የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ፍንጮች፣ ምስሎች፣ ምሳሌዎች፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ማጥኛ መንገድ



2ኛ ሩብ ዓመት 2025


ሰኔ 7 - 13

12ኛ ትምህርት

Jun 14 - 20




አስቀድመው የተሰጡ ምልክቶች



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዳን. 2:31–45፣ ዳን. 3:1–12፣ 17-18፣ ራእ. 13:11–17፣ ሮሜ 1:18–25፣ ሐዋ. 12:1–17፣ ማቴ. 12:9–14።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እግዚአብሔር የኀይልና የፍቅር፣ ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሀት መንፈስ አልሰጠንምና” (2ጢሞቴ. 1፡7)።

በዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት ክስተቶች የሚያስጠነቅቁንን አስደናቂ መረጃዎች በዝርዝር እንመለከታለን። በመጀመሪያ፣ በራእ. 13 የለተገለጹትን ጉዳዮች አስመልክቶ ግልጽ ማብራሪያ የያዘውን የሲድራቅን፣ የሚሳቅን እና የአብደናጎን ታሪክ እንመረምራለን።

ከዚያም ወደ አዲስ ኪዳን ተሻግረን በአሁን እና በክርስቶስ ዳግም ምጽአት መካከል ምን መጠበቅ እንዳለብን እገዛ የሚሰጡንን የቀደሙ ክርስቲያኖች ተሞክሮ እንዳስሳለን።

ሁለቱም ምሳሌዎች ለአስደናቂ ጀግንነት አጽንኦት ከመስጠታቸውም በላይ በእጅጉ ፈታኝ በሆኑ ሁናቴዎች ውስጥ የአእምሮ ሰላም ለማግኘት የሚያስችሉ ቁልፍ ነጥቦችንም አካትተዋል።

የሱስ “አትፍሩ”፣ “ልባችሁ አይጨነቅ” ሲል በተደጋጋሚ ተናግሯል። የትንቢት ዋነኛ ትኩረት ክርስቶስ መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። በመሆኑም በምድር ታሪክ መደምደሚያ ወቅት እውን እንደሚሆኑ በተገለጹት ትዕይንቶች ሁሉ ተመሳሳይ ምክር ማግኘት መቻል አለብን። የሱስ “ልባችሁ አይጨነቅ፣ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ” (ዮሐ. 14፡1) ሲል ደቀ መዛሙርቱን አስተማራቸው።

በሌላ አነጋገር፣ አዎን፣ የመጨረሻው ቀን ክስተቶች—ለእግዚአብሔር ታማኝ ለመሆን ለሚፈልጉ አስቸጋሪ እና ፈታኝ ይሆናሉ። ነገር ግን ውሎ አድሮ፣ እነዚህን ክስተቶች በፍርሃት ሳይሆን በተስፋ ልንመለከታቸው ይገባል።

ሰኔ 8
Jun 15

ዳንኤል ምዕራፍ ሁለት እና ታሪክን መሰረት ያደረገው


የትንቢት አፈታት

በቅዱሳን መጻሕፍት እጅግ ከፍ ያለ ስፍራ ከሚሰጣቸው ትንቢቶች አንዱ ዳንኤል 2 ነው። ትንቢቱ ከክርስቶስ ልደት አምስት መቶ ዓመታት በላይ ቀደም ብሎ የተጻፈ ነው። ነቢዩ የዓለምን ታሪክ በቅደም ተከተል ያስቀመጠው እርሱ ከነበረበት ከባቢሎን ሥርወ መንግሥት አንስቶ በተከታታይ የሚመጡትን፡ ሜዶንና ፋርስ፣ ግሪክ፣ ሮም እንዲሁም—የሮምን ወደ ዛሬው ዘመናዊ የአውሮፓ አገራት መከፋፈል ያካተተ ነበር።

ስለ እነዚህ የአውሮፓ አገራት አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናግሯል፡ “ ‘ከሰብዓዊው ዘር ጋር ይደባለቃሉ፤ ነገር ግን ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይዋሃድ ሁሉ እርስ በርሳቸው አይጣበቁም’ ” (ዳን. 2፡43)። ይህ ትንቢት በሚያስደንቅ ሁኔታ ፍጻሜ አግኝቷል። በሌላ አባባል በእነዚህ ብሔራት መካከል (ከመሳፍንት እስከ ሎሌ) የተለያዩ ጋብቻዎች ቢፈጸሙም አሁን ድረስ እንደተከፋፈሉ ይገኛሉ።

ለምሳሌ የእንግሊዝ ንጉሣዊ አገዛዝ ዘ ሃውስ ኦቭ ዊንዘ የተባለ ማለፊያ የእንግሊዝኛ ስያሜ ይዟል። ይሁን እንጂ ይህ ስያሜ በአንጻራዊ መልኩ ሲታይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማለትም በ1917 ላይ የተሰጠ ነው። ከዚያ ቀደም ብሎ ቤተሰቡ ይጠራ የነበረው ሳክስ-ኩበርግ-ጎታ በሚል ልዩ የጀርመንኛ መጠሪያ ነበር። ለዚህ መንስዔው በርካታ የብሪታንያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት “ከሰብዓዊው ዘር” ጋር በመደባለቃቸው ከጀመርመኖች ጋር የደም ዝምድና ስለፈጠሩ ነበር። ይሁን እንጂ እነዚህ የደም ትስስሮች ከጦርነት ይታደጓቸው ዘንድ በቂ አልነበሩም። ይህን ተከትሎ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከሚጠሏቸው ጠላቶቻቸው ራሳቸውን ማግለል ፈለጉ። ስለዚህ የንጉሣዊውን አገዛዝ ስያሜ ዘ ሃውስ ኦቭ ዊንዘ በሚል ቀየሩት። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዳን. 2፡31-45። የናቡከደነጾር ሕልም ምን ነበር? ዳንኤል እንዴት ተረጎመው?



በዳንኤል የተነገሩት እስከ ምድር መጨረሻ የሚዘልቁ ትንቢቶች በሙሉ በዳን. ምዕ. 2 የተጣለውን መሰረት ይከተላሉ። ይህም ማለት የተቀሩት ትንቢቶች፣ እንደ ዳን. 2 ሁሉ፣ እግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግሥቱን እስኪመሰርት ድረስ የሚነሡትን የዓለም ሉዓላዊ መንግሥታት በቅደም ተከተል ያስቀምጣል (ዳን. 2፡44፣ ዳን. 7፡13-14)። በሌላ አነጋገር፣ ትንቢቶቹ ከጥንት አንስቶ እስከ ወደ ፊት (የእኛንም ዘመን አካትቶ) ያልተቆራረጠ የታሪክ ምዕራፎቻቸውን እንደያዙ ይዘልቃሉ። ይህ ታሪክን መሰረት ያደረገ የትንቢት አፈታት ሲሆን፣ ጥቅሶቹም የሚጠይቁት ይህንኑ ነው። እንዲህ ያለውን ታሪክን መሰረት ያደረገ የትንቢት አፈታት ዘዴ ጥቅም ላይ ማዋል የመጨረሻዎቹን ቀናት ክስተቶች ለማስተዋል ወሳኝ ነው፤ በተለይ የራእይ መጽሐፍ ከቀረበበት አግባብ። እግዚአብሔር የወደፊቱን የሚያውቅ አምላክ ብቻ ሳይሆን፣ የጉዳዩ ባለቤት ጭምር መሆኑን ዳን. 2 እንዴት ያረጋግጥልናል?

ሰኔ 9
Jun 16

ለምስሉ መስገድ


ናቡከደነፆር የቱንም ያህል ተቀማጥሎ ቢኖርም ዳንኤል ባደረገው ነገር ልቡ በመነካቱ መጀመሪያ ላይ ለዳንኤል እና ለአምላኩ ተገቢውን አክብሮት አሳይቶ የነበረ ቢሆንም (ዳን. 2፣ በተለይ ቁ. 46-48) እስከ መጨረሻው ግን አልዘለቀበትም። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዳን. 3፡1-12። ምስሉ ሙሉ በሙሉ ከወርቅ የመሠራቱና ንጉሡ ለምስሉ እንዲሰገድ የመጠየቁ አንደምታ ምንድን ነው?



ንጉሡ ሙሉ በሙሉ ከወርቅ የተሠራ ምስል በማቆም የእግዚአብሔርን መልእክት መቃወሙን በይፋ አሳየ። ሊያስተላልፍ የፈለገው መልእክት ባቢሎን ፈጽሞ አትወድቅም፣ ናቡከደነፆርም ሁል ጊዜ በንጉሥነቱ ጸንቶ ይኖራል—የሚል ነበር። እናም ይህን ሐሳብ ለመቃወም የደፈረ ማንኛውም ሰው የሞት ጽዋ ይጨልጣል። ሰብዓዊው ፍጡር ሕይወቱን በገዛ እጁ ስር ማዋል እንደሚችል አድርጎ የማሰቡ አጉል ምኞት፣ ታላቁ ተጋድሎ ፍጻሜ የሚያገኝበትን እውነት መመልከት እንዳንችል አድርጎ በፍጥነት ዓይኖቻችንን ይሸፍናል። ይህ ጠንካራ ማሳሰቢያ በመሆን ያገለግላል።

ናቡከደነፆር በአንዳንድ ሁኔታው ከሉሲፈር ጋር የሚመሳሰሉ ባህሪያት ነበሩት፡ ከንቱ ክብር መሻቱ፣ ግብዝነቱ እና በእግዚአብሔር ሥልጣን ላይ ግልጽ በሆነ አመጻ መታበዩ። በሌላ ጎኑ ስንመለከት ደግሞ፣ ጉልህ ልዩነቶችን መታዘባችን እሙን ነው። ናቡከደነፆር በመጨረሻ እውነተኛውን አምላክ ወደ ማመን መጣ። እናም በመጀመሪያ ላይ እርሱን በመቃወም ከፍተኛ ግብ ግብ ውስጥ ገብቶ የነበረውን ናቡከደነፆር፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ እናገኘዋለን ብለን እናስባለን። ሦስቱ ዕብራውያን ወጣቶች ንጉሡን በመቃወም የተናገሯቸውን ቃላት ያንብቡ፡ ዳን. 3፡17-18። ይህ ስለ እምነት ምን ያስተምረናል? አንዳንዴ ከእኛ ሊጠየቅ ስለሚችል ነገርስ?



እነዚህ ሦስት ሰዎች ራሳቸውን እንዴት በቀላሉ ከዚህ አደገኛ ሁኔታ ማውጣት ይችሉ እንደ ነበር ያስቡ። ደግሞስ፣ ጎንበስ ብሎ ባለመስገድ ብቻ ተቃጥሎ ለመሞት ፈቃደኛ መሆን እንደ አክራሪ አያስቆጥራቸውም? በልባቸው ወደ አምላካቸው እየጸለዩ የጫማ ማሰሪያቸውን ለማሰር ጎንበስ ብለው ቢያስመስሉስ? ለተጋፈጡቱ ነገር በእርግጥ ያን ያህል መሥዋዕትነት መክፈል ነበረባቸው? ምንም እንኳ ከአንደበቶቻቸው የወጡት ቃላት ጉዳዩን በሕይወት ሊያመልጡ እንደማይችሉ ማሰባቸውን ገልጠው ቢያሳዩም፣ በጉዳዩ ዙሪያ የነበራቸው የእምነት ጽኑነት ግልጽ ነው። በእምነታችን ላይ ሰጥቶ የመቀበል ዕድሎችን ከሚሰጡን ቀለል ያሉ ምክንያቶች እንዴት መራቅ እንችላለን? ተመሳሳይ ፈተናን የሚዳስሰው የሚከተለው ጥቅስ ምን ይነግረናል? “በትንሽ ነገር ታማኝ የሆነ በትልቁም ይታመናል፤ በትንሽ ነገር ያልታመነ በትልቁም አይታመንም” (ሉቃ. 16፡10)።

ሰኔ 10
Jun 17

ለምስሉ መስገድ፣ (በድጋሚ)


የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በዳን. 3 እና የራእይ መጽሐፍ ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት በሚያስተምረው ትምህርት መካከል ግንኙነት መኖሩን ከረጅም ጊዜ በፊት መመልከት ችለዋል። በዳን. ምዕ. 3 “ለምስሉ የማይሰግድ” (ዳን. 3፡15) የሞት ቅጣት እንደሚጣልበት አስመልክቶ የወጣው ትእዛዝ፣ የራእይ መጽሐፍ ለሌላኛው ምስል አለመስገድ በሞት እንደሚያስቀጣ ያሰፈረውን ሀሳብ ያንጸባርቃል፡ “ደግሞም የመጀመሪያው አውሬ ምስል መናገር እንዲችል ለምስሉ እስትንፋስ ለመስጠትና ለዚህም ምስል የማይሰግዱ ሁሉ እንዲገደሉ ለማድረግ ሥልጣን ተሰጠው” (ራእ. 13፡15)። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 13፡11-17፣ ራእ. 14፡9፣11፣12፣ ራእ. 16፡2፣ ራእ. 19፡20፣ ራእ. 20፡4። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ከሰዎች ትእዛዛት ጋር የሚያጋጭ ምን ተቃርኖ ይስተዋላል?



የእግዚአብሔር ሕዝቦች “ ‘ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንና የውሃ ምንጮችን ለፈጠረው’ ” ይኸውም ከአውሬውና ከምስሉ በተቃራኒ—ለፈጣሪ ይሰግዱ ዘንድ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ሦስቱ ዕብራውያን ወጣቶች ተመሳሳይ አደጋ ከፊታቸው ቢደቀንም፣ ከፈጣሪ አምላክ በቀር ለሌላ ለማንም ላለመስገድ ተቃወሙ።

በመሆኑም በዱራ ሜዳ ላይ በተከሰተው ነገር እና ከፈጣሪ በተቃራኒ ለምስሉ እንዲሰገድ በወጣው ትእዛዝ መካከል ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ቢለያይም—ከፈጣሪ በተቃራኒ ለምስሉ እንዲሰገድ የሚቀርበውን ጥሪ ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሆነው ነገር በመርኅ ደረጃ ተመሳሳይ ነው። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሮሜ 1፡18-25። (በሮሜ 1፡18 እና በራእ. 14፡9-10 መካከል ያለውን ግንኙነት—“የእግዚአብሔር ቁጣ” ልብ ይበሉ።) ሰብዓዊ ፍጡራን ውሎ አድሮ ታማኝነታቸውን የሚገልጹበት ለምስሉ የመስገድ ጉዳይ የዚሁ ተመሳሳይ መርኅ ሌላኛው መገለጫ መንገድ የሆነው በምን መልኩ ነው?



አምልኮ አጎንብሶ በመስገድ እና ዕጣን ማጨስ ብቻ የግድ መወሰን የለበትም። የመጨረሻውን ታማኝነታችንን መውሰድ የሚችለውን ማንኛውንም ነገር እናመልካለን። የእግዚአብሔርን ማንነት ሲያጤኑ—ፈጣሪያችን እና በየሱስ ለእኛ ባደረገው ነገር—አዳኛችን እንደ መሆኑ እርሱ ብቻ መመለክ ይኖርበታል። ከዚህ ውጪ ያለ ሁሉ—ባዕድ አምልኮ ነው። ምናልባት የሱስ እንደሚከተለው የተናገረው ይህን ሀሳብ ሊያብራራው ይችላል፡ “ከእኔ ጋር ያልሆነ ሁሉ ይቃወመኛል፤ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ሁሉ ይበትናል” (ማቴ. 12፡30)።

ሰኔ 11
Jun 18

የቀደመው የቤተ ክርስቲያን ስደት


በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ለነበሩ ክርስቲያኖች ሕይወት ቀላል አልነበረም። መጀመሪያ ላይ ለሙሴ እምነት እንደ ስጋት በቆጠሯቸው በበርካታ የገዛ እምነት አጋሮቻቸው ጥላቻ ደርሶባቸው ነበር። በተጨማሪም የአረማዊውን ሮም ቁጣ መጋፈጥ ነበረባቸው። “የምድርና የሲኦል ኃይላት በአንድ ላይ ተሰድረው የክርስቶስ ተቃዋሚነታቸውን በተከታዮቹ ላይ ገለጹ። ወንጌሉ ስኬት ካገኘ ቤተ መቅደስዋና የመሰውያ ስፍራዋ እንደሚጠፉ የጣዖት አምላኪዋ ቤተ ክርስቲያን ተገነዘበች፤ በመሆኑም ሃይሏን አሰባስባ ክርስትናን ለማጥፋት ቆርጣ ተነሣች።

የስደት እሳት ተቀጣጠለ።” (ታላቁ ተጋድሎ፡ ገጽ 46-47)።

በራእ. 13 ወደ ተገለጸው ትዕይንት ስናመራ፣ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሊጠብቁ የሚገባቸውን ነገር በጠንካራ መንገድ የሚያመለክት ታሪክ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እናገኛለን። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሐዋ. 12:1–17። የመጨረሻዎቹን ክስተቶች የሚያሳዩ የዚህ ታሪክ ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?



ያዕቆብ ተሰየፈ፣ ጴጥሮስም በቀጣይ ሞቱን የሚጠባበቅ መሆኑን ተከትሎ በክርስቲያኖች ላይ ሞት ተበይኖ ነበር። ጴጥሮስ በሕይወቱ በገጠመው በዚያ እጅግ አስከፊ ሌሊት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ላይ መውደቁና መልአኩ የጴጥሮስን ጎን መታ አድርጎ እንዲነቃ መቀስቀሱ፣ ምናልባትም በዚህ ታሪክ ውስጥ በጣም አስደናቂ ከሆኑት ክስተቶች አንዱ ነው።

ጴጥሮስ ተዓምራዊ በሆነ መንገድ ከእስር ቤት ወጥቶ በአንድነት ተሰብስበው ይጸልዩ ወደ ነበሩ አማኝ ወንድሞች ዘንድ ሲደርስ እርሱ መሆኑን ለማመን እስኪቸገሩ ድረስ ተደነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ “ባዩትም ጊዜ ተገረሙ” ይለናል።

አንዳንዴ አብልጠን በጸሎት እየተጋን እግዚአብሔር ልመናችንን ይመልሳል ብሎ የማመን ድፍረት ግን ሲጎድለን ይስተዋላል—በሐዋርያት ዘንድ የሆነው ይኸው ነው።

አንዳንድ አማኞች ሲተርፉ ሌሎች ግን ተገደሉ። እኛም ወደ ፍጻሜው ዘመን ስንቃረብ የዚሁ ተመሳሳይ ሁኔታ ይከሰታል። ምንም እንኳ ጴጥሮስ በወቅቱ ተርፎ የነበረ ቢሆንም፣ ውሎ አድሮ ስለ እምነቱ ሰማዕት ሆነ። የሱስ ራሱም ቢሆን እንዲህ ብሎት ነበር፡ “እውነት እልሃለሁ፤ ወጣት ሳለህ ልብስህን ራስህ ለብሰህ ወደ ፈለግህበት ትሄድ ነበር፤ ስትሸመግል ግን እጅህን ትዘረጋለህ፤ ሌላም ሰው ልብስህን አስታጥቆህ ልትሄድ ወደማትፈልግበት ይወስድሃል።” ኢየሱስ ይህን ያለው ጴጥሮስ በምን ዐይነት ሞት እግዚአብሔርን እንደሚያከብረው ለማመልከት ነው። ከዚህ በኋላም፣ ‘ተከተለኝ’ አለው።” (ዮሐ. 21፡18-19)። ጴጥሮስ እንዴት እንደሚሞት ከነገረው በኋላም እንኳ “ተከተለኝ” ሲለው የሱስ ይደመጣል። የሞት ስጋትም እንኳ ቢሆን ጌታን ከመከተል ሊያግደን እንደማይገባ ይህ ምን ያስተምረናል?

ሰኔ 12
Jun 19

የአውሬው ምልክት


ዓመታት እያለፉ በሄዱ ቁጥር፣ የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች የሆኑት እንደ የሞት አዋጁና የአውሬው ምልክት ፍጻሜ አለማግኘት—የሰንበት እና የእሁድ ሕግ የመጨረሻው ክስተት አስኳል ሆነው አለመውጣታቸውትን ተከትሎ—አንዳንዶች በትንቢት አተረጓጎማችን ዙሪያ ጥርጣሬ ሲገባቸው ይታያል።

የራእይ መጽሐፍ በግልጽ እንደሚያስቀምጠው፣ አምልኮአችንን ለፈጣሪ ወይም ለአውሬውና ለምስሉ ማቅረባችን የግድ ይሆናል። ሰባተኛው ቀን ሰንበት የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት በማመላከት ወደ ኋላ እስከ ኤደን (ዘፍ. 2፡1-3) የሚዘልቅ መሰረታዊ ምልክት እንደመሆኑ፣ ፈጣሪን በማምለክ ረገድ የሰንበት አስኳልነት ሊያስገርመን አይገባም። በተጨማሪም፣ የአውሬው ኃይል የሰንበትን ትእዛዝ ያለ አምላካዊው ቃል ይሁንታ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ቀን ወደ እሑድ የለወጠ ያው ኃይል መሆኑ አጋጣሚ አይደለም። ይህን ታሪካዊ ዳራ በአእሮአችን እንደ ያዝን፣ በአምልኮ ጉዳይ ውስጥ የተካተተው የሰንበት እና የእሁድ ጽንሰ ሀሳብ፣ እንደገና ትርጉም ሊሰጥ የሚችለው ከፈጣሪ (ራእ. 14፡6-7) ወይም ከአውሬው አኳያ ብቻ እንደሆነ እንመለከታን። እንዲሁም በሰባተኛው ቀን ሰንበት እና በሰው በተሰየመው ሕግ ጉዳይ ዙሪያ አስፈላጊውን የቀደመ ፍንጭ አዲስ ኪዳን ይሰጠናል። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 12፡9-14፣ ዮሐ. 5፡1-16። የኃይማኖት መሪዎች የሱስን ለመግደል ያነሣሣቸው ጉዳይ ምን ነበር?



የሱስ እጁ ሽባ የሆነውን ሰው በሰንበት ከፈወሰ በኋላ (ማቴ. 12፡9-13) የኃይማኖት መሪዎች በጉዳዩ ዙሪያ ምን ምላሽ ሰጡ? “ፈሪሳውያን ግን ከዚያ ወጣ ብለው ኢየሱስን እንዴት እንደሚገድሉት ተማከሩ።” (ማቴ. 12፡14)። በሰባተኛው ቀን ምክንያት ሞት? በዮሐ. 5፡1-16 እንደቀረበው፣ በሰባተኛው ቀን ሰንበት ሌላ ታምራዊ ፈውስ ከተደረገ በኋላ፣ የኃይማኖት መሪዎች የሆኑት “አይሁድም፣ በሰንበት ቀን እነዚህን ድርጊቶች በመፈጸሙ፣ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር።” (ዮሐ. 5፡16)።

ስለ ሰው ወግና ልማድ ሲባል በሚደነገግ የሞት ፍርድ (መጽሐፍ ቅዱስ ቅዳሜ በእሁድ ተተክቷል ያለበት ስፍራ እንደሌለ ሁሉ፣ በሰንበት መፈወስን የከለከለበት ስፍራም የለም) እና በሰባተኛው ቀን ሰንበት መሃል ያለ ፍልሚያ? ምንም እንኳ እዚህ ላይ ከየሱስ አኳያ የቀረበው ጉዳይ ከመጨረሻዎቹ ቀናት ክስተቶች ጋር አንድ ዓይነት ባይሆንም፣ ተቀራራቢነት ግን አለው። ምክንያቱም ፍልሚያው የሚካሄደው በሰው እና በእግዚአብሔር ሕግ መካከል ነው። ይህ በፍልሚያ ላይ ያለ ሕግ ደግሞ፣ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ሰንበት ሕግ ዙሪያ ያጠነጥናል። ከእግዚአብሔር ትእዛዛት መካከል ከአንዱ የተነሣ መሞት? አንድ ሰው ከእንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ በአቋራጭ ለመውጣት ምን አመክንዮ ማቅረብ ይችላል?

ሰኔ 13
Jun 20


ተጨማሪ ሀሳብ


ኤለን ጂ ኋይት ከጻፈችው ታላቁ ተጋድሎ ከሚል መጽሕፍ ‹‹የእግዚአብሔር ሕዝብ ነጻ መውጣት›› የሚለውን ርዕስ ገጽ 635-652 ላይ ያንብቡ።

“በዘመናት ሁሉ፣ በቅዱሳን መላእክት በኩል ሕዝቦቹን ለመርዳትና ለማዳን እግዚአብሔር ሰርቷል። ሰማያዊ ፍጡራን በሰዎች ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል። እንደ መብረቅ በሚያንፀባርቅ ልብስ ሆነው ታይተዋል፤ የተጓዥ ልብስ ለብሰው፣ እንደ መንገደኛ ሰዎች ሆነው፣ መጥተዋል። መላእክት የሰው ቅርጽ ይዘው ለእግዚአብሔር ሰዎች ተገልጠዋል። እንደ ደከማቸው አይነት ሆነው በቀትር በዋርካ ዛፍ ስር አርፈዋል። የሰዎችን ቤት መስተንግዶ ተቀብለዋል። በጨለማ ለተዋጡ ተጓዦች እንደ መንገድ መሪ ሆነዋል። በራሳቸው እጅ የመሰዊያውን እሳት አቃጥለዋል። የእስር ቤት በሮችን ከፍተዋል፤ የእግዚአብሔርን አገልጋዮች ነፃ አውጥተዋል። በሰማይ _ አልባሳት አጊጠው ከአዳኙ መቃብር ድንጋዮችን ለማንከባለል መጥተዋል።

መላእክት በሰው ተመስለው፣ ፃድቃን በተሰበሰቡበት ቦታ ሁልጊዜ ይገኛሉ፤ የእግዚአብሔርን ትዕግስት ወሰን ማለፋቸውን አለማለፋቸውን ለመወሰን፣ ሥራቸውን ይመዘግቡ ዘንድ፣ ልክ ወደ ሰዶም እንደሄዱ፣ መላእክት የኃጥአንን ስብሰባዎች ይጎበኛሉ። ጌታ በምሕረት ደስ ይለዋል፤ በእርግጥ ለሚያገለግሉት ለጥቂቶች ሲል፣መቅሰፍቶችን ይገድብና፣ የሰዎችን ሰላምና ፀጥታ ያራዝማል።

እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ኃጢአተኞች፣ በጥቂት ታማኞች ላይ ማፌዝና እነርሱን መጨቆን የሚያስደስታቸው ቢሆንም፣ በሕይወት ለመኖራቸው ምክንያቶቹ እነዚህ ጥቂት ታማኞች ስለሆኑ ለእነርሱ ምን ያህል ባለዕዳ እንደሆኑ አያስተውሉም።” (ታላቁ ተጋድሎ፡ ገጽ 723)።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. ጥቅሱን ያንብቡ፡ 2ጢሞቴ. 1፡7። በእጅጉ በሚያሳስብዎ ትንቢት ነክ ጥቅሱን ያንብቡ፡ 2ጢሞቴ. 1፡7። በእጅጉ በሚያሳስብዎ ትንቢት ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ። በእምነታችን ምክንያት ስደት እንደሚደርስብን በትንቢት ቢነገረንም፣ የፍርሃትን መንፈስ አራግፈን የእግዚአብሔርን የተስፋ መልእክት መጨበጥ የምንችለው እንዴት ነው?

2. ምንም እንኳ ዛሬ በዚህ ወቅት፣ ሰንበት እና እሑድ በመጨረሻዎቹ ክስተቶች ምንም እንኳ ዛሬ በዚህ ወቅት፣ ሰንበት እና እሑድ በመጨረሻዎቹ ክስተቶች መሃል እንዴት ቀዳሚ እና አስኳል ሆነው እንደሚወጡ ለመረዳት ቢያስቸግርም፣ ዓለም እንዴት በፍጥነት እየተቀያየረች እንደሆነ መመልከቱ ግን ተገቢ ነው። ይህ እውነት እምነታችንን በቅጽበት ሊለዋወጡ በሚችሉ ጊዜያዊ ሁናቴዎች ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል ላይ መመስረት እንደሚገባን አስመልክቶ ምን ሊያስተምረን ይችላል?

3. በዳን. ምዕ. 2 እንዲሁም 7 ዙሪያ አሰብ ያድርጉ። ሁሉም የዓለም ልዕለ በዳን. ምዕ. 2 እንዲሁም 7 ዙሪያ አሰብ ያድርጉ። ሁሉም የዓለም ልዕለ ኃያላን መንግሥታት እንደ ተተነበየው መጥተው ሄደዋል። ዛሬ፣ ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት፣ በተተነበየው መሰረት ገቢራዊ እንደሆነ እንገነዘባለን። ከዛሬው እይታችን አኳያ፣ እነሆ አንድ ተጨማሪ መንግሥት ብቻ እንጠብቃለን። ይህ መንግሥት የትኛው ነው? በእርግጥ፣ በተተነበየው መሰረት እንደሚመጣ እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL