የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዘጸ. 1:1–22፤ ዘፍ. 37:26–28፤ ዘፍ. 39:2፣ 21፤ የሐዋ. 7:6፤ ገላ. 3:16፣ 17፤ ዘጸ. 2:1–25.
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤የግብፅ ንጉሥ ሞተ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ጮኹም፥ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ። እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን ድምፅ ሰማ፥ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ። እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አየ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ያለውን ነገር አወቀ።” (ዘጸ. 2:23–25)።
የዘጸአት መጽሐፍ የተጨቆኑ፣ የተገለሉ፣ የተሰደዱ፣ የተበዘበዙና የተዋረዱ
ሰዎችን ዘገባ ያስተጋባል። ስለዚህ ዛሬ እንደተጣሉ፣ እንደተረሱ እና
ለባርነት እንደተሸጡ የሚሰማቸው ሰዎች ዕብራውያንን ያዳነው ያው
አምላክ እነርሱንም ማዳን ስለሚችል ተስፋ ያገኛሉ።
የዘጸአት መጽሐፍ በሕይወት ውስጥ ለመኖር ስለሚደረጉ ጦርነቶች
እና የዚህ ሕይወት አካል ስለሆኑ ኢ-ፍትሃዊነቶችና ፈተናዎች ይናገራል። ሥቃይ
እየደረሰባቸው ያሉ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር ሕዝቡን በመደገፍ በፈጸማቸው
ጣልቃ መግባቶች ሊደፋፈሩ ይችላሉ። እግዚአብሔር የተጨቆነ ሕዝብን
ጩኸት ይሰማል፣ የሚያጋጥሟቸውን ተጋድሎዎች ይመለከታል፣ እንባዎቻቸውን
መዝግቦ ይይዛል፤ በሚደርስባቸው ሰቆቃም ሊረዳቸው ይመጣል።
እግዚአብሔር በእርሱ የሚታመኑትን ነጻ ለማውጣት ተነሳሽነቱን
ይወስዳል። እርሱ የሚሰጠንን ዝም ብለን በእምነት መቀበል ያስፈልገናል።
የዘጸአት መጽሐፍ መጠናት ያለበት ምክንያት ኢየሱስ ለሁላችንም ወዳደረገው
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ነገር ስለሚጠቁም ነው። በኢየሱስ ክርስቶስና እርሱ ጠብቆ ባቆየልን ነገር
ላይ ባለን እምነት ሁሉም የእኛ ስለሆኑት ስለ እምነት፣ ስለ መቤዠት፣ ነጻ
ስለመውጣትና ስለ መጨረሻው ድነት የሚናገር መጽሐፍ ነው።
በሕውከትና በጨለማ መካከል፣ ዓይኖቻችን በእግዚአብሔር ላይ
ካተኮሩ፣ እርሱ ወደ ዘላለማዊው “የተስፋ ምድር” እየመራን ሳለ የእርሱን
መገኘት፣ ጥንቃቄና እርዳታ መገንዘብ እንችላለን።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሰኔ 28 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ
የዘጸአት መጽሐፍ በዕብራይስጥ ሼሞት (shemot) የሚባል ሲሆን
በጥንቱ ሰነድ የመክፈቻ ቃላት መሰረት ወደ እንግልዝኛ ቋንቋ ሲተረጎም ቃል
በቃል “ስሞች” የሚል ትርጉም አለው። የሚጀምረው “እናም የእሥራኤል
ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው” በማለት ነው። የአበው ያዕቆብ ቤተሰብ ስሞች
ገና በጅምሩ ላይ ተዘርዝረዋል።
ዘጸ. 1:1–7ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ምን ወሳኝ እውነት ነው ያለው?
የዘጸአት መጽሐፍ የሚጀምረው የእግዚአብሔርን በረከት በማስታወስ ነው። አበው ያዕቆብና ቤተሰቡ በግብጽ ምድር መኖር በጀመሩ ጊዜ ሰባ ሰዎች ብቻ ነበሩ (ዘፍ. 46:27፣ ዘጸ. 1:5)፤ ነገር ግን እሥራኤላውያን “አፈሩ፥ እጅግም በዙ፥ ተባዙም፥ አጅግም ጸኑ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች” (ዘጸ. 1:7)። ነገር ግን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ቁጥራቸው “ከሕፃናቱም ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህል እግረኛ ነበረ” (ዘጸ. 12:37)። ዘጸ. 1:8–11ን ያንብቡ። ከግብጽ በወጡ ጊዜ የእሥራኤላውያን ሁኔታ ምን ነበር?
የእሥራኤል ልጆች በግብጽ ምድር የነበራቸውን ታሪክ የመጽሐፍ
ቅዱስ ጥቅስ በጥቁር ቀለሞች ይቀባዋል። የዘጸአት መጽሐፍ የሚጀምረው
በግብጻውያን አሰሪዎች ሥር ባሪያ በመሆናቸውና በዕብራውያን ላይ
በተጫነው ጭቆና የተሞላበት የጉልበት ሥራ ነው። ነገር ግን የዘጸአት
መጽሐፍ የሚያበቃው በእሥራኤላውያን መኖሪያ ሰፈር (ካምፕ) መካከል
ባለው ቤተ መቅደስ ውስጥ ሰላማዊና አጽናኝ የሆነ የእግዚአብሔር መገኘት
ነው (ዘጸ. 40ን ይመልከቱ)። በእነዚህ ሁለት ተቃራኒ ዋልታዎች መካከል
የእግዚአብሔር ድል አድራጊነት ተገልጾአል። እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ
ከባርነት ነጻ በማውጣቱ፣ ቀይ ባህርን በመክፈሉ፣ እና በዚያ ዘመን ከነበረው
ጦር ሁሉ እጅግ ብርቱ የሆነውን ጦር በማሸነፉ፣ እግዚአብሔር በክፉ ኃይሎች
ላይ ያገኘው አስደናቂ ድል ተገልጧል።
ታሪኩ ተጻራሪ በሆነ አባባል ጨቋኞቻቸው “እንዳስጨነቁአቸው መጠን
እንዲሁ በዙ፥ እጅግም ጸኑ” (ዘጸ. 1:12) የሚለውን ሀሳብ አጽንዖት
ሰጥቶ ይገልጻል። ይህ ማለት፣ ምንም ያህል ሰብአዊ ተንኮል ቢኖርም፣
ሁኔታዎች ቢያንስ ከሰብአዊ እይታ አንጻር ተስፋ ቢስ ቢመስሉም እንኳን፣
አሁንም እግዚአብሔር ልዑላዊ ስለሆነ ሕዝቡን ያድናል።
ዮሴፍን የማያውቅ አዲስ ንጉሥ ተነሣ። ሁኔታዎችን፣ በተለይም ጥሩ የሆኑትን፣
ሁልጊዜም እንዲሁ ሆነው እንደሚቀጥሉ አድርገን በፍጹም መውሰድ
እንደሌለብን ይህ ታሪክ ምን ይነግረናል?
የያዕቆብ ቤተሰብ በከነዓን ምድር ረሃብን ከተለማመዱ በኋላ ወደ
ግብጽ ሲደርሱ (ዘፍ. 46)፣ ስለ ዮሴፍና እርሱ ለግብጻውያን ካደረጋቸው
ነገሮች ሁሉ የተነሣ የግብጽ ንጉሥ ዕብራውያንን በወዳጅነት ተቀበላቸው።
“ፈርዖንም ዮሴፍን፦ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾምሁህ አለው። ፈርዖን
ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ በዮሴፍ እጅም አደረገው፥ ነጭ የተልባ እግር ልብስንም
አለበሰው፥ በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤ የእርሱም በምትሆን
በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፥ አዋጅ ነጋሪም፦ ስገዱ እያለ በፊት በፊቱ ይጮኽ
ነበር፤ እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ተሾመ” (ዘፍ. 41:41–43)።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ዮሴፍ ጎርበጥባጣ የሆነ መነሻ ቢኖረውም በግብጽ ምድር አስደናቂ የሆነ ስኬት
ስለማግኘቱ ቁልፉ ምን ነበር? (
ስለማግኘቱ ቁልፉ ምን ነበር? ( ዘፍ. 37:26–28 እና ዘፍ. 39:2፣ 21ን ያንብቡ።)
የዮሴፍን ታሪክ በተመለከተ እጅግ አሳማኝ የሆነው ታሪካዊ ዳራ
የሚከተለው ነው፡- በዘጸአት 1:8 ላይ “ዮሴፍን የማያውቅ” ተብሎ
የተገለጸው አዲሱ ንጉሥ አህሞስ (1570 አ.አ. –1546 አ.አ.) ነበር።
ከዚያ ቀጥሎ እሥራኤላውያንን የፈራና የጨቆነ አሜንሆቴፕ (1546 አ.አ.
–1526 አ.አ.) የተባለ ገዥ መጣ። ከዚያ ቀጥሎ ቱትሞስ 1ኛ (1525
አ.አ.–1512 አ.አ.) የእሥራኤል ወንድ ልጆች በሙሉ እንዲገደሉ የሞት
አዋጅ አወጣ። ሙሴን በማደጎ ልጅነት ተቀብላ ያሳደገችው የእርሱ ልጅ የሆነችው
ሃትሼፕሰት(1503 b.c.–1482 b.c.) ልዕልት ነበረች። ለተወሰነ ጊዜ
ከሃትሼፕሰት ጋር አብሮ እንደራሴ የነበረው ፈርዖን ቱትሞስ 3ኛው (1504
አ.አ.–1450 አ.አ.) በዘጸአት ውስጥ የተጠቀሰው ፈርዖን ነበር።
የተሻሉ ስሌቶች እንደሚያመለክቱት የመውጣቱ ጉዞ የተደረገው 1450
አ.አ. በመጋቢት ወር ነበር (see William H. Shea, “Exodus,
Date of the,” The International Standard Bible
Encyclopedia፣ edited by Geoffrey W. Bromiley
et al., vol. 2 [Grand Rapids፣ MI: William B.
Eerdmans፣ 1982], pp. 230–238). ከግብጽ የወጡበትን ጊዜ
ለመረዳት የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያጥኑ፡- ዘፍ. 15:13–16፤
ዘጸ. 12:40፣ 41፤ መሳፍንት 11:26፤ እና 1ኛ ነገሥት 6:1 (ደግሞ የሐዋ.
7:6 እና ገላ. 3:16፣ 17ን ይመልከቱ)።
የዘጸአት የመጀመሪያው ምዕራፍ፣ ያዕቆብ ከመላው ቤተሰቡ ጋር ወደ
ግብጽ ከገባበት ከዮሴፍ ጊዜ አንስቶ ፈርዖን እስካስተላለፈው የሞት አዋጅ ያለውን
ረዥም ጊዜ ይሸፍናል። ትክክለኛ ጊዜውን በተመለከተ ክርክር ቢኖርም ዋናው ጉዳይ
ሕዝቡ በባዕድ አገር ባሪያ ሆነው ሳሉ እንኳን እግዚአብሔር አልረሳቸውም ነበር።
ይህ ማለት፣ በዚያን ዘመን ዕብራውያን በግብጽ ምድር ስለነበሩበት
ሁኔታ ብዙ ዝርዝሮች ድብቅ ቢሆኑም፣ ቢያንስ ለአሁኑ (1ኛ ቆሮ. 13:12ን
ይመልከቱ)፣ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሁሉ እንደሆነው፣ አሁንም
የእግዚአብሔር ባህርይ መገለጥ በዚህ መጽሐፍ ገጾች ያበራል። ነገሮች
ምንም ያህል የከፉ ቢመስሉም፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ እዚያ መኖሩን ማወቅ
የምንችል ሲሆን በምንም አይነት መጥፎ ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን ብናገኝ
በእርሱ መታመን እንችላለን።
አንድ ሰው በዘፍጥረት አስተምህሮዎች ላይ ሳይመሰረት ዘጸአትን
መረዳት አይችልም። አይሁዶች ወደ ግብጽ ሄደው ከተወሰነ የብልጽግናና
የሰላም ጊዜ በኋላ ባሪያዎች ተደረጉ።
ነገር ግን አንዳንዴ እግዚአብሔር ሕዝቡን የተዋቸው ቢመስልም በችግራቸው
ውስጥ አልተዋቸውም ነበር። አብዛኞቹ ዕብራውያን በደረሰባቸው ነገር ተስፋ
ስለመቁረጣቸው ምንም ጥርጥር የለውም። ሆኖም በተጨነቁ ጊዜ በብርቱ እጁ
ሊረዳቸው ይመጣ ነበር። ጌታ ተከታዮቹን እንዲህ በማለት ያደፋፍራል፡- “በመከራ
ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ” (መዝ. 50:15)።
ዘጸ. 1:9–21ን ያንብቡ። ታማኝ የነበሩ አዋላጆች የተጫወቱት ቁልፍ ሚና
ምን ነበር? በታሪክ የሚታወሱትስ ለምንድር ነው?
በዘጸአት መጽሐፍ ውስጥ በስሙ የተጠራ አንድም ፈርዖን የለም።
ሁላቸውም “ፈርዖን” የሚል ማዕረግ ብቻ የተሰጣቸው ሲሆን ትርጉሙ
“ንጉሥ” ማለት ነው። ግብጻውያን ፈርዖን በምድር ላይ አምላክ፣ ራ (ወይም
ኦሲሪስ ወይም ሆሩስ) የሚባል ጣዖት አምላክ ልጅ እንደሆነ ያምኑ ነበር። ራ
ከሁሉ የበላይ የሆነ የግብጻውያን አምላክ ሲሆን እርሱ የፀሐይ አምላክ ነበር።
ነገር ግን ይህ ሁሉ ሥልጣን ቢኖረውም ይህ “አምላክ” አዋላጆቹ
ከሚያምኑት በተቃራኒ እንዲሄዱ ማስገደድ አልቻለም። እንዲያውም ከስም
የለሽ ፈርዖን በተቃራኒ ሁለቱ በስማቸው የተጠሩ አዋላጆች፣ ሲፓራ እና ፉሐ
(ዘጸ. 1:15)፣ እግዚአብሔርን ስለፈሩ ከፍተኛ አክብሮት ተሰጥቶአቸዋል።
ከምድራዊ ገዥ ትዕዛዝ የበለጠ እግዚአብሔርን ስላከበሩ የፈርዖን ክፉ ትዕዛዝ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
በእነርሱ ላይ ተጸጽእኖ አልፈጠረም ነበር (የሐዋርያት ሥራ 5፡29ን ደግሞ
ይመልከቱ)። ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር ከራሳቸው ታላቅ ቤተሰብ ጋር
ባረካቸው። እንዴት ያለ ለታማኝነት የተሰጠ ኃይለኛ ምስክርነት ነው። እነዚህ
ሴቶች፣ ስለ ሥነ-መለኮት ያላቸው እውቀት ምንም ያህል ትንሽ ቢሆንም፣ ትክክል
የሆነውን ማወቅ ብቻ ሳይሆን ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግም መረጡ።
ፈርዖን ሴራው እንደከሸፈበት ሲመለከት ከዕብራውያን ወገን የሚወለዱትን
ወንድ ልጆች በሙሉ እንዲገድሉ ግብጻውያንን አዘዘ። ልጆቹን ወደ አባይ ወንዝ
መጣል ነበረባቸው፤ ይህ ምናልባት የአባይ አምላክ እና የልምላሜ አምላክ ለሆነው
ሀፒ እንደ ሥጦታ ተደርጎ እንዲሰጥ ታስቦ ሊሆን ይችላል። (ይህ አይሁዶች አይሁድ
ስለሆኑ ብቻ እንዲገደሉ ስለመወሰኑ በታሪክ ተመዝግቦ ያለው ለመጀመሪያ ጊዜ
ነው።) የሞት አዋጁ ዓላማ ዕብራውያንን አንገት ለማስደፋት እና ሴቶቹን ከግብጽ
ሕዝብ ጋር እንዲዋሃዱ ለማድረግ ሲሆን በዚህም ፈርዖን ዕብራውያን ለሕዝባቸው
ስጋት እንደሆኑ ስላመነ ያንን ስጋት ወደ ፍጻሜ ለማምጣት ነበር።
አዋላጆቹ ምን ዓይነት ትክክለኛ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ማወቅ
ብቻ ሳይሆን በተግባር ላይ አውለውታል (ፈጽመውታል)።በዚህ ቦታ ለእኛ
የተሰጠው ግልጽ መልእክት ምንድር ነው?
የተሰጠው ግልጽ መልእክት ምንድር ነው?
ዘጸ. 2:1–10ን ያንብቡ። በሙሴ የመወለድ ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔር መሰናዶና ጥበቃ የተጫወተው ሚና ምን ነበር?
ሙሴ የኖረው ዝነኛ በነበረው 18ኛው የግብጽ ስርዎ-መንግስት--
“የግብጽ ናፖሊዮን” ተብሎ የሚጠራው ቱትሞስ 3ኛው በነገሰበት-- ዘመን
ስለነበር የእርሱ መወለድና ሕይወት ታሪካዊው ዳራ ደስታን የሚጭር ነው።
ምንም እንኳን ገና ከመወለዱ የሞት አዋጅ ሥር የነበረ ቢሆንም
(ዘጸ. 1:22ን ይመልከቱ)፣ ሙሴ “ልዩ” ልጅ ሆኖ ነበር የተወለደው።
(በዕብራይስጥ ቶብ (tob) የሚለው ቃል በቀጥታ ሲተረጎም “መልካም”
ማለት ነው) (ዘጸ. 2:2)። የዕብራይስጡ ቃል ከውጫዊ ውበት የበለጠ
ነገር ይገልጻል። ለምሳሌ፣ ቃሉ በፍጥረት ሳምንት የነበረውን የእግዚአብሔርን
ሥራ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ሁሉንም ነገር “መልካም፣” እንዲያውም
“እጅግ መልካም” ነበር በማለት ገልጾታል (ዘፍ. 1:4፣ 10፣ 31)።
ይህ “መልካም” ልጅ፣ አዲስ ፍጥረት እንደመሆኑ፣ በእግዚአብሔር
ዕቅድ መሰረት፣ ዕብራውያንን ከባርነት ወደ ነጻነት የሚመራ ጎልማሳ
ይሆናል። በዚህ ልጅ መወለድ፣ በተለይም ይህን በመሰለ እጅግ መጥፎ በሆነ
ሁኔታ፣ ወደፊት የተሻለ ነገር ይሆናል ብሎ ማን ሊያስብ ይችላል? ነገር ግን
እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ለይስሃቅና ለያዕቆብ የገባውን ቃል ይፈጽማል።
ለዘራቸው የተስፋይቱን ምድር እንደሚሰጥ ቃል ገብቶላቸው ነበር (ዘጸ.
2:24፣ 25). አዎን፣ ይህን ቶብ (መልካም) ህጻን፣ ከአስርተ አመታት
በኋላ፣ የእርሱን ቃል እንዲፈጽም ይጠቀምበታል።
እስከዚያ ድረስ የግብጽ ልዕልት የነበረችው ሃትሽፕሱት የማደጎ
ልጇ አድርጋ ተቀበለችው። ለሙሴ የተሰጠው ስም መነሻው ከግብጽ ሲሆን
ትርጉሙ አህ-ሞስ (“የአክህ ልጅ”) ወይም ቱት-ሞስ (“የቶት ልጅ”)
በሚሉ ስሞች እንደተንጸባረቀው “የ…ልጅ” ወይም “ወልደ…” የሚል ነው።
ስለዚህ በዕብራይስጥ ሞሼህ ተብሎ የተሰጠው ስም “ከውኃ የወጣ” የሚል
ነው። ከወንዝ “በመውጣቱ” ሕይወቱ ተዓምራዊ በሆነ ሁኔታ ድኗል።
ስለ ቀደምት ሕይወቱ የምናውቀው እጅግ ጥቂት ነው። ተአምራዊ
በሆነ ሁኔታ ከዳነ እና ሃትሸፕሱት የማደጎ ልጅ አድርጋ ከተቀበለችው በኋላ
ሙሴ ለመጀመሪያዎቹ አሥራ ሁለት ዓመታት ከመጀመሪያ ቤተሰቡ ጋር ኖረ
(ዘጸ. 2:7–9፤ Ellen G. White, Patriarchs and
Prophets, p. 244)። ከዚያ በኋላ በግብጽ ምድር ቀጣዩ ፈርዖን
እንዲሆን ለማዘጋጀት ከሁሉ የተሻለውን ትምህርት ተማረ (Patriarchs
and Prophets፣ p. 245)። ይህ ሁሉ ትምህርት፣ በርግጠኝነት
ወሳኝ ለሆነ ነገር፣ ያውም እግዚአብሔርንና እውነቱን ስለማወቅ ሲባል ዋጋ
ቢስ መሆኑ ወይም በተቃራኒ መስራቱ እንዴት ትኩረትን የሚስብ ነገር ነው።
ወሳኝ ለሆነ ነገር ሲባል በመጨረሻ የማይጠቅመውን ነገር ስለመተው ምን
ያህል እየተማሩ ነው?
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ዘጸ. 2:11–25ን ያንብቡ። የሙሴን ሕይወት ጠቅላላ አቅጣጫ ለመለወጥ በፍጥነት የተፈጸሙ ክስተቶች ምን ነበሩ? ከዚህ ታሪክ ምን ትምህርቶችን መማር እንችላለን?
ሙሴ ምን ያደርግ ይሆን? ለግብጽ ማታለያና በቤተ መንግሥት
ለሚያገኛቸው ደስታዎች ይሸነፍ ይሆን ወይስ ጦርነት ከበዛበት ሕዝብ ጋር መከራን
ታግሶ ይቀበል ይሆን? ክስተቶቹ ወዲያውኑ ውሳኔ እንዲያደርግ አስገደዱት።
“ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን
ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፥ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ በውኃም ጕድጓድ
አጠገብ ዐረፈ” (ዘጸ. 2:15)።
ሙሴ ግብጻዊውን ከገደለ በኋላ፣ ቢያንስ በግብጽ ምድር ለመቆየት
ምርጫ አልነበረውም። የግብጽን ዙፋን ለመቆናጠጥና “አምላክ” ለመሆን
ምንም ዓይነት ዕቅዶች ቢኖሩትም እነዚያ ዕቅዶች በፍጥነት ወደ መጨረሻ
መጡ። አምላክ፣ ለዚያም ውሸተኛ አምላክ፣ ከመሆን ይልቅ ሙሴ
እውነተኛውን አምላክ ያገለግላል። ሙሴ በሸሸ ጊዜ መጪው ጊዜ ምን ይዞለት
እንደሚጠብቀው ምንም የሚያውቀው ነገር እንዳልነበረ አያጠራጥርም።
“ጉዳዩን [ሙሴ ግብጻዊውን መግደሉ] ወዲያውኑ ግብጻውያን
እንዲያውቁት ተደረገ፣ እጅግም ከመጋነኑ የተነሣ ወዲያውኑ ወደ ፈርዖን ጆሮ
ደረሰ። ይህ ድርጊት ሙሴ ሕዝቡን በግብጻውያን ላይ እንዲያምጹ ለማድረግ፣
መንግሥትን ለመገልበጥና ራሱ በዙፋን ላይ ለመቀመጥ፣ አልፎ ተርፎም
እርሱ እስካለ ድረስ በግዛቱ ምንም ደህንነት እንዳይኖር ለማድረግ በሙሴ
የተዘጋጀ ዕቅድ እንደሆነ አድርገው ለንጉሡ አቀረቡ። ንጉሡ ሙሴ ወዲያውኑ
እንዲገደል ወሰነ፤ ነገር ግን ሴት ልጁ ጉዳዩን ስላወቀች ወደ አረብ አገር ሸሽቶ
እንዲያመልጥ አደረገች።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 247.
ሙሴ 120 ዓመት የኖረ ሲሆን (ዘዳ. 34:7)፣ ሕይወቱ እያንዳንዳቸው
40 ዓመታት ባሉት ሶስት ክፍሎች የተከፈለ ነበር። የመጀመሪያዎቹን አርባ
ዓመታት ያሳለፈው በግብጽ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፈው በቤተ መንግሥት
ነበር። ሁለተኛውን 40 ዓመት በምድያን አገር በዮቶር ቤት አሳለፈ።
ነገር ግን፣ አምስቱን የሙሴ መጻሕፍት አብዛኛውን ክፍል (እና ይህን ሩብ
ዓመት) የሸፈኑት የመጨረሻዎቹ አርባ አመታት ሲሆኑ፣ እሥራኤል በጣዖት አምልኮ
ለተሞላው ዓለም የእግዚአብሔርን እውነተኛ ተፈጥሮና ባህሪይ በመግለጥ እንዲመሰክሩ
አስቀድመው የመጠራታቸውን ታሪክ ይናገራሉ። ( ዘዳ. 4:6–8ን ይመልከቱ)።
ሙሴ ግብጻዊውን እንዲገድል የእግዚአብሔር ዕቅድ ነበርን? ካልሆነስ፣
እግዚአብሔር ማንኛውንም ሁኔታ በመቆጣጠር ለራሱ ዓላማ እንዴት
እንደሚጠቀም ይህ ታሪክ ምን ያስተምረናል? ይህን ጠቃሚ እውነት
እንድናስተውል ሮሜ 8፡28 የሚረዳን እንዴት ነው?
በዚህ ሳምንት በተጠናው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ላይ ወሳኝ የሆነ መረዳትን እንዲሰጥዎት ኤለን ኋይት ከጻፈችው አባቶችና
ነቢያት ከሚለው መጽሐፍ በእንግሊዝኛው ከገጽ 241-251 ላይ “ሙሴ”
በሚለው ርዕስ ሥር ያለውን ሀሳብ ያንብቡ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ “አዋላጆች ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፥ የግብፅ
ንጉሥም እንዳዘዛቸው አላደረጉም፥ ወንዶቹን ሕፃናትንም አዳኑአቸው”
(ዘጸ. 1:17) ይላል። ኤለን ጂ ኋይት በአዋላጆቹ ታማኝነትና በመሲሃዊው
ተስፋ ላይ ተገቢ የሆኑ አስተያየቶችን ትሰጣለች፡- “ሥራቸው ትዕዛዙን
እንዲፈጽሙ ዕድል ለተሰጣቸው ሴቶች የዕብራውያንን ወንድ ልጆች ገና
ሲወለዱ እንዲገድሉአቸው ትዕዛዝ ተሰጣቸው። በዚህ ጉዳይ አንቀሳቃሹ
ሰይጣን ነበር። በእሥራኤላውያን መካከል ነጻ አውጪ እንደሚነሳ ስላወቀ
ንጉሡ ልጆቻቸውን እንዲገድል በመምራት መለኮታዊ ዕቅድን አሸንፋለሁ
ብሎ ተስፋ አደረገ። ነገር ግን ሴቶቹ እግዚአብሔርን ስለፈሩ የጭካኔ ትዕዛዝን
ለመፈጸም አልደፈሩም። እግዚአብሔርም ለድርጊታቸው እውቅና በመስጠት
ስኬትን ሰጣቸው።”—Ellen G. White፣ Patriarchs and Prophets፣ p. 242.
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
በዚህ ሁሉ ውስጥ መልካሙ ዜና ሰይጣን ቢያቅድም እግዚአብሔር
ሁኔታውን በመቆጣጠር ጠላት ዕቅዱን እንዳይፈጽም ለመከልከል ታማኝ
ሰዎችን ተጠቀመ። ኢየሱስ “መስፍን” ወይም “የዚህ ዓለም ገዥ” (ኤፌ.
2:2፣ ፤ ዮሐንስ 14:30) ብሎ በጠራው የጠላታችን ግዛት ውስጥ
እንኖራለን። ሰይጣን ይህንን ሥልጣን ከአዳም ቀማው፣ ነገር ግን ኢየሱስ
ክርስቶስ በሕይወቱና በመስቀል ላይ ሞቱ አሸነፈው (ማቴ. 4:1–
11፣ ዮሐንስ 19:30፣ ዕብ. 2:14)። ምንም እንኳን እነዚያን ልጆች
ለመግደል ባደረገው ጥረት እንደተገለጠው ሰይጣን አሁንም በመስራት ላይ
ያለና ሕያው ቢሆንም፣ የራሱ ጥፋት የተረጋገጠ ነው (ዮሐንስ 12:31፤
ዮሐንስ 16:11፤ ራዕይ. 20:9፣ 10፣ 14)። መልካሙ ዜና በሕይወት
የሚገጥሙን ችግሮች በእግዚአብሔር ጸጋ ሊሸነፉ የሚችሉ ናቸው (ፊልጽ.
4:13)። ብቸኛው ተስፋችን ያ ጸጋ ነው።
1. ዕብራውያን በግብጽ እንዲኖሩና ጭቆና እንዲደርስባቸው
ዕብራውያን በግብጽ እንዲኖሩና ጭቆና እንዲደርስባቸው
እግዚአብሔር ለምን ፈቀደ? እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ጣልቃ
ለመግባት ይህን ያህል ረዥም ጊዜ ለምን ወሰደበት? እያንዳንዱ
ግለሰብ የተሰቃየው በሕይወት እስከኖረ ጊዜ ብቻ እንደሆነም ልብ
ይበሉ። ይህ ማለት ለሕዝቡ የመከራው ጊዜ ረዥም ነበር፣ ነገር
ግን እያንዳንዱ ግለሰብ የተሰቃየው እርሱ እስከኖረበት ጊዜ ብቻ
ነበር። ሰብአዊ ስቃይን በአጠቃላይ ለመረዳት ስንሻ ይህን ልዩነት
ማድረግ ጠቃሚ (አስፈላጊ) የሚሆነው ለምንድር ነው?
2. ሙሴ በንዴት ግብጻዊውን የመግደሉን ድርጊት እግዚአብሔር
ሙሴ በንዴት ግብጻዊውን የመግደሉን ድርጊት እግዚአብሔር
እንዴት ሊጠቀምበት እንደቻለ በሚመለከተው ጥያቄ ላይ የበለጠ
ጊዜ ይውሰዱ። እስኪ ድርጊቱን አልፈጸመም ብለው ያስቡ። ያ
ማለት ዕብራውያን ከግብጽ ምድር አምልጠው አይወጡም
ማለት ነው? ለመልስዎ ያለዎትን ምክንያት ያብራሩ።