የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

የማርቆስ መጽሐፍ



3ኛ ሩብ ዓመት 2024


መስከረም 4 - 10

12ኛ ትምህርት

Sep 14 - 20




የተፈተነ እና የተሰቀለ



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- : ማር. 15፤ ሉቃስ 13:1፣ መዝ. 22:18፣ ዮሐ. 20:24–29፣ ዮሐ. 1:1–3፣ ዳን. 9:24–27።


የመታሰቢያ ጥቅስ: “በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው።?” (ማርቆስ 15:34)።

ማርቆስ 15 የመከራው ታሪክ እምብርት ነው። የኢየሱስን የክስ ሂደት፣ ውግዘት፣ በወታደሮች የደረሰበትን ፌዝ፣ ስቅለቱን፣ መሞቱንና መቀበሩን ያቀርባል። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉ ክስተቶች እጥር ምጥን ባለ ሁኔታ ተዘርዝረው ቀርበዋል። ምናልባት ይህ የሆነበት ምክንያት ደራሲው ጭብጦቹ ለራሳቸው እንዲናገሩ ስለተዋቸው ሊሆን ይችላል።

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በሙሉ ምጸት ወሳኝ ሚናን ይጫወታል። ከዚህ የተነሳ ምጸት ምን እንደሆነ ግልጽ የሆነ ትርጉም ማግኘት ጠቃሚ ነው።

ብዙ ጊዜ ምጸት ሶስት ነገሮች ይኖሩታል፡-(1) ሁለት ደረጃዎች ያሉት ትርጉም፣ (2) ሁለቱም ደረጃዎች እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ወይም ተነጻጸሪ ናቸው (3) ግለሰቡ ምጸቱን ስለማያይ እየሆነ ያለውን ነገር አይገነዘብም፣ መዘዞቹ በእርሱ/በእርሷ ላይ ችግር እንደሚፈጥሩ አያውቅም/አታውቅም።

በዚህ ሳምንት “አንተ የአይሁድ ንጉስ ነህን?” ከሚለው የጲላጦስ ጥያቄ አንስቶ እስከሚያፌዙ ወታደሮችና የኃይማኖት መሪዎች፣ ከመስቀሉ ራስጌ “ሌሎችን አዳነ፣ ራሱን ማዳን ግን አይችልም” በማለት እስካስቀመጡት ምልክት፣ እንዲሁም ሳይጠበቅ እስከመጣው የአርማትያው ዮሴፍ ድረስ ምዕራፉ እጅግ በሚያምሙ ምጸቶች የተሞላ ቢሆንም ስለ ኢየሱስ ሞትና ይህ ምን ማለት እንደሆነ ኃይለኛ የሆኑ እውነቶችን ይገልጣል። *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለመስከረም 11 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ። የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ

መስከረም 5
Sep 15

“አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?”


ማር. 15:1–15ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ምን ዓይነት ምጸታዊ ሁኔታዎች ይታያሉ?



ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከ26-36 ዓ.ም ድረስ የይሁዳ ገዥ ነበር። ቸር መሪ ስላልነበር በርካታ ድርጊቶቹ በዚያ አገር ለሚኖሩ ሰዎች ተስፋ አስቆራጭ ነበሩ (ከሉቃስ 13፡1 ጋር አወዳድሩ)። በኢየሱስ ላይ የቀረበው ክስ ተሳድቧል በሚል ሰበብ የሞት ፍርድ እንዲፈረድበት አድርጓል። ነገር ግን በሮም ሕግ ሥር በአብዛኛው አይሁዶች ሰዎችን መግደል አይችሉም ነበር፤ ከዚህ የተነሣ እንዲፈረድበት ኢየሱስን ወደ ጲላጦስ አመጡት።

በጲላጦስ ፊት በኢየሱስ ላይ የቀረበው ክስ አልተጠቀሰም፣ ነገር ግን ጲላጦስ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” (ማር. 15:2) ብሎ በጠየቀው አጭር ጥያቄ በመመስረት ክሱ ምን እንደሆን ማረጋገጥ ይቻላል። በብሉይ ኪዳን ዘመን እሥራኤል የራሷን ነገሥታት ትቀባ ነበር፤ ስለዚህ መሲህ (“የተቀባው”) የሚለውን ቃል ለንጉሥ የሚገባውን መገዛት እንደሚፈልግና ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ሥልጣን እንደሚሻማ አድርጎ መጠምዘዝ እንደሚቻል ማየት አይከብድም።

ስለዚህ በመማክርቱ ፊት የቀረበው ክስ ተሳድቧል የሚል ሲሆን በገዥው ፊት የቀረበው ክስ ደግሞ አመጽ አነሳስቷል የሚል ነበር፤ ይህም ሞት የሚያስከትል ተግባር ነበር።

እዚህ ላይ ያለው ምጸት ኢየሱስ የአይሁድ መሲህና ንጉሥ መሆኑ ነው።

ተሳድቧል በማለትና አመጽ አነሳስቷል በማለት የቀረቡበት ክሶች ስህተት ነበሩ፤ እንዲያውም አክብሮትና አምልኮ ይገባው ነበር።

ሆኖም ኢየሱስ አሁንም የቸርነት ተግባሩን ቀጠለበት። ለጲላጦስ “አንተ አልክ” (ማር. 15:2) በማለት የመለሰው መልስ ግልጽ አልነበረም። ሥልጣኑ አይገባኝም ወይም ይገባኛል አላለም። ይህ መልስ እርሱ ንጉሥ መሆኑን ይጠቁማል፣ ነገር ግን በተለየ መልኩ ነው። (ከዮሐንስ 18:33–38 ጋር አወዳድሩ)።

ማርቆስ 15፡6 ላይ ያለው ታሪክ በፋሲካ ጊዜ አንድ እሥረኛን የመልቀቅ ልማድን ያስተዋውቃል። በማርቆስ 15፡9 ላይ “ የአይሁድ ንጉሥን” እንድለቅላችሁ ትፈልጋላችሁን ብሎ ጠየቃቸው። ነገር ግን ጥያቄው ምጸታዊ ሲሆን በምጸታዊ ሁኔታ እርሱን የማጥፋት ድራማ እየተጫወተ ነበር።

ማርቆስ 15፡9 በሚታይና በማይታይ መንገድ የሚደረግ ጥናት ነው።

የኃይማኖት መሪዎች በኢየሱስ ላይ የተነሱበት በቅናት እንደሆነ ጲላጦስ ተመልክቷል። ነገር ግን ሕዝቡን በመጠየቁ የኃይማኖት መሪዎችን እየረዳ መሆኑን አላየም ነበር።

ሕዝቡን በማነሳሳት ኢየሱስ እንዲሰቀል ጠየቁ። ጲላጦስ ወደ ኋላ አፈገፈገ። ስቅለት አሰቃቂ የሆነ የመግደል መንገድ ሲሆን በተለይ ጥፋት እንደሌለበት እያወቀ ይህን ፍርድ መፍረድ አሰቃቂ ነበር። የኃይማኖት መሪዎች ሊሰቅሉት እየፈለጉ ሳለ የአህዛብ ገዥ መሲህን ለመልቀቅ ማሰቡ ምንኛ የሚያም ምጸት ነው።

አንድን ነገር የማድረግ ጫናው ትልቅ በሚሆንበት ጊዜ ሕዝብን ከመከተል ሊጠብቅዎ የሚችል ነገር ምንድር ነው?

መስከረም 6
Sep 16

የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ላንተ ይሁን!


ማርቆስ 15:15–20ን ያንብቡ። ወታደሮቹ ለኢየሱስ ምን አደረጉ? ድርጊታቸው ምን ቁም ነገር አለው?



ሮማውያን እሥረኞችን ከመግደላቸው በፊት ከባድ የሆነ የግርፋት ዓይነትን ይጠቀሙ ነበር። ተጠቂው ልብሱ ይወልቅና ከግንድ ጋር ታስሮ የአጥንት፣ የብርጭቆ፣ የድንጋይና የምስማር ስብርባሪዎች በጫፉ ላይ በታሰሩበት ከቆዳ በተሰራ ጅራፍ ይገረፋል። ኢየሱስ በጅራፍ ከተገረፈ በኋላ እንዲገድሉት ሀላፊነት የተሰጣቸው ወታደሮች ሀምራዊ ልብስ አልብሰውት፣ በራሱ ላይ የእሾህ አክሊል ደፍተው የአይሁድ ንጉሥ እንደሆነ በማፌዝ እየተናገሩ የማዋረድ ተግባራቸውን ቀጠሉበት። በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ ወታደሮች ቡድን ጭፍራ የተባለ ሲሆን በውስጡ ከ200 እስከ 600 ወታደሮችን ይይዛል።

ኢየሱስ በርግጥም ንጉሥ ስለሆነ እና የወታደሮቹ የማሾፍ ቃላት ይህንን የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ እውነት ስለሚያውጁ በትዕይንቱ ውስጥ ያለው ምጸት ግልጽ ነው። የወታደሮቹ ተግባር፣ የሮምን ንጉሰ ነገሥት “ሰላም ለንጉሠ ነገስት ቄሳር!” እያሉ ወታደሮች የሚያወድሱበትን የቁም ነገር ተግባር በፌዝ መልክ ማቅረብ ነው። ስለዚህ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ግልጽ ያልሆነ ንጽጽር አለ።

ወታደሮቹ በኢየሱስ ላይ ለማሾፍ የተጠቀሙባቸው ተግባራት ራሱን በመቃ “መምታት፣” “መትፋት” እና የፌዝ ታዛዥነትን በማሳየት “መንበርከክ” ናቸው። እነዚህ ሶስቱ ተግባራት በግሪክ ቋንቋ ፍጹም ባልሆነ ጊዜ ተገልጸዋል።

በዚህ አውድ ይህ ጊዜ ተግባሩን በተደጋጋሚ የመፈጸም ሀሳብ አለው። መምታቱን፣ መትፋቱንና ማሾፉን እየደጋጋሙ ማድረጋቸውን ቀጥለውበት ነበር። ኢየሱስ ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ይህን ሁሉ በዝምታ ተቀበለ።

ሮማውያን የተፈረደበትን ወንጀለኛ በስቅለት የሚገድሉበት ምሳሌያዊ ተግባር ግለሰቡ እራቁቱን ሆኖ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ስቅለቱ ቦታ መሄድን ያካትት ነበር። ይህ ዘዴም ግለሰቡን በማህበረሰቡ ፊት ሙሉ በሙሉ ለማዋረድና ሀፍረት ውስጥ ለማስገባት የሚደረግ ተግባር ነበር። ነገር ግን አይሁዶች በሕዝብ ፊት ዕራቁት መሆንን ይጸየፉ ነበር። ማርቆስ 15፡20 ቀዩን ልብስ ገፈው የራሱን ልብስ እንዳለበሱት ይገልጻል። ይህ በዚያን ጊዜ እና ቦታ ሮማውያን የአይሁድን ሥርዓት ተቀብለው ፈቃድ መስጠታቸውን የሚገልጽ ይመስላል።

በዚህ ቦታ ስላሉ ምጸቶች በሙሉ ያስቡ። ምንም እንኳን ኢየሱስ በርግጥ ንጉሥ ቢሆንም፣ በማፌዝ እንደ ንጉሥ ለእርሱ መስገዳቸውና “አክብሮት” ማሳየታቸው ለአይሁዶች ብቻ ሳይሆን ለእነርሱም ንጉሥ መሆኑን ያሳይ ነበር።

እነዚህ ሰዎች ስለሚያደርጉት ነገር ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበራቸውም ነበር። ታዲያ አለማወቃቸው በፍርድ ቀን ተጠያቂ እንዳይሆኑ ምክንያት የማይሆንላቸው ለምንድር ነው?

መስከረም 7
Sep 17

ስቅለት


ማር 15:21–38ን ያንብቡ። በእነዚህ ንባቦች ውስጥ የሚታየው ምን አሰቃቂና የሚያም ምጸት ነው?





በመከራው ታሪክ ውስጥ፣ በዚህ ነጥብ ላይ ኢየሱስ እርሱን ወደ መግደል ባዘነበሉ ሰዎች ቁጥጥር ሥር የነበረ ዝምተኛ ሰለባ ነበር። በመላው ወንጌል ውስጥ እስከሚያዝበት ጊዜ ድረስ እርሱ የእንቅስቃሴዎቹ ጌታ ነበር። አሁን በእርሱ ላይ እየተሰራበት ነው። ምንም እንኳን ብርቱ ተጓዥ ሰባኪ ቢሆንም የደረሰበት ድብደባ፣ የምግብና የእንቅልፍ እጦት፣ እንግዳ የሆነ ሰው መስቀሉን እስኪሸከምለት ድረስ አድክመውት ነበር።

በሚሰቀልበት ጊዜ ልብሶቹ ወልቀው የወታደሮች ንብረት ሆነዋል፣ ወታደሮቹም ዕጣ ተጣጥለውባቸዋል (ከመዝሙር 22:18 ጋር ያነጻጽሩ)። ስቅለት ደም የማይፈስበት የመግደል ዘዴ ነበር። ግለሰቡን በመስቀል ላይ ለመቸንከር ጥቅም ላይ የዋሉት ምስማሮች ዋና የደም ሥሮች በሌለበት ከእጅ መዳፍ በታች ባለው ቦታ ውስጥ ይመቱ ነበር (በእብራይስጥና በግሪክ ቋንቋዎች “እጅ” የሚለው ቃል እጅንና ክንድን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።) የእጁ መዳፍ ራሱ በተሰቀለበት የሰውነትን ክብደት ለመሸከም አስፈላጊ የሆኑ መዋቅሮች የሉትም።

በእጅ ውስጥ ያለው ዋናው ነርቭ በክንዶቹ አማካይ ላይ ስለሚሄድ ምስማሮቹ በመጨፍለቅ በክንዱ ላይ አሰቃቂ ሕመም ሊያስከትሉ ይችላሉ። መተንፈሰ ከባድ ነበር። የስቅለት ሰለባዎች ጥሩ ትንፋሽ ለማግኘት በምስማር በተቸነከሩ እግሮች በተቃራኒ በመግፋት እጆቻቸውን የሚያጥፉ ሲሆን ይህ በድጋሚ ስቃይ ያለበትን ህመም ያስከትላል። ከድካም የተነሣ አእምሮ በቂ ኦክሲጅን አለማግኘት ሞትን ከሚያስከትሉ ምክንያቶች አንዱ ነበር።

ኢየሱስ በስቅለቱ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ፌዝና ውርደት ደርሶበታል። የማርቆስ ወንጌል ራዕይ አለው/ኢየሱስ ስለ ማንነቱ ለማንም እንዳይናገሩ የነገረበት የምስጢር ሀሳብ። ከዚህ የተነሣ እንደ “ጌታ፣” “የእግዚአብሔር ልጅ፣” እና “ክርስቶስ” ያሉ ክርስቶስን የሚገልጹ ማዕረጎች ብዙ ጊዜ በታሪኩ ውስጥ አይታዩም።

ይህ ነገር በመስቀል ላይ ተለወጠ። መደበቅ አይችልም። የኃይማኖት መሪዎች በኢየሱስ ላይ በማፌዝ እነዚህን ማዕረጎች መጠቀማቸው ምጸታዊ ነው።

እነዚህ ሰዎች ምንኛ ራሳቸውን እየኮነኑ ይሆን!

ለማፌዝ ከተጠቀሙባቸው አረፍተ ነገሮች መካከል አንዱ ከሁሉ ጎልቶ ይታያል። ማርቆስ 15፡31 ላይ “ ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ማዳን አይችልም” ያሉት ይህን ይገልጻል። በመስቀል ላይ ረዳት የለሽ መሆኑን ለማግለጽ ሌሎችን መርዳቱን አመለከቱ (የግሪክ ግሥ “ማደን” “መፈወስ” “መታደግ”) የሚል ትርጉም አለው።. የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ በመሆኑም ምጸታዊ በሆነ መልኩ መሲህ መሆኑን ተቀብለዋል። ምጸቱ ከዚህም አልፎ ይሄዳል--ራሱን ማዳን ያልቻለበት ወይም የማያድንበት ምክንያት በመስቀል በመሰቀሉ ሌሎችን እያዳነ ስለነበር ነው።

ዮሐንስ 1:1–3ን ያንብቡና ይህ ንባብ በማርቆስ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መሰቀሉ እየተናገረ ስላለው ኢየሱስ ምን እንደሚናገር ያስቡ። የክርስቶስ ሞት ለእኛ ምን ማለት ነው በሚለው ዙሪያ አእምሮአችንን መሰብሰብ የምንችለው እንዴት ነው?

መስከረም 8
Sep 18

በእግዚአብሔር የተተወ


ማርቆስ 15:33–41ን ያንብቡ። በማርቆስ ውስጥ የኢየሱስ ብቸኛ ቃላት ምንድር ናቸው? የክርስቶስ ሞት በመጨረሻ ለሁላችን ምን ማለት ነው?





የማርቆስ ወንጌል መስቀልን በአካላዊና መንፈሳዊ ሁኔታ እጅግ ጨለማ የሆነ ቦታ አድርጎ ያቀርበዋል። በዚያን አርብ ዕለት ከእኩለ ቀን ጀምሮ እስከ 9 ሰዓት ድረስ በቀራኒዮ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ጨለማ ወረደ። “ስድስት ሰዓት በሆነ ጊዜ እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ጨለማ ሆነ” (ማር. 15:33)።

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ለምን እንደተወው በመግለጽ ወደ አባቱ በመጸለይ ያሰማቸው ቃላት “የመተዉ ወይም እንክብካቤን የመነፈግ ጩኸት” ተብለዋል።

እርሱ እየጠቀሰ ያለው ከመዝሙር 22፡1 ላይ ነው። ያንኑ መዝሙር የሚገልጹ ሌሎች ጥቅሶች ማርቆስ 15፡24 እና 29 ላይ ያሉ ሲሆን በኢየሱስ ሞት መጻሕፍት ተፈጻሚነት እያገኙ እንደሆነ የሚያመለክቱ ነበሩ። በሰዎች ክፉ ሴራ ውስጥ እንኳን የእግዚአብሔር ፈቃድ እየተፈጸመ ነበር። የኢየሱስ ቃላት ከመስቀል ላይ በአረማይክ ቋንቋ ከነትርጉማቸው እየተዘገቡ ናቸው። በጥቅሱ ውስጥ የተገለጹት “አባቴ፣ አባቴ” የሚሉ ቃላት ኤሎሄ፣ ኤሎሄ ማለት ሲሆን (‹ኤላሂ› ከሚል የአረማይክ ቃል የተተረጎሙ ናቸው)። ኢየሱስ ኤልያስን እየጠራ ነው ብሎ መስማት ይቀላል (በአረማይክ ’ኤሊያህ’ ማለት “አምላኬ ያህዌህ ነው” ማለት ነው)። በዚያ ቆመው የነበሩ አንዳንዶች የፈጸሙት ስህተት ይህ ነው።

ስለዚህ ንባብ አስደናቂው ነገር ማርቆስ 1፡9-11 ላይ ካለው ከኢየሱስ ጥምቀት ጋር ያለው መመሳሰል ነው።




እነዚህ ንጽጽሮች የሚነግሩት ነገር ቢኖር ማርቆስ 1 ላይ ያለው የኢየሱስ ጥምቀት ዳንኤል 9፡24-27 ላይ እንደተተነበየው የአገልግሎቱ ጅምር እንደሆነ ሁሉ ማርቆስ 15 ላይ የተገለጸው በመስቀል ላይ የሆነው ነገር ለብዙዎች ካሳ በመሆን መሞቱ የአገልግሎቱ ፍጻሜ ወይም ግብ መምታት ነው (ማር. 10፡45)። የኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት ዳንኤል 9፡24-27 ላይ ያለውን ትንቢት በከፊል ተፈጻሚ ያደርገዋል። የቤተ መቅደሱ መጋረጃ መቀደድ (ማር. 15፡38) ምሳሌው ከአካሉ ጋር በመገናኘቱና የድነት ታሪክ አዲሰ ምዕራፍ በመጀመሩ የመስዋዕት ሥርዓት ወደ ፍጻሜ መምጣቱን የሚያመለክት ነው።

ምንም እንኳን ሰብአዊ ክፉ ሴራ ቢኖርም የእግዚአብሔር ዓላማዎች ተፈጽመዋል። በዙሪያችን ምንም ነገር ቢሆንም አሁንም በእግዚአብሔር መታመን እንደምንችልና የእርሱ መልካምነት በመጨረሻ እንደሚያሸንፍ እንድናውቅ ይህ ክስተት ትምህርት በመስጠት የሚረዳን ለምንድር ነው?

መስከረም 9
Sep 19

ተቀበረ


ማር. 15:42–47ን ያንብቡ። በተለየ ሁኔታ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከእይታ ስለጠፉ የአርማቲያው ዮሴፍ ጣልቃ የመግባት ወሳኝነት ምንድር ነው?



ከዚያ ሁሉ ድራማ በኋላ የበለጠውን የተለመዱ (በየዕለቱ የሚከናወኑ) የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ ነገሮች ቀጥለው ሆኑ። ለጀማሪዎች፣ የሞቱ ሰዎች ሁልጊዜም መቀበር አለባቸው።

ነገር ግን ተከትሎ በመጣው ነገር ውስጥ ያሉ በርካታ ነገሮች በመንፈሳዊ ሁኔታ ልብ የሚነኩ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በታሪካዊነታቸው እጅግ ወሳኝ ናቸው።

በዚህ ንባብ ውስጥ የአርማቲያው ዮሴፍ ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ በማርቆስ መጽሐፍ ውስጥ ታይቷል። እርሱ የተከበረ የአይሁድ መማክርት ጉባኤ አባልና “የከተማ ልሂቃን” ከሚባሉት መካከል አንዱ ነበር። ሀብታምና የተከበረ ሰው እንደመሆኑ ደፍሮ ወደ ጲላጦስ በመቅረብ የኢየሱስን ሥጋ መጠየቁ የሚያብራራው በአገር ገዥው ዘንድ ጥሩ ስም እንደነበረው ነው። የመማክርት ጉባኤ አባል የሆነ ሰው በኢየሱስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ይህን የመሰለ ፍላጎት ማሳየቱ ልብ የሚነካ ነገር ነው። ይህ ሁሉ ሲሆን የታመኑ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የት ነበሩ?

በዚህ ቦታ የቀረበው አንድ በታሪካዊነቱ እጅግ ወሳኝ የሆነው ዝርዝር የኢየሱስን መሞት የሚያረጋግጥ ነበር። ዮሴፍ የኢየሱስ ሥጋ እንዲሰጠው መጠየቁን ማርቆስ 15፡ 43 ይናገራል። ነገር ግን ጲላጦስ ኢየሱስ መሞቱን በመስማቱ ተደነቀ (ማር. 15፡44)። ከዚህ የተነሳ የዚህ ጉዳይ ሀላፊነት የተሰጠውን የመቶ አለቃ ጠርቶ ኢየሱስ ስለ መሞቱ ጠየቀው። የመቶ አለቃውም መሞቱን አረጋገጠለት። ይህ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ኋላ አንዳንዶች ኢየሱስ በመስቀል ላይ አእምሮውን ስቶ ነበር እንጂ አልሞተም ስለሚሉ ነው። የመቶ አለቃው ለሮም ገዥው የሰጠው ምስክርነት ይህንን አባባል በቀጥታ ይቃወማል። ሮማውያን ወንጀለኞችን እንዴት እንደሚገድሉ በደንብ ያውቃሉ።

ዮሴፍ ኢየሱስን የሚገንዝበትን በፍታ አመጣ፣ ከዓለት በተወቀረ መቃብርም አኖረው። ይህ መቃብር በውስጡ በእግር መራመድ እስከሚያስችል ትልቅ ነበር (ማር. 16፡5) የወንጌል ጸሐፊው ከዮሴፍ ጋር ቦታውን ስለተመለከቱ ሁለት ሴቶች ጽፏል። እነርሱም መቅደላዊት ማርያምና የያዕቆብ እናት የሆነችው ማርያም ናቸው። እነዚህ ሁለት ሴቶች ከሰሎሜ ጋር ስቅለቱን ከሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር። ሶስቱም እሁድ ማለዳ ወደ መቃብሩ በመሄድ ኢየሱስን ሽቱ የመቀባት ሥራቸውን ለማጠናቀቅ አሰቡ (ማር. 16፡1)።

እነዚህን ሶስት ሴቶች መጥቀስ ለምን አስፈለገ? ማርቆስ 16 ላይ እንደተጠቀሰው መቃብሩ ባዶ ስለመሆኑ ምስክሮች ስለሆኑ ስለ ኢየሱስ ትንሣኤ ወሳኝ ምስክሮች ናቸው። ኢየሱስ እንዲሞት የወሰነበት የመማክርት ጉባኤ አባል የሆነ ሰው በዚህ ቦታ ‹‹ጀግና›› ሆኖ ሲገኝ የኢየሱስ ተከታዮች “በዚህ ቦታ ሳይገኙ መቅረታቸው” ምንኛ ምጸታዊ ተግባር ነው። እኛም ወሳኝ በሆኑ ጊዜያቶች ከቦታችን (ከተግባራችን) እንዳንጠፋ እርግጠኛ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

መስከረም 10
Sep 20


ተጨማሪ ሀሳብ


የዘመናት ምኞት ከሚለው የኤለን ጂ ኋይት መጽሐፍ ገጽ 723-764 ላይ “በጲላጦስ የፍርድ አዳራሽ፣” “ቀራኒዮ” እና “ተፈጸመ” የሚሉ ርዕሶችን ያንብቡ።

“ጲላጦስ ኢየሱስን ሊፈታው ተመኘ። ነገር ግን ይህን አድርጎ ስልጣኑንና ክብሩን ሊያስጠብቅ እንደማይችል ተመለከተ። ዓለማዊ ክብሩን ላለማጣት ኃጢአት የሌለበትን ሕይወት መሰዋትን መረጠ። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ማጣትንና መሰቃየትን ለማምለጥ፣ መርህን መስዋዕት የሚያደርጉ ስንቶች ናቸው። ህሊናና ተግባር ወደ አንድ አቅጣጫ ሲያመለክቱ የራስ ፍላጎት ደግሞ ወደ ሌላ አቅጣጫ ያመለክታል። ማዕበሉ በተሳሳተ አቅጣጫ በኃይል እየሄደ ስለሆነ ከክፋት ጋር የሚደራደር ሰው ወደ በደለኛነት ድቅድቅ ጨለማ ተጠራርጎ ይወሰዳል።”—El- len G. White, The Desire of Ages, p. 738.

“ምትካችንና ዋስ ጠበቃችን በሆነው ክርስቶስ ላይ የሁላችንም በደል ተኖረ። ከሕግ ኩነኔ ሊያድነን እንደ ሕግ ተላላፊ ተቆጠረ። የአዳም ዘር በደል ሁሉ ልቡን ይጫነው ነበር። እግዚአብሔር በኃጢአት ላይ ያለው ቁጣ፣ በበደል ደስተኛ ያለመሆኑ አሰቃቂ መገለጫ፣ የልጁን ነፍስ በጭንቀት (በድንጋጤ) ሞላ።

ክርስቶስ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለወደቀው ዓለም የአባቱን ምህረትና ይቅር ባይ ፍቅር ሲያስተዋውቅ ነበር። የእርሱ ዋና ግብ ለኃጢአተኞች ዋና ለሆነው ድነትን ማምጣት ነበር። ነገር ግን አሁን አሰቃቂ ከሆነው የኃጢአት ሸክም የተነሣ የአብን የማስታረቅ ፊት ማየት አልቻለም። በዚህ ከፍተኛ በሆነው የመከራ ሰዓት መለኮታዊ ፊት ከአዳኙ መመለሱ ሰው በፍጹም ሙሉ በሙሉ ሊያስተውለው በማይችል ሀዘን ልቡን ወጋው። ይህ ሰቆቃ እጅግ ትልቅ ከመሆኑ የተነሣ አካላዊ ሕመሙ አልተሰማውም ነበር።”—Page 753. የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ


የመወያያ ጥያቄዎች




1. የኤለን ጂ ኋይት ስለ ምትክ የሚገልጸው የስነ መለኮት ትምህርት (እና መጽሐፍ ቅዱስ፣ ለምሳሌ ኢሳ. 53ን ይመልከቱ) ምን ያህል ማዕከላዊ እንደሆነ ይመልከቱ። ክርስቶስ በእኛ ፈንታ ምትክ ሆኖ የመሞቱን እና የኃጢአታችንን ቅጣት ራሱ የመክፈሉን ማዕከላዊ ሚና በማንኛውም መንገድ ዝቅ የሚያደርግ ማንኛውም ስነ መለኮታዊ ትምህርት ሀሰተኛ የስነ-መለኮት ትምህርት የሚሆነው ለምንድር ነው?

2. በዛሬው ዓለም ከኢየሱስ በተቃራኒ ለምርጫ የሚቀርበው “ባርናባስ” ማን ነው ወይም ምንድር ነው?

3. የአርማቲያው ዮሴፍ ታሪክ በውጫዊ እይታ መፍረድ እንደሌለብን ምን ሊነግረን ይገባል?

4. ዳን 9:24–27ን እንደገና ይከልሱ። ለሚጠይቅ ለማንኛውም ሰው በዚህ ርዕስ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መስጠት መቻል ያለብዎ ለምንድር ነው? ትምህርት መስጠትስ ይችላሉ?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL