የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- መዝ. 33:5፣ መዝ. 85:10፣ ዘዳ. 32፡4፣ ያዕ 1፡17፣ ቲቶ 1፡2፣ ዘጸ. 32፡14፣ ማቴ. 5፡43–48።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ነገር ግን የሚመካው ምሕረትንና ፍርድን
ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና
በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል
እግዚአብሔር (ኤር. 9፡24)።
በጥንታዊው የቅርብ ምሥራቅ አገሮች፣ የአሕዛብ “አማልክት”ተለዋዋጭ፣
ሥነ-ምግባር የጎደላቸው እና ባሕርያቸው የማይገመት ብቻ ሳይሆኑ፣ እንደ
ሕፃን መስዋዕት ያሉ አሰቃቂ ድርጊቶችንም ይጠይቁ ነበር። ያም ቢሆን፣
አረማውያኑ በእነርሱ መልካምነት ስለማይተማመኑ፣ የጎሳቸውን “አማልክት”
ማስቀየም አይደፍሩም ነበር።
እንደ ዘዳ. 32፡17 ከእነዚህ “አማልክት” ጀርባ የነበሩት አጋንንት ናቸው
(በተጨማሪ 1 ቆሮ. 10፡20, 21ን ይመልከቱ)። የአምልኮ ሥርዓታቸውም ለብዝበዛ
የተመቻቸ ስለነበር፣ ሕዝቡን በታላቅ መንፈሳዊና ሥነ-ምግባራዊ ጨለማ ውስጥ
ከትቷቸዋል።
የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ከእነዚህ የአጋንንት ኃይሎች እጅግ የተለየ ነው።
ያህዌ ፍፁም መልካምና ባሕርይውም የማይለዋወጥ ነው። እናም አሁንም ሆነ
ለዘለአለም ተስፋ ሊኖረን የሚችለው፣ በእግዚአብሔር የማያቋርጥ መልካምነት
ብቻ ነው።
በጥንቱ ዓለም ከነበሩት እና ዛሬም ካሉት የሐሰት “አማልክት” ፍጹም
ተጻራሪ በሆነ መልኩ፣ ያህዌ ክፋት፣ መከራ፣ ኢ-ፍትሐዊነት እና ጭቆና በጥልቅ
ያሳስበዋል—እነዚህንም ሁሉ ያለማቋረጥ በማያሻማ ሁኔታ ያወግዛል። ከሁሉም
በላይ ደግሞ አንድ ቀን እነዚህን ግፎች ሁሉ ያጠፋቸዋል።
*የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።
እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል
በቃሉ ውስጥ ፍቅር እና ፍትሕ የተጋመዱ ናቸው። እውነተኛ ፍቅር
ፍትሕን ይሻል፣ እውነተኛ ፍትሕም የሚኖረውና የሚሰጠው በፍቅር ብቻ ነው።
እነዚህን ሁለት ፅንሰ-ሀሳቦች የማይነጣጠሉ እንደሆኑ ለማሰብ አልታደልንም፣
ምክንያቱም ፍቅር እና ፍትሕ በሰዎች እጅጉን ተዛብተዋል።
መዝ. 33:5ን፣ ኢሳ. 61:8ን፣ ኤር. 9:24ን፣ መዝ. 85:10ን እና መዝ.
89:14ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች አምላክ ለፍትሕ ያለውን ትኩረት
የሚያሳዩት እንዴት ነው?
እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር ፍትሕን እንደሚወድ በግልጽ ይናገራሉ
(መዝ. 33፡5፣ ኢሳ. 61፡8)። በቃሉ ውስጥ የፍቅር እና የፍትሕ ሀሳቦች
በማይነጣጠሉ መልኩ የተቆራኙ ናቸው። የእግዚአብሔር ፍቅር እና ጽድቅ
አብረው ስለሚሄዱ፣ ጽድቅ እና ፍትሕ በዚህ አለም እንዲከወኑ እጅግ ይገደዋል።
ስለሆነም ነቢያት ፍትሐዊ ያልሆኑ ሕጎችን፣ የሐሰት ሚዛንን፣ የድሆችንና
መበለቶችን ወይም የተጠቁትን ጭቆና ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ኢ-ፍትሐዊነት
ያወግዛሉ። ሰዎች ብዙ ክፋትና ግፍ ቢፈጽሙም፣ እግዚአብሔር ግን ያለማቋረጥ
“ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ ያደርጋል” (ኤር. 9፡24)። በዚህም
መሠረት በቃሉ ውስጥ፣ ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆኑት በክፉ አድራጊዎች እና
ጨቋኞች ላይ ቅጣትን፣ የግፍና ጭቆና ሰለባ ለሆኑት ደግሞ ፍትሕ እና ነፃነትን
ስለሚያመጣ መልካም የሆነውን መለኮታዊ ፍርድ በጉጉት ይጠብቃሉ።
እንዲያውም ጽድቅና ፍትሕ የአምላክ መንግሥት መሠረት ናቸው።
የእግዚአብሔር የፍቅር መንግሥት ፍትሐዊና ጽድቅን የተሞላ ነው፤ ምግባረ
ብልሹ ከሆኑት ከዚህ ዓለም መንግሥታት ፈጽሞ የተለየ ነው። እነርሱ ብዙውን
ጊዜ ለግል ጥቅማቸውና ሥልጣናቸው ሲሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችን እንዲቀጥሉ
ያደርጋሉ። በእግዚአብሔር "ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም
ተስማሙ” (መዝ. 85:10)።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
እግዚአብሔርም ከእኛ የሚጠብቀውን ግልጽ አድርጓል። “ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር
በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? (ሚክ. 6:8)። ከእግዚአብሔር ባሕርይ
ውስጥ ልናንጸባርቀው የሚገባን ዋንኛው ነገር ፍቅር ሲሆን ይህም ከፍቅር
የሚመነጨውን ፍትሕና ምሕረት ያካትታል።
አሁንም ቢሆን የተዛባ የሰው ፍትሕ ምሳሌዎች ምንድናቸው? ታዲያ
አንድ ቀን የእግዚአብሔር ፍጹም ፍትሕ እንዲመጣ እንዴት መጮህ
የለብንም?
እግዚአብሔር እንዲሁ ፍትሕን እወዳለሁ የሚል እና ሰዎችንም ፍትሕን
እንዲወዱና እንዲያደርጉ የሚጎተጉት ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር
ራሱ እነዚህን ባሕርያት ፍጹም በሆነና በማያወላውል መልኩ በተምሳሌትነት
ያሳየናል። እግዚአብሔር ፍጹም ቅዱስ፣ ታማኝ፣ ጻድቅ እና አፍቃሪ እንደሆነ ቃሉ
ያስተምረናል። ሁልጊዜም የሚያደርገው የሚወደድ፣ ጽድቅ የተሞላና ፍትሃዊ
ነገር ብቻ ነው። እርሱ ፈጽሞ አይሳሳትም።
ዘዳ 32:4ንና መዝ. 92:15ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች ስለ እግዚአብሔር
ታማኝነት እና ጽድቅ ምን ያስተምሩናል?
እነዚህ እና ሌሎች ብዙ ጥቅሶች እግዚአብሔር ጻድቅና አፍቃሪ መሆኑን
ይናገራሉ—“በእርሱም ዘንድ ዓመፃ የለም” (መዝ. 92፡15፣ ከመዝ. 25፡8ና መዝ.
129፡4 ጋር ያስተያዩ)። እግዚአብሔር “ክፋትን አያደርግም። ፍርዱን በየማለዳው
ወደ ብርሃን ያወጣል፣ ሳያወጣውም አይቀርም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን
አያውቅም” (ሶፎ. 3፡5)። የእግዚአብሔር ባሕርይ የፍትሕ መጓደልን ከሚወዱ
ሰዎች በቀጥታ ተቃራኒ መሆኑን ያስተውሉ።
እግዚአብሔር ለሁሉም የሚበጀውን ያውቃል፣ ለሁሉም የተሻለው ነገር
እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል
እንዲሆን ይፈልጋል፣ ለሁሉም ውጤቱ ያማረ እንዲሆን ዘወትር ይሰራል።
መዝ. 9:7, 8ን እና መዝ.145:9–17ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ምን ያስተምራሉ?
የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ “ጻድቅ ዳኛ” ነው (መዝ. 7፡11)፣ ክፉም ከእርሱ
ጋር አይኖርም (መዝ. 5፡4)። 1ኛ ዮሐ. 1፡5 እንደሚያስተምረው፡- “እግዚአብሔር
ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም”። እግዚአብሔር ፍፁም መልካም
ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን እንደ ያዕ. 1፡13 “እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንም”
(ከዕን. 1፡13 ጋር ያስተያዩ)።
በዚህ ሁሉ፣ የእግዚአብሔር መልካምነትና ክብር ይታያል። ብዙዎች
ስልጣንን ጣዖት ቢያደርጉትም፣ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ስልጣኑን
የሚጠቀመው በጽድቅ እና በፍቅር መንገድ ብቻ ነው። ሙሴ እግዚአብሔርን
“ክብርህን አሳየኝ” ብሎ ሲጠይቀው፣ እግዚአብሔርም “ቸርነቴን ሁሉ በፊትህ
አሳልፋለሁ” ያለው በአጋጣሚ አይደለም (ዘጸ. 33፡18, 19)።
ለምንድነው እንደዚህ አይነቱ መልካም አምላክ በዚህ አለም ላይ ክፋት
እንዲበዛ የፈቀደው? በክፍላችሁ መልሳችሁን አብራሩ።
ሚል. 3:6ን እና ያዕ፣ 1:17ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች ስለ እግዚአብሔር ባሕሪ ምን ያስተምራሉ?
በሚል. 3፡6 ላይ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ አልለወጥም” ይላል። አንዳንዶች
ይህንን ጥቅስ አንብበው፣ እግዚአብሔር በምንም መንገድ አይለወጥም ብለው
ቢወስዱትም ፣ የቀረው የጥቅሱ ክፍልና አውዱ የሚያረጋግጠው የእግዚአብሔርን
የሞራል ባሕርይ አለመለዋወጥ ነው። የቀረው የጥቅሱ ክፍል እንደሚያመለክተው
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያለው ግንኙነት ሊለወጥ እንደሚችል ነው፤
ምክንያቱም እግዚአብሔር ‘‘እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፣ ስለዚህ የጠፋችሁ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
አይደላችሁም"ይላልና። ቀጥሎ ባለው ጥቅስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ "ወደ እኔ
ተመለሱ፣ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ " ይላል (ሚል. 3:7)።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር በሁኔታዎች የተመሰረተ ግንኙነቶች
ውስጥ ቢገባም፣ ባሕርይው ግን አይለወጥም - ሁልጊዜ ያው ነው። ይህም በያዕ.
1፡17 ላይ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በጎና ፍጹም ስጦታዎች ሁሉ ከማይለዋወጠው
ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚመጡ ያውጃል። ስለዚህ እግዚአብሔር የክፋት
ምንጭ አይደለም።
እዚህ እና በሌሎችም ቦታዎች፣ ቃሉ በተደጋጋሚ የእግዚአብሔር
ባሕርይ የማይለዋወጥ መሆኑን ያስተምራል። በሌላ አነጋገር መጽሐፍ ቅዱስ
ወጥ በሆነ መልኩ የእግዚአብሔርን የሞራል አለመለዋወጥ ያስተምራል። ሆኖም
እግዚአብሔር ከፍጥረታት ጋር እውነተኛ ግንኙነት ውስጥ በመግባት፣ ሁልጊዜ
ፍቅር የተሞላና ፍትሃዊ ምላሽ ይሰጣቸዋል።
2 ጢሞ. 2:13ን፣ ቲቶ 1:2ን እና ዕብ. 6:17, 18ን ያንብቡ። እነዚህ
ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ምን ያስተምራሉ?
እግዚአብሔር ራሱን ሊክድ አይችልም፤ ፈጽሞ አይዋሽም፤ ተስፋዎቹም
የፀኑ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ስለ እኛ ራሱን በመስቀል ላይ (በክርስቶስ)
በፈቃዱ የሰጠ ያው አምላክ እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። እርሱ
ያለምንም ጥርጥር የሚታመን አምላክ ነው፣ ለወደፊቱም አስተማማኝ ተስፋ
ሊኖረን ይችላል ምክንያቱም ዕብ. 13: 8 "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ
ለዘላለምም ያው ነው" ይላል።
በሕይወታችሁ ነገሮች የተበላሹ ቢሆኑም እንኳን በእግዚአብሔር
መልካምነት መታመንን እንዴት መማር ትችላላችሁ? በመልካምነቱ
ለመታመን በመስቀል ላይ ያለው የእግዚአብሔር ምስል ምን
ያስተምረናል?
እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል
እግዚአብሔር “ሊፀፀት” ይችላል? ከሆነ ምን ማለት ነው? የእግዚአብሔር
ባሕርይ ፈጽሞ እንደማይለወጥ አይተናል። ሆኖም አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥቅሶች እግዚአብሔር “ተጸጸተ”ወይም “ሐሳቡን ለወጠ” ብለው ይናገራሉ።
ለሰዎች መጸጸት መሳሳትን ማወቅን ያካትታል። ታዲያ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍሎች አምላክን “ተጸጸተ” ብለው የሚገልጹት እንዴት ነው?
ዘጸ. 32:14ን አንብበው ከኤር. 18:4–10 ጋር ያስተያዩ። ስለ
እግዚአብሔር “መጸጸት” የተሰጡትን እነዚህን ገለፃዎች እንዴት
ይረዷቸዋል?
በእነዚህ እና በሌሎች በርካታ ክፍሎች ውስጥ፣ እግዚአብሔር
ሰዎች ሲጸጸቱ ወይም ሲማልዱ በምላሹ ከፍርዱ እንደሚመለስ ተገልጿል።
እግዚአብሔር ሰዎች ከክፋታቸው ቢመለሱ፣ ሊያደርገው ካቀደው ፍርድ
እንደሚፀፀት ቃል ገብቷል።
ዘኍ. 23:19ን እና 1 ሳሙ. 15:29ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ
እግዚአብሔር “መጸጸት” ምን ያስተምራሉ?
እነዚህ ክፍሎች እግዚአብሔር “ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም” (1ሳሙ. 15፡
29)፤ "ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው
ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?”
ይላሉ (ዘኍ. 23:19)። ከሌሎቹ ክፍሎች አንፃር ስናነባቸው፣ እነዚህ ጥቅሶች
እግዚአብሔር በጭራሽ “አይጸጸትም” ይላሉ ብለን ልንወስድ አንችልም፣
ይልቅስ እንደ ሰው “አይጸጸትም” የሚለውን እውነት ነው የሚያስተላልፉት።
እግዚአብሔር ሁልጊዜ የገባውን ቃል ይጠብቃል። ምንም እንኳን በሰዎች ንስሐ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
ምክንያት የሚወስደውን እርምጃ ቢለውጥም፣ ያን የሚያደርገው ሁልጊዜም እንደ
መልካምነቱና እና እንደ ቃሉ ነው። ሰዎች ንስሐ ሲገቡ፣ እግዚአብሔር በምላሹ
ሊፈጽመው ከነበረው ፍርድ ይመለሳል፣ ምክንያቱም ባሕርይው መልካም፣
ጻድቅ፣ አፍቃሪ እና መሐሪ ስለሆነ ነው።
ስለ መለኮታዊው “ጸጸት” የመጽሐፍ ቅዱስ መግለጫዎች አስፈላጊነት
ምንድነው? ይህ ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ ወጥነት ምን ያስተላልፋል
- ጎን ለጎን እግዚአብሔር ወደ እውነተኛ ሰጥቶ የመቀበል ግንኙነት
የሚገባና ያም ለእርሱ ለውጥ የሚያመጣ ቢሆንም?
ቃሉ እየደጋገመ እንዲህ ብሎ ያስተምራል፡- "አንተም አምላክህ እግዚአብሔር
እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና
ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ "
(ዘዳ. 7:9)። የመልካምነቱና የፍቅር ባሕርይው ከምንም በላይ በመስቀል ላይ በኢየሱስ
ተገልጧል (ሮሜ 3፡25, 26ን፣ ሮሜ. 5፡8ን ይመልከቱ)። መዝ. 100:5 "እግዚአብሔር
መልካም ነው፣ ፅኑ ፍቅሩም ለዘላለም፣ ታማኝነቱም ለትውልድ ሁሉ ነው” ይላል
(ከመዝ. 89፡2 ጋር ያስተያዩ)። ስለዚህ እግዚአብሔር ሊታመን ይችላል፤ ለልጆቹም
የሚሰጣቸው በጎ ስጦታዎችን ብቻ ነው (ያዕ. 1፡17፤ ከሉቃ. 11፡11–13 ጋር ያስተያዩ)።
እንዲያውም ጠላቶቹ ለሆኑት እንኳን ሳይቀር መልካም ነገሮችን ይሰጣቸዋል።
ማቴ. 5:43–48ን ያንብቡ። ይህ ስለ እግዚአብሔር አስደናቂ ፍቅር
ምን ያስተምረናል? ከዚህ የኢየሱስ አስተምህሮ አንጻር ለሌሎች ምን
ማድረግ አለብን?
ማቴ. 5 የእግዚአብሔርን ፍቅር ፍጹም ፍቅር እንደሆነ አድርጎ
ይገልጸዋል። ፍጽምና የጎደለው ፍቅር የሚወዱትን ብቻ የሚወድ ፍቅር ነው።
ነገር ግን እግዚአብሔር የሚጠሉትን፣ ጠላቶቹም የሆኑትን እንኳን ይወዳቸዋል።
ፍቅሩ ሙሉ፣ ፍጹምም ነው።
እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል
ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ፍቅር እና ምሕረት ልናስበው ከምንችለው
በላይ የላቀ ቢሆንም፣ ፍትሕን ፈጽሞ አይሽረውም ወይም አይጻረረውም።
በተቃራኒው ፍርድንና ምሕረትን በአንድ ያጣምራቸዋል (መዝ. 85፡10)።
በተመሳሳይ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይመክረናል፡- “ምሕረትንና ፍርድን
ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን” (ሆሴ. 12፡6)። ሌላ እትም “ፍቅርንና
ፍትሕን አጥብቀህ ያዝ”ይላል (ሆሴ. 12፡6፤ ከሉቃ. 11፡42 ጋር ያስተያዩ)።
በመጨረሻ እግዚአብሔር ራሱ ፍጹም ፍትሕን ያመጣል። ሮሜ 2፡5 “ቅን
ፍርዱ ይገለጣል” ብሎ ያስተምራል። በመጨረሻም የተዋጁት እንዲህ ይዘምራሉ፡
- “ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ
ንጉሥ ሆይ፥ መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ፥ የማይፈራህና ስምህን
የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፥ የጽድቅም ሥራህ (ፍርድህ) ስለ
ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ በፊትህም ይሰግዳሉ።” (ራዕ. 15:3, 4፤ ከራዕ. 19:1,
2 ጋር ያስተያዩ)።
ኢሳ. 25፡1 “አቤቱ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን
በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም
አመሰግናለሁ” ብሎ ይናገራል። በመጥፎ ጊዜም ቢሆን አምላክን
ማመስገንን እንዴት መማር እንችላለን? በጎ ተጽዕኖ ልታደርግ
በምትችልበት ሁሉ ፍትሕን በሚያጎለብት መልኩ ሕይወትህ ራሱ
ለአምላክ የምስጋና መስዋዕት ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ ከተባለው የኤለን
ጂ. ኋይት መጽሐፍ “እግዚአብሔር ለሰው ያለው ፍቅር” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ
9-15 ያንብቡ።
"የእግዚአብሔር ቃል ባሕርይውን ይገልጻል። እርሱ ራሱ ወሰን
የሌለውን ፍቅሩንና ርኅራኄውን ገልጿል። ሙሴ ‘ክብርህን አሳየኝ’ ብሎ በጸለየ
ጊዜ፣ እግዚአብሔር ‘መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ’ ሲል መለሰ (ዘጸ.
33:18, 19)። ክብሩም ይህ ነው። ጌታም በሙሴ ፊት አለፈና፡- 'እግዚአብሔር፥
እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥ እስከ
ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የሚል’ ሲል አወጀ (ዘጸ. 34:6, 7)። እርሱ 'ለቍጣ የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ ነው'፣
'ምሕረትን ይወድዳልና' '' (ዮና. 4፡2፣ ሚክ 7፡18)።
"በሰማይና በምድር ሊቆጠሩ በማይችሉ መልካምነቶቹ እግዚአብሔር
ልባችንን ከእርሱ ጋር አቆራኝቷል። በተፈጥሮ እና የሰው ልብ ሊረዳው በሚችለው
ጥልቅና ፍቅር የተሞላበት ምድራዊ ግንኙነት ራሱን ሊገልጥልን ፈለገ። ሆኖም
እነዚህ ፍቅሩን በሙላት አይገልጹትም። ምንም እንኳን እነዚህ ማስረጃዎች ሁሉ
የተሰጡ ቢሆንም፣ የመልካም ጠላት የሆነው ሰይጣን የሰውን አእምሮ አሳወረ፣
እግዚአብሔርንም በፍርሃት እንዲመለከቱት አደረገ፤ ጨካኝና ይቅር የማይል
አድርገው ተረዱት። ሰይጣን ሰዎችን የእግዚአብሔር ዋናው ባሕርይ ፅኑ ፍርድ
መፍረድ፣ ደግሞም ጨካኝ ዳኛ፣ ክፉና የማይምር አበዳሪ እንደሆነ አድርገው
እንዲያስቡት መራቸው። ፈጣሪን በሰዎች ላይ ፍርዱን ያፈስባቸው ዘንድ በቅናት
ጥፋታቸውንና ስህተታቸውን የሚመለከት አድርጎ ሳለው። ኢየሱስ በሰዎች
መካከል ሊኖር የመጣው፣ የአምላክን ወሰን የሌለው ፍቅር ለዓለም በመግለጥ፣
ይህንን ድቅድቅ ጨለማ ለማስወገድ ነበር።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ ወደ ክርስቶስ
የሚያደርስ መንገድ፣ ገጽ 10, 11
1. የእግዚአብሔር ክብር ከመልካምነቱ ጋር የተጣመረ መሆኑን መገንዘብ
በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህ የእግዚአብሔርን
ፍቅር እና ባሕርይ ሳያጎላ፣ ታላቅ ኃይሉ ላይ የሚያተኩረውን
የክብር ሥነ-መለኮት አስተምህሮ እንዴት ያርማል?
2. የእግዚአብሔርን
መልካምነት
ተጠራጥረህ
ታውቃለህ?
እግዚአብሔርን እንከተላለን የሚሉ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ
በሚያደርጉት ነገር ወይም በዓለም ላይ ካለው ክፋት የተነሳ
የእግዚአብሔርን መልካምነት የተጠራጠረ የምታውቀው ሰው አለ?
ለዚህ ጥያቄ ምላሽ እንዴት አገኘህለት? እናም በእግዚአብሔር
መልካምነት ጥያቄ ያደረበትን ሰው እንዴት መርዳት ትችላለህ?
የሚቀጥለውን ሳምንት ትምህርት ይመልከቱ።
3. በክፍል ውስጥ ለሰኞው ጥያቄ መልስ ይፈልጉ። የታላቁ ተጋድሎ
እውነታ አሁን ያለውን ክፋት ሁሉ እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው?