የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ



1ኛ ሩብ ዓመት 2025


የካቲት 22 - 28

10ኛ ትምህርት

Mar 1 - 7




የተጋድሎው መርሆዎች



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዳን. 10፡1–14፣ ራዕ. 13፡1–8፣ ኢዮ. 1፡1–12፣ ኢዮ. 2፡1–7፣ ዮሐ. 12፡31፣ ዮሐ. 14፡30፣ ማር. 6፡5፣ ማር. 9፡29።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው÷ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና። ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ” (1ኛ ዮሐንስ 3፡8)።

የአለማትን ተጋድሎ ምንነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ታሪክ በ1ኛ ነገ. 18፡19-40 ላይ ይገኛል። ኤልያስ በቀርሜሎስ ተራራ ላይ በነበረ ጊዜ ጌታ “የአሕዛብ አማልክት” የተባሉትን ያጋልጣቸዋል። ሆኖም እነዚህ “አማልክት” የአረማውያን ምናባዊ ፈጠራዎች ከመሆናቸው ባሻገር ከበስተጀርባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። በእሥራኤል ዙሪያ የነበሩ አህዛብ እያመለክን ነው ብለው ከሚያስቡት “አማልክት” ጀርባ በእርግጥም ሌላ ነገር ነበር።

“እግዚአብሔር ላልሆኑ አጋንንት፥ ለማያውቋቸውም አማልክት፥ በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶች አባቶቻቸውም ላልፈሩአቸው አማልክት ሠዉ” ይላል (ዘዳ. 32፡17)። በተጨማሪም ጳውሎስ “አሕዛብ የሚሠዉት ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር ማኅበረተኞች እንድትሆኑ አልወድም” በማለት ይናገራል (1 ቆሮ. 10፡20)።

በእርግጥም ከአህዛብ ሐሰተኛ “አማልክት” ጀርባ የተሰወሩ አጋንንት ነበሩ። ይህ ማለት እንግዲህ ስለ ጣዖት አምልኮና ስለ ባዕድ አማልክት የሚናገሩት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች “ስለ አለማት ተጋድሎ” የሚናገሩ ናቸው ማለት ነው።

በዚህ መሠረት የአለማት ተጋድሎ ጭብጥ በተሻለ ሁኔታ ይስተዋላል። እናም ይህ እውነት ስለዚህ ተጋድሎ ምንነት እና የክፋት ምስጢር የበለጠ ለመረዳት ትልቅ አንድምታ አለው። የተጋድሎው መርሆዎች *የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።

የካቲት 23
Mar 2

እንዲዘገይ የተደረገው መልአክ


ቀደም ሲል እንደተመለከትነው፣ የአሕዛብ ሐሰተኛ “አማልክት” በስውር የሚሰሩ አጋንንት ናቸው። በሌላ ቦታ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ከምድራዊ ገዥዎች ጀርባ ከፍ ባለ ስፍራ ያሉ አጋንንታዊ ገዥዎች እንዳሉ የሚያሳይ ማስረጃ እንመለከታለን። ከእግዚአብሔር የተላኩ መላእክት እንኳን በጠላት ኃይሎች ተቃውሞ ሊደርስባቸው ይችላል።

ዳን. 10:1–14ን ያንብቡ፤ በቁጥር 12, 13 ላይ ልዩ ትኩረት ያድርጉ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ አለማቀፋዊው ተጋድሎ ምን ያስተምራሉ? እግዚአብሔር የላከው መልአክ ለሃያ አንድ ቀን “ተቃውሞ” ደረሰበት ሲባል ምን ይረዳሉ?



እግዚአብሔር የላከው መልአክ ለሦስት ሳምንታት እንዴት ጠላት ‘ሊቋቋመው’ ይችላል? ሁሉን ቻይ በመሆኑ፣ እግዚአብሔር ፍቃዱ ቢሆን ኖሮ ለዳንኤል ወዲያውኑ ምላሽ ለመስጠት ኃይል ነበረው። ይህን ለማድረግ ኃይሉን ቢጠቀም፣ መልአኩ ወዲያውኑ ለዳንኤል እንዲገለጥለት ማድረግ ይችል ነበር።

ሆኖም አምላክ የላከውን መልአክ “የፋርስ መንግሥት አለቃ” ለሦስት ሳምንታት ያህል “ተቋቋመው”። እዚህ ላይ ምን እየሆነ ነው?

“ገብርኤል በቂሮስ አእምሮ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረውን ኃይል ለመቋቋም በመፈለግ ለሦስት ሳምንታት ከጨለማ ኃይላት ጋር ታገለ። . . . ሰማይ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ሊያደርግ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል። ድሉም በመጨረሻ ተገኝቷል፤ ቂሮስና ልጁም ካምባይሲዝ በኖሩበት ዘመን ሁሉ፣ የጠላት ኃይላት በአምላክ ቁጥጥር ሥር ሆነው ነበር።”—ኤለን ጂ. ኋይት፣ ነቢያት እና ነገሥታት፣ ገጽ. 572.

እንዲህ ያለ ተጋድሎ እንዲካሄድ፣ እግዚአብሔር ኃይሉን ሙሉ በሙሉ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት አልተጠቀመም ማለት ነው። ዝርዝር ሁኔታው ባይገለጥልንም፣ ጠላት በስውር ወዲያውኑ ያልተወገደ፣ ነገር ግን በሁለቱም ወገኖች በሚታወቁ መንገዶች የተገደበ፣ እውነተኛ ነፃነትና ኃይል ተሰጥቶት ነበር። በአለማቀፋዊው ተጋድሎ የእግዚአብሔር መላእክት እንኳን የሚሠሩባቸው ገደቦች አሉ ማለት ነው፣ ይህም በሚቀጥሉት ትምህርቶች “የተጋድሎው መርሆዎች” ተብሎ ተጠቅሷል።

በተወሰነ መልኩ፣ እግዚአብሔር የሚሠራው በፍቅር ብቻ እንደሆነ፣ የመንግሥቱም መሠረት ፍቅር እንጂ ማስገደድ እንዳልሆነ ካስተዋልን፣ እነዚህን ገደቦች መረዳት ከባድ ላይሆን ይችላል። እግዚአብሔር የሚሠራው ከፍቅር በሚመነጩ መርሆች ብቻ ነው የሚለው ይህ ሃሳብ ታላቁን ተጋድሎ የበለጠ እንድንረዳ ያደርገናል።

በግድ ሳይሆን በፍቅር መርሆች ብቻ የመሥራትን ገደብ እንዴት ነው የተለማመዱት? ስለ ኃይል (ስልጣን) ውስንነትስ ምን ትምህርት ተማሩ?

የካቲት 24
Mar 3

በራዕይ ላይ ያለው ዘንዶ


በአለማቀፋዊው ተጋድሎ ውስጥ ስላሉ ሰማያዊ ገዥዎች ጠቅለል ያለ ሐሳብ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ተገልጿል። በዚያም ዲያብሎስ እግዚአብሔርን በመቃወም “ዓለሙንም ሁሉ በሚያስተው በታላቁ ዘንዶ” ተመስሏል (ራዕ.12:9)።

ራዕ. 13:1-8ን ያንብቡ። ይህ ስለ ዘንዶው የሥልጣን ወሰን ምን ያሳየናል?



ዘንዶው (ሰይጣን) እግዚአብሔርን (ራዕ. 12፡7-9) እና አገልጋዮቹን (ለምሳሌ ራዕ. 12፡1–6) ብቻ የሚቃወም ሳይሆን ፣ በዘመናት ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በሚያሳድዱ የምድር መንግሥታት ጀርባ ያለው ገዥ እሱ እንደሆነ ተገልጧል። ዘንዶውም ከባሕር ለወጣው አውሬ “. . . ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው” (ራዕ. 13፡2፤ ከራዕ. 13:5፣ ራዕ. 17:13, 14 ጋር ያስተያዩ)። ይህ የተጋድሎው መርሆዎች ከባሕር የወጣው አውሬ “ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ ለአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው” (ራዕ. 13፡5)።

ስለዚህ ሰይጣን ለአውሬው (ለምድራዊው ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ኃይል) ኃይልንና የመግዛት ሥልጣንን ይሰጠዋል። ይህ ኃይል ሥራ ላይ የሚውለው ለእግዚአብሔር የሚገባውን አምልኮ ለመቀማት ነው። አውሬው የእግዚአብሔርን ስም ይሳደባል፤ ደግሞም ለተወሰነ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቅዱሳን ይዋጋል፣ ያሸንፋቸውማል። ይህ ዓለም አቀፋዊ ሥልጣን የተሰጠው የዚህ ዓለም ገዥ በሆነው በዘንዶው ነው።

ሆኖም፣ በሰይጣንና በአጀንዳ አስፈፃሚዎቹ ላይ ግልጽ የሆኑ የጊዜ ገደቦች አሉ። “ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ነዋሪዎች ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና” ይላል (ራእ. 12፡12)።

ሰይጣን “ዘመኑ አጭር እንደ ሆነ ያውቃል” (ራዕ. 12፡12)፣ በራዕይ ላይ የተገለጹት ኩነቶች የሚፈጸሙት በትንቢታዊ የጊዜ ሰሌዳዎች ነው፣ ይህም እነዚህ የክፉ ኃይሎች የሚሰለጥኑበትን የተወሰኑ ገደቦች ያሳያል (ራዕ. 12፡14፣ ራዕ. 13፡ 5)።

እውነት ነው - እግዚአብሔር በመጨረሻ ያሸንፋል። “እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ” (ራዕ. 21:4)።

አሁን ለማየት ቢከብደንም፣ በመጨረሻ በጎነት ለዘላለም በክፋት ላይ ያሸንፋል። ይህን አስደናቂ ተስፋ ፈጽሞ መዘንጋት የሌለብን ለምንድን ነው?

የካቲት 25
Mar 4

የኢዮብ ጉዳይ


በኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ታላቁ ተጋድሎ አንዳንድ አስደናቂ ግንዛቤዎች ተሰጥተውናል። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ኢዮ. 1፡1–12ንና ኢዮ. 2፡1–7ን ያንብቡ። እዚህ ላይ ተገልጠው የምናያቸው የታላቁ ተጋድሎ መርሆዎች ምንድን ናቸው?



ከእነዚህ ጥቅሶች ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል። በመጀመሪያ በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል የሚደረግ ንግግር ብቻ ሳይሆን፣ በሰማይ ምክር ቤት ያለ ይመስላል፤ ሌሎች የሰማይ ፍጥረታትም ተሳትፈውበታል።

ሁለተኛ እግዚአብሔር ሰይጣንን ኢዮብን ተመለከትኸውን? ብሎ መጠየቁ አንዳንድ አለመግባባቶች እንዳሉ የሚጠቁም ነው። ኢዮብን ለምን ይመለከተዋል? ጥያቄው ትርጉም የሚኖረው ከፍ ባለና በመካሄድ ላይ ባለ ሙግት አውድ ውስጥ ነው።

ሦስተኛ እግዚአብሔር ኢዮብን ነቀፋ የሌለበት፣ ጻድቅና አምላክን የሚፈራ ብሎ ሲገልፀው፣ ሰይጣን ግን ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ የሚመስለው አምላክ ስለሚጠብቀው ብቻ እንደሆነ ይሞግታል። ይህም የኢዮብን እና የእግዚአብሔርን ባሕርይ ማንቋሸሽ ነው (ከራዕ. 12፡10 እና ከዘካ. 3 ጋር ያስተያዩ)።

አራተኛ ሰይጣን አምላክ ኢዮብን መጠበቁ (ማጠሩ) ፍትሐዊ እንዳልሆነ ይከሳል፣ ክሱንም ለማረጋገጥ እንደማያስችለው ተናግሯል። ይህም በሰይጣን ላይ አንዳንድ ገደቦች (የተጋድሎ መርሆዎች) መኖራቸውንና ሰይጣንም ኢዮብን ለመጉዳት መሞከሩን ያሳያል።

እግዚአብሔር ለሰይጣን ክስ በሰማያዊው ምክር ቤት ፊት ምላሽ የሰጠው፣ ሰይጣን በተቀመጠለት ገደብ ብቻ ኢዮብን እንዲፈትነው በመፍቀድ ነው። በመጀመሪያ ለሰይጣን ኢዮብ “ባለው ሁሉ” ላይ ስልጣን ሰጠው፣ ነገር ግን አካላዊ ጉዳትን ይከለክል ነበር (ኢዮብ 1፡12)። በኋላ ሰይጣን ኢዮብ የሚያስበው ለራሱ ብቻ እንደሆነ ሲሞግት፣ እግዚአብሔር ለሰይጣን ኢዮብን እንዲያሠቃየው ፈቀደለት - ከሕይወቱ በስተቀር (ኢዮብ 2፡3-6)።

ሰይጣን በኢዮብ ቤተሰብ ላይ ብዙ መቅሰፍቶችን አመጣ፤ ሆኖም የተጋድሎው መርሆዎች በእያንዳንዱ ሁኔታ ኢዮብ ያምላክን ስም መባረኩን በመቀጠሉ (ኢዮ. 1:20–22፣ ኢዮ. 2:9, 10)፣ የሰይጣንን ክሶች አመከነ።

እዚህ ላይ ብዙ ነገሮችን እንማራለን፣ ለምሳሌ በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ የተጋድሎ መርሆዎች አሉ። በሰማያዊው ዙፋን በእግዚአብሔር ላይ የተነሱት ክሶች እልባት የሚያገኙበት መስፈርቶች አሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የመንግስቱ መሠረት በሆነው ፍቅር ውስጥ ያሉትን የተቀደሱ መርሆች፣ እንዲሁም አለማትንና በውስጣቸው ያሉትን የማሰብ ችሎታ ያላቸውን ፍጥረታት የሚገዛባቸውን ደንቦች አይጥስም።

በኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ ሰማያዊ ትዕይንቶች፣ ስለ ታላቁ ተጋድሎና በዚህ ምድር ላይም እንዴት እንደሚከናወን አስደናቂ ማስተዋል ይሰጡናል።

የካቲት 26
Mar 5

የዚህ ዓለም ጊዜያዊ ገዥ


ቀደም ብለን በታላቁ ተጋድሎ ሰይጣንና ግብረ-አበሮቹ በተጋድሎው መርሆዎች ተወስነው፣ በዚህ ዓለም ውስጥ ለጊዜው ጉልህ የሆነ ስልጣን እንደተሰጣቸው አይተናል።

እነዚህ የተጋድሎ መርሆዎች የዲያብሎስንና የአጋሮቹን ድርጊት ብቻ ሳይሆን፣ በጠላት ግዛት ውስጥ ለጊዜው የሚፈጠረውን ክፋት እንዳያስወግድ የእግዚአብሔርንም እርምጃ ይገድባሉ። ጌታ የገባውን ቃል በፍፁም ስለማያጥፍ፣ በተስማማባቸው የተጋድሎው መርሆዎች መሠረት የተወሰነና ጊዜያዊ ስልጣን ለዲያብሎስ በመስጠቱ፣ እግዚአብሔር ምንም እንኳን ኃይሉ ታላቅ ቢሆንም ወደፊት የሚወስዳቸው እርምጃዎች ግን የተገደቡ ይሆናሉ።

ዮሐ. 12:31ን፣ ዮሐ. 14:30ን፣ ዮሐ. 16:11ን፣ 2 ቆር. 4:4ን፣ ሉቃ. 4:⁠6ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች በዚህ ዓለም ላይ ጠላት ስላላው ስልጣን ምን ያስተምራሉ?



የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

አዲስ ኪዳን የብርሃንና የጨለማ መንግሥታትን ውጊያ ይገልጻል።

ጨለማውም ከሰይጣንና ከአመፃው የተነሳ የመጣ ነው። የክርስቶስ ተልዕኮ የሰይጣንን መንግሥት ማሸነፍ ነበር። “ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ” (1ኛ ዮሐንስ 3፡8)።

ቢሆንም እግዚአብሔር ለመንግሥቱ መርሆዎች ታማኝ ስለሆነ፣ ሊያደርግ የሚችለው ነገር “በደንቦቹ” መሠረት የተገደበ (የተወሰነ) ነው። እነዚህ ገደቦች ቢያንስ (1) ለፍጡራኑ የምርጫ ነፃነት መስጠትን እና (2) አሁን የማናስተውለውን የተጋድሎውን ኪዳናዊ ደንቦች ማክበርን ያካትታሉ። እነዚህ ክልከላዎችና ገደቦች፣ እግዚአብሔር ክፋትን ከዓለም ላይ ለመቀነስ ወይም ወዲያውኑ ለማስወገድ እንዳያስችለው ስለሚያደርጉ፣ በመለኮት አሰራር ላይ ጉልህ አንድምታ አላቸው።

ስለዚህ ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን መኖር ወይም በጎነቱን እንዲጠራጠሩ የሚያደርግ ቀጣይ የሆነ ክፋትና መከራ እናያለን። ነገር ግን የታላቁን ተጋድሎ ምንነትና እግዚአብሔር ክፋትን የሚያስታምምበትን ምክንያቶች ከተረዳን፣ ነገሮች ለምን አሁን ባሉበት ሁኔታ እንዳሉ በተሻለ ሁኔታ እናስተውላለን - ቢያንስ እግዚአብሔር ክፋትን መጨረሻ ላይ ድል እስኪያደርግ ድረስ።

ኢየሱስ ሰይጣንን የዚህ ዓለም “ገዥ” ብሎ መጥራቱ፣ አሁን በዓለም ላይ ያለውን ክፋት እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? ጊዜያዊ ስልጣን ብቻ መሆኑን ማወቁ ምንኛ የሚያጽናና ነው!

የካቲት 27
Mar 6

ገደቦች እና ደንቦች


ታላቁ ተጋድሎ በዋነኛነት በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ የተነሳ ውዝግብ ነው። ይህም በእግዚአብሔር መልካምነት፣ ፍትሕና አገዛዝ ላይ በዲያብሎስ የተጠነሰሰ የስም ማጥፋት ክስ ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ግጭት በኃይል ሊፈታ አይችልም፣ ይልቁንም ባሕርይው መገለፅ ያስፈልገዋል። ስልጣን ባለው ሰው ላይ ከባድ ውንጀላዎች ከተነሱ፣ ክሱን ለማሸነፍ የተሻለውና ምናልባትም ብቸኛው መንገድ ነፃ፣ ፍትሐዊና ግልጽ ምርመራ ማድረግ ነው። ክሱ መላውን የፍቅር መንግሥት የሚያሰጋ ከሆነ፣ ዝም ብሎ ችላ ማለት አይቻልም። የተጋድሎው መርሆዎች

ይህ ሁሉ ክፋትን በተመለከተ የተነሳውን ታላቁን ተጋድሎ ለመረዳት እንዴት ይረዳናል? እግዚአብሔር ቃል ከገባ፣ ቃሉን ያጥፍ ይሆን? በጭራሽ።

እግዚአብሔር በተጋድሎው ደንቦች ከተስማማ፣ የወደፊት ድርጊቱ በስምምነቱ መሠረት የተገደበ ይሆናል። ስለዚህ አንዳንድ ክፋቶች በጊዜያዊው የጨለማው መንግሥት ግዛት ውስጥ ሊፈፀሙ ይችላሉ።

ማር. 6:5ንና ማር. 9:29ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች መለኮታዊው ድርጊት ከእምነትና ከጸሎት ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ምን ያሳያሉ?



በሁለቱም ታሪኮች፣ ከእምነትና ከጸሎት ጋር ግንኙነት ያላቸው አንዳንድ ገደቦች ወይም የተጋድሎ ደንቦች እንዳሉ የሚያመለክቱ ይመስላሉ። በሌሎች ጥቅሶችም ጸሎት በዚህ ዓለም ላይ ለውጥ እንደሚያመጣና ለመለኮታዊው አሰራር በሮችን እንደሚከፍት ብዙ ማስረጃዎችን እናያለን። ይሁን እንጂ እምነትና ጸሎት ብቻ ናቸው ወሳኞቹ ብለን በማሰብ መሳሳት የለብንም። እኛ የማናውቃቸው ሌሎች ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።

ይህ ቀደም ሲል ካየናቸው የተጋድሎው መርሆዎች ጋር ይስማማል።

እግዚአብሔር ቃል ከገባ ወይም በተጋድሎው ደንቦች ከተስማማ፣ የወደፊት ድርጊቱ በስምምነቱ መሠረት የተገደበ ይሆናል። ስለዚህ አንዳንድ ክፋቶች በጊዜያዊው የጨለማው መንግሥት ግዛት ውስጥ ሊፈፀሙ ይችላሉ።

ሮሜ 8:18ንና ራዕ. 21:3, 4ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ብዙ የማናውቃቸው ነገሮች ቢኖሩም፣ አምላክ ከሁሉ የሚሻለውን እንደሚያውቅና እንደሚፈልግ፣ እንዲሁም ለክፋት ፍፃሜ አድርጎ ዘላለማዊ ደስታን እንደሚያመጣ እንድንታመንበት የሚያደርጉን እንዴት ነው?

የካቲት 28
Mar 7


ተጨማሪ ሀሳብ


የቤተክርስቲያን ምክሮች ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ ”የሰይጣን ኃይል” የተሰኘውን ርዕስ ጥራዝ 1 ከገጽ 341–347 ያንብቡ።

"የወደቀው ሰው የሰይጣን ህጋዊ ምርኮኛ ነው። የክርስቶስ ተልዕኮ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት እርሱን ከክፉ ባላጋራው ኃይል ማዳን ነው። ሰው በተፈጥሮው የሰይጣንን ምክሮች የመከተል ዝንባሌ አለው። እናም ኃያል የሆነው ድል አድራጊው ክርስቶስ በእርሱ ውስጥ ካላደረ፣ ምኞቱን ካልገራውና ኃይልን ካልሰጠው በስተቀር፣ ያንን አስፈሪ ጠላት በተሳካ ሁኔታ መቋቋም አይችልም። የሰይጣንን ኃይል ገደብ የሚያበጅለት እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰይጣን ምድርን ሁሉ በመዞር ይመላለስባታል። ነፍሳትን ለማጥፋት እድሉን እንዳያጣ በመፍራት፣ ለአፍታ እንኳን አያንቀላፋም። የእግዚአብሔር ሕዝብ ከወጥመድ ያመልጡ ዘንድ ይህንን መገንዘብ አለባቸው። ሰይጣን በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ በሚያደርገው የመጨረሻ ዘመቻ፣ እርሱ መሆኑን እንዳይረዱ በማድረግ ማታለያዎቹን እያዘጋጀ ነው። 2ኛ ቆሮ. 11:14፡- ‘ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና’ ይላል። አንዳንድ የተታለሉ ነፍሳት ሰይጣን የለም ሲሉ፣ ይማርካቸውና በእነርሱ አማካኝነት በከፍተኛ ደረጃ እየሰራ ይገኛል።

ኃይላቸው በክርስቶስ ሲሆን፣ በእርሱ ላይ ሊኖራቸው የሚችለውን ኃይል ከእግዚአብሔር ሰዎች ይልቅ ሰይጣን ያውቃል። ኃያል የሆነውን ድል አድራጊ በትሕትና እንዲረዳቸው ሲማፀኑት፣ እውነትን የሚያምነው እጅግ ደካማ ሰው እንኳን፣ በክርስቶስ በመታመን ሰይጣንንና ሠራዊቱን በሙሉ በተሳካ ሁኔታ መቃወም ይችላል። እጅግ ተንኮለኛ ስለሆነ ፈተናዎቹን በግልጽ ይዞ አይመጣም፤ ያማ ቢሆን የደነዘዘው የክርስቲያን ጉልበት ይነቃና በጠንካራውና በኃይለኛው አዳኝ ይተማመናል። እርሱ ግን ሳይታሰብ ይመጣል፣ የአምልኮ መልክ ባላቸው በማይታዘዙ ልጆች አማካኝነት በድብቅ ይሠራል።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የቤተክርስቲያን ምክሮች፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 341 የተጋድሎው መርሆዎች


የመወያያ ጥያቄዎች




1. “የሰይጣን ህጋዊ ምርኮኛ” መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ዲያብሎስ በሰዎች ላይ የፈለገውን ማድረግ ይችላል ማለት ነው? አይችልም ካልን፣ ለምን አይችልም? ይህ በታላቁ ተጋድሎ "የተጋድሎው ደንቦች" ብለን ከምንጠራው ጋር እንዴት ይዛመዳል?

2. አምላክ በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ፣ ለጊዜውም ቢሆን፣ ለሰይጣን አንዳች ሥልጣን የሚሰጠው ለምንድን ነው? ይህ አምላክ ለሰይጣን ክሶች መልስ ለመስጠት ስለሚፈልግበት መንገድ ምን ይነግረናል?

3. ክርስቲያኖችን ጨምሮ፣ ሰይጣን የሚባል ፍጡር መኖሩን ለሚክዱ ምን ምላሽ ይሰጧቸዋል? ምንም እንኳን ሰይጣን መኖሩን በአካል ማረጋገጥ ባንችልም፣ በጣም የተታለለን ሰው ሊረዳው የሚችል ምን ማስረጃ ሊያቀርቡ ይችላሉ?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL