የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ማቴ. 12:38–42፣ ዮናስ 3:5–10፣ ራእ. 18:4፣ ዳን. 5:1–31፣ ራእ. 16:12–19፣ 2ቆሮ. 36:22, 23።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እርሱም፣‘እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ የብስንና
ባሕርን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ’
አለ።” (ዮናስ 1፡9)።
ይህ ሳምንት ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት ክስተቶች ያለንን ግንዛቤ ግልጽ ለማድረግ
የሚረዱንን ዘገባዎች ለመጨረሻ ጊዜ የምንመረምርበት ይሆናል። በዚህ
ሳምንት ዮናስ ወደ ነነዌ እንዲያመራ የተሰጠውን ተልዕኮ፣ የባቢሎንን
ውድቀት፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ነጻ ያወጣውንና ወደ ተስፋይቱ ምድር
እንዲመለሱ ያስቻለውን የፋርስ ንጉሥ—ቂሮስ መነሣትን እንመለከታለን።
እንደ ሌሎቹ የመረመርናቸው ታሪኮች ሁሉ እነዚህ ታሪካዊ ዘገባዎች ለእያንዳንዱ
ትውልድ የሚበጅ ጥልቅ ትርጉም አላቸው። ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት በፊት ለሚኖሩ
የመጨረሻዎቹ ትውልዶችም እንዲሁ ልዩ አግባብ አላቸው። በዚህም “ወቅታዊ እውነት”
ብለን የምንጠራውን የጊዜውን ሁኔታ በተሻለ ለመረዳት የሚያስችሉንን በርካታ አላባዎች
ከእነዚህ ታሪክን መሰረት ካደረጉ ዘገባዎች ቆፍረን ማውጣት እንችላለን።
በተመሳሳይ፣ የመጨረሻዎቹን ክስተቶች የሚያሳዩ የማስጠንቀቂ ገጽታ
የተላበሱ መስለው ስለሚታዩ ታሪኮች አንድ ነገር ማስታወስ አለብን። ስፋት ያላቸውን
ርዕሰ ጉዳዮች እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ላይ-ላዩን የተጠቀሱ ጭብጦችን
ስንመለከት፣ ጥንቃቄ ማድረግ እና ለእያንዳንዱ ዝርዝር ሁኔታ የማይመስል ትርጉም
ዐልባ ትንቢታዊ ትንታኔ ለመስጠት ከመሞከር መታቀብ ተገቢ ይሆናል። እንደ
የሱስ ምሳሌዎች ሁሉ፣ ዐበይት ርዕሰ ነጥቦችንና መርኅዎችን ማሰስ ይኖርብናል።
አንዳንድ የተሰወሩ እውነቶችን ለማግኘት ብለን እያንዳንዱ ሽርፍራፊ ዝርዝር ነጥብ
ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ፣ ርዕሰ ነጥቦችንና መርኅዎችን ማጤን ለመጨረሻዎቹ
ቀናት ገጣሚ የሆኑ አላባዎች ላይ መድረስ ያስችላል።
የዮናስ ታሪክ (ዮናስ 1–4) አጭር ቢሆንም ተጽእኖው ግን ታላቅ ነው። በርካታ አማኞች በዚህ ዳተኛ ነቢይ ውስጥ የገዛ ራሳቸውን ነጸብራቅ አግኝተዋል። በተጨማሪም ታሪኩ ወደፊት ፍጻሜ ስለሚያገኙ ክስተቶች አስደናቂ መግለጫዎችንም እንዲሁ ይዟል። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 12፡38-42። የሱስ ለጻሕፍትና ለፈሪሳውያን የጠቀሰው የትኛውን የዮናስ ታሪክ ክፍል ነው? እርሱ በሰጠው መግለጫ ፍርድን በተመለከተ የምናገኛቸው ትምህርቶች ምንድን ናቸው?
የሱስ ከዮናስ ይልቅ እርሱ እንደሚበልጥ ነገራቸው። ወደዚህ ዓለም
የመምጣቱ ትርጉም መስቀል እንደሆነ ያውቅ ነበር፤ እርሱ “የጠፋውን ሊፈልግና
ሊያድን” (ሉቃ. 19፡10) መጥቶአልና። ዮናስ በትልቁ ዓሣ ሆድ ውስጥ ሦስት
ቀናት ያሳለፈው በገዛ ራሱ ኃጢአት የተነሣ ሲሆን፣ የሱስ በመቃብር ውስጥ ለሦስት
ቀናት የቆየው ግን በእኛ ኃጢአት ምክንያት ነው። ይኸውም የጠፉትን ለማዳን
ያስከፈለው ዋጋ ነው።
ዛሬ ዮናስን የምናውቀው ወደ ነነዌ ለመሄድ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ዳተኛ
ነቢይ ነው። ከሰዋዊ ዕይታ አኳያ አሦራውያን በጭካኔ የተሞላ አረመኔያዊ አገዛዝ
ማራመዳቸውን ማስተዋል ብዙ የሚከበድ አይሆንም። የአሦራውያን ጥንታዊ
የግድግዳ ሥዕሎች ሊገመቱ በማይችሉ ጭካኔያዊ ትዕይንቶች የተሞሉ ናቸው። ታዲያ
ወደ እነርሱ ርዕሰ መዲና ጎራ ብሎና ሁኔታውን ተጋፍጦ የንስሐ ስብከት ለመስበክ
ተስፋ የሚያደርግ ማን ነው?
በታሪኩ ውስጥ ወደ መጨረሻዎቹ ትሩፋን እንቅስቃሴ ማመላከት የሚችል አንድ
ወሳኝ ክፍል አለ። ዮናስ ማን እንደሆነ ሲጠየቅ “ ‘እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ የብስንና ባሕርን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ’ ” በሚል የሰጠው መልስ
ከመጀመሪያው መልአክ መልእክት ጋር ተመሳሳይ ነው (ዮሐ. 1፡9፣ ራእ. 14፡
7)። እርሱ “ ‘የብስንና ባሕርን የፈጠረውን’ ” የሚል አጽንኦት ለጌታ መስጠቱ፣
የፈጣሪነት ሥልጣኑን ማመላከቱ እሙን ነው። ይህ እውነታ እርሱን የማምለካችን
ምክንያት መሰረት ሲሆን፣ አምልኮ ደግሞ የመጨረሻዎቹ ክስተቶች አስኳል ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ እኛም በባቢሎን አስተምህሮ ስር ለወደቀው ሰብዓዊ
ወገን እንድናካፍል የተሰጠንን መልእክት ዓለም ጆሮ ዳባ ልበስ—ሲል እያስተዋልን
ነው። ሕዝቤ ሆይ… ከእርሷ ውጡ” (ራእ. 18፡4) ማለት፣ ንስሐ መግባት የግድ
ነው ብሎ ለዓለም መንገር ሲሆን፣ ይህ መልእክት በተቻለ መጠን ደግነት በተሞላው
አኳኋን ቢነገርም እንኳ በርካቶችን እያስቆጣና አሉታዊ ምላሽ ሲሰጡ ማየት እንግዳ
አይደለም። ከእኛ መሃል በመመስከሩ ብቻ አሉታዊ ምላሽ ያላገኘ—አልፎ ተርፎም
በጥላቻ ዓይን ያልታየ ማን አለ? ይህ የዓለም “ሥራው” ሆኗል።
የዮናስ ምን ያህሉ መጠን በእርስዎ ውስጥ አለ? ከዚህ የተሳሳተ አመለካከት
ባሻገር መጓዝ የሚችሉት እንዴት ነው?
ዮናስ ለነነዌ ሕዝብ የሚበጅ በዓይነቱ ለየት ያለ መልእክት ነበረው።
“ዮናስም ወደ ከተማዪቱ ገብቶ የመጀመሪያውን ቀን ከተጓዘ በኋላ ‘ ነነዌ በአርባ
ቀን ውስጥ ትገለበጣለች’ ብሎ ዐወጀ።” (ዮናስ 3፡4)። ስፍራው ሊያመልጡት
በማይችሉት አምላካዊ ፍርድ ስር መውደቁ አንድና ሁለት የለውም። ደግሞስ ይህ
ቃል በቀጥታ ከጌታ ነቢይ የመጣ አልነበረምን?
አዎ ነበር። ታዲያ፣ በነነዌ ላይ ምን ደረሰ? ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዮናስ 3፡5-10።
ትንቢቱ ሳይፈጸም ለምን ቀረ?
መላው የከተማዋ ነዋሪ ንስሐ በመግባቱ በትንቢት የተነገረው ጥፋት፣
ቢያንስ በዚያን ወቅት ሳይደርስ ቀረ። “ሊደርስባቸው የነበረው ጥፋት ተቀለበሰ፤
የእስራኤል አምላክ በመላው አረማዊ ዓለም ከበረ፣ ከፍ ከፍም አለ፤ ሕጉም
ከበሬታ አገኘ። ነነዌ እስከ ቀጣዮቹ በርካታ ዓመታት፣ እንደ አጎራባቾቿ አገራት
በእግዚአብሔር ላይ የመታበይ ሰለባ ሳትሆን ቆየች።—Ellen G. White,
Prophets and Kings, p. 271.
በእነዚያ የመጨረሻዎቹ ቀናት፣ የመጨረሻው መልእክት ለወደቀው ዓለም
በሚቀርብበት ወቅት ከዚህ ተመሳሳይ ክስተት መጠበቅ እንችል ይሆን? መልሱ
አዎ—እና አይሆንም ነው። “ሕዝቤ ሆይ፤ በኀጢአቷ እንዳትተባበሩ፤ ከመቅሠፍቷም
እንዳትካፈሉ፤ ከእርሷ ውጡ” (ራእ. 18፡4) የሚለውን ጥሪ በመላው ዓለም
የሚሰሙና የሚቀበሉ ብዙዎች ይኖራሉ። በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ ሕዝቦች ከአውሬው
በተቃራኒ በመሰለፍ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የሚጠብቁና ለኢየሱስም ታማኝ
ሆነው በትዕግሥት የሚጸኑ ቅዱሳን” (ራእ. 14፡12) አካል ይሆናሉ። እነዚህ
ሕዝቦች እንደ ነነዌዎቹ ሁሉ፣ በጠፉት ላይ ከሚሰጠው የፍርድ ብይን ይተርፋሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ እግዚአብሔር ነነዌ ትጠፋለች ብሎ እንዳስታወቀው
ዓይነት ያሉ አንዳንድ ትንቢቶች—ሕዝቡ ከእርክስናው ካልተመለሰ በቀር ትጠፋለች—
የሚል በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ አንደምታ አላቸው (ኤር. 18፡7-10)።
ሆኖም ሌሎች ትንቢቶች ደግሞ ከእነዚህ በተመሳሳይ በሁኔታዎች ላይ ተመስርተው
አይመጡም። የሰዎች ምላሽ ምንም ይሁን ምን—ፍጻሜ ያገኛሉ። የመጀመሪያው
የክርስቶስ መሲሐዊ ምጽአት እና ዳግም ምጽአት ትንቢቶች፣ የአውሬው ምልክት፣
የመቅሰፍቶቹ መውረድ፣ የመጨረሻው ዘመን ስደት—በሁኔታዎች ላይ የተመሰረቱ
ስላልሆኑ ሰዎች ምንም ቢያደርጉ እንኳ ይፈጸማሉ። በነቢያት የተነገሩት የመጨረሻዎቹ
ክስተቶች ፍጻሜ ሲያገኙ፣ የሰዎች ድርጊት ብሎም ምርጫ የተሰለፉበትን ጎራ ይወስናል።
ለእግዚአብሔር ወይም ለአውሬው መስገድ አስገዳጅ የሚሆንባቸው እነዚያ ቀኖች
ሲመጡ ትክክለኛው ውሳኔ ላይ መድረስ ይችሉ ዘንድ የዛሬ ምርጫዎ ምንድን ነው?
የነነዌ ከተማ በሜዶናውያን እና ባቢሎናውያን (በናቡከደነፆር አባት
በተመራ) ጥምር ጦር ከተሸነፈች (ከክ.ል.በ. 6112) በኋላ፣ የባቢሎን
ከተማ በተሐድሶ ተሞክሮ ውስጥ አለፈች። ከተማዋ ከታላቁ ሕግ አውጪአቸው
ሐሙራቢ ዘመን ወዲህ እንዲህ ያለውን ተሐድሶ አይታ አታውቅም ነበር። በወቅቱ
ከአሦራውያን ወረራ ስጋት ነጻ መሆን የቻለችውና በናቡከደነፆር አስተዳደር ስር
የነበረችው የባቢሎን ከተማ በሐብቷና ተደማጭነቷ ሽምጥ መጋለቧን ተከትሎ
አጎራባች አገራት የበላይነቷን በቁጭት አምነው ከመቀበል ውጪ ሌላ አማራጭ
አልነበራቸውም። እርሷ የዓለም ልዕለ ኃያል ንግሥት ነበረች፤ እናም መበልጸግ
የሚፈልጉ አገሮች ለእርሷ ያላቸውን ታማኝነት ይገልጹ ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ (እንደምንረዳው) ናቡከደነፆር የዳንኤል አምላክ
በእርግጥም የነገሥታት ሁሉ ሕጋዊ ገዢ መሆኑን አምኖ ሞተ (ዳን. 4፡34-37)።
ዳንኤል በቀጣይ ዘገባ የገለጸው በእርሱ ቦታ ሆኖ የገዛውን ብልጣሶር ነበር።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዳን. 5፡1-31። ከዚህ ዘገባ የምናገኛቸው ጠቃሚ መንፈሳዊ
መልእክቶች ምንድን ናቸው? ብልጦሶርን ውሎ አድሮ ስህተት ላይ እንዲወድቅ
መንስዔ የሆነው ምን ነበር?
እጅግ አሳዛኝ የሆነው የዚህ ዘገባ ክፍል የሚገኘው በዳን. 5፡22 እንደሆነ
ይገመታል። ዳንኤል የናቡከደነፆርን ውድቀትና መነሣት አንድ ባንድ ዘርዝሮ
ለንጉሡ ከነገረው በኋላ እንዲህ አለው፡ “ ‘ብልጣሶር ሆይ፥ አንተ ልጁ ስትሆን
ይህን ሁሉ እያወቅህ በሰማይ ጌታ ላይ ኰራህ እንጂ ልብህን አላዋረድህም’ ”
(ዳን. 5፡22 /1962 ትርጉም/)። ይኸውም፣ ምንም እንኳ እውነትን ለማወቅ
የሚያስችለው ዕድል ቢሰጠውም፣ በናቡከደነፆር ላይ ለደረሰው ነገር ሁሉ ምስክር
መሆን ቢችልም—እነዚህን ሁሉ ክስተቶች እንዳላየና እንዳልሰማ መሆንን መረጠ።
በዚህም አባቱን ለብዙ ችግር በዳረገው በዚያው ተመሳሳይ የጥፋት መንገድ ተጓዘ።
ናቡከደነፆር የወርቁን ምስል በማቆም ካደረገው በተመሳሳይ ብልጣሶርም
የዳንኤል አምላክ የተነበየውን ነገር በግልጽ እየተቃወመ ነበር። ብልጣሶር የቤተ መቅደሱን
ንዋየ ቅዱሳት ርኩስ በሆነ መንገድ መጠቀሙ—አይሁዳውያን በባቢሎን ድል ሆነው
በምርኮ እንደዋሉ ሁሉ እነሆ አሁን ደግሞ የአምላካቸው ንዋየ ቅዱሳት በባቢሎን ግዞት
ስር ለመዋሉ አጽንኦት ለመስጠት እንደነበር ይታመናል። በሌላ አነጋገር ውድመታቸውን
በተነበየው በዚህ አምላክ ላይ አሁንም የበላይነት እንደ ነበራቸው ያምናሉ።
ምንም እንኳ ብልጣሶር የበለጠውን ለማወቅ የሚያስችል ከበቂ በላይ
ማስረጃ ቢኖረውም፣ ድርጊቱ ሙሉ በሙሉ በትምክህት ለመወጠሩ አንድና ሁለት
የለውም። እውነቱን ለመገንዘብ የሚያስችል በቂ የአእምሮ ብስለት ቢኖረውም፣
ችግሩ የነበረው ልቡ ላይ ነው። በመጨረሻዎቹ ቀናት፣ የመጨረሻው ቀውስ በዓለም
ላይ ሲከሰት ሰዎችም እንዲሁ፣ እውነቱን የማወቅ ዕድል ይሰጣቸዋል። እንደ
ብልጣሶር ሁሉ ምርጫቸውን የሚወስነው ልባቸው ይሆናል።
ከባቢሎን ጠንካራ ጎኖች አንዱ የኤፍራጥስ ወንዝ ከቅጥሯ ግንቦች ስር
እንዲፈስ ተደርጎ የተሠራበት መንገድ ሲሆን ይህም ከተማዋ ባልተገደበ የውሃ አቅርቦት
አንድትንበሸበሽ አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ የድክመቷ መንስዔም ነበር ለማለት ይቻላል።
ጥንታዊቷ የባቢሎን ንግሥት ኒቶክሪስ ከኤፍራጥስ ወንዝ በተጓዳኝ ቁፋሮ እንዲካሄድ
ያዘዘች ሲሆን፣ ቁፋሮው ወደ ከተማይቱ እንዲያልፍ ተደርጎ የተሠራ የልማት ሥራ
ነበር። ሆኖም በሂደት ሠራተኞች ተግባራቸውን ያለ እንከን ማከናወን እንዲያስችላቸው
በሚል ወንዙ የሚተኛበት ረግረጋማ ስፍራ እንዲፈጠር ተደረገ። ቂሮስ ተቃራኒ ሥራ
ሠርቶ ኤፍራጥስን በማድረቅ ወታደሮቹ በቀላሉ በቅጥሩ ግንብ ስር አልፈው እንዲገቡ
ማድረግ እንደሚችል ተገነዘበ። የከተማውን ቅጥር አልፎ አንዴ ከገባ በኋላ ወንዙን
ተከትሎ የተሠሩ ሌሎች የመከላከያ ግንቦች ቢያገኝም ጥበቃ ግን አልነበራቸውም።
ስለዚህ ከተማዋ በአንድ ሌሊት በእጁ ወደቀች። የጥንቱ ግሪካዊ ታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶተስ
ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይለናል፡ “በባቢሎን ከተማ እምብርት ይኖሩ የነበሩ ሁሉ፣
የከተማው ዳርቻ በጠላት እጅ ስለመውደቁ የሚያውቁት ነገር አልነበረም። ምክንያቱም
ሁሉም የሚጨፍርበትና ራሱን የሚያዝናናበት ታላቅ ድግስ የተደረገበት የግብዣ ወቅት
ነበር።”—Herodotus, The Histories, Tom Holland,
trans. (New York: Penguin, 2015), p. 94. ይህ ድግስ
በዳን. 5 ከተገለጸው ጋር ተመሳሳይ ለመሆኑ የሚያጠራጥር ነገር ሊኖር ይችላል?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዳን. 5፡18-31፣ ራእ. 16፡12-19። በራእይ መጽሐፍ
ከቀረቡ አንዳንድ መቅሰፍቶች እና በባቢሎን ውድቀት ታሪክ መሃል ምን
ተመሳሳይነት አለ?
የሱስ የዘመኑን ምልክቶች አንዴት መለየት እንዳለባቸው አስመልክቶ ደቀ
መዛሙርቱን እንዲህ ሲል አስጠንቅቋል፡ “ ‘እንግዲህ ጌታችሁ የሚመጣበትን ቀን
ስለማታውቁ ነቅታችሁ ጠብቁ። ይህን ልብ በሉ፤ ባለቤት ሌሊት ሌባ በየትኛው
ሰዓት እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ፣ በነቃ፣ ቤቱም እንዳይደፈር በተጠባበቀ ነበር’
” (ማቴ. 24፡42-43)። በባቢሎን ውድቀት እንደሆነው ሁሉ፣ የክርስቶስ
በድንገት መገለጥ ዘመናዊቷን ባቢሎን በድንገት ያገኛታል። ይሁን እንጂ ነገሮች
በዚህ መልኩ መሄድ የለባቸውም፣ ምክንያቱም በቅርቡ ስለሚገለጠው የሱስ
በርካታ ትንቢታዊ ማስረጃዎች ተሰጥተውናል።
ዓለምን ድንገተኛ ሁኔታ የሚገጥማት እግዚአብሔር በትንቢት የተናገረውን
ባለማወቋ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ይሆናል ያለውን ለማመን ባለመምረጧ ነው።
ጥቅሱን ያንብቡ፡ ራእ. 16፡15። በእነዚህ የፍጻሜ ጊዜ ማስጠንቀቂያዎች እንኳ
ሳየቀር የምናገኘው የወንጌል የምሥራች መልእክት ምንድን ነው? “ዕራቍቱን
እንዳይሆን ኀፍረቱም እንዳይታይ” ሲል ምን ማለቱ ነው?
ቂሮስ የባቢሎንን ከተማ ከወረረና ከዘረፈ በኋላ በርካታ ዓመታት የፈጀው
የእግዚአብሔር ሕዝቦች የግዞት ዘመን ወደ ፍጻሜ መጣ። እናም ወደ ተስፋይቱ ምድር
ተመልሰው ቤተ መቅደሱን እንደገና ይገነቡ ዘንድ ፋርሳውያን ፈቀዱላቸው። በቂሮስ
የግዛት ዘመን የፋርስ ግዛት በታሪክ ውስጥ ትልቁን ቦታ የያዘ ሆነ። ይህን አስመልክቶ
የታሪክ ጸሐፊው ቶም ሆላንድ እንዲህ ብሏል፡ “ዓለም ከዚያ ቀደም አይታው
የማታውቅ የበርካታ ነገሮችን ስብስብ የያዘ ታላቅ ግዛት”—Tom Holland,
Dominion Basic Books, Kindle Edition, p. 25.
እንዲሁም በፋርሳውያን ልማድና ወግ መሰረት ቂሮስ “ታላቁ ንጉሥ”
ወይም “የነገሥታት ንጉሥ” ተብሎ እስከመጠራት ደረሰ።
ቂሮስ ክርስቶስ ዳግም ሲገለጥ የሚሆነውን ነገር ገልጦ ያሳያል፡ እርሱ በባቢሎን
ላይ ጦርነት ከፍቶ እና በመጨረሻ ሕዝቡ ከባቢሎን ያመልጥ ዘንድ ነፃ አውጥቶ ወደ
ተስፋይቱ ምድር የሚመልስ ከምስራቅ የሚመጣው (ማቴ. 24፡27) ንጉሥ ነው
(ራእ. 19፡11-16)። እግዚአብሔር “ለቀባሁት” (ኢሳ. 45፡1) ሲል ስለ ቂሮስ
መናገሩ፣ ይህ ስመ ጥር ፋርሳዊ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ነፃ ስላወጣ ብቻ ሳይሆን፣
በባቢሎን ላይ ያካሄደው ውጊያ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ምሳሌ ከመሆኑ የተነሣ ነው።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 2ዜና 36፡22-23። የቂሮስ ታሪክ ከናቡከደነፆር ታሪክ ጋር
የሚመሳሰለው በየትኞቹ መንገዶች ነው? የሚለያየውስ? የአዋጁ አንደምታ
ምንድን ነው? ደግሞስ፣ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ገቢራዊ በሆነው በየሱስ
የመጀመሪያ ምጽአት ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል?
የቀደመው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ቅደም ተከተል፣ በእኛ ዘመን
በሚልክያስ መጽሐፍ እንዲያልቅ የተደረገው አይደለም። ይልቁንም ብሉይ ኪዳን
የተጠናቀቀው በዚህ ከቂሮስ በተላለፈው መግለጫ ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት ሕገ
ደንብ መሰረት ቀጣዩ ክፍል ማቴዎስ ሲሆን፣ መጽሐፉ በክርስቶስ መወለድ ይኸውም
የኦሪት ምሳሌ ፍጻሜ በሚያገኝበት ቂሮስ ይጀምራል። ቂሮስ ምድራዊውን ቤተ
መቅደስ መልሶ የመገንባት ሥራ ሲያደራጅ—የሱስ ወደ ዳግም ምጽአቱና ነጻነታችንን
ወደ ምንቀዳጅበት የሚያመራውን የሰማያዊውን መቅደስ አገልግሎት መርቆ ከፈተ።
እርግጥ ነው፣ ቂሮስ የክርስቶስ ፍጹም ምሳሌ አልነበረም። ቢሆንም እርሱ
የ “አዳኙ” ምሳሌ ሆኖ በሰፊው ይሠራል።
እግዚአብሔር ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ አንድን አረማዊ ንጉሥ በእንዲህ ያለ ልዩ መንገድ
መጠቀሙ ምንኛ አስደሳች ነው! ማለትም፣ ነገሮች የትኛውንም ዓይነት ውጫዊ ገጽታ
ተላብሰው ቢታዩንም እንኳ፣ ጌታ በትንቢት በተነገረው መሰረት የመጨረሻዎቹን
ጊዜያት ክስተቶች እውን የማድረጉን እውነት እንዴት ማስተዋል እንችላለን?
Read Ellen G. White, “The Unseen
Watcher,” pp. 535–538, in Prophets and Kings.
“ግቡን ለማሳካት በንቁ እርምጃ ሂደቶች ውስጥ የሚያልፍ እያንዳንዱ
መንግሥት ግዛቱን በምድር ላይ ያንሰራፋ ዘንድ የተፈቀደለት ሲሆን፣ ይኸውም
የቅዱሱን ጠባቂ ዓላማ ይፈጽም እንደሆነ ለማየት ነው። ትንቢቱ የዓለምን ልዕለ
ኃያላን ግዛቶች ማለትም የባቢሎንን፣ የሜዶንና ፋርስን፣ የግሪክን እና የሮምን እድገትና
ግስጋሴ በጉልህ አሳይቷል። በእነዚህ በእያንዳንዳቸው መንግሥታት፣ አነስተኛ አቅም
ባላቸው ትናንሽ አገራት ከሚሆነው በተመሳሳይ ታሪክ ራሱን ሲደግም ተስተውሏል።
ሁሉም ልዕለ ኃያላን የየራሳቸው መፈተኛ ወቅቶች የነበሯቸው ሲሆን፤ አንዳቸውም
ሳይቀሩ ወድቀዋል፣ ክብርና ሞገሳቸው ተገፏል፣ ጉልበታቸውም ከድቷቸዋል። አገራት
አምላካዊውን መርኅዎች ለመቀበል አሻፈረኝ ባሉ ቁጥር፣ ይህ እምቢተኝነታቸው ለገዛ
ራሳቸው ውድቀትና ጥፋት ሲዳርጋቸው ተስተውሏል። በመለኮት ላይ የመሠልጠን
ፍላጎት እና ዓላማ ግልጽ በሆነ መንገድ ለዘመናት ሥራ ላይ ሲውል ታይቷል”—
Ellen G. White, Prophets and Kings, p. 535.
በኤርምያስ 18 ላይ ነቢዩ ሸክላ ሠሪው በጭቃ ቅርጽ የማውጣትና
የማበጃጀት ዕደ ጥበብ ሥራ ሲሠራ ተመልክቷል። እግዚአብሔር በመጽሐፍ
ቅዱሳዊ ትንቢቶች ውስጥ ያለውን በሁኔታዎች ላይ የመመስረት መርኅ ለማስረዳት
የተጠቀመው ሸክላ ሠሪ ጭቃውን ሲቀርጽ የሚያሳየውን ምስል ነው። ጉዳዩን
መረዳታችንን ለማረጋገጥ ሲል ብቻ፣ ጌታ እንዲህ ሲል በኤርምያስ በኩል ተናግሯል፡
“ ‘አንድ ሕዝብ ወይም መንግሥት እንዲነቀል፣ እንዲፈርስና እንዲጠፋ በተናገርሁ
ጊዜ፣ ያስጠነቀቅሁት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፣ እኔ ላደርስበት ያሰብሁትን ክፉ ነገር
እተዋለሁ። በሌላም ጊዜ አንድን ሕዝብ ወይም መንግሥት አንጸውና እተክለው ዘንድ
ተናግሬ፣ በፊቴ ክፉ ነገር ቢያደርግና ባይታዘዘኝ፣ አደርግለታለሁ ብዬ ያሰብሁትን
መልካም ነገር አስቀርበታለሁ።’ ” (ኤር. 18፡7-10)።
1. አምላካዊው ፍርድ ከእውነት ርቀው ከሄዱት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ይልቅ
አምላካዊው ፍርድ ከእውነት ርቀው ከሄዱት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ይልቅ
ለነነዌ ቀላል እንደሚሆን የሱስ የተናገረውን ያስቡ (ማቴ. 12:39–
42)። የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ማስጠንቀቂያ ምን ትምህርት
ማግኘት ትችላለች?
2. በእያንዳንዱ ሥርዓት እግር ተተኪ አገዛዝ “ታሪክ ራሱን ደግማል” የሚለውን
በእያንዳንዱ ሥርዓት እግር ተተኪ አገዛዝ “ታሪክ ራሱን ደግማል” የሚለውን
የኤለን ጂ. ኋይት አባባል ልብ ይበሉ። በትንቢት በተዘረዘሩት በሁሉም
ልዕለ ኃያል መንግሥታት ውስጥ ምን የጋራ ነጥብ ይመለከታሉ? ተመሳሳይ
ትንቢታዊ መንገዶችን የተከተሉባቸው አቅጣጫዎች የትኞቹ ናቸው? የዛሬው
ዓለም እነርሱን እየተከተለ ያለው እንዴት ነው?
3. ብዙውን ጊዜ ሰዎችን ከእምነት የሚያርቀው አእምሮ፣ ማለትም የማሰብ
ብዙውን ጊዜ ሰዎችን ከእምነት የሚያርቀው አእምሮ፣ ማለትም የማሰብ
ችሎታ ሳይሆን ልብ በመሆኑ ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ አሰብ ያድርጉ። ይህን
መገንዘብዎ ለሌሎች በሚሰጡት ምስክርነት ላይ ተጽእኖ የሚኖረው እንዴት ነው?
ማሳሰቢያ
ድርጅቱ