የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ: ዘጸ. 5:1–23፣ ራዕይ 11:8፣ ዘጸ. 6:1–13፣ መዝ. 73:23–26፣ 2ኛ ቆሮ 6:16፣ ዘጸ. 6:28–7:7።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን መጥተው
ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል፦ በምድረ በዳ በዓል ያደርግልኝ ዘንድ ሕዝቤን
ልቀቅ። ፈርዖንም፦ ቃሉን እሰማ ዘንድ እስራኤልንስ እለቅቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማን ነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፥ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም አለ” (ዘጸ. 5:1፣ 2)።
ብዙ አማኞች አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመከተል ሲወስን፣
እርሱ/ሷ የሚለማመደው/የምትለማመደው ደስታ፣ ብልጽግና
እና ስኬት ነው ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ብዙ ጊዜ መጽሐፍ
ቅዱስ ራሱ እንደሚያሳየው ሆኖ የሚታየው ይህ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ
በርካታ እንቅፋቶችና አዳዲስ ችግሮች ይከሰታሉ። ይህ እጅግ ተስፋ አስቆራጭ
ሊሆን ስለሚችል ሁልጊዜ ቀላል መልስ የሌላቸው ወይም በፍጹም መልስ
የማይገኝላቸው ከባድ ጥያቄዎች እንዲነሱ ያደርጋል።
በእግዚአብሔር የሚታመኑትን በርካታ ፈተናዎች ይገጥሟቸዋል። ነገር
ግን ስንታገስ፣ በእርሱ መንገድና ጊዜ የሚሆኑ መፍትሄዎችን እግዚአብሔር
ያመጣል። እኛ ፈጣንና ቅጽበታዊ መፍትሄዎችን ከምንጠብቀው ጋር የእርሱ
መንገድ ሊጋጭ ይችላል፣ ነገር ግን በእርሱ መታመንን መማር አለብን።
ስለዚህ የዚህ ሳምንት ርዕስ፡-ሙሴ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከግብጽ መርቶ
እንዲያወጣ የተሰጠ ትዕዛዝ--ማንም ሰው ሊሰጠው እንደሚችል ያለ ግልጽ ጥሪ
ነው። በርግጥ፣ ተአምራቶችን እና እግዚአብሔር ራሱ ለሙሴ በቀጥታ መናገርንና
ሙሴ በትክክል ምን እንዲያደርግ እንደሚፈልግበት ማሳወቅን አካትቷል።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ያኔ እግዚአብሔር እንደጠራው እና እንዲያውም የተለየ ሥራ
እንደሰጠው ማወቅ ለሙሴ ምን ያህል ቀላል ይሆንለት ነበር?
ያኔ ቀላል ሊሆን ይችል ነበር፣ ልክ ነው?
ማንበብዎን ይቀጥሉ።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሐምሌ 12 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
“ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ አውጣ” (ዘጸ. 3:10) የሚለውን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመከተል ሙሴ ሂደቱን ለመጀመር ወደ ፈርዖን ሄደ። “ሕዝቤን ልቀቅ” “ሕዝቤን ልቀቅ” (ዘጸ. 5:1፣2ን ይመልከቱ) ለሚለው የእግዚአብሔር ለሚለው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ የፈርዖን መልስ ምን ነበር? በዚህ ምላሽ ውስጥ ምን ወሳኝ ነገር ሊገኝበት ይችላል?
ፈርዖን “እግዚአብሔር ማን ነው?” አለ። ይህን ያለው እርሱን ለማወቅ
ከመፈለግ የተነሣ ሳይሆን በእርሱ ላይ የማመጽ፣ ወይም አለውቀውም ባለው
መሰረት እርሱን የመካድ ተግባር ነው። ኩራት እየተሰማው “እግዚአብሔርን
አላውቅም” አለ (ዘጸ. 5፡2) ።
በታሪክ ውስጥ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር የተናገሩት ምን ያህል ሰዎች
ናቸው? ኢየሱስ ራሱ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” (ዮሐንስ
17:3) ስላለ እግዚአብሔርን አናውቅም ማለታቸው እንዴት አሳዛኝ ነው።
ግብጽ ከንጉሷ ፈርዖን ጋር የእግዚአብሔርን መገኘትና ሥልጣን
የሚቃወም ኃይል ምልክት ነች። እግዚአብሔርን፣ ቃሉንና ሕዝቡን በመካድ
የሚቆም አካል ነው።
“እሥራኤልን አልለቅም” የሚለው ቀጣዩ የፈርዖን ንግግር በሕያው
እግዚአብሔር ላይ ያለውን አመጽ የበለጠውን አጉልቶ ያሳያል። ይህ ደግሞ
ግብጽ እግዚአብሔርን የመካድ ምልክት ብቻ ሳይሆን እርሱን የሚዋጋ ሥርዓት
ምልክትም ነች።
ብዙዎች ከብዙ ሺህ ዓመታት በኋላ በፈረንሳይ አብዮት ተመሳሳይ
አመለካከትን መመልከታቸው አያስደንቅም (ደግሞ ኢሳ 30:1–3 እና
ራዕይ 11:8ን ይመልከቱ)። ፈርዖን ራሱን አምላክ ወይም የአምላክ ልጅ
እንደሆነ አሰበ።: ይህ አንድ ሰው በራሱ ትልቅ ሥልጣን፣ ብርታትና እውቀት
የማመን ሰፊ ማሳያ ነው።
“በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ከቀረቡ አገሮች ሁሉ ግብጽ እጅግ
በድፍረት የሕያው እግዚአብሔርን መኖር በመካድ ትዕዛዛቱን ተቋቁማለች። ማንም
ንጉሥ እንደ ግብጽ ንጉሥ በእግዚአብሔር ላይ በግልጽና በበረታች እጅ ለማመጽ
አልደፈረም። መልእክቱ በእግዚአብሔር ስም በሙሴ አማካይነት በመጣለት ጊዜ፣
ፈርዖን በኩራት እንዲህ በማለት መለሰ፡- ‘ቃሉን እሰማ ዘንድ እስራኤልንስ
እለቅቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማን ነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፥ እስራኤልንም
ደግሞ አልለቅቅም’ ዘጸ. 5:2። ይህ ክህደት ሲሆን በግብጽ የተወከለ ሕዝብ
ለሕያው እግዚአብሔር ጥያቄ ተመሳሳይ የሆነ ክህደትን የሚያሰማ ድምጽ
በመስጠት ተመሳሳይ የሆነ የአለማመንና የአመጽ መንፈስን ይገልጣል።”—
Ellen G. White፣ The Great Controversy፣ p. 269.
የሆነ ሰው እግዚአብሔርን ታውቃለህን? ብሎ ቢጠይቅዎ መልስዎ ምን ይሆን?
መልስዎ አዎን ከሆነ፣ ስለ እርሱ ማንነት (እርሱ ምን እንደሚመስል) ምን
ብለው ይመልሳሉ? ለምን?
ሙሴ እንዲፈጽመው እግዚአብሔር የሰጠው ሥራ ቀላል እንደማይሆን ከመጀመሪያ ጀምሮ ቢያውቅም (ከዚያ ለማምለጥ የፈለገውም ከዚህ የተነሳ ነበር)፣ ምናልባት እየመጣ ስለነበረው ነገር የሚያውቀው ነገር አልነበረውም ይሆናል። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ዘጸ. 5:3–23ን ያንብቡ። ሙሴና አሮን ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈርዖን ጋር በተገናኙ ጊዜ ወዲያውኑ የታዩ ውጤቶች ምን ነበሩ?
ሙሴና አሮን ገና ወደ ፈርዖን ከመሄዳቸው በፊት የእሥራኤል
ሕዝብ ሽማግሌዎችን ሰብስበው የእግዚአብሔርን ቃል ነገሩአቸው፣
የእግዚአብሔርንም ምልክቶች አሳዩአቸው። እነዚህ ነገሮች እግዚአብሔር
ከባርነት እንደሚያወጣቸው እሥራኤላውያን እንዲያምኑ አደረጉአቸው። ከዚህ
የተነሣ ለእግዚአብሔር ሰገዱ (ዘጸ. 4:29–31)። ይጠብቁ የነበሩአቸው
ነገሮች በእርግጠኝነት ከፍ ያሉ ነበሩ፡- እግዚአብሔር በመጨረሻ የዕብራውያንን
ሕዝብ ከባርነት ሊያወጣቸው ነበር!
እግዚአብሔር በጠየቀው መሰረት ሙሴ ወደ ግብጽ ንጉሥ ሄደ፤ በዚህ
ምክንያት ሁኔታዎች ለእሥራኤላውያን የከፉ ሆኑ። መከራቸው ጨመረና
ዕለታዊ ሥራቸው ከመጀመሪያው የበለጠ ከባድና ልፋት የሚጠይቅ ሆነ። ሰነፍ
እንደሆኑ ተደርገው ተወነጀሉ፣ የበለጠውን ጭካኔ ተፈጸመባቸው፣ የሚሰጡት
አገልግሎት ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ በጣም ከባድ ሆነ።
መሪዎቻቸው ደስተኞች አልነበሩም፣ በእነርሱ መካከል እና
በሙሴና አሮን መካከል የነበረው ፍጥጫ የሚያስጠላ ነበር። ይህም (ኋላ
እንደምንመለከተው) በቀጣዮቹ አመታት ሙሴ ከራሱ ሕዝብ ጋር የሚኖረውን
ግጭት የሚያመለክት ነበር።
ዘጸ. 5:21ን ያንብቡና እነዚህ ሰዎች ሙሴንና አሮንን ሲጋፈጡአቸው በነበሩበት
ቦታ ራስዎን ያስቀምጡ። የተናገሩትን ነገር የተናገሩበት ምክንያት ምን ነበር?
ቦታ ራስዎን ያስቀምጡ። የተናገሩትን ነገር የተናገሩበት ምክንያት ምን ነበር?
በሙሴ ላይ የተናደዱበትን ምክንያት ማየት ከባድ አይደለም
(“እግዚአብሔር ይመልከታችሁ ይፍረድባችሁም” አሉአቸው)። ሙሴ
በግብጻውያን ሥር ሆነው ሕይወታቸውን ከበፊቱ የበለጠ ከባድ ለማድረግ
ሳይሆን ከግብጻውያን ነጻ ሊያወጣቸው እየመጣ ነው ብለው አስበው ነበር።
በዚህ ምክንያት ሙሴና አሮን ከግብጻውያን ሌላ ከራሳቸው ሕዝብ
ጋርም መነጋገር ነበረባቸው።
አለመግባባቶች መፈጠራቸው የማይቀር ነገር ስለሆነ እነዚህ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ
እርስዎና ሌሎች ሰዎች ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን አለመግባባቶችን
መፍታት የምትችሉባቸው አንዳንድ የተሻሉ መንገዶች ምንድር ናቸው?
ምስኪን ሙሴ! መጀመሪያ ፈርዖን አምባረቀበት፣ ቀጥሎ ደግሞ
የራሱ ሕዝብ በሙሉ ረገሙት።
በመሆኑም ሙሴ ብሶቱን ወደ እግዚአብሔር አመጣ። የእሥራኤላውያን
ሁኔታ ከመጀመሪያው የበለጠ በመክፋቱ በመማረርና ተስፋ በመቁረጥ እንዲህ
በማለት ጠየቀ፡- “ ጌታ ሆይ፥ ስለ ምን ይህን ሕዝብ አስከፋህ? ስለ ምንስ
ላክኸኝ? በስምህ እናገር ዘንድ ወደ ፈርዖን ከገባሁ ወዲህ፥ ይህን ሕዝብ
አስከፍቶታልና አንተም ሕዝብህን ከቶ አላዳንኸውም ” (ዘጸ. 5:22፣
23)። ሙሴ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በእግዚአብሔር ላይ
ያማረረበትን ምክንያት መረዳት አይከብድም።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ምላሽ ኃይለኛ ነበር። ወሳኝ የሆነ እርምጃ
ይወስዳል። “አሁን በፈርዖን የማደርገውን ታያለህ” አለው(ዘጸ. 6:1 )።
ዘጸ. 5:22–6:8ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ለሙሴ የመለሰለት መልስ ምንድር ነው? በዚህ ቦታ የተገለጡት ሥነ-መለኮታዊ እውነቶች ምንድር ናቸው?
ከአሁን በኋላ እግዚአብሔር ዝም ብሎ አይናገርም፤ ለሕዝቡ በብርቱ
ጣልቃ ይገባል። እየተነሳ ስላለው ጉዳይ ለሙሴ ጥቂት ጭብጦችን አስታወሰው፡
- (1) እኔ ጌታ ነኝ፤ (2) ለአባቶች ተገለጥሁ፤ (3) ቃል ኪዳኔን ከእነርሱ
ጋር መሰረትሁ፤ (4) የከንዓንን ምድር ልሰጣቸው ቃል ገበሁላቸው፤ (5)
የእሥራኤልን ልጆች ጩኸት ሰማሁ፤ እና (6) የተስፋይቱን ምድር ልሰጣችሁ
የገበሁላችሁን ቃል ኪዳን አስታወስሁ።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመለኮታዊ “እኔ”ን ድግግሞሾች ልብ ይበሉ። እኔ፣ አምላካችሁ
እግዚአብሔር፣ እኔ ይህንና ያንን አድርጌያለሁ፣ ስለዚህ እኔ ላደርግላችሁ ቃል
የገበሁላችሁን ነገር እንደማደርግላችሁ መታመን ትችላላችሁ።
እግዚአብሔር ሕያው አምላካቸው ስለሆነ ለእሥራኤላውያን አራት
ታላላቅ ነገሮችን እንደሚያደርግላቸው አሁን አወጀ፡- (1) “ከግብጻውያን
ቀንበር ነጻ አወጣችኋለሁ፤” (2) “ከባርነት ነጻ አወጣችኋላሁ፤” (3)
“በተዘረጋ ክንድና በታላቅ ፍርድ እታደጋችኋለሁ፤” እና (4) “የራሴ ሕዝብ
አድርጌ እወስዳችኋለሁ፣ አምላካችሁም እሆናለሁ” (ዘጸ. 6:6፣ 7)።
እነዚህ አራት መለኮታዊ እርምጃዎች ከሕዝቡ ጋር ያለውን ግንኙነት
ይመሰርቱና ይጠብቃሉ። የእነዚህ ተግባራት ሁሉ ርዕስ እግዚአብሔር
ሲሆን እሥራኤላውያን ደግሞ የእነዚህ የጸጋ ጥቅሞች ሁሉ ተቀባይ ናቸው።
እግዚአብሔር እነዚህን ስጦታዎች የሚሰጠው በነጻ እና ከፍቅር የተነሳ ነው።
ያኔ ለእነርሱ እንዳደረገው ሁሉ ዛሬም ለእኛ ያደርግልናል።
በቂ ምክንያት ኖሯቸው በእግዚአብሔር ፊት ብሶታቸውን በመግለጽ የጮኹት
የትኞቹ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ ባህሪያት ናቸው? አንዳንድ ጊዜ ነፍስዎን
በእግዚአብሔር ፊት ማፍሰስና ስላሉበት ሁኔታም ብሶትዎን መግለጽ ትክክል
የሚሆነው ለምንድር ነው? ቢሆንም ሁልጊዜ በእምነትና በመታመን ማድረግ
ያለብዎትስ ለምንድር ነው?
እግዚአብሔር ሊያደርግ ስላለው ነገር ለሙሴ አንዳንድ ኃይለኛ የሆኑ ተስፋዎችን ሰጥቶታል። ምንም እንኳን ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገው ግንኙነት ቢያደፋፍረውም፣ ከሕዝቡ ከተቀበለው መልስ የተነሣ ማደፋፈሪያው ለአጭር ጊዜ ብቻ የቆየ ነበር። ዘጸ. 6:9–13ን ያንብቡ። ቀጥሎ ምን ሆነ? በሕይወታችን ስለሚገጥሙን የተስፋ መቁረጥና ችግር ጊዜያቶች ከዚህ ታሪክ ምን ትምህርት መውሰድ እንችላለን?
ዕብራውያን ከደረሰባቸው ሀዘን፣ መከራና ከባድ ሥራ የተነሣ ልባቸው
በመዛሉ እግዚአብሔር የገባውን ቃል ለመፈጸም እንደሚሰራ ሙሴ የሰጣቸውን
ማረጋገጫ አልሰሙም። የዚህን ተስፋ ተፈጻሚነት ለብዙ ጊዜ ቢጠብቁም
ይሆናል ብለው የጠበቁት ነገር አልተፈጸመም። አሁን የተለየ መሆን ያለበት
ለምንድር ነው? ምናልባት በሕይወታቸው ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ፣ እርግጠኛ
የሆነ ነጻ የመውጣት ተስፋ ስለተመለከቱና ይህ በአብዛኛው እጅግ መራር
ስለነበር፣ ድፍረትና ተስፋ እያጡ ነው።
በተመሳሳይ ቦታ ሆኖ የማያውቅ ማን ነው? በሆነ ነጥብ ላይ ድባቴ፣
ተስፋ መቁረጥ፣ ዕርካታ ማጣት--እንዲያውም እግዚአብሔር እንደተወዉ
ያልተሰማው ማን አለ?
የኢዮብን ታሪክ ያስታውሳሉ? የኃጢአተኞችን ብልጽግናና የጻድቃንን መከራ
በተመለከተ ከነበሩት ጥያቄዎች ጋር ትግል ያደረገውን ባለመዝሙሩን አሳፍንስ
ያስታውሳሉ? ሆኖም፣ ከትግሉ ባሻገር አሳፍ እጅግ ካማሩ የእምነት ኑዛዜዎች አንዱ
የሆነ ኑዛዜ አለው፡- “እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።
በአንተ ምክር መራኸኝ፤ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ። በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው?
በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ? የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ
አለቀ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው” (መዝ. 73:23–26)።
በቅዱስ ታሪክ መካከል እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደሆነ ለሕዝቡ
ማረጋገጫ ሰጥቷቸዋል (ኢሳ 41:13፣ ማቴ. 28:20)። በሕይወት
ግድድሮሾች መካከል ማለፍ እንዲችሉ ሰላሙን፣ መጽናናቱን እና ብርታቱን
ይሰጣቸዋል (ዮሐንስ 14:27፤ ዮሐንስ 16:33፤ ፊልጽ. 4:6፣ 7)።
“ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ”
(ዘጸ. 6:7) የሚለው የቃል ኪዳኑ ቀመር (ፎርሙላ) እግዚአብሔር
ከሕዝቡ ጋር መፍጠር የሚፈልገውን የቀረበ ግንኙነት ይገልጻል።
“ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ”
(ዘጸ. 6:7) የሚለውን ሀረግ ያስታውሱ። ምንም እንኳን አውዱ የወል
ቢሆንም፣ ይህ እያንዳንዳችንን በግል የሚመለከተው እንዴት ነው? ይህ
ግንኙነት በዕለታዊ ሕይወታችን መገለጥ ያለበት እንዴት ነው? (ደግሞ 2ኛ
ቆሮ 6:16ን ይመልከቱ።)
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ዘጸ. 6:28–7:7ን ያንብቡ። እግዚአብሔር የሙሴን ተቃውሞ (ጥሪውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆን) የያዘው እንዴት ነበር?
እግዚአብሔር ራሱን ለሙሴ ያቀረበው እንደ ያህዌህ ነበር፤ ይህ ማለት
እርሱ ግላዊና ቅርብ የሆነ አምላክ፣ ከእነርሱ ጋር የቃል ኪዳን ግንኙነት የፈጠረ
አምላክ ማለት ነው።
ይህ ቅርብ የሆነ አምላክ ሙሴ ሄዶ ለፈርዖን እንዲናገር በድጋሚ
ያዘዋል። ሙሴ በራስ መተማመን ስላልነበረው አሁንም ፈቃደኛ አለመሆኑን
ገለጸ፡- “ፈርዖን ለምን እኔን ይሰማኛል?” በዚህ ቦታ በድጋሚ የሙሴን
ትህትና (ራሱን ዝቅ ማድረጉን) የምንመለከት ብቻ ሳይሆን፣ እስካሁን በጥሩ
ሁኔታ እየሄደ ካልሆነው ንግግር ራሱን የማውጣት ፍላጎትን እንመለከታለን።
“ሙሴ ወደ ፈርዖን ተመልሶ እንዲሄድ እግዚአብሔር ባዘዘው ጊዜ
ሙሴ በራሱ እምነት እንደሌለው ገለጸ። ‘ኣራል ሴፓታይም (aral
sepatayim)—የሚለው ሀረግ ቃል በቃል ሲተረጎም ‘ያልተገረዙ ከንፈሮች’
የሚል ሲሆን በዚህ ቦታ ሙሴ የመናገር ችሎታ እንደሌለው ለመግለጽ ጥቅም ላይ
የዋለ ሲሆን (6:12፣ 30) በዘጸ. 4፡10 ላይ ከሚገኘው ‘አፈ ኮልታፋ’”
ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው።—Andrews Bible Commentary:
Old Testament, “Genesis” (Berrien Springs,
MI: Andrews Uersity Press, 2020), p. 205.
እግዚአብሔር በምህረቱ ሙሴን እንዲረዳ አሮንን ሰጠ። ሙሴ ለአሮን
ይናገራል፣ አሮን ደግሞ በሕዝብ ፊት ለፈርዖን ይናገራል። ስለዚህ ሙሴ በግብጽ
ንጉሥ ፊት የእግዚአብሔርን ሚና የሚጫወት ሲሆን አሮን የእርሱ ነቢይ ይሆናል።
ይህ ዘገባ የነቢይ ሚና ምን እንደሆነ እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ ትርጉም
ይሰጣል። ነቢይ እግዚአብሔር የነገረውን ነገር የሚናገር ነው፤ እርሱ ወይም
እርሷ የእግዚአብሔርን ቃል ለሕዝቡ የሚያስተላልፍ/ የምታስተላልፍ እና
የሚተረጉም/የምትተረጉም አፈ-እግዚአብሔር ነው/ነች። ሙሴ ለአሮን
እንደተናገረ እና ከዚያም አሮን ለፈርዖን እንዳሳወቀ፣ እግዚአብሔርም ለነቢይ
ይናገርና ነቢዩ እግዚአብሔር ያስተማረውን ነገር ለሕዝቡ ያውጃል። ይህ
ሊሆን የሚችለው በመናገር፣ በአካል በመገኘት፣ ወይም እጅግ በተለምዶ
እንደሚደረገው ነቢዩ መልእክቱን ከእግዚአብሔር ተቀብሎ በመጻፍ ነው።
ሙሴ ከፈርዖን ጋር ሲገናኝ ምን መጠበቅ እንደሚችል እግዚአብሔር
አብራራለት። የፊት ለፊት ፍጥጫው የከረረ እና ረዥም እንደሚሆን
አስጠነቀቀው። ፈርዖን እንደሚተብትና ልቡን እንደሚያደነድን በድጋሚ አጽንዖት
ሰጥቶ ነገረው (ዘጸ. 4:21፣ ዘጸ. 7:3)። ነገር ግን “እኔ እግዚአብሔር
እንደ ሆንሁ ስለሚያውቁ” (ዘጸ. 7:5) ፍጻሜው ጥሩ ይሆናል። ይህ ማለት፣
ተከትሎ በሚመጣው ውዝግብ ውስጥም ቢሆን፣ እግዚአብሔር ይከበራል።
ሙሴ እግዚአብሔር እንዲፈጽመው የጠራውን ነገር ላለማድረግ የሚያቀርባቸው
ሰበቦች አለቁበት። እኛ እንድንሰራው እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር
እያወቅን ከዚያ ሀላፊነት ለማምለጥ ምን ሰበቦችን እንጠቀም ይሆን?
ኢ. ጂ. ኋይት ከጻፈችው አባቶችና ነቢያት
ከሚለው መጽሐፍ “የግብጽ መቅሰፍቶች” የሚለውን ርዕስ ከገጽ 257–
265 ላይ ከእንግሊዝኛው መጽሐፍ ላይ ያንብቡ።
ሙሴ መጀመሪያ ወደ ፈርዖን ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ ለሙሴም ሆነ
ለሕዝቡ ነገሮች እንዴት በመጥፎ ሁኔታ እንደጀመሩ ይመልከቱ።
“ንጉሡ ሕዝቡ አገልግሎት ላለመስጠት አመጽ ሊያስነሱ ነው ብሎ
ስለተጠራጠረ በጣም ተናደደ። አለመርካት ሥራ የመፍታት ውጤት ነው፤
ስለዚህ አደገኛ የሆነ ነገር ለማቀድ ያላቸው ጊዜ እጅግ ጥቂት መሆኑን ተመለከተ።
ወዲያውኑ ገመዳቸውን ለማጥበቅና የነጻነት መንፈሳቸውን ለመጨፍለቅ
እርምጃዎችን ወሰደ። በዚያው ቀን ሥራቸው የበለጠውን ጭካኔ የተሞላበትና
ጭቆና ያለበት እንዲሆን ትዕዛዝ ተሰጠ። የአገሩ እጅግ የተለመደው የግንባታ
መሣሪያ በጸሐይ የደረቀ ጡብ ስለነበር እጅግ ውብ የሆኑ ሕንጻዎች ግድግዳቸው
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
በዚህ ጡብ ተሰርቶ በድንጋይ ይታጠር ነበር። ከዚህ የተነሣ በጡብ ማምረት ሥራ
ብዙ ባሪያዎች ተቀጥረው ነበር። ጡቡን ለማያያዝ የተቆራረጠ ገለባን ከጭቃው
ጋር መቀላቀል ስለሚያስፈልግ ለሥራው ብዙ ገለባ ያስፈልግ ነበር። ንጉሡ ምንም
ገለባ እንዳይቀርብላቸው አዘዘ። ሰራተኞቹ ራሳቸው ገለባን ፈልገው በማምጣት
ከዚህ በፊት ያመርቱ የነበሩትን ያህል ጡብ እንዲያመርቱ ታዘዙ።
“ትዕዛዙ በአገሪቱ ባሉ እሥራኤላውያን ላይ ታላቅ ጭንቀት አመጣ።
የግብጽ አስገባሪዎች (ሹማምንት) የሕዝቡን ሥራ የሚከታተሉ ዕብራውያን
አለቆችን ሹመው ስለነበር እነዚህ አለቆች ከሥራቸው ያሉ ሰራተኞች
ለሚያከናውኑት ሥራ ኃላፊነት ነበረባቸው። የንጉሡ ጥያቄ ተፈጻሚ እንዲሆን
ሲታዘዝ ሕዝቡ በገለባ ፋንታ ዕብቅ ለመሰብሰብ በምድሪቱ ሁሉ ተበተኑ፣ ነገር
ግን ከዚህ በፊት የሚያመርቱትን ያህል ጡብ ማምረት አልቻሉም። ይህ ባለመሆኑ
በዕብራውያን ላይ የተሾሙ አለቆች በጭካኔ ተገረፉ (ተደበደቡ)።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 258.
1. በሕይወትዎ የእግዚአብሔርን ጥሪ ሲሰሙ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ
በሕይወትዎ የእግዚአብሔርን ጥሪ ሲሰሙ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ
ያልሄዱበትን ወይም በጥሩ ሁኔታ ያልጀመሩበትን ጊዜ ያስቡ።
በጊዜ ሂደት ከእነዚህ ልምምዶች ምን ትምህርት ተማሩ?
2. እግዚአብሔር እንዲረደዎት በጸለዩ ጊዜ ወይም ይሆናል ብለው
እግዚአብሔር እንዲረደዎት በጸለዩ ጊዜ ወይም ይሆናል ብለው
ባልጠበቁት ሰዓት እግዚአብሔር በሕይወትዎ እንዴት ጣልቃ
እንደገባ ለሌሎች ይናገሩ። በእግዚአብሔር በሚታመኑት ላይ
እንኳን ክፉ ነገሮች ሲሆኑ እንዴት የእግዚአብሔርን መልካምነት
ማመን እንችላለን?
3. እርስዎ “እግዚአብሔርን አላውቅም” ለሚል ሰው ምን ይላሉ?
እርስዎ “እግዚአብሔርን አላውቅም” ለሚል ሰው ምን ይላሉ?
እንበልና፣ ግለሰቡ በትዕቢት ተነሳስቶ ሳይሆን ስለ ራሱ ሕይወት
ባለው ቀላል እውነታ (ጭብጥ) ላይ ተመስርቶ ቢልስ? ያ
ሰው “እግዚአብሔርን እንዲያውቅ” ለመርዳትና ማወቁ ለምን
አስፈላጊ እንደሆነ ለግለሰቡ ለማስረዳት ምን ማድረግ ይችላሉ?