የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 2:23–25፣ ኤፌ. 5:29–32፣ ሕዝ. 16:4–14፣ ራእ. 18:1–4፣ ዘፍ. 24:1–4፣ ራእ. 19:1–9።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “መልአኩም፣ “ ‘ወደ በጉ ሰርግ
እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው’ ብለህ ጻፍ” አለኝ፤ ቀጥሎም፣ ‘እነዚህ
የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃሎች ናቸው’ አለኝ።” (ራእ. 19፡9)።
መጽሐፍ ቅዱስ የመዳንን ገጽታዎች ብሎም እግዚአብሔር ለሕዝቦቹ
ያለውን ፍቅር በሚገባ በሚገልጹ የፍቅር ታሪኮች የተሞላ ነው።
ከጓደኝነት በላቀ በእጅጉ የጠበቀ ግንኙነት ላይ የተመሠረተው
ጋብቻ፣ እግዚአብሔር ለእኛ ባሰበው መንገድ እንለማመደው ዘንድ ፈቃዳችን
ከሆነ፣ ይህ አምላክ ምን ያህል እንደሚወደን፣ ከእርሱ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ምን
መምሰል እንዳለበት እና እኛን ለመዋጀት ስለተጓዘው ርቀት ጥልቅ ትምህርቶችን
የምንቀስምበት ትምህርት ቤት መሆኑን እንገነዘባለን።
ዘመናዊ የፍቅር እና የጋብቻ ጽንሰ ሀሳቦች እግዚአብሔር በጋብቻ ቃል
ኪዳን አማካይነት ሊያስተምረን እየሞከረ ያለውን ነገር ማድነቅ እንዳንችል አድርገው
አዛብተውታል። ምንም እንኳ ሰብዓዊው ኃጢአተኛነት ጋብቻን (ሌሎች በርካታ
ነገሮችንም ጨምሮ) በእጅጉ ቢያጣምም፣ ጋብቻ ዛሬም ብርቱ በሆነ መንገድ
እውነትን ለመግለጽ የሚያስችል መሣሪያ ከመሆን አልፎ ተርፎ፣ ትንቢታዊውንም
ሐቅ የሚያሳይ ነው። ትዳር እኛን ከማስደሰት ባሻገር ስለ እርስ በርስ ብሎም
ከእግዚአብሔር ጋር ስለሚኖረን ግንኙነት ጥልቅ ትምህርት የምንቀስምበት ትምህርት
ቤት መሆን ይኖርበታል።
በዚህ ሳምንት የእግዚአብሔር ቃል ጋብቻን አስመልክቶ በተለያየ
መንገድ የሚናገራቸውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ሁናቴዎች እንመርምራለን።
ሕዝቡ ከታለመለት ግብ ከመድረስ ሲሰናከል እንኳ፣ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር
ያለውን ተዛምዶ በተሻለ ለመረዳት ከነዚህ ምሳሌዎች ትምህርት መውሰድ እና
የመጨረሻውን ቀን ክስተቶች በተሻለ ሁኔታ እንድንረዳ የሚረዱንን አምላካዊውን
ፍቅር የተመለከቱ አንዳንድ እውነቶች መማር እንችላለን።
እግዚአብሔር ከሰብዓዊው ዘር ጋር ከጋብቻ የጠበቀ ግንኙነት ይኖረው ዘንድ ፍላጎቱ መሆኑን ጥቂት ዘይቢያዊ አነጋገሮች አጽንኦት ይሰጣሉ። ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ውስጥ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ መዋሉና በራእይ መጽሐፍ እጅግ ግልጽ በሆነ መንገድ መቅረቡ፣ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ይህን አገላለጽ የመጠቀሙን አንደምታ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ማስተዋላቸው እጅጉ ወሳኝ ነው። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 2:23–25 እና ኤፌ. 5:29–32። ሰብዓዊው ጋብቻ ክርስቶስ ከሰዎች ጋር ያለውን ትስስር የሚያንጸባርቅባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
በአንድ ወቅት የሱስ ጋብቻን አስመልክቶ ከፈሪሳውያን ጋር ሲነጋገር፣
ስለ አዳምና ሔዋን ትዳር በዘፍጥረት መጽሐፍ የቀረበውን ዘገባ ጠቀሰላቸው።
እነርሱም፡ “ ‘ታዲያ፣ ሙሴ አንድ ወንድ የፍቺውን የምስክር ወረቀት ሰጥቶ
ሚስቱን እንዲያሰናብት ለምን አዘዘ?” (ማቴ. 19፡7) ሲሉ በፍጥነት ጠየቁት።
እርግጥ ነው፣ ሙሴ እንደ እስራኤል ሕዝብ መሪና እና ፈር ቀዳጅ ነቢይ ይቆጠር
ነበር። የጋብቻ ተቋም መሥራች የሆነውን እርሱን ከገዛ ነቢዩ ጋር ለማቃረን እየጠየቁት
መሆኑን በዓይነ ሕሊናዎ ለመመልከት ይሞክሩ። ይህ ድርጊት የሱስን ለማጥመድ ጥቅም
ላይ ያውሏቸው ከነበሩ አካሄዶች አንዱ ከመሆኑ አኳያ፣ የእርሱ ትምህርቶች ከቅዱሳት
መጻሕፍት ጋር ይቃረናሉ የሚል እንከን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ያደርጉ ነበር።
እግዚአብሔር ጋብቻን ያቋቋመው መላውን የሕይወት ዘመን የሚያካትትና
በታማኝነት የሚዘልቅ የትዳር ሕይወትን ታሳቢ በማድረግ ነበር። ሆኖም ውድቀት
የደረሰበት የሰው ልጅ፣ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ይህን ከእግዚአብሔር የተቸረ ገጸ በረከት
ከሥረ መሠረቱ አበላሸው።
ምናልባት ቅዱሳት መጻሕፍት ለትዳር ከሰጡት አዎንታዊ አጽንኦት አንጻር፣
በተቋሙ ላይ የማያቋርጥ ምህረት የለሽ ጥቃት ሲደርስ መኖሩ አጋጣሚ አይደለም።
ሰንበትን ጨምሮ ጋብቻ በኤደን ከተሰጡን ሁለት ስጦታዎች አንዱ ነው። እናም
ሁለቱም የታለሙት—እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ይኖረው ዘንድ
ምን ያህል ፍላጎቱ እንደሆነ ለማሳየት ነበር።
ፍጽምና የጎደላቸው ወንድ እና ሴት የእርስ በርስ ጥብቅ ትስስር
የሚፈጥረው ጋብቻ፣ ምንጊዜም ለውጥረት መንስኤ ነው። በክርስቶስ እና በቤተ
ክርስቲያን መካከል ያለው የጋብቻ ግንኙነት፣ ፍጹም በሆነው አዳኝ እና ፍጽምና
በጎደላት ሙሽራ መካከል የተደረገ ጥምረት ነው። ይሁን እንጂ ከአምላካዊው
ፍቅር አኳያ መልካም ትዳር የሚያስገኛቸውን ትሩፋቶች መማር እንችላለን።
ለጋብቻ የሚጠቅሙ ሦስት መሠረታዊ መርኅዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።
በመጀመሪያ ክርስቶስ ይቅርታ የማይገባንን እኛን ይቅር እንዳለ ሁሉ፣ እርስዎም
ምንም እንኳ የትዳር ጓደኛዎ የማይገባቸው ቢሆንም—ይቅር ይበሏቸው። ሁለተኛ፡
ክርስቶስ ከነጉድለታችን እንደተቀበለን ሁሉ እርስዎም የትዳር ጓደኛዎን ይቀበሉ።
በሦስተኛ ደረጃ፡ ክርስቶስ ከራሱ እንዳስቀደመን ሁሉ እርስዎም የትዳር ጓደኛዎን
ከራስዎ ያስቀድሙ። እነዚህ ሦስቱም በወንጌል ላይ የተመሠረቱ መርኅዎች
እግዚአብሔር እንዴት ራሱን ከእኛ ጋር እንደሚያዛምድ እንድናስተውል ብቻ
ሳይሆን፣ ነገር ግን የትኛውንም ጋብቻ በመርዳት ረገድ ምን ሚና ይኖራቸዋል?
ሕዝቅኤል 16 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ትኩረት የሚያሳይ አስደናቂ ምስል ይሰጠናል። እስራኤልን ተወልዳ ገና በጨቅላነቷ እንድትሞት አውላላ ሜዳ ላይ እንደተጣለች ሕፃን አድርጎ ይገልጻታል። እርሱ ግን ወደ ቤቱ ይወስዳትና ያጸዳታል፣ ዕድሜዋ ለጋብቻ ሲደርስ ያገባታል። ይህ የማይመስል ትዳርን የሚያሳይ ጠንካራ ምሳሌ ነው። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሕዝ. 16፡6-14። ይህች ሙሽራ እንክብካቤ የማግኘቷና ከፍ ከፍ የመደረጓ ምስጢር እግዚአብሔር ለእኛ ስላለው ዓላማ ምን ያስተምረናል?
እግዚአብሔር ለእስራኤል እንደተናገረው ከሆነ በእርሱ ጥበቃና እንክብካቤ
“እጅግ ውብ” (ሕዝ. 16፡13) ለመሆን በቃች። እግዚአብሔር በመጀመሪያ
ሲያገኛት በማንም ዓይን ውስጥ የማትገባ፣ ከሌሎች ልጆች ተነጥላ የተተወች እና
ይህችስ መሞቷ አይቀሬ ነው—በሚል የተጣለች ነበረች። ነገር ግን እግዚአብሔር
ትኩረቱን በእርሷ ላይ ሲያዥጎደጉድ፣ ውበት ከእርሷ በላይ ላሳር እንዲሉ፣ የዓለም
መነጋገሪያ እስከመሆን የደረሰ ቁንጅና እና ደም ግባት ተምሳሌት እየሆነች መጣች።
ይህ በተለይ የቀደሙት ዕብራውያን ነገሥታት ማለትም የዳዊት እና የሰሎሞን ዘመን
እውነታ ነው። የኢትዮጵያ ንግሥት ሳትቀር በእስራኤል ግርማ ክፉኛ ተደምማ ያን
ዝና በዐይኗ በብረቱ ለማየት እነሆ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጉዞ አደረገች!
ይሁን እንጂ የእስራኤል ውበት ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ስጦታ
ነበር። በተለይ የእርሱ ሙሽራ መሆኗን ተከትሎ የተላበሰችው ልቅም ያለ ውበት
የአገራት መነጋገሪያ አድርጓት ነበር። እግዚአብሔር ሲናገር “እኔ ከሰጠሁሽ
ሞገስ የተነሣ ውበትሽ ፍጹም በመሆኑ ዝናሽ በአሕዛብ መካከል ገነነ” ይላል”
(ሕዝ. 16፡14)።
ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ የቀረበ ጭብጥ ነው፡ የእግዚአብሔር
ሙሽራ የተዋበችው ባደረገችው ነገር ሳይሆን እግዚአብሔር ሞገሱን ስላፈሰሰባትና
በዚያ መንገድ ስላበጃጃት ነው። በተመሳሳይ አማኞች በሰማይ ከፍ ያለ ግምት
የሚሰጠንና የተዋብን ሆነን የምንታየው ያን ለማግኘት ብለን ስላደረግነው ነገር
ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት፣ እርሱ ባዘነበልን የማዳን ጸጋ ነው። አምሮብንና
ውብ ሆነን የመታየታችን ምስጢር በጽድቁ ማለትም “በእግዚአብሔር ጽድቅ”
በመሸፈናችን ነው። (2ቆሮ. 5፡21)።
በሕዝቅኤል እስከቀረበው ቀጣይ ጥቅስ ድረስ ሁሉም ነገር መልካም
ነበር፡ “ ‘ነገር ግን በውበትሽ ተመካሽ፤ ዝናሽንም ለአመንዝራነት ተጠቀምሽበት፤
ከዐላፊ አግዳሚው ጋር ያለ ገደብ አመነዘርሽ፣ ውበትሽም ለማንም ሆነ።’ ”
(ሕዝ. 16፡15)።
እነሆ የእግዚአብሔርን መልካምነትና ክብር እናንጸባርቅ ዘንድ ተፈጠርን።
የእግዚአብሔር ፍጥረታት ውበታቸው የራሳቸው እንደሆነ አድርገው ሲገምቱ፣ ያ
ውበት ርካሽና ችግር የሚያስከትል ይሆናል።
“በገዛ ራሳችን ውበት” መታመናችን ምን አደጋ ያስከትላል? ምንጊዜም ቢሆን
ከመንፈሳዊ ኩራት መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር ለነቢዩ ሆሴዕ የሰጠው ትእዛዝ ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን እንኳ ሲለው ያልተደመጠ፣ እጅግ እንግዳና ያልተለመደ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል— ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ! ነገር ግን እግዚአብሔር ሆሴዕን እየተጠቀመበት የነበረው የሰውን ኃጢአት እና አመጽ ህመም ከራሱ እይታ አኳያ እንድንረዳው በማሰብ ነበር። እግዚአብሔር ወድዷትና አፍቅሯት እስራኤል የተባለችውን እንስት በሚስትነት ቢመርጥም፣ እርሷ ግን በተደጋጋሚ በእርሱ ላይ ማገጠች። ሆኖም እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ መልሶ ወስዶ የራሱ አደረጋት። ጥቅሶቹን ያስተያዩ፡ ሆሴዕ 1:2፣ ሆሴዕ 3:1፣ ራእ. 17:1-2፣ ራእ. 18:1–4። በጥቅሶቹ የቀረበው አመንዝራነት ምንድን ነው? ቤተ ክርስቲያን ከሆሴዕ ታሪክ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለች? ቤተ ክርስቲያን የብሉይ ኪዳንን ኃጢአት የደገመችው በምን መንገዶች ነው?
እስራኤል በብሉይ ኪዳን ዘመን የሠራቻቸው ስህተቶች ክርስቶስ ባቋቋማት
የአዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያን በስፋት እንደሚደገም መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል።
የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሕዝቦች በግዞት ቀንበር ስር ከመዋላቸው በፊት
ከቀናው መንገድ በስፋት በማፈንገጥ፣ የአጎራባች ብሔራትን የጣዖት አምልኮ
ወደ አምላካዊው የቃል ኪዳን ሕዝብ አሰረጹ። በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን
መጀመሪያ ላይ ቤተ ክርስቲያን ጥቅም የምታገኝበት ነገር መኖሩን በመገንዘብ፣
የወቅቱን የሮም ንጉሠ ነገሥት ቆስጠንጢኖስ በመማጸን በቤተ ክርስቲያኒቱ መካከል
ያለውን አለመግባባት ይፈታ ዘንድ ግብዣ አቀረበችለት። የእግዚአብሔር ሕዝቦች
በእያንዳንዱ ጉዳይ ለሚገጥሟቸው ችግሮች “መፍትሔ” ያሉትን ለማግኘት፣ ከእርሱ
ጋር ያላቸውን ግንኙነት እየጣሱ ወደ ገዛ መንገዶቻቸው ተቅበዝብዘዋል።
የእግዚአብሔር የቃላት ምርጫ፣ የሠራነውን ስህተት ለማሳየት ብቻ ሳይሆን
ነገር ግን ተግባራችን ምን ያህል ስሜቱን እንደሚጎዳው ሊያሳየን እየሞከረ እንደሆነ
ግልጽ ነው። በትዳር ጓደኛቸው ክህደት የደረሰባቸው ወገኖች ለክርስቶስ ታማኝ
አለመሆናችን በሰማያዊው ቅጥር ሊያስከትል የሚችለውን የሐዘን ስሜት በጨረፍታ
ይረዱ ይሆናል። ምናልባትም ከሆሴዕ ታሪክ በጣም የሚያስደንቀው ነቢዩ ሂያጅ
ሚስቱን ለመቤዠት የሄደበት ርቀት ነው።
የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከባቢሎን እንዲወጡ የቀረበውን የመጨረሻ ጥሪ
ስንመለከት፣ ይህ አምላክ እንግዶችን ሳይሆን የገዛ ሕዝቡን እየጠራ እንደሆነ ልብ
ይሏል። በቅርብ ያውቃቸዋል፤ ይወዳቸዋልም። ዓለም በራሷ መንገድ ወደ ከፋው
ሰዓት እየገሰገሰች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ እኛን በገዛ ደሙ መልሶ ለመግዛት ሲል
የከፈለውን ያን የመቤዠት ዋጋ አሁንም እያቀረበ ይገኛል። የክርስቶስ መስቀል
ከምንም ነገር በላይ ጌታ ምን ያህል በከፍተኛ ጽናት ሂያጅ ሕዝቡን የማዳን ልባዊ
ፍላጎት እንዳለው ሊያሳየን ይገባል።
ዛሬ ማንኛውም ቤተ ክርስቲያን፣ ሌላው ቀርቶ የገዛ ራሳችንም እንኳ ብትሆን
በመንፈሳዊ ምንዝር ልትታመስ የምትችልባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
አብርሐም በሸመገለ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ስለ ትውልዱ የገባውን ቃል ሲያስብ (ዘፍ. 15፡5) በዕድሜ ጠና ላለውና እምነት ለሚጣልበት አገልጋዩ ከባድ ኃላፊነት ሰጠው። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 24:1–4። አብርሐም የልጁን “ ‘ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ጋር’ ” አለመጋባት እጅግ አስፈላጊ አድርጎ የቆጠረው ለምን ነበር?
ምንም እንኳ ምክሩ አንዱን ከሌላው ነጥሎ የሚመለከት ዓይነት ቢመስልም፣
የአብርሐም ጉዳይ መንፈሳዊ እንጂ ብሔር ተኮር አልነበረም፣ ኃይማኖታዊ እንጂ
ብሔራዊ አንደምታ አልነበረውም። ከነዓናውያን የሐሰት አማልክትን ማምለክ
ይቅርና—ራሱ አምልኮአዊ ሥርዓታቸው ምን ያህል የሥነ ምግባር ዝቅጠት ውስጥ
የወደቀ እንደነበር ጠንቅቆ ያውቅ የነበረው አብርሐም፣ ልጁ ከመካከላቸው ከአንዷ
ጋር ቢጋባ በቀላሉ በእነዚህ ልማዶች ሊወሰድ እንደሚችል አስተውሏል።
በርካታ የጥንቷ እስራኤል ታሪክ፣ ሌላው ቀርቶ ያለፉት መቶዎች ዓመታት
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ለዓለም መመሥከር የነበረባቸው የእግዚአብሔር ሕዝቦች
በዓለምና በእርሷ የሐሰት ትምህርቶች ብሎም ኃይማኖታዊ ሥርዓቶች የተጠመዱበት
መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ምናልባት ለዚህ አሳዛኝ እውነታ ግዙፍ ምሳሌ
የሚሆነው በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ሰባተኛ ቀን ሰንበት ምትክ እሁድ፣ አረማውያኑ
የፀሐይ ቀን (Sunday) መተዋወቅ ሊሆን ይችላል። ይህ እውነታ በምድር
የመጨረሻዎቹ ቀናት ጉልህ ሚና ይኖረዋል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 24፡57-67። በዚህ ታሪክ ውስጥ ከምናገኛቸው
አንዳንድ ዝርዝር ጉዳዮች ስለ ክርስቶስ እና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ምን ትምህርት
እናገኛለን? ለአብነት ያህል ርብቃ እርቃ እና ተነጥላ የምትኖር የይስሐቅ ዘመድ
የመሆኗ እውነታ፣ በኃጢአት ስለ ወደቀው ማንነታችን ምን ያስተምረናል?
እኛ በመጀመሪያ በፈጣሪ አምሳል እንደ መፈጠራችን ከእርሱ ጋር ያለን
ዝምድና ጥያቄ ውስጥ አይገባም። በኃጢአት ጠንቅ ከእርሱ ተለይተን የነበረ
ቢሆንም፣ ዛሬም ለእርሱ እንደ ትክክለኛ ሙሽራ እንቆጠራለን፤ ይህም ሆኖ የገዛ
ምርጫዎቻችን ጋብቻውን በሁከት የተሞላ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ልብ ይሏል።
አዎ፣ እግዚአብሔር ከምንወደው በላይ ሙሽራዎቹ የሆንነውን እኛን ይወደናል።
ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር የሚያጠናክሩ፣ በየዕለቱ ልናደርጋቸው የምንችላቸው
ምርጫዎች ምንድን ናቸው? በተመሳሳይ—ፍቅራችንን ከማደንዘዝ ውጪ ፋይዳ
የሌላቸው የትኞቹ ምርጫዎች ናቸው?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 19፡1-9። የሁለት ነገሮች የከበረ ሥነ ሥርዓት በአንድ ጊዜ ይፈጸማል፡ የጋለሞታይቱ ፍፃሜ እና ክርስቶስ ከሙሽራው ጋር የሚያደርገው ጋብቻ። እነዚህ ሁለቱም ክስተቶች የእግዚአብሔርን ጽድቅ እና አፍቃሪ ባህሪ እንዴት በአንዴ ማሳየት ይችላሉ?
በትዳር ላይ ማመንዘር በጣም ከባድ ዋጋ ያስከፍላል። ጦሱ ለልጆች ብሎም ለሌሎች ሕይወት ሳይቀር የሚተርፍ ይሆናል። በጣም ታጋሽ የሆኑ የትዳር ጓደኞች እንኳ ሳይቀሩ ውሎ አድሮ ትዳሩን መታደግ የሚቻልበት ጊዜ እንዳለፈበትና ወደ ቀድሞው መመለስ እንደማይችል ሊገነዘቡ ይችላሉ። ዓለማችን ሰዎች ንስሐ ሊገቡ ወደማይችሉበትና ልባቸው በጥልቅ የሚደነድንበት ደረጃ ላይ ስትደርስ፣ ተመሳሳይ ታሪክ እና ያልተገራው የኃጢአት ሥቃይ እንዲቀጥል መፍቀድ አንዳችም ፋይዳ አይኖረውም። ምንም እንኳ የሰዎች መጥፋት ልብ ሊሰብር ቢችልም፣ በዚህ ዓለም የኃጢአት ሥርዓት መከራ የደረሰባቸው ወገኖች በመጨረሻ ሥቃይና ዋይታው ማክተሙንና ዓለም እግዚአብሔር መጀመሪያ ሲያበጃጃት ወዳቀደው ንጽህና በመመለሷ ሐሴት ሊያደርጉ ይችላሉ። በዚህ ወቅት ፊታችንን ከእግዚአብሔር የምንመልስበት ሁኔታ አይፈጠርም። ምክንያቱም ራሳችንን ከእርሱ መነጠላችን ውድመት እንደሚያስከትልብን የተነገረን ቃል ትክክል እንደ ነበር በመከራ ተምረናል። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 21:1–4። ይህ ተምሳሌታዊ የጋብቻ አቀራረብ ምን ትርጉም አለው? በጥቅሶቹ ለቀረበው ተስፋ ዋስትናችን ምንድን ነው?
“የሕይወት ጥምረት የሆነው ገብቻ፣ በክርስቶስ እና በቤተ ክርስቲያኑ መካከል
ያለው ጥምረት ምሳሌ ነው። ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን የገለጠው መንፈስ፣ ባል እና
ሚስት እርስ በርስ ሊገልጡት የሚገባ መንፈስ ነው”—Ellen G. White,
Testimonies for the Church, vol. 7, p. 46.
ሰብዓዊው ዘር እርሱን በመናቁና የእርሱ የሆነውን ፍቅር ለሌሎች አማልክት
በመስጠቱ ክርስቶስ ሊታሰብ የማይችል ብርቱ ሕመም ደርሶበታል። እንዲህም ሆኖ
እንኳ፣ የእኛ ቃል ኪዳን ማፍረስና ምንዝር የሚያስከፍለንን ዋጋ እርሱ ስለከፈለና
ራሱን ስለ እኛ ስለ ሰጠ፣ ንስሐ ብንገባና ከመንገዳችን ብንመለስ እነሆ የዘላለም
ሕይወት ተስፋ አለን።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 1ጴጥ. 1:18-19። በራዕ. 21፡1-4 ስለ ተገለጸው ፍጻሜ
በጥቅሶቹ ምን ማረጋገጫ ተሰጥቶናል?
ዮሐ. 2:1–11፣ ማቴ. 22:1–14፣ 2ቆሮ.
11:1–5፣ ማቴ. 25:1–13።
ስለ ትንቢቶች ያለዎትን ግንዛቤ ለማስፋት ሊረዳዎ የሚችል ምን ያህል መረጃ
በተቀረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደሚገኝ አንዴ ግንዛቤ ካገኙ በኋላ፣ መረጃውን
ከልክ በላይ መተግበር ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ባለፉት መቶ ዓመታት አንዳንድ
ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ውስጥ ለሚገኙ ተምሳሌታዊ አገላለጾች የተለየ
አጽንኦት እና ማሰላሰል ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ በተጨባጭ ገቢራዊ ሆኖ
ያለፈውን ታሪካዊ ክስተት እንደ ተረት የመመልከት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። የትርጉም
ንብርብሮች በቅዱሳት መጻሕፍት በሁሉም ቦታ ሊገኙ ቢችሉም፣ እግዚአብሔር
በተጨባጭ ሰዎችን የሚመለከቱ እውን ክስተቶችን ገቢራዊ የሚያደርግበትና ከቤተ
ክርስቲያን ጋር ስላለው የወደፊት መስተጋብር እኛን ለማስተማር የሚጠቀምበት
መንገድ እንዳለው ሁሌም ማስታወስ ይኖርብናል።
ለምሳሌ ያህል በቃና የተደረገው የሠርግ ድግስ ጋብቻ በትንቢት ጥቅም ላይ
በዋለበት ዓይነት ዘይቤያዊ አገላለጽ የቀረበ ሊመስል ይችላል፤ ሆኖም የሠርጉ ሥነ
ሥርዓት በተጨባጭ የተፈጸመ ክስተት ነው። “የክርስቶስ ቃል ለሠርጉ በቂ ድግስ
እንዲኖር አደረገ። የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ፤ ነፍስን ለማደስና ለመንከባከብ
የጸጋው ድግስ የተትረፈረፈ ነው።” (የዘመናት ምኞት፡ ገጽ፡ 135)
“ልዑል እግዚአብሔር ምስጢሩን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት አስቀድሞ
ሳይገልጥ ምንም ነገር አያደርግም።” (አሞጽ 3:7)። “እግዚአብሔር አምላካችን
ምስጢር አድርጐ የሰወራቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ሕጉን ግን ገልጦልናል፣ ስለዚህ
እኛና ዘሮቻችን ለዘላለም ልንጠብቀው ይገባናል።” (ዘዳ.29:29)።
እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ሰጥቶናል፣ በአክብሮትና በጸሎት ትንቢቶችን
በሚያጠኑ ላይ በረከቱን ያወርድባቸዋል።” (የዘመናት ምኞት፡ ገጽጽ 223)
1. ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዮሐ. 2፡1-11። በዮሐንስ ወንጌል የክርስቶስን
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዮሐ. 2፡1-11። በዮሐንስ ወንጌል የክርስቶስን
የወደፊት አገልግሎት የሚተነብዩ በርካታ ባሕሪያት ያሉ ሲሆን፣ ሐተታ
ሰጪዎች ዮሐንስ እንዴት አድርጎ አንባቢውን በዘዴ ወደ መስቀሉ እንዳቀና
አስተውለዋል። በዚህ ታሪክ ውስጥ የክርስቶስን ባህሪ እና የወደፊት
መንግሥት ልዩ ልዩ ገጽታዎች በየትኛው ስፍራ ይመለከታሉ? ስለ ደኅንነት
እቅድ ወይም ለእግዚአብሔር ልጅ ቃል ስለተገባው የመጨረሻው የሠርግ
ድግስ ምን ያስተምረናል?
2. ስለ አሥሩ ቆነጃጅት የሚገልጸው ምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች
ስለ አሥሩ ቆነጃጅት የሚገልጸው ምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች
ዘንድ በሰፊው የሚታወቅና በእጅጉ የሚወደድ ነው። ይህ ወሳኝ ታሪክ
ስለ መጨረሻው ቀን ክስተቶች ምን ያስተምረናል? የሙሽራው መዘግየት
ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነውን? ይህ ምሳሌ ከክርስቶስ ጋር ስላለን
የግል ግንኙነትና ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ስላለው ግንኙነት ምን
ትምህርት ይሰጠናል?
3. ከአምላካዊው አስተምህሮ ውጪ ወደ ክርስትና ስለገቡ የሐሰት ልማድና
ከአምላካዊው አስተምህሮ ውጪ ወደ ክርስትና ስለገቡ የሐሰት ልማድና
ትውፊቶች አሰብ ያድርጉ። ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ሰንበት በተቃራኒ በግልጽ
ከቀረበው እሁድ ቀን በተጨማሪ የተስተዋሉ ሌሎች የሐሰት አስተምህሮዎች
የትኞቹ ናቸው? እንዴት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡ? ራሳችንን ከእነርሱ
ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎች በተጨባጭ ምን እንደሆኑ እንዲገነዘቡ
ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን? የሦስቱ መላእክት መልእክት ሰዎች
ወደ እምነት የገቡትን የሐሰት አስተምህሮዎች መገንዘብ እንዲችሉ ጥረት
የሚያደርግበት መንገድ ምን ይመስላል?