የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዮሐ. 18፡37፣ ሮሜ 3፡ 23–26፣ ሮሜ 5፡8፣ ኢሳ. 5፡1–4፣ ማቴ. 21፡33–39፣ ኢሳ. 53፡4፣ ሮሜ 3፡1–4።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ጲላጦስም፦ እንግዲያ ንጉሥ ነህን?
አለው። ኢየሱስም መልሶ፡- እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ
ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤
ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው” (ዮሐ. 18፡37)።
ከጥቂት ከዓመታት በፊት፣ ጥልቅ ትምህርት ያለው የልጆች ታሪክ በጋይድ
(Guide) መጽሔት ታትሞ ነበር። ታሪኩ የሚያተኩረው በመካከለኛው
ዘመን ከአንድ ቤተሰብ ጋር በማደጎ ልጅነት ይኖር በነበረ ዴኒስ በተባለ
ልጅ ላይ ነው። ዴኒስ ወላጆቹ በታመሙ ጊዜ የንጉሱ ወታደሮች ስለወሰዱትና
ከዚያ በኋላ እንደገና ወላጆቹን ስላላያቸው፣ የአገሩን ንጉሥ አምርሮ ይጠላው
ነበር። ንጉሡ በሕይወት ያሉትን ከአስከፊው የተስቦ ወረርሽኝ ለማትረፍ ሲል
እንደለያቸው የተረዳው በኋላ ነበር። ስለ ንጉሡ የተረዳው እውነት ዴኒስን ከሞላ
ጎደል እድሜውን ሁሉ ይዞት ከነበረው ጥላቻ ነፃ አውጥቶታል። ንጉሡ ሁልጊዜ
በማንኛውም ሁኔታ ነገሮችን ያደርግ የነበረው ለሕዝቡ ካለው ፍቅር የተነሣ ነበር።
ዛሬም ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን ዴኒስ ንጉሡን ባየበት መንገድ
ይመለከቱታል። ያዩት ወይም ያጋጠማቸው ክፋት እግዚአብሔርን እንዲጠሉት
ወይም የለም እንዲሉ ያደርጋቸዋል። በስቃይ ጊዜ እግዚአብሔር የት ነው?
እግዚአብሔር መልካም ከሆነ፣ ክፋት ለምን በዛ? ምንም እንኳን አሁንም ብዙ
ጥያቄዎች ቢኖሩንም፣ ታላቁ ተጋድሎ ይህንን ወሳኝ ጉዳይ እንድናስተውል
ይረዳናል። ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ የምናደርገው ሙከራ ሁሉ ባያረካንም፣
አሁንም ያልተመለሱ ጥያቄዎች ቢኖሩንም፣ ወደ ተሰቀለው ኢየሱስ ልንመለከትና
እግዚአብሔር ሊታመን እንደሚችል ልንረዳ እንችላለን።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
*የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።
ምንም እንኳን ክርስቶስ ራሱ “የዚህ ዓለም ገዥ” ብሎ የሚጠራው በሥራ
ላይ ያለ ጠላት ቢኖርም፣ እውነተኛው የዓለማት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
በእኛ ምትክ ድል ያደረገው ኢየሱስ ነው፤ በችግርና በመከራ ውስጥም ቢሆን፣
በእርሱ ድል ማድረግ እንችላለን። በእርግጥም የክርስቶስ ሥራ ሁልጊዜ የጠላትን
ሴራ ያከሽፋል።
ቃሉ ዲያብሎስን እንዲህ ይገልፀዋል፡-
1.
ከመጀመሪያው ጀምሮ ዓለምን ሁሉ የሚያስት (ራዕ. 12:9፣ ማቴ.
4:3፣ ዮሐ. 8:44፣ 2 ቆሮ. 11:3፣ 1 ዮሐ. 3:8).
2. በሰማይ እግዚአብሔርንና ሕዝቡን የሚሳደብና የሚከስ (ራዕ. 12፡
10፣ ራዕ. 13፡6፣ ኢዮ. 1–2፣ ዘካ. 3፡1, 2፣ ይሁዳ 9)።
3. ያላግባብ (በግድ) የዚህ ዓለም ገዥ የሆነ (ዮሐ. 12፡31፣ ዮሐ. 14፡30፣
ዮሐ. 16፡11፣ ሐዋ. 26፡18፣ 2 ቆሮ. 4፡4፣ ኤፌ. 2፡2፣ 1ዮሐ. 5፡19)።
ዮሐ. 18:37ን ያንብቡ። ይህ የጠላትን ማታለያዎች ለመቋቋም ክርስቶስ
ስላደረገው ሥራ ምን ይነግረናል? ኢየሱስ ንጉሥ ነው ማለት ምን
ማለት ነው?
ምንም እንኳን ቃሉ ሰይጣንን የዚህ ዓለም አታላይ፣ ተሳዳቢ (ስም
አጥፊ)፣ ከሳሽና ገዥ እንደሆነ ቢያስተምርም፣ ኢየሱስ ደግሞ በሰይጣን ላይ
በሁሉም መንገድ ድል አድራጊ እንደሆነም ያስተምራል።
1. ኢየሱስ “ወደ ዓለም የመጣው ለእውነት ሊመሰክር” ነው
(ዮሐንስ 18፡37)
2. ኢየሱስ በመስቀሉ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ጽድቅና ፍቅር
ከዚህ በላይ ምን ማድረግ እችል ነበር?
አሳይቷል (ሮሜ 3:25, 26፣ ሮሜ 5:8)፤ በዚህም የዲያብሎስን
የሀሰት ክሶች ውድቅ አድርጓል (ራዕ. 12:10, 11)
3. በመጨረሻም ኢየሱስ “ዘመኑ ጥቂት እንደ ሆነ የሚያውቀውን”
የዲያብሎስን መንግሥት ያጠፋል (ራዕ. 12:12፤ ከሮሜ 16:20
ጋር ያስተያዩ)፤ ክርስቶስም “ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል”
(ራዕ. 11:15)።
በመጨረሻ ሰይጣን ምንም ቢያደርግ፣ እሱ የተሸነፈ ጠላት ነው፤ ለእኛ
ቁልፉ ነገር የክርስቶስን ድል በየዕለቱ በየደቂቃው፣ እንዲሁም መስቀሉ የሰጠንን
ተስፋዎች የእኛ አድርገን መቀበል ነው።
በታላቁ ተጋድሎ የትኛው ወገን እንደሚያሸንፍ እናውቃለን። የዕለት
ተዕለት ምርጫዎቻችን በመጨረሻ በማን ወገን እንደምንሆን ምን
ተጽዕኖ ያሳድራሉ? አሁን እንኳን በአሸናፊው ወገን መሆናችንን
እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?
ሁልጊዜ የክርስቶስ ሥራ የዲያብሎስን ሥራ ይሽራል። ኢየሱስ
“የተገለጠው የዲያብሎስን ሥራ ለማፍርስ” (1ኛ ዮሐ. 3፡9) እና “በሞት ላይ
ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስ ለመሻር” ነው (ዕብ. 2፡14)። ሆኖም የጠላት አገዛዝ
አጠቃላይ ሽንፈት በሁለት ደረጃዎች ይከናወናል። በመጀመሪያ፣ በመስቀሉ
ክርስቶስ የሰይጣንን የስም ማጥፋት ክሶች ሐሰት መሆናቸውን አረጋግጧል።
በኋላም ሰይጣንና መንግሥቱ ይደመሰሳል።
ሮሜ 3፡23–26ንና ሮሜ 5፡8ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች ክርስቶስ
የዲያብሎስን ክሶች ስለሚረታበት መንገድ ምን ይገልጻሉ?
አስቀድመን እንዳየነው ጠላት እግዚአብሔርን ፍፁም ጻድቅና አፍቃሪ
አይደለም ይላል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ጽድቅና ፍቅር ግሩም በሆነ ሁኔታ
በክርስቶስ ተገልጧል፣ ይህንም ያደረገው በመስቀሉ ነው።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ኢየሱስ ከሞተ በኋላ፣ “ሰይጣን የማታለያ ካባው እንደ ተቀደደ አየ።
የእርሱ አስተዳደር ባልወደቁት መላእክትና ዓለማት ፊት ተገለጠ። ራሱን ነፍሰ-
ገዳይ እንደሆነ አጋለጠ። የእግዚአብሔርን ልጅ ደም በማፍሰሱ፣ በሰማይ ያሉ
ፍጥረታትን አዘኔታ አጣ።”—ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 761.
ራዕ. 12፡10–12ን ከዘፍ. 3፡15 አንጻር ያንብቡ። ይህ ክፍል ክርስቶስ
በመስቀል ላይ የተጎናፀፈው ድል ለአለማት ሁሉ ያለውን ጠቀሜታ
እንዴት ይገልፃል?
የመቤዠታችን ታሪክ እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚሠራው
በስተመጨረሻ ለሁሉም በጎ እንዲሆን ለማድረግ እንደሆነ እንድንታመንበት
ብዙ ማስረጃዎችን ይሰጠናል። የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ በታላቁ ተጋድሎ
ውስጥ ሊሰራ በሚችልባቸው መንገዶች ሁሉ ሁልጊዜ መልካምና ተመራጭ
የሆነውን ያደርጋል (ዘዳ. 32:4፣ 1 ሳሙ. 3:18፣ መዝ. 145:17፣ ዳን. 4:37፣ ዕን.
1፡13፣ ራዕ. 15፡3፣ ዘፍ. 18፡25)።
በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ የእግዚአብሔር ጽድቅና ፍቅር በተግባር
መገለፁ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በደህንነት እቅድ
ውስጥ ስለ መስቀሉና ስለ ሁሉም የእግዚአብሔር ሥራዎች ስታሰላስሉ፣
አሰራሩ በፈተናና በስቃይ ውስጥ እንኳን በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ
እንድትታመኑ ድፍረት የሚሰጣችሁ እንዴት ነው?
በታላቁ ተጋድሎ ውስጥም ቢሆን፣ በአስደናቂ መንገድ እግዚአብሔር ፍቅሩንና ጽድቁን አሳይቷል። ሆኖም አንዳንዶች አምላክ ክፋትን ለመከላከል እንዲሁም ለማስወገድ ካደረገው የበለጠ ማድረግ አልነበረበትምን? ብለው ይጠይቃሉ። በታላቁ ተጋድሎ ማዕቀፍ፣ እግዚአብሔር በእርሱና በሰዎች መካከል ያለው የፍቅር ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ አስፈላጊ የሆነውን የምርጫ ነፃነት በማክበር የሚበጀውን እንዳደረገ አይተናል። በተጨማሪም በባሕርይው ዙሪያ የተነሳው አለም አቀፋዊ ሙግትሊፈታ የሚችለው ፍቅሩን በተግባር ከዚህ በላይ ምን ማድረግ እችል ነበር? በማሳየት ብቻ ስለነበር፣ የሞራል ገደቦችን ወይም የተጋድሎ መርሆዎችን በማክበር ሥራውን ፈፅሟል። ኢሳ. 5:1-4ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የሚናገረው ማነው? ኢሳያስ ስለ ማን ነው የሚናገረው? የወይኑ ቦታ እና የወይኑ ቦታ ባለቤት ማንን ያመለክታሉ? የወይኑ ቦታ ባለቤት ለወይኑ ቦታ ያደረጋቸው ነገሮች አስፈላጊነት ምንድን ነው? ውጤቱስ ምንድን ነው?
በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ኢሳይያስ ለወይን ቦታው ቅኔ ይቀኛል። የወይኑ
ቦታ ባለቤት እግዚአብሔር ራሱ ነው፣ የወይኑም ቦታ የእግዚአብሔርን ሕዝብ
ይወክላል (ለምሳሌ ኢሳ. 1፡8ን፣ ኤር. 2፡21ን ይመልከቱ)። ነገር ግን እዚህ ላይ
ያለው አንድምታ፣ በዚህ ዓለም የሚደረገውን ሰፊውን የእግዚአብሔርን ሥራ
ሊያሳይ ይችላል። በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት፣ የወይኑ ቦታ ባለቤት የወይኑን ቦታ
ፍሬአማ ለማድረግ የሚጠበቅበትን ሁሉ አድርጓል። የወይኑ ቦታ ጥሩ የወይን ፍሬ
ማፍራት ነበረበት፤ ይሁን እንጂ የማይረባ “ሆምጣጣ ፍሬ” አፈራ። በእርግጥም
እዚህ ላይ ያለው የዕብራይስጥ ቃል የሸተተ ፍሬ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
የእግዚአብሔር የወይን ቦታ የማይረባ የወይን ፍሬ አፈራ።
ኢሳ. 5፡3 ላይ እግዚአብሔር ራሱ ሰዎችን በእርሱና በወይኑ ቦታው
መካከል “እንዲፈርዱ” ይጋብዛል። በኢሳ. 5፡4 ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ በጣም
አስፈላጊ የሆነውን ጥያቄ ይጠይቃል፡- “ለወይኔ ያላደረግሁለት፣ ከዚህ ሌላ
አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድን ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስጠብቅ፣ ስለ ምን
ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?” ይላል። ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላል? እንዲያውም
እርሱ ያደረገውን ነገር ሌሎች እንዲፈርዱ መጠየቁ እንዴት የሚደንቅ ነው!
እግዚአብሔር ራሱን ለኃጢአታችን ሁሉ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበበትን
መስቀል ሲመለከቱ፣ “ለወይኔ ያላደረግሁለት፣ ከዚህ ሌላ አደርግለት
ዘንድ የሚገባኝ ምንድን ነው?” የሚለው ቃል እንዴት ያለ ትልቅ
ጠቀሜታ ይኖረዋል?
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
በማቴ. 21 ባለው የወይኑ ቦታ ባለቤት ምሳሌ፣ ኢየሱስ ኢሳይያስ 5
ካቆመበት ይቀጥልና የወይኑ ቦታ ባለቤት የወይን ቦታውን በተመለከተ ባለው
ባሕርይና ድርጊት ላይ ተጨማሪ ብርሃን ይሰጠናል።
የኢሳ. 5:4ን ጥያቄ በአእምሮዎ ይዘው ማቴ. 21:33–39ን ያንብቡ።
ካደረገው በላይ ምን ማድረግ ይችላል?
የክርስቶስ ምሳሌ የመጀመሪያው ክፍል ስለ ወይን ቦታው ባለቤትና ስለ
ወይን ቦታው ከኢሳ. 5 ቅኔ በቀጥታ ይጠቅሳል። ከዚያም ኢየሱስ የወይኑ ቦታ
ባለቤት የወይኑን ቦታ “ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሩቅ አገር ሄደ”በማለት ያክላል
(ማቴ. 21፡33)። ሆኖም የወይኑ ቦታ ባለቤት ሁለት ጊዜ አገልጋዮቹን (ነቢያትን)
ምርቱን እንዲቀበሉ ቢልካቸውም፣ የወይኑ ቦታ ተከራዮች አገልጋዮቹን
ደበደቧቸው፣ ገደሏቸውም (ማቴ. 21፡34–36)። በመጨረሻም “ልጄንስ
ያከብሩታል” ብሎ ልጁን (ኢየሱስን) ላከው (ማቴ. 21፡37)። ነገር ግን ልጁን
ደግሞ “ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ። ይዘውም
ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት (ማቴ. 21፡38, 39)።
ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላል? አብ እጅግ ስለ ወደደን የሚወደውን
ልጁን ሰጠን (ዮሐ. 3፡16)። ታላቁ ተጋድሎ እዚህ የተጠቆመው ዓይነት ከሆነ፣
መለኮታዊ ኃይልን በመጠቀም በእንጭጩ መፍታት አይቻልም፤ ይልቁንስ
በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ባሕርይ በአደባባይ በተግባር ማሳየትን ይጠይቃል።
ይህም ደግሞ በክርስቶስ ሥራ በገሃድ ታይቷል (ሮሜ 3፡25, 26፣ ሮሜ. 5፡8)።
ፍርዱንና ፍፁም ፍቅሩን በምንም ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ሳያስገባ ያጸድቀን ዘንድ፣
እግዚአብሔር (በክርስቶስ) ለእኛ ሲል ለሞት ራሱን አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ
ምን ልንጠይቀው እንችላለን?
እውነተኛ ፍቅር የሚበለፅግበትን ሁኔታ ሳያዳፍን፣ መስቀሉ እግዚአብሔር
ከዚህ በላይ ምን ማድረግ እችል ነበር?
ክፋትን ለመቀልበስና ለማስወገድ የሚቻለውን ሁሉ ማድረጉን ያሳያል።
እግዚአብሔር ሌላ የሚበጅ መንገድ ቢኖር ኖሮ፣ ያን አይመርጠውም ነበርን?
በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ ሰዎች እጅግ ቢሰቃዩም፣ እግዚአብሔር ራሱ ከሁሉም
በላይ ይሠቃያል። መስቀሉን ስንመለከት፣ በእርግጥ ኃጢአት በእግዚአብሔር ላይ
ያመጣውን ስቃይና ህመም ማየት እንችላለን። ሆኖም በፍቅር ውስጥ ያለው ነፃነት
በጣም የከበረ ስለሆነ፣ ክርስቶስ ለእኛ ሲል ይህንን ሁሉ ለመሸከም ፈቃደኛ ሆነ።
ኢሳ. 53:4ን ያንብቡ። ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተሸከመው የማንን
"ደዌ" እና "ህመም" ነው? ይህ እግዚአብሔር ስላደረገልን ነገር ሁሉና
የኛ መዳን ስላስከፈለው ዋጋ ምን ሊነግረን ይገባል?
በመጨረሻ የእግዚአብሔር ስም ከማንኛውም ክስ ነፃ ይሆናል። በደህንት
እቅድ ውስጥ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በሚያደርጉት ሥራ፣ ፍጹም የሆነው
የእግዚአብሔር ጽድቅና ፍቅር ያለምንም ጥርጣሬ ይገለጣል (ሮሜ. 3፡25, 26፣
ሮሜ. 5፡8)።
ሮሜ 3:1–4ን ከኢሳ. 5:3, 4 አንጻር ያንብቡ። ይህ እግዚአብሔር
በአለማቀፋዊው ተጋድሎ መጨረሻ ነፃ ስለመሆኑ ምን ያስተምራል?
በሮሜ 3 እና በኢሳ. 5 ላይ ምንም እንኳን መብት ባይኖረንም ወይም የማይገባን
ቢሆንም፣ እግዚአብሔር (በተወሰነ መልኩ) ፍጡራኑን በባሕርይው እንዲፈርዱ
ሲጋብዛቸው እናያለን። በመጨረሻ ሁሉም “መጻሕፍት” ሲከፈቱ፣ እግዚአብሔር
ፍጹም በጎና ጻድቅ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን እንመለከታለን። እግዚአብሔር
በሚያስተውሉ ፍጥረታት ሁሉ ፊት ራሱን ከክስ (ከጥፋተኝነት) ነፃ ያደርጋል።
ራዕ. 15:3ንና ራዕ. 19:1–6ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች በመጨረሻ
የእግዚአብሔር ስም ከማንኛውም ክስ ነፃ እንደሚሆን ምን ያስተምሩናል?
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
በቃሉ ውስጥ እግዚአብሔር ለስሙ እንደሚገደው ያሳያል። ለምን?
ባሕርይውን ከምትጸየፉት ወይም ከማታምኑት ሰው ጋር ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት
ሊኖራችሁ አይችልም። አንድ ሰው ለትዳር ጓደኛዎ ወይም ለእጮኛዎ ስለ
ባሕርይዎ ዘግናኝ ውሸቶችን ቢነገግሯቸው፣ ይህን ለመቃወም የሚችሉትን ሁሉ
ያደርጋሉ፤ ምክንያቱም እንደዚህ ያሉ ወሬዎች ከታመኑ፣ የፍቅር ግንኙነትዎ
እንዲቋረጥብዎ ያደርጋሉና።
በመጨረሻ እግዚአብሔር በመስቀሉና በጠቅላላው የደህንነት እቅድ
ሂደት ጻድቅ መሆኑ ይረጋገጣል። በቅድመ-ምጽአት ፍርድ፣ እግዚአብሔር
በሚመለከቱት አለማት ፊት ነፃ መሆኑ ተረጋግጧል።
ከዚያም ከዳግም ምፃቱ በኋላ ባለው ፍርድ የተቤዣቸው ሰዎች
“በመላእክት ላይ በሚፈርዱበት” ጊዜ (1 ቆሮ. 6:2, 3)፣ የተዋጁት መዛግብትን
እንዲመረምሩና የአምላክን አሰራር ራሳቸው እንዲያውቁ በሚሰጣቸው ዕድል፣
እግዚአብሔር ጻድቅ መሆኑ ይረጋገጣል። ፍርዱም ሁልጊዜ በፍጹም ጽድቅና
ፍቅር የተሞላ እንደሆነ ያስተውላሉ። ከመካከላችን መልስ የሚያስፈልጋቸው
ብዙ ጥያቄዎች የሌለው ማነው? ሁሉም ነገር ከመጠናቀቁ በፊት፣ ለጥያቄዎቻችን
መልስ እናገኛለን (1 ቆሮ. 4፡5ን ይመልከቱ)።
በመጨረሻም ጉልበት ሁሉ ለስሙ ይንበረከካል፣ ምላስም ሁሉ ኢየሱስ
ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል (ፊል. 2፡10, 11)። ይህ ሁሉ የእግዚአብሔር ባሕርይ
ትክክል ነው ተብሎ የሚረጋገጥበት አሰራር አካል ነው።
የቤተክርስቲያን ምክሮች ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት
መጽሐፍ “ከልብ በመጣር የሚገኝ ሽልማት” የተሰኘውን ርዕስ ጥራዝ 9 ከገጽ
285–288 ያንብቡ።
"በእግዚአብሔር ምሪት ዙሪያ ግራ ያጋባን ነገር ሁሉ በሚመጣው አለም
ግልፅ ይሆንልናል። ለመረዳት የሚከብዱ ነገሮች ማብራሪያ ያገኛሉ። የጸጋው
ምስጢሮች በፊታችን ይገለጣሉ። ውስን የሆነው አእምሯችን ግራ መጋባትንና
ያልተፈፀሙ ተስፋዎችን ብቻ በተረዳበት፣ እጅግ ፍጹምና የሚያምር ስምምነትን
ከዚህ በላይ ምን ማድረግ እችል ነበር?
እናያለን። እጅግ ፈታኝ የሚመስሉ የሕይወት ልምምዶችን ወሰን የሌለው ፍቅሩ
እንዳዘዛቸው እናውቃለን። ሁሉንም ነገሮች ለበጎ እንዲሆኑልን የሚያደርገውን
የእርሱን ግሩም ጥንቃቄ ስንገነዘብ፣ በማይነገርና በከበረ ሐሤት ደስ ይለናል።”—
ኤለን ጂ. ዋይት፣ የቤተክርስቲያን ምክሮች፣ ጥራዝ 9፣ ገጽ 286
1. የእግዚአብሔርን ችሮታዊ ምሪቶች ለመረዳት ግራ ተጋብተው
ያውቃሉ? እንዲህ ያሉት ነገሮች ሁሉ በመጨረሻ ግልጽ እንደሚሆኑ
ማወቅዎ እንዴት ያጽናናዎታል?
2. ክርስቶስ ሰው ለመሆንና ለዚህ ዓለም ለመሞት የተዋቸውን ነገሮች
ያሰላስሉ። ይህ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ሊታመን የሚችል
ስለመሆኑ ምን እንደሚነግረን ያስቡ። ከዚህ በላይ ምን ማድረግ
ይችላል?
3. የእግዚአብሔርን “ስም” በተመለከተ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ነገር
ምንድን ነው? ይህ እራሳችንን ክርስቲያን ብለን ለምንጠራ ሰዎች
ምን አንድምታ አለው? ክርስቲያኖች አንዳንድ ጊዜ በክርስቶስ
ስም ላይ ውርደትን የሚያመጡት በምን መንገዶች ነው? እኛስ
ክርስቶስን መከተል በተግባር ምን እንደሚመስል ለማሳየት
በሰፈራችን ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን?
4. አሁን ስለ ክፋት ያሉን ምርጥ "መልሶች" እንኳን ያልተሟሉ ናቸው።
እግዚአብሔር ብቻ ሊያመጣ የሚችለውን የመጨረሻውን የክፋት
መፍትሄ እየጠበቅን ሳለ፣ በሥቃይ ላይ ወዳሉት ለመቅረብና በዚህ
ዓለም ሰቆቃዎችን ለማስወገድ ወኪሎች እንሆን ዘንድ በተግባር
ምን ማድረግ እንችላለን?
5. በኢሳ. 53:4 ላይ ክርስቶስ "ደዌያችንን" እና "ሕመማችንን"
የመሸከሙን እውነታ ያሰላስሉ። በመስቀል ላይ የደህንነትን እቅድ
እና እግዚአብሔር እኛን ለማዳን የከፈለውን ዋጋ እንድንገነዘብ
የሚረዳን ምን ተፈፀመ?