀት ምን ማድረግ
እንደነበረባቸው እግዚአብሔር ልዩ መመሪያዎችን ሰጥቶ ነበር። ውጫዊ ንጽህናቸው
ለእግዚአብሔር ያላቸውን ሙሉ መሰጠት ማንጸባረቅ ነበረበት። ሊመጣ ስለነበረው
አስደናቂ የእግዚአብሔር ክብር መገለጥ መዘጋጀት ነበረባቸው። የእግዚአብሔር
ክብር መገለጥ በሚከተሉት ነገሮች የታጀበ ነበር፡- “ነጐድጓድና መብረቅ ከባድም
ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩም
የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ” (ዘጸ. 19:16)።
ሕግጋቱ (አሥርቱ ትዕዛዛት) የእግዚአብሔር መገለጥና መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ሥነ-ምግባር እምብርት ናቸው። ትዕዛዛቱ ለሰብአዊ ዘር በሙሉ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመለኮታዊ መስፈርቶች አንኳርና መሰረት ናቸው፤ መርሆዎቹ ዘላለማዊና
ዓለም አቀፋዊ ናቸው።
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ አሥርቱን ትዕዛዛት ለሰዎች ያሳወቀው
እግዚአብሔር ሲሆን (ዘጸ. 19:19፤ ዘጸ. 20:1፤ ዘዳ. 5:4፣ 5፣
24)፣ የጻፈውም እርሱ ራሱ ነው (ዘጸ. 24:12፣ ዘጸ. 31:18፣ ዘዳ.
5:22)። ለሙሴ ሁለት ጊዜ እንደ ልዩ ስጦታ ተሰጥተዋል (ዘጸ. 32:19፤
ዘጸ. 34:1፤ ዘዳ. 10:1፣ 2)።
በዘጸአት መጽሐፍ ውስጥ አስርቱ ትዕዛዛት፣ “ምስክር” (በዕብራይስጥ
‘ኢዱት፤ ዘጸ. 31:18)፤ ወይም “የቃል ኪዳን ቃሎች” (በዕብራይስጥ ዲብሬ
ሃቤሪት፤ ዘጸ. 34:28) የሚል ስያሜ ተሰጥቶአቸዋል። በዘዳግም መጽሐፍ
ውስጥ አስርቱ ትዕዛዛት “የቃል ኪዳን ጽላቶች” (ዘዳ. 9:9፣ 11፣ 15) ላይ
እንደተጻፉ ተገልጾአል። በዕብራይስጥ የትኛውም መጽሐፍ “አስርቱ ትዕዛዛት”
(በዕብራይስጥ ሚትዝወት፣ “ትዕዛዛት”) የሚል ቃል አይጠቀምም። ከዚህ
ይልቅ፣ ሶስት ጊዜ “አሥርቱ ቃላት” የሚል ስያሜ ሰጥተዋል። ዕብራይስጡ
‘አሰረት ሃዴባሪም የሚል ሲሆን ዳባር ከሚል መነሻ ቃል የመጣ ስለሆነ ትርጉሙ
“ቃል፣ አረፍተ ነገር፣ ቁም ነገር፣ ነገር፣ ንግግር፣ ታሪክ፣ ቃል ኪዳን፣ የተነገረ
ቃል” የሚል ነው (ዘጸ. 34:28፣ ዘዳ. 4:13፣ ዘዳ. 10:4ን ይመልከቱ)።
መጠነኛ ልዩነት ያላቸው ሁለት የአሥርቱ ትዕዛዛት ትርጉሞች ያሉ ሲሆን
የመጀመሪያው ዘጸ. 20:1–17 ላይ የተመዘገበ ሲሆን ሁለተኛው ዘዳግም
21:3–21 ላይ ተመዝግቦ ይገኛል። ሙሴ ለእሥራኤላውያን በቃል ያቀረበው
ሁለተኛው ትርጉም ከሲና በኋላ ወደ አርባ ዓመት ገደማ፣ ሕዝቡ ወደ ተስፋይቱ
ምድር ከመግባታቸው በፊት የተከሰተ ነበር (ዘዳ. 1:3፣ 4፤ ዘዳ. 4:44–
47)። እነዚህ ሁኔታዎች በሁለቱ መካከል ያሉትን መጠነኛ ልዩነቶች ያብራራሉ።
ጳውሎስ ሕግን ፍቅር ነው በማለት ማጠቃለያ በሰጠበት ጊዜ ከአስርቱ
ትዕዛዛት ጠቅሷል (ሮሜ 13:8–10)። እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ስለሆነ
ፍቅር በርግጥም የእግዚአብሔር ሕግ አጠቃላይ ድምር ነው (1ኛ ዮሐንስ 4:16)።
አሥርቱ ትዕዛዛት የእግዚአብssሔር ፍቅር መግለጫ ናቸው የሚለውን ሀሳብ
እንዴት ይረዱታል? ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በእነዚህ ትዕዛዛት ውስጥ
የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጸው እንዴት ነው?
ዘጸ. 20:1–17ን ያንብቡ። የአስርቱ ትዕዛዛት መርሆዎች ምንድር ናቸው? የተደራጁትስ እንዴት ነው?
አሥርቱ ትዕዛዛት የሚጀምሩት በትዕዛዛት ሳይሆን እግዚአብሔር
ለሕዝቡ ባደረገው የቸርነት ድርጊት እንደሆነ ልብ ይበሉ፡-
“ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ
እኔ ነኝ” (ዘጸ. 20:2)። እግዚአብሔር ለእስራኤል ነጻነትንና ድነትን
በመስጠት በመጀመሪያ ቸርነቱን ያሳያል፤ ፈቃዱን ማሳወቅ የሚችለው ያኔ
ብቻ ነው። እነዚህ ትዕዛዛት መጠበቅ ያለባቸው በፍቅርና እግዚአብሔር
ስላደረገላቸው ነገር በማመስገን ነው።
እግዚአብሔር ለአሥርቱ ትዕዛዛት የሰጠው ቁልፍ የማጠቃለያ ቃል
“ፍቅር” ነው (ሮሜ 13:10)። ከትዕዛዛት ሁሉ የሚበልጠው ትዕዛዝ በሁለት
መንገዶች የተገለጸው የፍቅር ትዕዛዝ ሲሆን እርሱም እግዚአብሔርን መውደድ
(ዘዳ. 6:5) እና ባልንጀራን መውደድ (ዘሌ. 19:18) ናቸው።
የመጀመሪያዎቹ አራት ትዕዛዛት እግዚአብሔርን መውደድ ምን ማለት
እንደሆነ ትርጉም ይሰጣሉ። ቀጣዮቹ ስድስት ትዕዛዛት ባልንጀራን መውደድ
ምን ማለት እንደሆነ ትርጉም ይሰጣሉ። አሥርቱ ትዕዛዛት የሚጀምሩት
ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን በማክበር (አምዳዊ ፍቅር) ሲሆን በመቀጠል
ሌሎችን ማክበርን መግለጻቸውን ይቀጥላሉ (አግድማዊ ፍቅር)።
1. በሕይወታችን በእያንዳንዱ ሁኔታ ለእግዚአብሔር የመጀመሪያውንና
ከፍተኛውን ቦታ በመስጠት እግዚአብሔርን ማክበርና ማምለክ
(የመጀመሪያው ትዕዛዝ)፤
2. እግዚአብሔርን በማንኛውም መልክ (አካላዊ፣ ምሳሌያዊ ወይም
መንፈሳዊ በሆነ ሁኔታ) በጣዖት ባለመተካት የእርሱን ልዩ የሆነ ሥልጣን
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ማክበርና መጠበቅ። እጅግ ንጹህ የሆነውን ፍቅራችንን ማግኘት የሚገባው
እግዚአብሔር ነው (ሁለተኛው ትዕዛዝ)፤
3. የእግዚአብሔርን መልካም ስም (ዝና) እና ባህሪይ ማክበር (ሶስተኛው
ትዕዛዝ)፤
4. የአምልኮና የእረፍት ቀን የሆነውን ሰንበትን ማክበር (አራተኛው
ትዕዛዝ)፤
5. ወላጆችን ማክበር (አምስተኛው ትዕዛዝ)፤
6. ሕይወትን ማክበር (ስድስተኛው ትዕዛዝ)፤
7. ጋብቻን ማክበር (ሰባተኛው ትዕዛዝ)፤
8. የሰዎችን ንብረት ማክበር (ስምንተኛው ትዕዛዝ)፤
9. የሌሎችን መልካም ስም (ዝና) አለማጉደፍ ወይም ማክበር (ዘጠነኛው
ትዕዛዝ)፤ እና
10. የራስ ወዳድነት ፍላጎቶች ባህሪያችንን እንዳያበላሹ ራሳችንን ማክበር
(አስረኛው ትዕዛዝ) ናቸው።
ኢየሱስ “ብትወዱኝ ትዕዛዛቴን ጠብቁ ” ብሏል (ዮሐንስ 14:15፤ ደግሞ
1ኛ ዮሐንስ 4:20፣ 21ን ይመልከቱ)። ስለሆነም እውነተኛ መታዘዝ ለኢየሱስ
ያለን ፍቅርና አመስጋኝነት መግለጫ ነው፤ ይህ ፍቅር እጅግ ኃይለኛ በሆነ ሁኔታ
የሚገለጸው ለባልንጀሮቻችን (ጎሮቤቶቻችን) በምናደርገው ነገር ነው።
የእግዚአብሔር ሕግ የእርሱን ባህርይና ማንነቱን ይገልጣል።
እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ጻድቅና መልካም እንደሆነ ሁሉ ሕጉም እንደዚያው
ነው። ይህን ጳውሎስ እንዲህ በማለት ያረጋግጣል፡- “ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው
ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት” (ሮሜ 7:12)።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ሕግ እጅግ አዎንታዊ በሆነ
ብርሐን ታይቷል (ማቴ. 5:17፣ 18፤ ዮሐንስ 14:15፤ 1ኛ ቆሮ.
7:19)። በመዝሙር 119 ላይ እንደሆነው አንድ ሰው ስለ ሕግ ግጥም
ሊገጥም ይችላል፣ ቀንና ማታ ሊያሰላስልም ይችላል (መዝ. 1:2፣ ኢያሱ
1:8)። ሕግ ሰው ከክፉ እንዲጠበቅ በመርዳት ጥበብን፣ መረዳትን፣ ጤናን፣
ብልጽግናን እና ሰላምን ይሰጣል (ዘዳ. 4:1–6፣ ምሳሌ 2–3)።
1. የእግዚአብሔር ሕግ ለሕይወት ትልቅ ነጻ የሆነ ክፍት ቦታ
እንደሚፈጥር እና ከዚያ ነጥብ ባሻገር አደጋ፣ ችግር፣ ምስቅልቅልና
ሞት እንደሚጠብቅ እንደሚያስጠነቅቅ አጥር ነው (ዘፍ.
2:16፣ 17፤ ያዕቆብ 2:12)።
2. ደግሞ ሕግ ኃጢአታችንን ይቅር ወደሚለውና ሕይወታችንን
ወደሚለውጠው ወደ ኢየሱስ የሚያመለክት ምልክት ነው (2ኛ ቆሮ
5:17፣ 1 ዮሐንስ 1:7–9)። በዚህ መንገድ እንደ የግል መምህርና
ጠባቂ/ሞግዚት ወደ ክርስቶስ ይመራናል (ገላ. 3:24)።
ያዕቆብ 1:23–25ን ያንብቡ። ያዕቆብ ምን እያለን ነው ያለው? እነዚህ
ቃላት ሕግ ሊያድነን ባይችልም የሕግን ጥቅምና አስፈላጊነት መረዳት
እንድንችል ሊረዱን የሚችሉት እንዴት ነው?
መስታወት ጉድለቶችዎን ያሳያል። ነገር ግን መስታወት እነዚያን
ጉድለቶች ማስተካከል አይችልም። መስታወት ችግሮቹን ይጠቁማል፣ ነገር
ግን ለችግሮቹ ምንም መፍትሄ አይሰጥም። ሕግም እንደዚያው ነው። ሕግን
በመጠበቅ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ለመሆን መሞከር፣ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ
በስተቀር፣ መስታወቱ ጉድለቶችዎን ያስወግዳል ብለው ተስፋ በማድረግ
በመስታወቱ ላይ እንደማፍጠጥ ነው።
ድነት በእምነት እንጂ በሥራ ስላልሆነ፣ የሕግ ሥራን ጨምሮ፣ አንዳንድ
ክርስቲያኖች ሕግ ስለተሻረ ሕግን መጠበቅ አይጠበቅብንም ይላሉ። በርግጥ
ኃጢአት ምን እንደሆነ የሚገልጸው ሕግ መሆኑን ስናስብ— “በሕግ ባይሆን
ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር” (ሮሜ 7:7 )—ሕግ ተሽሮአል ብሎ ማሰብ
በሕግና በወንጌል መካከል ያለውን ግንኙነት በተሳሳተ መልክ ማስቀመጥ ነው።
ወንጌል የሚያስፈልገን በእርግጠኝነት ሕግ በመኖሩ ነው።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የእግዚአብሔርን ሕግ ለመታዘዝ ባደረጉት ጥረትዎ ምን ያህል ስኬታማ ነዎት?
ሕግ ድነትዎን በርሱ ላይ ለመመስረት በቂ ነው? ካልሆነ፣ ወንጌል ለምን
ያስፈልግዎታል?
ሮሜ 3:20–24ን ያንብቡ። አስርቱን ትዕዛዛት በመጠበቅ መዳን እንደማንችል ጳውሎስ በጣም እርግጠኛ ቢሆንም ሕግጋቱ በእኛ ሕይወት ሥራቸውን የሚሰሩት እንዴት ነው?
በሙሴ ጽሁፎች ውስጥ አሥርቱን ትዕዛዛት ለመግለጽ ጥቅም ላይ
የዋለው የዕብራይስጡ ዳባሪም የሚለው ቃል (ዘጸ. 34:28፣ ዘዳ. 4:13፣
ዘዳ. 10:4) ቃል በቃል ሲተረጎም “ትዕዛዛት” የሚል ሳይሆን “ቃላት”
የሚል ትርጉም አለው። ይህ “ቃል፣” ዳባር (ነጣለ)፣ “የተስፋ ቃል” የሚል
ትርጉም ሊኖረው ይችላል። ዳባር የሚለው ቃል በብዙ ቦታዎች (1ኛ ነገሥት
8:56፤ 2ኛ ዜና 1:9፤ ነህሚያ 5:12፣ 13፤ ዘዳ. 1:11፤ ዘዳ. 6:3፤ ዘዳ.
9:28፤ ኢያሱ 9:21፤ ኢያሱ 22:4፤ ኢያሱ 23:5)፣ የተስፋ ቃል ሀሳብን
ይዞ እንደ ስም ወይም ግሥ የተተረጎመው ከዚህ የተነሣ ነው።
ኤለን ጂ ኋይት የአስርቱን ትዕዛዛት ተግባር በተመለከተ “አስርቱ ትዕዛዛት
. . . አስር የተስፋ ቃላት ናቸው” በማለት ማብራሪያ ትሰጣለች። —Ellen
G. White Comments፣ The SDA Bible Commentary፣
vol. 1፣ p. 1105። አስርቱ ትዕዛዛት መስተዋል ያለባቸው እግዚአብሔር
አስደናቂ ነገሮችን እንዲያደርግልን በትክክለኛው መንገድ ሊመሩን ከእርሱ
የተሰጡን የተስፋ ቃላት እንደሆኑ ነው። ነገር ግን ልንታዘዛቸው ይገባል።
ሮሜ 10:4ን ያንብቡ። ክርስቶስ የሕግ “ፍጻሜ” ነው የሚለውን የጳውሎስን
አረፍተ ነገር መረዳት ያለብን እንዴት ነው?
ጳውሎስ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ (telos) እንደሆነ ይናገራል፣
ነገር ግን ይህን ሲል ክርስቶስ ሕግን ሽሯል ወይም አስወግዷል በሚል ስሜት
አይደለም። ከዚህ ይልቅ ክርስቶስ የሕግ ግብና አላማ ነው ማለት ነው፤ የእርሱ
የስርየት መስዋዕትነት የህግን ትክክለኛነትና ዘላቂነት ያስቀራል ማለት አይደለም።
ከዚህ በተቃራኒ ስለ ሕግ አስፈላጊነት፣ ሕጋዊነት እና የማይሻር
ሥልጣኑ ይናገራል (ሮሜ 3:31፣ 1ኛ ቆሮ. 7:19፣ ገላ. 5:6)። ቴሎስ
(telos) የሚለው ቃል ትርጉም ከጊዜ ጋር የተገናኘ ሳይሆን በቀዳሚነት
ዓላማ ያለውና ግብን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው። ክርስቶስ የእግዚአብሔርን
ሕግ እውነተኛ ትርጉምና ዓላማ የሚከፍት ቁልፍ ነው። ስለዚህ ክርስቶስ ሕግን
ዋጋ አሳጥቶታል፣ ሽሮታል ወይም አስቀርቶታል ማለት ስህተት ነው። ሕግ ወደ
ክርስቶስ ስለሚያመለክት ክርስቶስ የሕግ ግብ ነው።
ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመለክተው እንዴት ነው? ሕግ ወደ ክርስቶስ
እንድንመለከት ለማድረግ ስለ ራሳችን ምን ይገልጥልናል?
ኤለን ጂ ኋይት ከጻፈችው አባቶችና ነቢያት ከሚለው
መጽሐፍ “ለእሥራኤል የተሰጠ ሕግ” የሚለውን ክፍል ገጽ 303–310 እና
“ሰይጣን ለሕግ ያለው ጠላትነት” የሚለውን ክፍል ገጽ 331–342 ላይ ያንብቡ።
“እግዚአብሔር ሕጉን የተናገረበትን አጋጣሚ ከከበረው ባህሪዩ ጋር
በተገናኘ ሁኔታ አስፈሪ ግርማ ሞገስ ያለው ትዕይንት እንዲሆን አቀደ። ሕዝቡ
ከእግዚአብሔር አገልግሎት ጋር ግንኙነት ያለው እያንዳንዱ ነገር እጅግ ትልቅ
የሆነ አክብሮት ሊሰጠው እንደሚገባ መረዳት ነበረባቸው።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 303.
ይህ የአክብሮት መርህ ዛሬም ተቀባይነት ያለው ነው። ይህ መርህ
የሚመነጨው የእግዚአብሔርን ታላቅነት፣ የላቀ ችሎታ እና ግርማ ከመረዳት ነው።
የእግዚአብሔርን ክብር መመልከት በልባችን አመስጋኝነትን በመፍጠር ኩራታችንን
ዝቅ ያደርጋል። የእግዚአብሔርን ቅድስና በቅርበት ስንመለከት በሕይወታችን ያሉ
ጉድለቶችን አብልጠን ለይተን ስለምናውቅ የሚለውጠንን የእርሱን መገኘት
የበለጠውን ወደ መጠማትና እርሱን ለመምሰል ወደ መፈለግ ይመራናል።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ከእርሱ እና ከቅዱስ ሕጉ ጋር ራሳችንን በማነጻጸር እኛ ማን እንደሆንን
ማወቃችን ደግሞ ክርስቶስ ለእኛ በፈጸመው የምትክ ሞት ሙሉ በሙሉ
እንድንደገፍ ያደርገናል።
ራሳችንን ዝቅ በማድረግ እግዚአብሔርን እንደ አምላካችንና ንጉሣችን
ስንቀበል ትዕዛዛቱ ለመታዘዝ ከባድ እንደማይሆኑ ኢየሱስ ግልጽ አድርጓል (ማቴ.
11:28–30)። መለኮታዊ ሕግ ቋሚ የሆነ (የማይለወጥ) መሰረት እንዳለው
ክርስቶስ ግልጽ አድርጓል (ማቴ. 5:17–20)። እግዚአብሔር ድነትን
በነጻ ስለሰጠን ለእግዚአብሔር ካለን ፍቅርና አመስጋኝነት በመነሳት የእርሱን
ሕግጋት ስንጠብቅ ከእርሱ ጋር የሚያድን ግንኙነትን ሙላት እንለማመዳለን።
ሕግን የመጠበቅን ታላላቅ መልካም ዕድሎች እየተጠቀምን ሳለ (ሕግን መጣስ
የሚያስከትለውን ሕመምና መከራ ይመልከቱ)፣ ድነታችን ሕግን በመጠበቃችን
ሳይሆን በኢየሱስ እንደሚገኝ በማወቃችን እርግጠኝነት መደሰት እንችላለን።
1. ሕዝቡ ሕግን ለመቀበል ያደረጉት ዝግጅት ያስፈልጋቸው የነበረውን
ሕዝቡ ሕግን ለመቀበል ያደረጉት ዝግጅት ያስፈልጋቸው የነበረውን
የአክብሮት ስሜት እንዲረዱ ረዳቸው። ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችንና
በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ይህን የመሰለ በእግዚአብሐር ፊት
በአክብሮትና በፍርሃት የመቅረብ ስሜት ያለው የት ነው? ወይስ
በሆነ መንገድ ቀስ በቀስ ጠፍቶብናል?
2. በዚህ የቃል ኪዳን ቀመር ላይ ያሰላስሉ፡- “እኔ አምላካቸው
በዚህ የቃል ኪዳን ቀመር ላይ ያሰላስሉ፡- “እኔ አምላካቸው
እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።” ይህ ዛሬ ለእኛ ምን ማለት
ነው? እንደ ግለሰብና እንደ ቡድን መገለጥ ያለበትስ እንዴት ነው?
3. እግዚአብሔር እንድንፈጽም የሚያዘንን ነገር እንድንፈጽመው
እግዚአብሔር እንድንፈጽም የሚያዘንን ነገር እንድንፈጽመው
ያስችለናል። ኤለን ጂ ኋይት እንዲህ ትላለች፡- “ትዕዛዞቹ
ሁሉ እንድንፈጽም የሚያስችሉን ናቸው።”—Christ’s
Object Lessons፣ p. 33
3. አንድ ግለሰብ ይህን
ተስፋ (ዳባር) በሥራ መተርጎም የሚችለው እንዴት ነው?
4. ከመስቀል በኋላ ሕግ ተሸሯል ለሚለው የተለመደ መከራከሪያ
ከመስቀል በኋላ ሕግ ተሸሯል ለሚለው የተለመደ መከራከሪያ
መልስ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? በአብዛኞቹ አጋጣሚዎች
ተሽሯል እያሉ ያሉት ምንድር (የትኛውን ትዕዛዝ) ነው?