የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ማር. 7፣ ኢሳ. 29:13፣ ዘጸ. 20:12፣ ማር.8:11–21.
የመታሰቢያ ጥቅስ:- “ ‘ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ
ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል
ምንም የለም።” (ማር. 7:15)።
የዚህ ሳምንት ትምህርት ማርቆስ ምዕራፍ 7 እና ምዕራፍ 8 የመጀመሪያው
አጋማሽ ይሆናል። በማርቆስ መጽሐፍ ምዕረራፍ 7 ጅምር ላይ ኢየሱስ
ኃይማኖታዊ ትውፊትን በመቃወም ተቃርኖን ቀሰቀሰ። ነገር ግን ኢየሱስ
ያደረገውን ነገር ያደረገው ዛሬ ካለው የክርስትና ሕይወት ጋር በጥልቀት ግንኙነት
ላለው ነገር አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ድጋፍ በሚሰጥ መንገድ ነበር።
ከዚያም እምነት በእርግጠኝነት ስለ ምን እንደሚገልጽ በትክክል መረዳት
እንዲቻል በር የሚከፍትን እንቆቅልሽ አቀረበ። ከዚህ በኋላ ወደ ጢሮስና ሲዶና
በመሄድ በወንጌላት ውስጥ ከኢየሱስ ጋር ተከራክራ ካሸነፈች ብቸኛ ሴት ጋር
ተገናኘ። ከእርሷ ጋር የነበረው ግንኙነት ያልተለመደ ሲሆን ከሥሩ ሴትዮዋ
ያነሳቻቸው ጥቂት የምስጢር ግንኙነቶች ነበሩ፤ ከእምነቷ የተነሣ ኢየሱስ
የጠየቀችውን ነገር ሰጣት።
ማርቆስ 7 ሌላ የተፈጸመ ፈውስን ጨምሮ ተዓምራቶች ምንም ያህል
ማራኪ ቢሆኑም ብቻቸውን ልብን ለእውነት ክፍት ለማድረግ በቂ ያለመሆናቸውን
ወሳኝ እውነት ይገልጻል። ኢየሱስን ወደ አለመቀበል ላዘነበሉ የኃይማኖት መሪዎች
ተዓምራቶች ምን ይጠቅማሉ?
የማርቆስ 8 ጥናት ዳቦ የትምህርቶችና የትውፊቶች ምልክት በመሆን
ያለውን ወሳኝነት ይመለከታል። እነዚህ ታሪኮች ስለ ኃይማኖታዊ ሕይወት
ትርጉምና ልምምድ ታላላቅ ትምህርቶችን ይይዛሉ።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሃሴ 4 ሰንበት ለመዘጋጀት ያንብቡ።
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ማርቆስ 7፡1-13ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ምን አግባብነት ያላቸው እውነቶች ቀረቡ?
ልጆች በሰንበት ትምህርት ክፍላቸው ይህንን ንባብ ከተማሩ በኋላ ወደ
ቤት መጥተው ኢየሱስ እጅ መታጠብ አያስፈልግም ስላለ ከመመገባቸው በፊት
እጃቸውን መታጠብ እንደማያስፈልጋቸው ለእናቶቻቸው እንደሚነግሩ አድርጎ
የሆነ ሰው ማሰብ ይችላል። ነገር ግን ይህ ታሪክ የሚናገረው ስለ ንጽህና አጠባበቅ
አይደለም።
በኢየሱስ ዘመን በዚያ አገር የነበሩ ብዙ ሰዎች ሥርዓታዊ ንጽህና
የሚያስጨንቃቸው ነበሩ። ሥርኣታዊ በሆነ ሁኔታ ንጹህ ለመሆን እጆችን
የመታጠብ ሀሳብ፣ ምንም እንኳን መጀመሪያ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ለነበሩ
ካህናት የተሰጠ ቢሆንም (ዘጸ. 30፡17-21)፣ በኪዳኖቹ መካከል በነበረው ዘመን
ወደ ተራው ሕዝብ ሁሉ ደርሶ ነበር። የኃይማኖት መሪዎች ስለ ደቀ መዛሙርቱ
ለኢየሱስ ስሞታ ያቀረቡት ይህንን ጽንሰ ሀሳብ በመያዝ ነበር።
ኢየሱስ ለተጠየቀው ጥያቄ በቀጥታ መልስ አልሰጠም። በዚህ ፈንታ
መንታ የሆነ መልስ በመስጠት ለደቀ መዛሙርቶቹ ተከላከለላቸው። በመጀመሪያ
እግዚአብሔርን በቃል የሚያከብር ግን ልቡ ከእርሱ የራቀ ሕዝብን ኢሳይያስ
የገሰጸበትን ጠንካራ ቃላት ይጠቅሳል (ኢሳ. 29፡13)። ከኢሳይያስ የተወሰደው ጥቅስ
በመለኮታዊ ትዕዛዛት ፈንታ ሰብአዊ ትውፊትን ማስቀመጥን በመኮነን ይቀጥላል።
የኢየሱስ መልስ ሁለተኛው ክፍል የኢሳይያስን ጥቅስ ያሟላል። ጌታ
ወላጆችን ስለማክበር የሚናገረውን ትዕዛዝ ይጠቅሳል (ዘጸ. 20፡12)። ይህ ማለት
ሲያረጁ ለእነርሱ እንከብካቤ ማድረግን የሚያመለክት ሲሆን ይህንን ሀሳብ አንድ
ሰው ለእግዚአብሔር የሆነ ነገርን ከሚሰጥበትና ለራሱ ከሚጠቀምበት፣ ነገር ግን
ለሚያስፈልጋቸው በዕድሜ አንጋፋ ለሆኑ ወላጆች ያለውን ጠቀሜታ ከማይቀበል
ኃይማኖታዊ ትውፊት ጋር ያነጻጽረዋል (ስጦታ፣ ቁርባን)። “አባቴ ሆይ፣ አዝናለሁ።
ብረዳህ ደስ ይለኝ ነበር፣ ነገር ግን ገንዘቡን ለቤተ መቅደስ ሰጥቻለሁ” የሚለውን
ንግግር አንድ ሰው ማሰብ ይችላል። ኢየሱስ ያለ አንዳች ድርድር እየነቀፈ ያለው የዚህን
ዓይነት ግብዝነት ነው። ሰብአዊ ትውፊትን ከእግዚአብሔር ቃል በላይ ያስቀመጡ
ሲሆን በዚህ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን በድለዋል (ኃጢአት ሰርተዋል)።
ስለዚህ ለፈሪሳውያን ጥያቄ የተሰጠው መልስ ምን ነበር? የእግዚአብሔር
ፈቃድ በሚያሳየው መሰረት እጅ እንዲታጠቡ ማስገደዳቸው አሳማኝ ሆኖ
እንዳላገኘው የኢየሱስ መልስ ያመለክታል። በዚህ ፋንታ ከሰው ትውፊት ይልቅ
የእግዚአብሔር ሕግጋት እንደሚበልጡ መልሱ በግልጽ ይደግፋል። (ደግሞ ማር.
1:44፤ ማር. 7:10፣ 11፤ ማር. 10:3–8፤ ማር. 12:26, 29–31 ይመልከቱ።)
ምናልባት ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት መርሆዎች ጋር የሚጋጩ አንዳንድ “ትውፊቶች”
ይኖሩን ይሆን? እንዲህ ከሆነ እነዚህ ትውፊቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
ማር. 7:14–19ን ያንብቡ። በማር. 7፡15 ላይ ኢየሱስ እንቆቅልሽ ሲሰጥ ምን ማለቱ ነበር?
ብዙዎች በዘሌዋውያን ምዕራፍ 11 ላይ ንጹህና ንጹህ ያልሆኑ ምግቦችን
በተመለከተ ስለቀረቡ ትምህርቶች እያሰቡ ሳለ የኢየሱስ ቃላት ለብዙዎች ከባድና
ግራ የሚያጋቡ ነበሩ። ኢየሱስ የዚህ ዓይነቶቹን ልዩነቶች እያስወገደ ነውን?
ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ሥጋን የሚበሉ የቤተ ክርስቲያን አባላት መብላት
ያለባቸው ንጹህ እንስሳት ተብሎ ከተሰጠው ዝርዝር ውስጥ ያሉትን ብቻ እንደሆነ
በማስተማራቸው ተሳስተዋልን?
በመጀመሪያ ኢየሱስ በማርቆስ 7፡6-13 ላይ ከተሰጠው ትውፊት በተቃራኒ
ሙሴን የተከላከለ ሲሆን በማርቆስ 7፡14-19 ላይ በድንገት የሙሴ መማሪያዎችን
ተቀባይነት ቢያሳጣ እንግዳ ነገር ይሆንበታል። ሁለተኛ፣ ፈሪሳውያን እያስተዋወቁ
ያሉት ያው ትውፊት በብሉይ ኪዳን ትምህርት ውስጥ መሰረት የለውም፤
በንጽጽር ሲታይ የምግብ ሕጎች መሰረት አላቸው። ሶስተኛ፣ ማርቆስ 7፡19 ኢየሱስ
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ሁሉንም ምግብ ያነጻል ሲል የምግብ ሕጎች ተሽረዋል ማለት አይደለም፣ ነገር ግን
ፈሪሳውያን የፈጠሩት በመንካት የሚፈጸም የመርከስ ትውፊት ዋጋ ቢስ ነው።
ለምሳሌ፣ ከአህዛብ ጋር አካላዊ ንክኪ ከፈጠርክ ትረክሳለህ የሚለው አስተሳሰብ
እነርሱ የነኩትን ምግብ ከነካህም ትረክሳለህ እንደ ማለት ነው።
ማርቆስ 7:20–23ን ያንብቡ። ኢየሱስ አንድን ሰው ያረክሳል ያለው ነገር ምን
ነበር?
ማርቆስ 7:19 ላይ ኢየሱስ ምግብ ወደ ልብ ሳይሆን ወደ ሆድ ይሄድና
እዳሪ ሆኖ ወደ ውጭ ይወጣል። ነገር ግን ማርቆስ 7፡21-23 ላይ ክፋት ከልብ፣
ግለሰቡ ማን እንደሆነ ከሚወስንበት ማዕከል ይወጣል በማለት አሳስቧል። ከክፉ
ሀሳብ የሚነሱ ክፋቶችን ዝርዝር በማቅረብ እነዚህ ክፋቶች በክፉ ድርጊቶች
እንደሚጠናቀቁ ይገልጻል።
ማርቆስ 7፡10 ላይ የተጠቀሰው 5ኛውን ትዕዛዝ የሚያመለክተው ሀሳብ
ከክፋት ዝርዝር ጋር ሲካተት በሁለተኛው ጽላት ላይ የተጻፈው እያንዳንዱ ትዕዛዝ
ተካትቷል። ስለዚህ ኢየሱስ በዚህ ንባብ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር
ሕግ ተከላካይ ሆኖ ቆሟል።
ትክክለኛ የሆነ የሥነ-መለኮት ትምህርት እውቀት ሊኖርዎ ይችላል፣ ነገር ግን ልብዎትን
ሙሉ በሙሉ እና በመጨረሻ የያዘው ማን ነው?
ማር. 7:24–30ን ያንብቡ። በዚህ ታሪክ ውስጥ ምን ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶች ይገኛሉ?
የትላንት ትምህርትን ከባድ ንባብ እግር በእግር በመከተል በዚህ ንባብ
ውስጥ ያለው ታሪክም አስቸጋሪ የሆኑ ጥያቄዎችን ያነሳል። ኢየሱስ ለዚህች ሴት
ብዙ ቃላትን በመጠቀም ውሻ ብሎ እየጠራት እጅግ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ
ለምን መልስ ይሰጣል?
ምክንያቱን በግልጽ ባያብራራም ለእርሷ በሰጠው መልስ መካከል ያሉ
ሁለት ባህሪያት እርሱ እያስተማረ ያለውን ነገር ይጠቁማሉ። ማርቆስ 7፡27 ላይ
“በመጀመሪያ” ልጆች መመገብ አለባቸው አለ። “መጀመሪያ” ካለ “ሁለተኛ”
የመኖሩ ጉዳይ አመክኒዮአዊ ነው። ኢየሱስ የተጠቀመው ሌላኛው ገጸ ባህሪይ ውሻ
የሚለውን ቃል እጅግ አሳንሶ የተጠቀመበት ሲሆን አባባሉ ቡችላ ለማለት ሳይሆን
ስድ ከተለቀቁ ውሾች በተቃራኒ እቤት ውስጥ እንዲሆኑ በሚፈቀድላቸው ውሾች
አውድ ነበር። ሴትዮዋ ለኢየሱስ መልስ ስትመልስ እነዚህን ሁለት መነሻዎች
በመውሰድ መሆኑ የእርሷን መልስ ለማብራራት ይረዳል።
የሴትዮዋ መልስ ቀጥተኛ ነበር። “ጌታ ሆይ፥ ቡችሎች እንኳ ከማዕድ
በታች ሆነው የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ” በማለት መልስ ሰጠች(ማር. 7:28).
ሴትዮዋ ለኢየሱስ የዚህን ዓይነት መልስ እንዴት መስጠት ቻለች?
በእርግጠኝነት ለልጇ የነበራት ፍቅር ይህንን እንድታደርግ አስገድዷታል። ነገር
ግን እርሱም አደፋፍሯታል። “መጀመሪያ” ማለቱ “ሁለተኛ” ሊኖር እንደሚችል
ያመለክት ነበር። ከዚህ በተጨማሪ እርሷ ከጠረጴዛው ሥር ያለች ውሻ መሆኗን
ያመለክታል።
ውሻው ከጠረጴዛ ሥር እቤት ውስጥ እንደነበረ ሁሉ እርሷም ስለ ልጇ
እየለመነች በኢየሱስ እግር ሥር ነበረች። ስለዚህ በመሬት ላይ የሚወድቀውን
ፍርፋሪ የሚበላው የውሻ መብት እንዲሰጣት ጠየቀች።
የሴትዮዋ መልስ እምነቷን ይገልጻል። ለልጇ የሚደረገውን ታላቅ የፈውስ
ተዓምራት “ፍርፋሪ” ብላ መጥራቷ የኢየሱስ ኃይል በተለየ ሁኔታ ታላቅ መሆኑን
(የዚህ ዓይነቱ ተዓምራት ፍርፋሪ ከሆነ ሙሉ ዳቦው ምን ሊሆን ይችላል?) እና
የእርሷን ጥያቄ መመለስ ለእርሱ ትንሽ ነገር መሆኑን ያመለክታል። ኢየሱስ ልቡ
ስለተነካ የጠየቀችውን ሰጣት።
“ለእርሷ ባደረገው ነገር በእሥራኤል ሕዝብ ዘንድ የተወገዘች ብትሆንም
አሁን ግን ባዕድ እንዳልሆነች፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ያለች
ልጅ እንደሆነች አሳይቷል። እንደ ልጅ የአባቷን ስጦታዎች የመጋራት መብት
አላት።”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 401.
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
በሌሎች ዘሮችና ዜጎች ላይ ያለው የጥላቻ አመለካከት ከኢየሱስ ትምህርቶች ታቃራኒ
የሚሆነው ለምንድር ነው? ከዚህ ክፋት ተረጭተን ልንነጻ የምንችለው እንዴት ነው?
ማር. 7:31–37ን ያንብቡ። ሰዎች ወደ ኢየሱስ ያመጡት ሰው ማን ነበር? ኢየሱስ ምን አደረገለት?
ኢየሱስ ከጢሮስና ሲዶና ወደ ገሊላ ለመመለስ አጭሩን መንገድ
አልተከተለም። ኢየሱስ ከጢሮስ አከባቢ ወደ ሰሜን በሲዶና ውስጥ አልፎ ወደ ላይ
በመሄድ፣ ከዚያም በአገር ውስጥና ወደ ታች ከገሊላ ባህር ወደ ሰሜን ምሥራቅ አከባቢ
በማለፍ በመጨረሻ ወደ ገሊላ ባህር የደረሰ ይመስላል። የሄደበት መንገድ ጠመዝማዛ
እንደመሆኑ ደቀ መዛሙርቱን ለማስተማር ተጨማሪ ጊዜ ያገኘ ይመስላል።
ሰውዬውን ማን ወደ ኢየሱስ እንዳመጣው ጥቅሱ በትክክል አያመለክትም፣
ነገር ግን የሰውዬው ችግር ግልጽ ነበር--መስማት የማይችልና የመናገር ችግር
የነበረበት ሰው ነበር። መስማት አለመቻል ሰዎችን ከአካባቢያቸው የሚለያቸው
ሲሆን ጠለቅ ያለ የመስማት ችግር ደግሞ ንግግርን በመማር ላይ ችግር ይፈጥራል።
የዚህ ሰው ችግር ለብዙ ጊዜ የቆየ ሊሆን ይችላል።
ኢየሱስ የሰውዬውን አስቸጋሪ ሁኔታ በመረዳት ከሕዝቡ ለይቶ ለብቻው
ወሰደው። ጌታ ሰውዬውን ያዳነበት ሁኔታ፣ በተለይ ዘመናዊ ለሆኑ አንባቢያን
የማወቅ ጉጉትን የሚፈጥር ነው። በሰውዬው ጆሮዎች ውስጥ ጣቶቹን አገባ፣
እንትፍም ብሎ ምላሱን ዳሰሰና ቃተተ። ኢየሱስ የሚፈውሳቸውን የተጎዱ የአካል
ክፍሎችን ነካ፣ ነገር ግን ለምን መቃተት አስፈለገው? “እርሱ የቃተተው ለእውነት
ስለማይከፈቱ ጆሮዎችና ለአዳኙ እውቅና መስጠት እምቢ ስላሉ ምላሶች በማሰብ
ነበር”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 404.
ኢየሱስ በተዓምራዊ መንገድ የሰውዬውን የመስማት ችሎታ የመለሰ
ሲሆን በግልጽ መናገር እንዲችልም አድርጎታል። መቃተቱ የሚያሳየው
እግዚአብሔር ለሰብአዊ ዘር የሰጠውን የምርጫ ነጻነትን በተመለከተ በራሱ ላይ
ያስቀመጠውን ገደብ ነው። እርሱ ፈቃድን አያስገድድም። ሰብአዊ ዘር በሙሉ
ሕይወታቸውን ማን መምራት እንዳለበት--የሕይወት ልዑል ወይም የጨለማው
ልዑል--የመምረጥ ነጻነት አላቸው። ኢየሱስ የደነቆሩ ጆሮዎችን መክፈት ይችላል፣
ነገር ግን የማያምኑ ልቦች የእርሱን መሲህነት እንዲቀበሉ አያስገድድም።
ይህ አጭር ታሪክ ወደ እርሱ በፈቃደኝነት ለሚመለሱ ሰዎች እግዚአብሔር
ምን ማድረግ እንደሚችልም ያሳያል። ምናልባት እምነትዎን ለሌሎች ለማጋራት
ፈቃደኛ አለመሆንን ተለማምደውና መናገር ስላለብዎ ነገር የአንደበተ ኮልታፋነት
ስሜት ተሰምቶት ሊሆን ይችላል። ይህ ተዓምራት የሌሎች ሰዎች ችግር
እንዲሰማዎትና በጉዞአቸው ቀና የሚያደርግ የተዘጋጀ ቃል ማካፈል እንዲችሉ ጌታ
ጆሮዎችዎን መክፈት እንደሚችል ማበረታቻ ይሰጣል።
መስማትንና መናገርን በተመለከተ የተሰጡ ስጦታዎች ሥጦታ ስለሆኑ በእነዚህ
ስጦታዎችዎ ምን ያደርጋሉ? እርስዎ እነዚህን ስጦታዎች እንዴት እየተጠቀሙባቸው
ነው?
ማር. 8:11–13ን ያንብቡ። ኢየሱስን በጥልቀት ተስፋ ያስቆረጠው የፈሪሳውያን አቀራረብ ምን ነበር?
ኢየሱስ መለኮታዊ ኃይሉን በማሳየት እነዚህን አጉረምራሚዎች ለምን
አያሳምናቸውም? ችግሩ ኢየሱስ በማርቆስ ምዕራፍ 3 መጨረሻ ላይ መንፈስ
ቅዱስን ስለ መሳደብ ወደተናገረው ኃጢአት ወደ ኋላ ይሄዳል። የአንድ ሰው
ጆሮዎች ከተደፈኑና ዓይኖች ከተጨፈኑ፣ ከሰማይ ሌላ ምልክት ቢሰጥ እንኳን
አያምንም። አስቀድሞ እንደሆነው ሁለ ሁሉም ነገር ተቀባይነት ያጣል። ላለማመን
የወሰኑ ሰዎችን ለማሳመን ተዓምራቶች እንኳን በቂ አይደሉም።
ማር. 8:14–21ን ያንብቡ። ደቀ መዛሙርት ረስተው የነበረው ምን ነበር? ከዚህ
ላይ ኢየሱስ አውጥቶ ያሳየው ነጥብ ምን ነበር?
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ “እርሾ” እንዲጠነቀቁ
(ማር. 8:15) ለማስጠንቀቅ አጋጣሚውን ተጠቀመ። ይህ ማለት ከትምህርቶቻቸው
እንዲጠነቀቁ ማለት ነው (ከማርቆስ 16፡12 ጋር ያነጻጽሩ)።
ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ትክክለኛውን ዳቦ
እንዳይገዙ እንደሆነ በማሰብ በስህተት ተረዱ። ከዚህ በፊት ልማዱ እንደነበረው
ሁሉ ደቀ መዛሙርት በተሳሳተ መንገድ ሲረዱ ኢየሱስ ትምህርት ይሰጣቸዋል።
ጌታ ተልዕኮውን ባለመረዳታቸው ተስፋ መቁረጡን በመግለጽ ተከታታይነት
ያላቸውን ጥያቄዎች ይጠይቃል፣ ይህም ተፈጥሮን በመጠቀም ሰዎችን ለማሳመን
ከተናገራቸው በርካታ ንግግሮች የመጀመሪያው ውጤታማ ንግግር ነው።
ቃላቱ በማርቆስ 4፡10-12 ላይ ስለማያስተውሉ ሌሎች ወገኖች ያለውን ነገር
የሚያስታውሱ ናቸው። ጠንካራ ቃሎቹ ደቀ መዛሙርቱን ከመንፈሳዊ ግድ
የለሽነት (ስንፍና) ለመቀስቀስ የታለሙ ናቸው።
በማርቆስ 8:19፣ 20 ላይ ኢየሱስ 5000 ሰዎችን (ማር. 6፡30-44) እና
4000 ሰዎችን (ማር. 8፡1-10) ከመገበ በኋላ ስንት ቅርጫት ፍርፋሪ እንደሰበሰቡ
እንዲነግሩት ቀለል ያሉ ጥያቄዎችን ጠየቃቸው። የእነዚህ ጥያቄዎች ዓላማ
የግብዓቶች ውስንነት ብቻውን ለእግዚአብሔር መሲህ እንቅፋት እንዳልሆኑ
ማሳየት ነበር። በማርቆስ 8፡21 ላይ “ገና አላስተዋላችሁምን?” በማለት የጠየቀው
የመጨረሻው ጥያቄ በድጋሚ እነርሱን ለማሳመን ታስቦ የቀረበ ጥያቄ ነበር።
ከኢየሱስ ጋር እስካሁን ድረስ ያዩትንና የተለማመዱትን ሁሉ ተመልከቱ።
ለእግዚአብሔር እውነታ እና ለፍቅሩ ልባችንን እና አእምሮአችንን ክፍት ማድረግን
መማር የምንችለው እንዴት ነው? ስለ እግዚአብሔርና ስለ ፍቅሩ በተሰጡን
ማስረጃዎች ሁሉ ላይ ጊዜ ወስደው ያስቡ። አንዳንድ ጊዜ ለመጠራጠር እጅግ ቀላል
የሚመስለው ለምንድር ነው?
የዘመናት ምኞት ከሚለው የኤለን ጂ ኋይት መጽሐፍ
“ወግ፣” “እንቅፋቶች (መሰናክሎች) ተወገዱ፣” እና “እውነተኛው ምልክት” የሚሉ
ርዕሶችን ከእንግሊዝኛው መጽሐፍ ከገጽ 395–409 ላይ ያንብቡ።
“በዛሬዎቹ የጌታ ተከታዮች መካከል፣ እንደ ጥንቶቹ ሁሉ፣ ይህ ረቂቅና
አሳሳች ኃጢአት ተስፋፍቶ ያለው ምን ያህል ነው! ለክርስቶስ ያለን አገልግሎትና
ከእርስ በርሳችን ጋር ያለን ግንኙነት ራስን ከፍ ከፍ ከማድረግ ምስጢራዊ
ፍላጎት የተነሣ የተበላሸው ምን ያህል ጊዜ ነው! ሀሳብ በራሱ ስኬት ያለውን
ደስታ ለመግለጽና ሰብአዊ እውቅናን ለማግኘት ያለው ፍላጎት ምን ያህል
ነው! በመለኮታዊ ትዕዛዛት ፋንታ ሰብአዊ መላምቶችንና ወጎችን ወደመተካት
የሚመራው የራስ ፍቅርና እግዚአብሔር ካስቀመጠው ውጭ ቀላል መንገድን
መፈለግ ነው። ክርስቶስ ለራሱ ደቀ መዛሙርት ‘ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ’
በማለት የማስጠንቀቂያ ቃላትን ተናግሯል።-
“የክርስቶስ ኃይማኖት ራሱ ቅንነት ነው። ለእግዚአብሔር ክብር መቅናት
መንፈስ ቅዱስ የተከለው ውስጣዊ ማነሳሻ ነው። ይህንን ማነሳሻ የሚተክለው
የመንፈስ ቅዱስ ውጤታማ ሥራ ብቻ ነው። ራስ ወዳድነትንና ግብዝነትን ማጥፋት
የሚችለው የእግዚአብሔር ኃይል ብቻ ነው። ይህ ለውጥ የእርሱ ሥራ ምልክት
ነው። የምንቀበለው እምነት ራስ ወዳድነትንና ማስመሰልን ሲያጠፋ እና የራሳችንን
ሳይሆን የእግዚአብሔርን ክብር እንድንሻ ሲመራን ነገሩ ከትክክለኛ ሥርዓት የሆነ
መሆኑን እናውቃለን። ‘አባት ሆይ፣ ስምህን አክብር’ (ዮሐ. 12:28) የሚለው ንግግር
የክርስቶስ ሕይወት ዋና ነጥብ ስለነበር እርሱን ከተከተልን ይህ የእኛም ሕይወት ዋና
ነጥብ ይሆናል። ‘እርሱ እንደተመላለሰ እናንተም እንዲሁ ተመላለሱ’ ብሎ ያዘናል።
‘ትዕዛዛቱን ብንጠብቅ እርሱን እንደምናውቀው በዚህ እናውቃለን’ 1 ዮሐንስ 2:6፣
3።”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 409.
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
1. ልብን ንጹህ አድርጎ ለመጠበቅ የሚረዱ ምን ክርስቲያናዊ ልምምዶችን አገኙ?
2. በእርስዎ ማህበረሰብ ውስጥ “እርኩስ” የሚባሉ ሰዎች እነማን ናቸው? እነርሱ
ወደ ወንጌል እንዲሳቡ ለመርዳት ምን ማድረግ ይችላሉ?
3. እንደ ክፍል ወንጌልን ለጎረቤቶቻችሁ በቀላል መንገድ ለማጋራት ምን ማድረግ
እንደምትችሉ አስቡ።
4. አራት ሺሆችን ስለመመገብ የሚገልጸውን ማርቆስ 8:1–10ን ያንብቡ።
አህዛብ ለሆነው ሕዝብ ይህን ንባብ መተርጎም ምን ልዩነት ያመጣል? ምንም
ለውጥ ማምጣት የሌለበት ለምንድር ነው?
5. በኃጢአት እንደወደቁ ፍጡራን በውርስ ካገኘነው ራስን ከፍ ከፍ ከማድረግ
ፍላጎት ራሳችንን ተግተን መከላከል የምንችለው እንዴት ነው?