የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ መዝ. 46፣ ኤር. 4:23–26፣ መዝ. 47:1–4፣ 1ተሰ. 4:13–17፣ መዝ. 75፣ ራእ. 14:6–12።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤
ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ። ለሕዝቦች በቅን ስለምትፈርድላቸው፣
ሰዎችንም በምድር ላይ ስለምትመራ፣ ሕዝቦች ደስ ይበላቸው፤
በእልልታም ይዘምሩ።”(መዝ. 67፡3-4)።
ስለ መጨረሻው ዘመን ክስተቶች ስናስብ በአውሬዎች እና በራእይ ኃይላት
ላይ ማተኮር ይቀናናል። ለነገሩ እነዚህ ኃይላት ከሚጫወቱት ግዙፍ ሚና
አኳያ ለእነርሱ ትልቅ ስፍራ መሰጠቱ ብዙም አይገርምም። ይህ ባይሆን
ኖሮ እግዚአብሔር እነርሱን እናስተውል ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስፍራ
ባልሰጣቸው ነበር (ራዕ. 1፡3)።
ትንቢት እንደ ኃጢአት፣ ሥቃይ፣ ፍርድ፣ በመልካም እና በክፉ ኃይላት
መካከል የሚደረግ ተጋድሎ፣ ፍትሐዊና ኢ-ፍትሐዊ ባሕሪያት፣ ስደት እና ሌሎች
በርካታ ቁልፍ ርዕሰ ጉዳዮችን ይዟል።
መዝሙረ ዳዊትም እነዚህን ርዕሰ ጉዳዮች ከፍ ባለ ጥልቀት በመፈተሽ—
የሰው ልጅ ሊያጋጥመው ከሚችለው ማንኛውም ዓይነት ስሜት ማለትም
ከጽልመታዊ ተስፋ መቁረጥ እስከ ገደብ የለሽ ደስታና ፈንጠዝያ ያለውን
ይመረምራል። እስራኤል ከጨለማ ኃይላት ጋር ለመዋጋት ስትዘጋጅ እንመለከታለን።
እግዚአብሔር ለምንድን ነው ለክፋት ቀጥተኛና ፈጣን መፍትሔ የማይሰጠው
ከሚሉ ጥያቄዎች ጋር የሚታገሉ ግለሰቦችን ታሪክ እናነባለን። በእርግጥ ይህ
ጥያቄ የእኛም ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። መልሶችን ለማግኘት ፊታችንን ወደ
ቤተ መቅደሱ እንድናቀና ስንደረግ፣ የፈጣሪ ማዕረግ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር
የሚቀርቡ ተደጋጋሚ ልመናዎችን በዚያ እናገኛለን። ታዲያ እነዚህ—እኛም ዛሬ
ባለንበት ሁኔታ እየታገልናቸው ያሉ ጥያቄዎችና ጉዳዮች አይደሉምን?
እነዚህን ወሳኝ እውነቶች ይበልጥ ማጤን እንችል ዘንድ በመዝሙረ ዳዊት
ጥናታችን መግፋታችንን እንቀጥል!
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አርባ ስድስትን ያንብቡ። አሁን ካለው የሕይወት ውጣ ውረድ ጎን ለጎን የታላቁ ተጋድሎ የመጨረሻ ቀናት ክስተቶችን ተከትሎ በምድር ላይ አስከፊ ምስቅልቅሎች እውን ከመሆናቸው አኳያ፣ ከዚህ ልንወስድ የምንችለው የተስፋ መልእክት ምንድን ነው?
መዝሙር 46 በዕብራውያን መጽሐፍ—ስለ አንድ የበለጠ ወይም የላቀ
ነገር የቀረበን ጭብጥ የሚነካ ይመስላል። የሱስ ከምድራዊ ሊቀ ካህናት የበለጠ
ነው፤ የእርሱ መሥዋዕትነት ከእንስሳት መሥዋዕት ሁሉ የላቀ ነው፤ ሰማያዊው
መቅደስም እንዲሁ በምድር ላይ ካሉ ምሳሌዎች የላቀ ነው።
በዚህ የመዝሙር መጽሐፍ ክፍል ለየት ያለ አመለካከት ይስተዋላል። ባለ
መዝሙሩ መልካም ነገሮችን እየወሰደ ከተሻሉ ነገሮች ጋር አያነጻጽርም። የአርሱ
ንጽጽር በአመጻ ያለችው ዓለም—ከሚከተላት አስከፊ መዘዝ እና እግዚአብሔር
ለእኛ ካቀዳቸው አዎንታዊ ተስፋዎች አኳያ ነው።
በእርግጥ ይህ የመዝሙር መጽሐፍ ክፍል በተስፋና በቃል ኪዳን የተሞላ
እንደመሆኑ ሊያጋጥሙን በሚችሉ ውድመቶች፣ ፈተናዎች፣ መከራ እና ጦርነት
ውስጥም እንኳ “ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ” (መዝ. 46፡
10) እንደሚለው፣ እንደ ቃሉ ስናርፍ፣ አንድ ቀን ይህ ሁሉ አክትሞ እግዚአብሔር
“በምድር ላይ ከፍ ከፍ” (መዝ. 46፡10) እንደሚል ማረጋገጫ ተሰጥቶናል።
ይህን ጥቅስም እንዲሁ ልብ ይበሉ፡ “ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ እንኳ፣
ተራሮችም ወደ ባሕር ጥልቅ ቢሰምጡ አንፈራም።” (መዝ. 46፡2)።
በዳግም ምጽአቱ ወቅት ገቢራዊ የሚሆኑ ትዕይንቶችን በአእምሮአችን
ከማኖር በዘለለ ሌላ ማድረግ የምንችለው አይኖርም፡ “ሰማይ እንደ ጥቅልል
መጽሐፍ ተጠቅልሎ ዐለፈ፤ ተራሮችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወገዱ”
(ራእ. 6፡14)። ይህ “ደግሞም የእግዚአብሔርን ቀን እየተጠባበቃችሁ
መምጫውን ልታፋጥኑ ይገባል። በዚያን ቀን ሰማያት በእሳት ተቃጥለው ይጠፋሉ፤
የሰማይም ፍጥረት በታላቅ ትኵሳት ይቀልጣል” (2ጴጥ. 3፡12)። አሁን
ያለንባት ምድር፣ ዙሪያ ገባዋን ከሞላው ክፋት ጋር ለዘላለም አትዘልቅም። ውሎ
አድሮ የሚመጣው ነገር፣ አሁን አእምሯችን መርምሮ ሊረዳ የማይችለውን ተስፋ
ይሰጠናል። ለአሁን ግን፣ እምነታችንን ጠብቀንና በእግዚአብሔር ካገኘነው መገለጥ
በተለይ ከየሱስ መስቀል ጋር ራሳችንን ልናስተሳስር ይገባል።
በዚህ ዓለም የቱንም ያህል መጥፎ ነገሮች ቢኖሩም (እየከፉ እንደሚሄዱም
እናውቃለን) ስለ እግዚአብሔር መልካምነት፣ ኃያልነት እና ባሕሪ ካሎት ዕውቀት
አኳያ ሊስሉ የሚችሉት ተስፋ ምንድን ነው?
በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘው አብዛኛው ቋንቋ ጥቅም ላይ
የዋለው ምሳሌያዊ በሆነ አቀራረብ ነው። ይሁን እንጂ ምድራችን እንደገና መታደሷን
የሚጠቁመውን ቋንቋ ምሳሌያዊ ነው ብለን እንድናምን የሚገፋፋን ምንም ምክንያት
አይኖርም። ምድር በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ክፉኛ እንደምትታወክ መዝ. 46
ያስታውሰናል። ሆኖም በትዕይንቱ የሚታወኩት ዓለቶች እና ውቂያኖሶች ብቻ
አይሆኑም፤ የምድር ታሪክ ታላቁ መደምደሚያ የዓለማዊ መንግሥታት መፍረክረክ
ነው—ለሺዎች ዓመታት መጠነ ሰፊ መከራና ሥቃይ ያስከተሉ አሳዛኞቹ የሰው ልጅ
አስተዳደራዊ ሥርዓቶች መፈራረስ!
በመጨረሻም እነዚህን ሁሉ ኃይሎች ጨምሮ፣ በሰው ልጆች ላይ ያደረሱት
ክፋት እና ሥቃይ በሙሉ ወደ ፍጻሜ ይመጣል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ኤር. 4፡23-26። “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” (ራእ. 2፡
11) እስኪገለጥ ቢያንስ ስለዚህች ምድር ዕጣ ፈንታ ምን ይነግረናል?
በዚህች ምድር ላይ የሚሆነውን አስመልክቶ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች
የሚያሳዩን ነገር አለ። ለምሳሌ የዳን. 7 ራእይ ዓለምን የሚገዙ ሉዓላዊ
መንግሥታት የሚነሡበትን የባሕር መናወጥ ያሳየናል። የሁከትና የጦርነት ነፋሳት
በመላው የአረማውያን ባሕር (ምድር) እየነፈሱና አንዱን ዓለማዊ መንግሥት
ሽረው በሌላኛው እየተኩ መውተርተራቸውን ቢቀጥሉም፣ አንዳቸውም ቢሆኑ
ሰብዓዊውን ዘር እያዋከቡ የሚገኙትን ተጨባጭ ችግሮች መፍታት አልሆነላቸውም።
ሁሌም እንተማመንባቸው ዘንድ የምንዳዳው ዓለማዊ መሪዎች፣ እንደ ሌሎቻችን
ሁሉ ኃጢአተኞችና ራስ ወዳድ ከመሆን የዘለሉ ሆነው አያውቁም።
ለዳንኤል ከተገለጹት መንግሥታት መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ
ለእግዚአብሔር ሕዝቦች አስተማማኝ መጠጊያ ሆነው አልተገኙም (አንዳንዶቹ
ከሌሎቹ የተሻሉ ሊሆኑ ቢችሉም)። እኛ ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች
መሆናችንን እናውቃለን (ፊልጵ. 3፡20)። ደግሞም ከዚህ ውጥንቅጥ ዓለም
ባሻገር የማይናወጥ ዙፋን አለ (ሕዝ. 1፡26)። ወደ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት
እየተቃረብን በመጣን ቁጥር ዓለም ጥልቅ ወደ ሆነ የሥርዓት መፋለስ እንደምትገባ
የሱስ አስተምሯል (ማቴ. 24)። ነገር ግን የምድራችን ሁኔታ ምንም ይሁን
ምን ችግሮች ተቋቁመንና በእምነት ጸንተን መቆም እንችላለን። ምክንያቱም ነገሮች
ከእግዚአብሔር ቁጥጥር ውጪ አለመሆናቸውንና እርሱ የገባውን ቃል የሚጠብቅ
አምላክ መሆኑን እናውቃለን። “ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታትም ወደቁ፤
ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች። የሰራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤
የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።” (መዝ. 46፡6-7)። ሕይወት በምድር
ብቻ ሊቀጭ—ያ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን ለየሱስ ምስጋና ይግባውና ጉዳዩ ከዚያ
ፍጹም የተለየ ሆነ።
ዓለማችን በሁከት የታመሰች እና ሥርዓተ አልበኝነት የነገሠባት የመሆኗ
ጉዳይ የአደባባይ ምስጢር ነው። ለአብነት ያህል በዳን. ምዕ. 7 ላይ የሚገኘው
ትንቢት በታማኝነት መመላለሳችንን ከቀጠልን ነገሮች ውሎ አድሮ መልካም ገጽታ
ይዘው እንደሚከሰቱ እንዴት መመልከት እንደምንችል ይረዳናል?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ መዝ. 47፡ 1-4። ጥቅሶቹ ውሎ አድሮ በክርስቶስ መንግሥት ስለሚኖረን ስፍራ ምን ይላሉ?
እነሆ ረጅም ዘመናትን አልፎ የሚሻገረው የወደፊቱ ተስፋ
ብሩህ ነው። እስከዚያው ግን የሰው ልጅ ምድርን የመግዛት ሥልጣኑን
ለሉሲፈር አሳልፎ ሰጥቷል። ሰይጣን የኢዮብን አጀንዳ ይዞ በሰማያዊው
ጉባዔ በተገኘበት ወቅት ይህች ምድር የእርሱ እንደሆነች በትዕቢት ሲናገር
ተደምጧል፡ “እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ ‘ከወዴት መጣህ?’ አለው።
ሰይጣንም፣ ‘በምድር ሁሉ ዞርሁ፤ ወዲያና ወዲህም ተመላለስሁባት’
ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ።” (ኢዮ. 1፡7)።
ሰይጣን የባለቤትነት መብቱን እያወጀ ነበር፡ በጥንት ጊዜ መመላለስ
የተሰኘው አባባል ባለቤትነትን ለመወከል ጥቅም ላይ ይውል ነበር። “ ‘እንግዲህ
ምድሪቱን ስለምሰጥህ ተነሣ፤ በርዝመቷም፣ በስፋቷም ተመላለስባት።’ ” (ዘፍ.
13፡17) ሲል እግዚአብሔር አብርሐምን አዘዘው።
ጥቅሶቹን ያስተያዩ፡ 1ተሰ. 4፡13-17፣ ዘካ. 14፡4። በመልእክቶቹ እንደቀረበው
ለክርስቶስ እግሮች መረገጫ ትኩረት ይስጡ። በእነዚህ ሁለት ጥቅሶች መካከል
ምን ልዩነት ይመለከታሉ? እነዚህ ሁለት የተለያዩ ግን ዝምድና ያላቸው
ገጽታዎች—በመጨረሻ ገቢራዊ በሚሆነው የክርስቶስ በዚህ ምድር ሉዓላዊ መሆን
ምን ያስተምሩናል
ክርስቶስ ከትንሳኤው በኋላ ባረገበት፣ መላእክትም የመመለሱን ተስፋ
በደገሙበት በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ወረደ። ነብዩ እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔርም
አምላኬ ይመጣል ቅዱሳኑም ሁሉ ካንተ ጋራ።"፤ “በዚያም ቀን እግሮቹ በየሩሳሌም
ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ. እጅግም
ታላቅ ሸለቆ ይሆናል።" "እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ይነግሳል፤ በዚያ ቀን
እግዚአብሔር አንድ ይሆናል፣ ስሙም አንድ (there shall be one
lord, and his name one)" [ዘካ 14÷5፣4፣9]። አዲሲቱ
የሩሳሌም፣ በሚያስገርም ውበትዋ ከሰማይ ስትወርድ ጸድቶና ተዘጋጅቶ በሚቀበላት
ስፍራ አረፈች፤ ከዚያም ክርስቶስ ከሕዝቦቹና ከመላእክቱጋር ወደ ቅድስቲቱ ከተማ
ገባ።” (ታላቁ ተጋድሎ፡ ገጽ 757)።
በየሱስ ስለተሰጠን የተስፋ ቃል ይመልከቱ። ሁሉም ነገር ለዘላለም በሞት
ቢደመደም ኖሮ ሕይወት ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችል አሰብ ያድርጉ።
ሁሉም ከንቱ ሆኖ ይቀር ነበር—አይደል?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ መዝ. ምዕ. 75፣ ማቴ. 26፡26-29፣ ራእ. 14፡9-12።
ይህ የመዝሙር ክፍል በፍርድ ዙሪያ ለሚነሱ አንዳንድ ጥያቄዎች ምን ይላል?
ሌሎቹ ጥቅሶችስ እነዚህን ጉዳዮች ለማስተዋል እንዴት ይረዱናል?
አንዳንዶች ይህ መዝሙር የተዘመረው የሰናክሬም ሠራዊት ታምራዊ በሆነ
መንገድ ከተደመሰሰ በኋላ ነው ይላሉ (2ዜና 32፡፣ 2ነገሥ. 19)። ሆኖም
ታሪኩ ወደፊት በኃጥአን ላይ የሚደርሰውን በራእ. 20 የቀረበውን የመጨረሻ
ውድመት የመሚያመላክት ይመስላል። የእግዚአብሔር ሕዝቦች በቅድስቲቱ ከተማ
ከጻድቁ ንጉሣቸው ጋር እያሉ፣ የክፉ ሠራዊት ወጥቶ ይከብባቸዋል፤ ከዚያም በራሱ
በእግዚአብሔር ይደመሰሳሉ።
እግዚአብሔር በሚሰጠው ፍርድ ከሚያርማቸው ነገሮች መካከል አንዱ፣
በዚህች በወደቀች ምድራችን እየተፈጸመ ያለውን ቅጥ ያጣ የሥልጣን ምዝበራ
መልክ ማስያዝ ነው። በኃጢአት የወደቀው ሰብዓዊ ፍጡር ለገዛ ጥቅሙ እንጂ
ለሌሎች ወይም ለእግዚአብሔር ክብር አይኖርም። ዛሬ በአጽናፈ ዓለም አንዳችም
ትርጉም ያለው ወይም ተጨባጭ የሥነ ምግባር መስፈርት የለም የሚለውን እሳቤ
ለማመን መምረጣችን ያስከተለብንን መዘዝ በብዙ መንገድ እየኖርነው እንገኛለን።
ነገር ግን ትርጉም አለው የምንል ከሆነ፣ ፈላስፋው ፍሬድሪክ ኒቼ አጽንኦት ሰጥቶ
እንደተናገረው፣ የአጽናፈ ሰማይ ሕልውና ለገዛ ጥቅማችን እንደተሰየመ አድርገን
ማስመሰል ይኖርብናል። ይህ ሲሆን እያንዳንዱ ግለሰብ—እርሱ ወይም እርሷ
ራሳቸውን እንደ አማልክት በመቁጠር ይመላለሳሉ።
(አንድ ሰው፡ ይህ ፍልስፍና ለራሱ ለኒቼ ምን ያህል መልካም ውጤት
አስገኝቶለታል? የሚለውን ጥያቄ ቢጠይቅ ተገቢ ይሆናል። እንደ እውነቱ ከሆነ ጥሩ
አልነበረም። ፈላስፋው ኒቼ አንድ ሰው ፈረሱን ለመግራት ሲመታው፣ ለማስቆም
ከሞከረ በኋላ የአእምሮ ቀውስ ገጥሞት በጣሊያን ጎዳናዎች ላይ ወደቀ። ፍሬድሪክ
ኒቼ በ1900 እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ለቀጣዮቹ 11 ዓመታት በከፊል የማይናገርና
የማይንቀሳቀስ ነበር።
ችግሮች የቱንም ያህል የከፉ ሊሆኑ ቢችሉም እንኳ፣ እኛ እንደ አማኝ
በተስፋ እየተመላለስን ዛሬ በምናያቸው ክስተቶች፣ መጪው ጊዜ ላይ እንዳንፈርድ
ተጠርተናል። የሥልጣኔ ምሰሦዎች—ከአምላክ የለሾቹ ወይም መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ያልሆነ አምላካዊ አመለካከት ከሚያራምዱ ሰዎች ልብ እና አእምሮ ውስጥ
ያለማቋረጥ እየተሸረሸሩ ሲሄዱ ስንመለከት በቀላሉ ተስፋ ልንቆርጥ እንችላለን።
ዛሬ እየኖርን ያለነው፣ ከሥነ ምግባር እሴቶች መካከል እንደውም መሠረታዊ
የሆነው የሰብዓዊው ፍጡር ጾታ ማለትም ወንድ እና ሴት፣ ቢያንስ በአንዳድ የዓለም
ክፍሎች ጥቃት ላይ በወደቀበት ዘመን ነው። በርካቶች በስውር እንኳ ሊያወሯቸው
የማይደፍሯቸው አንዳንድ የሥነ ምግባር እርክስናዎች ዛሬ በአደባባይ አድናቆትና
ጭብጨባ ሲቸራቸው እየታዘብን እንገኛለን። ነገሮች ምን ያህል እየከፉ እንደሄዱ
እነዚህ በራሳቸው ማሳያ ናቸው።
ምንም እንኳ ሕይወት ለሌሎች የተሻለ ይሆን ዘንድ እኛ ዛሬ የበኩላችንን ድርሻ
መወጣት ቢኖርብንም፣ በመጨረሻ ሁሉም ነገር በመለኮት እንደ አዲስ ከመፈጠሩ
አስቀድሞ፣ በዚህ አሁን ባለው ዓለም ላይ ሙሉ ውድመት እየደረሰ መሆኑን
ማስታወስ ሁሌም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ መዝ. ምዕ. 67። ይህ የምስጋና መዝሙር በራእ. 14፡ 6-12 የቀረበውን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሚና ለማተዋል እንዴት ይረዳዎታል?
ኤም. አይ. ቲ. በመባል የሚታወቀው የምርምር ተቋም መሐንዲሶች
አንድ አዲስ ነገር ፈልስፈዋል። የምርምራቸው ውጤት እንደሚያመለክተው፣
አንድን ዕቃ እነርሱ የፈለሰፉትን ጥቁር ቀለም ሲቀቡ፣ ቀለሙ ዕቃውን እንዳይታይ
አድርጎ ይሰውረዋል። ናኖቲውብሰ ከሚባሉ ንጥረ ነገሮች የተሠራው ይህ ጥቁር
ቀለም ከዚህ ቀደም በምርምር ከተፈጠረ ማንኛውም ጥቁር ቀለም በብዙ እጥፍ
ይጠቁራል። ይህ አዲስ ነገር 99.995 ከመቶ ብርሃንን መጥጦ ማስቀረት
ይችላል። በጣም ደማቅ ብርሃን እንኳ፣ በዚህ ጥቁር ቀለም በተቀባ ዕቃ ላይ
ቢፈነጥቅ ዕቃውን ማሳየት አይችልም።
መዝሙር 67 “እግዚአብሔር… ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ መንገድህ
በምድር ላይ… ይታወቅ ዘንድ።” ብሎ ይጀምራል። እግዚአብሔር በደኅንነት እቅድ
አማካኝነት ኃጢአተኞች ከክብሩ የተነሣ ሳይጠፉ ወደ እርሱ መገኘት የሚቀርቡበትን
መንገድ የቀየሰ ሲሆን፤ ዛሬም እንኳ በዚህ ሕይወት፣ የእግዚአብሔር ፊት በእኛ ላይ
ያበራ ዘንድ የክርስቶስ መስቀል አስችሏል።
ሌላም ነገር አለ፡ እግዚአብሔር ብርሃኑን ለተቀረው ዓለም እንድናንጸባርቅ
ይፈልጋል። ለእስራኤል የተሰጠው ተግባር ይህ ነበር፡ ቤተ መቅደሱ ለአሕዛብ
ሁሉ የጸሎት ቤት መሆን ነበረበት፡ “ ‘ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤
በጸሎት ቤቴም ውስጥ ደስ አሰኛቸዋለሁ። የሚቃጠል መሥዋዕታቸውንና ሌሎች
መሥዋዕቶቻቸውን፣ በመሠዊያዬ ቢሠዉ እቀበላቸዋለሁ፤ ቤቴ፣ ለሕዝቦች ሁሉ
የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።” (ኢሳ. 65፡7)።
በዚህ የመዝሙረ ዳዊት ክፍል እግዚአብሔር መንገዱ በምድር ላይ
ይታወቅ ዘንድ ፍላጎቱ መሆኑን (መዝ. 67፡2) ዳዊት ሊያሳስበን ይፈልጋል።
የእግዚአብሔር ሕዝቦች በዚህ ኃላፊነት ዙሪያ በተደጋጋሚ ሲወድቁ መታየታቸው
የሚያሳዝን ነው። የብሉይ ኪዳኑ የእስራኤል ታሪክ ከአዲስ ኪዳኑ የ2ሺ ዓመታት ጉዞ
በተመሳሳይ አንዳንድ በጨለማ የተዋጡ ምዕራፎችን ይዟል። እናም፣ እግዚአብሔር
አንጸባራቂውን የብርሃኑን ጸዳል ወደ እኛ ቢልክም፣ እኛ ግን ያን ብርሃን ለሌሎች
በማንጸባረቅ ፋንታ ውስጣችን እንዲቀር የሚያደርግ ጥቁር አዚም ልቦቻችንን
የቀባን ይመስላል።
አንዳንዴ፣ የእግዚአብሔር የመጨረሻ ቀን ንቅናቄ ሕዝብ ራሳችንን እንደ
መንፈሳዊ ልዑላን ወይም የተመረጠ፣ የተደላደለና የላቀ መንፈሳዊ ማስተዋል
የተቸረው፣ ከፍ ያለ ተሞክሮ ወይም ደረጃ የተቆናጠጠ ባለ ልዩ መብት የአየር
ተጓዥ አድርገን የምንቆጥር ሲሆን፤ በመንፈሳዊው ነገር እምብዛም ያልተዘጋጀው
ዓለም ግን ምቾት በጎደለው—የአውሮፕላን ማረፊያ ተሳፋሪዎች ከዋናው የመነሻ
አዳራሽ ወደ አውሮፕላኑ የሚሸጋገሩበት ጫጫታ የበዛበት ስፍራ በመቀመጡ—
ደስተኞች የሆንን እንመስላለን። ነገር ግን የራእ. 14 ትሩፋኗ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ
ከክርስቶስ ጋር በጽዮን ላይ በመቆማቸው ብቻ ደስተኞች አይደሉም። ይልቁንም፣
የዓለም ሕዝቦች በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ይቀላቀሏቸው ዘንድ እየተማጸኑ
በመላው የምድር ገጽ ይበርራሉ።
እኛ እንደ ቤተ ክርስቲያን እና እንደ ግለሰብ አብልጠን የምንወደውን እውነት
ለሌሎች ለማስተማር ምን ዓይነት ግዴታ ሊሰማን ይገባል?
የሚከተሉትን ያንብቡ፡ መዝ. 133፣ ሐዋ. 1:4–9፣
ራእ. 5:4–7።
“ምንም እንኳ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ቀደም ባሉት የኃይማኖት አባቶች
ዘመን በተለየ መንገድ ይገለጽ የነበረ ቢሆንም፤ በሙላት የወረደበት ሁናቴ
ተስተውሎ አያውቅም። አሁን፤ የአዳኙን ቃል የታዘዙት ደቀ መዛሙርት ስጦታዎቹን
ይቀበሉ ዘንድ ልመናቸውን ወደ እርሱ ሲያቀርቡ፤ በሰማይ ክርስቶስ ምልጃውን
አከለላቸው። መንፈስ ቅዱስን በሕዝቡ ላይ ያፈስላቸው ዘንድ ይህን የመንፈስ
ስጦታ እንደሚሰጣቸውም አረጋገጠላቸው።”—Ellen G. White, The
Acts of the Apostles, p. 37.
ደቀ መዛሙርት የክርስቶስን ዳግም ምጽአት የሚያውጅ ሥራ እየሠሩ “
‘እስከ ምድር ዳርቻ’ ” ለክርስቶስ ምስክር እንዲሆኑ ተጠርተው ነበር (ሐዋ.
1፡8)። እኛም ይህን በእነርሱ የተጀመረ ሥራ መቀጠል ይኖርብናል።
ክርስቶስ ወንጌልን ለዓለም እንድናደርስ ሲነግረን ብቻችንን አልተወንም።
ሥራውን የሚመራው ከሰማያዊው ቤተ መቅደስ ሆኖ ነው። በመሆኑም የእኛ
ኃላፊነት ከክርስቶስ ጋር በጥብቅ መቆራኘት ነው። ይህ ሲሆን ከእርሱ ምሪትና
ኃይል እንቀበላለን። ሥራው የእኛ ሳይሆን የእርሱ እንደመሆኑ ምሪቱን እንድንከተል
ተጠይቀናል። ይህ ደግሞ እንዴት ለእስራኤል እንደሠራ ስንመለከት—እግዚአብሔር
የእርሱን መመሪያዎች እንዲከተሉ ጠየቃቸው፣ ከዚያም የማይቻለውን አደረገ።
መንፈሱ በባልንጀሮቻችን ልብ ውስጥ እየሠራ እንደሚገኝ አንርሳ። ሆኖም ወደ
ውሳኔ የሚመጡበት ወቅት ሲቃረብ ከጎናቸው እንድንሆን የተጠራነው ከበጉ ጋር
በጽዮን የሚቆሙትን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ይቀላቀሉ ዘንድ ነው። የሥራው
ባለቤት እርሱ ራሱ እንጂ እኛ ሆነን ስለማናውቅ፣ አዳዲስ ዘዴዎችንና አሠራሮችን
መፈልሰፍ አይጠበቅብንም።
1. ምንም እንኳ የሦስቱ መላእክት መልእክቶች በመላው ዓለም ቢሰራጩም
ምንም እንኳ የሦስቱ መላእክት መልእክቶች በመላው ዓለም ቢሰራጩም
ነገር ግን ይህ እውነት ያልደረሳቸው በርካቶች አሉ። ክርስቶስ እቅዱን
ለማሳካት እኛን እየተጠቀመ ከመሆኑ አኳያ፣ እንደ ቤተ ክርስቲያን እርሱ
የሰጠንን ኃላፊነት እንዴት ከግብ ማድረስ እንደምንችል ተወያዩ። እነዚህን
የመጨረሻው ዘመን እውነቶች አያሌ ሕዝቦች ያለመስማታቸው ሐቅ ተስፋ
ሊያስቆርጠን እንደማይገባ እንዴት መማር እንችላለን?
2. በራእ. ምዕ. 5 በጉ በማኅተም የታሸገውን ጥቅልል ለመፍታትና መጽሐፉን
በራእ. ምዕ. 5 በጉ በማኅተም የታሸገውን ጥቅልል ለመፍታትና መጽሐፉን
ለመክፈት የተገባው በመሆኑ ለእርሱ እንደተሰጠ እናነባለን። በራእ. 6
እንደቀረበው፣ የመጽሐፉ ማኅተሞች ሲፈቱ፣ የአዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያንን
ታሪክ እስከ ዘመኑ ፍጻሜ በግልጽ ሲተነብይ እንመለከታለን። እግዚአብሔር
ሥራውን ለመጨረስ ስላሰበበት መንገድ ከዚህ መግለጫ የምንማረው
ትምህርት ምንድን ነው?
3. በራእ. ምዕ. 13 እና 14 ትንቢት መሰረት እየመጣ እንደሆን
በራእ. ምዕ. 13 እና 14 ትንቢት መሰረት እየመጣ እንደሆን
ወደምናውቀው—በቀላሉ መምራት የሚችሉዛሬ በዓለም ዙሪያ
ወደምናውቀው—በቀላሉ መምራት የሚችሉዛሬ በዓለም ዙሪያ
የምንመለከታቸው ክስተቶች ምንድን ናቸው? የተቀሩት እንቅፋቶችስ
ምንድን ናቸው?