የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ዘጸአት



3ኛ ሩብ ዓመት 2025


ሐምሌ 19 - 25

5ኛ ትምህርት

Jul 26 - Aug 1




ፋሲካ



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ: ዘጸ. 11:1–10፣ ሚክ. 6:8፣ ዘጸ. 12:1–30፣ 1ኛ ቆሮ. 5:7፣ ዘጸ. 13:14–16፣ ዕብ. 11:28።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ፦ ይህ አምልኮ ለእናንተ ምንድር ነው? ባሉአችሁ ጊዜ፥ እናንተ፦ በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ይህች ናት ትሉአቸዋላችሁ” (ዘጸ. 12:26፣ 27)።

አሥረኛውና የመጨረሻው መቅሰፍት ሊወርድ ነው። ማስጠንቀቂያው ተሰጥቷል፤ የመጨረሻው ውሳኔ መወሰን አለበት። ነገሩ የሕይወትና የሞት ጉዳይ ነው። የግለሰብ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦችና የመላው ሕዝብ ብልጽግና በአደጋ ላይ ነው። በብዙ ሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ሞት ወይም ሕይወት ፈርዖንና የእርሱ ባለሥልጣናት ተጠያቂ ናቸው። ሕያው ለሆነው የእሥራኤል አምላክ ያለው አመለካከት የእርሱን የወደፊት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን የሕዝቡንም ሁኔታ ይወስናል።

የሁኔታዎች አስከፊነት በላያችን ሲከብድ እና ከራሳችን ባሻገር በሌሎች ብዙ ሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደር የሚችል ቀጣይ እርምጃና አቅጣጫ መምረጥ ሲኖርብን እንዴት ይሰማናል? እንዴትስ ማድረግ እንችላለን?

ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ እግዚአብሔር ጥበብን፣ ማስተዋልን እና ኃይልን ሊሰጠን ፈቃደኛ ነው (1ኛ ቆሮ. 1:30፣ ፊልጽ. 2:13)።

ነገር ግን ችግሩ በራሳችን ትዕቢተኛ ልቦች ሁልጊዜ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ አንፈልግም። ምን እንደሆነ እናውቃለን፣ ነገር ግን ለማድረግ ፈቃደኛ አንሆንም። በዘጸአት ዘገባ ውስጥ፣ አንድ ሰው ከበቂ በላይ የሆነ ማስረጃ እያለ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ለእግዚአብሔር ለመገዛት ፈቃደኛ አለመሆን፣ ከራሱ ባሻገር በብዙዎች ላይ አሳዛኝ ክስተት አምጥቷል። ብዙ ጊዜ የሚሆነውም ይኸው ነው። *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሐምሌ 26 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።

ሐምሌ 20
Jul 27

አንድ ተጨማሪ መቅሰፍት


ነቢዩ አሞጽ እንዲህ ይላል፡-በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም” (አሞጽ 3:7)።

እናም በነቢዩ ሙሴ አማካይነት ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ ለፈርዖን ገለጠለት። ለፈርዖን እጅግ ጥብቅ የሆነ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል። ይህ ደግሞ በኩራት፣ በብዝበዛ፣ በአመጽ እና በጣዖት አምልኮ ላይ የሚደረግ ፍትሃዊ ፍርድ ነው።

እነዚህ ሁሉ በግብጽ ላይ መቅሰፍቶች እንዲመጡ ያነሳሱ ነገሮች ናቸው። ዘጸ. 11:1–10ን ያንብቡ። እግዚአብሔር በግብጽ ላይ ፍርድ ከማምጣቱ በፊት ምን ማስጠንቀቂያ ነበር የሰጠው?



እግዚአብሔር በቅርቡ ስለተከሰቱ ክስተቶችና እነዚህ ክስተቶች ምን ማለት እንደሆኑ እንዲያስቡ ለግብጻውያን ጊዜ ሰጠ—ሶስት የጨለማ ቀናት (ዘጸ. 10:23)። ደግሞም የመጨረሻውን ግልጽ ማስጠንቀቂያ፣ ትክክል የሆነውን ነገር እንዲያደርጉ የመጨረሻ ዕድል ሰጠ።

ነገር ግን ዘጸ. 11:8 “ሙሴ ከፈርዖን ፊት በታላቅ ቁጣ ወጣ” ይላል። ሙሴ ለምን ተቆጥቶ ይወጣል? ምናልባትም ከፈርዖን የልብ ድንዳኔ የተነሳ ሊመጣ ያለውን አሳዛኝ ክስተት፣ ብዙ የዋህ ሕዝብን ሊመታ ስላለው አስረኛው መቅሰፍት፣ ስለሚያውቅ ሊሆን ይችላል።

ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች ውስጥ አስር ወሳኝ ቁጥር ነው። አስር ሙሉነትን ወይም ፍጹምነትን ይወክላል። (አስርቱ ትዕዛዛት የእግዚአብሔር የግብረገብ ሕግ ፍጹም መገለጥ እንደሆኑ ያስቡ)። በግብጽ ላይ የወረዱ አስሩ መቅሰፍቶች የእግዚአብሔር ፍትህና በቀል በሙላት መገለጡን የሚጠቁሙ ናቸው።

እግዚአብሔር ፈራጅ ስለሆነ ኩራትን (ትዕቢትን)፣ ኢ-ፍትሃዊነትን፣ መድልዎን፣ እብሪተኝነትን፣ ብዝበዛን፣ ጭካኔን እና ራስ ወዳድነትን ይቃወማል።

እርሱ ከሚሰቃዩት፣ ጥቃት ከደረሰባቸው፣ ከተበደሉት እና ከተሰደዱት ጎን ይቆማል። እግዚአብሔር ፍትህን የሚያሰፍን ሲሆን ይህም በርግጠኝነት የፍቅሩ ሌላኛው መግለጫ ነው። (መዝ. 2:12፣ መዝ. 33:5፣ መዝ. 85:11፣ መዝ. 89:14፣ መዝ. 101:1፣ ኢሳ 16:5፣ ኤር. 9:24ን ይመልከቱ)።

እኛም በተቻለን መጠን አፍቃሪና ፍትሃዊ ለመሆን መጣር አለብን።

ነገር ግን በአንድ ወይም በሌላ መንገድ በቀላሉ ወደ ጽንፍ ልንወድቅ እንችላለን። ከ“ፍቅር” የተነሳ ለስህተት ልንጋለጥና መስተካከል ላለባቸው ነገሮች ዓይናችንን ልንጨፍን እንችላለን። ወይም ከብረት የተሰራ ይመስል ፍትህን በጭካኔ ልንፈጽም እንችላለን። የትኛውም ጽንፍ ትክክል አይደለም።

ከዚህ ይልቅ መሆን ያለበት ይህ ነው፡- “እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?” (ሚክ. 6:8)። ትክክለኛ የሆነ ሚዛንን መጠበቅ ካልቻልን (እኛ ማድረግ አንችልም)፣ ከፍትህ ይልቅ ከምህረት ወገን ሆኖ መሳሳት የሚሻለው ለምንድር ነው? ወይም ይሻል ይሆን?

ሐምሌ 21
Jul 28

ፋሲካ


ዘጸ. 12:1–20ን ያንብቡ። እሥራኤላውያን ግብጽን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት እግዚአብሔር ምን የተለዩ መመሪያዎችን ሰጣቸው?



ሰው የሚጠብቀው ሕዝቡ ከግብጽ የሚወጡበትን መንገድ እንዴት እንደሚያደራጁ፣ ማለትም ለማምለጥ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በተለይም ለአዛውንት፣ ትናንሽ ሕጻናትን ለያዙ እናቶች፣ ለእንስሳት፣ ወዘተ. እንዴት እንደሚያዘጋጁ እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መመሪያ ይሰጣቸዋል ብሎ ነው። የእግዚአብሔር መመሪያ ግን የሚያስደንቅ ነበር፡-ፋሲካን እንዴት ማክበር እንዳለባቸው ነገራቸው።

በሌላ አገላለጽ፣ ትኩረቱ ሊያድናቸው የነበረውን እግዚአብሔርን በማምለክ ላይ ነው።: ሌላው ነገር ሁሉ በራሱ ጊዜ ተከትሎ ይመጣል። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

እያንዳንዱ ቤተሰብ በግ ማዘጋጀት ያለበት ሲሆን ምንም የሚባክን ነገር አይኖርም። እያንዳንዱ ሰው የራሱን ድርሻ መመገብ አለበት። ቤተሰቡ ብቻውን በጉን በልቶ መጨረስ የማይችል ከሆነ ከሌላ ቤተሰብ ጋር ሆነው መብላት ነበረባቸው። ዘጸ. 12:13፣ 14ን ያንብቡ። የመጨረሻው መቅሰፍት ሲወርድ እግዚአብሔር ምን ያደርግላቸዋል? ይህ ሁሉ ምንን ይወክላል?



ነጻ መውጣቱ በቋሚነት በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን የሚከበረውም እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ያደረገውን ያለፈውን ክስተት ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን የአሁኑን ትውልድ ነጻ ያወጣበትን ተግባር እውነተኛነት ለማረጋገጥም ነው። ይህ ለእያንዳንዱ ቡድን አዲስ (ትኩስ) ልምምድ መሆን ነበረበት።

ቁጥር 12 እና 13 የፋሲካን/ የመታለፍን ትርጉም ያብራራል፡ - የእግዚአብሔር የጥፋት ፍርድ እሥራኤላውያንን “ያልፋቸዋል፤” ስለዚህ “ፋሲካን/መታለፍን” ያከብራሉ። ይህ በእንግሊዝኛው ፓስ ኦቨር “pass over” የሚለው ቃል ፓስ እና ኦቨር የሚባሉ የሁለት ቃላት ድብልቅ ሲሆን ጥቅም ላይ የዋሉበት ምክንያት የበር መቃኖቻቸው የሕይወትና የድነት ምልክት በሆነው በበጉ ደም የተቀቡ የእሥራኤላውያንን ቤቶች ጥፋት ሳይነካ “አልፏቸው ስለሄደ” ነበር። በዕብራይስጥ ፋሲካ የሚለው ስም ፔሳች (Pesach) የሚል ሲሆን “አልፎ መሄድ” ከሚል ግሥ የመጣ ነው። ይህ አልፎ መሄድ የሚል ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የደጆቻቸው መቃን የሕይወትና የመዳን ምልክት በሆነው በበጉ ደም ምልክት የተደረገባቸውን የእሥራኤላውያንን ቤቶች ጥፋት (አጥፊው መልአክ) አልፎአቸው ስለሄደ ነበር። በዕብራይስጥ ፋሲካ የሚለው ቃል የመጣው “አልፎ መሄድ” ከሚል ግሥ ነው።

የፋሲካ አከባበር እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ያደረጋቸውን ኃይለኛና በጸጋ የተሞሉ ተግባራት ለእያንዳንዱ እሥራኤላዊ ለማስታወስ የታቀደ ነበር። ይህ በዓል ብሄራዊ ማንነታቸውን እንዲጠብቁና ኃይማኖታዊ እምነቶቻቸውን እንዲያትሙ ረድቷል። እግዚአብሔር ባለፉት ጊዜያቶች ያደረገልዎን መልካም ነገር ሁልጊዜ ማስታወስና ወደ ፊትም በተመሳሳይ ሁኔታ መልካም እንደሚያደርግልዎ መታመን እጅግ ወሳኝ የሚሆነው ለምንድር ነው?

ሐምሌ 22
Jul 29

ፋሲካ


ዘጸ. 12:17–23ን ያንብቡ። ይህ አዲስ በዓል ሲከበር ደም ምን ሚና ይጫወታል?



በዚህ በዓል ላይ የመስዋዕቱ እንስሳ ደም ቁልፍ ነገር ነው። በዚህ ግብዣ ላይ የተሳተፉ በቤቶቻቸው መቃኖች ላይ የታረደውን በግ ደም መቀባት ነበረባቸው። በዚህ መንገድ በደሙ ያልተሸፈኑ ከሚገጥማቸው ነገር እግዚአብሔር እንደሚያድናቸው በማመን በእርሱ ላይ ያላቸውን እምነት አሳዩ። እንዴት ያለ ኃይለኛ የወንጌል መግለጫ ነው!

የፋሲካው በግ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደውን የእግዚአብሔርን በግ” (ዮሐንስ 1:29፣ ) ስለሚወክል ነውር የለሽ መሆን ነበረበት።

የእንስሳው ደም ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡- ከአደጋ መጠበቅን ስለሚወክል በሞት ጊዜ የሕይወት ምልክት ነበር።

“ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም” (ዘጸ. 12:13)።

ከባርነት ነጻ ወጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር መሄድን ብቻ ሳይሆን ለኃጢአታችን የተፈጸመውን የኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕትና በእርሱ ደም በተሸፈኑት ሁሉ ላይ የተደረጉትን የእርሱን መልካም ተግባራት ስለሚወክል መላው ወንጌል ከፋሲካ በዓል ጋር ተገናኝቶ ነበር።

ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ጳውሎስ ወደ ኋላ ዞር ብሎ ይህን በዓል ሲመለከት እንዲህ በማለት ጽፏል፡- “እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና” (1ኛ ቆሮ. 5:7)።

እርሾ የተለያየ ዓይነት ሊጥ ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ ይውላል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሰበት ጊዜ እሥራኤላውያን ከግብጽ ከመውጣቸው በፊት በነበረው ምሽት ያልቦካ ቂጣ ካዘጋጁበት ጋር የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት በተገናኘ ነበር። ደግሞ እርሾ ከቤቶቻቸው መወገድ ነበረበት (ዘጸ. 12:8፣ 15–20፤ ዘጸ. 13:3–7)። በዚህ አውድ፣ እርሾ የኃጢአት ምልክት ነው (1ኛ ቆሮ. 5:6–8)፤ ስለዚህ በፋሲካ በዓል ጊዜ ለአንድ ሳምንት ጥቅም ላይ መዋል አልነበረበትም።

ያልቦካው ቂጣ ፈተናዎችን ሁሉ በማሸነፍ ሕይወቱን ለእኛ የሰጠው ኃጢአት የሌለበት መሲህ ምልክት ነው (ዮሐንስ 1:29፣ 1ኛ ቆሮ. 5:7፣ ዕብ. 4:15)። በደም የተነከረው “ሂሶጵ” የሚወክለው የሚያነጻውን የእግዚአብሔርን ጸጋ ነው (መዝ. 51:7)። በአጭሩ፣ በመላው የፋሲካ ሂደት ውስጥ የኢየሱስ የማዳን ሥራ ተገልጧል። ኃጢአትን ማስተሰረይ የኢየሱስን ደም፣ ራሱን አምላክን፣ የመጠየቁ እውነታ ኃጢአት በርግጠኝነት ምን ያህል ከፉ ስለመሆኑ ምን ያስተምረናል?

ሐምሌ 23
Jul 30

ችቦውን ማስተላለፍ


ልጆቻችን እግዚአብሔርንና የእርሱን የፍቅር እንክብካቤ እንዴት ማወቅ እንደሚችሉ መዝሙረኛው እንዲህ በማለት ይገልጻል፡- “አንድ ትውልድ ለሌላኛው ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥ ኃይልህንም ያወራሉ” (መዝ. 145:4)። ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ተአምራዊ ሥራዎቹ እና ስለ ትምህርቶቹ አንድ ቤተሰብ ለሌላኛው ቤተሰብ መናገር አለበት፤ ይህ መሆን ያለበት የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀትን ለሌላኛው ትውልድ ለማስተላለፍ ነው። ዘጸ. 12:24–28ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ እየተገለጸ ያለው ወሳኝ ነጥብ ምንድር ነው?



በእሥራኤል፣ ወላጆች የመጀመሪያ መምህራን ስለነበሩ የዘጸአትን ታሪክ ለልጆቻቸው መተረክ ነበረባቸው። መነገር የነበረበት ከዚህ በፊት ሆኖ እንዳለፈ ታሪካዊ ክስተት ሳይሆን፣ ምንም እንኳን ከረዥም ጊዜ በፊት የተፈጸመ ቢሆንም፣ እንደ ራሳቸው ልምምድ ተደርጎ ነበር። ይህንን በዓል በማክበር ራሳቸውን ከቅድመ አያቶቻቸው ጋር ስለሚያመሳስሉ ታሪኩን እንደገና መኖርና ተጨባጭ ማድረግ ነበረባቸው። አባት እንዲህ ይላል፡- “እኔ በግብጽ ነበርኩ፣ የግብጻውያን አማልክት ሽንፈት ሲገጥማቸውና በግብጻውያን ላይ የወረዱትን መቅሰፍቶች ተመልክቻለሁ፣ ነጻም ወጥቻለሁ።” በዘጸአት መጽሐፍ ውስጥ ልጆች ስለ ፋሲካ የሚጠይቁአቸውን ጥያቄዎች ወላጆች እንዴት መመለስ እንዳለባቸው ሁለት ጊዜ ተሰምሮበታል (ዘዳ. 6:6–8 እና ዘጸ. 13:14–16ን ይመልከቱ)።

እሥራኤላውያን ከግብጽ ነጻ መውጣቻውን እንዲያከብሩ በተነገራቸው ጊዜ ገና በግብጽ እንደነበሩ ማስታወስ ጥሩ ነው። ስለዚህ ጠቅላላው በዓሉን የማክበር ሥርዓት የእምነት ተግባር ነበር። ሕዝቡ መመሪያዎቹን ከተቀበሉ በኋላ ለአዳኛቸው “ተጎነበሱ ሰገዱም” (ዘጸ. 12:27)፣ ከዚያም የፋሲካን መመሪያዎች ተከተሉ።

በዘዳግም መጽሐፍ ውስጥ እሥራኤላውያን ያደረጉትን ጉዞ እንደ ራሳቸው ጉዞ አድርው እንዲወስዱ በሚያደርግ መልኩ ለልጆቻቸው ታሪካቸውን መንገር እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቶአቸዋል። ታሪኩ በጥቅሉ ያለውን ቃና እና በአሁኑ ልምምድ ላይ የሰጠውን አጽንዖት ልብ ይበሉ፡- “ አባቴ የተቅበዘበዘ ሶርያዊ ነበረ፤ በቍጥር ጥቂት ሳለ ወደ ግብፅ ወረደ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ የሆነ የበረታም ቍጥሩም የበዛ ሕዝብ ሆነ። ግብፃውያንም ክፉ ነገር አደረጉብን፥ አስጨነቁንም፥ በላያችንም ጽኑ ከባድ ሥራን ጫኑብን ወደ አባቶቻችንም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፥ ጭንቀታችንንም ድካማችንንም ግፋችንንም አየ፤ እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ድንጋጤ፥ በተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤ ወደዚህም ስፍራ አገባን፥ ወተትና ማር የምታፈስሰውንም ይህችን ምድር ሰጠን” (ዘዳ. 26:5-9)።

የፋሲካን ታሪክ (ወይም በቅዱስ ታሪክ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም ክስተት) ለልጆች መተረካቸውና እንደገና መንገራቸው እግዚአብሔር ለራሳቸውና ለሕዝቡ ያደረገውን እንዲያስታውሱ በከፍተኛ ሁኔታ ረድቷቸዋል። ታሪኩን መንገር ለሰሚዎቹ የሚያስፈልገውን ያህል ለተናጋሪውም አስፈላጊ ነበር። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

ሐምሌ 24
Jul 31

መለኮታዊ ፍርድ


እግዚአብሔር የግብጻውያንን በኩር እንዴት እንደመታ ለማወቅ ዘጸ. 12:29፣ 30ን ያንብቡ። እግዚአብሔር በበኩር ላይ ትኩረት ያደረገው ለምን ነበር? (ደግሞ ዕብ. 11:28ን ይመልከቱ)። )።



የግብጻውያን የመጨረሻው መቅሰፍት የወረደው በበኩር ልጅ ላይ ነበር። የሰዎችን የራሳቸውን ፍትወት፣ ፍላጎትና ፍርሃት ያንጻባርቁ በነበሩ ዋጋ ቢስ የግብጽ አማልክትና እነዚህን የውሸት አማልክት ባመለኩት ቤተሰቦች ሁሉ ላይ የወረደ መለኮታዊ ፍርድ ነበር።

ቀደም ብለው የወረዱ መቅሰፍቶች እንዳመለከቱት ጣዖቶቹ ሕዝቡን ማዳን አልቻሉም። ዋጋቢስነታቸው አሁን፣ በግብጻውያን ላይ እጅግ ታላላቅ መዘዞችን ባመጣው በ10ኛው መቅሰፍት ጊዜ፣ የበለጠውን ግልጽ ሆኗል።

“እጅግ ሰፊ በሆነው የግብጽ ግዛት ውስጥ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ኩራት ተሰብሯል። የሀዘንተኞች ጩኸትና ዋይታ አየሩን ሞልቶታል። ንጉሥና በቤተ መንግሥት አደባባይ ያሉ ሁሉ፣ ፊታቸው ገርጥቶና እግሮቻቸው እየተብረከረኩ፣ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ፍርሃት ተሸብረው ቆመዋል።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 280.

ፈርዖን የግብጽ አምላክን የመጨረሻውን ሥልጣን ይወክላል፤ የእርሱ የበኩር ልጅ የአምላክ ልጅ ተደርጎ ይወሰዳል። ኢሲስ ልጆችን የምትጠብቅ አምላክ ነበረች፤ ሄቄት በወሊድ ጊዜ ሴቶችን የምትከታተል አምላክ ነበረች፤ ሚን የመራባት አምላክ ነበር። ከእነዚህ አማልክት በተጨማሪ በግብጽ የነበሩ በርካታ የወላድነት አማልክት ነበሩ። እነዚህ አማልክት በሙሉ ከሕያው አምላክ ጋር ሲነፃፀሩ ኃይል የለሽ ነበሩ። ሙሴ እንዲህ ይላል፡- “ አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ በቅድስና የከበረ እንዳንተ ያለ ማን ነው?” (ዘጸ. 15:11)። ኋላ ዮቶር እንዲህ በማለት መስክሯል፡- “ ትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አሁን አወቅሁ” (ዘጸ. 18:11)።

እንደ ዘጸአት ምዕራፍ 1፣ እሥራኤላውያንን ለማድከምና ተገዥ አድርጎ ለማዋረድ በፈርዖን ትዕዛዝ ግብጻውያን አዲስ የሚወለዱ ወንዶችን ገድለዋል።

አሁን የእግዚአብሔር ቅጣት የግብጻውያንን የበኩር ወንድ ልጅ መታ። ሰዎች የዘሩትን ያጭዳሉ።

ውሳኔዎቻችንና ባህሪያችን የሚያስከትሉአቸው መዘዞች አሏቸው።

የስህተት ድርጊቶቻችን በሚያስከትሉአቸው መዘዞች የምንሰቃይ እኛ ብቻችንን አለመሆናችንን ሁላችንም የተለማመድነው የሚያም እውነት ነው። አንዳንድ ጊዜ ሌሎች ብዙ ሰዎች፣ ክፋት እንኳን የሌለባቸው፣ በተመሳሳይ ይሰቃያሉ። ይህ የኃጢአት ተፈጥሮ ነው። ከሌሎች ኃጢአት የተነሣ በምን ተሰቃይተዋል? ወይም ከእርስዎ ኃጢአት የተነሣ ሌሎች የተሰቃዩባቸው መንገዶች ምንድር ናቸው? ብቸኛው ተስፋችን ምንድር ነው?

ሐምሌ 25
Aug 1


ተጨማሪ ሀሳብ


“ፋሲካ” የሚለውን ርዕስ ኤለን ጂ ኋይት ከጻፈችው አባቶችና ነቢያት ከሚለው መጽሐፏ ከገጽ 273–280 ያለውን ያንብቡ።

“ፋሲካ ከግብጽ መውጣትን ወደ ኋላ የሚያመለክት ብቻ ሳይሆን ክርስቶስ ሕዝቡን ከኃጢአት ባርነት የሚያወጣበትን ታላቁን ነጻ መውጣት ወደ ፊት የሚያመለክት ለመታሰቢያነት የሚውልና ምሳሌያዊም ነው።

የመስዋዕቱ በግ የመዳናችን ብቸኛው ተስፋ ያለበትን ‘የእግዚአብሔርን በግ’ ይወክላል። ጳውሎስ እንዲህ ይላል፡- ‘ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናልና’ 1 ቆሮ. 5:7። የፋሲካው በግ መታረድ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ደሙ በበር መቃን ላይ መቀባት ነበረበት። በዚህም የክርስቶስ ደም መልካም ተግባር ነፍስን የማንጻት ተግባር መፈጸም ነበረበት። ለዓለም መሞቱን ብቻ ማመን ሳይሆን ለእያንዳንዳችን በግላችን እንደሞተልን ማመን አለብን። የስርየት መስዋዕቱን መልካም ምግባር ጸጋ የራሳችን ማድረግ አለብን።”—Ellen የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 277.

እስከ ዛሬ ድረስ በመላው ዓለም የሚኖሩ ጥንቁቅ የአይሁድ ቤተሰቦች የፋሲካን በዓል ያከብራሉ። “የፋሲካ ዝግጅት” የሚሉት ነገር አላቸው (“ዝግጅት” ማለት “ቅደም ተከተል/ማደራጀት”) ማለት ነው። በዚህ ጊዜ ነጻ የመውጣትን ታሪክ ያወሩና እንደ ቤተሰብ የተለየ ምግብ ይመገባሉ። ይህ ከነጻ መውጣት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ መጠበቁ አስደናቂ ነው! ጥንቁቅ የሆኑ አይሁዶች የሚጠብቁት ሰባተኛ ቀን ሰንበት ብቻ ከዚህም አልፎ ወደ ኋላ ወደ ጥንት ዘመን ይሄዳል።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. አብዛኞቻችን በርግጠኝነት እግዚአብሔር “የዋህ” የሆኑትን አብዛኞቻችን በርግጠኝነት እግዚአብሔር “የዋህ” የሆኑትን የበኩር ልጆች በመምታቱ የእርሱን “ፍትሃዊነት/ቅንነት” እንዴት ማስተዋል እንችላለን”? ይህንን ከእግዚአብሔር ፍቅር ኃይለኛ እውነታ ጋር እንዴት ማጣጣም እንችላለን? ስለ ውኃ ጥፋትም አስቡ። ይህንንስ እንዴት እንረዳዋለን?

2. አማኞች በኢየሱስ ደም ተሸፍነዋል የሚለውና የእርሱ ደም አማኞች በኢየሱስ ደም ተሸፍነዋል የሚለውና የእርሱ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻቸዋል የሚለው ምሳሌያዊ አባባል ትርጉሙ ምንድር ነው?

3. የሚከተሉትን ቃላት ያንብቡ፡- “የክርስቶስ ተከታዮች የልምምዱ የሚከተሉትን ቃላት ያንብቡ፡- “የክርስቶስ ተከታዮች የልምምዱ ተካፋዮች መሆን አለባቸው። የሕይወትና የተግባር ማነሳሻ ኃይል እንዲሆን የእግዚአብሔርን ቃል መቀበልና በሕይወታቸው ማዋሃድ አለባቸው። በክርስቶስ ኃይል ወደ እርሱ አምሳያነት መለወጥ እና መለኮታዊ ባህርይን ማንጻባረቅ አለባቸው።…የክርስቶስ መንፈስና ሥራ የደቀ መዛሙርቱ መንፈስና ሥራ መሆን አለበት።”— Ellen G. White፣ Patriarchs and Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 278። በዚህ ቦታ የተጻፈውን ክርስቶስ በእኛ ውስጥ እንዲተገብር እንዴት እንፈቅድለታለን?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL