የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ



1ኛ ሩብ ዓመት 2025


የካቲት 1 - 7

7ኛ ትምህርት

Feb 8 - 14




የክፋት መከሰትና መዘዙ



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ኢዮ. 30፡26፣ ማቴ.27:46፣ ኢዮ. 38:1-12፣ መዝ. 73፣ ዘፍ. 2:16, 17፣ ራዕ. 21:3, 4።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ” (ራዕ. 21:4)።

ምናልባት ክርስትናን የገጠመው ትልቁ ችግር የኃጢአት መከሰት ሲሆን፣ እግዚአብሔር ፍጹም መልካምና አፍቃሪ ከሆነ፣ በዚህ ዓለም ክፋት እንዴት ሊኖር ቻለ የሚለውን ማስታረቅ ነው። ባጭሩ እግዚአብሔር መልካምና ሁሉን ቻይ ከሆነ፣ እንዴት እጅግ ብዙ ክፋት ሊኖር ቻለ?

ይህ ተግባራዊ አንድምታ የሌለው የጽንሰ ሐሳብ ችግር ብቻ ሳይሆን፣ ብዙ ሰዎችን የሚያስጨንቅ እና አንዳንዶችን እግዚአብሔርን እንዳያውቁትና እንዳይወዱት የሚያደርግ ነው።

“ለብዙዎች የኃጢአት መነሻውና የመከሰቱም ምክንያት እጅግ ግራ ያጋባቸዋል። የክፋትን ሥራ ከአሰቃቂ ስቃይና ጥፋት ውጤቱ ጋር ሲያዩት፣ ይህ ሁሉ በጥበቡ፣ በኃይሉና በፍቅሩ ወሰን በሌለው አምላክ ግዛት ውስጥ እንዴት ሊኖር ይችላል ብለው ይጠይቃሉ። ይህ ምንም ማብራሪያ የማያገኙለት ምስጢር ነው።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 492

አምላክ የለም የሚሉ ብዙ ሰዎች በፈጣሪ የማያምኑበት ምክንያት የክፋት መኖር ነው ይላሉ። ነገር ግን በዚህና በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደምንመለከተው፣ የወደቀውን ዓለማችንን የሚጎዳ ክፋት ቢኖርም፣ የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ሙሉ በሙሉ መልካምና ልንተማመንበት የምንችል ነው። *የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የካቲት 2
Feb 9

"እስከ መቼ ጌታ ሆይ?"


የክፋት መዘዝ በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜም ይነሳ ነበር።

ኢዮ. 30፡26ን፣ ኤር. 12፡1ን፣ ኤር. 13፡22ን፣ ሚል. 2፡17ን እና መዝ. 10፡1ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ክፋት በሰዎች ልምምድ ውስጥ ዋንኛው ችግር እንደሆነ እንዴት ያሳያሉ?



እነዚህ ጥቅሶች ዛሬም የእኛ ጥያቄ የሆኑ ብዙ ጥያቄዎችን ያነሳሉ።

ሁልጊዜም ባይሆን በአብዛኛው፣ ክፉዎች የሚበለፅጉና ክፉ የሚሰሩ በክፋታቸው የሚጠቀሙ የሚመስሉት ለምንድነው? ጻድቃን ሲበዛ የሚሰቃዩት ለምንድን ነው? ክፋት ሲፈፀም እግዚአብሔር የት ነው ያለው? አንዳንዴ እግዚአብሔር ከእኛ የራቀ፣ እንዲያውም የተሰወረ፣ የሚመስለው ለምንድነው?

ስለ እነዚህ ጥያቄዎችና ስለ ክፋት መዘዝ ምንም ብንናገር፣ ክፋትን አለማቃለላችንን እርግጠኛ መሆን አለብን። በዓለም ላይ ያለውን የክፋት ዓይነት ወይም መጠን በማቅለል ችግሩን ለመፍታት መሞከር የለብንም። ክፋት በጣም መጥፎ ነው፣ እግዚአብሔርም ከእኛ ይልቅ ይጠላዋል። ስለዚህ በዓለም ላይ ካለው ብዙ ክፋትና ኢ-ፍትሃዊነት የተነሳ፣ በቃሉ ውስጥ ከሚገኘው “እስከ መቼ ጌታ ሆይ?” ከሚለው ጩኸት ጋር ልንቀላቀል እንችላለን።

ማቴ. 27:46ን ያንብቡ። እነዚህን የኢየሱስን ቃላት እንዴት ይረዷቸዋል? ክፋት እግዚአብሔርን በሚገርም መልኩ እንዴት እንደጎዳው ምን ያስተላልፋሉ?



በመስቀል ላይ ኢየሱስ ራሱ “አምላኬ፣ አምላኬ፣ ለምን ተውከኝ?” (ማቴ. 27፡46) በማለት ይጠይቃል። እዚህ ላይ በተለየ ሁኔታ እግዚአብሔር ራሱ በክፋት እንደተጎዳ እናያለን። ይህም አስደናቂ እውነት፣ የአለም ሁሉ ክፋት በእርሱ ላይ የክፋት መከሰትና መዘዙ ተጭኖ፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሰቃየቱና በመሞቱ ጎልቶ ይታያል።

እንዲህም ቢሆን ግን ተስፋ አለ። ክርስቶስ በመስቀል ላይ ያደረገው ነገር፣ የክፋት ምንጭ የሆነውን ሰይጣንን አሸንፏል፤ በመጨረሻም ክፋትን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል። ኢየሱስ እነዚህን ቃላት ከመዝ. 22:1 የጠቀሰ ሲሆን፣ የቀረው የመዝሙሩ ክፍል ደግሞ በድል አድራጊነት ይጠናቀቃል።

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ፣ በዚያን ጊዜ ማየት የማይችለውን ተስፋ ወደፊት ተመለከተ። እኛም ከፊታችን ተስፋ አልታየን ሲል፣ ከእርሱ ተሞክሮ መፅናናትን ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

የካቲት 3
Feb 10

"የማናውቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ"


ፍቅር በክፋት ላይ ድል የሚያደርግበት የታሪክ ፍጻሜ ይመጣል።

እስከዚያው ድረስ ግን ብዙ ግራ የሚያጋቡ ጥያቄዎች ይኖራሉ። ስለ ክፋት አስቸጋሪነት ጠቃሚ ሊሆን በሚችል መልኩ ማሰብና መነጋገር እንዴት እንችላለን? ኢዮብ 38:1–12ን ያንብቡ። አምላክ ለኢዮብ የሰጠው መልስ የክፋትን ምስጢር እንድናስተውል እንዴት ይረዳናል? ከመጋረጃው በስተጀርባ የሚሆነውን ምን ያህል እናውቃለን? ምን ያህልስ አናውቅም?



በታሪኩ ውስጥ፣ ኢዮብ ብዙ ስቃይ ደርሶበት ስለነበር፣ እጅግ ክፋትና መከራ ለምን እንደደረሰበት ብዙ ጥያቄዎችን አንስቷል። ከመጋረጃው በስተጀርባ በሰማያዊው ዙፋን የሚሆኑ ብዙ ነገሮችን ሳያውቅ፣ ለጥያቄዎቹ መልስ ለማግኘት እግዚአብሔርን ለማነጋገር ጠይቋል (ኢዮብ 1–2ን ይመልከቱ)።

እግዚአብሔር ለኢዮብ የሰጠው ምላሽ አስደናቂ ነው። በተለይ “እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፡- ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው?” (ኢዮ. 38:1, 2)።

አንድ ትርጉም “ትንሽ የምታውቅ ሆኖ ሳለ ብዙ የምታወራው ለምንድን ነው?” ሲል ገልጾታል (ኢዮ. 38:2)። እግዚአብሔር በኢዮ. 38፡4 ላይ “ምድርን በመሠረትሁ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር” ሲል ያክላል።

ኢዮ. 42:3ን ያንብቡ። የኢዮብ ምላሽ ለራሳችን ስላለን ግምት ምን እንድናስተውል ይረዳናል?



እግዚአብሔር ለኢዮብ በሰጠው ምላሽ፣ ኢዮብ ያላወቃቸውና ያልተረዳቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ ግልጽ አድርጎለታል። ልክ እንደ ኢዮብ፣ ከመጋረጃው ጀርባ ምንም የማናውቃቸው በዓለም ውስጥ እየሆኑ ያሉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ በትሕትና ልንገነዘብ ይገባናል። ለጥያቄዎቻችን መልሱ ምን እንደሆነ አለማወቃችን፣ ጥሩ መልስ የለም ማለት አይደለም አንድ ቀን ሁሉም ነገር መፍትሄ ያገኛልና። እስከዚያው ድረስ በብዙ መንገድ የተገለጠልንን የእግዚአብሔርን መልካምነት ልንታመን ይገባናል።

ስለማንኛውም ነገር የምናውቀው ምን ያህል ትንሽ እንደሆነ ያስቡ። ታዲያ ለምንድነው በጣም ከባድ ስለሆኑት የክፋትና ስቃይ ጉዳዮች ካልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ጋር መኖርን መለማመድ ያለብን?

የካቲት 4
Feb 11

ብልሁ አማኝ


በኢሳ. 55:8, 9 ላይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- “አሳቤ እንደ አሳባችሁ፣ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።”

የእግዚአብሔር ሃሳብ ከኛ ሃሳብ ይልቅ እጅግ ከፍ ያለ ነው። በታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን እቅድ ረቂቅነት መገመት እንኳን አንችልም። ከዚህ አንጻር፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ አምላክ ለሚሠራው ወይም ለማይሠራው ነገር ምክንያቶቹ ምን እንደሆኑ ለማወቅ እንድንችል የምንጠብቀው ለምንድን ነው?

እኛ የምናውቀው ትንሽ መሆኑን በመገንዘብ ላይ የተመሰረተ የክፋትን አስቸጋሪነት የምንፈታበት አንዱ መንገድ “ብልሁ (ጠርጣራው) አማኝ” የክፋት መከሰትና መዘዙ በመባል ይታወቃል። ብልሁ አማኝ እግዚአብሔር ለሚያደርገው ነገር በቂ ምክንያቶች እንዳሉት የሚያምን ነው። ነገርግን ካለን ውስን እውቀት አንጻር፣ እነዚህ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ለማወቅ መጠበቅ የለብንም። ብልሁ አማኝ በዚህ ዓለም ውስጥ ካለው ክፋት የተነሳ፣ ሰዎች የእግዚአብሔርን ምክንያቶች ለማወቅ ወይም ለመረዳት አቅም የላቸውም ብሎ ያምናል። ለምሳሌ፡- አንድ ሰው በዙሪያችን በአየር ላይ ያሉትን ጀርሞች ማየት ስለማይችል፣ ጀርሞቹ የሉም ማለት አይደለም። አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ካላወቀ፣ በርግጥም እግዚአብሔር በቂ ምክንያቶች የሉትም ማለት አይደለም።

መዝ. 73ን ያንብቡ። ዘማሪው በዙሪያው ያለውን ክፋትና ኢ-ፍትሃዊነት የሚያስተውለው እንዴት ነው? ግንዛቤውን እንዲቀይር ያደረገውን ምንን አየ?



ዘማሪው በዓለም ላይ በነበረው ክፋት ይተክዝ ነበር። ዙሪያውን ሲመለከት ክፉዎች ሲበለጽጉ አየ። ሁሉም ነገር ኢ-ፍትሃዊና ሚዛናዊ ያልሆነ መሰለው።

የሚሰጠው መልስም አልነበረውም። አምላክን ማመንና ማገልገል ተገቢ ነው ወይ ብሎ ጠየቀ። ይህም የሆነው ወደ መቅደሱ እስኪመለከት ድረስ ነው።

መቅደሱ የክፋትን ችግር ለመፍታት የቁልፉ አንድ ክፍል ነው—ይህም በራሱ ጊዜ ፍትሕንና ፍርድን የሚያመጣ ጻድቅ ዳኛ እንዳለ መገንዘብ ነው።

ስለ ፍርዱና ስለ መቅደሱ አስተምህሮዎች አድቬንቲስቶች ያላቸው መረዳት የክፋትን ምስጢር ለማስተዋል እንዴት ይረዳናል? ምንም እንኳን አሁን ብዙ ጥያቄዎች ያሉን ቢሆንም፣ የታሪክም ሆነ የእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርዶች ዝርዝር በመጨረሻ እንደሚገለጡ ማወቁ ለርሶ ጠቃሚ ነውን?

የካቲት 5
Feb 12

የምርጫ ነፃነት አመክንዮ


የእግዚአብሔርን መንገድና ሐሳብ ባንረዳውም፣ ቃሉ የክፋትን አስቸጋሪነት ለመፍታት የሚረዱ አንዳንድ ነገሮችን ይገልጻል። የክፋትን ምስጢር የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ለመፍታት አንዱ መንገድ የምርጫ ነፃነት አመክንዮ በመባል ይታወቃል።

የምርጫ ነፃነት አመክንዮ፣ ክፋት የምርጫ ነፃነትን ያላግባብ የመጠቀም ውጤት ነው የሚል አመለካከት ነው። እንግዲያውስ ለክፋት ተጠያቂው እግዚአብሔር አይደለም፣ ምክንያቱም ክፋት ፍጡራን እግዚአብሔር ለበጎ የሰጣቸውን የምርጫ ነፃነት ያላግባብ መጠቀማቸው ነውና። ይሁን እንጂ አምላክ እንዲህ ዓይነቱን የምርጫ ነፃነት ለምን ይሰጣል? ይህን በተመለከተ ሲ.ኤስ. ሉዊስ በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ጽፏል፡- “የምርጫ ነፃነት፣ ምንም እንኳን ክፋትን ለመሥራት የሚያስችል ቢሆንም፣ ሊኖረን የሚገባውን ማንኛውንም ፍቅር ወይም መልካምነት ወይም ደስታ እንዲኖር የሚያደርገው ብቸኛው ነገር ነው።

እንደ ማሽን የሚሠሩ ፍጥረታት ያሉበትን ዓለም- መፍጠር ዋጋ የለውም። ከፍ ላሉ ፍጡራኑ እግዚአብሔር የነደፈው ደስታ፣ ከእርሱና ከእርስ በርሳቸው ጋር በነጻነትና በፈቃዳቸው የመስማማት ደስታ ነው። . . . ለዚህም ደግሞ ነፃ መሆን አለባቸው።”—ተራ ክርስትና (ኒው ዮርክ÷ ማክሚላን፣ 1960)፣ ገጽ. 52. ዘፍ. 2:16, 17ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ለአዳምና ለሔዋን የተሰጣቸውን የምርጫ ነፃነት የሚያሳዩት እንዴት ነው?



መጀመሪያውኑ የምርጫ ነፃነት ካልነበራቸው በስተቀር ለምን ያዛቸዋል? አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ በሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምድራችን በክፋት ተሞልታለች። ከውድቀት ታሪክ ቀጥሎ ባለው በዘፍ. ምዕራፍ 4 ውስጥ የኃጢአት አስከፊ ውጤት አቤል በወንድሙ በመገደሉ ይታያል። የውድቀት ታሪክ አዳምና ሔዋን የምርጫ ነፃነታቸውን ያላግባብ በመጠቀማቸው ኃጢአትና ክፋት ወደ ምድራችን እንዴት እንደመጣ ያሳያል።

በቃሉ ውስጥ የምርጫ ነፃነትን እውነታ እናያለን (ዘዳ. 7:12, 13ን፤ ኢያ. 24:14, 15ን፤ መዝ. 81:11–14ን፤ እና ኢሳ. 66:4ን ይመልከቱ)። ይብዛም ይነስም በሕይወታችን በእያንዳንዷ ቀን ፈጣሪ የሰጠንን የምርጫ ነፃነት እንጠቀማለን።

የምርጫ ነፃነት ከሌለን ሰው አንሆንም ነበር። እኛ ማሽን ወይም ደግሞ አእምሮ የሌለው ሮቦት እንመስል ነበር። የክፋት መከሰትና መዘዙ የሶኒ ኮርፖሬሽን አይቦ የሚባል የሮቦት ውሻ ፈጥሯል። እውነተኛ ውሻ ይመስላል ነገር ግን አይታመምም፣ በቁንጫዎች አይጠቃም፣ አይናከስም፣ መርፌ አይወጋም፣ ፀጉርም አያረግፍም። ታዲያ ትክክለኛ ውሻህን በአይቦ ትለውጠዋለህ? ካልሆነ፣ የአንተ ምርጫ፣ ምንም እንኳን አደጋ ቢኖረውም እግዚአብሔር ለምን የምርጫ ነፃነት እንዲኖረን አድርጎ እንደፈጠረን የተሻለ እንድትገነዘብ የሚረዳህ እንዴት ነው?

የካቲት 6
Feb 13

ፍቅር እና ክፋት?


እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ስለሆነ፣ ለፍጡራኑ የምርጫ ነፃነትን ሰጥቷል። ይህንን የምርጫ ነፃነት ያላግባብ መጠቀም ደግሞ የክፋት መንስኤ ነው። አሁንም ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ። እግዚአብሔር ክፋትን አምርሮ ቢጠላውም፣ ለጊዜውም ቢሆን እንዲኖር ይፈቅዳል ምክንያቱም የመከሰት ዕድሉን መከልከል የፍቅር ባሕርይ ስላልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋትም ደግሞ ለፍቅር አስፈላጊ የሆነውን መተማመንን ስለሚጎዳ ነው።

“እግዚአብሔርን ባለማወቅ ምድር ጨልማ ነበር። የጨለማው ግርዶሽ እንዲበራ፣ ዓለምም ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ፣ የሰይጣን የማታለል ኃይል መክሸፍ ነበረበት። ይህም በጉልበት ሊሆን አይችልም። ኃይልን መጠቀም ከእግዚአብሔር መንግሥት መርሆዎች ጋር ተጻራሪ ነው። እርሱ የሚፈልገው የፍቅርን አገልግሎት ብቻ ነው፤ ፍቅርም ሊገደድ አይችልም፤ በጉልበትም ሆነ በሥልጣን ሊገኝ አይችልም። ፍቅር የሚቀጣጠለው በፍቅር ብቻ ነው።

እግዚአብሔርን ማወቅ እርሱን መውደድ ነው፤ የእርሱ ባሕርይ ከሰይጣን ባሕርይ አንፃር መገለፅ አለበት።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 22.

ያለምርጫ ነፃነት ፍቅር ሊኖር አይችልም። እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ፣ ፍቅር እንዲኖር አስፈላጊ የሆነውን ነፃነት መከልከል ለእግዚአብሔር አማራጭ እንዳልሆነ ግልጽ ይመስላል። እንደ እግዚአብሔር መጨረሻውን ከመጀመሪያው የምናውቅ ብንሆን ብለን ብናስብ፣ ነፃነታችንን እንዲነሳን አንፈልግም ነበር።

ደግሞስ ፍቅር በሌለበት ዓለም ውስጥ መኖር የሚፈልግ ማን ነው? የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ሮሜ 8:18ን እና ራዕ. 21:3, 4ን ያንብቡ። በዓለማችን ውስጥ ብዙ ክፋት ቢኖርም፣ እነዚህ ጥቅሶች በእግዚአብሔር መልካምነት እንድንተማመን የሚያደርጉን እንዴት ነው?



በጨለማው ውስጥ ማየት ባንችልም፣ እግዚአብሔር መጨረሻውን ከመጀመሪያው ይመለከታል። ደግሞም በኢየሱስ ለሚያምኑ ሁሉ ተስፋ የተሰጣቸውን ዘላለማዊ ደስታ ማየት ይችላል። በሮሜ 8፡18 ላይ፡- “ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ” ይላል። ይህን አስደናቂ ተስፋ ለማመን እምነት አለን?

በተጨማሪም ፍቅርና ከፍቅር ጋር የተቆራኘው የምርጫ ነፃነት በጣም የተቀደሰና መሰረታዊ ስለሆነ፣ እኛን ከሚከለክለን ይልቅ፣ ኢየሱስን ብዙ ስቃይ ወደሚቀበልበት ወደ መስቀል እንደሚያመራው ያውቅ ነበር። የሚያስከፍለውን ዋጋ እያወቀም ቢሆን ይህንን ነፃነት ሰጠን። ለምንድነው ይህ ሁልጊዜ ልናስላስለው የሚገባ ወሳኝ ሐሳብ የሆነው? እግዚአብሔር የምርጫ ነፃነት የሰጠን መሆኑን ማሰላሰላችን፣ የሚሆነው ነገር ሁሉ የአምላክ ፈቃድ ነው ብለን እንዳናስብ የሚጠብቀን እንዴት ነው?

የካቲት 7
Feb 14


ተጨማሪ ሀሳብ


አበውና ነቢያት ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “ኃጢአት ለምን ተፈቀደ?” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 33-43 ያንብቡ።

“ከሰማይ ቢጣልም እንኳን፣ አምላክ በጥበቡ ሰይጣንን አላጠፋውም።

በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው የፍቅር አገልግሎት ብቻ ስለሆነ፣ የፍጡራኑ ታማኝነት በርሱ ፍትሕና ደግነት ላይ በማመን መመስረት አለበት። የሰማይና የዓለማት ነዋሪዎች፣ የኃጢአትን ምንነት ወይም መዘዝ ሊረዱ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ስለነበሩ፣ ያኔ ሰይጣንን ቢያጠፋው ኖሮ የእግዚአብሔርን ፍትሓዊነት ማየት ባልቻሉም ነበር። እርሱን ወዲያውኑ ቢደመስሰው ኖሮ፣ አንዳንዶች በፍቅር ሳይሆን በፍርሃት እግዚአብሔርን ያገለግሉ ነበር። የአሳቹ ተጽእኖ ወይም የክፋት መከሰትና መዘዙ የዓመፅ መንፈስ ሙሉ በሙሉ ባልጠፋ ነበር። ማብቂያ በሌላቸው ዘመናት ሁሉ ለዓለማት ጥቅም ሲባል፣ በመለኮታዊው መንግሥት ላይ የሰነዘራቸው ክሶች በሁሉም ፍጥረታት ዘንድ በእውነተኛው ብርሃን እንዲታዩ፣ የእግዚአብሔር ፍርድ፣ ምሕረትና የማይለወጠው ሕጉ ለዘላለም ጥያቄ እንዳይነሳባቸው፣ የሰይጣን መርሆዎች ፍሬ ማፍራት ነበረባቸው።

“ስለ ኃጢአት ምንነትና ስለ አስፈሪ ውጤቶቹ ዘላለማዊ ምስክር ይሆን ዘንድ፣ የሰይጣን አመጽ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ለዓለማት ትምህርት መሆን ነበረበት። የሰይጣን አሰራርና በሰዎችም ሆነ በመላእክት ላይ ያለው ውጤት መገለጡ፣ መለኮታዊውን ሥልጣን ወደ ጎን የመተው ፍሬ ምን እንደሚሆን ያሳያል።

የፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ደህንነት የተንጠለጠለው በእግዚአብሔር መንግሥት መኖር መሆኑን ይመሰክራል። ስለዚህ ይህ የዓመፅ አስከፊው ታሪክ ቅዱሳንን ሁሉ በመተላለፍ እንዳይታለሉ፣ ኃጢአት እንዳይሰሩና በቅጣቱ እንዳይሰቃዩ ለዘላለም ይጠብቃቸዋል።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ አበውና ነቢያት፣ ገጽ 42, 43


የመወያያ ጥያቄዎች




1. “ቲዮደሲ (Theodicy)” ማለት ክፋትም ቢኖር እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው ማለት ነው። ነገር ግን ለክፋት መኖር ምክንያት አያቀርብም። በሰማይ አንድ ሰው እንዲህ አለ ብለህ አስብ፣ “ኦ! አዎ ኢየሱስ፣ አሁን ቤተሰቦቼ በፊቴ ለምን እንደተሰቃዩና እንደተገደሉ ገብቶኛል። አዎ አሁን ሁሉም ነገር ትርጉም ይሰጣል። አመሰግናለሁ ኢየሱስ!” ይህ ልክ አይደለም። በታላቁ ተጋድሎ በስተመጨረሻ ነጻ የሚሆነው እግዚአብሔር እንጂ ክፋት እንዳልሆነ እንዴት ልንረዳ እንችላለን? (ትምህርት ዘጠኝን ይመልከቱ)

2. እንደ ኢዮብ ያለ ስሜት ተሰምቶህ ያውቃል? አንተ ወይም የምትወዳቸው ሰዎች ለደረሰባቸው ሥቃይ አሳማኝ ማብራሪያ ሊኖር አይችልም ብለህ ለማሰብ ተፈትነህ ታውቃለህ? ኢዮብ በመጨረሻ “የማያስተውለውን ነገር እንደተናገረ” መገንዘቡ (ኢዮ. 42: 3)፣ ጥያቄዎቻችንን ለማስተዋል የሚረዳን እንዴት ነው?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL