የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ማር8:22–38;፤ማቴ. 20:29–34፤ ዮሐ. 12:25፤ ማር. 9:1–50፤ ሚልክ. 4:5፣ 6፤ ሉቃስ 9:30, 31።
የመታሰቢያ ጥቅስ:- “ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ
እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ
መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።” ማርቆስ 8:34)።
የማርቆስ ወንጌል የመጀመሪያው አጋማሽ የሚያተኩረው በኢየሱስ ማንነት
ላይ ነው። ኃይለኛ ትምህርቱና ተዓምራቶቹ ተመሳሳይ አቅጣጫን፣ እርሱ
መሲህ መሆኑን ያመለክታሉ። በትረካው ወሳኝ መታጠፊያ ላይ እርሱን
ማን ብለው እንደሚያምኑ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ይጠይቃቸዋል። ለጥያቄው
ጴጥሮስ ግልጽ የሆነ መልስ ይሰጥና ኢየሱስ ወዲያውኑ እንደ መሲህ እግሮቹ
ወዴት እያመሩ እንደሆነ፣ እንደምናውቀው ወደ መስቀል እያመሩ መሆናቸውን፣
ማብራራት ይጀምራል።
ከማርቆስ ምዕራፍ 8 የመጨረሻ ክፍል ጀምሮ እስከ ማርቆስ ምዕራፍ 10
ድረስ ደቀ መዛሙርቱን ስለ ጉዞው በማስተማር ላይ ትኩረት አድርጓል። በእነዚህ
ምዕራፎች ስለ መስቀሉ ትንበያዎችን ይሰጣል። እነዚህን ትንበያዎች በደቀ
መዝሙርነት ላይ የሚሰጥ ልዩ ትምህርት ይከተላል። እነዚህ ኃይለኛ ትምህርቶች
ለዛሬም የሚሆኑ ናቸው።
የሁለተኛው ወንጌል ይህኛው ክፍል ሁለት የተለያዩ ዓይነ ስውራንን
በመፈወስ ተለይቶ የሚታወቅ ሲሆን አንደኛው በማርቆስ ምዕራፍ 8 መሀል
ላይ ሲገኝ ሌላኛው ደግሞ ማርቆስ ምዕራፍ 10 መጨረሻ ላይ ይገኛል። እነዚህ
የተዓምራት “ድጋፎች” ስለ ኢየሱስ ማንነትና ወዴት ይሄድ እንደነበር በተመለከተ
ደቀ መዝሙርነት እንዴት መንፈሳዊ መረዳትን እንደሚያካትት ትዕይንታዊ በሆነ
ሁኔታ ያሳያሉ። የእርሱ ትምህርቶች የዛሬ 2000 ዓመታት ገደማ ደቀ መዛሙርቱን
እንደተገዳደሩ ሁሉ የዛሬዎቹ ደቀ መዛሙርትም ኢየሱስን መከተል ከሚያስከፍለው
ጥልቅ ዋጋና ከሚያስገኘው ጥቅም ጋር መጋፈጣቸውን ይቀጥላሉ።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሃሴ 11 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ማርቆስ 8:22–30ን ያንብቡ። ኢየሱስ ዓይነ ስውሩን ሰው ለማዳን ሁለት ጊዜ መንካት ለምን አስፈለገው? ከዚህ መግለጫ ምን ትምህርት ይገኛል?
ወንጌላት ኢየሱስ ስለ ፈወሳቸው በርካታ ዓይነ ስውራን ዘገባ ያቀርባሉ።
በማርቆስ ምዕራፍ 8 ላይ ከተጠቀሰው ዓይነ ስውር ሌላ በማርቆስ 10፡ 46-52
ላይ ዓይነ ስውሩ በርጤሜዎስ ስለ መፈወሱ ዘገባ ቀርቧል። ማቴዎስ ሁለት ዓይነ
ስውራንን የጠቀሰ ሲሆን (ማቴ. 20፡29-34) ዮሐንስ ምዕራፍ 9 ከመወለዱ ጀምሮ
እውር የነበረውንና በሰሊሆም መጠመቂያ የታጠበውን ዓይነ ስውር ኢየሱስ
የመፈወሱን ታሪክ ይነግራል።
ነገር ግን በማርቆስ ምዕራፍ 8 ላይ ያለው ይህ ታሪክ የተለየ ነው። ታሪኩ
የሚገኘው በማርቆስ ውስጥ ብቻ ሲሆን ኢየሱስ ፍጹም የሆነ ፈውስን ለማምጣት
ሁለት ተግባሮችን መፈጸም ያስፈለገው ብቸኛው ተዓምር ነው። እንደ ታሪኩ አካል
ሆኖ ኢየሱስ የሰውዬውን እጅ ይዞ ከመንደር ወደ ውጭ የመምራቱ ጉዳይ ልብ
የሚነካ ዝርዝር ነው። ሰውዬው ስለነበረበት የአካል ጉድለት ምን ያህል ርኅራኄ
እንደተሰማው ሊሰማን ይችላል።
ነገር ግን ሁለት ጊዜ መንካት ለምን አስፈለገ? ይህ ታሪክ ሁለት ድርጊቶችን
ያካተተ ብቸኛው ታሪክ እንደመሆኑ ይህ የሆነበት ምክንያት ኢየሱስ ኃይል
ስላልነበረው (የኃይል ማነስ ስለገጠመው) አይደለም። ከዚህ ይልቅ አንዳንድ ጊዜ
መንፈሳዊ መረዳትን መግለጥ እንዴት ጊዜ እንደሚወስድ ለማሳየት የተተወነ ምሳሌ
ሊሆን ይችላል። ይህ ትርጉም በዚህኛው የማርቆስ መጽሐፍ ክፍል በቀረበው ሥነ-
ጽሁፋዊ አቀማመጥ የተረጋገጠ ሲሆን ሊመጣ ስላለው ሞቱና ትንሣኤው ደቀ
መዛሙርቱን ባሰለጠነበት መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ዓይነ ስውሩን ሰው የፈወሰበት
ታሪክ ይህንን ያመለክታል። የዓይን ዕይታን መመለስ ግልጽ የሆነ መረዳት ያለበትን
ደቀ መዝሙርነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው።
መምህራን ጥያቄ መጠየቅ ይወዳሉ። ጥያቄዎች የተማሪውን ግንዛቤ
ለመክፈት የሚረዱ ቁልፍ ናቸው። በማርቆስ ምዕራፍ 8 ላይ ባለው ንባብ
ውስጥ መጽሐፉ አቅጣጫ የሚቀይርበት ቦታ ደርሷል። ይህንን አባባል ሶስት
ባህሪያት ያረጋግጣሉ። በመጀመሪያ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ስለ እርሱ ማንነት
ይጠይቃቸዋል። ይህ ነገር ከዚህ በፊት አድርጎት የማያውቀው ነገር ነው። ሁለተኛ፣
ጴጥሮስ ኢየሱስ መሲህ መሆኑን የተናገረ በአጋንንት ያልተያዘ የመጀመሪያው ሰው
ነው። ሶስተኛ፣ ኢየሱስ ማን እንደሆነ የተገለጠበትን ይህንን መገለጥ ተከትሎ
ወዲያውኑ ወዴት እየሄደ እንደሆነ (ወደ መስቀል እየሄደ መሆኑን) ማስረዳት ጀመረ።
ኢየሱስ እርሱ መሲህ መሆኑን ለማንም እንዳይነግሩ ለደቀ መዛሙርቱ
ለምን ነገራቸው? ለሚያቋቁመው የእግዚአብሔር መንግሥት ተቃራኒ ስለሚሆን
ይመስላል። ነገር ግን በኢየሱስ ዘመን “መሲህ” የሮም አገዛዝን የመገርሰስ ፖለቲካዊ
አንደምታ ነበረው። ኢየሱስ የዚያ ዓይነት መሲህ ለመሆን አልመጣም። የእርሱን
ማንነት እንዳይገልጹ የተነገረው ከዚህ የተነሣ ነው።
አንዳንድ ነገሮች እውነት ቢሆኑም መነገር የሌለባቸው ጊዜያቶች ስለመኖራቸው ይህ
ታሪክ ምን ያስተምረናል?
ማርቆስ 8:31–38ን ያንብቡ። ክርስቶስን መከተል ስለሚያስከፍለው ዋጋ በዚህ ቦታ ኢየሱስ ምን ያስተምረናል?
ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ባላቸው ግንኙነት ወሳኝ እጥፋት ላይ
ደርሰዋል። አሁን እርሱ መሲህ መሆኑን አውቀዋል። ይህን ነገር የማርቆስ መጽሐፍ
አንባቢ ከመጽሐፉ ጅምር ላይ አውቋል (ማርቆስ 1፡1)፣ ከዚህ የተነሣ አንዳንድ ጊዜ
የማይረቡ ስህተቶችን ይፈጽሙ ከነበሩ ደቀ መዛሙርት ይልቅ የተሻለ ጥቅም
አግኝቷል።
ኢየሱስ መጀመሪያ ደቀ መዛሙርትን በጠራ ጊዜ ሰው አጥማጅ
አደርጋችኋለሁ ብሏቸዋል (ማር. 1፡7)። ስለ ችግር አልተናገረም። ነገር ግን አሁን
ማን እንደሆነ በትክክል ስላወቁ የተልዕኮውን ግብ--ብዙ መከራ እንደሚቀበል፣
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ተቀባይነት እንደሚያጣና እንደሚገደል፣ ከዚያም በሶስተኛው ቀን ከሙታን
እንደሚነሳ--ይገልጥላቸዋል።
ይህ አስደንጋጭ ዜና ነው። ኢየሱስ መሲህ መሆኑን የመሰከረው ጴጥሮስ
ወደ አንድ ጥግ ወስዶት ስለ መከራው በመናገሩ ገሰጸው። ይህ ሁሉ ቀጥተኛ
ባልሆነ ንግግር የተነገረ ሲሆን አሁን የወንጌል ጸሐፊው ኢየሱስ የተናገራቸውን
ቃላት ይዘግባል። ጴጥሮስ እነዚህን ቃላት ሲሰማ ቃላቱ አቁስለውት መሆን
አለባቸው። ጴጥሮስን ሰይጣን ብሎ በመጥራት ከመንገዱ ዞር እንዲልለት
ነገረው። ይህን ያለበት ምክንያት የዚህ ዓይነት ሀሳብ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር
የማይስማማ ስለሆነ ነበር።
“ኢየሱስን ከፊቱ እየጠበቀው በነበረው ታላቅ ፈተና የጴጥሮስ ቃላት
እርዳታና ማጽናኛ የሚሰጡ አልነበሩም። ለጠፋው ዓለም እግዚአብሔር ካለው
የጸጋ ዓላማ ጋር ወይም ኢየሱስ በራሱ ምሳሌ ሊያስተምር ከመጣው ራስን
መስዋዕት ከማድረግ ትምህርት ጋር የሚጣጣሙ አልነበሩም።”—Ellen G.
White, The Desire of Ages, p. 415.
የኢየሱስ ተከታዮች ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ ግብ እንዲኖራቸው--መስቀሉን
ተሸክመው እንዲከተሉት-- ተጠርተዋል። ስቅለት ሮማውያን ይፈጽሙት የነበረው
እጅግ ጭካኔ የተሞላበት፣ አዋራጅና አስፈሪ የሆነ በሞት የመቅጣት ዘዴ ነበር።
እያንዳንዱ ሰው ከመስቀል ቅጣት ማምለጥ ይፈልግ ነበር። ታዲያ ማንም ቢሆን ራሱን
ለኢየሱስ ቀድሶ የመስጠት ምልክት አድርጎ መስቀልን ለመሸከም ለምን ይፈልጋል?
ኢየሱስ ደቀ መዝሙርነት የሚያስከፍለውን ዋጋ ብቻ ሳይሆን ያለውን
ትልቅ ዋጋም አብራርቷል። በክርስትና እምነት እንቆቅልሽ ሕይወትን ማጣት
የማግኘ መንገድ ይሆናል። ከዚህ በተቃራኒ ዓለምን በሙሉ ማግኘትና የዘላለም
ሕይወትን ማጣት ከንቱ ነው። ጂም ኢሊዮት የተባለ ሚስዮናዊ እ.አ.አ ጥቅምት
28፣ 1949 ዓ.ም ባወጣው ጆርናል ላይ እንደሚከተለው አስቀምጦታል፡-
“ሊያጣው የማይችለውን ነገር ለማግኘት ሊያቆየው የማይችለውን ነገር የሚሰጥ
ሰው ሞኝ አይደለም።”
ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት
ይጠብቃታል።” (ዮሐንስ 12:25)። የእነዚህን ቃላት እውነታ የተለማመዱት
እንዴት ነው?
ማርቆስ 9:1–13ን ያንብቡ። ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር ሆነው አንድ ሌሊት ያዩት ምን ነበር?
ኢየሱስ በማርቆስ 9፡1 ላይ ከእርሱ ጋር ከቆሙት አንዳንዶች የእግዚአብሔር
መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ ሞትን እንደማይቀምሱ የተናገረው
ትንቢት ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ለብቻቸው ወደ ተራራው ይዞ በወጣበት
ጊዜ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተፈጽሟል። በዚያ ቦታ በፊታቸው ወደ ሰማይ
መንግሥት ክብር ተለወጠ። ኤልያስና ሙሴ ከሰማይ መጥተው ከኢየሱስ ጋር
ተነጋገሩ። ሉቃስ በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለመውጣቱ (በግሪክ ጉዞ)
እያወሩ እንደነበር ሉቃስ ጽፏል (ሉቃስ 9፡30፣ 31)። ስለዚህ ይህ የክብር ትዕይንት
እየመጣ ካለው የኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት ጋር ተቆራኝቷል (ከማርቆስ
9፡9 ጋር ያወዳድሩ)። ደቀ መዛሙርቱ እርሱን ተሰቅሎ ሲያዩ ተስፋ ይሰጣል።
ከተራራው ከወረዱ በኋላ፣ በሚቀጥለው ቀን ሶስቱ ደቀ መዛሙርት ስለ ኤሊያስ
አስቀድሞ መምጣት ጠየቁት። ይህ ሀሳብ ከመሲሁ በፊት ኤሊያስ አንደገና
ይገለጣል ከሚለው ግምት ጋር የተቆራኘ ሊሆን ይችላል (ከሚልኪያስ 4፡5፣6
ጋር ያነጻጽሩ)። ኢየሱስ የመጥምቁ ዮሐንስን መምጣት ለመጠቆም ኤልያስማ
አስቀድሞ መጥቷል ብሎ መለሰላቸው። ዮሐንስን እንደገደሉት ኢየሱስም በእነርሱ
እጅ ይገደላል፣ ነገር ግን በሶስተኛው ቀን ይነሳል።
በክብር ከተገለጠበት ሌሊት በኋላ በተራራው ግርጌ የነበረው ትዕይንት
አሳዛኝ ትርምስ የነበረበት ነበር (ማር. 9፡14-29ን ይመልከቱ)። ዘጠኙ ደቀ
መዛሙርት ሊፈውሱት ያልቻሉት በአጋንንት የተያዘ ልጅ ገጥሞአቸው ነበር።
ኢየሱስ ወደዚያ ሲመጣ ሁሉም ሊያገኙት ወደ እርሱ ሮጡ። ታሪኩ አጋንንት
በልጁ ላይ የነበረውን ኃይል ይገልጣል። ኢየሱስ ልጁ በአጋንንት ስለመያዙ
እየጠየቀ ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደ ይመስላል። ‘ቢቻልህ ግን እዘንልን እርዳንም’ ”
(ማር 9:22) በማለት ሳያስብ ለተናገው አባት ጊዜ መውሰዱ ከሚችለው በላይ
ሆኖበታል። ኢየሱስ ወዲያውኑ የጥርጣሬ ንግግሩን ነቅሶ አወጣ።
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
የጌታ ምላሽ በሌላ አገላለጽ ሲቀመጥ እንዲህ የሚል ይሆናል፡- “የሚቻልህ
ከሆነ ስትል ምን ማለትህ ነው?” (ማር. 9:23)። አባትዮው በድንገት በሰማይ
ላይ እንደሚታይ መብረቅ፣ ችግር ያለበት ልጁ ብቻ እንዳልሆነ እና እርሰ ራሱ
የአለማመን ችግር እንዳለበት ተመለከተ። የእርሱ አለማመን ደግሞ ልጁ
እንዳይፈወስ ሊያደርግ ይችላል። ተስፋ የቆረጠው አባት ራሱን በኢየሱስ ምህረት
ሥር በመጣል “ ‘አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው!’ ” በማለት የማይረሱ ቃላትን
ተናገረ (ማር.9:24)። ኢየሱስ ልጁን ፈወሰለት።
“ ‘አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው!” ብለው የጮሁባቸው ሁኔታዎች ካሉ እነዚያ
ምን ዓይነት ሁኔታዎች ነበሩ? ከእነዚያ ልምምዶች ምን መማር ቻሉ?
ማር. 9:30–41ን ያንብቡ። ኢየሱስ ስለ ሞቱና ትንሣኤው ስለተናገረው ሁለተኛ ትንቢት ልዩ የሆነው ነገር ምንድር ነው (ከማርቆስ 8:31 ጋር ያነጻጽሩ)? ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ የተከራከሩት ስለ ምን ነበር? ኢየሱስ ምን ትምህርት (መመሪያ) ሰጣቸው?
ኢየሱስ በመጀመሪያው ትንቢቱ እርሱን አልቀበል ብለው ስለሚገድሉት
ጠቅሷል። በሁለተኛው ትንቢቱ አልፎ እንደሚሰጥ ጠቅሷል። አሳልፎ የሚሰጠው
ማን እንደሆነ በዚህ ሰዓት አልተጠቀሰም፣ ነገር ግን ለይሁዳ ከተሰጠው መለያ
የተነሣ አንባቢው ማን እንደሆነ አስቀድሞ ያውቃል (ማርቆስ 3፡19ን ያንብቡ)።
በድጋሚ ጌታ እንደሚገደልና ከሶስት ቀናት በኋላ እንደሚነሳ አመልክቷል። ነገር
ግን ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያው ትንቢት ላይ ካላቸው ፍላጎት ይልቅ በዚህኛው
ትንቢት ላይ አነስተኛ ፍላጎት ያላቸው ይመስላል። ተቀባይነት የሌላቸው ዜናዎች
ውይይትን አይሰበስቡም።
ማርቆስ 8:27 ላይ ኢየሱስ ከገሊላ ባህር በስተ ሰሜን በፊልጶስ ቄሳርያ
ነበር። ማርቆስ 9፡30 ላይ በገሊላ ሲያልፍ የነበረ ሲሆን ማርቆስ 9፡33 ላይ ደግሞ
ወደ ቅፍርናሆም ገባ። ስለዚህ ከሰሜን ወደ ደቡብ ያደረገውን ጉዞ በዓይነ ህሊና
ማየት አይከብድም። ነገር ግን 12ቱ ደቀ መዛሙርት ወደ ኋላ ቀርተው ሳለ እርሱ
ብቻውን ወደ ቅፍርናሆም ገባ። እቤት እያሉ በመንገድ ስለነበራቸው ውይይት
ጠየቃቸው። ስህተት የሆነ ነገር እያደረጉ እንደተያዙ ልጆች አንዳቸውም ትንፍሽ
ያላሉ ሲሆን ይህ ድርጊታቸው በጥያቄው ምቾት እንዳልተሰማቸው የሚያመለክት
እርግጠኛ ምልክት ነበር። የነበራቸው ውይይት ከእነርሱ ከሁሉ የሚበልጠው ማን
ነው የሚል ነበር። አብዛኞቹ ሰዎች የመቀበል ፈቃደኝነታቸው ትንሽ እንደሆነ ሁሉ
ከሁሉ የሚበልጠው ማን ነው የሚለው ጥያቄም ሁሉም የሚያስብቡት ጥያቄ ነው።
ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ይህንን ሀሳብ ይገለብጠዋል። ኢየሱስ ለችግሩ
መልስ የሰጠው በሁለት ደረጃዎች ነው። በመጀመሪያ፣ የመጀመሪያ ለመሆን (ከሁሉ
ለመብለጥ) ባሪያ (አገልጋይ) መሆን አለብህ የሚለውን ግልጽ አረፍተ ነገር ተናገረ።
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ትርጉሙን በድርጊት አሳየ። የሆነ ልጅ በአቅረቢያቸው ቆሞ
እየሰማ ነበር። ኢየሱስ ልጁን ወስዶ በመካከላቸው አቆመው። ይህ ድርጊት ለልጅ
የሚያስፈራ ድርጊት ነው። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ትዕይንቱን ዘና ለማድረግ ኢየሱስ
ልጁን በክንዱ ተሸከመው። ይህን ልጅ ከተቀበላችሁ እኔንም ትቀበላላችሁ ብሎ
አስተማራቸው። እኔን ከተቀበላችሁ አባቴን ትቀበላላችሁ አላቸው። በዚህ መልክ
ከሁሉ ዝቅተኛ የሆነው ልጅ ከእግዚአብሔር ከራሱ ጋር ተገናኝቷል።
ዮሐንስ በውጭ ስላሉት ጥያቄ ጠየቀና ኢየሱስ የማይቃወሙን ከእኛ ጋር
ናቸው የሚል ወሳኝ ትምህርት አስተማረ። በክርስትና አገልግሎት ውስጥ ያሉትን
መርዳትን፣ በትናንሽ መንገዶች እንኳን ቢሆን፣ ሰማይ ሳያያቸው እንደማያልፋቸው
ጌታ ማረጋገጫ ሰጠ።
ከዓለም አስተሳሰብ በተቃራኒ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትልቅነት ያለው ሀሳብ ምንድር ነው?
እርስዎ ለየትኛው ነው ጥረት እያደረጉ ያሉት?
ማርቆስ 9:42–50ን ያንብቡ። በዚህ ንባብ ውስጥ የኢየሱስን ትምህርት አንድ ላይ የሚያስረው ነገር ምንድር ነው?
በመጀመሪያ፣ ይህ ንባብ ምንም ዓይነት መመሳሰል ወይም ምክንያት
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ሳይኖራቸው አንድ ላይ የተወረወሩ የኢየሱስ ተስፋ ቢስ ትምህርቶች ስብስብ
ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በቅርበት ሲመለከቱአቸው እያንዳንዱ ቀጣይ
ትምህርት ከመጀመሪያው ጋር እውቅ በሆነ አገናኝ ቃል ተገናኝቷል። ንባቡ
ትምህርቱን ደረጃ በደረጃ ወደ ፊት በሚያንቀሳቅሱ ሶስት ዋና ቃላት ዙሪያ
ይሽከረከራል። እነርሱም “የሚያሰናክል (ኃጢአት እንዲሰራ የሚያደርግ)፣”
“እሳት፣” እና “ጨው” ናቸው።
የመጀመሪያው ትምህርት ስለ “ትንንሽ ልጆች” የሚናገር ሲሆን
የሚያመለክተው አዲስ አማኞችን ነው። መምህራንና መሪዎች ለእነዚህ አዲስ
ለተለወጡ ነፍሳት ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር መንግሥት ሀላፊነት
ተሰጥቶአቸዋል። ይህ ደግሞ በብሉይ ኪዳን ዘመን በሕብረተሰቡ ውስጥ ላሉ
ባልቴቶች፣ ወላጅ አልባ ልጆች እና መጻተኞች ከመጠንቀቅ ሥነ-ምግባር ጋር
ተመሳሳይ ነው። ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዲሰናከል (ኃጢአት እንዲሰራ)
ከማድረግ ይልቅ ወደ ጥልቅ በህር ወድቆ መስመጥ ይሻላል በማለት ኢየሱስ በቃለ
አጋኖ ተናግሯል።
“ኃጢአት እንዲሰራ የሚያደርግ” የሚለው ዋና አገናኝ ሀረግ በዚህ ንባብ
ውስጥ ወዳለው ከሁሉ ረዥም ወደሆነው ትምህርት ይመራል። አንባቢው ሁለት
ግራ የሚያጋቡ ጥያቄዎችን ይጋፈጣል። የመጀመሪያው፣ በርግጥ ሰዎች እጃቸውን
ወይም እግራቸውን እንዲቆርጡ ወይም ዓይናቸውን እንዲያወጡ ኢየሱስ
እየጠየቃቸው ነውን? የሚለው ነው። ሁለተኛው፣ ዘላለም ስለሚቃጠለው ገሃነም
እያስተማረ ነውን? የሚለው ነው። የመጀመሪያው ጥያቄ መልስ፣ ኢየሱስ የአካል
ክፍልን ስለመቁረጥ እያስተማረ አይደለም የሚል ነው። በአይሁድ እምነት የአካል
ክፍልን ቆርጦ አካለ ጎዶሎ ማድረግ ተቀባይነት የለውም (ከዘዳግም 14፡1 እና 1ኛ
ነገሥት 18፡27፣28 ጋር ያነጻጽሩ)። ኢየሱስ ቃለ አጋኖ እየተጠቀመ ያለው ትምህርቱ
ትኩረት እንዲያገኝ ነው። እጅን፣ እግርን ወይም ዓይንን ማጣት አሰቃቂ ነገር ከሆነ
ክርስቲያን ኃጢአትን መስራት ምን ያህል ከዚያ የበለጠ መቅሰፍት ይሆን ይሆን!
የሁለተኛው ጥያቄ መልስም አሉታዊ ነው። ኢየሱስ ለዘላለም ስለሚቃጠል
የገሃነም እሳት እያስተማረ አይደለም። እንዴት እናውቃለን? በመጀመሪያ፣ ንባቡ
የተወሰነ አዝናኝ ገጽታ ይዟል። አንድ ዓይን ወይም አንድ እጅ ወይም አንድ እግር
ይዘው ወደ ሰማያዊ ከተማ ስለሚገቡ ሰዎች አስቡ። ከዚያም ሙሉ አካል ይዘው
ወደ ገሃነም ስለሚሄዱ ሰዎች አስቡ።
ከዚህ በተቃራኒ ሊሆን አይችልምን? ጤናማ የሆነ ሰው በገሃነም? ይህ
የሚያስቅ ነገር ነው። እንደዚህ ባለ ጥብቅ ርዕስ ላይ ይህን የመሰላ አስቂኝ ነገር
ሲቀርብ ሰዎች ኢየሱስ መግለጽ የፈለገውን ነገር በቃለ አጋኖ እያሳየ እንደሆነ
እንዲያስቡ ይመራቸዋል። ኃጢአት ከመስራት ይልቅ እጅን፣ እግርን ወይም
ዓይንን ማጣት ስለሚሻል የኃጢአት አሳሳብነት መታወቅ አለበት።
ገሃነም ዘላለማዊ እንዲሆን የሚያደርገው የእሳቱ ዘላለማዊነት ሳይሆን
ውጤቶቹ ዘላለማዊ መሆናቸው ነው። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት
እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን
እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ. 3:16)። የጠፉ ሰዎች ለዘላለም አይቃጠሉም፤ ነገር ግን
ለዘላለም ይጠፋሉ። በእነዚህ ሁለት አባባሎች መካከል በጣም ትልቅ ልዩነት አለ!
የዘመናት ምኞት ከሚለው የኤለን ጂ ኋይት መጽሐፍ
“አገልግሎት” እና “ከሁሉ የሚበልጠው ማን ነው የሚሉ ርዕሶችን ገጽ 426–446
ያንብቡ።
“ከክብር በፊት ውርደት አለ። በሰዎች ፊት ከፍ ያለውን ቦታ ለመያዝ
እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ ያለውን ቦታ የሚይዘውን
ሰራተኛ ሰማይ ይመርጣል። ከሁሉ ይልቅ የሕጻን ባሕሪይ ያለው ደቀ መዝሙር
በእግዚአብሔር ሥራ ከሁሉ ይልቅ ውጤታማ ነው። ራሱን ከፍ ለማድረግ ሳይሆን
ነፍሳትን ለማዳን ከሚሻው ሰው ጋር የሰማይ አካላት መተባበር ይችለሉ።”—El-
len G. White, The Desire of Ages, p. 436.
“ከሌሎች የተሻለ ዕድል እንዲኖረን ባደረጉ ነገሮች ሁሉ--ትምህርትና
ብቃት፣ የከበረ ባህሪይ፣ ክርስቲያናዊ ስልጠና፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ--እንደ
እኛ ላልታደሉ ሰዎች ባለዕዳዎች ነን። አቅማችን በሚፈቅደው መጠን እነርሱን
ማገልገል አለብን። ብርቱ ከሆንን የደካሞችን እጅ መደገፍ አለብን። በሰማይ
የአብን ፊት ሁልጊዜ የሚመለከቱ የክብር መላእክት ትንንሽ ልጆቹን በማገልገል
ይደሰታሉ። በባህሪያቸው ብዙ የሚያስጠሉ ነገሮች ላሏቸው የሚብረከረኩ ነፍሳት
እንዲጠነቀቁ ልዩ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። መላእክት እጅግ በሚፈለጉበት ቦታ፣
ከራሳቸው ጋር የሚዋጉት እጅግ ጠንከራ ጦርነት ካለባቸው እና ዙሪያቸው እጅግ
ተስፋ አስቆራጭ ከሆነባቸው ሰዎች ጋር ሁልጊዜ ይገኛሉ። በዚህ አገልግሎት
የክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ይተባበራሉ።”—P. 440.
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
1. ማርቆስ 8:27–29ን በድጋሚ ያንብቡ። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ
ስለማመንዎ ምን ያህል ጊዜ ለሌሎች ይመሰክራሉ?
2. በተራራው ጫፍ ላይ ከክርስቶስ ጋር ከነበራቸው ልምምድና ከተራራው ሥር
በሜዳው ላይ ለሌሎች ፍላጎቶች በተደረገው አገልግሎት ልምምድ መካከል ያለው
ትክክለኛ ሚዛን ምንድር ነው?
3. በክፍላችሁ በረቡዕ ትምህርት መጨረሻ ስለ ታላቅነት ለተነሳው ጥያቄ በተሰጣው
መልስ ላይ ተወያዩ። ታላቅነትን ዓለም በሚመለከትበትና እግዚአብሔር
በሚመለከትበት መንገድ መካከል ስላለው ልዩነት የእርስዎ ውሳኔ ምንድር ነው? ዓለም ታላቅ እንደሆኑ የሚናገርላቸውና ምናልበትም እግዚአብሔር ታላቅ
ናቸው የማይላቸው አንዳንድ ሰዎች እነማን ናቸው? ከዚህ በተቃራኒ፣ ዓለም
ችላ የሚላቸውና እንዲያውም የሚቀልድባቸው ሆነው እግዚአብሔር ታላቅ
አድርጎ የሚቆጥራቸው እነማን ይሆኑ ይሆን? ይህ ልዩነት ዓለም ለትልቅነት
የሚያስቀምጣቸው መስፈርቶች ምን ያህል የጎበጡና የተጣመሙ እንደሆኑ ምን
ይነግረናል?
4. ኢየሱስ እንደተናገረው ኃጢአትን ከመስራት ይልቅ አንዱ የአካል ክፍል መቆረጥ
እስከሚሻል ድረስ ኃጢአት አሳሳቢ መሆኑን መማር የምንችለው እንዴት ነው?