የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ



1ኛ ሩብ ዓመት 2025


የካቲት 15 - 21

9ኛ ትምህርት

Feb 22 - 28




አለማትን ያካተተው ተጋድሎ



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ማቴ. 13:24–27፣ ዘፍ. 1:31፣ ሕዝ. 28:12–19፣ ኢሳ. 14:12–15፣ ማቴ. 4:1–11፣ ዮሐ. 8:44, 45።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ” (ዘፍ 3፡15)።

በክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ያለው ታላቁ ተጋድሎ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እምብርት ነው። ምንም እንኳን በእግዚአብሔር እና በወደቁትና በአምላካቸው ላይ ባመፁት ሰማያዊ ፍጥረታት መካከል ያለው አለማቀፋዊው ተጋድሎ ዋነኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ ቢሆንም (ማቴ. 13፡24– 30፣ 37–39፤ ራእይ 12፡7–10)፣ እንዲሁም በብዙ የክርስትና ወጎች ውስጥ ቢገኝም፣ ብዙ ክርስቲያኖች ይህንን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል ወይም ችላ ብለውታል።

ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር ግን፣ የአለማቀፋዊው ተጋድሎ ጭብጥ የሆነው የእግዚአብሔር መንግሥት በዲያብሎስና በመላእክቱ የሚደርስበት ተቃውሞ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ያሉ ታሪኮችን ባለመረዳት ካልሆነ በስተቀር ችላ ልንለው የምንችለው ጉዳይ አይደለም። ወንጌል ብቻ እንኳን እግዚአብሔርን በሚቃወሙት በዲያቢሎስና በአጋንንት ታሪኮች የተሞላ ነው።

በዚህ ሳምንት በአንዳንድ ወሳኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መሠረት የሚከተሉት ሁለት ጥያቄዎች እንዴት መልስ ሊያገኙ እንደሚችሉ እናያለን፡-

በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል አለማቀፋዊ ተጋድሎ እንዳለ የሚያስተምረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው?

በቃሉ መሠረት የተጋድሎው ሁኔታ ምን ይመስላል? የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት *የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።

የካቲት 16
Feb 23

ጠላት ይህን አደረገ


ማቴ. 13:24–27ን ያንብቡ። ምሳሌው በዓለማችን ውስጥ ያለውን ክፋት እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው?



ኢየሱስ በእርሻው ላይ መልካም ዘር ብቻ ስለዘራ አንድ የመሬት ባለቤት ታሪክ ይናገራል። ይሁን እንጂ እንክርዳድ በስንዴው መካከል በቀለ። ይህን ሲያዩ አገልጋዮቹ ባለቤቱን ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት” (ማቴ. 13:27)። ይህ ዛሬም ስለ ክፋት ሚስጥር በተደጋጋሚ ከሚጠየቀው ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ ነው፡- እግዚአብሔር ዓለምን ሙሉ በሙሉ መልካም አድርጎ ከፈጠረ፣ ለምን በውስጡ ክፋት ሊኖር ቻለ? ማቴ. 13፡28–30ን በማቴ. 13፡37–40 ላይ ክርስቶስ ከሰጠው ማብራሪያ አንጻር ያንብቡ። ይህ ደግሞ ስለ አለማቀፋዊው ተጋድሎ ምንነት የሚያስረዳን እንዴት ነው?



ጌታው ለአገልጋዮቹ ጥያቄ ሲመልስ፡- “ጠላት ይህን አደረገ” አላቸው (ማቴ. 13፡28)። ኢየሱስ በኋላ ላይ “መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው” በማለት ገልጾታል፤ እርሱም ኢየሱስ ራሱ ነው (ማቴ. 13:37)። ቀጥሎም ሲያብራራ “እርሻው ዓለም ነው” (ማቴ.13:38)፣ እንክርዳዱን “የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው” (ማቴ.13:39) በማለት በክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ያለውን አለማቀፋዊ ተጋድሎ በግልፅ ያሳያል። በዓለም ላይ ክፋት ያለው ለምንድን ነው? ክፋት ጌታውን የሚቃወመው የጠላት (የዲያብሎስ) ውጤት ነው። “ጠላት ይህን አደረገ” (ማቴ. 13፡28)። አለማትን ያካተተው ተጋድሎ

ይህ መልስ ግን “እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን?” የሚለውን ተከታይ ጥያቄ አስነሳ (ማቴ. 13፡28)። በሌላ አገላለጽ ክፋት ለምን ወዲያውኑ አይነቀልም? የሚል ነው። ‘‘እርሱ ግን፡- እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም። ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ’’ ብሎ መለሰላቸው (ማቴ. 13፡29, 30፣ ከማር. 4፡29 ጋር ያስተያዩ)።

በምሳሌው መሠረት እግዚአብሔር በመጨረሻ ክፋትን ያስወግዳል፣ ነገር ግን ያለጊዜው መንቀል በመልካሙ ላይ የማይቀለበስ የጎንዮሽ ጉዳት ያስከትላል።

እንክርዳዱን ከስንዴው አሁን ለመንቀል መፈለግ የሚያመጣቸው አንዳንድ አደጋዎች ምንድን ናቸው? ይህ ሲባል ግን የሚያጋጥመንን ክፋት ችላ ማለት አለብን ማለት ነውን?

የካቲት 17
Feb 24

በምድር ላይ የተጋድሎው መንስኤ


በምሳሌው ላይ ባለቤቱ ጥሩ ዘር ብቻ ከዘራ በእርሻው ላይ ለምን መጥፎ ዘር በቀለ? ከሚለው ጥያቄ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሌላው ጥያቄ፡- እግዚአብሔር ዓለምን ሙሉ በሙሉ መልካም አድርጎ ከፈጠረ፣ ክፋት እንዴት ሊመጣ ቻለ? የሚለው ነው።

ዘፍ. 1:31ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ፍጥረትን ፈጥሮ በጨረሰ ጊዜ ስለ ፍጥረት ሁኔታ የተናገራቸው ቃላት የሚገልጹት ምንድን ነው? ይህስ መልስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?



እንደ ዘፍ. 1:31 አባባል እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ ሲጨርስ “እጅግ መልካም” ነበር ይላል። በዘፍ. 1 ላይ እግዚአብሔር ይህችን ዓለም ሲፈጥር ምንም አይነት የክፋት ፍንጭ አልነበረም። ታዲያ ክፋት እንዴት ወደ ሰዎች መጣ? ዘፍ. 3:1-7ን ያንብቡ። ክፋት ወደ ምድር እንዴት እንደ መጣ ይህ ምን ይነግረናል? ይህ በአለማቀፋዊው ተጋድሎ ምንነት ላይ ምን ያስተምረናል? (ራዕ. 12:7–9ን ይመልከቱ)



የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

በዚህ ታሪክ ውስጥ እባቡ በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ ያነሳቸውን ውሸቶች እናያለን። በራዕ. 12፡7-9 ላይ እባቡ ዲያብሎስ ራሱ (“የቀደመው እባብ”) እንደሆነ ይናገራል። እባቡ በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ጥርጣሬን ለመፍጠር ጥያቄን ይጠቀማል፤ በጥያቄውም እግዚአብሔር ያዘዘውን ለመቀልበስ ሞክሯል። ከዚያም እባቡ ለሔዋን “ሞትን አትሞቱም” በማለት እግዚአብሔር የተናገረውን በቀጥታ ይሞግታል (ዘፍ. 3፡4)።

ከሁለቱ አንዳቸው ማለትም እባቡ ወይም እግዚአብሔር ሔዋንን ዋሽተዋታል፣ እርሷም አሁን እባቡ ወይም አምላክ የተናገራትን ለማመን መምረጥ ነበረባት።

በዚህና በሌሎች ጥቅሶች ውስጥ፣ የዚህ ተጋድሎ ትኩረት በዋናነት ምንና ማንን ማመን ላይ ነው፤ ይህም ራሱ ከፍቅር ጋር የተያያዘ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ስለ አንድ ሰው ያለህ እምነት፣ በሰውየው ስብዕና እና ሊታመን በመቻሉ የተመረኮዘ ሆኖ፣ ያንን ግለሰብ ለመውደድም ሆነ ለማመን ብሎም የሚነግርህን ለመስማት ተጽእኖ ያሳድርብሃል።

ዘፍ. 3:15ን ያንብቡ። የሴቲቱ ዘር ማለትም መሲሑ የእባቡን ጭንቅላት እንደሚቀጠቅጠው እግዚአብሔር ለእባቡ የተናገረው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጀመሪያው ወንጌል በመባል ይታወቃል። ይህ የተጋድሎውን እውነታ የሚያረጋግጠውና በተጋድሎውም ውስጥ ተስፋ የሚሰጠን እንዴት ነው?

የካቲት 18
Feb 25

በሰማይ የተጋድሎው መንስኤ


ዘፍ. 1–3 ክፋት አዳምና ሔዋን ከመውደቃቸው በፊት እንደነበረ ያሳያል። በፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ “ክፋት” “መልካሙንና ክፉውን በሚያስታውቀው ዛፍ” ስም ተከስቷል (ዘፍ. 2፡9, 17)። ከዚያም የሚዋሸው ራሱ እባቡ ሆኖ ሳለ፣ እግዚአብሔርን ይዋሻል ብሎ ከሰሰ። የእባቡ መኖርና (ራዕ. 12፡9) መዋሸቱ፣ የክፋትን እውነታ ያሳያል። ስለዚህ ከውድቀት በፊት በኤደን ውስጥ እንኳን የክፋት መኖር ተገልጧል። አለማትን ያካተተው ተጋድሎ ሕዝ. 28:12–19ን ከዘጸ. 25:19, 20 አንጻር ያንብቡ። የዚህ ፍጡር ውድቀት ምን አይነት ነው?



በዚህ ጥቅስ መሠረት የክፋት መንስኤና አለማቀፋዊው ተጋድሎ የጀመረው በሰማይ ነው። ሰይጣን በመባል የሚታወቀው ፍጡር፣ ከመውደቁ በፊት የሚጋርድ ኪሩብ ነበር። በተጨማሪም “ጥበብን የተሞላህ፣ ውበትህም የተፈጸመ፣ መደምደሚያ አንተ ነህ። በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ” ይላል (ሕዝ. 28፡12, 13)። ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ ለሰብዓዊው የጢሮስ ንጉሥ (ወይም ለሌላ ሰው) ሊባሉ አይችልም። ስለዚህ እዚህ ላይ ስለ ሉሲፈር ውድቀት ፍንጭ እንደተሰጠን እናውቃለን።

ኢሳ. 14:12–15ን ንብቡ። ይህ ስለ ታላቁ ተጋድሎ መንስኤ ምን ተጨማሪ ብርሃን ይሰጠናል?



በኢሳ. 14 መሠረት ሉሲፈር ራሱን ከፍ ከፍ ለማድረግና እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ወሰነ። ይህ ጥቅስ በሕዝ. 28 ላይ የተመለከትነውን “በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል” (ሕዝ. 28፡17) የሚለውን የሚያጠናክር ሲሆን፣ ውበቱ ያማረ አድርጎ የፈጠረውን አምላክ እንዲያከብር ሊያደርገው ይገባ ነበር። ይልቁንም ኩሩ ሆነ። ይባስ ብሎ በትዕቢት የእግዚአብሔርን ቦታ ለመውሰድና እርሱን ለመስደብ ተነሳ። በሕዝ. 28፡16 ላይ “ንግድ” የሚለው ቃል የዕብራይጡ ትርጉም “ስም ማጥፋት” ማለት ሲሆን፣ ሰይጣን በእግዚአብሔር እና በእኛም ላይ እንዴት እንደሚሠራ የሚያመለክት ነው።

የወደቀው ሉሲፈር በመጀመሪያ “ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ በደል እስኪገኝበት ድረስ በመንገዱ ፍጹም ነበረ” (ሕዝ. 28:15) የሚለውን እውነታ እንዴት እንረዳዋለን? ፍጹም የሆነ ፍጡር፣ “ፍጹም” መሆን እውነተኛ የምርጫ ነፃነትን ካላካተተ በስተቀር፣ እንዴት ሊወድቅ ይችላል? የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የካቲት 19
Feb 26

ብትሰግድልኝ


ሰይጣን የእግዚአብሔርን ዙፋን ለመንጠቅ ያደረገው ጥረት በማቴ. 4 እና በሉቃ. 4 ላይ በሚገኙት ፈተናዎች ውስጥ ተገልጧል። በኢየሱስ እና በፈታኙ መካከል በነበረው አስገራሚ ፍጥጫ፣ ስለ ተጋድሎው ምንነት ብዙ ነገር ተገልጧል። እዚህ ላይ በክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ያለውን የታላቁን ተጋድሎ እውነታ በግልጽና ስዕላዊ በሆነ መልኩ እናያለን።

ማቴ. 4:1-11ን ያንብቡ። እዚህ ላይ በክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ያለው ታላቁ ተጋድሎ እንዴት ተገለጠ?



መንፈስ ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ የመራበት ዓላማ “ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ” ነው (ማቴ. 4፡1)። ኢየሱስ አስቀድሞ የታቀደውን ይህንን ፍጥጫ ከመጋፈጡ በፊት ለአርባ ቀናት ጾሟል። ስለዚህ ዲያብሎስ በመጣ ጊዜ፣ የኢየሱስን ከፍተኛ ረሃብ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ድንጋዮቹን ወደ እንጀራ እንዲለውጣቸው ፈተነው።

ኢየሱስ ግን ይህንን ፈተና በቃሉ ተጋፍጦታል፤ የሰይጣንም ተንኮል ከሽፏል።

ከዚያም ኢየሱስን በዘፈቀደ ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ እርምጃ እንዲወስድ ለማድረግ፣ ዲያብሎስ ኢየሱስን ከቤተ መቅደሱ ጫፍ ላይ ራሱን እንዲጥል ፈተነው። ሰይጣን ቃሉን በማጣመም፣ ኢየሱስ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ መላእክት እንደሚጠብቁት ተናገረ ። ነገር ግን ቃሉን በትክክል በማንበቡ፣ ኢየሱስ እንደገና ፈተናውን ተቋቋመ።

ሦስተኛው ፈተና ዲያቢሎስ ሊፈጽመው የፈለገውን በግልጽ ያሳያል።

ኢየሱስ እንዲሰግድለት ፈልጓል። ሰይጣን ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገባውን አምልኮ ለመቀማት ሞክሯል።

ይህን ለማድረግ ደግሞ ኢየሱስን “የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፣ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” ይለዋል አለማትን ያካተተው ተጋድሎ (ማቴ. 4:8, 9 )። በእርግጥም ከማቴዎስ ጋር በሚመሳሰለው በሉቃ. 4፡6 ዲያብሎስ እንዲህ ይላል፡- “ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል፣ ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁ” (ሉቃስ 4፡6)።

አሁንም ኢየሱስ ፈተናውን በቃሉ ተቋቋመው፤ ሰይጣንም እንደገና ሳይሳካለት ቀረ። በሦስቱም ፈተናዎች የጠላትን ጥቃት ለመከላከል ኢየሱስ ቃሉን ተጠቅሟል።

ኤፌ. 6፡12 “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ” በማለት ያስታውሰናል። ምንም እንኳን በፍርሃት መኖር ባይገባንም፣ በዙሪያችን ያለውን ትግል ሁልጊዜ ማስታወስ ያለብን ለምንድን ነው?

የካቲት 20
Feb 27

የአለማቀፋዊው ተጋድሎ ይዘት


በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ስላለው አለማቀፋዊ ተጋድሎ የሚያስተምሩ አንዳንድ ክፍሎችን ተመልክተናል። ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ተጋድሎ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ማን ሊቃወመው ይችላል? አለማቀፋዊ ተጋድሎ የኃይል ጉዳይ ቢሆን ኖሮ፣ ሳይጀመር በፊት ያበቃ ነበር። ስለዚህ የተለየ ዓይነት መሆን አለበት። በእርግጥ ቃሉ ተጋድሎው በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ የተነሳ ክርክር እንደሆነ ይገልፃል - ዲያብሎስ እግዚአብሔርን ፍጹም መልካምና አፍቃሪ አይደለም እያለ በማጥላላት ይከሰዋል።

እንደዚህ አይነቱን ክስ የሁለቱን ተፎካካሪዎች ባሕርይ በማወዳደር እንጂ በኃይል ወይም በጉልበት መርታት አይቻልም።

“ለኃጢአት መፍትሄ ለማምጣት እግዚአብሔር ጽድቅንና እውነትን ብቻ ይጠቀማል። ሰይጣን ግን አምላክ የማይጠቀማቸውን ሽንገላንና ማታለልን ይጠቀማል። በመላእክቱ ፊት የእግዚአብሔርን ቃል በማጣመምና የአስተዳደሩን እቅድ በተሳሳተ መንገድ በማቅረብ፣ እግዚአብሔር በሰማይ ነዋሪዎች ላይ ሕጎችንና ድንቦችን ማውጣቱ አግባብ አይደለም አለ። ፍጡራኑ እንዲገዙለትና እንዲታዘዙት የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት የሚፈልገው ራሱን ከፍ ለማድረግ ብቻ ነው አለ። ስለዚህ በሰማይ ነዋሪዎችና በዓለማት ሁሉ ፊት የእግዚአብሔር መንግሥት ፍትሃዊ፣ ሕጉም ፍጹም እንደሆነ መገለጽ ነበረበት። ሰይጣን ራሱ ዓለማት መልካም እንዲሆኑ የሚፈልግ እንደሆነ አስመስሎ ነበር። ሥልጣንን በኃይል ለመንጠቅ የሚፈልገውን ጠላት እውነተኛ ባሕርይና አላማ ሁሉም ሊረዱት ይገባ ነበር። በክፉ ሥራዎቹ ማንነቱን ይገልጽ ዘንድ ጊዜ የግድ ያስፈልገው ነበር።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ. 498. ዮሐ. 8:44, 45ን ከራዕ. 12:7–9 አንፃር ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች ስለ ዲያብሎስ ባሕርይና ስለ ስልቱ ምን ይገልፃሉ?



ከመጀመሪያ ጀምሮ የዲያቢሎስ እቅድ እግዚአብሔር በእውነት ፍትሃዊና አፍቃሪ እንዳልሆነ እና ሕጉም ጨቋኝና ጎጂ እንደሆነ ፍጥረታት እንዲያምኑ ለማድረግ መሞከር ነው። ኢየሱስ ዲያብሎስን “ሐሰተኛ የሐሰትም አባት” ብሎ መጥራቱ ምንም አያስደንቅም (ዮሐ. 8፡44)። በአንጻሩ ኢየሱስ የመጣው “ለእውነት ለመመስከር” (ዮሐ. 18፡37) እና በቀጥታ የሰይጣንን ውሸቶችና ስድቦች ለመቃወም፣ ብሎም ዲያብሎስንና ኃይሉን ለማሸነፍና በመጨረሻም ለማጥፋት ነው (1ኛ ዮሐ. 3፡8፣ ዕብ.2፡14)።

ራዕ. 12:9, 10 ሰይጣንን (1) “የቀደመው እባብ” ፣ (2) በሰማይ ዙፋን የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚከስ እና (3) ዓለምን በማሳት የሚገዛ ዘንዶ እንደሆነ ይገልጸዋል። “ዲያብሎስ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ተሳዳቢ (ስም አጥፊ)” ማለት ሲሆን የተጋድሎው ምንነት በእግዚአብሔር ባሕርይ በማመን ላይ መሆኑን በድጋሚ ያሳያል።

የካቲት 21
Feb 28


ተጨማሪ ሀሳብ


ታላቁ ተጋድሎ ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “የክፋት መንስኤ” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 492–504 ያንብቡ።

“ለኃጢአት መከሰት እግዚአብሔር በጭራሽ ተጠያቂ እንዳልሆነ በቃሉ ውስጥ ከሚናገረው በላይ በግልጽ የተነገረ ሌላ ጉዳይ የለም፤ ለአመፅ መነሳት አለማትን ያካተተው ተጋድሎ ምክንያት የሚሆን በዘፈቀደ የተነፈገ መለኮታዊ ፀጋ፣ በመለኮታዊውም መንግሥት ውስጥ እንከን አልነበረም። ኃጢአት ለመኖሩ ምንም ምክንያት የማይገኝለት ሰርጎ- ገብ ነው። ሚስጥራዊና ምክንያት አልባ ነው፤ ሰበብ መፈለግ የኃጢአትን መከሰት መደገፍ ነው። . . . ሰይጣን ወዲያውኑ ቢደመሰስ ኖሮ፣ የሰማይና የሌሎች ዓለማት ነዋሪዎች እግዚአብሔርን በፍቅር ሳይሆን በፍርሃት ባገለገሉት ነበር። የአሳቹ ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ባልጠፋ ነበር፤ የዓመፅ መንፈስም ፈጽሞ አይወገድም ነበር። ክፋት እንዲጎመራ መፈቀድ ነበረበት። ማብቂያ በሌላቸው ዘመናት ሁሉ ለዓለማት ጥቅም ሲባል፣ በመለኮታዊው መንግሥት ላይ የሰነዘራቸው ክሶች በሁሉም ፍጥረታት ዘንድ በእውነተኛው ብርሃን እንዲታዩ፣ የእግዚአብሔር ፍርድ፣ ምሕረትና የማይለወጠው ሕጉ ለዘላለም ጥያቄ እንዳይነሳባቸው፣ የሰይጣን መርሆዎች ፍሬ ማፍራት ነበረባቸው። ”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ ፣ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ. 492, 493, 499


የመወያያ ጥያቄዎች




1. ብዙ ሰዎች እንደ ሉሲፈር ያለ ኃጢአት የሌለበት ፍጡር ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት ኃጢአት ሊሠራ ቻለ ብለው ይገረማሉ። ለምንድነው ኃጢአት እጅግ “ምስጢራዊ” እና “ምክንያት አልባ የሆነው”? ይህንን የመጀመሪያ ኃጢአት ያለ ሰበብ ወይም ያለ ምክንያት እንዴት ልንገልጸው እንችላለን? ይኸውም የኃጢአትን መነሻ ማስረዳት ምክንያት እንደማቅረብ የሚሆነው ለምንድነው?

2. እግዚአብሔር ሰይጣንን ወዲያውኑ ያላጠፋው ለምንድን ነው? ክፋት 'እንዲጎመራ የተፈቀደው' ለምንድን ነው? ይህ “ማብቂያ በሌላቸው ዘመናት ሁሉ ለዓለማት የሚበጀው” እንዴት ነው?

3. በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል ያለው ተጋድሎ የስልጣን ሳይሆን የተለዮ መልክ ያለው መሆኑን መረዳት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የባሕርይ ተጋድሎ መሆኑን መረዳት ከስልጣን ተጋድሎ ይልቅ እንዴት ትርጉም ይሰጠናል?

4. የተጋድሎውን ምንነት መረዳቱ ግርዶሹን በማስወገድ፣ የራስዎ ሕይወት የአለማትን ተጋድሎ በትንሹ እንዴት ሊያሳይ ይችላል? አሁን እንኳን የዚህን ተጋድሎ እውነታ በሕይወትዎ በምን መልክ እያለፉበት ነው? ከማን ወገን እንደሆኑ በሚያሳይ መንገድ እንዴት ምላሽ መስጠት ይችላሉ?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL