የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- : ማር.11፤ 1ኛ ነገሥት 1:32–48፤ ዘካ.9:9፣ 10፤ ኢሳ. 56:7፤ ኤር. 7:11፤ ማር. 12:1–34.
የመታሰቢያ ጥቅስ: “ ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው
አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ
አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት” (ማር 11:25)።
ማርቆስ ምዕራፍ 2 እና 3 ላይ በክርስቶስና በኃይማኖት መሪዎች መካከል
የነበሩ ተከታታይነት ያላቸው አምስት ተቃርኖዎች ተመዝግበዋል
(3ኛውን ትምህርት ይመልከቱ)። በዚህ ሳምንት ትምህርት፣
ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርስ ከኃይማኖት መሪዎች የደረሱበትን ስድስት
ተከታታይነት ያላቸውን ተቃርኖዎች እንመለከታለን። የተቃርኖዎቹ ሁለቱ
ስብስቦች በምድራዊ አገልግሎቱ መጀመሪያና መጨረሻ ላይ እንደ ማጠቃለያ
የተቀመጡ ናቸው። እያንዳንዱ ስብስብ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የሚገጥሙ
ወሳኝ ጉዳዮችን የሚመለከት ነው። በእነዚህ ተቃርኖ ባለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ
እንኳን የኢየሱስ መመሪያዎች አማኞችን መሰረታዊ በሆኑ የእምነት ጉዳዮችም
ሆነ በየዕለቱ ልምምድ ተግባራዊ ጉዳዮች ላይ ለመምራት ይረዳሉ።
የኃይማኖት መሪዎች የመጡት ኢየሱስን ለመጋፈጥ፣ ግራ ለማጋባት እና
ለማሸነፍ ነበር፤ ነገር ግን አልተሳካላቸውም። ገሚሱ የዚህ ሳምንት ትምህርት
ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲቃወሙ የሚያደርግ ነገር ምን እንደሆነ መተንተንን
እና ክርስቲያኖች ስለ ሌሎች ያላቸውን የተዛባ (የጥላቻ) አመለካከት ጥሰው
በማለፍ የመንፈስን ጥሪ እየተቋቋሙ ላሉ ሰዎች ልቦች ለመናገር ምን ማድረግ
እንዳለባቸው ማሰብን ያካትታል።
ማርቆስ 11 ላይ የኢየሱስ አገልግሎት ለፋሲካ (ከመጋቢት-ሚያዝያ)
በኢየሩሳሌም ይሆናል። ማርቆስ ምዕራፍ 11-16 ከአንድ ሳምንት ያልበለጠ ጊዜን
ይሸፍናል፤ የትረካው ጊዜ በሚታይ መልኩ አዝግሟል። የመጀመሪያዎቹ 10
ምዕራፎች በግምት ሶስት አመት ተኩልን ይሸፍናሉ። ይህ ማዝገም የእነዚህን
የመዝጊያ ትዕይንቶች አስፈላጊነት ይጠቁማል።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሃሴ 25 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ማር 11:1–11 እና ዘካ. 9:9፣ 10ን ያንብቡ።. በእነዚህ ቦታዎች እየሆነ ያለው ነገር ምንድር ነው?
የዚህ ታሪክ ግማሹ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ለመጓዝ የሚጋልበውን
አህያ በዚያ አካባቢ ከነበረው መንደር እንዲያመጡ ሁለት ደቀ መዛሙርትን
የላከበትን ታሪክ ያካትታል። በዚህ ዘገባ ላይ ይህን ያህል ብዙ ጊዜ የባከነው
ለምንድር ነው? መልሱ ሁለት ነው። በመጀመሪያ፣ የኢየሱስን ወደዚያ የመድረሱን
ስብዕና በማጉላትና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በማገናኘት የኢየሱስን ትንቢታዊ
ኃይል ያሳያል። ሁለተኛ፣ የታሪኩ ይህኛው ክፍል ንጉሡ በአህያ ውርንጭላ ወደ
ኢየሩሳሌም መሄዱን ከሚናገረው ከዘካሪያስ 9፡9፣10 ጋር ያገናኛል። ይህ ታሪክ
አዶንያስ የአባቱን ዙፋን በማታለል መውሰድ በፈለገ ጊዜ ዳዊት ወዲያውኑ
ለሰለሞን የንግስና ዘውድ እንዲጫን በማዘዙ ሰለሞን አህያን እየጋለበ ወደ
ኢየሩሳሌም መግባቱን ያሳስባል (1ኛ ነገ. 1፡32-48)።
“ከክርስቶስ ልደት አምስት መቶ ዓመታት በፊት ነቢዩ ዘካሪያስ የንጉሡን
ወደ እሥራኤል መምጣት ተንብዮ ነበር። ይህ ትንቢት አሁን ሊፈጸም ነው። እስካሁን
ድረስ የንጉሥነት ክብሮችን አልቀበል ያለው አሁን ተስፋ የተገባለት የዳዊት ዙፋን
ወራሽ ሆኖ መጣ።”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 569.
ኢየሩሳሌም ከባህር ጠለል 2400 ጫማ (740 ሜትር ገደማ) ላይ
በኮረብታማ ክልል ውስጥ ትገኛለች። በኢየሱስ ዘመን የነበረው የሕዝቧ ብዛት
ከ400000 እስከ 500000 ድረስ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በፋሲካ ጊዜ ከዚህም
ሊበልጥ ይችላል። ከተማው የተቀመጠበት ቦታ ወደ 250 ሄክታር ብቻ ሊሸፍን
ይችላል፣ ነገር ግን ከእነዚህ ሄክታሮች ውስጥ የቤተ መቅደሱ ተራራ ወደ 37
ሄክታር የሚሆነውን ይሸፍናል። ውብ የሆነው የቤተ መቅደሱ ሕንጻ በከተማው
ጎልቶ ይታይ ነበር።
ኢየሱስ ከደብረ ዘይት ተራራ በመውረድ በቤተ መቅደስ ተራራ ባለው
በወርቃማው በር ወደ ከተማዋ በምሥራቅ በኩል ገባ (በሩ አሁን በሸክላ ግንብ
ተዘግቷል)። በእርሱ መግባት መላው ከተማ የተሸበረ ሲሆን ሁሉም ሰው እርሱ
የፈጸመውን ምሳሌያዊ ድርጊት ተገንዝቧል። ክርስቶስን አጅቦ የነበረው ሕዝብ
ሆሳዕና በማለት ይጮህ ነበር። የቃሉ ትርጉም በመጀመሪያ ‹‹አሁን አድን›› የሚል
ሲሆን በመጨረሻ ‹‹ምሥጋና ለእግዚአብሔር ይሁን›› የሚል ሆኗል።
ኢየሱስ በመላው የማርቆስ መጽሐፍ ውስጥ በምስጢር እንዲያዝ
የጠየቀው ጊዜ አልፏል። አሁን ኢየሱስ በደንብ የሚታወቅ የንጉስነት ምልከት
የሆነ ተግባርን በመጠቀም ወደ ኢየሩሳሌም በግልጽ ይገባል። ወደ ቤተ መቅደስ
ገባ፤ ነገር ግን ቀኑ ሊመሽ ተቃርቦ ስለነበር ዝም ብሎ አከባቢውን ተመልክቶ ከደቀ
መዛሙርቱ ጋር ወደ ቢታኒያ ሄደ። ወደ ህውከት ወይም ወደ አመጽ ሊለወጥ
ይችል የነበረው ሁኔታ ከዚያ በተቃራኒ በጸጥታ ወደ ማደሪያ በመሄድ ተጠናቀቀ።
ነገር ግን ቀጣዩ ቀን የተለየ ይሆናል።
አህያን የመጋለብ ሀሳብ የትህትናን (ራስን ዝቅ የማድረግን) ሀሳብ ይቀሰቅሳል። ይህ
በተለይ ለክርስቲያኖች አስፈላጊ ባህሪይ የሆነው ለምንድር ነው? በመስቀል ብርሃን እኛ
ልንኮራበት የሚገባው ነገር ምንድር ነው?
ማር. 11:12–26ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ የተገለጹ ክስተቶች ወሳኝነት ምንድር ነው?
ጧት ከቢታኒያ ሲመጣ ከኢየሩሳሌም ወደ ሁለት ማይሎች በሚሆን ርቀት
(ከሶስት ኪሎ ሜትር ትንሽ በሚበልጥ) ኢየሱስ ተራበ። በቅጠል የተሸፈነ የበለስ ዛፍ
በመመልከት ምናልባት ፍሬ አገኝበት እንደሆን በማለት ወደ ዛፉ ሄደ። እንደ ብሉይ
ኪዳን ሕግ አንድ ሰው ከተራበ ከጎረቤቱ እርሻ ወይም የአትክልት ቦታ መብላት
ስለሚችል የኢየሱስ ድርጊት እንደ ስርቆት አይቆጠርም (ዘሌ. 19፡9፤ 23፡22፤ ዘዳ. 23፡
25)። ነገር ግን ምንም ፍሬ ስላላገኘባት ዛፊቱን “ ከእንግዲህ ማንም ለዘላለም ፍሬ
አይብላብሽ” አላት (ማር. 11:14)። ይህ ድርጊት ለኢየሱስ እንግዳና ያልተለመደ ተግባር
ነበር፤ ነገር ግን ተከትሎ የመጣው ነገር ደግሞ የበለጠውን የሚያስገርም ነበር።
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ቀጥሎ የሆነው ነገር የተከሰተው በአህዛብ አደባባይ መስዋዕቶች
በሚሸጡበት ቦታ (በቅርቡ በቀያፋ የተጀመረ) ይመስላል። ጸጥ ያለ አምልኮ
ይመለስ ዘንድ ኢየሱስ ሻጮችን ከአደባባዩ አስወጣቸው። የእርሱ ድርጊት በቤተ
መቅደስ ሥርዓት ኃላፊነት ከነበራቸው ሰዎች ድርጊት ይለያል።
ኢየሱስ ቅዱስ ላልሆነው ሕዝብ ከባድ ተግሳጽ የሚሆኑ ሁለት የብሉይ
ኪዳን ንባቦችን አገናኘ። ቤተ መቅደሱ አህዛብን ጨምሮ ለሰዎች ሁሉ የጸሎት
ቤት እንደሚሆን ተናገረ (ኢሳ.56፡7)። ከዚያ በመቀጠል መሪዎች ቤተ መቅደሱን
የሌቦች ዋሻ አድርገውታል አለ (ኤር. 7፡11)። ከዚያም አስደናቂ በሆነው በዚህ ቀን
መጨረሻ ላይ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከተማውን ለቆ ሄደ (ማር. 11፡19)።
በቀጣዩ ጧት ወደ ከተማው ተመልሰው ሲሄዱ (ማር. 11፡20-26ን ይመልከቱ)
በለሲቱ ከስርዋ ደርቃ ሲመለከቱ ተደነቁ። ኢየሱስ ስለሆነው ነገር እያብራራ ሳለ ስለ
ጸሎትና ስለ ይቅርታ ትምህርት ሰጠ። ይህ ሁሉ ምን ማለት ነው?
እነዚህ ሁለት ታሪኮች በማርቆስ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ አራተኛ በሌላ ታሪክ
መካከል የገቡ (የሳንዲዊች) ታሪኮች ናቸው (3ኛውን ትምህርት ይመልከቱ)።
እነዚህን በሚመስሉ ታሪኮች በትወና መልክ የቀረበ ምጸት (አይሮኒ) ተቃራኒ
ተግባር ከሚፈጽሙ ገጸ ባህሪያት ጋር ወይም ትይዩ ተግባራትን ከሚፈጽሙ
ተቃራኒ ባህሪያት ጋር ቀርቧል። ኢየሱስ የበለስ ዛፏን ረግሞ ቤተ መቅደሱን አነጻ፣
ተቃራኒ ተግባሮች። ነገር ግን ምጸቱ (አይሮኒ) የኃይማኖት መሪዎች ኢየሱስን
ለመግደል ያሴሩ ሲሆን ድርጊቱ በኢየሱስ ተፈጻሚነት ያገኙ የቤተ መቅደስ
አገልግሎቶች ወደ ፍጻሜ መምጣታቸውን ይገልጻል።
ኢየሱስ ከሕይወትዎ እንዲያጸዳ የሚፈልጉአቸው ነገሮች ምንድር ናቸው? ይህ
እንዴት ይሆናል?
ማር. 11:27–33ን ያንብቡ። የኃይማኖት መሪዎች ወደ ኢየሱስ ያመጡአቸው ተግዳሮቶች ምን ነበሩ? ኢየሱስ ለግድድሮሾቹ መልስ የሰጠው እንዴት ነበር?
ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን ካነጻ ከአንድ ቀን በኋላ የኃይማኖት መሪዎች
ትናንት የሰራውን ነገር በምን ሥልጣን እንዳደረገ በመጠየቅ በቤተ መቅደሱ ቅጥር
ጊቢ ውስጥ ተጋፈጡት። እውነትን እየፈለጉ ሳይሆን ሊያጠምዱት እየፈለጉ ነበር።
ሥልጣኑ ከእግዚአብሔር ነው ካለ አንድ ተራ የሆነ የገጠር አናጺ ይህ ሥልጣን
እንዳለው አያምኑም። ሥልጣኑ ሰብአዊ ነው ካለ እንደ ሞኝ ሰው በመቁጠር
ከእርሱ ተለይተው ይሄዳሉ።
ነገር ግን ኢየሱስ ያዘጋጁለትን ወጥመድ በመመልከት እርሱ
የሚጠይቃቸውን ጥያቄ ከመለሱ እርሱም ጥያቄአቸውን እንደሚመልስ
ነገራቸው። ጥያቄውም የመጥምቁ ዮሐንስ ጥምቀት ከእግዚአብሔር ነው ወይስ
ከሰው የሚል ነበር።
ወጥመድ ውስጥ የገቡት ራሳቸው እንደሆኑ መሪዎቹ ወዲያውኑ ተመለከቱ።
ከእግዚአብሔር ነው ካሉ ኢየሱስ ‹‹ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?›› ሊላቸው ነው።
ከሰዎች ነው እንዳይሉ ደግሞ ሕዝቡን ፈሩ። ስለዚህ አናውቅም ብለው ዋሹ። ይህ
ኢየሱስ የእነርሱን ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ አንዳይሆን ዕድል ሰጠው።
ማር. 12:1–12ን ያንብቡ። ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን
ኢየሱስ የገለጸው እንዴት ነበር? ውጤቱስ ምን ነበር?
ኢየሱስ ስለ ወይን ቦታ፣ ስለ ወይኑ ባለቤትና በማሳው እንዲሰሩ
ስለቀጠራቸው ጭሰኞች ምሳሌ ተናገረ። ኢየሱስ የተናገረው ታሪክ እግዚአብሔር
ታማኝ ባልሆነችው እሥራኤል ላይ ክስ ካቀረበበት በኢሳይያስ ምዕራፍ 5 ላይ
ካለው ወይን ስፍራ ምሳሌ ጋር ትልቅ መመሳሰል አለው። እያንዳንዱ ሰው፣
በተለይም የኃይማኖት መሪዎች ንጽጽሩን ይገነዘባሉ።
ታሪኩ ባልተለመደ ሁኔታ ጭሰኞቹ ከማሳው ምንም ፍሬ ለባለቤቱ
ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ይገልጻል። ይልቁንም ባሪያዎቹን
ደበደቡአቸው ገደሉአቸውም። በመጨረሻ የእርሻው ባለቤት ያከብሩታል
ብሎ ያሰበውን ተወዳጅ ልጁን ላከ። ነገር ግን እርሱ እንደገመተው አልሆነም።
ባልተለመደ ሁኔታ ልጁን ከገደሉ የወይን ቦታው የእነርሱ እንደሚሆን ተነጋገሩ።
የስህተት ምክንያታቸው የሚያስገርም ሲሆን በእነርሱ ላይ የሚመጣው ፍርድ
ትክክለኛነት ተረጋገጠ።
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
በዚህ ታሪክ ውስጥ ኢየሱስ እያደረገ የነበረው ነገር የኃይማኖት መሪዎቹ
እርምጃዎች ወዴት እያመሩ እንደሆነ የሚገልጽ አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ነበር። በዚህ
ብርሃን ሲታይ ምሳሌው የፍቅር ማስጠንቀቂያ ነበር። ለመለወጥና ከማይቀረው
ፍርድ ለማምለጥ አልመሸባቸውም ነበር። አንዳንዶች ይናዘዛሉ፣ ይለወጣሉ፣
ኢየሱስንም ይቀበላሉ። ሌሎች ግን ይህን አያደርጉም።
ተግባሮችና ሰማያዊ ውጤቶች ማር. 12:13–27ን ያንብቡ። እዚህ እየሆነ ያለው ነገር ምንድር ነው? ኢየሱስ ምን እውነቶችን አስተማረ?
የኃይማኖት መሪዎች በሮም ገዥ ወይም በሕዝብ ላይ ኢየሱስን የሚከሱበትን
ነገር ለማግኘት እየሞከሩ ነበር። በዚህ ተቃርኖ ውስጥ የተጠቀሙት ግብርን
የመክፈል ጥያቄ ነበር። በዚህ ጊዜና ቦታ ግብርን ለመክፈል ፈቃደኛ አለመሆን
በሮም መንግሥት ላይ እንደማመጽ ተደርጎ ስለሚወሰድ ከባድ ወንጀል ነው።
ኢየሱስ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ ብሎ
መመለሱ በወጥመዳቸው እንዳይያዝ ጠበቀው። ከዚህ በተጨማሪ አማኞች
ለገዦች ስላላቸው ሀላፊነትም መሰረታዊ የሆነ መመሪያ ሰጠ። “በሮም መንግሥት
ጥበቃ ሥር እስካሉ እና ድርጊታቸው ከፍ ካለው ተግባር ጋር የማይጋጭ እስከሆነ
ድረስ፣ ይህ ኃይል እንዲሰጡ የሚጠይቅባቸውን ድጋፍ መስጠት አለባቸው።
ነገር ግን ለአገሪቱ ሕጎች ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መገዛት ቢኖርባቸውም በመጀመሪያ
መታዘዝ ያለባቸው ሁል ጊዜ ለእግዚአብሔር መሆን አለበት።”—Ellen. G.
White, The Desire of Ages, p. 602.
ተከትሎ የሚመጣው ጥያቄ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው። ሰዱቃውያን
አምስቱን የሙሴ መጻሕፍት ብቻ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚቀበሉ የካህናት
ቡድን ናቸው። በሙታን ትንሣኤ አያምኑም ነበር። ለኢየሱስ ያቀርቡለት የነበረው
መግለጫ ምናልባት መላምት ሊሆን ይችላል። ሰባት ወንድማማቾችንና አንዲት
ሴት አካትቷል። እንደ ሙሴ ሕግ፤ የሞተው ሰው ልጅ ካልተካ፣ የቤተሰብ ንብረትን
ለመጠበቅ የሟቹ ወንድም ባሏ የሞተባትን ሴት ያገባና በዚህ የጋብቻ ጥምረት
የሚፈጠሩ ልጆች በሕጋዊ መንገድ የሟቹ ሰው ይሆናሉ። (ዘዳ. 25:5–10).
ለትንሣኤ አስተምህሮ ዋጋ ላለመስጠት በመፈለግ በትንሣኤ ቀን ይህቺ
ሴት ከሰባቱ ወንድማማቾች ለየትኛው ትሆናለች የሚለውን የግብረገብ (የሞራል)
እንቆቅልሽ ጠቆሙ። ኢየሱስ ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል
በመጥቀስ ክርክራቸውን በሁለት ደረጃዎች መከተ። በመጀመሪያ፣ በትንሣኤ ላይ
ያለውን የእግዚአብሔርን ኃይል በማሳየት በሰማይ መጋባት እንደሌለ አመለከተ።
ዘጸአት 3፡1-22ን በመጥቀስ እግዚአብሔር የአብርሃም፣ የይስሃቅና የያዕቆብ አምላክ
መሆኑን በመግለጽ የትንሣኤን አስተምህሮ ተከላክሏል። ኢየሱስ በተዘዋዋሪ
እያመለከተ ያለው እግዚአብሔር የአብርሃም፣ የይስሃቅና የያዕቆብ አምላክ እስከሆነ
ድረስ አሁን ሞተው በመቃብር ያሉት ሞተው እንደማይቀሩና እንደሚነሱ ነው።
የሆነ ሰው “የእግዚአብሔርን ኃይል ያውቃሉን?” ብሎ ቢጠይቅዎ ምን ብለው ይመልሳሉ? ለምን?
ማር. 12:28–34ን ያንብቡ። በወዳጅነት የቀረበው ጸሐፊ የጠየቀው ጥያቄ እንዴት ያለ ጥልቅ ነበር? ኢየሱስ እንዴት ያለ እጥፍ መልስ ነበር የሰጠው?
በማርቆስ ወንጌል ውስጥ እስከዚህ ነጥብ ድረስ ከጥቂቶች በስተቀር
አብዛኞቹ የኃይማኖት መሪዎች ኢየሱስን የሚቃወሙ ናቸው። ይህ ደግሞ ኢየሱስ
የአይሁዳዊነት ልብ በሆነው በቤተ መቅደስ አገልግሎት ላይ አመራሩን በኢየሩሳሌም
ለተጋፈጠበት ሁኔታ በተለየ ሁኔታ በእውነትነት ይሰራል። አንድ ጸሐፊ ሰዎች
በኢየሱስ ላይ ያላቸውን ጠላትነት እየተመለከተ ንትርኮቹን መስማትና የኢየሱስን
መልስ ማድነቅ የነበረውን ቅንነትና ድፍረት ያሳያል። ሰዎች ለኢየሱስ ቢራሩለት
እንኳን ራሳቸውን ችግር ውስጥ ላለማስገባት ዝም ብለው በመቆም የሚሆነውን
መመልከት ይቀል ነበር፤ ነገር ግን ይህ ሰው እንደዚህ አላደረገም።
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ጸሐፊው ከትዕዛዛት ሁሉ የሚበልጠው የትኛው ነው ብሎ በመጠየቅ
የኃይማኖት ልብ የሆነውን ነገር አነሳ። ኢየሱስ ከዘዳግም 6፡4ና 5 ላይ በአይሁዳዊነት
የእምነት ኑዛዜ የሆነውን ‹‹ስማ››ን በመጥቀስ በትህትናና በግልጽነት ምላሽ ሰጠ።
ኢየሱስ ከትዕዛዛት ሁሉ የሚበልጠው እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ
ነፍስህ፣ በሙሉ ሀሳብህ እና በሙሉ ኃይልህ ውደድ የሚለው ነው በማለት
መለሰለት። ይህ ማለት በሁለንተናህ ማለት ነው። ኢየሱስ በድጋሚ ከብሉይ ኪዳን
ዘሌዋውያን 19፡18ን በመጥቀስ ለጸሐፊው ሁለተኛውን እጅግ ወሳኝ የሆነውን
ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚለውን ትዕዛዝ ጨመረለት።
አንዳንዴ ፍቅርን እንዴት ማዘዝ ይቻላል በማለት ሰዎች ይገረማሉ።
በዘዳግም ውስጥ ያለው የትዕዛዙ ባህላዊ አውድ ለማብራራት ይረዳል። ቋንቋው
የመጣው ጥንት በሁለት አካላት መካከል ከሚደረጉ ስምምነቶች ሲሆን
“መውደድ” የሚለው ቃል ስምምነቱ የሚጠይቃቸውን ነገሮች በታማኝነት
በመፈጸም ለመስፈርቶቹ ታማኝ መሆን ማለት ነው። ስለዚህ በሁለት አካላት
መካከል ያለውን ጥልቅ የሆነ ፍቅር ይገልጻል የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ ባያስቀርም
የበለጠውን ትኩረት የሚያደርገው ታማኝነትን በሚያሳዩ ተግባራት ላይ ነው።
ጸሐፊው ተንኮል የሌለበት ስለነበር የኢየሱስን ምላሽ ቀላልነትና ግልጽነት
በመመልከት የተናገረውን ተናገረ። ሌሎች ለማድረግ ፈቃደኛ የማይሆኑትን
ይህ እውነተኛ ጸሐፊ የኢየሱስ ምላሽ ዋጋ ያለው (ትክክለኛ) መሆኑን ማረጋገጡ
በሌሎች የኃይማኖት መሪዎች መካከል ስለፈጠረው ቁጣ ወይም ተስፋ
መቁረጥ ማሰብ ይቻላል። ኢየሱስም ጸሐፊው በታማኝነት ለመለሰው መልስ
ከእግዚአብሔር መንግስት የራቅህ አይደለህም በማለት ማረጋገጫ ሰጠ። የራቅህ
አይደለህም ማለት እዚያ ውስጥ ነህ ማለት አይደለም። ጸሐፊው ያስፈልገው
የነበረው ኢየሱስ ማን እንደሆነ ተረድቶ መከተል ሲሆን ይህም በእምነት ጉዞ ላይ
ተጨማሪ እርምጃ ነበር።
እግዚአብሔርን መውደድን እና ባልንጀራችንን እንደ ራሳችን መውደድን እንዴት
እንማራለን? እነዚህን ትዕዛዛት ለመከተል መስቀል ቁልፍ የሚሆነው ለምንድር ነው?
ኤለን ጂ ኋይት ከጻፈችው የዘመናት ምኞት ከሚል መጽሐፍ
“ለጥፋት የተፈረደበት ሕዝብ፣” “ቤተ መቅደሱ እንደገና ነጻ፣”እና “ተቃርኖ” የሚሉ
ርዕሶችን ከእንግሊዝኛው መጽሐፍ ገጽ 580–609ን ያንብቡ።
“የራሱ ኃይል የፈጠራትን ዛፍ የረገመበት የክርስቶስ ተግባር ለሁሉም ቤተ
ክርስቲያናትና ለሁሉም ክርስቲያኖች ማስጠንቀቂያ ነው። ማንም ቢሆን ሌሎችን
ሳያገለግል የእግዚአብሔርን ሕግ መተግበር አይችልም። ነገር ግን የክርስቶስን መሃሪ
የሆነ እና ራስ ወዳድነት የሌለውን ሕይወት የማይኖሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ራሳቸውን
ምርጥ ክርስቲያኖች አድርገው የሚያስቡ አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔርን ማገልገል
ምን እንደሚያካትት አይረዱም። ራሳቸውን ለማስደሰት ያቅዳሉ ይማራሉም።
የሚያደርጉትን ሁሉ የሚያደርጉት ከራሳቸው አንጻር ብቻ ነው። ለእነርሱ ጊዜ ዋጋ
የሚኖረው ለራሳቸው መሰብሰብ የሚችሉ ከሆነ ብቻ ነው። ይህ በሁሉም የሕይወት
ጉዳዮች ዋናው ዓላማቸው ነው። የሚያገለግሉት ሌሎችን ሳይሆን ራሳቸውን ነው።
እግዚአብሔር ራስ ወዳድነት የሌለው አገልግሎት መሰጠት ባለበት ዓለም እንዲኖሩ
ፈጥሯቸዋል። የእግዚአብሔር እቅድ መሰሎቻቸውን በሚቻልበት መንገድ ሁሉ
እንዲረዱ ነው። ነገር ግን ራስ እጅግ ትልቅ ከመሆኑ የተነሣ ሌላ ምንም ነገር ማየት
አይችሉም። ከሰብአዊነት ጋር ግንኙነት የላቸውም። ስለዚህ ለራሳቸው ብቻ የሚኖሩ
ሰዎች ፍሬ ያለው መስሎ ምንም ፍሬ እንዳልነበረው የበለስ ዛፍ ናቸው። የአምልኮ መልክ
አላቸው፣ ነገር ግን ንስሃ ወይም እምነት የላቸውም። በንግግራቸው የእግዚአብሔርን
ሕግ ይጠብቃሉ፣ ነገር ግን ታዛዥ አይደሉም። ይናገራሉ፣ ግን አያደርጉም። ይህ ከንቱ
ማስመሰል በእግዚአብሔር ዓይኖች ምን ያህል የተጠላ እንደሆነ ክርስቶስ በበለስ
ዛፏ ላይ በተናገረው አረፍተ ነገር አሳይቷል። ግልጽ የሆነ ኃጢአተኛ እግዚአብሔርን
እንደሚያገለግል እየተናገረ ለእርሱ ክብር የሚሆን ፍሬ ከማያፈራ ሰው ይልቅ በደሉ
ያነሰ ነው።”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 584.
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
1. የክርስቶስ ቤተ መቅደሱን ማንጻት በሚሰጠው ትርጉም ላይ ያስቡ። ያ መርህ
አሁን ለእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚሰራው እንዴት ነው? የዚህ ዓይነት ማንጻት
መካሄድ ያለበት እንዴት ነው?
2. በሁሉም ወንጌላት ውስጥ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍትና እንዴት መፈጸም እንዳለባቸው
ኢየሱስ በተደጋጋሚ ጠቅሷል። እነዚህ ነገሮች ለእምነት ሕይወት እንዴት ማዕከላዊ
እንደሆኑ ይህ ምን ይነግረናል? የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን ዝቅ አድርጎ የማየት
ጥረትን ፣ በተለይም ቅዱሳት መጻሕፍት ሰዎች ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ማንነቱ
እና እንዴት እንደሚሰራ የሚገልጹ የሰዎች የግላቸው ሀሳቦች ናቸው የሚለውን
አመለካካት ተግተን መቃወም ያለብን ለምንድር ነው?
3. በቤተ ክርስቲያንና በመንግሥት መካከል ያለው ትክክለኛ መለያ መስመር ያለው
የት ነው? ኢየሱስ በማርቆስ 12፡13-17 ላይ ያስተማረው ትምህርት ይህንን
ውይይት የሚመራው እንዴት ነው?
4. ስለ ትንሣኤ የሚናገሩ ጥቅሶችን ይፈልጉ። ይህ አስተምህሮ ለእምነታችን፣
በተለይም የሙታንን ሁኔታ በተመለከተ እጅግ ማዕከላዊ የሆነበት ምክንያት
ምንድር ነው?