የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉጥን ጥቅሶች ያንብቡ:- ዘጸ. 18:3፣ 4፤
ዘጸ. 3:1–22፤ ዘፍ. 22:11፣ 15–18፤ ዘጸ. 6:3፤ ኢዮኤል 2:32፤
ዘጸ. 4:1–31፤ ዘፍ. 17:10፣ 11።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እግዚአብሔርም አለ፦ በግብፅ ያለውን
የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ
ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ፤ ከግብፃውያንም
እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው
አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም
ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም
ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ
ወረድሁ” (ዘጸ. 3:7፣ 8)።
እግዚአብሔር ለእኛ የሚያደርግልን ጥሪ ብዙ ጊዜ የሕይወታችንን
አቅጣጫ ይለውጣል። ነገር ግን ያንን ጥሪ ከተከተልን የእግዚአብሔር
መንገድ ለእኛ ሁልጊዜም የተሻለ መንገድ መሆኑን እንረዳለን። ነገር ግን
አንዳንድ ጊዜ፣ በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ጥሪ መቀበል ቀላል አይደለም።
ሙሴ በሚነድደው ቁጥቋጦ እግዚአብሔርን በተገናኘ ጊዜ እርሱንና
ከእግዚአብሔር የቀረበለትን ጥሪ በተመለከተ የነበረው ሁኔታ የዚህ ዓይነት
ነበር። ሙሴ ስለ መቃጠል ሕጎች ቢያውቅም ባያውቅም፣ እየተመለከተ ያለው
ነገር ተዓምር መሆኑን ስላወቀ ትኩረቱን ሳበው። እግዚአብሔር ለተለየ ሥራ
እየጠራው ስለመሆኑ ምንም የሚያጠያይቅ ነገር አልነበረም። ጉዳዩ ይህ ጥሪ
በሕይወቱ የሚያመጣው መሰረታዊ ለውጥ ምንም ቢሆን ለጥሪው መልስ ይሰጥ
ይሆን? የሚለው ነው። በመጀመሪያ፣ ጥሪውን ለመቀበል ፈቃደኛ አልነበረም።
እርስዎ የራስዎ የተለዩ ግቦች ቢኖርዎትም እግዚአብሔር እነዚያን
እቅዶች አቅጣጫ ያስቀየረባቸውን አጋጣሚዎች ሊያስታውሱ ይችላሉ።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ለእግዚአብሔር በብዙ መንገዶች ጠቃሚ መሆን መቻላችን እውነት ነው፣ ነገር
ግን በሕይወታችን የእርሱን ጥሪ መከተልና እርሱ እንድናደርግ የሚመራንን
ነገር ማድረግ በርግጠኝነት እጅግ የሚያረካ ሕይወት ወደመኖር የሚመራ
መንገድ ነው። ሁልጊዜ ቀላል ላይሆን ይችላል፣ ለሙሴም ቀላል አልነበረም፣
ነገር ግን እግዚአብሔር በሌላ አቅጣጫ እየጠራን ሳለ በራሳችን መንገድ መሄድ
እንዴት ያለ ሞኝነት ነው!
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሐምሌ 5 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
ሙሴ ወደ ምድያን ከሸሸ በኋላ በንጽጽር ቀለል ያለ ሕይወት ነበረው።
አግብቶ ሁለት ልጆችን፣ ጌርሳምንና አልዓዛርን፣ አፍርቶ ነበር (ዘጸ. 18:3፣
4)። የሚድያን ካህን የነበረው የአማቱ የዮቶር ቤተሰብ አባል ሆኖ ይኖር ነበር።
እንደ ዳዊት በእረኝነት (2ኛ ሳሙ. 7:8) 40 ዘና ያሉ ዓመታትን፣ በተለይ
በተፈጥሮ ውስጥ በተገለጠው የእግዚአብሔር መገኘት እየተደሰተ አሳለፈ።
ሆኖም፣ ይህ ጊዜ ሙሴ ዝም ብሎ አበቦችን የሚያሸትበት ጊዜ
አልነበረም (ወይም ምናልባት፣ በዚህ አጋጣሚ፣ የበረሃ ቁልቋልን ሽታ?)።
እነዚህ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ የመጓዝ አመታት ለውጠውት ለአመራር
ሚና አዘጋጅተውታል። በዚህ ጸጥ ባለ ምድረ በዳ፣ በመለኮታዊ ምሪት፣
ሙሴ ጥንታዊ የሆኑ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሆኑትን፣ ኢዮብንና
ዘፍጥረትን፣ እንዲጽፍ እግዚአብሔር ተጠቅሞበታል (see Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 251፤
Francis D. Nichol፣ et al.፣ eds.፣ The SDA
Bible Commentary፣ vol. 3፣ p. 1140)። እግዚአብሔር
ለሙሴ ስለ ታላቁ ተጋድሎ፣ ስለ ፍጥረት፣ ስለ ውድቀት፣ ስለ ውኃ ጥፋት፣ ስለ
አባቶች እና ከሁሉም የበለጠ ስለ ድነት ዕቅድ ወሳኝ የሆነ መረዳት ሰጥቶት
ነበር። ስለዚህ ሙሴ ፈጣሪያችንና ደጋፊያችን ስለሆነው ሕያው እግዚአብሔር፣
እና በዚህች ምድር ላይ ሽብር የፈጠረውን ኃጢአት በተመለከተ እግዚአብሔር
ምን እያደረገ እንደሆነ ለሰብአዊ ዘር ሁሉ እውነተኛ እውቀት ለማስተላለፍ
በመሣሪያነት አገልግሏል። የመጽሐፍ ቅዱስ እና የድነት ታሪክ፣ ሙሴ በመንፈስ
ቅዱስ ምሪት፣ በተለይም በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ከሰጠን ወሳኝ መሰረት
ተነጥሎ ብዙም ስሜት አይሰጥም።
ዘጸ. 3:1–6ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ራሱን ለሙሴ “የአብርሃም አምላክ፣
የይስሃቅ አምላክ እና የያዕቆብ አምላክ” እንደሆነ ከማስተዋወቁ ምን ጥቅም
ሊገኝበት ይችላል?
ሙሴ የሚነድደው ቁጥቋጦ እየተቃጠለ አለመሆኑን ተመለከተ። ከዚህ
የተነሣ ተዓምር እየተፈጸመ መሆኑን እና የሆነ ትዕይንታዊና ወሳኝ ነገር በፊቱ
እየተከሰለተ መሆኑን አወቀ። እየቀረበ ሲሄድ የእግዚአብሔር መገኘት ቦታውን
ስለቀደሰው፣ ጥልቅ የሆነ የአክብሮት ምልክት እንዲሆን ከእግሩ ጫማውን
እንዲያወልቅ እግዚአብሔር ነገረው።
እግዚአብሔር ራሱን ለሙሴ ያቀረበው እንደ “የአብርሃም አምላክ፣
የይስሃቅ አምላክ እና የያዕቆብ አምላክ” አድርጎ ነበር (ዘጸ. 3:6)።
እግዚአብሔር ለእነዚህ አባቶች ዝርያዎቻቸው ከነዓንን እንደሚወርሱ ቃል
ገባላቸው። ሙሴም ስለዚህ ተስፋ በእርግጠኝነት ያውቅ ነበር። ስለዚህ፣
ገና ከመናገሩ በፊት፣ እየመጣ ስላለው ነገር እና ምን ዓይነት ወሳኝ ሚና
እንደሚጫወት እንዲያውቅ እግዚአብሔር መንገድ እየከፈተለት ነበር።
እግዚአብሔር ለሥራው ገጣሚ እስኪያደርገው ድረስ ሙሴ 80 ዓመታት
አስፈልገውት ነበረ። ይህ እውነት ስለ ትዕግስት ምን ሊያስተምረን ይችላል?
“የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ነበልባል በእሳት ቁጥቋጦ መካከል”
ለሙሴ ታየው(ዘጸ. 3:2 )። “ከሚነድደው ቁጥቋጦ መካከል” ለሙሴ
በቀጥታ ይናገር የነበረው እግዚአብሔር ራሱ ነበር (ዘጸ. 3:4)።
“የጌታ መልአክ” የሚለው ማዕረግ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያመለክት
አድርገው ግራ አይጋቡ። “የጌታ መልአክ” የሚለው ቃል ትርጉሙ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
“መልእክተኛ” (በዕብራይስጥ መልአክ) ማለት ነው። ይህ መልአክ ሰብአዊ
ወይም መለኮታዊ ተብሎ የመተርጎሙ ጉዳይ የሚደገፈው በአውዱ ላይ ነው
(ሚልክያስ 3፡1ን ይመልከቱ)። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የጌታ መልአክ”
መለኮታዊ ግለሰብን ያመለከተባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ (ለምሳሌ፡- ዘፍ.
22:11፣ 15–18፤ ዘፍ. 31:3፣ 11፣ 13፤ መሳ. 2:1፣ 2፤ መሳ.
6:11–22፤ ዘካ. 3:1፣ 2ን ያጥኑ)። ይህ የእግዚአብሔር መልአክ
በእግዚአብሔር ስም ብቻ የሚናገር ሳይሆን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነበር።
ኢየሱስ የአባቱን ቃል ለእኛ ለማስተላለፍ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነው።
ዘጸ. 3:7–12ን ያንብቡ። እግዚአብሔር በግብጽ ምድር ባሪያዎች ለተደረጉ
እሥራኤላውያን ለምን ጣልቃ መግባት እንደፈለገ ለሙሴ ያብራራው እንዴት ነበር?
የእግዚአብሔር ሕዝብ በግብጽ ምድር የደረሰባቸው ሥቃይ ለእርዳታ
መቃተትንና ጥልቅ ጩኸትን በሚገልጽ ደማቅ ቀለም ተገልጾአል። እግዚአብሔር
ጩኸታቸውን ሰማና ሥቃያቸው አሳሰበው (ዘጸ. 2:23–25). “ሕዝቤ” ብሎ
ጠራቸው(ዘጸ. 3:7)። ይህ ማለት፣ ከሲና በፊት እና ቃል ኪዳን ከመፈጸማቸው
በፊት፣ እነርሱ ሕዝቡ ስለነበሩ ለአባቶቻቸው ቃል በገባላቸው በከነዓን ምድር
እንዲኖሩና እንዲከናወንላቸው (እርሱን ከታዘዙት) ያደርጋል ማለት ነው።
እግዚአብሔር የተለየ ሥራ እንዲሰራ ወደ ፈርዖን እየላከው እንደሆነ
ለሙሴ ነገረው፡- “አሁንም ና፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ታወጣ
ዘንድ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ” (ዘጸ. 3:10)። በድጋሚ እግዚአብሔር
“ሕዝቤ” ብሎ ይጠራቸዋል።
እግዚአብሔር ለባሪያው ያቀረበለት እንዴት ያለ ሥራ ነው! ስለዚህ
ሙሴ እንዲህ በማለት በጥያቄ መልስ ሰጠ፡- “እኔ ማን ነኝ?” ይህ ማለት፣
ሊሆን ያለውን ነገር ወሳኝነት በመገንዘብ እና በዚህ ሁሉ ውስጥ የእርሱ
ሚና ምን ሊሆን እንደሚችል ከመረዳቱ የተነሣ እንደ እርሱ ያለ ሰው ለምን
ለዚህ ሥራ እንደተመረጠ ግራ ገባው። በዚህ ቦታ፣ ገና ከጅምሩ፣ የባህሪዩ፣
የትህትናው እና እንዲፈጽመው እየተጠራ ስላለው ነገር እርሱ ብቁ ((ተገቢ)
ያለመሆን ስሜት እንደነበረው የሚያመለክቱ ነገሮችን እናያለን።
ትህትና እና የራሳችን “ብቁ ያለመሆን” ስሜት እግዚአብሔርን ለመከተልና ለእርሱ
የሆነ ነገር ለማድረግ ለሚሻ ለማንኛውም ሰው አስፈላጊ የሚሆኑት ለምንድር ነው?
ዘጸ. 3:13–22ን ያንብቡ። ሙሴ የእግዚአብሔርን ስም ማወቅ የፈለገው ለምን ነበር? እናም ስሙ ምን ወሳኝነት አለው?
እግዚአብሔር ራሱን ለሙሴ ያቀረበው እንደ “’ኤሄጄህ አሽር ’ኤሄጄህ”
ሲሆን ይህ ቃል በቃል ሲተረጎም “እኔ ነኝ የምሆን ፣” ወይም “እኔ እኔ ነኝ”
የሚል ነው። እግዚአብሔር ዘጸ. 3:12 ላይ ለሙሴ “እሆናለሁ” (ከአንተ
ጋር) ባለ ጊዜ በቁጥር 14 ላይ ከተጠቀመው ጋር ተመሳሳይ የሆነውን ኤሄጄ
የሚለውን ግሥ ይጠቀማል። ይህ ማለት እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው ማለት ነው።
እግዚአብሔር ወሰን የለሽም ሊደረስ የሚችልም አምላክ ነው። “የተቀጠቀጠና
የተዋረደ መንፈስ” ባላቸው ውስጥ ይኖራል (ኢሳ 57:15)።
የእግዚአብሔር የተጸውኦ ስም “ያህዌህ” (በእንግሊዝኛ መጻሕፍት
“ጌታ” ተብሎ የተተረጎመው) ቃል የእግዚአብሔር ሕዝብ ጥልቅ ትርጉሙን
ባያውቁም እንኳን ከመጀመሪያው ጀምረው ያውቁት ነበር። ሙሴም ያህዌህ
የሚለውን ስም ያውቅ ነበር፣ ነገር ግን እንደ ሌሎቹ ሁሉ ትክክለኛውን ትርጉም
አያውቅም ነበር። “ስምህ ማን ነው?” የሚለው ጥያቄው የጠለቀውን
ትርጉም ለማወቅ የመፈለግ ጥያቄ ነው።
ለዚህ ጠቃሚ የሆነ ፍንጭ ዘጸአት 6:3 ላይ እግዚአብሔር
“ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤
ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር” (ዘጸ. 6:3) ባለው
ውስጥ ይገኛል። አዳም፣ ኖህ፣ አብርሃም፣ እና አባቶች “ያህዌህ” የሚለውን
ስም አለማወቃቸውን አያመለክትም( ዘፍ. 2:4፣ 9፤ ዘፍ. 4:1፣ 26፤
ዘፍ. 7:5፤ ዘፍ. 15:6–8፤ ወዘተ… ይመልከቱ.)። ይልቁን ጥልቅ
የሆነውን ትርጉሙን አላወቁም ማለት ነው።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ያህዌህ የሚለው ስሙ አካላዊ አምላክ፣ የሕዝቡ አምላክ እና የቃል
ኪዳን አምላክ መሆኑን ይጠቁማል። በሰብአዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ የሚገባ
የቅርብና ወዳጅነት የሚፈጥር አምላክ ነው። ኤልሻዳይ (ኃያል) አምላክ (ዘፍ.
17:1) በኃይሉ ተዓምራዊ በሆነ ሁኔታ ጣልቃ የገባ አምላክ ነው። ነገር ግን
ያህዌህ የግብረገብ ኃይሉን በፍቅርና በመጠንቀቅ የሚያሳይ አምላክ ነው። እንደ
ኤሎህም (“ብርቱ፣ ጠንካራ፣ እና ወሰን የለሽ አምላክ፣” “የሁሉም ሕዝብ
አምላክ፣” “የዩኒቨርስ ገዥ፣” “የሁሉም ነገር ፈጣሪ”) ያለ ያው አምላክ
ነው። እንደ ኤሎህም ያለ የሆነ አምላክ ነው፣ ነገር ግን ከሰብአዊነት ጋር ያለው
ግንኙነት የተለያዩ ገጽታዎች ያህዌህ በሚለው ስም ተገልጠዋል።
ስሙን ማወቅ ወይም የእግዚአብሔርን ስም መጥራት የሆነ አስማታዊ
ነገር አይደለም። ጉዳዩ ስሙን የማወጅ ጉዳይ ሲሆን ይህን አምላክና ወደ እርሱ
በእምነት ለሚመጡት ስለሚሰጠው ድነት ሌሎችን ማስተማር ማለት ነው።
ኢዮኤል እንዳለው፡- “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል” (ኢዮኤል 2:32)።
ያህዌህ ራሳቸውን ለእርሱ አሳልፈው ከሰጡት ሁሉ ጋር ሊፈጥር የሚፈልገውን
ዓይነት ቅርበትና ወዳጅነት በራስዎ ሕይወት የተለማመዱት በምን መንገዶች ነው?
ዘጸ. 4:1–17ን ያንብቡ። እንደ እግዚአብሔር መልእክተኛ፣ ሙሴ ያለውን አቋም ለማጽናት እግዚአብሔር የሰጠው ምን ያህል ተአምራቶችን እንዲፈጽም ነበር?
ሙሴ እግዚአብሔር እንዲፈጽም ከጠየቀው ተግባር ለማምለጥ በድጋሚ
ሰበብ ለመስጠት ሞከረ (ዘጸ. 3:11ን ይመልከቱ)። ወደ ግብጽ ሄዶ ፈርዖንን
ለመጋፈጥ አልፈለገም። አስቀድሞ በራሱ ተነሳሽነት ዕብራውያንን ለመርዳት
ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም። የራሱ ሕዝብም አላመኑበትም ወይም እንደ
መሪ አልተቀበሉትም ነበር። “ ‘ቃሌን ባይሰሙና ባያምኑኝስ?” (ዘጸ. 4:1)
የሚለውን ሶስተኛውን ያለመቀበል ሀሳብ ያቀረበው ከዚህ የተነሣ ነበር። ይህ
ጥያቄ የሆነ አዲስ ነገር ለመማር የቀረበ ጥያቄ ሳይሆን እግዚአብሔር እንዲፈጽም
እየጠየቀ ላለው ኃላፊነት እምቢተኛነቱን የመግለጽ ጥረት ነው።
ሙሴ በእሥራኤል ሽማግሌዎች ፊት እና ኋላም በፈርዖን ፊት እንዲፈጽም
ሁለት ተዓምራዊ ምልክቶች ተሰጥተውት ነበር፡- (1) በትሩ ወደ እባብ
እንዲለወጥና ተመልሶ በትር እንዲሆን እና (2) እጁ ለምጻም እንዲሆንና በቅጽበት
ደግሞ እንዲፈወስ። ሁለቱም ተዓምራቶች እግዚአብሔር ለእነርሱ እየሰራ እንደሆነ
ሽማግሌዎቹን ማሳመን ነበረባቸው። ነገር ግን እነዚህ ተዓምራቶች ካላሰመኑአቸው
ውኃን ወደ ደም መለወጥ መታከል ነበረበት (ዘጸ. 4:8፣ 9)።
እግዚአብሔር እነዚህን ኃይለኛ የሆኑ ተዓምራቶችን ለሙሴ ቢሰጥም፣
አሁንም ለአራተኛ ጊዜ፣ ጥሩ ተናጋሪ አይደለሁም በማለት ሰበብ ሰጠ።
ዘጸ. 4:10–18ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ለሙሴ መልስ የሰጠው እንዴት ነበር? እግዚአብሔር ይጠራናል ብለን በምናምንበት በማንኛውም ሁኔታ
ውስጥ ከዚህ ለራሳችን ምን ትምህርት እናገኛለን?
የእነዚህ አራት ሰበቦች ስብስብ ሙሴ የእግዚአብሔርን ጥሪ ለመከተል
ያሳየውን ዳተኝነት ያሳያል። “ምክንያታዊ” በሆኑ እምቢታዎች፣ ለመሄድ
ፈቃደኛ አለመሆኑን ሸፈነ። የመጀመሪያዎቹ ሶስት ሰበቦች የቀረቡት በጥያቄ
መልክ ነበር፡- (1) እኔ ማን ነኝ? (2) አንተ ማን ነህ? እና (3)
ባያምኑኝስ? የሚሉ ናቸው። (4) አራተኛው እምቢታ በጥያቄ መልክ
ሳይሆን “አንደበተ ርቱዕ አይደለሁም” በሚል አረፍተ ነገር የተገለጸ ነበር።
እግዚአብሔር ለሁሉም ሰበቦች መልስ በመስጠት ኃይለኛ የሆነ መፍትሄ ሰጠ።
ለእነዚህ ሰበቦች እግዚአብሔር ብዙ ከፍ የሚያደርጉ ተስፋዎችን አቀረበ።
ከዚያ በኋላ ሙሴ አምስተኛውንና የመጨረሻውን ተማዕጽኖ
በማቅረብ በቀጥታ እንዲህ በማለት ጠየቀ፡- “ጌታ ሆይ፥ በምትልከው ሰው
እጅ ትልክ ዘንድ እለምንሃለሁ” (ዘጸ. 4:13)። በምላሹ፣ እንዲረዳው
ወንድሙን አሮንን እየላከለት እንደሆነና ሊገናኘው እየመጣ እንደሆነ
እግዚአብሔር ነገረው። በመጨረሻ፣ ሙሴ በዝምታ በመስማማት ወደ ግብጽ
ከመሄዱ በፊት እንዲባርከው አማቱን ዮቶርን ጠየቀው።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ዘጸአት 4:18–31ን ያንብቡ። ይህን እንግዳ የሆነ ታሪክ እንዴት እንረዳዋለን? ከዚህስ ምን ትምህርት መውሰድ እንችላለን?
ሙሴ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ወደ ግብጽ ጉዞ ከጀመረ በኋላ
“እግዚአብሔር ሊገድለው ፈለገ” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች
ሲያነቡ እጅግ ይደነግጣሉ(ዘጸ. 4:24፣ )። ከታሪኩ አውድ ሲታይ ጉዳዩ
ግዝረት መሆኑ ግልጽ ነው። ከልጆቹ መካከል ታናሹ የአብርሐም ቃል ኪዳን
በሚጠይቀው መሰረት አልተገረዘም ነበር (ዘፍ. 17:10፣ 11)።
ሙሴ፣ እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ መሪ፣ ሌሎች ሰዎችን ወደ መታዘዝ
የመምራት ብቃት እንዲኖረው፣ ለእግዚአብሔር ያለውን ፍጹም መገዛትና መታዘዝ
ማሳየት ነበረበት። ለእግዚአብሔር ራስን ሙሉ በሙሉ አሳልፎ የመስጠት ምሳሌ
መሆን ነበረበት። ሚስቱ ሲፓራ የተግባር ሰው ስለነበረች የባሏን ሕይወት ለማዳን
ልጇን ገረዘችው። ከዚያም “ደም በነበረበት ሸለፈት ” ሙሴን ነካችው፤ ይህ
ደም ስርየትን፣ ሕይወትን እና የቃል ኪዳኑን ሕትመት የሚያሳይ ነበር። ድርጊቱ
በፍጥነት የመከናወኑ እውነታ ለሁኔታው ትዕይንት ተጨማሪ ነገር ሆኗል።
ከዚህ ክስተት ጠቃሚ ትምህርት መማር ይቻላል፤ ያውም ትክክል እንደሆነ
የምናውቀውን ነገር ከማድረግ በፍጹም ወደ ኋላ ማለት እንደሌለብን ነው።
“ከምድያም ያደርግ በነበረው ጉዞ ላይ፣ እግዚአብሔር ደስተኛ
ያለመሆኑን የሚገልጽ አስገራሚና አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው። መልአክ
ወዲያውኑ ሊያጠፋው እንደተዘጋጀ ሆኖ፣ ለሕይወቱ አስጊ በሆነ ሁኔታ
ተገለጠ። ምንም ማብራሪያ አልተሰጠም ነበር፣ ነገር ግን ሙሴ ከእግዚአብሔር
መስፈርቶች መካከል አንዱን ችላ እንዳለ አስታወሰ። ያውም ታናሽ ልጁን
መግረዝ ችላ ማለቱን ነበር። ልጁን እግዚአብሔር ከእሥራኤላውያን ጋር
ለፈጸማቸው የቃል ኪዳን በረከቶች ባለመብት እንዲሆን የሚያደርገውን ቅድመ
ሁኔታ ችላ ብሏል። በተመረጠው መሪያቸው በኩል የዚህን ዓይነት ቸልተኝነት
ማሳየት የእግዚአብሔር ሕግጋት በሕዝቡ ላይ ያላቸውን ኃይል ዝቅ ያደርጋል።
ሲፓራ፣ ባሏ እንዳይገደልባት በመፍራት ሥርዓቱን ራሷ ፈጸመችው። ከዚያ በኋላ
ሙሴ የሚያደርገውን ጉዞ እንዲቀጥልበት ፈቀደለት። ለፈርዖን እንዲያስተላለፍ
በታዘዘው ተልዕኮ ሙሴ ትልቅ አደጋ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ሊሆን ነው፤ ሕይወቱ
ሊጠበቅ የሚችለው በቅዱሳን መላእክት ጥበቃ ብቻ ነው። ነገር ግን መፈጸም
እንዳለበት የሚያውቀውን ተግባር ችላ ብሎ ሲኖር፣ በእግዚአብሔር መላእክት
ሊከለል ስለማይችል ከአደጋ ነጻ መሆን አይችልም ነበር።”–Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ pp. 255፣ 256.
እርስዎ ማድረግ እንዳለብዎት የሚያውቁትን ነገር ችላ በማለትዎ በደለኛ ከሆኑ
ይህ ታሪክ ለእርስዎ ምን ይነግርዎታል? አሁን፣ በዚህች ሰዓት እንኳን፣ ምን
ለውጦችን ነው ማድረግ ያለብዎት?
ኤለን ጂ ኋይት አባቶችና ነቢያት በሚለው መጽሐፏ፣ “ሙሴ” በሚል ርዕስ፣ ከገጽ 251–256 ላይ የጻፈችውን ሀሳብ
ከእንግሊዝኛው መጽሐፍ ያንብቡ።
ትዕይንታዊው የሚነድደው ቁጥቋጦ ጥሪ ምናልባት በሙሴ ሕይወት
ውስጥ እጅግ ለውጥ ያመጣ ልምምድ ሊሆን ይችላል። በሕይወቱ የነበሩ
ሌሎች የከፍታ ነጥቦች በሙሉ የሚደገፉት ዕብራውያንን ከግብጽ ወደ ተስፋይቱ
ምድር እንዲመራ እግዚአብሔር ለሰጠው ተልእኮ አዎንታዊና የታዛዥነት ምላሽ
በመስጠት ላይ ነበር።
እርግጥ ነው፣ ሁሉም ነገር እንዴት እንደተፈጸመ አሁን እናውቃለን።
ነገር ግን በሚነድደው ቁጥቋጦ ጊዜ ሙሴ ምን እንደተሰማው ለማወቅ
ራስዎን በሙሴ ቦታ ያስቀምጡ። ሕይወቱን ለማዳን ከግብጽ ሸሽቷል። በ40
ዓመታት ውስጥ፣ ምናልባትም አብዛኞቹ ስለ እርሱ ብዙም የማያውቁ አዲስ
የዕብራውያን ትውልድ መጥቷል፤ ወይም ምናልባት ስለ እርሱ የሰሙት ነገር
ስህተትና በጊዜ ሂደት ከተወሩ አፈ ታሪኮች እየተጣሩ በመምጣት የተዛቡ ሊሆኑ
ይችላሉ። ቢሆንም፣ ይህንኑ ሕዝብ ኃይለኛ ከሆነ መንግሥት ነጻ እንዲያወጣ
ተጠርቷል ማለት ነው? በመጀመሪያ ዳተኛ መሆኑ አያስደንቅም!
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
አዎን፣ እጅግ በጣም አድካሚ ሥራ ነበር፤ ነገር ግን በመጨረሻ
“አልችልም” ብሎ ለእግዚአብሔር መልስ ቢሰጥ ኖሮ ያጣው የነበረውን
ነገር ያስቡ። በውስጡ በሚሰራው የእግዚአብሔር ኃይል ታሪክ በመስራት፣
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም ውስጥ እንኳን፣ እጅግ በጣም
ታላቅና ተጽእኖ ፈጣሪ ሰው ከመሆን ይልቅ በታሪክ ውስጥ ጠፍቶ ይቀር ነበር።
1. ሙሴ በምድረ በዳ ባሳለፋቸው የጸጥታ አመታት እግዚአብሔር
ሙሴ በምድረ በዳ ባሳለፋቸው የጸጥታ አመታት እግዚአብሔር
እንዲሰራ የጠራውን ነገር ሰራ። ቤተሰብ የነበረው ሰው ነበር፣
በጎችን ይጠብቅ ነበር፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ታላቅ መሪ እንዲሆን
ከመጠራቱ በፊት በእግዚአብሔር ምሪት ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ
መጻሕፍትን ጻፈ። የሙሴ ልምምድ እኛ በሕይወት ስለሚኖሩን
ተግባራት ምን ይነግረናል?
2. ሙሴ ያቀረባቸው ሰበቦች ላይ ላዩን ሲታዩ በራሳቸው በደንብ
ሙሴ ያቀረባቸው ሰበቦች ላይ ላዩን ሲታዩ በራሳቸው በደንብ
ምክንያታዊ ስለመሆናቸው መከራከር ይቻላል፤ ምክንያታዊ
አይደሉም? ሰዎች ለምንድር ነው ሊያምኑኝ የሚገባው?
ሲጀመር እኔ ማን ነኝ? በደንብ መናገር አልችልም። እግዚአብሔር
እንድንሰራ የጠራንን ነገር መስራት እንድንችል እንደሚያስችለን
በእርሱ መታመንን እንዴት መማር እንዳለብን ይህ ታሪክ ምን
ይነግረናል?
3. ስለ ሙሴ የዘፍጥረት መጽሐፍ ፀሐፊነት እና ያ ሥራ ቅዱስ
ስለ ሙሴ የዘፍጥረት መጽሐፍ ፀሐፊነት እና ያ ሥራ ቅዱስ
ታሪክንና የድነት ዕቅድን ለመረዳት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ
ለማወቅ በእሁድ ትምህርት ውስጥ በቀረበው ነጥብ ላይ የበለጠ
ጊዜ ውሰዱ። የመጽሐፉን ሥልጣን ለማዳከም፣ በተለይም
የመጀመሪያዎቹን ሁለት ምዕራፎች ታሪካዊነት በመካድ፣
የሚደረገውን እያንዳንዱን ጥረት (ብዙ ጥረቶች አሉ) መዋጋት
ያለብን ለምንድር ነው?