የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

የማርቆስ መጽሐፍ



3ኛ ሩብ ዓመት 2024


ነሐሴ 11 - 17

8ኛ ትምህርት

Aug 17 - 23




ደቀ መዛሙርትን ማስተማር:- ክፍል 2



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ማርቆስ 10፤ ዘፍ. 1:27፤ ዘፍ. 2:24፤ ገላ. 4:1፣ 2፤ ሮሜ. 6:1–11፤ ኢሳ. 11:1–16።


የመታሰቢያ ጥቅስ: “እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” (ማር. 10:45)።

ይህ ሳምንት ኢየሱስ ለመስቀል እየተዘጋጀ ሳለ ደቀ መዛሙርቱን ያስተማራውን ልዩ ክፍል በማጠናቀቅ ማርቆስ ምዕራፍ 10ን ይሸፍናል። ከምዕራፉ ግማሽ ያክሉ ስለ ደቀ መዛሙርቱ የሚናገር ሲሆን ቀሪው ክፍል ከክርስቶስ ጋር ከሚነጋገሩ ሌሎች ሰዎች መነጽር ለደቀ መዝሙርነት አስፈላጊ ስለሆኑ ጉዳዮች የሚናገር ነው። ፈሪሳውያን ወደ እርሱ በመምጣት ስለ ፊቺ ጉዳይ ይከራከራሉ። ወላጆች እንዲባርክላቸው ልጆቻቸውን ወደ እርሱ ያመጣሉ። ሀብታሙ ሰው ስለ ዘላለም ሕይወት ይጠይቃል፣ ዓይነ ሥውሩ ሰው ደግሞ ማየት እንዲችል ይጠይቃል።

የማርቆስ ይህኛው ምዕራፍ ኢየሱስን መከተል ምን ማለት እንደሆነ፣ በተላይም በዚህ ቦታና አሁን ከመኖር ጋር በተገናኘ፡- ስለ ጋብቻ፣ ስለ ልጆች፣ ከሀብታሞች ጋር እንዴት ግንኙነት መፍጠር እንደሚቻል እና እርሱን በመከተል ስለሚገኝ ሽልማትና ስለሚያስከፍለው ዋጋ ጠቃሚ ትምህርቶችን ይይዛል። በዚህ ላይ ተጨማሪ የሆነው ለዚህ ክፍል መደምደሚያ የሚሆን ድጋፍ (ማር. 8፡22-10፡ 52) እና ኢየሱስን መከተል ምን ዋጋ እንደሚያስከፍልና ወዴት እንደሚመራ ውብ የሆነ መግለጫ የሚሰጠው ሁለተኛውን ዓይነ ስውር ማዳኑ ነው (ማር. 10፡46-52፣ ከማርቆስ 8፡22-26 ጋር ያነጻጽሩ)።

በአንድ ላይ እነዚህ ትምህርቶች የኢየሱስን ተከታይ፣ የዛሬ 2000 ዓመታት ገደማ የኖሩትን ደቀ መዛሙርት ወይም በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሚኖሩ ደቀ መዛሙርትንም ቢሆን፣ ከደቀ መዝሙርነት ጋር ስለሚመጡ ግድድሮሾች ያዘጋጃሉ። *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሃሴ 18 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ። የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ

ነሐሴ 12
Aug 18

እግዚአብሔር ለጋብቻ ያለው ዕቅድ


ማርቆስ 10:1–12፤ ዘፍ. 1፡27 እና ዘፍ. 2፡24ን ያንብቡ። ፈሪሳውያን ስለ ፍቺ ባነሱት ጥያቄ ስር የተደበቀው ወጥመድ ምንድር ነው? ኢየሱስ በመለሰው መልስ ኢየሱስ ምን ትምህርቶችን አስተማረ?



በዚህ ንባብ ውስጥ ፈሪሳውያን ሰው ሚስቱን እንዲፈታ ይፈቀዳል ወይ ብለው ኢየሱስን ጠየቁት። በፈሪሳውያን መካከል ሚስትን መፍታት እንደሚፈቀድ ተደርጎ ይታይ ነበር። ጥያቄው በምን መነሻ ነው የሚፈቀደው የሚለው ነው።

የሻማይ ትምህርት ቤት አከራካሪ በሆነ መልኩ እጅግ የሚገድብ ሲሆን ፍቺን የሚፈቅደው ልጅ ካልተወለደ፣ ትዳርን ችላ ከማለት፣ የስሜት ቸልተኝነት ወይም ለትዳር ታማኝ ካለመሆን የተነሳ ብቻ ነው። የሂሌል ትምህርት ቤት የበለጠ ልል ሲሆን የፍቺን ፈቃድ የመስጠት ሂደቱ እጅግ ውስብስብ ቢሆንም በማንኛውም ምክንያት ፍቺን ይፈቅዳል። የፍቺ ፈቃድ የመስጠት ሂደቱ ውስብስብነት ነገሮች በጥድፊያ እንዳይፈጸሙ ይረዳ ነበር።

ስለዚህ፣ ፍቺ የተፈቀደ እስከሆነ ድረስ ኢየሱስን አጠቃላይ የሆነ ጥያቄ መጠየቃቸው ትንሽ እንግዳ ነገር ይመስላል። በዚህ ጥያቄ ሥር ተደብቆ የነበረው ተንኮል አሁን ኢየሱስ በነበረበት ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ በነበረው አውራጃ ገዥ ከነበረው ከሄሮድስ አንትጳስ ጋር ኢየሱስ ችግር ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ነበር።

አንትጳስ ሚስቱን ፈትቶ የወንድሙ ሚስት የነበረችውን ሄሮዲያዳን አግብቶ ነበር። ሄሮድስ የመጥምቁ ዮሐንስ አንገት እንዲሰየፍ ያደረገው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ሕገወጥ ግንኙነት በመፍጠሩ ስለገሰጸው ነበር። (ማቴ. 14:1–12ን ይመልከቱ)።

ኢየሱስ ስለዚህ ጉዳይ ሙሴ ምን አዘዛችሁ በማለት የፈሪሳውያንን ጥያቄ በጥያቄ መለሰ። ፈሪሳውያን መልስ ሲመልሱ የጠቀሱት ዘዳግም 24፡1-4 ላይ ከፍቺ በኋላ እንደገና ስለተፈጸመ አንድ ጉዳይ ነበር። በሙሴ ዘመን እሥራኤላውያን ፍቺን እየፈጸሙ ቆይተዋል። ዘዳግም ምዕራፍ 24 ላይ የተገለጸው የሕግ ጉዳይ ለሴት ጥበቃ ለማድረግ የተቀመጠ ነው። ነገር ግን ይህ ክፍል በኢየሱስ ዘመን በማንኛውም ምክንያት ፍቺን መፈጸምን ቀላል ለማድረግ በሂለል ትምህርት ቤት ተጠምዝዞ ቀርቦ ነበር። ስለዚህ ሴቷን ለመጠበቅ ተብሎ የተሰጠው ሕግ እርሷን መወርወርን ቀላል ለማድረግ ጥቅም ላይ እየዋለ ነበር።

ዘዳግም 24 ላይ ባለው የሕግ ጉዳይ ላይ ከመከራከር ይልቅ እግዚአብሔር ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 እና 2 ላይ ስለ ጋብቻ የሰጠውን የመጀመሪያ ምሳሌ ጠቀሰ።

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ብሎ ነገራቸው (ዘፍ. 1፡:27)፣ ሁለት ግለሰቦችን። ይህን ጉዳይ ዘፍጥረት 2፡24 ላይ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፣ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፣ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ከሚለው እውነት ጋር አዋሃደ። ይህ የአንድነት ጽንሰ ሀሳብ ኢየሱስ የጋብቻ ግንኙነትን ለማጽናት መሰረት ሆነ። እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው አይለየው።

በመካከላችሁ ያሉ ጋብቻዎችን ለማጠንከር የእርስዎ ጉባኤ ምን ማድረግ ይችላል? ጋብቻቸው የፈረሰባቸውን ሰዎች እንዴት ይረዳሉ?

ነሐሴ 13
Aug 19

ኢየሱስና ልጆች


ማር. 10:13–16ን ያንብቡ። ኢየሱስ ልጆችን ወደ እርሱ ላመጡት ምን አደረገላቸው?



በጥንቱ ዓለም ልጆች በከፍተኛ ደረጃ የሚፈለጉ ሆነው ሳለ (በተለይም የወንድ የበላይነት በነበረበት ባህል ወንድ ልጆች)፣ ልጅ መውለድና ልጅነት ቀላል አልነበሩም። በሰለጠነው በአሁኑ ዓለም ያለው የሕክምና ክብካቤ ባልነበረበት እናቶች በወሊድ ጊዜ የሚገጥሙአቸው አደጋዎች፣ አዲስ የተወለዱ ሕጻናት፣ ጨቅላዎችና ልጆች የነበሩባቸው አደጋዎች ከፍ ያሉ ነበሩ። ብዙ ባህሎች እነዚህን ተጋላጭ ግለሰቦች አደጋ ለማስከተል ከሚፈልጉ ኃይሎች ለመከላከል የሚጠቀሙባቸው ባህላዊ ሕክምናዎችና ክታቦች ነበሩአቸው።

ልጆች ቢፈለጉም በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ደረጃ ዝቅተኛ ሲሆን ከባሪያዎች ተርታ እንዲመደቡ የሚያደርግ ነበር (ገላ. 4፡1፣2)። በግሪክና ሮም ዓለም አካለ ስንኩላን ወይም የማይፈለጉ ልጆች ተጋላጭ ነበሩ፣ ወይም ወደ ወንዝ የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ ይወረወሩ ነበር። ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ዋጋ ይሰጣቸዋል፤ አንዳንድ ጊዜ ሴት ሕጻናት በተፈጥሮ ኃይላት መካከል እንዲሞቱ ይተዋሉ። አንዳንድ ጊዜ እነዚህን የተጣሉ ልጆች ሰዎች ‹‹ከሞት ያድኑአቸውና›› ካሳደጉአቸው በኋላ ለባርነት ይሸጡአቸዋል።

ማርቆስ 9 ላይ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ልጆች ስለ መቀበል ኢየሱስ የተናገረውን ደቀ መዛሙርቱ ያስተዋሉ አይመስሉም (ማር. 9፡33-37)።

ኢየሱስ እንዲባርካቸው ያመጡአቸውን ሰዎች ገሰጹአቸው። ይህንን ያደረጉበት ምክንያት ምናልባት ለእንደዚህ ዓይነቱ ቀላል ለሆነ ሥራ ጊዜ እንደሌላቸው ስላሰቡ ሊሆን ይችላል።

ድርጊታቸው ስህተት ነበር። ኢየሱስ ተቆጣቸው። በመላው የማርቆስ መጽሐፍ ውስጥ ኢየሱስ ለሕዝቡ የሚሰጣቸው አንዳንድ አስደናቂ ምለሾች የነበሩት ሲሆን ከሰጣቸው ጠንካራ ምላሾች መካከል አንዱ ልጆች ወደ እርሱ እንዳይመጡ ይከለክሉ ለነበሩ ሰዎች መሆኑ አስተማሪ ነው።

ደቀ መዛሙርቱ በልጆች መንገድ ላይ እንዳይቆሙ አጠንክሮ ተናገረ።

ለምን? ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት ለእነርሱ ስለሆነች ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት በልጆች አመለካከትና እይታ መቀበል ስላለባቸው ነው። ይህ ምናልባት የሚያመለክተው ቀላልና ጥርጣሬ የሌለውን በእግዚአብሔር መታመን ሊሆን ይችላል።

“ክርስቶስን የማይመስል ባህሪያችሁ ኢየሱስን በተሳሳተ መልክ አይወክል።

ርኅራኄ በሌለውና ጭካኔ ባለበት አቀራረባችሁ ልጆችን ከክርስቶስ አታርቁ። እናንተ በዚያ ቦታ ካላችሁ ሰማይ የማያስደስት ቦታ እንደሚሆን እንዲሰማቸው የሚያደርግ ጉዳይ አትስጡአቸው። ስለ ኃይማኖት ስትናገሩ ልጆች ሊያታልሉ እንደማይችሉ ነገር አድርጋችሁ አትናገሩ፣ ወይም በልጅነታቸው ክርስቶስን እንዲቀበሉ እንደማይጠበቅባቸው አድርጋችሁ አትናገሩ። የክርስቶስ ኃይማኖት ደስታ የራቀው ስለሆነ ወደ አዳኙ ሲመጡ ሕይወትን ደስተኛ የሚያደርጉ ነገሮችን ሁሉ መተው እንዳለባቸው አድርጋችሁ የተሳሳተ እይታ አትስጡአቸው።”—El- len G. White, The Ministry of Healing, pp. 43, 44. በዙሪያዎ ላሉ ልጆች ኢየሱስን በተሻለ ሁኔታ መግለጥ የሚችሉት እንዴት ነው?

ነሐሴ 14
Aug 20

ከሁሉ የተሻለ ሀብትን ሥራ ላይ


ማዋል (ሀብት ማፍሰስ) ማር. 10:17–31ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ለማንም ቢሆን፣ ለሀብታም ወይም ለድሃ፣ ስለ እምነትና ስለ ደቀ መዝሙርነት ዋጋ ምን ወሳኝ ትምህርቶች ተገልጠዋል?



የሰውዬው አቀራረብ ለኢየሱስ ያለውን ልባዊ ፍላጎትና አክብሮት ያሳያል።

ሩጦ በፊቱ በመንበርከክ ለእያንዳንዱ ነፍስ መዳረሻ ማዕከላዊ የሆነ ጥያቄ ጠየቀ። ጥያቄው የዘላለም ሕይወትን ለመውረስ ምን ላድርግ? የሚል ነበር። ኢየሱስ አስርቱ ትዕዛዛት ከተጻፉባቸው ጽላቶች በሁለተኛው ላይ ያሉትን በመጥቀስ መልስ መለሰለት። በድጋሚ ሰውዬው እነዚህን ነገሮች ከልጅነቱ ጀምሮ እንደጠበቃቸው በመናገር ስለ ራሱ ያለውን ከፍ ያለ አመለካከት አሳየ።

ከአራቱ ወንጌላት መካከል የማርቆስ ወንጌል ብቻ ኢየሱስ ሰውዬውን መውደዱን ገልጾአል። ሰውዬው ስለ ራሱ ስላለው ከፍ ያለ አስተሳሰብ የሆነ የሚወደድ ነገር አለው። ነገር ግን ኢየሱስ ሰውዬው የሚናገረው ከልቡ መሆኑን ለመፈተን ያለውን ሁሉ ሽጦ እንዲከተለው ጠየቀው። ግለሰቡ ብዙ ንብረት ስለነበረው አዝኖ ሄደ።

በርግጥ ትዕዛዛቱን እየጠበቀ አልነበረም። በሕይወቱ የሆነ ነገርን ከእግዚአብሔር በላይ በማስቀመጥ የመጀመሪያውን ትዕዛዝ ጥሷል። ሀብቱ ጣዖቱ ነበር።

ከዚያ በኋላ ሀብት ምን ያህል አሳሳች እንደሆነ እና ሀብታም ሰው ሰማይ ከሚገባ እንደ ግመል ያለ ትልቅ እንስሳ በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ እንደሚቀል አስረዳ።

ደቀ መዛሙርት በኢየሱስ ንግግር በመደነቅ ማን ይድናል በማለት አግራሞታቸውን ገለጹ። ኢየሱስ በማርቆስ 10፡27 ላይ የታሪኩን የመጨረሻ አረፍተ ነገር እንዲህ በማለት ተናገረ፡- “ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አይቻልም፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ይቻላል። በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና።”

ማርቆስ 10፡27 ታሪኩን ለመጨረስ ውብ የሆነ ቦታ ይመስላል። በራስህ መንገድ ሰማይ መድረስ አትችልም፣ ለመዳን የእግዚአብሔር ጸጋ ያስፈልግሃል። የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ

ነገር ግን ጴጥሮስ እርሱና ጓደኞቹ ኢየሱስን ለመከተል ሁሉን ነገር እንደተዉ ተናገረ። ኢየሱስ እኔን ለመከተል ብላችሁ የተዋችሁት ማንኛውም ነገር አሁንም ሆነ ‹‹በሚመጣው ዘመን›› ከምትቀበሉት ነገር ጋር ሲነጻጸር ምንም አይደለም ብሎ መለሰለት።

ነጥቡ ይህ ነው፡- ለሰብአዊ በደል መፍትሄን የሚሰጥ የክርስቶሰስ ሞት ነው። ከዚያም ትዕዛዛቱን እንዲታዘዙ ኃይል የሚሰጡት የክርስቶስ ጸጋና የትንሣኤ ሕይወቱ ናቸው።

ሮሜ 6:1–11ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች እኛን በማጽደቅም ሆነ ለእርሱ አዲስ ሕዝብ በማድረግ በሕይወታችን የእግዚአብሔርን ጸጋ እውነታዎች የሚገልጡት እንዴት ነው?

ነሐሴ 15
Aug 21

እኔ የምጠጣውን ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?


ማር. 10:32–45ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ደቀ መዛሙርቱ የኢየሱስን ተልዕኮ በተመለከተ ብቻ ሳይሆን እርሱን መከተል ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቀጣይነት የነበራቸውን አለማስተዋል የሚገልጡት እንዴት ነው?



ኢየሱስ በሚያደርጋቸው ጉዞዎቹ ወደ ኢየሩሳሌም እየቀረበ በመሄድ ላይ ሲሆን እዚያ ምን እንደሚከሰት ለደቀ መዛሙርቱ ገለጠላቸው። ሁኔታው የሚያምኑት ወይም መስማት የሚፈልጉት ነገር አይደለም። ኢየሱስ ስለ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ነቅሶ መናገሩ የሚያስገርም ነው። ነገር ግን መስማት የማትፈልጉት ነገር ሲሆን አለመስማት እጅግ ቀላል ነው።

ያዕቆብና ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ የግል ጥያቄ ይዘው በመጡ ጊዜ ያደረጉት ይህን ነበር። ኢየሱስ ስለዚህ ጉዳይ ነጥቦችን እያነሳ በትክክል ሲጠይቃቸው እነርሱም እርሱ በክብሩ ሲገለጥ በቀኙና በግራው መቀመጥ እንደሚፈልጉ ነገሩት። ጥያቄያቸውን ስልጣን ከመፈለግ የመነጨ የራስ ወዳድነት ጥያቄ ነው ብሎ መተቸት ቀላል ነው። ነገር ግን እነዚህ ሁለት ሰዎች ለኢየሱስ አገልግሎት ራሳቸውን ቀድሰው የሰጡ ስለሆኑ ምናልባት ፍላጎቶቻቸው ሙሉ በሙሉ የራስ ወዳድነት ባህሪይ ያለው ላይሆን ይችላል።

ኢየሱስ እየጠየቁ ስላሉት ነገር ያላቸው መረዳት የበለጠ ጥልቅ እንዲሆንላቸው ለማድረግ ይፈልጋል። እርሱ የሚጠጣትን ጽዋ መጠጣት ወይም እርሱ የሚጠመቃትን ጥምቀት መጠመቅ እንደሚችሉ ጠየቃቸው። የእርሱ ጽዋ በጌትሰማኔ በመስቀል ላይ የሚደርስበት የስቃይ ጽዋ ሲሆን (ከማርቆስ 14፡36 ጋር ያነጻጽሩ) እርሱ የሚጠመቃት ጥምቀት ደግሞ ሞቱና መቀበሩ ይሆናሉ (ማር. 15፡ 33-47)፤ እዚያ ያሉ ክስተቶች በማርቆስ ምዕራፍ 1 ላይ ከተመዘገበው ጥምቀቱ ጋር ይመሳሰላሉ።

ነገር ግን ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ነገር አልተመለከቱም። ብዙም ትኩረት ሳይሰጡ እንደሚችሉ ተናገሩ። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ የእርሱን ጽዋ እንደሚጠጡና የእርሱን ጥምቀት እንደሚጠመቁ ተነበየ። የሰማዕትነትን ሞት ለመሞት ከሐዋርያት መካከል ያዕቆብ የመጀመሪያው ነበር (የሐዋ. 12፡2)። ዮሐንስ ከሐዋርያት ሁሉ ረዥም ዕድሜ የኖረና ወደ ፍጥሞ ደሴት የተሰደደ ነበር (ራዕይ 1፡9)። ነገር ግን የክብር ቦታዎች ለማን እንደሚሰጡ የሚወስነው እግዚአብሔር እንደሆነ ኢየሱስ አመለከተ። ለኢየሱስ መልስ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ምላሽ የሰጡት እንዴት ነበር? መልሳቸው ጥሩ አልነበረም። በማርቆስ 10፡41 ላይ የደቀ መዛሙርቱን ስሜት ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለው የግሪክ አጋናክቴዎ የተባለው ቃል በማርቆስ 10፡ 14 ላይ ሕጻናት ወደ እርሱ እንዳይመጡ ሲከለክሉ ኢየሱስ የተቆጣበትን ሁኔታ ለመግለጽ ጥቅም ላይ ከዋለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹መቆጣት፣ በጣም መቆጣት›› የሚል ነው። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ እጅግ ጥልቅ ማሰብን ከሚሹ ትምህርቶች አንዱ የሆነውን ትምህርት ለመስጠት ቡድኑን ጠራ። የአህዛብ ገዦች ለግል ጥቅማቸው ኃይል እንደሚጠቀሙ አመለከተ። ነገር ግን በእግዚአብሔር መንግሥት ኃይል ሁልጊዜ ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ሌሎችን ከፍ ለማድረግና ለመባረክ ነው። ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር መንግሥት ንጉሥ ሆኖ መንገዱን ይመራል። እንዴት? ተከታዮቹ ለመስማት በፈለጉት መንገድ ሳይሆን የራሱን ሕይወት ቤዛ አድርጎ በመስጠት ነው።

እንደ ክርስቲያን ለሌሎች “ባሪያ” መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ይህንን መርህ በየዕለቱ ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት መግለጥ የሚችሉት እንዴት ነው? የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ

ነሐሴ 16
Aug 22

‘ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?’


ማር. 10:46–52ን ያንብ። በርጤሜዎስ ኢየሱስ በዚያ ማለፉን ሲሰማ ለጉዳዩ ምለሽ የሰጠው እንዴት ነበር?



በማርቆስ ወንጌል ውስጥ እስከዚህ ነጥብ ድረስ፣ ከጥቂቶች በቀር፣ ኢየሱስ ስለ ተአምራቶቹና ስለ ማንነቱ ሰዎች ዝም እንዲሉ ሲነግራቸው ነበር። በዚህ ዘገባ ውስጥ ከኢያሪኮ እየወጣ ሳለ በመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ እየለመነ የነበረ ዓይነ ስውር ሰው በዚያ እያለፈ ያለው የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በመስማቱ “ ‘የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ ማረኝ!” ብሎ መጮህ ጀመረ (ማር. 10:47)። መጽሐፉ ካለው የመገለጥ/የምስጢር ሀሳብ ጋር በመስማማት ሕዝቡ ይጮህ የነበረውን ለማኝ ጸጥ ለማድረግ አላስፈላጊ ጥረት ያደርጉ የነበሩ ሰዎችን ሚና ወሰዱ።

ነገር ግን በርጤሜዎስ በዚህ ሳይደናቀፍ ከመጀመሪያው የበለጠ ድምጹን ከፍ አድርጎ “የዳዊት ልጅ ማረኝ!” ብሎ ጮኸ (ማር. 10:48)። ቃላቶቹ በኢየሱስ መሲህነት ላይ የነበረው እምነት ኑዛዜና እርሱ ሊያድነው እንደሚችል ያለው መተማመን መግለጫ ነበሩ። በኢየሱስ ዘመን “የዳዊት ልጅ” የሚለው ማዕረግ ከእርሱ ጋር የተገናኙ ሁለት ጽንሰ ሀሳቦች አሉት። እነርሱም ንጉሥን ወደ እሥራኤል ዙፋን መመለስ (ከኤሳ. 11፤ ኤር. 23፡5፣ 6፤ ኤር. 33፡15፤ ሕዝ. 37፡24፤ ሚኪ. 5፡2-4፤ ዘካ. 6፡12 ጋር ያነጻጽሩ) እና ይህ ሰው ፈዋሽና ከክፉ መንፈስ ነጻ የሚያወጣ ይሆናል።

ኢየሱስ ቆሞ ዓይነ ስውሩን ሰው እንዲጠሩት ነገራቸው። ዓይነ ስውሩ ወደ ኢየሱስ እየመጣ ሳለ ልብሱን ከላዩ ወረወረ። በኢየሱስ ዘመን ዓይነ ስውራን ከባልቴቶችና ወላጅ አልባ ልጆች ጋር በሕብረተሰቡ ውስጥ የመጨረሻውን ዝቅተኛ ደረጃ የያዙ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ለራሳቸው በቂ የሆነ መተዳደሪያ የሌላቸውና ግልጽ በሆነ አደጋ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ናቸው። ልብሱ ለሰውዬው ዋስትናው ነበር። ያንን መተው ማለት ኢየሱስ እንደሚያድነው እምነት ነበረው ማለት ነው።

ኢየሱስ ተስፋ አያስቆርጥም። በወንጌላት ውስጥ ከእርሱ እርዳታ ፈልጎ የሚመጣ ሁሉ ሁልጊዜም ይቀበላል። ኢየሱስ ማርቆስ 10፡36 ላይ ያዕቆብንና ዮሐንስን የጠየቀውን ያንኑ ጥያቄ ጠየቀው፡- “ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?’ ” (ማር. 10:51)።

አይነ ስውሩ ያለ አንዳች ማመንታት ማየት እንደሚፈልግ ገለጸ፤ ኢየሱስም ወዲያውኑ እይታውን መለሰለት። ዓይነ ስውሩ በመንገድ ላይ ኢየሱስን ተከተለው።

ይህ ታሪክ በማርቆስ 8፡22-26 ከተገለጸው ሌላ ዓይነ ስውርን ከማዳን ታሪክ ጋር በመጨረሻ ላይ ስለተቀመጠ በማርቆስ ውስጥ የደቀ መዝሙርነት ክፍል መዝጊያ ነው። ሁለቱ ታሪኮች ደቀ መዝሙርነት በሁለት ዓይኖች ዓለምን ስለማየት የሚገልጽ መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ በመጀመሪያ በደንብ ባያዩም፣ ሁልጊዜ ኢየሱስን እርሱ በሚመራው መንገድ መከተልን የሚያሳዩ ናቸው።

አንዳንድ ጊዜ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ፣ ማረኝ!” ብላችሁ በምን መንገዶች ነው የጮኻችሁት? ስትጮኹ ምን ሆነ? ከዚህ ልምምድ ምን ተማራችሁ?

ነሐሴ 17
Aug 23


ተጨማሪ ሀሳብ


የዘመናት ምኞት ከሚል የኤለን ጂ ኋይት መጽሐፍ “ልጆችን መባረክ” እና “‘አንድ ነገር ይጎልሃል” የሚሉ ርዕሶችን ገጽ 511–523 ላይ ያንብቡ።

“ኢየሱስ ሁልጊዜ የልጆች አፍቃሪ ነበር። የልጅነት ርኅራኄያቸውን እና ግልጽና በተጽእኖ ሥር ያልወደቀውን ፍቅራቸውን ተቀበለ። ከንጹህ ከናፍራቸው ይወጣ የነበረው በምስጋና የተሞላ ውዳሴ በጆሮቹ ሙዚቃ የነበረ ሲሆን ተንኮለኛና ግብዝ በሆኑ ሰዎች ግንኙነት ጫና ሥር ሲወድቅ መንፈሱን ያድሱለት ነበር። አዳኙ በሄደበት ሁሉ ጉዳት የማያስከትለው ፊቱ እና ጨዋና ቸር ባህርዩ የልጆችን ፍቅርና አመኔታ አተረፈለት።”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 511.

“እንደ ወጣቱ ገዥ ከፍተኛ መታመንን በሚጠይቅ ቦታ ለተቀመጡ እና ብዙ ሀብት ላላቸው ሰዎች ክርስቶስን ለመከተል ሁሉን መተው እጅግ ትልቅ መስዋዕትነትን መክፈል ሊመስላቸው ይችላል። ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ ለሚሆኑ ሁሉ ይህ የባህሪይ ደንብ ነው። ከመታዘዝ ያነሰ ምንም ነገር ተቀባይነት የለውም።

የክርስቶስ ትምህርቶች ዋናው ነጥብ ራስን አሳልፎ መስጠት ነው። ሰውን ለማዳን፣ ተቀባይነት ካገኙ፣ መላ ማንነትን አጋንንታዊ ባህሪይ እንዲላባስ የሚያደርጉ ነገሮችን ከሕይወቱ ከመቁረጥ ውጭ ሌላ መንገድ ስለሌለ ይህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ሥልጣን ያለው በሚመስል ቋንቋ ቀርቧል፣ ታዟልም።”—The Desire of Ages, p. 523. የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ


የመወያያ ጥያቄዎች




1. ልጆችና ወጣቶች ከክርስቶስ ጋር እና ከቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ጋር ግንኙነታቸውን ጠብቀው እንዲያቆዩ እርስዎ በምን መንገዶች ሊረዱ ይችላሉ? ይህን ማድረጋችን በጣም አስፈለጊ የሚሆነው ለምንድር ነው?

2. አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ስለ ገንዘብ ግድ እንደሌላቸው ሲናገሩ እንሰማለን። ይህ እውነት አይደለም። ሁሉም ሰው ስለ ገንዘብ ግድ ይለዋል፣ ይህ ደግሞ ስህተት አይደለም። ታዲያ ገንዘብን በተመለከተ ችግሩ እምኑ ላይ ነው? ታማኝ ክርስቲያኖች ሀብታም ቢሆኑ ድሃ፣ ከገንዘብ ጋር ባላቸው ግንኙነት መጠንቀቅ ያለባቸው ለምንድር ነው?

3. ኢየሱስ “ምን እንዳደርግልህ ትሻለህ?” ብሎ ቢጠይቅዎ እንዴት ይመልሳሉ?

4. ማርቆስ 10፡43-45 ላይ ባሉ የኢየሱስ ቃላት ላይ አብልጠው ትኩረት ያድርጉ። እንደዚህ መኖር ማለት ምን ማለት ነው? ከመገልገል ይልቅ ማገልገልን መማር የምንችለው እንዴት ነው? እንዴት እንደምንኖርና ከሌሎች ጋር የምንፈጥረውን ግንኙነት በተመለከተ ይህ ምን ይላል?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL