የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 10:1–12፣ ዘፍ. 12:1–9፣ 1ሳሙ. 8:4–18፣ ማቴ. 20:25–28፣ ራእ. 18:1–4።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ ‘ሥልጣን፣ ክብርና ታላቅ ኀይል
ተሰጠው፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፣ መንግሥታትና ሕዝቦች
ሰገዱለት፤ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ
የማይጠፋ ነው።’ ” (ዳን. 7፡14)።
የራእይ መጽሐፍ እግዚአብሔር ለወደቀው ዓለም የሰጠውን መፍትሔ
ያሳየናል። በመጨረሻዎቹ ምእራፎች እንደተመለከተው፣ እንደገና ወደ
ሕይወት ዛፍ መድረስ በመቻሉና እርግማኑ በመነሣቱ በእግዚአብሔር
ፊት ዳግም ተቀባይነት ማግኘት ሆኖልናል። የራእይ መጽሐፍ በአንዳንድ ይዘቶቹ
የዘፍጥረት መጽሐፍ ግልባጭ ሆኖ እናገኘዋለን። የዓለም ችግሮች እንዴት መጀመሪያ
እንደተፈጠሩ ለመረዳት ዘፍጥረት ቁልፍ መሣሪያ የሆነው በዚህ የተነሣ ነው።
በዳንኤልም ሆነ በዮሐንስ ራእይ ውስጥ ከተካተቱት ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ፣
ሰብዓዊው መንግሥት የእግዚአብሔር ሕጋዊ ንብረት የሆነችውን ዓለም በቁጥጥሩ
ስር ለማዋል በተከታታይ እያደረገ ያለውን ጥረት ያሳየናል። ሆኖም ይህ አስከፊ
የኃጢአትና የዓመጽ ምዕራፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለዘላለም ከተዘጋ በኋላ፣
ውሎ አድሮ ምድር በጽድቅ የምትገዛ ይሆናል።
በሺዎች የሚቆጠሩ የረጅም ዘመናት የሰብዓዊው ፍጡር መንግሥታዊ
ሥርዓተ ሙከራ ሂደት ወደዚህ የመጨረሻ ምዕራፍ ያደርሳል። በዚህ ሂደት ታላላቅ
የተባሉ ጽንሰ ሀሳቦች እንኳ ሳይቀሩ ሁሌም ክሽፈትን ከማስተናገድ በዘለለ የፈየዱት
አንዳች ነገር የለም። ለሺዎች ዓመታት የተስተዋለው አብዛኛው የሰው ልጅ ታሪክ ሌላ
ሳይሆን እነዚህ የከሸፉ ሥርዓቶች በእኛ ላይ ያደረሱትን አሳዛኝ ክስተቶች የሚተርክ
ነው። በመጨረሻ፣ የእግዚአብሔር “ዘላለማዊ መንግሥት” (ዳን. 7፡27)
እስከሚመሠረት ድረስ ሰብዓዊው መንግሥት እየከፋ እንጂ እየተሻለ አይሄድም።
ኤደን ለሰው ልጆች ተስማሚ መኖሪያ ሆና ተፈጠረች። ሆኖም አንዴ ኃጢአት
ከገባ በኋላ፣ እግዚአብሔር ሰብዓዊውን ፍጡር ቢያንስ ለጊዜው ከአትክልቱ ስፍራና
ከሕይወት ዛፍ ከመለየት ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረውም።
ከገነት ውጪ የሰው ልጆች ለቀጣዩ ሕልውና የሚያስፈልጋቸውን ማሟላት
ይችሉ ዘንድ ጠንክሮ መሥራት ይጠበቅባቸው ነበር። ሕይወት ከበደ፤ በሥቃይና ጥረን
ግረን በግንባራችን ላብ መኖር ግዴታችን ሆነ (ዘፍ. 3፡16–19)። የመጀመሪያዎቹ
ወላጆቻችን ሕጋዊው ንጉሥ ወደ ገነት የሚመለሱበትን መንገድ እንደሚያዘጋጅ እምነት
ነበራቸው። እናም እግዚአብሔር ገና በመጀመሪያ ለወደቀው ዓለም የሰጠውን ቤዛነት
በታማኝነት ተስፋ በማድረግ እነሆ መሥዋዕቶቻቸውን ወደ ኤደን ደጃፍ አቀረቡ።
“ሰብዓዊው ፍጡር አስደሳች ከሆነው የዔደን ገነት ከተባረረ በኋላም እንኳ
ዔደን ለረጅም ጊዜ በምድር ላይ ይታይ ነበር… አዳም እና ልጆቹ እግዚአብሔርን
ለማምለክ ወደዚህ ስፍራ በመቅረብ በመተላለፋቸው ምክንያት አሁን በዐይን ብቻ ከሚያዩት ዔደን ገነት ያስወጣቸውን ሕግ ለመጠበቅ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ገቡ። ኋላ ላይ የምግባረ ብልሹነት ማዕበል ዓለምን ሲመታና የሰዎች በጥፋት ውሃ
መውደም ሲወሰን ዔደን ገነትን ያስቀመጣት አምላክ ከምድር ላይ አነሣት። ነገር
ግን በመጨረሻው ቀን “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” (ራእይ 21፡1) ሲገለጥ፤
መጀመሪያ ከነበራት ሞገስ በላይ እጥፍ ድርብ ውበት ተጎናጽፋ እነሆ ዳግመኛ
ትመጣለች።” (የኃይማኖት አባቶች እና ነቢያት ገጽ፡ 57-58)
ሌሎች ግን፣ ለአዳዲሶቹ ችግሮቻችን ሰው ሠራሽ “መፍትሔዎች” ለማግኘት
መሥራታቸውን ገፉበት። በዚህም ምናልባት በኤደን የታጣውን መልሶ ለማግኘት
ይረዳል ያሉትን እና ሕይወትን ያቀላል ብለው ያሰቡትን የከተማ አወቃቀር ለማዋለድ
የሄዱበትን ረጅም ርቀት እንመለከታን።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 10፡1-12። ይህ—መጽሐፍ ቅዱስ ነነዌንና ባቢሎንን
ጨምሮ በተቀረው የመጽሐፉ ክፍል የሚገኙ በርካታ ቁልፍ የፖለቲካ ተዋናይዎችን
የሚያስተዋውቅበት ክፍል ነው። እነዚህ ከተሞች በቀጣይ ስለሚኖራቸው ሚና
ከተነገረን አኳያ ከጥቅሶቹ ምን መገንዘብ እንችላለን?
አንዳንዶች ስለ ናምሩድ ካነበቡ በኋላ ግለሰቡ የአረማዊ አፈ ታሪክ ድል
አድራጊ ጀግኖች ዓይነት ስመ ጥር ጀግና ነው ወደሚል ድምዳሜ ደርሰዋል። መጽሐፍ
ቅዱስ “በምድር ላይ ኃያል ሰው” እና “በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ አዳኝ” ብሎ
እርሱን ሲገልጽ፣ እያመሰገነው አልነበረም። ናምሩድ በራሱ ግምት ታላቅ ሰው
ሲሆን፤ በጌታ ፊት የቆመው ለእርሱ ንቀት በማሳየት ዓይነት ስሜት ነበር። ከእነዚህ
ጥቅሶች የምንመለከተው በእግዚአብሔር ላይ የተነሣው አመጽ እየተስፋፋ መሄዱን
ነው። በዚህም ይኸው አመጽ ውሎ አድሮ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስከ ዘላለም
እስኪወገድ ድረስ ይኖራል።
በእግዚአብሔር ላይ የማመጽ ኃጢአት ልንገነዘብ ከምንችለው በላይ ስውር ባህሪ
ያለው ለምንድን ነው? ራሳችንን ከዚህ ሰብዓዊ ባህሪ መጠበቅ የምንችለው
እንዴት ነው?
በኦሪት ዘፍጥረት አሥረኛው ምዕራፍ ስለ ተለያዩ ብሔረሰቦች መወለድ
እንመለከታለን። ብሔር አሕዛብን ለማመልከትም እንዲሁ ጥቅም ላይ ይውላል።
ዘፍጥረት 10፣ የሰው ዘር በነገድ፣ በጎሳ እና በቋንቋ መከፋፈሉን ይነግረናል
(ዘፍ. 10፡5 ራእ. 14፡5)።
ይህ ጽንሰ ሀሳብ ተዋውቆ ብሎም ሥራ ላይ ውሎ ብዙም ሳይቆይ፣ ከእነዚህ
ብሔራት መካከል በአንዱ ውስጥ የነበረው አብራም፣ ከብሔሩም ሆነ ብሔሩ
ከሚወክለው ማንኛውም ነገር ተለይቶ እንዲወጣ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርብለታል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 12፡1-9። አብራም (ኋላ ላይ አብርሃም የተባለው)
ከመጣበት ብሔር ተለይቶ እንዲወጣ እግዚአብሔር ጥሪ ያደረገለት ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር አብርሃምን ተጠቅሞ ሰዎች ከሚያቋቁሟቸው መንግሥታት በተቃራኒ የሚቆም ሕዝብ ለመመሥረት አስቦ ነበር። እነዚህ ሕዝቦች ከራሱ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ ንጉሥ አይኖራቸውም። ይህን ተከትሎ ሰብዓዊው ዘር ወደ ፈጣሪው ቢመለስ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሳየት ነበረባቸው። እስራኤል “በምድር ለሚኖሩ ሕዝቦች” (ዘፍ. 12፡3) ሁሉ በረከት ትሆን ዘንድ ተቋቋመች። እግዚአብሔር ምናልባትም ከጥፋት ውሃ በፊት በምድር ላይ ያልታየ ብርሃን ብሎም ልዩ መብትና ጥቅም ባለቤት አደረጋቸው። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 4፡5-9። እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባለት ኪዳን መሠረት የእርሱ ተስፋ ፍጻሜ ሕዝቦች ለሆኑት የአብርሃም ልጆች ምን እያላቸው ነበር?
ይህ አንድ ግለሰብ ለአንድ የሕብረተሰብ ክፍል ምስክር የሚሆንበት ሳይሆን፣
ይልቁንም መላው ሕዝብ በአንድነት በመሥራትና ከእግዚአብሔር ጋር በመተባበር
አምላካዊውን ባህሪ ገልጾ የሚያሳይበት ነው። እነርሱን ከሌሎች ሕዝቦች የተለዩ
ያደረጋቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ ሰጥቷቸው የነበረው “ሥርዓትና ፍርድ”
ብቻ ሳይሆን፣ ለእነዚህ ለተሰጧቸው የሚኖራቸው ታማኝነት “በእውነቱ ይህ
ታላቅ ሕዝብ የቱን ያህል ጥበበኛና አስተዋይ ነው” (ዘዳ. 4፡6) ብለው ሌሎች
ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ጭምር የሚያደርግ እንደ ነበር ስለ እነርሱ ከተነገሩ
ቃላት ማስተዋል ተገቢ ነው። ለሕዝቡ የተሰጡት እውነቶች የቱንም ያህል አስደናቂ
ሊሆኑ ቢችሉ እንኳ፣ ከእነርሱ ጋር ተስማምተው መኖርና መታዘዝ አለመቻላቸው፣
በበረከትና በሕይወት ፋንታ ሞትና እርግማን ማስከተሉ አይቀሬ ነበር።
እነዚህን እውነቶች ስለ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ስለ መታዘዝም አጽንኦት የሚሰጠው
ያው ተመሳሳይ መርኅ ዛሬም እንደ ዳግም ምጽአቱ ተጠባባቂ ሕዝብ በእኛ ላይ
የሚሠራው እንዴት ነው?
እስራኤል ከመጀመሪያ አመሠራረቷ በተቃራኒ እንደሌሎቹ ብሔራት ሰብዓዊ ንጉሥ ሊኖራት አይገባም ነበር። ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ የእስራኤል እምነት የደረሰበትን መዳከም ተከትሎ አሕዛብ የነበራቸውን ዓይነት “ነገሥታት” አጥብቆ ወደ መሻት ቁልቁለት ወረዱ። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 1ሳሙ. 8፡4-18። ሽማግሌዎቹ ንጉሥ እንዲነግሥላቸው የመፈለጋቸውን ሀሳብ አጓጊ ሆኖ ያገኙት ለምን ይመስሎታል? እኛም የተመሳሳይ ፈተናዎች ሰለባ የምንሆነው እንዴት ነው?
እስራኤላውያን ንጉሥ እንዲነግሥላቸው ጥያቄ ያቀረቡት እግዚአብሔር
ንጉሣቸው እንዲሆን ካለመፈለጋቸው የተነሣ መሆኑን ልብ ይሏል። ቀደም
ሲል በተቋቋመው ሥርዓት መሠረት ሕዝቡ ለፈጣሪ ቀጥተኛ ምላሽ መስጠት
ይጠበቅበት የነበረ ሲሆን፣ ከእርሱ ጋር የነበራቸው ግንኙነት በቤተ መቅደሱ
እና በዚያ ይፈጸሙ ከነበሩ ሌሎች አገልግሎቶች አኳያ ይገለጥ ነበር። ንጉሥ
እንዲነግሥላቸው በመጠየቃቸው፣ የአሕዛብ መንግሥታት በገባሩ መደብ ላይ
ያደርሱ የነበረው ዓይነት ተመሳሳይ መከራ በገዛ ራሳቸው ላይ እንዲደርስ እየፈቀዱ
የነበረ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ ንጉሡ ለጦርነት ለሚሰለፍባቸው ዐውደ ውጊያዎች
ሁሉ በወታደራዊ የግዳጅ ምልመላዎች ውስጥ ማለፍ፣ የንብረት መወረስ፣ ግብር
እና ቀረጥ መክፈል እንዲሁም ሌሎች መከራዎችን ያካተተ ነበር። እነዚህ ሕዝቦች
በእግዚአብሔር ቸርነት ከመገዛት ይልቅ ሰብዓዊ ንጉሥና ልዑላን ለገዛ ጥቅሞቻቸው
በተሻለ የሚቆሙ ሊሆኑ እንደሚችሉ አድርገው አስበዋል።
በተጨማሪ አዲሱ ሥርዓት ዘላቂ ይሆናል። እስራኤላውያንም የጠየቁት
ይሰጣቸዋል። በእጅ የያዙት ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል እንዲሉ፣ የጠየቁት
ነገር የነበራቸውን የሚያሳጣ የቁልቁለት ጉዞ መሆኑን የተገነዘቡ ዕለት የሚኖራቸው
ብቸኛ ምርጫ እዚያው ላይ ተጣብቆ መቅረት ብቻ ይሆናል። “ ‘ያም ቀን
በደረሰ ጊዜ፣ ወዳችሁ ከመረጣችሁት ንጉሥ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ ነገር ግን በዚያ
ቀን እግዚአብሔር አይመልስላችሁም’ ” (1ሳሙ. 8፡18)።
የሕዝቡን ድክመት አስቀድሞ የሚያውቀው አምላክ እስራኤላውያን ሰብዓዊ
ንጉሥ እንዲነግሥላቸው እንደሚጠይቁ ቀደም ብሎ በትንቢት ተናግሯል። የጠየቁትን
ያገኙ ሲሆን፣ አብዛኛው አምልኮ ነክ ቅዱስ ታሪክ የዚያ ምርጫ ውጤት ጥንቅር ነው።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 17፡14-20። እግዚአብሔር “ንጉሥ
እሰጣችኋለሁ” እንዳላለ፣ ነገር ግን ሕዝቡ ንጉሥ ይኖረው ዘንድ ቁርጠኛ መሆኑን
ልብ ይሏል። የሕዝቡና የነገሥታቱ ታሪክ እንደሚያሳየው እግዚአብሔር ሕዝቡን
ከአንዳንድ ሰብዓዊ ነገሥታት እኩይ ተግባራት ለመታደግ ጥበቃ ያደርግላቸው የነበረ
ቢሆንም፣ ነገር ግን ጥበቃዎቹና ከለላዎቹ ብዙውን ጊዜ ችላ ይባሉ ነበር።
ሕዝቡ ንጉሥ እንዲኖረው ከወሰነበት ጊዜ አንስቶ በነገሥታቱ ዘመን ነገሮች ምን
ያህል እየከፉ እንደሄዱ ለማየት የእስራኤልን ታሪክ መመልከት ብቻውን በቂ ነው። ምንም
እንኳ አንዳንድ ነገሥታት ከሌሎቹ የተሻሉ ሆነው ቢገኙም፣ “መልካም” የተባሉት ሳይቀሩ
ስህተት ሠርተዋል (ዳዊትን እና ቤርሳቤህን ያስቡ)። ባብዛኛው እንደተመለከተው፣
ሕዝቡን የሚገዙ ነገሥታት በተተካኩ ቁጥር “በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት”
ይፈጽሙ ነበር። (1ነገሥ. 11:6፣ 15:26፣ 16:30፣ 2ነገሥ. 3:2 ወዘተ)።
በዚያን ዘመንም ሆነ ዛሬ፣ ሁሉንም ሰብዓዊ መንግሥታት በአንድ የሚያመሳስላቸው
ነገር ያለ ሲሆን፣ ይኸውም ኃጢአተኞችን የሚገዙ ኃጢአተኞች መሆናቸው ነው።
ሁኔታው እየከፋ እንጂ እንደታሰበው ወይም እንደተጠበቀው ሊሄድ ይችላል?
እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የነበረው ግንኙነት ከአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ጋር ላለው ግንኙነት በርካታ ጥልቅ ግንዛቤዎችን ያስጨብጣል። እንዲያውም እስራኤል ለቤተ ክርስቲያን ስህተቶች እንደ ማስጠንቀቂያ በመሆን በብዙ መንገዶች አገልግላለች። ከጥንት እስራኤላውያን በላቀ መንፈሳዊነት ላይ እንገኛለን ብለው አፋቸውን ሞልተው መናገር በማይችሉበት ርቀት የሚገኙት ክርስቲያኖችም እንኳ፣ ዛሬም ለተመሳሳይ ፈተናዎች ስስና በቀላሉ ተጠቂዎች ሆኖው ይገኛሉ። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 20፡25-28። ደቀ መዛሙርት ቤተ ክርስቲያንን በማቋቋም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ የሱስ ከምን ዓይነት ስህተት እንዲጠበቁ ነበር ያስጠነቃቸው?
እስራኤል ሰብዓዊ ንጉሥ እንዲሰጣት መጠየቋ፣ በሕዝቡ ላይ የሥነ ምግባር
ውድቀት አስከተለ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ለማረም በባቢሎናውያን ምርኮ ሥር
እንዲወድቁ እስከፈቀደበት ጊዜ ድረስ ነገሥታቱ ያለማቋረጥ የክፋትን ጎዳና ሽምጥ
መጋለባቸውን ተያያዙት።
በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ቢሆን ተመሳሳይ የሆነ ነገር ተከስቷል። ምንም
እንኳ እንደ አሕዛብ ብሔሮች ሁሉ ራሳቸውን ማዋቀር ባይችሉም፣ ቆስጠንጢኖስ
ወደ ሥልጣን መጥቶ ክርስቲያን ነኝ ሲል አማኞች እፎይታ አገኙ። ስደት አሁን
አበቃ! ያ በራሱ በረከት ቢሆንም፣ የንጉሠ ነገሥቱን ሥልጣን ለራሳቸው ጥቅም
ሥራ ላይ ሊያውሉ የሚችሉበት ሁኔታ የተመቻቸ መሰለ።
በአራተኛው መቶ ዘመን ላይ በክርስቲያኖች መካከል በርካታ ወሳኝ
የሚባሉ አለመግባባቶች ተከስተው ነበር። ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ልዮነቶቿን
ለመፍታት የሚያስችል ቁመና ላይ አለመሆኗን በመገንዘቧ ንጉሠ ነገሥቱ ጣልቃ
እንዲገባ ተማጽኖ አቀረበች። ከዚህ ጊዜ አንስቶ በአንድ ወቅት በደረጃ እኩል ከነበሩ
ወንድሞች መካከል በዕድሜ ጠና ያለውና የቤተ ክርስቲያን መሪ የነበረው የሮሙ
ጳጳስ፣ አሁን ከፍ ወዳለ እውቅና ተሸጋገረ። ቤተ ክርስቲያኗ መንግሥት በኃይማኖታዊ
ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀች፣ እናም መንግሥት አንዴ እግሩን ካስገባ
በኋላ፣ ነገሮች ከቀድሞው ወደ ባሰ የከፋ ሁኔታ ተሸጋገሩ።
እንደ ጥንቷ እስራኤል ሁሉ፣ በክርስትና ታሪክ በርካታዎቹ በጽልመት
የተዋጡ ምዕራፎች፣ ቤተ ክርስቲያን ከዓለም ጋር ያደረገቻቸው ቀጥተኛ ሰጥቶ
የመቀበል ውጤቶች ናቸው። እስራኤል ፊቷን ወደ ጣኦት አምልኮ—ብልሹዎቹ
ነገሥታቶቿም በሥልጣን ጥም ሰክረው ሕፃናትን መሥዋዕት አድርጎ እስከ ማቅረብ
እንደ ደረሱ ሁሉ፣ ቤተ ክርስቲያንም ቀስ በቀስ አያሌ የአረማዊ መንግሥታትን
ልምዶችና አሠራሮች በመከተል ስፍር ቁጥር የሌላቸው ታማኝ አማኞች እራሱን
ከመንግሥት ጋር ላቆራኘው ቤተ ክርስቲያናዊ ተቋም እንደ ስጋት በመቆጠራቸው
የሰማዕትነትን ጽዋ ጨለጡ።
በእርስዎ ባህልና ማኅበረሰብ ውስጥ እነዚህ ተመሳሳይ ፈተናዎች የእምነታችንን
ጽኑ አቋም አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉባቸው አካሄዶች የትኞቹ ናቸው?
እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ የመሠረተበት ዋና ዓላማ የተቀረውን
ዓለም ለመኮነን ሳይሆን ለማዳን ነበር። አንዳንዴ ጻድቅ ባህሪ ከፊት ለፊታችን ሲገጥመን
ራሳችንን እንደ ከንቱ በመቁጠር የጠፋን አድርገን ብናስብ አይፈረድብንም።
በተመሳሳይ የእስራኤልም መፈጠር የአጎራባች ብሔራትን ኃጢአትና ራስ ወዳድነት
አጉልቶ የሚያሳይ ነበር። ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምተው የሚኖሩ አማኞች
የጽድቅ ባሕሪውን በጉልህ የሚገልጹ ሲሆን ይህም ጽኑ መሠረት ወዳለው እምነት
ይመራቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ” (ራዕ.
14፡12) ወገኖች ሕይወት፣ የእርሱን ባህሪ እንደ መስታወት ማሳየት ይኖርበታል።
ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ማድረግ የሚገባቸውን ቢያደርጉና የታዘዙትን
ቢፈጽሙ ኖሮ፣ መንግሥታት ስለ እነርሱ እና ስለ አምላካቸው የበለጠ ለማወቅ
በመሻት በሰላም ወደ እነርሱ በመጡ ነበር። ሆኖም ከባቢሎን ምርኮ አሳዛኝ ታሪክ
እንዳሳየው፣ በዚያ ፋንታ እነዚህ መንግሥታት ጦርነት ለመግጠም መጡ።
እርግጥ ነው፣ የእግዚአብሔርን ባሕሪ ፍጹም በሆነ መንገድ ያሳየ ብቸኛው
ሰው የሱስ ነው። ልቦችን እርግጠኛና ጥልቅ በሆነ መንገድ የነካውና ፍጹም የሆነው
የእርሱ ምሳሌነት እነሆ ለሰዎች የቀረበ ግብዣ ነበር (ዮሐ. 3፡16-21)።
እስራኤልን እንደ ሕዝብ የመመሥረት የመጨረሻው ዓላማ፣ እግዚአብሔር
ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረት ከነበረው ዓላማ ጋር ተመሳሳይ ነበር። እርሱ
ኃጢአተኞችን ወደ ክርስቶስ ይስብ ዘንድ ሕዝቡን ለመጠቀም ይናፍቃል። በቤተ
ክርስቲያኑ አማካይነት የሚቀርበው የሦስቱ መላእክት መልእክት ጥሪ ለተመረጡ
ጥቂቶች ሳይሆን “በምድር ላይ ለሚኖሩ ለሕዝብ፣ ለነገድ፣ ለቋንቋና ለወገን ሁሉ”
ነው (ራእ. 14፡6)። ራእ. 18፡1 ክርስቶስ ዳግም ከመገለጡ አስቀድሞ ምድር
ዳር እስከ ዳር በእግዚአብሔር ክብር እንደምታበራ ይተነብያል።
የሚከተሉት ጥቅሶች እግዚአብሔር በምድር ለሚገኙ ለሕዝቦቹ ስላለው እቅድ
ምን ያስተምሩናል? እነዚህን መርኅዎች በሕይወታችን መተግበር የምንችለው
እንዴት ነው?
(ሀ) ዘኁ. 14:17–21
(ለ) ኢሳ. 42:6፣ ኢሳ. 49:6፣ ኢሳ. 60:3
(ሐ) ራእ. 18:1–4
ጥቅሶቹን በድጋሚ ያንብቡ፡ 18፡1-4። ይህ “ሕዝቦቼ” በሚል የተገለጸው፣
የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከባቢሎን እንዲወጡ የቀረበ ጥሪ ነው። ይህ መሆን
የሚችለው እንዴት ነው? በሌላ አነጋገር እኛ፣ እንደ ቤተ ክርስቲያን ከባቢሎን
ውጪ እንደመሆናችን—ዛሬም በባቢሎን ላሉ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ጥሪ
ለማቅረብ እርሱ እንዴት ሊጠቀምብን ይችላል?
ኢሳ. 44፡24-45፡13 “ጥቂት በጥቂት፣ መጀመሪያ
በስውርና በዝምታ፣ ከዚያም ጉልበት ሲያገኝና የሰዎችን አእምሮ መቆጣጠር ሲችል
በገሃድ፣ የኃጢአት ምስጢር፣ የማታለልና የስድብ ሥራውን ወደ ፊት ገፋበት።
ለማስተዋል ከባድ በሆነ አኳኋን የዓረማዊያን ልማድ ወደ ክርስትና ቤተ ክርስቲያን
መግባት ቻለ። በጣዖት አምልኮ ዘመን ቤተ ክርስቲያን በደረሰባት ከባድ ስደት
ምክንያት የመቻቻልና የመመሳሰል መንፈስ ለተወሰነ ጊዜ ተገትቶ ነበር። ስደት
ሲቆምና ክርስትና ወደ ነገሥታት ሰገነቶችና ቤተ-መንግሥታት ሲገባ ግን የክርስቶስንና
የሐዋርያቱን ትሑት የሆነ ተራ ሕይወት ወደ ጎን ገፍትራ፣ በጦዖት አምላኪ
ካህናትና ገዢዎች ኩራትና አንጸባራቂ ታይታ ተካችው። በእግዚአብሔር መጠይቆች
(መስፈርቶች) ፈንታም የሰውን ጽንሰ ሀሳብና ወግ ተካች። በአራተኛው መቶ
ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የቆስጠንጢኖስ ወደ የይስሙለ ክርስትና መለወጥ
ታላቅ ፈንጠዝያን በመቀስቀስ፣ ዓለም ከነዓለማዊነቱ አስመሳይ የጽድቅ ካባ ደርቦ
ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ። አሁን የብልሽት ሥራ በፍጥነት ይስፋፋ ጀመር። ጣዖት
አምላኪነት የጠፋች መስላ አሸናፊ ሆነች። መንፈሷ ቤተ ክርስቲያንን በቁጥጥሩ
ሥር አደረገ። አስተምህሮዎችዋ፣ ክብረ በዓላቶቿ እንዲሁም መላምቶችዋ (አጉል
አምልኮዎችዋ) ከክርስቶስ ተከታዮች አምልኮና እምነት ጋር ተዋሃዱ።” (ታላቁ
ተጋድሎ፡ ገጽ፡ 58-59)።
በረቡዕ ጥናት መጨረሻ ላይ ከቀረበው ጥያቄ አኳያ እኛ በተለይ የዚህ
ምድር ቆይታችን በተራዘመ ቁጥር ትኩረታችንን “በፍጹም ትሕትና ራሱን ዝቅ
ካደረገው ከክርስቶስ እና ከደቀ መዛሙርቱ” እየመለስን—ለታይታ፣ ለሥልጣን፣
ለውዳሴ ከንቱ እና ለዓለም ፈተናዎች ተጋላጭ በመሆን ረገድ ሁላችንም አደጋ ላይ
አይደለንምን? ከዚህ በተቃራኒ የምናስብ ከሆነ ራሳችንን እያሞኘን ነው።
1. እግዚአብሔር ሕዝቡን በግዞት ወደ ባቢሎን ያመጣበት ትዕይንት በእጅጉ
እግዚአብሔር ሕዝቡን በግዞት ወደ ባቢሎን ያመጣበት ትዕይንት በእጅጉ
ልብ የሚሰብር ዓይነት ነበር። አብርሃም ለምድራችን ብርሃን የሚሆን የቃል
ኪዳን ሕዝብ ይመሠርት ዘንድ ከከለዳውያን ምድር ከዑር ቢጠራም፤ አሁን
ግን ትውልዱ በሰንሰለት ታስሮ እንዲጋዝ ሆነ። እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር
ታማኝ ቢሆኑ ኖሮ ምን ሊከሰት ይችል እንደ ነበር በምርኮ ዘመናቸው
አሳይቷቸዋል። እግዚአብሔርን ፍጹም ይቃወም የነበረ ሥርዓት ራስ
የሆነው ናቡከደነፆር ወደ ክርስቶስ እንደመጣ በዳን. 4 እንመለከታለን።
በግዞት ዘመናቸው መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር እንደ ክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ
የሚያገለግል አንድ የፋርስ ንጉሥ ያስነሣ ሲሆን፣ ንጉሡ የእግዚአብሔርን
ሕዝብ ከባቢሎን ግዞት ነፃ በመልቀቅ ወደ ተስፋይቱ ምድር የሚመልስ ነበር።
ቂሮስ እስራኤላዊ አልነበረም። ነገር ግን እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ሕዝብ
ወደ የሩሳሌም በመመለስ የመዳንን ዕቅድ ለዓለም ያሳይ ዘንድ መረጠው።
እግዚአብሔር ግቡን ለማሳካት ከእስራኤል ውጪ የነበሩ ሰዎችን ከመጠቀሙ
አኳያ፣ ለሰው ልጆች ስላለው አመለካከት ምን ትምህርት እናገኛለን?
2. እኛ ባቢሎን ውስጥ ላንሆን እንችላለን ነገር ግን ምን ያህሉ ባቢሎን በእኛ
እኛ ባቢሎን ውስጥ ላንሆን እንችላለን ነገር ግን ምን ያህሉ ባቢሎን በእኛ
ውስጥ ይኖር ይሆን? የችግሩን መኖር እንዴት አምነን መቀበል ብሎም
መለወጥ እንችላለን?