የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ዘጸ. 15:22–
16:36፣ ዘፍ. 3:1–6፣ ዘጸ. 17:1–7፣ 1ኛ ቆሮ. 10:4፣ ዘጸ.
18: 1–27፣ 1ኛ ቆሮ. 10:11።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ትእዛዞቼንና ሕጎቼን
ለመጠበቅ እስከ መቼ እንቢ ትላላችሁ? እግዚአብሔር ሰንበትን እንደ
ሰጣችሁ እዩ፤ ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሁለት ቀን እንጀራ ሰጣችሁ፤
ሰው ሁሉ በስፍራው ይቀመጥ፥ በሰባተኛው ቀን ማንም ከስፍራው
አይሂድ አለው። ሕዝቡም በሰባተኛው ቀን ዐረፈ” (ዘጸ. 16:28–30)።
እሥራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ በኋላ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመሄድ
ያልታወቀ ጉዞ ላይ ነበሩ። አድካሚና ረዥም መንገድ የተከተሉ ሲሆን
ብዙ አዳዲስ ነገሮችን መማር ነበረባቸው። እግዚአብሔር ይመራቸውና
ይጠነቀቅላቸው ነበር፤ እንዲያድጉ ለመርዳትም ፈለገ፤ ነገር ግን ሥርዓትን፣
ራስን መግዛትን፣ መስዋዕትነትን፣ ራስ ወዳድ አለመሆንን፣ በእግዚአብሔር
መታመንን እና በተለይም መታዘዝን መማር ነበረባቸው።
ሙሴ የሚታይ መሪ ስለነበር ሕዝቡ ድል መንሳት ከፈለጉ እርሱንና
የእርሱን አመራር መከተል ነበረባቸው። እንደ ማህበረሰብ አብረው መሆን፣
መተባበርና መረዳዳት ወሳኝ ነበር። ከፊታቸው ብዙ መሰናክሎችና ተግዳሮቶች
ነበሩ። ከዚህ የተነሳ፣ በተላይ ተግዳሮቶች ትልቅ በሚሆኑበት ጊዜ፣ አብዛኛው
መንፈሳዊ ዕድገታቸው እነዚህን ተግዳሮቶች በሚጋፈጡበትና ለሙሴ ምላሽ
በሚሰጡበት ሁኔታ ላይ ይደገፍ ነበር።
“የሺህ ማይሎች ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀምራል” የሚለው የተለመደ
የቻይናውያን አባባል ለእነርሱ ሁኔታ እውነት ስለነበር በእያንዳንዱ እርምጃ በጌታ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
መመሪያ መታመን ያስፈልጋቸው ነበር። ነገር ግን አሁን እንደምንመለከተው፣
በሚያሳዝን ሁኔታ፣ እነዚያን ትምህርቶች በቀላሉ አልተማሩም።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሐሴ 10 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ
በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ውስጥ መጥፎ ወይም መልካም የሆኑ
የተለያዩ ገጸ ባህሪያት የተለያዩ ሚናዎችችን ተጫውተዋል። ስለዚህ ለታሪኩ፣
ለቦታዎቹ፣ ለጊዜው እና ለእኩይ ገጸ-ባህሪያቱ ትኩረት መስጠት አለብን።
ነገር ግን በታሪኩ ውስጥ እጅግ ወሳኙ ነገር መፍትሄውና ከእርሱ የምንማረው
ትምህርት ነው። በእነዚህ ታሪኮችም ከዚህ የተለየ ነገር የለም።
ድርጊቱ ሲታይ እግዚአብሔር ችግር ፈቺና ሰላም ፈጣሪ ነው፤ ነገር
ግን የእርሱ ሥራ ከሰዎች አለማመን የተነሣ ተወሳስቧል። ከማያቋርጥ
ማጉረምረምና አለመታዘዝ የተነሣ ዕብራውያን ከባድ ችግሮችንና አሳዛኝ
ክስተቶችን ተለማምደዋል። ካለማመናቸውና ካለመናዘዛቸው የተነሣ
በራሳቸው ላይ ብዙ ችግሮችን አምጥተዋል።
ዘጸ. 15:22–27ን ያንብቡ። ቀይ ባህርን ከተሻገሩ በኋላ መጀመሪያ
ለተፈጸመው ተዓምር መነሻው (ዳራው) ምን ነበር?
የእሥራኤላውያን እምነት የመጀመሪያው ፈተና ከውኃ ፍላጎት
ጋር የተገናኘ ነበር፤ ከባድ፣ ሞቃትና ደረቅ የበረሃ አከባቢ እንደመሆኑ ይህ
የሚያስገርም አይደለም። ለሶስት ቀናት ከተጓዙ በኋላ ሕዝቡ በመጨረሻ ውኃ
አገኙ፣ ነገር ግን ውኃው ለመጠጥ የሚሆን አልነበረም። ማራ ማለት “መራራ”
ማለት ነው። ውኃው መራራ ስለነበር በሚጠነቀቅላቸው አምላክ ላይ የነበራቸው
የእሥራኤላውያን እምነት ዋዠቀ። ነገር ግን እግዚአብሔር በርኅራኄ ምላሽ ሰጠ፣
የመጀመሪያው ተዓምራትም በእንጨት ቁራጭ ተፈጸመ። ውኃው እንዲጣፍጥና
ለመጠጣት እንዲቻል ያደረገው እንጨቱ ሳይሆን እግዚአብሔር ነበር። ከዚህ
ታሪክ ሰዎች ወሳኝ ትምህርቶችን መማር ነበረባቸው፡- (1) የእግዚአብሔርን
ጊዜ ለመጠበቅ ትዕግስተኛ መሆን እንዳለባቸው እና (2) እግዚአብሔር ነገሮችን
የሚያደርገው ከሰብአዊ ፍጡራን ጋር በመተባበር እንደሆነ ነው።
ነገር ግን የእሥራኤል ልጆች ብዙ ነገሮችን ዝም ብሎ እንደሚሆን ነገር
አድርገው በመቀበል እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ታላላቅ ተዓምራቶች በፍጥነት
ረሱ። ስለ እነዚህ ተዓምራቶች እንዲህ በማለት በታላቅ ግለት ለእግዚአብሔር
የምሥጋና ዝማሬ አቅርበው ነበር፡- “አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ በቅድስና የከበረ እንዳንተ ያለ ማን ነው?” (ዘጸ. 15:11)።
ሆኖም ካጉረመረሙ በኋላ እንኳን “በግብጻውያን ላይ ያመጣውን በሽታ”
እንደማያመጣባቸው ቃል ገባላቸው (ዘጸ. 15:26)። እርሱ ይጠብቃቸዋል።
ይህን ተስፋ መለማመድ የሚችሉት ለእርሱ ታማኝ ሆነው ከቆዩ ብቻ ነው።
በራስዎ ላይ ያመጡአቸው ፈተናዎችና ችግሮች ምንድር ናቸው? ከእርሱ ጋር
ቢተባበሩ አሁንም እግዚአብሔር ለእርስዎ እንደሚሰራልዎ በማወቅዎ እንዴት
ያለ መጽናኛ ማግኘት ቻሉ?
እንደ አለመታደል ሆኖ በእነዚህ የጉዞ ታሪኮች የአመጽ ድግግሞሽ አለ። ሕዝቡ ብርቱ የሆነው የእግዚአብሔር እጅ ባለፈው ጊዜ እንደረዳቸውና ለችግሮቻቸው መፍትሄዎችን እንደሰጠ በሚያሰለች ሁኔታ ረሱ። የአሁኑ ችግሮቻቸው ስለ መጨረሻው ግባቸውና ቃል ስለተገባላቸው ድንቅ መጪ ጊዜ ዓይኖቻቸውን እንዲያሳውሩ ፈቀዱ። ችግሩ ዛሬ ባለው የእግዚአብሔር ሕዝብ መካከልም የተለመደ ነው። ዘጸ. 16:1–36ን ያንብቡ። እሥራኤላውያን እንዲያጉረመርሙ ያደረጋቸው ምን ነበር? ይህን ተከትሎ ምን መጣ?
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ፈተናዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ከምግብ ጋር የተገናኙ
መሆናቸውን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። በኤደን ገነት ውስጥ የተከሰተው
ውድቀት፣ ከተከለከለችው ክፉንና መልካምን ከምታስታውቅ ዛፍ ፍሬ ከመብላት
ጋር የተገናኘ ነው (ዘፍ. 2:16፣ 17፤ ዘፍ. 3:1–6)። ኢየሱስ በምድረ
በዳ በተፈተነ ጊዜ ሰይጣን በመጀመሪያ ያቀረበለት የምግብ ፈተና ነበር (ማቴ.
4:3)። ኤሳው ካልተገራ የምግብ ፍላጎቱ የተነሣ ብኩርናውን አጣ (ዘፍ.
25:29–34)። የእሥራኤላውያን አለመታዘዝም ከምግብና ከመጠጥ ጋር
የተገናኘው ምን ያህል ጊዜ ነው! ይህን ጉዳይ ለኋለኛው ትውልድ ሙሴ ማሳሰቡ
አያስደንቅም፡- “ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት
እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ
አስጨነቀህ” (ዘዳ. 8:3)።
መና እሥራኤላውያን ለ40 ዓመታት በምድረ በዳ በተጓዙበት ጊዜ
እግዚአብሔር የሰጣቸው ሰማያዊ እንጀራ ነው። በዚህ ስጦታ አማካይነት
እርሱ የሁሉም ነገር ፈጣሪና የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ሰጭ መሆኑን
አስተማራቸው። ከተፈጥሮ ውጭ በሆነ መንገድ መናን በመስጠት ደግሞ
ሰባተኛውን ቀን ሰንበትን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ለማሳየትም
ተጠቅሟል።
በየሳምንቱ አራት ተዓምራቶች ተፈጽመዋል፡- (1) ለአምስት
ቀናት ለየዕለቱ የሚሆናቸውን መና ሰጣቸው ፤ (2) በየአርቡ እጥፍ መና
ተሰጥቶአቸዋል፤ (3) ከአርብ ጀምሮ እስከ ሰንበት ድረስ መናው አልተበላሸም፣
እና (4) በሰንበት ቀን መና አልወረደም። ሕዝቡ የሰንበትን ቀን እንዲያስቡና
በዚያ ቀን በእግዚአብሔር መልካምነት እንዲደሰቱ እግዚአብሔር እነዚህን
ተአምራቶች በየሳምንቱ ያለማቋረጥ ይፈጽም ነበር። እግዚአብሔር እንዲህ
አለ፡- “እግዚአብሔር ሰንበትን እንደ ሰጣችሁ እዩ” (ዘጸ. 16:29)።
ሰዎች መብላትን ይወዳሉ። መብላትን እንድንወድ ተደርገን ተፈጥረናል።
ከምድር በቅሎ ያደገው የተትረፈረፈው ምግብ (መጀመሪያ እግዚአብሔር
ለሰው ልጅ የሰጠው ምግብ) የሚገልጠው እግዚአብሔር እንድንበላ
እንደሚፈልግ ብቻ ሳይሆን እኛም የምንበላውን መውደድ እንዳለብንም ነው።
ይህ አስደናቂ የሆነ የምግብ ስጦታ እና እርሱን መውደዳችን ያለ አግባብ ጥቅም
ላይ ሊውል የሚችለው እንዴት ነው?
በምድረ በዳ ብዙ ውኃ ያስፈልጋል።ሕዝቡ ጠበኛ ቢሆኑም፣
በእግዚአብሔር ባይታመኑበትም፣ እንዲሁም ውኃ ሊሰጣቸው ያለውን
ፈቃደኝነትና ችሎታ ቢፈታተኑም፣ የዚህን ችግር ሀላፊነት እርሱ ወሰደ።
ባለማመናቸው ወደ ኋላ ዞረው ግብጽን ተመለከቱ።
ዘጸ. 17:1–7ን ያንብቡ። ከዚህ ገጠመኝ ሕዝቡ ምን ትምህርት መማር
ነበረባቸው?
ሙሴ ይህን ቦታ ማሳ፣ ብሎ ጠራው፤ ትርጉሙም “መፈታተን” ማለት
ሲሆን “መጣላትን” የሚያመለክት ነበር። እሥራኤላውያን ባያምኑበትም
እግዚአብሔር ውኃ ሰጣቸው። እነዚህ ሁለቱ ስሞች እሥራኤላውያን
እግዚአብሔርን እንዳይፈታተኑና ከእርሱ ጋር እንዳይጣሉ ሊያስታውሱአቸው
ይገባ ነበር (ዕብ. 3:7፣ 8፣ 15)። ስለ እግዚአብሔር በመካከላቸው
መገኘት ብቻ ሳይሆን ስለ ኃይሉና ሥልጣኑም ጭምር ማረጋገጫ በአይኖቻቸው
ቢያዩም እግዚአብሔር በመካከላቸው ስለመሆኑ ጥያቄ ነበረባቸው።
“ሙሴ ዓለቱን መታው፣ ነገር ግን ሕይወት ሰጭ የሆነው ውኃ እንዲፈልቅ
ያደረገው በደመና ዓምድ ተጋርዶ ከሙሴ አጠገብ የቆመው የእግዚአብሔር
ልጅ ነበር። ሙሴና ሽማግሌዎቹ ብቻ ሳይሆኑ በርቀት ቆሞ የነበረው ጉባኤ ሁሉ
የእግዚአብሔርን ክብር ተመለከተ። ነገር ግን ደመናው ተገፎ ቢሆን ኖሮ በዚያ
ቦታ ከነበረው ከእርሱ ኃይለኛ ብሩህነት የተነሳ ይሞቱ ነበር።”——Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 298.
ያለ ውኃ ሕይወት ስለማይኖር ውኃ የሕይወት ምልክት ነው።
በአካላችን ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሴል ውኃ ይፈልጋል። እኛ ራሳችን
ከመቶ ስልሳ እጅ ውኃ ነን። አጥንቶቻችን እንኳን በከፊል ከውኃ የተሰሩ
ናቸው። ስለዚህ ለእሥራኤላውያን በምድረ በዳ ውኃ መስጠቱ እግዚአብሔር
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የሚያስፈልጉአቸውን ነገሮች ስላዘጋጀላቸው በእርሱ መታመን እንደሚችሉ
ምልክት ነበር። ነገር ግን በድጋሚ መታዘዝ ይጠበቅባቸዋል።
ጳውሎስ ከብዙ መቶ ምዕተ ዓመታት በኋላ በ1ኛ ቆሮንቶስ 10፡4 ላይ
እሥራኤላውያን በምድረ በዳ ያለፉበት ልምምድ የተለየ መሆኑን ለአማኞች
ያስታውሳል። ክርስቶስ ዝም ብሎ አልመራቸውም፣ ነገር ግን ውኃ ሰጣቸው
(መዝ. 78:15፣ 16)። መንፈሳዊና አካላዊ ፍላጎቶቻቸውንም አሟላ።
ለእነርሱ ክርስቶስ የሕይወት ምንጭ እና ዘላለማዊ ሕይወት ሰጭ ስለነበር “ያ
ዓለት ክርስቶስ ነበር።” አለት ጠንካራ እንደሆነ ሁሉ እግዚአብሔር ሕዝቡን
በጽናት መራ፡ እርሱ ተስፋዎቹን ሳይፈጽም ስለማይቀር በእርሱ መታመን ይቻላል።
አሁን በእግዚአብሔር መታመን ያለብዎ አንዳንድ ነገሮች ምንድር ናቸው?
ለእርሱ ፈቃድ በመገዛት እርሱ በራሱ ጊዜ የሚያደርገውን ነገር እንዲያደርግ
እርሱን መጠበቅን መማር የሚችሉት እንዴት ነው? ይህን ማድረግ ሁልጊዜ
ቀላል የማይሆነው ለምንድር ነው?
ሙሴ ራጉኤል ተብሎ በሚጠራው በአማቱ ዮቶር ተጎብኝቶ ነበር (ዘጸ. 2:18)። ዮቶር ሲፓራ የምትባለውን የሙሴን ሚስት እና ጌርሳምና አልዓዛር የሚባሉ ሁለት ልጆችን ከእርሱ ጋር አመጣ። እየመጡ መሆናቸውን ሙሴ በሰማ ጊዜ ሊቀበላቸው ሄደ። ዘጸ. 18:1–27ን ያንብቡ። በሕዝቡ ታሪክ ውስጥ የተፈጸሙት ዋና እርምጃዎች ምን ነበሩ?
ዮቶር የመጣው እግዚአብሔር ለእሥራኤላውያን ያደረገውን አስደናቂ
ማዳን ስለሰማ ነበር። ሙሴም “እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን
ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥
እግዚአብሔርም እንዳዳናቸው ለአማቱ ነገረው” (ዘጸ. 18:8)።
ዮቶር እግዚአብሔር ለሕዝቡ ስላደረገው ቸርነትና ስለ እነርሱ
ስላደረገው ከተለመደው ውጭ የሆነ ጣልቃ መግባት እግዚአብሔርን እንዲህ
በማለት አመሰገነ፡- “ዮቶርም፦ ከግብፃውያንና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ፥
ከግብፃውያንም እጅ ሕዝቡን ያዳነ እግዚአብሔር ይባረክ። ትዕቢት
ባደረጉባቸው ነገር እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አሁን አወቅሁ
አለ” (ዘጸ. 18:10፣ 11)።
እዚህ ላይ የምንመለከተው እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል
የሚያደርገው ነገር እውነተኛው አምላክ ማን እንደሆነና እርሱ ለሕዝቡ
ምን ማድረግ እንደሚችል ለዓለም እንዴት ምስክር እንደሚሆን የሚያሳይ
ምሳሌ ነው።
በተመሳሳይ ጊዜ ዮቶር ስለ እውነተኛው አምለክ የሆነ ነገር ተማረ፤
እርሱ ራሱ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ነገር ነበረው፤ ያውም ለእግዚአብሔር
ሕዝብ የሚሰጠው ጥበብ ያለበትና ጠቃሚ ምክር ነበር። ሙሴ የፍትህና ርትዕ
መርሆዎች ያሉበትን የዳኝነት ሥርዓትን ማደራጀት ይፈልግ ነበር። ራሳቸውን
የሰጡ፣ ታማኝና ሀቀኛ የሆኑ ዳኞችንም ይፈልግ ነበር። ዮቶር የሚከተሉትን
ብቃቶች በጥበብ ዘረዘረ፡- (1) እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች፤ (2)
የሚታመኑ ሰዎች ፤ እና (3) ታማኝነትን በማጉደል የሚገኝ ጥቅምን የሚጠሉ
ሰዎች። መልካም ባህርይና ብቃት ያላቸው የሺህ አለቆች፣ መቶ አለቆች፣
አምሳ አለቆችና አሥር አለቆች መሾም ነበረባቸው። በዚህ መንገድ የሙሴ
አስተዳደራዊ ሸክም ይቀንስና ወሳኝ በሆኑ ችግሮች ላይ ትኩረት ማድረግ
ይችላል። በመሆኑም ሕዝቡ ጥሩ አገልግሎት ማግኘት ይችላል።
ሙሴ ጥበብ ያለበትን የዮቶርን ምክር ተቀብሎ (ዘጸ. 18:24)
የተለያዩ አስተዳደራዊ ሚናዎችን የሚጫወቱ መሪዎችን ሾመ (ደግሞ ዘዳ.
1:9–18ን ይመልከቱ)።
ሙሴ ይህ ጉዳይ አይመለከትህም ብሎ ሽማግሌውን ማሰናበት ይችል ነበር።
ነገር ግን እንደዚህ አላደረገም። ይህን ዕብራዊ ያልሆነውን ሰው እንኳን
ለመስማት ፈቃደኛ ከመሆኑ ምን ጠቃሚ ትምህርቶችን መማር እንችላለን?
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
1ኛ ቆሮ. 10:11ን ያንብቡ። እነዚህ ክስተቶች ተመዝግበው ስለመቀመጣቸው ሙሴ ምን ምክንያት ይሰጣል?
ለእሥራኤላውያን የሆኑላቸው ነገሮች ሁሉ ምሳሌዎችና ለክርስቶስ
ተከታዮች ማስጠንቀቂያዎች ስለሆኑ ወደ ችግር እንዳይገቡ ይረዱአቸዋል፣
ማለትም ከእነዚህ ምሳሌዎች ትምህርት ያገኛሉ በማለት ጳውሎስ ያብራራል። ይህ
“በዘመን መጨረሻ” ለምንኖር ለእኛም የሚሆን ትምህርት ነው። እግዚአብሔር
አማኞችን “በኃይል፣ በፍቅርና ራስን በመግዛት” ሊያበረታ ለሕዝቡ መንፈስ
ቅዱስን ይሰጣል (2 ጢሞ. 1:6፣ 7) ። ይህን የሚያደርገው ትክክለኛ
ውሳኔዎችን እንዲያደርጉና ትምህርቱን እንዲከተሉ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ
የአዲስ ሕይወት ምንጭ ስለሆነ (ዮሐንስ 14:6)፣ እርሱ ብቻ በሚከተለው
መልክ ሊለውጠን ይችላል፡- “ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና
ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር
ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን
እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን
ዓለም አትምሰሉ” (ሮሜ 12:1፣ 2)።
ኋላ ኢየሱስ ከእነዚህ ዘገባዎች ውስጥ፣ በተለይም በምድረ በዳ
ስለመራቸው ስለ ራሱ እውነቶችን ለማስተማር፣ የመናን እና ውኃን ምሳሌዎች
በመጠቀም ትምህርቶችን ነቅሶ አወጣ።
ዮሐንስ 4:7–15 እና ዮሐንስ 6:31–51ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ለእኛ
እንደ ክርስቲያኖች ምን እውነቶች ተገልጠውልናል?
ሳምራዊቷ ሴት የትም ቢሆን ማግኘት የማትችለውን ነገር ክርስቶስ
ሊሰጣት እንደሚችል ተገነዘበች። ሰላምን፣ ደስታንና ፍስሃን ከውስጥ መጠማት
የሚመጣው ከእግዚአብሔር ስለሆነ ሊያረካው የሚችለውም እግዚአብሔር
ብቻ ነው (መዝ. 42:1፣ 2)።
ኋላ፣ በመናው አውድ፣ ለሕዝቡ መና የሰጠው ሙሴ ሳይሆን
እግዚአብሔር መሆኑን ኢየሱስ አብራራ። ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፡-
“የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም” (ዮሐንስ
6:35)። ኢየሱስ ሶስት ጊዜ ደጋግሞ እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ ብሏል
(ዮሐንስ 6:35፣ 41፣ 48)።
በምድረ በዳ የወረደው መና “ከሰማይ የወረደ እንጀራ” እንደነበረ ሁሉ
(ዮሐንስ 6:31፣ 32) ከአለት የፈለቀው ውኃም ጥማታቸውን ለማርካት
ከክርስቶስ የተሰጠ ስጦታ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ “የሕይወት እንጀራ”
(ዮሐንስ 6:35፣ 48) እና “ሕያው ውኃ” (ዮሐንስ 4:10፣ 11፣ 14፤
ዮሐንስ 7:37፣ 38) ስለሆነ እንጀራውና ውኃው ከእነዚህ በውጫዊ ሁኔታ
ከሚታዩ ገጽታዎች ባሻገር መንፈሳዊ ወሳኝነትም አላቸው። ስለዚህ መንፈሳዊ
ጥማታችንንና ረሃባችንን በትክክል ሊያረካ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው።
“ከቀይ ባህር ወደ ሲና” የሚለውን ርዕስ አባቶችና
ነቢያት ከሚለው የኤለን ጂ ኋይት መጽሐፍ ከገጽ 291–302 ላይ ያንብቡ።
ሕዝቡ ከውኃ ጋር ከነበረው ክስተት በኋላ ብዙም ሳይቆይ አዲስ
አደጋ፣ ያውም ጨካኝና ጦርነት ወዳድ የሆኑ የአማሌቃውን ጎሳ ገጠማቸው
(ዘጸ. 17:8–16ን የይመልከቱ)። “አማሌቃውያን ስለ እግዚአብሔር
ወይም ስለ እርሱ ሉአላዊነት አላዋቂ አልነበሩም፣ ነገር ግን እርሱን
በመፍራት ፋንታ የእርሱን ኃይል ለመቃወም ተዘጋጁ። ሙሴ በግብጻውያን
ፊት የሰራቸው ተዓምራቶች በአማሌቃውያን ዘንድ ማሾፊያ ሆኑ፣ በዙሪያቸው
ያሉ ሕዝቦች ፍርሃትም የመቀለጃ ርዕስ ሆነ። ዕብራውያንን አንድ ሰው
እንኳን ሳያመልጥ ለማጥፋት ከአማልክቶቻቸው ጋር መሃላ ስለፈጸሙ
የእሥራኤላውያን አምላክ የሚመክትበት ኃይል አይኖረውም ብለው ተኩራሩ።
እሥራኤላውያን አልጎዱአቸውም ወይም አላስፈራሩአቸውም። ጥቃት
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የሰነዘሩት ያለ አንዳች ትንኮሳ ነበር። የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማጥፋት
የፈለጉት ለእግዚአብሔር ያላቸውን ጥላቻና ሥልጣኑን እንደማይቀበሉ
ለማሳየት ነበር። አማሌቃውን ለረዥም ጊዜ በትዕቢት የተነፉ ኃጢአተኞች
ስለነበሩ የፈጸሙአቸው ወንጀሎቻቸው ለበቀል ወደ እግዚአብሔር ይጮኹ
ነበር። ሆኖም የእግዚአብሔር ምህረት አሁንም ወደ ንስሃ እየጠራቸው ነበር፤
ነገር ግን የአማሌቅ ሰዎች በደከሙና አቅመ-ቢስ በሆኑ እሥራኤላውያን
ላይ በወደቁባቸው ጊዜ የሕዝባቸውን ጥፋት አተሙ።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 300.
1. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ካደረገው ነገር ዮቶር ስለ እውነተኛው
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ካደረገው ነገር ዮቶር ስለ እውነተኛው
አምላክ በተማረበት ሀሳብ ላይ ትኩረት ያድርጉ። (ዘዳ. 4:4–
8ን ይይልከቱ።) ይህ መርህ ዛሬም እውነት የሚሆነው ለምንድር ነው? የእኛ ቤተ ክርስቲያን ለዓለም የምታቀርበው ምን ዓይነት
ምስክርነት ነው? በማለት ራስዎንና ክፍልዎን ይጠይቁ። ስለ
አምላካችን ተፈጥሮና ባህርይ ለዓለም ምን እንላለን?
2. 1ኛ ቆሮ. 10፡4ን እንደገና ያንብቡ። በኢየሱስ ከምንመለከተው
1ኛ ቆሮ. 10፡4ን እንደገና ያንብቡ። በኢየሱስ ከምንመለከተው
በተቃራኒ የብሉይ ኪዳን አምላክ ተበቃይ፣ በጥላቻ የተሞላ እና
ይቅር የማይል ነው ስለሚለው ስለ ጥንቱ ክህደት እና ዛሬም
አንዳንዶች ስለሚያምኑት ይህ ምን ሊያስተምረን ይገባል? ያ
እምነት ስህተት መሆኑን ይህ ጥቅስ የሚያሳየው እንዴት ነው?
3. አማሌቃውያን ስለ እውነተኛው አምላክ ለመማር እንዴት ዕድል
አማሌቃውያን ስለ እውነተኛው አምላክ ለመማር እንዴት ዕድል
እንደነበራቸው ኤለን ጂ ኋይት ከላይ የጻፈችውን እንደገና ያንብቡ።
የእነርሱን አመለካከት ከዮቶር አመለካከት ጋር ያነጻጽሩ።
እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን ከእሥራኤላውያን ጋር
ግንኙነት በነበራቸው በጥንቱ ዓለም በነበሩ ብዙ ጎሳዎች ላይ ፍርድ
ካመጣበት ምክንያት ምን ትምህርቶችን ማግኘት እንችላለን?